#ድንቅ_ስጦታ #በድምቀት_ተከናውኗል
በLove and Care አዘጋጅነት በየአመቱ የሚደረገው ድንቅ ስጦታ በትላንትናው ዕለት በምስራቅ መሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በድምቀት ተከናውኗል።
የወንጌላውያን ክርስትና መጽሐፍ ቅዱስን መሰረት ያደረገ ሁለንተናዊነቱ የተሟላ መዝሙር ባልዋዥቀ ጽናትና ባልተቋረጠ ዕድገት ያቀረቡት እጅግ ተወዳጁ የክብር ዶ/ር ዘማሪ ተስፋዬ ጋቢሶ አገልግለዋል።
ሌላው በየአመቱ ይሄንን ዝግጅት ከLove and Care ጋር በትጋት ያለመታከት እያዘጋጀ ያለው ዳዊት ጌታቸው ከኪንግደም ሳውድን ጋር በዝማሬ አገልግለዋል።
የሃገረኛ ዝማሬን ከአለም አቀፍ የዝማሬም ምቶች ጋር በማቀናጀት የተዋቡ ድንቅ ዛምሬዎችን የሚያቀርቡት "ሪትም ኳይሮችም" ተወዳጅ ዝማሬዎቻቸውን አስደምጠዋል።
Love and Care ወላጅ አልባ ህጻናትን እና አቅመ ደካሞችን ለማገልገል ልባቸው ያላቸው የበጎ ፈቃደኞች ቡድን ሲሆን በመዲናችን አዲስ አበባ ብቻ ከ20 በላይ የሚሆኑ ድጋፍ ማድረጊያ እና ወላጅ አልባ ህጻናት ማሳደጊያ ማዕከል አላቸው።
በአዲስ አበባ እና በአቅራቢያው ባሉ ከተሞች በተለያዩ ወላጅ አልባ ህጻናት ውስጥ የሚገኙ ወላጅ አልባ ህጻናትን እና አቅመ ደካሞችን የሚያገለግል ሲሆን በርካታ ቁጥር ያላቸው ክርስቲያን ወጣቶች በዚህ ቡድን ውስጥ በፍቃደኝነት ያገለግላሉ።
በትላንትናው እለትም የተደረገው #ድንቅ_ስጦታ የተሰኘው ልዩ የመዝሙር ኮንሰርት በማዕከሉ ውስጥ ለሚገኙ ድጋፍ ማሰብሰቢያ እንደሆነ በመድረኩ ተገልጿል።
The Christian News - የክርስቲያን ዜናበስፍራው ተገኝተን ተከታትለን ዝርዝሩን ነገርንችሁ።
📸 Love and Care

❤1
#ስለ_ፍቅር
ተወዳጁ አርቲስት ጋሽ ስዩም ተፈራ በአንድ ወቅት ጥበብ በቤተክርስቲያን ውስጥ (ልጅ) ነበረች። የሚንከባከባት እና የሚጠብቃት ስታጣ ወደ እንጀራ እናቷ (አለም) ሄደች ብለው ሲናገሩ ሰምቼ ነበር።
አሁን ጥበብ ወደ ቤተክርስቲያን እየተመለሰች ይመስላል። ለማንኛው በከሬጅ አርት ሚኒስትሪ የተዘጋጀ #ስለ_ፍቅር የተሰኘ ልዩ የወንጌል ኢነ ጥበብ ፌስቲቫል ተዘጋጅቷል።
በአዲስ አበባ እና በአቅራቢያዋ ለምትገኙ በሙሉ ታሕሳስ 22/2015ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ጀመሮ በወንጌል አምኞች ምርጦቹ 7000 ቤተክርስቲያን ተጋብዛችኋል።
በእለቱ በጥበብ ስራዎቻቸው የምንወዳቸው ድንቅ የኪነ ጥበብ ባለሞያዎች ታድመው የጥበብ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ። ከሌሎች ቦታዎች ለሚመጡ የጥበብ ፍቅር ላላቸው በሙሉ ልምዳቸውን ያካፍላሉ። ወንጌልን በጥበብ ሲያስተላልፉ ይቆያሉ።
ተወዳጇ አርቲስት ማክዳ ሃይሌ Mackda Haile Maki ላለፉት አመታት በከሬጀ አርት ሚኒስትሪ እጅግ ብዙ ስራዎች ስትሰራ ቆይታለች አሁን ደግሞ በጋራ የምንሰራበትን ድንቅ ዝግጅት አሰናድታልናለች በመታደም እየተዝናናን ቁም ነገር እንድንጨብጥ #እነሆ_ጥሪያችን_ለሁላችሁም ይድረስ።
አድራሻ #ምርጦቹ 7000 ቤተክርስቲያን (ከደንበል ወደ MKC Head Office) ሲጓዙ

#ምንድነው #የተፈጠረው?
#1971ዓ.ም
ወዳንተ መልሰን እንመለሳለን ኦ ጌታ
በእጅህ ቀስቅሰን በሃይልህ አድሰን ኦ ጌታ (2X)
በበደላችን ምክንያት አሳልፈህ አትስጠን
አህዛብ ቢስቁብን ቢዘባበቱን
ምንም ቢሆን ጌታ በስምህ ተጠርተናል
አሁንም እባክህ ስለ ስምህ ብለህ ይቅር በለን
ወዳንተ መልሰን እንመለሳለን ኦ ጌታ
በእጅህ ቀስቅሰን በሃይልህ አድሰን ኦ ጌታ (2X)
ጩኸታችንን ስማ የዘለዓለም አምላክ
የለመኑህን ሁሉ ... እያለ ይቀጥላል።
እጅግ ወደ ልብ የሚገባ የንሰሃ መዝሙር ነው። ግን ምናልባት ጉባኤው ውስጥ ከነበሩት መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ዝማሬውን የምናውቀው አልመሰለኝም።
እጅግ ተወዳጁ ክቡር ዶ/ር ዘማሪ ተስፋዬ ጋቢሶም ይህ ዝማሬ በ1971ዓ.ም የተጻፈ እንደሆነ ተናግረዋል።
ለመሆኑ በ1971ዓ.ም ምን እንደተፈጠረ የሚያውቅ ሰው አለ? ብለው ጠየቁ ማንም ምላሽ የሰጠ ሰው የለም። ለማንኛውም በወቅቱ ምን እንደተፈጠረ ለማወቅ የነበረን ጉጉት እጅግ እየጨመረ ሄደ።
ይህንን የምታነቡ ቤተሰቦቻችን አሁን ይሄንን ለብዙ ሰዎች #share #share በማድረግ በወቅቱ የተፈጠረው ምን እንደሆነ የሚነግረንን ሰው እንፈልግ።
ምናልባት በወቅቱ የተፈጠረው ጉዳይ አሁን እኛ ላለንበት ብዙ ትምህርት የምንማርበት እና አባቶቻችን ያለፉበትን ታሪክ (ጥሩም ይሁን ጥሩ ያልሆነ) ብንሰማው እንማርበት ይሆናል።
ዜናዎቹን ለወዳጅ ዘመዶ Share በማድረግ ያጋሩ።
ፔጃችንን like በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ.
ያሎትን አስተያየት በcomment ላይ ያስቀምጡልን።
በየቀኑ አዳዲስ እና አስገራሚ ዜናዎችን ከመላው አለም ይከታተሉ።
Share,like,Comment ...

#የክርስቲያን_ሚዲያዎች_ጉባኤ
የእስራኤል 6ኛው የክርስቲያን ሚዲያ ጉባኤ በኢየሩሳሌም ተካሄዷል።
በዚህ ትልቅ ጉባኤ ላይ ከ28 ሀገራት የተወጣጡ 150 የሚደርሱ
ከፍተኛ የክርስቲያን የዜና ስራ አስፈፃሚዎችን እና በአለም ዙሪያ ያሉ ታዋቂ የክርስቲያን ሚዲያዎች መስራቾች እና ዋና ስራ አስፈፃሚዎችና የሚዲያ ባለሞያዎች ተሳትፈዋል።
ለአራት ቀናት የሚቆየው የመሪዎች ጉባኤ ከክርስቲያን ማህበረሰብ ጋር የበለጠ ትብብር ለመፍጠር እና ከእስራኤል ጋር ያለውን ትብብር ለማጠናከር ያለመ እንደሆነ ተገልጿል።
በ2017 የተጀመረው ይህ ጉባኤ ከመጠናቀቁ አስቀድሞ ተሰብሳቢዎቹ የመጽሐፍ ቅዱስን ታሪክ ትክክለኛነት ለማረጋገጥ የንጉሥ ዳዊት ቤተ መንግሥት ትልቅ የድንጋይ መዋቅር የዳዊትን ከተማ ጎብኝተዋል።
የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኃን አገልግሎት ኃላፊ ሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ሙጬ ከኢትዮጵያ እንደተሳተፉ ታውቋል።
በነገራችን ላይ በሀገራችን ቁጥራቸው 40 የሚደርሱ የመንፈሳዊ (ወንጌላውያን ክርስቲያን) ሚዲያዎች ቢኖሩም አንድም በጉባኤው ላይ መገኘት የሚያስችል አቋማ ያለቸው ሚዲያ ስለመኖራቸው የሚታወቅ ነገር የለም።
ይህ የሚዲያ ጋጋታ እንጂ የተሻለ ሚዲያ እንደሌለን እና ይህንን ለመፍጠር ትልቅ የቤት ስራ እንዳለብን የሚያሳይ ነው።

እስራኤል ዳንሳ ነኝ በማለት ከተለያዩ ግለሰቦች ከ100 ሺሕ ብር በላይ የተቀበለዉ ግለሰብ በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተገለጸ
እስራኤል ዳንሳ ነኝ በሚል የሀይማኖት ሽፋን በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከምዕራብ ኦሞ ዞን፣ ከቤንች ሸኮ፣ ዞን ሚዛን አማን ከተማ አስተዳደር እና ቤንች ሸኮ ዞን ደቡብ ቤንች ወረዳ ነዋሪ ከሆኑት ግለሰቦች ከ100 ሺሕ ብር በላይ የተቀበለዉ ግለሰብ በቁጥጥር ሥር መዋሉን የቤንች ሸኮ ዞን ፖሊስ አስታወቀ፡፡
ግለሰቡ የግል ተበዳይን ማንነት በማጥናትና ስልክ በመደወል ራሱን የፀሎት ሰዉ በማስመሰል ልጅህ በቅርብ ቀን ወደ ካናዳ እንድትሄድ ፀሎት አድርጌያለሁ የተጀመረውን ህንፃ ግንባታ ለማጠናቀቅ የገንዘብ ድጋፍ አድርጉልኝ በማለት፤ በመጀመሪያ ዙር 30 ሺሕ ብር በባንክ ቁጥሩ ከግል ተበዳይ ገቢ ማስደረጉ ተገልጿል።
በተጨማሪም ከሌሎች አራት ሰዎች ማንነትና የስራ ቦታን ጥናት በማድረግ ስልክ በመደወል የሃይማኖት መሪ እስራኤል ዳንሳ ነኝ በማለትና የተለያዩትን የተሳሰቱ ምልዕክቶችን ለሰዎች በማስተላለፍ 109 ሺሕ 500 ብር የማታላል ወንጀል ሲፈፅም ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሠረት በህግ ቁጥጥር ሥር ውሎ ምርመራ እየተጣራበት እንደሚገኝ የቤንቺ ሸኮ ዞን ፖሊስ አዛዥ የታክቲክ ምርመራ ባለሞያ ሳጅን ደመላሽ አስፋዉ ተናግረዋል፡፡
በተለያዩ ጊዜያት የማታለል ወንጀል የተፈፀመባቸው ግለሰቦች መረጃውን በፍጥነት ወደ ቤንች ሸኮ ዞን ፖሊስ መምሪያ ቀርበው ክስ እንዲመሰርቱ ጥሪ ያቀረበው ፖሊስ፤ ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎችም ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡
#አዲስ_ማለዳ

#ሊለቀቅ_ነዉ።
የተወዳጁ ዘማሪ ግርማ አዴቦን "ጆሪን ጋጋቡክስዮ" ነጠላ ዝማሬ ነገ ይለቀቃል።
ተወዳጆቹ ዘማሪ ተስፋዬ ግርማ እና ዘማሪት የምስራች አብረሃም የተሳተፉበት ዝማሬ ወደ እናንተ ሊደርስ ነዉ።
ነገ አርብ ታህሳስ 21 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 9 ሰዓት በሆሳዕና ፕሮዳክሽን ዮቲዮብ ቻናል ይጠብቁ።
ሊንኩን በመንካት ቻናሉን Subscribe በማድረግ ተደምጠዉ የማይጠገቡ ዝማሬዎችን ይከታተሉ። https://youtu.be/_AqGaf1Doa8

#ሕብረቱ_አስቸኳይ_መግለጫ_እየሰጠ_ነዉ።
#በዮናታን_አክሊሉ ጉዳይ መግለጫ እየተሰጡ ነወ።
የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ሕብረት ከሰሞኑ በአንዳንድ በቤተዕምነት መሪዎች መካከል የነበረዉን ዉዝግብ አስመልክቶ ቦርዱ የደረሰበትን ዉሳኔ ለሚዲያዎች ጋዜጣዊ መግለጫ እየሰጡ ነዉ።
ጋዜጣዊ መግለጫዉን የሕብረቱ ፕሬዚዳንት መጋቢ ፃዲቁ አብዶ እና የሕብረቱ የቦርድ ሰብሳቢ መጋቢ ሰንበቶ በሼ በጋራ እየሰጡ ይገኛል።
መሪዎቹ በመግለጫቸው ከሰሞኑ የተፈጠረዉ ጉዳይ ወደ ከፍተኛ አመራሮች ድረስ ስለተጓዘ በጉዳዩ ዙሪያ የሕብረቱን አቋም እና የቦርዱን ወሳኔ ልናሳዉቅ ተገደናል ብለዋል።
በሕብረቱ ዉስጥ የሚገኙ አባል ቤተዕምነቶች ከአካሔድ ዉጪ የሚንቀሳቀሱ ከሆነ እንደ መሪዎች እንገስፃለን ነገር ግን ጠቅልሎ ሁሉንም ወንጌላውያን አላግባብ ቃላትን መናገር ተገቢ አይደለም ብለዋል።
በኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዉስጥ በጋራ ለመስራት ስንስማማ እንደዚህ አይነት ችግሮች ሲፈጠሩ በጋራ ለመነጋገር እንደሆነ የጠቆሙት መሪዎች በወቅቱ ሌሎቹ መሪዎች ተነጋግረው ቀሩ በሚል የተላለፈው መልዕክት የተሳሳተ እንደሆነ ተናግረዋል።
The Christian News - የክርስቲያን ዜና በስፍራው ተገኝተን መግለጫውን እየተከታተልን ሲሆን ዝርዝር ሙሉ መግለጫውን ይዘን የምንመለስ ይሆናል።

#ሊቀ_ጳጳሱ_አርፈዋል።
ፖፕ ቤኔዲክት 16ኛ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የቀድሞ ሊቀ ጳጳስ ፖፕ ኤሜራተስ ቤኔዲክት 16ኛ ባደረባቸው ሕመም በ95 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ቫቲካን ይፋ አድርጋለች።
የወቅቱ የሮማ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስ ከቀናት በፊት ባወጡት መግለጫ፣ ሊቀ ጳጳስ ፖፕ ቤኔዲክት 16ኛ ክፉኛ ሕመም ላይ መሆናቸውን ገልጸው ምእመኑ እንዲጸልያላቸው ጠይቀው ነበር።

#እንኳን ደስ አለሽ
ተወዳጇ ዘማሪት ሀና ተክሌ በድጋሜ በThe Christian News - የክርስቲያን ዜና ስም እንኳን ደስ አለሽ።
አዳዲስ እና ተዓማኒነት ያላቸዉ የክርስቲያን ዜና እንዲደርሳችሁ የቴሌግራም ገፃችንን ይቀላቀሉ።
https://t.me/TCNEW