በሃይማኖት መገናኛ ብዙኃን የሚፈጸሙ የሥነ ምግባር ጥሰቶች በአስቸኳይ እንዲቆሙ የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን አሳሰበ
ከተቋቋመበት መርህና አላማ በተቃረነ አኳኋን በተለያዩ የሃይማኖት መገናኛ ብዙኃን የሚፈጸሙ ህጋዊና ሙያዊ የሥነ ምግባር ጥሰቶች በአስቸኳይ እንዲቆሙ የመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን አሳሰበ።
ባለስልጣኑ ለዋልታ በላከው መግለጫ የሃይማኖት መገናኛ ብዙኃን ለኢትዮጵያውያን መልካም ዕሴቶች መጎልበት ወሳኝ ሚና እንዳላቸው መንግስት እንደሚያምን ገልጿል።
መንግስት የመገናኛ ብዙኃኑ ያላቸውን አወንታዊ ሚና በማመን ለተቋማቱ ህጋዊ እውቅና በመስጠት ድጋፍና እገዛ እያደረገ እንደሚገኝም ገልጿል፡፡
የሃይማኖት መገናኛ ብዙኃን ሃይማኖታዊ አስተምህሯቸውን ለተከታዮቻቸው ሲያስተምሩ የሌሎችን ሃይማኖትና እምነት አክብረው እንዲያስተምሩ፣ ከተቋቋሙበት ሃይማኖታዊ ጉዳይ ውጭ ሌሎች ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸው ጉዳዮች እንዳያስተላልፉ እና ከጥላቻ፣ በዜጎች መካከል አብሮ መሆንን ከሚያውክ በማንኛውም አግባብ ሁከትና ግጭት ሊቀሰቅስ ከሚችል በዜጎች ላይ ሥነ ልቦናዊም ሆነ አካላዊ ጥቃት እንዲደርስ ከሚያነሳሳ ንግግር እና ከመሰል አሉታዊ መልዕክቶች እንዲታቀቡ ይጠበቅባቸዋል ብሏል።
በተጨማሪ ሃይማኖት ተኮር ፕሮግራም ሲያሰራጩ በተለያዩ ሃይማኖት ተከታዮች መካከል የእርስ በእርስ ግጭት ማነሳሳት፣ የሌሎችን ሃይማኖት ማንኳሰስ እንዲሁም በሃይማኖቶች ተከታዮች መካከል አለመቻቻል እንዲፈጠር መቀስቀስም የተከለከለ መሆኑንም አብራርቷል፡፡
#ዳጉ_ጆርናል

#የእህታችን_የመክሊት_ስርዓተ_ቀብር_ዛሬ_ተፈፅሟል
#በትንሳኤ_ማለዳ_እንገናኛለን_እህታችን😥
ወጣቷን ሳስብ በሕይወቷ አጅግ እደነቃለሁ። የዝማሬዎቿ ግጥሞች ጥንካሬ እና መልዕታቸዉ
"ሰላሜ ኢየሱስ ሰላሜ
እረፍቴ ኢየሱስ እረፍቴ"
እንዳለችሁ ወደ እረፍቷ ሄዳለች።
እሷ በሄደችበት ቀን እንኳን ብዙዋች የወንጌሉን ቃል የሰሙበት ቀን ነው።
እህታችን ማኪ ያከበረቹ አምላክ በቀብሩዋ ቀን ከብሩዋል ስሙ ተሰብኩዋል ጌታ በስራው ፃድቅ ነው ።
The Christian News - የክርስቲያን ዜና በተወዳጇ ዘማሪት መክሊት ህልፈት የተሰማንን ሀዘን እየገለፅን ለቤተሰቦቿ መፅናናትን እንመኛለን።
እሷ ዛሬ ከምትወደው እና በልጅነቷ ካገለገለቸዉ አባቷ ጋር በመሆኗ ግን እጅግ ደስ ይለናል።

“ፈጣሪን ለማሳየት” 1 ሺህ 600 ዶላር ክፍያ የጠየቀው የደቡብ አፍሪካ ፓስተር
ኤምኤስ ቡደሊ የተባለው ፓስተር፥ ምዕመናን ክፍያ መፈጸም ከቻሉ የማይታመን የሚመስሉ ተአምራቶችን ማሳየት እችላለሁ ባይ ነው።
በዚህም “በገነት እግዚአብሄርን ለመመልከት” 20 ሺህ ራንድ ወይም 1 ሺህ 600 ዶላር መክፈል ግዴታ ነው። ብድራቸው እንዲሰረዝላቸው የሚፈልጉ ምዕመናን ደግሞ 5 ሺህ ራንድ (290 ዶላር) እንዲከፍሉ ዋጋ ወጥቶለታል።
በአምልኮው ቀን ማግስት ለማግባት የፈለገ ሰው 10 ሺ ራንድ መክፈል ይኖርበታል ይላል ቡደሊ የለጠፈው የቅሰቀሳ ፖስተር። በስማርት ስልኮቻቸው መጻኢያቸውን መመልከት ያሰኛቸው ወገኖችም 1 ሺህ 660 ዶላርን ይከፍሉ ዘንድ ተጠይቀዋል።

#ድንቅ_ስጦታ
ለእያንዳንዳችን የተሰጡን እጅግ ብዙ ስጦታዎች ይኖራሉ። በምንም የማናወዳድራቸዉ ስጦታዎችም አሉ።
ለእርሶ የተሰጦት #ድንቅ_ስጦታ ምንድነዉ? 🤔
ይህ ደግሞ በየአመቱ @Love and Care እየተዘጋጀ የሚቀርብ ልዩ ፕሮግራም ነዉ።
ከወጣት እስከ አንጋፋ ዘመሪዎች የሚያገለግሉበት ድንቅ የአምልኮ ፕሮግራም #በምስራቅ መሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን
#ሁላችሁም ተጋብዛችኋል።
ነገ ታሕሳስ 16/2015ዓ.ም
ከ10:00 ጀምሮ
📍 ከመገናኛ ወደ ቦሌ ሲጓዙ ኢምፔሪያል ማብራትን እንደተሻገሩ በስተግራ
📍 ከቦሌ ድልድይ ወደ መገናኛ ሲመጡ ኢምፔርያል ማብራት ጋር ሳይደርሱ በስተቀኝ

የስኮትላንድ ፓርላማ ዕድሜያቸው 16 ዓመት የሆናቸው ታዳጊዎች ጾታቸውን በህጋዊ መንገድ እንዲቀይሩ የሚፈቅድ ህግ አፀደቀ።
የስኮትላንድ ፓርላማ ዕድሜያቸው 16 ዓመት የሆኑ ዜጐች የሥርዓተ-ፆታ dysphoria የሕክምና ምርመራ ሳያስፈልግ በሕጋዊ መንገድ እንደ ትራንስጀንደር እንዲታወቁ የሚፈቅድ ሕግ ባሳለፍነዉ ሐሙስ አጽድቋል።
የሥርዓተ-ፆታ እውቅና ማሻሻያ (ስኮትላንድ) ህግ ተብሎ የሚታወቀው፣ ልኬቱ በ86 ለ69 ድምጽ ተላለፈ።
በኦፊሴላዊ መግለጫው መሰረት፣ ህጉ የስኮትላንድ ዜጎች "የፆታ እውቅና ሰርተፍኬት" እንዲኖራቸው ደረጃዎችን ለመቀየር ይፈልጋል፣ ህጋዊ ሰነድ "የአንድ ሰው ጾታ ሲወለድ የተመደበው ጾታ አይደለም፣ ነገር ግን የተገኘ" ነው ጾታ" ይላል።
ይህንን ህግ በማፅደቅ "በ2012 አርጀንቲና የመጀመሪያዋ ሀገር ከሆነች ጀምሮ፣ ሌሎች በርካታ ሀገራት ቤልጂየም፣ ኮሎምቢያ፣ ዴንማርክ፣ ፈረንሳይ፣ አየርላንድ፣ ማልታ እና ኖርዌይን ጨምሮ በርካቶች ይህንን ህግ አፅድቀዉታል።
ዉድ The Christian News - የክርስቲያን ዜና ቤተሰቦችን የስልጣኔ ቁንጮ ላይ ደርሰናል የሚሉት ምዕራባውያን በየጊዜው የሚወስኗቸዉ ዉሳኔዎች እጅግ አስደንጋጭ ከመሆናቸውም በላይ ለቀጣዩ ትዉልድ እጅግ አስጊ እና አሳሳቢ በመሆናቸው ምክንያት ሁሌም በፀሎት ዉስጥ እንድናስባቸዉ መልዕክታችን ነዉ።

#ቤተልሄም #የገና_በዓል
ቤተልሄም ከኮሮና ወረርሽን አገግማ በዘንድሮው በርካታ ቱሪስቶችን ይዛ የገና በዓልን በድምቀት እያከበረች ነው።
የኢየሱስ ክርስቶስ ልደትን በዓል ለማክበር በርካታ የዓለማችን ዜጎች ቤተልሔም የገቡ ሲሆን ቤተልሔም በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ክርስቲያኖች በዛሬው ዕለት የገናን በዓል ያበድምቀት እያከበሩ እንደሆነ ተገልጿል።
በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በርካታ ክርስቲያኖች ቅድስት ወደምትባለው ስፍራ የሚያደርጉት ጉዞም ተስተጓጉሎ የነበረ ቢሆንም ለሁለት ዓመታት ያህል ክብረ በዓላት ሳይከበር የቆዩት የቤተልሔም ጎዳናዎች በምዕመናን ተጨናንቀዋል።
የቤተ ክርስቲያን መሪዎች የተለያዩ የሙዚቃ መሳሪያዎችን በሚጨወቱ የስካውት ባንዶች ታጅበው ከእየሩሳሌም ተነስተው ወደ መንገር አደባባይ ተምመዋል።
የኢየሱስ ክርስቶስ ትውልድ ስፍራ ናት ተብሎ በሚታመንበት ቦታም ላይ በተገነባችው ቤተክርስቲያን በሚደረገው የእኩለ ሌሊት ቅዳሴም ላይ ይገኛሉ።
ከገሊላ እና ከጋዛ ሰርጥ የመጡ ፍልስጥኤማውያን ክርስቲያኖችን ጨምሮ ከዓለም ዙሪያ የመጡ ምዕመናን አሉ።

#ድንቅ_ስጦታ #በድምቀት_ተከናውኗል
በLove and Care አዘጋጅነት በየአመቱ የሚደረገው ድንቅ ስጦታ በትላንትናው ዕለት በምስራቅ መሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን በድምቀት ተከናውኗል።
የወንጌላውያን ክርስትና መጽሐፍ ቅዱስን መሰረት ያደረገ ሁለንተናዊነቱ የተሟላ መዝሙር ባልዋዥቀ ጽናትና ባልተቋረጠ ዕድገት ያቀረቡት እጅግ ተወዳጁ የክብር ዶ/ር ዘማሪ ተስፋዬ ጋቢሶ አገልግለዋል።
ሌላው በየአመቱ ይሄንን ዝግጅት ከLove and Care ጋር በትጋት ያለመታከት እያዘጋጀ ያለው ዳዊት ጌታቸው ከኪንግደም ሳውድን ጋር በዝማሬ አገልግለዋል።
የሃገረኛ ዝማሬን ከአለም አቀፍ የዝማሬም ምቶች ጋር በማቀናጀት የተዋቡ ድንቅ ዛምሬዎችን የሚያቀርቡት "ሪትም ኳይሮችም" ተወዳጅ ዝማሬዎቻቸውን አስደምጠዋል።
Love and Care ወላጅ አልባ ህጻናትን እና አቅመ ደካሞችን ለማገልገል ልባቸው ያላቸው የበጎ ፈቃደኞች ቡድን ሲሆን በመዲናችን አዲስ አበባ ብቻ ከ20 በላይ የሚሆኑ ድጋፍ ማድረጊያ እና ወላጅ አልባ ህጻናት ማሳደጊያ ማዕከል አላቸው።
በአዲስ አበባ እና በአቅራቢያው ባሉ ከተሞች በተለያዩ ወላጅ አልባ ህጻናት ውስጥ የሚገኙ ወላጅ አልባ ህጻናትን እና አቅመ ደካሞችን የሚያገለግል ሲሆን በርካታ ቁጥር ያላቸው ክርስቲያን ወጣቶች በዚህ ቡድን ውስጥ በፍቃደኝነት ያገለግላሉ።
በትላንትናው እለትም የተደረገው #ድንቅ_ስጦታ የተሰኘው ልዩ የመዝሙር ኮንሰርት በማዕከሉ ውስጥ ለሚገኙ ድጋፍ ማሰብሰቢያ እንደሆነ በመድረኩ ተገልጿል።
The Christian News - የክርስቲያን ዜናበስፍራው ተገኝተን ተከታትለን ዝርዝሩን ነገርንችሁ።
📸 Love and Care

❤1
#ስለ_ፍቅር
ተወዳጁ አርቲስት ጋሽ ስዩም ተፈራ በአንድ ወቅት ጥበብ በቤተክርስቲያን ውስጥ (ልጅ) ነበረች። የሚንከባከባት እና የሚጠብቃት ስታጣ ወደ እንጀራ እናቷ (አለም) ሄደች ብለው ሲናገሩ ሰምቼ ነበር።
አሁን ጥበብ ወደ ቤተክርስቲያን እየተመለሰች ይመስላል። ለማንኛው በከሬጅ አርት ሚኒስትሪ የተዘጋጀ #ስለ_ፍቅር የተሰኘ ልዩ የወንጌል ኢነ ጥበብ ፌስቲቫል ተዘጋጅቷል።
በአዲስ አበባ እና በአቅራቢያዋ ለምትገኙ በሙሉ ታሕሳስ 22/2015ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ጀመሮ በወንጌል አምኞች ምርጦቹ 7000 ቤተክርስቲያን ተጋብዛችኋል።
በእለቱ በጥበብ ስራዎቻቸው የምንወዳቸው ድንቅ የኪነ ጥበብ ባለሞያዎች ታድመው የጥበብ ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ። ከሌሎች ቦታዎች ለሚመጡ የጥበብ ፍቅር ላላቸው በሙሉ ልምዳቸውን ያካፍላሉ። ወንጌልን በጥበብ ሲያስተላልፉ ይቆያሉ።
ተወዳጇ አርቲስት ማክዳ ሃይሌ Mackda Haile Maki ላለፉት አመታት በከሬጀ አርት ሚኒስትሪ እጅግ ብዙ ስራዎች ስትሰራ ቆይታለች አሁን ደግሞ በጋራ የምንሰራበትን ድንቅ ዝግጅት አሰናድታልናለች በመታደም እየተዝናናን ቁም ነገር እንድንጨብጥ #እነሆ_ጥሪያችን_ለሁላችሁም ይድረስ።
አድራሻ #ምርጦቹ 7000 ቤተክርስቲያን (ከደንበል ወደ MKC Head Office) ሲጓዙ

#ምንድነው #የተፈጠረው?
#1971ዓ.ም
ወዳንተ መልሰን እንመለሳለን ኦ ጌታ
በእጅህ ቀስቅሰን በሃይልህ አድሰን ኦ ጌታ (2X)
በበደላችን ምክንያት አሳልፈህ አትስጠን
አህዛብ ቢስቁብን ቢዘባበቱን
ምንም ቢሆን ጌታ በስምህ ተጠርተናል
አሁንም እባክህ ስለ ስምህ ብለህ ይቅር በለን
ወዳንተ መልሰን እንመለሳለን ኦ ጌታ
በእጅህ ቀስቅሰን በሃይልህ አድሰን ኦ ጌታ (2X)
ጩኸታችንን ስማ የዘለዓለም አምላክ
የለመኑህን ሁሉ ... እያለ ይቀጥላል።
እጅግ ወደ ልብ የሚገባ የንሰሃ መዝሙር ነው። ግን ምናልባት ጉባኤው ውስጥ ከነበሩት መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ዝማሬውን የምናውቀው አልመሰለኝም።
እጅግ ተወዳጁ ክቡር ዶ/ር ዘማሪ ተስፋዬ ጋቢሶም ይህ ዝማሬ በ1971ዓ.ም የተጻፈ እንደሆነ ተናግረዋል።
ለመሆኑ በ1971ዓ.ም ምን እንደተፈጠረ የሚያውቅ ሰው አለ? ብለው ጠየቁ ማንም ምላሽ የሰጠ ሰው የለም። ለማንኛውም በወቅቱ ምን እንደተፈጠረ ለማወቅ የነበረን ጉጉት እጅግ እየጨመረ ሄደ።
ይህንን የምታነቡ ቤተሰቦቻችን አሁን ይሄንን ለብዙ ሰዎች #share #share በማድረግ በወቅቱ የተፈጠረው ምን እንደሆነ የሚነግረንን ሰው እንፈልግ።
ምናልባት በወቅቱ የተፈጠረው ጉዳይ አሁን እኛ ላለንበት ብዙ ትምህርት የምንማርበት እና አባቶቻችን ያለፉበትን ታሪክ (ጥሩም ይሁን ጥሩ ያልሆነ) ብንሰማው እንማርበት ይሆናል።
ዜናዎቹን ለወዳጅ ዘመዶ Share በማድረግ ያጋሩ።
ፔጃችንን like በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ.
ያሎትን አስተያየት በcomment ላይ ያስቀምጡልን።
በየቀኑ አዳዲስ እና አስገራሚ ዜናዎችን ከመላው አለም ይከታተሉ።
Share,like,Comment ...

#የክርስቲያን_ሚዲያዎች_ጉባኤ
የእስራኤል 6ኛው የክርስቲያን ሚዲያ ጉባኤ በኢየሩሳሌም ተካሄዷል።
በዚህ ትልቅ ጉባኤ ላይ ከ28 ሀገራት የተወጣጡ 150 የሚደርሱ
ከፍተኛ የክርስቲያን የዜና ስራ አስፈፃሚዎችን እና በአለም ዙሪያ ያሉ ታዋቂ የክርስቲያን ሚዲያዎች መስራቾች እና ዋና ስራ አስፈፃሚዎችና የሚዲያ ባለሞያዎች ተሳትፈዋል።
ለአራት ቀናት የሚቆየው የመሪዎች ጉባኤ ከክርስቲያን ማህበረሰብ ጋር የበለጠ ትብብር ለመፍጠር እና ከእስራኤል ጋር ያለውን ትብብር ለማጠናከር ያለመ እንደሆነ ተገልጿል።
በ2017 የተጀመረው ይህ ጉባኤ ከመጠናቀቁ አስቀድሞ ተሰብሳቢዎቹ የመጽሐፍ ቅዱስን ታሪክ ትክክለኛነት ለማረጋገጥ የንጉሥ ዳዊት ቤተ መንግሥት ትልቅ የድንጋይ መዋቅር የዳዊትን ከተማ ጎብኝተዋል።
የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኃን አገልግሎት ኃላፊ ሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ሙጬ ከኢትዮጵያ እንደተሳተፉ ታውቋል።
በነገራችን ላይ በሀገራችን ቁጥራቸው 40 የሚደርሱ የመንፈሳዊ (ወንጌላውያን ክርስቲያን) ሚዲያዎች ቢኖሩም አንድም በጉባኤው ላይ መገኘት የሚያስችል አቋማ ያለቸው ሚዲያ ስለመኖራቸው የሚታወቅ ነገር የለም።
ይህ የሚዲያ ጋጋታ እንጂ የተሻለ ሚዲያ እንደሌለን እና ይህንን ለመፍጠር ትልቅ የቤት ስራ እንዳለብን የሚያሳይ ነው።