እንኳን ለቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ። በዓሉ ለማክበር የእግር ጉዞ ስላለው እና ፀበል ጻድቅ ሰለሚኖር የዛሬ የክረምት ኮርስ አይኖርም። መልካም በዓል ይሁንላችሁ
❤17
ዝክረ ቅዱስ ጳውሎስ
3ተኛው የነገረ ድኅነት ሃንዳውት.pdf
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ልጆች የ"ዝክረ ቅዱስ ጳውሎስ" ማኅበር አባላትና የትምህርቱ ተካፋዮች በሙሉ፦ የእግዚአብሔር ሰላም ፍቅርና ጥበቃ በያላችሁበት ይብዛላችሁ፡፡ ማኅበራችን "ዝክረ ቅዱስ ጳውሎስ" በዚህ ዓመት የክረምት ወቅት ለወልድያ ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶችና ምዕመናን ባዘጋጀው ልዩ የመንፈሳዊ ትምህርት መርሐ ግብር መሠረት ትምህርታችን የሆነውን "የነገረ ድኅነት" ትምህርት በሰፊው እየተማርን እንገኛለን።
ይህ እጃችሁ ላይ የደረሰው የነገረ ድኅነት 3ተኛው (Handout) በክፍል ውስጥ የተማርነውን ይዘት በቤታችሁ ሆናችሁ በሰፊው እንድታነቡት እንድታጠናውና ለሕይወታችሁ ስንቅ እንድታደርጉት ይበልጥ በሚያመች መልክ ተደራጅቶ የተዘጋጀ የፒዲኤፍ (PDF) ሰነድ ነው።
በዚህ ክፍል ሦስት ሰነድ ውስጥ፦
የሰዎች ውድቀት፦ አዳምና ሔዋን በሕግ መተላለፋቸው ያስከተለውን መዘዝ
ጥንተ አብሶ እና ምልዕተ ኃጢአት፦ የቃሉን ምስጢራዊና መጽሐፋዊ ትርጉም፣
የባሕርይ መጎስቆልና ሞት፦ የሰው ልጅ ከኃጢአት በኋላ ያጣውን ክብርና የደረሰበትን የባሕርይ ውድቀት ኃጢአት በዘር ይተላለፋልን? የሚለውን ጥያቄ ከነቢያትና ከአበው ትምህርት አንጻር
አዳኝ ማግኘት አለመቻሉን፦ ነቢያት፣ መላእክት፣ የመሥዋዕተ ኦሪትና የኦሪት ሕግ ሰውን ሙሉ በሙሉ ማዳን ያልቻሉበትን ምክንያቶች ለአቀራረብ በሚመችና ግልጽ በሆነ ቋንቋ በዝርዝር በዚህ ሃንዳውት አስቀምጠናል።
ይህ መነሻ አዳም ከምን ዓይነት የጸጋ ከፍታ ላይ እንደወደቀና የእግዚአብሔር አምላክ የማዳን ሥራ ምን ያህል አስፈላጊና ድንቅ እንደሆነ ለአእምሯችን ፍጹም መረዳትን ይሰጠናል።
እናንተም ይህንን ሰነድ ከግሩፑ አውርዳችሁ (Download አድርጋችሁ) https://t.me/Stpoulos በስልካችሁ ላይ ዝም ብሎ እንዲቀመጥ ሳይሆን በጸሎት መንፈስ ሆናችሁ በደንብ እንድታነቡትና እንድታጠኑት በቅዱስ እግዚአብሔር ስም አደራ ማለት እወዳለሁ።
የቀደሙት አባቶቻችንና ቅዱሳን ሐዋርያት የተጋደሉለትን ደማቸውን ያፈሰሱለትንና የጻፉልንን እውነተኛውን የመዳን እውቀት (የነገረ ድኅነት ምስጢር) አውቀን በእምነት እንድንጸና እግዚአብሔር አምላክ ማስተዋሉን ይደልውልን!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን።
አቤል ተፈራ በላይ
ሐምሌ 30 2018 ዓ/ም

👏5❤3
በዚህ ሱባኤ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በምን እየተሳተፋችሁ ነው ?
Anonymous Poll
9%
ሀ) በቅዳሴ በሰዓታት
48%
ለ) በቅዳሴ ብቻ
13%
ሐ) በኪዳን ብቻ
39%
መ) አረ ምንም አልሳተፍም 😭
Negere Kirstos.docx
111.2 KB
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።
የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ልጆች የ"ዝክረ ቅዱስ ጳውሎስ" ማኅበር አባላትና የትምህርቱ ተካፋዮች በሙሉ፦ የእግዚአብሔር ሰላም ፍቅርና ጥበቃ በያላችሁበት ይብዛላችሁ፡፡ ማኅበራችን "ዝክረ ቅዱስ ጳውሎስ" በዚህ ዓመት የክረምት ወቅት ለወልድያ ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶችና ምዕመናን ባዘጋጀው ልዩ የመንፈሳዊ ትምህርት መርሐ ግብር መሠረት ትምህርታችን የሆነውን "የነገረ ክርስቶስ" ትምህርት በሰፊው እየተማርን እንገኛለን።
ይህ እጃችሁ ላይ የደረሰው የነገረ ክርስቶስ በክፍል ውስጥ የተማርነውን ይዘት በቤታችሁ ሆናችሁ በሰፊው እንድታነቡት እንድታጠናውና ለሕይወታችሁ ስንቅ እንድታደርጉት ይበልጥ በሚያመች መልክ ተደራጅቶ የተዘጋጀ ሰነድ ነው።

የተወደዳችሁ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቤተሰቦች
ነገ የተወዳጁ አባታችን የቅዱስ ጳውሎስ ወርሃዊ የዝክር መርሐ ግብር ስለሆነ ሁላችንም ሁለት ሁለት ጓደኞቻችንን በመጋበዝ በበረከቱ እንድንካፈል ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
ቦታ፦ አዳጎ ፀደይ ባንክ
ሰዓት፦ ከቀኑ 9:00 ሰዓት
የእግዚአብሔር ጸጋና ሰላም ከሁላችሁ ጋር ይብዛ። ዝክረ ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ማኅበር

❤15
❤27🙏8
እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የደብረ ታቦር (መለኮታዊ ክብሩን የገለጠበት) በዓል በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ። በዓሉን የበረከት ያድርግልን።
🙏18❤14
አንድ ሰው ቢበላም ቢጠጣም ቢቀመጥም በመንገድ ቢጓዝም ወይም ሌላ ማንኛውንም ነገር ቢያደርግ ዘወትር እንዲህ እያለ መጮህ (መጸለይ) አለበት "የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ማረኝ!" ..... ስለዚህ ልብህ የጌታ ፍቅር ማደሪያ እንዲሆን በፍቅሩ ሙቀትም ከኃጢአት ዝገት እንዲያነጻህ የጌታችን የኢየሱስን ስም ሳታቋርጥ ጥራ።
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ @Stpoulos
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ @Stpoulos
❤38
እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሰላም አደረሰዎት! አዲሱን ዓመት በበጎ ሥራ እና በበረከት እንጀምር።
ዝክረ ቅዱስ ጳውሎስ የገጠር አብያተ ክርስቲያናትን አገልግሎት ለመደገፍ እና መገልገያ ቁሳቁሶችን ለማሟላት የ 200 ብር ቻሌንጅ አዘጋጅቷል። እርስዎም አቅም በፈቀደ መጠን በዚህ ቻሌንጅ ላይ በመሳተፍ የገጠር አብያተ ክርስቲያናት አገልግሎት እንዳይቋረጥ የበኩልዎን አስተዋጽኦ ያድርጉ፤ የቅዱሳኑም በረከት ተካፋይ ይሁኑ!
የማኅበሩ የባንክ ሂሳብ ቁጥር፦
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፡ 1000764435617
ይህን መልእክት ለወዳጅ ዘመድዎ በማጋራት አብሮነትዎን ያሳዩን። መልካም አዲስ ዓመት!

❤11