ዝክረ ቅዱስ ጳውሎስ
642 subscribers
21 photos
1 video
40 files
27 links
Download Telegram
⚽️ አርሴናል ዋንጫ እንዲያገኝ ብጸልይ ኃጢአት ነውን?

ይህ ጥያቄ በተለይ በወጣቱ ኦርቶዶክሳዊ ማኅበረሰብ ዘንድ በተደጋጋሚ የሚነሳ ለአንዳንዶች ቀላል ወይም አስቂኝ ሊመስል የሚችል ነገር ግን በጥልቀት ስንመረምረው የእምነት ሕይወታችንን ሥር የሚነካ ትልቅ አጀንዳ ነው። በዚህ ጉዳይ ላይ በግልጽ መወያየታችንና ትክክለኛውን መንፈሳዊ ምላሽ መፈለጋችን የሚጠቅመን በዘመናዊው ዓለም መዝናኛዎችና ስሜቶች ተገፍተን ሳናውቀው ከመንፈሳዊው መስመር እንዳንወጣ በዕለት ተዕለት ምርጫዎቻችን ውስጥም የእግዚአብሔርን ስፍራ በትክክል እንድንረዳ ስለምንማርበት ነው።

ስለምንወደው ክለብ መጨነቅ ማሸነፉን መመኘትና ከልብ መውደድ በራሱ ኃጢአት ባይሆንም ትኩረት የመሳትና ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ነገሮች የማዘበራረቅ ምልክት መሆኑን ግን መካድ አይገባንም። ከዚህም ባለፈ እንደ አንድ ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያን ወደ ጸሎት ስንመጣ ነገሩን በሚገባ ልናስተውለው ይገባል።

በቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ መሠረት ጸሎት ማለት ከእግዚአብሔር ጋር የምናደርገው ሰማያዊና መንፈሳዊ ውይይት በመሆኑ የምንጸልየው ለነፍሳችን ድኅነት ለኃጢአታችን ሥርየት ለዓለም ሰላም ነው። መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በወንጌል "አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል" (ማቴ. 6፥33) እንዳለን፣ የሰማዩን አምላክ ለምድራዊ፣ ጊዜያዊና መዝናኛ ለሆነ ጨዋታ ውጤት ብለን በጸሎት በፊቱ ስንቆም የጸሎትን ከፍ ያለ ክብርና ሰማያዊ ዓላማ ማሳነስ ይሆንብናል።

በሌላ በኩል ደግሞ ጨዋታው በችሎታ በስልጠናና በዕድል ላይ የተመሰረተ ምድራዊ ውድድር ከመሆኑ የተነሳ የአርሴናል ደጋፊዎች ስንጸልይ የማንችስተር ሲቲ ወይም የሌላ ክለብ ደጋፊ የሆኑ ኦርቶዶክሳውያን ወንድሞቻችንም የነሱ ክለብ እንዲያሸንፍ መጸለያቸው አይቀሬ ነው። እግዚአብሔር የሁላችንም አባት በመሆኑ በአንዱ ደስታ የሌላውን ማዘን ስለማይመርጥ የእግዚአብሔርን ጣልቃ ገብነት ለእንዲህ ዓይነቱ ውድድር መመኘት ክብሩን መጋፋት ሰለሆነ ለክቡርነቱ አይስማማም።

ከሁሉ በላይ ግን ልንጠነቀቅበት የሚገባው ትልቁ መንፈሳዊ አደጋ የእግር ኳስ ፍቅራችን ከፈጣሪ ፍቅር በልጦ ወደ ጣዖት አምልኮ እንዳይቀየር ነው። ክለባችን ሲሸነፍ የምናዝነውንና የምናለቅሰውን ያህል ለኃጢአታችን የማናልቅስ ከሆነ ለጨዋታው የምንሰጠው ትኩረትና ጉልበት ከቅዳሴና ከጸሎት ጊዜያችን በላይ ከበለጠ እንዲሁም የእግር ኳስ ተጫዋቾችን ከቅዱሳን በላይ የምናከብር ከሆነ ጨዋታው በሕይወታችን ላይ ጣዖት እየሆነ መምጣቱን ያሳያል።

ስለዚህ ወንድሜ ሆይ! አርሴናልን መውደድህ ጨዋታ መመልከትህና እንዲያሸንፍ መመኘትህ በራሱ ኃጢአት ባይሆንም በጸሎትህ ጊዜ ለእግር ኳስ ዋንጫ ከመጨነቅ ይልቅ ለሀገርህ ሰላም ለቤተሰብህ ጤና ለነፍስህ ድኅነት እና ወደ መንግሥተ ሰማያት የሚያስገባህን ዘላለማዊ የጽድቅ ዋንጫ እንድታገኝ ብትጸልይ ይበልጥ ክርስቲያናዊና ኦርቶዶክሳዊ ይሆናል። እግዚአብሔር በምድራዊው መዝናኛችን ውስጥ መንፈሳዊ ማንነታችንን የምንጠብቅበትን ማስተዋል ይስጠን! አሜን

አቤል ተፈራ በላይ

https://t.me/Stpoulos
13🙏2
የእመቤታችን_መገለጥ_ከደብረ_ምጥማቅ_እስከ_ዘይቱን.pdf
2.3 MB
ውድ ኦርቶዶክሳዊያን እንኳን ለእመቤታችን የመገለጥ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

ቅድስት ድንግል ማርያም በደብረ ምጥማቅ ተገለጠች ሲባል ተረት ለሚመስለው ለዚህ ዓለም ሕዝብ ሕያው ማስረጃ ነው።

ፎቶ ማስቀረት በሚችልበት በዚህ ዘመን ከ60,000 ሺህ ህዝብ እየታየች የተገለጠችበት ሁኔታ የሚያሳይ ይህ PDF በአንድ ወንድማችን የተዘጋጀ ድንቅ ማስረጃ ነው ተጠቀሙበት።
👍5
📢 ታላቅ የበረከት ጥሪ ለወልድያ ኦርቶዶክሳውያን በሙሉ!

“የእግዚአብሔር ቃል እንዲሮጥና እንዲከበር...” (2ኛ ተሰ. 3፡1)

የማኅበራችን ዝክረ ቅዱስ ጳውሎስ የክረምት ኮርስ ምዝገባ መጀመሩን በማስመልከት ኮርሱን ለሁሉም ኦርቶዶክሳውያን ተደራሽ ለማድረግ እና የተለያዩ መንፈሳዊ ሐሳቦችን ትምህርቶችንና መረጃዎችን ለማጋራት አዲስ የቲክቶክ አካውንት ከፍተናል።

ይህ የወንድሞችና የእህቶች ስብስብ ይበልጥ እንዲሰፋና የክረምቱን ኮርስ ተማሪዎች ቁጥር ከፍ ለማድረግ የእናንተ የሁላችሁም ትብብርና ክርስቲያናዊ አደራ ይፈለጋል።

📌 ከእናንተ ምን ይጠበቃል?
1. አካውንቱን መከተል (Follow): ከታች ያለውን የቲክቶክ ሊንክ በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ።

2. ማጋራት (Share): ይህንን ማስታወቂያ ፎቶ/ስክሪንሾት በማድረግ (Screenshot) በየግል ማኅበራዊ ሚዲያዎ ላይ ለወልድያ ኦርቶዶክሳውያን እንዲደርስ ያድርጉ።

3. ግብዣ (Invite): ለጓደኞቻችሁ ለቤተሰቦቻችሁና ለወዳጆቻችሁ በማጋራት የክረምቱን ኮርስ እንዲማሩ ይጋብዙ።

🔗 የቲክቶክ አካውንታችን ሊንክ፦
👉 tiktok.com/@saintpoul21
👉 @saintpoul21

ኑ ይሄንን መንፈሳዊ ጥሪ ለሁሉም በማድረስ የበረከቱ ተሳታፊ እንሁን! የማኅበራችን ዝክረ ቅዱስ ጳውሎስ
1👍1
የምስገባ አማራጮች

ሀ) በአካል ለመመዝገብ ለሚፈልጉ
አዳጎ -> ማሚ ህንፃ ጌጤ ጫማ ቤት
ፒያሳ -> ፎቶ ግዕዝ
ጎንደር በር -> ቴድሮስ ኤሌክትሮኒክስ

ለ) በስልክ ለምትመሰገቡ ይሄንን ተጠቀሙ
0965106126 ሀብታሙ አገኘሁ
0929077309 ዳዊት ደርቤ
0921975099 ሙሉቀን አከለ
0992304006 ማህሌት አስራት

ሐ) በቴሌግራም ለምትመሰገቡ ይሄንን ተጠቀሙ
t.me/ha21a21
t.me/dev199207
t.me/Fidel19kal
t.me/Maki92

#ሳይሞላባችሁ #ተመዝገቡ
6
20260526_095243 (2).jpg
5.7 MB
የማኅበራችን ዝክረ ቅዱስ ጳውሎስ የክረምት ኮርስ ምዝገባ መጀመሩን በማስመልከት ኮርሱን ለሁሉም ኦርቶዶክሳውያን ተደራሽ ለማድረግ ይሄንን ፎቶ Story ሁላችሁም በቅስቀሳው እንድትሳለፉ በእግዚአብሔር ስም አደራ።
7
https://vt.tiktok.com/ZSCYp9H8X/

የማህበራችን መልእክትና አገልግሎት ለብዙሃን እንዲደርስ ይረዳን ዘንድ፤ ሁላችሁም የማህበሩን አካውንት ፎሎው (Follow)፣ ቪዲዮዎቹን ደግሞ ላይክ (Like) እና ሪፖስት (Repost) በማድረግ የበኩላችሁን ድርሻ እንድትወጡ በልዑል እግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።
👍7
ነገረ ድኅነት 1ኛ ሳምንት ትምህርት .pdf
1009 KB
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ልጆች የ"ዝክረ ቅዱስ ጳውሎስ" ማኅበር አባላትና የትምህርቱ ተካፋዮች በሙሉ፦ የእግዚአብሔር ሰላም ፍቅርና ጥበቃ በያላችሁበት ይብዛላችሁ፡፡ ማኅበራችን "ዝክረ ቅዱስ ጳውሎስ" በዚህ ዓመት የክረምት ወቅት ለወልድያ ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶችና ምዕመናን ባዘጋጀው ልዩ የመንፈሳዊ ትምሀርት መርሐ-ግብር መሠረት የመጀመሪያው ሳምንት ትምህርታችን የነበረውን ጥልቅና መሠረታዊ የሆነውን "የነገረ ድኅነት" ትምህርት በሰፊው ተምረናል።

ይህ እጃችሁ ላይ የደረሰው ጽሑፍ (Handout) በክፍል ውስጥ የተማርነውን ይዘት በቤታችሁ ኾናችሁ በሰፊው እንድታነቡት እንድታጠኑትና ለሕይወታችሁ ስንቅ እንድታደርጉት ይበልጥ በሚያመች መልክተደራጅቶ የተዘጋጀ የመጀመሪያው ሳምንት የፒዲኤፍ (PDF) ሰነድ ነው።

በዚሁ መሠረት፣ በሚቀጥሉት ሳምንታት የምንማራቸውን ተከታታይ ትምሀርቶች በሙሉ እያዘጋጀን በማኅበራችን ይፋዊ የቴሌግራም ግሩፕ እና ቻናል ላይ የምንለቅ መሆኑን እንገልጻለን። እናንተም ይሀንን ሰነድ ከግሩፑ አውርዳችሁ (Download አድርጋችሁ) በስልካችሁ ላይ ዝም ብሎ እንዲቀመጥ ሳይሆን በጸሎት መንፈስ ኾናችሁ በደንብ እንድታነቡትና እንድታጠኑት በቅዱስ እግዚአብሔር ስም አደራ ማለት እወዳለሁ።

የቀደሙት አባቶቻችንና ቅዱሳን ሐዋርያት የተጋደሉለትን ደማቸውን ያፈሰሱለትንና የጻፉልንን እውነተኛውን የመዳን እውቀት (የነገረ ድኅነት ምስጢር) አውቀን በእምነት እንድንጸና እግዚአብሔር አምላክ ማስተዋሉን ይደልውልን! ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን።

አቤል ተፈራ በላይ

ሰኔ 20 ቀን 2018 ዓ.ም

ወልድያ ኢትዮጵያ
🙏81
Channel name was changed to «ዝክረ ቅዱስ ጳውሎስ»
ምሽቱን በጥያቄ እና መልስ እንቆይ። ለመጠየቅ የምትፈልጉ ሰዎች ጥያቄ መምረጥ ትችላላችሁ።

1) የቤተ ክርስቲያን ታሪክ
2) የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት
3) ነገረ ድኅነት
4) ገዳማዊ ሕይወት
5) የቤተ ክርስቲያን ዓለም አቀፋዊ ጉባኤያት

ተከታታይ አምስት ጥያቄዎችን የመለሰ"ሥላሴ በተዋሕዶ" የተሰኘውን ዳጎስ ያለና እጅግ ጠቃሚ መንፈሳዊ መጽሐፍ ይሸለማል! የመጀመሪያው ጥያቄ አሁን ይጀምራል!

ለመሳተፍ ዝግጁ የሆናችሁና ርዕስ መምረጥ የምትፈልጉ በኮመንት (Comment) መስጫው ላይ የርዕሱን ቁጥር በማስቀመጥ ተሳትፎአችሁን አሳውቁ!
የደስታ ቀን ወደ ጥቁር ሐዘን የተቀየረበት አስደንጋጭ አደጋ

የህይወት አጋርነታቸውን በጋብቻ ያጸኑት መምህር አብርሃም ግዛው እና ባለቤታቸው መምህርት ራሄል አክሊ በሰኔ 23 ቀን 2018 ዓ.ም በደረሰ አሰቃቂ የትራፊክ አደጋ ህይወታቸው አልፏል።

ረጅም የድካም ዘመኗን በኮሌጅ ምረቃ አጠናቃ የደስታዋ ተካፋይ ከሆነው ባለቤቷ ጋር የየቀኑን ድል አክብረው ወደ ቤታቸው በመመለስ ላይ ሳሉ ነበር ይህ ያልታሰበ መቅሰፍት የገጠማቸው። ከቦንጋ ወደ ሺሾ በመጓዝ ላይ የነበረው የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ በካፋ ዞን ሺሾ እንዴ ወረዳ (ዋና ቦላ ቀበሌ) መንገድ ስቶ ወደ 50 ሜትር ገደል በመግባቱ ጥንዶቹ እዚያው ህይወታቸው ሊያልፍ ችሏል።

የወደፊት ህልማቸውንና የትዳር ህይወታቸውን ገና መገንባት በጀመሩበት የምረቃ ሳቅና ጨዋታ በሞላበት በዚያው ቅጽበት የሁለቱም ህይወት በአንድነት ተቀጥፏል።

ለሟች ቤተሰቦች ወዳጅ ዘመዶች እና ለስራ ባልደረቦቻቸው በሙሉ መጽናናትን እንመኛለን። ፈጣሪ ነፍሳቸውን በገነት ያኑር።

https://t.me/Stpoulos
😭12
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ልጆች የ"ዝክረ ቅዱስ ጳውሎስ" ማኅበር አባላትና የትምህርቱ ተካፋዮች በሙሉ፦ የእግዚአብሔር ሰላም ፍቅርና ጥበቃ በያላችሁበት ይብዛላችሁ፡፡ ማኅበራችን "ዝክረ ቅዱስ ጳውሎስ" በዚህ ዓመት የክረምት ወቅት ለወልድያ ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶችና ምዕመናን ባዘጋጀው ልዩ የመንፈሳዊ ትምህርት መርሐ ግብር መሠረት የሁለተኛው ሳምንት ትምህርታችን የነበረውን መሠረታዊ የሆነውን "የነገረ ድኅነት" ትምህርት በሰፊው ተምረናል። በክፍል 1 ትምህርታችን የላኩላችሁን PDF እንዳነበባችሁት ተስፋ አደርጋለሁ።

ይህ እጃችሁ ላይ የደረሰው የነገረ ድኅነት ክፍል 2 ጽሑፍ (Handout) በክፍል ውስጥ የተማርነውን ይዘት በቤታችሁ ኾናችሁ በሰፊው እንድታነቡት እንድታጠኑትና ለሕይወታችሁ ስንቅ እንድታደርጉት ይበልጥ በሚያመች መልክ ተደራጅቶ የተዘጋጀ የፒዲኤፍ (PDF) ሰነድ ነው።

በዚህ ክፍል ሁለት ሰነድ ውስጥ የሰውን ልጅ ውድቀትና የስደት ታሪክ ከመመልከታችን በፊት ፈጣሪ በጥንተ ተፈጥሮ ለሰው ልጅ የሰጠውን ወደር የለሽ ክብርና ልዕልና በ22ቱ ፍጥረታት አውድ ውስጥ እንመለከታለን። በመቀጠልም ምንም እንኳ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ቀጥተኛው ቃል ባይቀመጥም በባሕርዩ ሙሉ በሙሉ መለኮታዊ ውል የነበረውን የአዳምና የእግዚአብሔርን ግንኙነት የቃል ኪዳኑን አራት መሠረታዊ ዓምዶች (የቃል ኪዳን ሰጭ ተቀባይ ተስፋና ምልክት እንዲሁም የሚጸናበትን ሁኔታ) ለአቀራረብ በሚመችና ግልጽ በሆነ ቋንቋ በዝርዝር እንመረምራለን። ይህ መነሻ አዳም ከምን ዓይነት የጸጋ ከፍታ ላይ እንደወደቀ ለአእምሯችን ፍጹም መረዳትን ይሰጠናል።

በዚሁ መሠረት በሚቀጥሉት ሳምንታት የምንማራቸውን ተከታታይ ትምህርቶች በሙሉ እያዘጋጀን በማኅበራችን ይፋዊ የቴሌግራም ግሩፕ እና ቻናል ላይ የምንለቅ መሆኑን እንገልጻለን። እናንተም ይሀንን ሰነድ ከግሩፑ አውርዳችሁ (Download አድርጋችሁ) https://t.me/Stpoulos በስልካችሁ ላይ ዝም ብሎ እንዲቀመጥ ሳይሆን በጸሎት መንፈስ ኾናችሁ በደንብ እንድታነቡትና እንድታጠኑት በቅዱስ እግዚአብሔር ስም አደራ ማለት እወዳለሁ።

የቀደሙት አባቶቻችንና ቅዱሳን ሐዋርያት የተጋደሉለትን ደማቸውን ያፈሰሱለትንና የጻፉልንን እውነተኛውን የመዳን እውቀት (የነገረ ድኅነት ምስጢር) አውቀን በእምነት እንድንጸና እግዚአብሔር አምላክ ማስተዋሉን ይደልውልን! ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን።

አቤል ተፈራ በላይ
ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም
11
በእኛ ላይ ጥሏት እንጂ አበቶቻችን ክርስትናን ያስረከቡን በእንደዚህ ዓይነት ተጋድሎ ነበር🥺
በእግር ብረት ታስረው ወደ በጉድጓድ ተጥለው ጤዛ ልሰው ድንጋይ ተንተርሰው፣ግርማ ሌሊትን ድምጸ አራዊትን ታግሰው፣ቋርፍና ቅጠል በልተው፣ከአንዱ ወደ ሌላ ተሰደው ነበር።

ብቻ እግዚአብሔር ያበርታን🙏💖
🥰155
እንኳን ለቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ። በዓሉ ለማክበር የእግር ጉዞ ስላለው እና ፀበል ጻድቅ ሰለሚኖር የዛሬ የክረምት ኮርስ አይኖርም። መልካም በዓል ይሁንላችሁ
17
ዝክረ ቅዱስ ጳውሎስ
3ተኛው የነገረ ድኅነት ሃንዳውት.pdf
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ልጆች የ"ዝክረ ቅዱስ ጳውሎስ" ማኅበር አባላትና የትምህርቱ ተካፋዮች በሙሉ፦ የእግዚአብሔር ሰላም ፍቅርና ጥበቃ በያላችሁበት ይብዛላችሁ፡፡ ማኅበራችን "ዝክረ ቅዱስ ጳውሎስ" በዚህ ዓመት የክረምት ወቅት ለወልድያ ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶችና ምዕመናን ባዘጋጀው ልዩ የመንፈሳዊ ትምህርት መርሐ ግብር መሠረት ትምህርታችን የሆነውን "የነገረ ድኅነት" ትምህርት በሰፊው እየተማርን እንገኛለን።

ይህ እጃችሁ ላይ የደረሰው የነገረ ድኅነት 3ተኛው (Handout) በክፍል ውስጥ የተማርነውን ይዘት በቤታችሁ ሆናችሁ በሰፊው እንድታነቡት እንድታጠናውና ለሕይወታችሁ ስንቅ እንድታደርጉት ይበልጥ በሚያመች መልክ ተደራጅቶ የተዘጋጀ የፒዲኤፍ (PDF) ሰነድ ነው።

በዚህ ክፍል ሦስት ሰነድ ውስጥ፦

የሰዎች ውድቀት አዳምና ሔዋን በሕግ መተላለፋቸው ያስከተለውን መዘዝ

ጥንተ አብሶ እና ምልዕተ ኃጢአት፦ የቃሉን ምስጢራዊና መጽሐፋዊ ትርጉም፣

የባሕርይ መጎስቆልና ሞት፦ የሰው ልጅ ከኃጢአት በኋላ ያጣውን ክብርና የደረሰበትን የባሕርይ ውድቀት ኃጢአት በዘር ይተላለፋልን? የሚለውን ጥያቄ ከነቢያትና ከአበው ትምህርት አንጻር

አዳኝ ማግኘት አለመቻሉን፦ ነቢያት፣ መላእክት፣ የመሥዋዕተ ኦሪትና የኦሪት ሕግ ሰውን ሙሉ በሙሉ ማዳን ያልቻሉበትን ምክንያቶች ለአቀራረብ በሚመችና ግልጽ በሆነ ቋንቋ በዝርዝር በዚህ ሃንዳውት አስቀምጠናል።

ይህ መነሻ አዳም ከምን ዓይነት የጸጋ ከፍታ ላይ እንደወደቀና የእግዚአብሔር አምላክ የማዳን ሥራ ምን ያህል አስፈላጊና ድንቅ እንደሆነ ለአእምሯችን ፍጹም መረዳትን ይሰጠናል።

እናንተም ይህንን ሰነድ ከግሩፑ አውርዳችሁ (Download አድርጋችሁ) https://t.me/Stpoulos በስልካችሁ ላይ ዝም ብሎ እንዲቀመጥ ሳይሆን በጸሎት መንፈስ ሆናችሁ በደንብ እንድታነቡትና እንድታጠኑት በቅዱስ እግዚአብሔር ስም አደራ ማለት እወዳለሁ።

የቀደሙት አባቶቻችንና ቅዱሳን ሐዋርያት የተጋደሉለትን ደማቸውን ያፈሰሱለትንና የጻፉልንን እውነተኛውን የመዳን እውቀት (የነገረ ድኅነት ምስጢር) አውቀን በእምነት እንድንጸና እግዚአብሔር አምላክ ማስተዋሉን ይደልውልን!

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን።
አቤል ተፈራ በላይ
ሐምሌ 30 2018 ዓ/ም
👏53