ዝክረ ቅዱስ ጳውሎስ
642 subscribers
21 photos
1 video
40 files
27 links
Download Telegram
IMG_20260305_102752_311.jpg
413.4 KB
ሁላችሁም ስቶሪ አድርጉት
13❤‍🔥1
​በቆላስይስ መልእክት ጥናታችን ምዕራፍ 1 እና 2 በዚህ ሳምንት ለማጥናት ዛሬ ሁለተኛ ቀን ላይ ደርሰናል። በዚህ ክፍል የክርስቶስን የባሕርይ አምላክነት የቤተክርስቲያን ራስ መሆኑንና በእርሱ ስላገኘነው ቤዛነት የሚያመለክት ክፍል ነው። በቆላስይስ መልእክት የእግዚአብሔር ሐሳብ ለመረዳት ጠንክራችሁ እንድታጠኑ በክርስቶስ ፍቅር አደራ በማለት አሳስባችኋለሁ።
🙏6👏4
ቅዱስ ጳውሎስ 'በእርሱም የኃጢአታችን ስርየት የሆነው ቤዛነታችንን አገኘን' (ቆላ. 1:14) በማለት እንደገለጠልን በእርሱ ያገኘነውን ድንቅ ጸጋ እያስተዋላችሁ የእግዚአብሔርን ሐሳብ ይበልጥ ለመረዳት ጥናቱን ጠንክራችሁ እንድትቀጥሉ በክርስቶስ ፍቅር አደራ እላለሁ።

ጸጋና ሠላም ይብዛላችሁ
👏53
IMG_20260312_190244_647.jpg
564.7 KB
ሁላችሁም እስቶሪ አድርጉት
ሰላም ተወዳጆች እንደምን አደራችሁ?

   😥  የሐዘን መልእክት 😥

አባ ዐይናለም የወልድያ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለም ካቴድራል ደብር አስተዳዳሪ በተተኮሰ ጥይት ትናንት ማታ ከዚኽ ዓለም ዐርፈዋል።


ስለኾነም የቻላችሁ ከቅዳሴ በኋላ በመድኀኔዓለም ቤተክርስቲያን በመገኘት እንድንሸኛቸው አደራ ማለት እንፈልጋለን።

የአባ ዐይናለምን ነፍስ በደጋጎቹ ቅዱሳን ዕቅፍ ያስቀምጥልን!🙏
🙏11😭86
ኤፌሶን ከምዕራፍ 1-3 ማብራሪያ.pdf
258.9 KB
📢 የትምህርት ምዘና ማስታወቂያ

እግዚአብሔር ረድቶን የኤፌሶን እና የቆላስይስ መጻሕፍት ጥናታችንን በሰላም አጠናቅቀናል። አሁን ደግሞ ካጠናነው ትምህርት ምን ያህል ግንዛቤ እንዳገኘን የምንመዝንበት የፈተና ወቅት ላይ እንገኛለን።

ስለ መጀመሪያው ምዘና ዝርዝር መረጃ፦

የፈተናው ይዘት፦ የኤፌሶን መልእክት ማብራሪያ (ከምዕራፍ 1 እስከ 3)

የጥናት ምንጭ፦ በቴሌግራም ቻናላችን t.me/Stpoulos ላይ የሚገኘው የፒዲኤፍ (PDF) ሰነድ።

ጠቅላላ ነጥብ፦ 35%

የጥያቄዎች አይነትና ስርጭት፦

1) ምርጫ (10 ጥያቄዎች)፦ እያንዳንዳቸው 1 ነጥብ (10%)

2) እውነት ወይም ሐሰት (10 ጥያቄዎች)፦ እያንዳንዳቸው 1 ነጥብ (10%)

3) ባዶ ቦታ መሙላት (5 ጥያቄዎች)፦ እያንዳንዳቸው 2 ነጥብ (10%)

4) ማብራሪያ (2 ጥያቄዎች)፦ እያንዳንዳቸው 2.5 ነጥብ (5%)

ማሳሰቢያ፦ የፈተናውን ቀን በቅርቡ የምናሳውቅ በመሆኑ ሰነዱን በጥልቀት በማንበብ በቂ ዝግጅት እንድታደርጉ እናሳስባለን።

ጠንክራችሁ አንብቡ መልካም የጥናት ጊዜ!
11
ይችን ሳምንት እግዚአብሔር በሰላም በብርታት በጾም በጸሎት እና በስግደት አስፈጽሞ በሰላም ለብርሃነ ትንሣኤው ያድርሰን። አሜን
🙏185
"በሰሙነ ሕማማት ማማተብ አይቻልም" የሚለው ወሬ ፍጹም ስህተት ነው። አንዳንድ ሰዎች ባለማወቅ ቤተ ክርስቲያን ሲገቡም ሆነ ለግል ጸሎት ሲቆሙ ማማተብ ስህተት እንደሆነ ያስባሉ። ነገር ግን መስቀሉን ከግል ክርስቲያናዊ ሕይወታችሁ ልትለዩት አይገባም። መስቀልን በማማተብ የግል ጸሎት መጀመር በሰሙነ ሕማማት የሚሻር ነገር አይደለም። እናስተውል
🙏133
Audio
ሂዱ ንገሩ አውሩ ለዓለም
ተነስቷል በዚህ የለም
ተነስቷል በዚህ የለም
መድኃኔዓለም
ሞት የማይችለው የበረታ
ኃያል ነው የማይረታ
ማህተሙን የፈታ
የትንሳኤው ጌታ
13
እመቤታችን የተወለደችበት መታሰቢያ ትውፊቱን በጠበቀ መልኩ ከሞቀው ቤታችን ወጥተን ድንኳን በመጣል ወደ ውጭ እንወጣለን የሚያሳዝነው ነገር ግን ድንኳኖቻችን በዝማሬ መድመቅ ሲገባቸው እኛ ግን የልደቷን ባለቤት በማይመጥን መልኩ የዘፈን ዳንኪራ ቦታ እናደርጋቸዋለን። አካባቢያችሁን ቃኝታችሁ እስቲ ንገሩኝ ተወዳጆች ተሳስቻለሁ ?

በየመንደሩ በዚህ የተነሳ ድኅነት የሚገኝባት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስም እና ክብሯ ይጎድፋል። በዓላቶቻችን ሁሉ የጌታን ክብር የመግለጥ አባቶቻችን እስከ ሙሉ መንፈሳዊ ሞገሳቸው ቢሰጡንም እኛ ግን የኃጢአት እና የዓለማዊነት ፍላጎታችን መፈጸሚያ የርኩሰት ሜዳ እያደረግናቸው መሆኑ ሲታይ ያሳዝናል።
👍75🤔1
⚽️ አርሴናል ዋንጫ እንዲያገኝ ብጸልይ ኃጢአት ነውን?

ይህ ጥያቄ በተለይ በወጣቱ ኦርቶዶክሳዊ ማኅበረሰብ ዘንድ በተደጋጋሚ የሚነሳ ለአንዳንዶች ቀላል ወይም አስቂኝ ሊመስል የሚችል ነገር ግን በጥልቀት ስንመረምረው የእምነት ሕይወታችንን ሥር የሚነካ ትልቅ አጀንዳ ነው። በዚህ ጉዳይ ላይ በግልጽ መወያየታችንና ትክክለኛውን መንፈሳዊ ምላሽ መፈለጋችን የሚጠቅመን በዘመናዊው ዓለም መዝናኛዎችና ስሜቶች ተገፍተን ሳናውቀው ከመንፈሳዊው መስመር እንዳንወጣ በዕለት ተዕለት ምርጫዎቻችን ውስጥም የእግዚአብሔርን ስፍራ በትክክል እንድንረዳ ስለምንማርበት ነው።

ስለምንወደው ክለብ መጨነቅ ማሸነፉን መመኘትና ከልብ መውደድ በራሱ ኃጢአት ባይሆንም ትኩረት የመሳትና ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ነገሮች የማዘበራረቅ ምልክት መሆኑን ግን መካድ አይገባንም። ከዚህም ባለፈ እንደ አንድ ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያን ወደ ጸሎት ስንመጣ ነገሩን በሚገባ ልናስተውለው ይገባል።

በቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ መሠረት ጸሎት ማለት ከእግዚአብሔር ጋር የምናደርገው ሰማያዊና መንፈሳዊ ውይይት በመሆኑ የምንጸልየው ለነፍሳችን ድኅነት ለኃጢአታችን ሥርየት ለዓለም ሰላም ነው። መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በወንጌል "አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ ይህም ሁሉ ይጨመርላችኋል" (ማቴ. 6፥33) እንዳለን፣ የሰማዩን አምላክ ለምድራዊ፣ ጊዜያዊና መዝናኛ ለሆነ ጨዋታ ውጤት ብለን በጸሎት በፊቱ ስንቆም የጸሎትን ከፍ ያለ ክብርና ሰማያዊ ዓላማ ማሳነስ ይሆንብናል።

በሌላ በኩል ደግሞ ጨዋታው በችሎታ በስልጠናና በዕድል ላይ የተመሰረተ ምድራዊ ውድድር ከመሆኑ የተነሳ የአርሴናል ደጋፊዎች ስንጸልይ የማንችስተር ሲቲ ወይም የሌላ ክለብ ደጋፊ የሆኑ ኦርቶዶክሳውያን ወንድሞቻችንም የነሱ ክለብ እንዲያሸንፍ መጸለያቸው አይቀሬ ነው። እግዚአብሔር የሁላችንም አባት በመሆኑ በአንዱ ደስታ የሌላውን ማዘን ስለማይመርጥ የእግዚአብሔርን ጣልቃ ገብነት ለእንዲህ ዓይነቱ ውድድር መመኘት ክብሩን መጋፋት ሰለሆነ ለክቡርነቱ አይስማማም።

ከሁሉ በላይ ግን ልንጠነቀቅበት የሚገባው ትልቁ መንፈሳዊ አደጋ የእግር ኳስ ፍቅራችን ከፈጣሪ ፍቅር በልጦ ወደ ጣዖት አምልኮ እንዳይቀየር ነው። ክለባችን ሲሸነፍ የምናዝነውንና የምናለቅሰውን ያህል ለኃጢአታችን የማናልቅስ ከሆነ ለጨዋታው የምንሰጠው ትኩረትና ጉልበት ከቅዳሴና ከጸሎት ጊዜያችን በላይ ከበለጠ እንዲሁም የእግር ኳስ ተጫዋቾችን ከቅዱሳን በላይ የምናከብር ከሆነ ጨዋታው በሕይወታችን ላይ ጣዖት እየሆነ መምጣቱን ያሳያል።

ስለዚህ ወንድሜ ሆይ! አርሴናልን መውደድህ ጨዋታ መመልከትህና እንዲያሸንፍ መመኘትህ በራሱ ኃጢአት ባይሆንም በጸሎትህ ጊዜ ለእግር ኳስ ዋንጫ ከመጨነቅ ይልቅ ለሀገርህ ሰላም ለቤተሰብህ ጤና ለነፍስህ ድኅነት እና ወደ መንግሥተ ሰማያት የሚያስገባህን ዘላለማዊ የጽድቅ ዋንጫ እንድታገኝ ብትጸልይ ይበልጥ ክርስቲያናዊና ኦርቶዶክሳዊ ይሆናል። እግዚአብሔር በምድራዊው መዝናኛችን ውስጥ መንፈሳዊ ማንነታችንን የምንጠብቅበትን ማስተዋል ይስጠን! አሜን

አቤል ተፈራ በላይ

https://t.me/Stpoulos
13🙏2
የእመቤታችን_መገለጥ_ከደብረ_ምጥማቅ_እስከ_ዘይቱን.pdf
2.3 MB
ውድ ኦርቶዶክሳዊያን እንኳን ለእመቤታችን የመገለጥ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

ቅድስት ድንግል ማርያም በደብረ ምጥማቅ ተገለጠች ሲባል ተረት ለሚመስለው ለዚህ ዓለም ሕዝብ ሕያው ማስረጃ ነው።

ፎቶ ማስቀረት በሚችልበት በዚህ ዘመን ከ60,000 ሺህ ህዝብ እየታየች የተገለጠችበት ሁኔታ የሚያሳይ ይህ PDF በአንድ ወንድማችን የተዘጋጀ ድንቅ ማስረጃ ነው ተጠቀሙበት።
👍5