ዋጋህ(ሽ) ትልቅ ነው!!
እንደ ወትሮ ሁሉ በስልኬ ላይ የተሞላችው የማንቂያ ደውል ለማለዳ ዲቮሽን ክተት አውጃለች፤ በመተኛትና በመንቃት መካከል ሆኜ የላፕቶፔን የማብሪያ ቁልፍ በመጫን ለማላድ ጸሎት የሚሆንውን ጥእመ ዝማሬ ለመስማት ከዝማሬ ማጫወቻ መተግበሪ ፡ አጫውት የምትለዋን ቁልፍ በመጫን ትእዛዝ እስተላለፍኩ እናም መተግበሪያው ቀደም ሲል ከተሞላለት የአጫውት ዝርዝር ውስጥ ማጫወቱን ቀጥለ ፤ ከድምጽ ማጫወቻው መተግበሪያ የተደመጠው የምጀመሪያው ዝማሬ በጣም የተወደደችው እህታችን (በተለይ በኔ ሕይወት ልዩ ስፍራ አላት) ቃልኪዳን ጥላሁን(ሊሊ) ዝማሬ ነበር ከቁጥር 6 አልበሟ ላይ ስድስተኛው ትራክ ይኮል ጀመር፣ ይህች እጀግ እጭር ደቂቃ ይሆነች እጭር የግጥም ስንኝና በጥኡም ዜማ ተቀምራ በእህታችን ፍጹም ከመልኮት በሆነ የጸጋ ስጦታ በተሰጠ ድምጽ ይፈስ ጀመር፤ እናም ድሮም ስሰማት ንፍስም እይቀርልኝ አሁን ግን ባሰብኝ፤ ይህ ከሕይወት ቃል የስነቀችው ጥኡመ ዝማሬ ከነፍሴ አልፎ ምንፈሴን ገዛው፣ ዜማውን ለናተ የግጥሙን ስንኝ ግን እንካችሁ።
አይዞሽ ፡ በርቺ ፡ ግድ ፡ የለም(፪x)
ሁሉም ፡ ያልፋል ፡ እንደማያልፍ ፡ የለም
ጨለማው ፡ ሲያልፍ ፡ ሌሊቱ ፡ ሲነጋ
ሁሉም ፡ አለው ፡ ከእግዚአብሔር ፡ ዘንድ ፡ ዋጋ
አይዞህ ፡ በርታ ፡ ግድ ፡ የለም (፪x)
ሁሉም ፡ ያልፋል ፡ እንደማያልፍ ፡ የለም
ጨለማው ፡ ሲያልፍ ፡ ሌሊቱ ፡ ሲነጋ
ሁሉም ፡ አለው ፡ ከእግዚአብሔር ፡ ዘንድ ፡ ዋጋ
ሁሉም ፡ አለው ፡ ከእግዚአብሔር ፡ ዘንድ ፡ ዋጋ (፬x)
በዝማሬው ደግሞ ሁለንተናዬን የተቆጣጠረው፣ ዋጋዬን ከሌላ ስፍራ እንዳልፈልገው ጌታ በሷ አልፎ የመከረኝን ነው። በዚህ ዝማሬ ማሰላሰል ውስጥ ሆኜ መንፈስ ቅዱስ በቃሉ የሆነ አንድ እስተውሎት ወደ ልቤ አመጣ፡ አግዚአብሔር ለአብርሃም የገባለት ታላቅ ቃል ኪዳን፤ " ከዚህ ነገር በኋላም የእግዚአብሔር ቃል በራእይ ወደ አብራም መጣ፥ እንዲህ ሲል። አብራም ሆይ፥ አትፍራ፤ እኔ ለአንተ ጋሻህ ነኝ፤ ዋጋህም እጅግ ታላቅ ነው።" ዘፍ 15፥1 አብራሃምን የጠራው እርሱ ትልቁ እግዚአብሔር ነውና " ዋጋህም እጅግ ታላቅ ነው" ይለዋል፣ ምክንያቱም የጠራው፣ ወደ ራሱ የሳበውና ያስጠጋው ፣ ታመንብኝ ያለው አምላክ እርሱ እግዚአብሔር ትልቅ ነውና ዋጋው ትንሽ አደለም። ወዳጆቼ ዛሬ አንድ ታላቅ ሚስጥር ልንገራችሁ ትልቁ እግዝአብሔር በናንተ ሕይወት ትንሽ ፕሮግራም የለውም፤ የእናት ፍጻሜ እያለፋችሁበት ያለው ሁናቴ አይደለም፣ እየሆነባችሁ ያለው አዎንታዊም ይሁን አሉታዊ ገጽታ አይደለም። የእናንተ ፍጻሜ ያለው በጌታ እጅ ነው፡ በርታ ወንድሜ፣ ብርቺ እህቴ እሱ ጋር እይደለም ፍጻሜው፤ ኢያሱን ወደ ራሱ አጀንዳ የጠራው ጌታ የነገረው ተስፋ እንዲህ የሚል ነበር " ነገር ግን ጽና፥ እጅግ በርታ፤ ባሪያዬ ሙሴ ያዘዘህን ሕግ ሁሉ ጠብቅ፥ አድርገውም፤ በምትሄድበትም ሁሉ እንዲከናወንልህ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አትበል።" ኢያሱ 1፥7፤ በረታ ወንድሜ፣ ብርቺ እህቴ ፡ ያየላችሁን ትወርሳላችሁ እንጂ ያያችሁት አይወርሳችሁም " በምትሄድበት ሁሉ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነውና ጽና፥ አይዞህ፤ አትፍራ፥ አትደንግጥ ብዬ አላዘዝሁህምን? " ኢያሱ 1፥9 ፤ በርታ ወንድሜ፣ በርቺ እህቴ ፤ ጽና ወንድሜ፣ ጽኚ እህቴ ጌታ መከራውን ያስራሳችሁል፤ ያልፋል ነገሩ፣ ያልፋል ጨለማው፣ ያልፋል ሁኔታው፣ የክብር ተስፋ ያልው ክርስቶስ በእናተ ውስጥ ነውና ታልፉታላችሁ፤ " እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን።" (ሮሜ 8፥28) ። ዋጋችሁን የሚከፍላችሁ ትልቁ እግዚአብሔር ብዙፋኑ አለና።
This is Repost!!
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@StewardsChristArmy
@StewardsChristArmy
👆👆👆 #join_it_now 👆👆👆
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉👉👉 @NeosKtizo 👈👈👈✌
👉👉👉 @NeosKtizo 👈👈👈✌
Click this ☝☝☝to inbox me your Opinions. Shalom!!!!

ለቸርነቱ ወሰን የለውም
መጽሐፍ ቅዱስ በቸርነቱ ወደር የሌለው እግዚአብሔር መሆኑን ‹‹ቸርነትህና ምሕረትህ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ይከተሉኛል÷ በእግዚአብሔርም ቤት ለዘላለም እኖራለሁ››፣ ‹‹የእግዚአብሔር መንገድ ሁሉ ቸርነትና እውነት ነው። ቃል ኪዳኑንና ምስክሩን ለሚጠብቁ›› ‹‹በአንተ ለሚያምኑ በሰው ልጆች ፊት ያዘጋጀሃት ለሚፈሩህም የሰወርሃት÷ ቸርነትህ እንደ ምን በዛች!›› በማለት ያስነብባል (መዝሙር 23፥6፤ 25፥10፤ 31፥19)፡፡
ቸር የሚለው ቃል ትርጉም ‹‹የሚሰጥ፣ ለጋስ፣ አባ መስጠት፣ እጀ ሰፊ›› የሚል በመሆኑ ከሰዉ ልጆች መካከል በልዩ ልዩ ቸርነት ውስጥ ሊገለጡ የሚችሉ ሰዎች ሞለተዋል፡፡ ነገር ግን ደካማ የሰው ልጅ በመሆናችን ቸርነታችን ፍጹም አይደለም፡፡ በአንዱ ቸር ብንሆን በሌላው ንፉግ (ስስታም) ሆነን እንታያለን፡፡ ለቸርነቱ ወሰን የሌለው እግዚእሔር አምላክ ብቻ ነው፡፡ መንገዱም እውነትና ቸርነት ነው፤ የእግዚአብሔርን ቸርነት ብዛት መልኪያው፣ በኃጥያት ምክንያት ቆሽሸን ልንጠፋ የነበርነውን እኛን፣ አንድያ ልጁን በመስጠት ነውር አልባ ልጆቹ አድርጎ ወደ እራሱ የጠራበት ልክ ነው፤ ይህ የሚያመልክተው ፍጹም የሆነ ቸርነቱን ነው። ቸር ነውና ምህረቱም ለዘላለም ነውና አባታችንን እግዚአብሔርን አመስግኑት!!

የከበረ ኅብረት !!
"ወደ ልጁ ወደ ጌታችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ኅብረት የጠራችሁ እግዚአብሔር የታመነ ነው።ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ሁላችሁ አንድ ንግግር እንድትናገሩ በአንድ ልብና በአንድ አሳብም የተባበራችሁ እንድትሆኑ እንጂ መለያየት በመካከላችሁ እንዳይሆን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እለምናችኋለሁ።"(1ቆሮ 1፥9-10)
እግዚአብሔር የጠራን በመንፈስ ቅዱስ ከራሱ፤ ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ እና ከቅዱሳን ሁሉ ጋር ወደሚሆን የከበረ ህብረት መሆኑን በመረዳት፣ ለተጠራንለት ለዚህ ህብረት በሚመጥን ህይወት መመላለስ እንደሚገባን ልንረዳ ያስፈልጋል። አንድነት እና ህብረታችንን ሊከፋፍሉ ወይንም ሊለያዩ የሚነሱ ጊዚያው ችግሮችን በመናቅ በአንድነት ተያይዘን በጌታ ፊት ልንቆም ያስፈልገናል። ሲጀምርም አማኝ የተጠራው ከእግዚአብሔር፤ ከልጁም ከኢየሱስ ክርስቶስ፤ ከመንፈስ ቅዱስ እና ፤ ከቅዱሳን ወገኖች ጋር ኅብረት እንዲኖረው መሆኑን ሊረዳ ይገባል። ሰው በዘፈቀደ የጀመረው ሳይሆን እግዚአብሔር አስቦ የመሰረተው ኅብረት እንደሆነ ማወቅ አለብን፤ የዚህን ህብረት መንፈሳዊ ምስጢር የጠለቀ እና የከበረ መሆኑንን በትክክል ተረድተን ለአንድነታችን ትኩረት ልንሰጠው ግድ ይላል።በክርስቶስ ድነን ህብረት ልናደረግ ወደተጠራንበት አንድነት ስንመጣ፣ ከተለያየ ማህበረሰብ ፣ባህል ፣ዘር፣አስተሳሰብ፣ እምነት የመጣን እንደመሆኑ ምክንያት፡ አንዳችን ከሌላችን የምንለይባቸው ጥቃቅን የሆኑ ጉዳዮች ሊኖሩ እንደሚችሉ መካድ አይገባም። ይሁን እንጂ አሁን ባለንበት በዚህ ህብረት ጌታን በልብ አንድነት የምናመልክ እና እጅ ለእጅ በመያያዝ የምናገለግለው ልንሆን ይገባናል። ስለዚህ እግዚአብሔር የሰጠንን ኅብረት የመጠበቅ ኃላፊነት የጋራችን እንደሆነ የእግዚአብሔር ቃል ያስተምራል። በመሆኑም መለያየትም ሆነ መከፋፈል በመካከላችን እንዳይፈጠር ለዚህ ኅብረት እየተጠነቀቅን በማስተዋል መመላለስ እና መኖርም እንድንችል ሁላችንንም ጌታ ይርዳን።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@StewardsChristArmy
@StewardsChristArmy
👆👆👆 #join_it_now 👆👆

በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ!
በአዲሱ ዓመት የመጀመሪያ ወር ጅማሬ አካባቢ ላይ ሆነን ይህን እንድናስተውል በማሰብ ነው ይህችን መልክት ላስተላልፍ ያሰብኩት። ምልዕክቱንም እስቲ በጥያቄ ቢጤ ልጀምር። እኛ ነን ወደ አዲሱ ዓመት የደረስነው ወይስ ዘመኑም እንደ እኛው እየሄደ ነው?
ቆሞ የሚጠብቅ ዘመን የለም። ዘመኑም እኛም በዘመኑ ውስጥ እየሄድን ነው። እግዚአብሔር በዓመት፤ በዓመቱ የሚሰራው አዲስ ዘመን የለም። እግዚአብሔር ዘመናትን የሠራው አንድ ጊዜ ነው። በእግዚአብሔር አስቀድሞ የተሠራው ዘመን በራሳችን እድሜ ላይ ሲቆጠር «አዲስ ዘመን» ከማለታችን በስተቀር ዘመኑም ለማለቅ ራሱ ወደ እርጅና እየተጓዘ ነው። ሰውም ዘመናትም የማለቂያ እድሜ አላቸው። ዘመናት የተሠሩት፤ ለሰው ልጆች አገልግሎትና የእግዚአብሔርን ፈቃድ አውቀው መልካሙን ሁሉ ይሠሩባቸው ዘንድ ነው። እንኳን «ለአዲሱ ዘመን አደረሰን!» ስንል እኛ በዘመን ውስጥ መታደሳችንንና መለወጣችንን መናገራችን ነው። እንደዚያ ካልሆነማ ዘመናት የተሠጣቸውን ግዳጅ እየፈጸሙ ወደ ተሰጣቸው እርጅና እየሄዱ እንጂ መቼ ቆመው ይጠብቁናል? ክረምትና በጋ፣ ብርሃንና ጨለማ፣ መዝራትና ማጨድ፡ ዘመናት ከመስጠት አለማቆማቸውና በዘመን ስሌት መፈራረቃቸው እስከ ጊዜው የተሰጣቸውን ግዳጅ እየተወጡ መሆናቸውን ልብ ልንል ይገባል። እድሜአቸው አልቆ እስኪጠቀለሉም ይህንኑ ግዳጃቸውን ይወጣሉ።
«አቤቱ፥ አንተ ከጥንት ምድርን መሠረትህ፥ ሰማያትም የእጅህ ሥራ ናቸው። እነርሱ ይጠፋሉ፥ አንተ ግን ትኖራለህ ሁላቸው እንደ ልብስ ያረጃሉ፥ እንደ መጐናጸፊያም ትለውጣቸዋለህ፥ ይለወጡማል» መዝ 102፥25-26
ሐዋርያው ጴጥሮስም በመልዕክቱ አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር እንደምንጠባበቅ መናገሩ አሁን ያለን ሰማይና የምንኖርባት ምድር አርጅተው እንደሚለወጡ በግልጽ ያስረዳናል።
«ነገር ግን ጽድቅ የሚኖርባትን አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር እንደ ተስፋ ቃሉ እንጠብቃለን» 2ኛ ጴጥ 3፥13
ስለዚህ በዘመን ውስጥ በእድሜ ጣሪያ የምንጓዝ እኛ የሰው ልጆች ምን ማድረግ ይገባናል? በጎ መመኘት በጎ ነው። በጎ መመኘት ብቻውን በጎ ነገር አያመጣም። የተመኘነውን በጎ ነገር ለመሥራት በጎ ጥረት ያስፈልገናል። አዲስነት ከእኛነታችን ውጪ የሚገኝ አይደለም። ዘመን በተቆጠረ ቁጥር «እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሳችሁ» መባባሉ ጥሩ ቢሆንም ባልተለወጠ ማንነታችን ውስጥ ምን አዲስ ለውጥ አይመጣም። መታደስ፤ መለወጥ ለሰው ልጆች ማንነት ልዩ ግኝት ስለሆነ መለወጥ ያለብን እኛ ነን።
ቁጡና ቂመኛ ሆነን ስለአዲሱ ዘመን ማውራት ምን ይጠቅማል? በውሸትና በክፋት እየኖርን ከጉዞው ጨብጠን ልናስቀረው ስለማንችለው አዲስ ዘመን መልካምነት መመኘት በራሱ የሚጨምርልን አንዳች ነገር የለም። ይልቁንስ ሐዋርያው ጳውሎስ የተናገረውንና ሁልጊዜ እያነበብን ለመተግበር የተቸገርነውን በጎ ነገር እየፈጸምን ስለአዲስ ዘመን በጎ ምኞት እናስብ።
«በእርግጥ ሰምታችሁታልና፥ እውነትም በኢየሱስ እንዳለ በእርሱ ተምራችኋል፤ ፊተኛ ኑሮአችሁን እያሰባችሁ እንደሚያታልል ምኞት የሚጠፋውን አሮጌውን ሰው አስወግዱ፥ በአእምሮአችሁም መንፈስ ታደሱ፥ ለእውነትም በሚሆኑ ጽድቅና ቅድስና እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠረውን አዲሱን ሰው ልበሱ። ስለዚህ ውሸትን አስወግዳችሁ፥ እርስ በርሳችን ብልቶች ሆነናልና እያንዳንዳችሁ ከባልንጀሮቻችሁ ጋር እውነትን ተነጋገሩ። ተቆጡ ኃጢአትንም አታድርጉ፤ በቁጣችሁ ላይ ፀሐይ አይግባ፥ ለዲያብሎስም ፈንታ አትስጡት። የሰረቀ ከእንግዲህ ወዲህ አይስረቅ፥ ነገር ግን በዚያ ፈንታ ለጎደለው የሚያካፍለው እንዲኖርለት በገዛ እጆቹ መልካምን እየሠራ ይድከም። ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ። ለቤዛም ቀን የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔርን መንፈስ አታሳዝኑ። መራርነትና ንዴት ቁጣም ጩኸትም መሳደብም ሁሉ ከክፋት ሁሉ ጋር ከእናንተ ዘንድ ይወገድ። እርስ በርሳችሁም ቸሮችና ርኅሩኆች ሁኑ፥ እግዚአብሔርም ደግሞ በክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ ይቅር ተባባሉ» ኤፌ 4፥21-32
አለበለዚያ ዘመን ካልሰራንበት «እንኳን አደረሳችሁ ሲባባሉብኝ ጊዜያቸውን በከንቱ ፈጸሙ ብሎ በኋለኛው ቀን እንዳልሰራንበት ይመሰክራል።
«ሰማያት የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ፥ የሰማይም ጠፈር የእጁን ሥራ ያወራል» ስለዚህ ንስሐ እንግባ፤ በልባችንም መታደስ እንለወጥ! ለዚህም እግዚአብሔር ይርዳን! አሜን!
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@StewardsChristArmy
@StewardsChristArmy
👆👆👆 #join_it_now 👆👆👆
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉👉👉 @NeosKtizo 👈👈👈✌
👉👉👉 @NeosKtizo 👈👈👈✌
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻

#የሕይወት_መጨረሻ!!
ሳይንቲስቱ ላፕላስ በሕይወቱ መጨረሻ ሞቱን በመጠባበቅ በነበረበት ሰዓት በአልጋው ዙሪያ የከበቡት ጓደኞቹ በአንድ ድምፅ ሆነው፡- ‹‹ላፕላስ አይዞህ ትላልቅ የሆኑ ግኝቶችህ እና ሥራዎችህ በዓለም ዙሪያ ሁሉ እንድትታወስ ያደረጉሃልና ተጽናና…፡፡›› ባሉት ጊዜ ላፕላስ፡- ‹‹እነዚህ የምትሉኝ ነገሮች ሁሉ ምንም ዋጋ የላቸውም፣ ከንቱ የከንቱ ናቸው፡፡ በእነዚህ እናንተ በምትሉት ሳይንሳዊ ግኝቶቼ እና መጻሕፍቶቼ መታሰቤ ለእኔ ምኔ ነው!? በማለት ጠየቃቸው፡፡ ጓደኞቹም በመደንቅ ሆነው፡- ‹‹ላፕላስ ታዲያ የአተነትህ ሕያው ማስታወሻ፣ ሀውልት እና ቅርስ ምን እንዲሆን ትፈልጋለህ?›› በማለት በጉጉት ሆነው ጠየቁት፡፡
ሽማግሌው ሳይንቲሲስት ላፕላስም በተቆራረጠ ድምፅ በለሆሳስ ሆኖ ‹‹መታወሻዬ የሕያውነቴ ምስጢርም ፍ-ቅ-ር ብቻ እንዲሆን ነው የምፈልገው!›› ነበር በማለት የተሰናበታቸው፡፡ ፍ-ቅ-ር የሕያውነት ምስጢር፣ ለዘላለም ከመቃብር በላይ መታሰቢያችን፣ ሞትን ማሸነፊያው እውነተኛ መንገዱ አዎን ፍ-ቅ-ር እና ፍ-ቅ-ር ብቻ ነው፡፡ ኃያሉ ጌታ ኢየሱስን ከመንበሩ ስቦ ሰው እንዲሆን ያደረገው እና ከኃጢአት በቀር እንደ እኛ ተፈትኖ፣ በምድር ላይ ተመላልሶ ሞታችንን በሞቱ ቀይሮ ሕይወትን የሰጠን ከወደድን ከታላቅ ፍቅሩ የተነሳ ነው፡፡ እናም በፍቅር የሞት መውጊያ ለዘላለም ተሰብሯል፣ ሲኦልም ድል ተነስቷል! በፍቅር እና በበጎ ሥራችን ዘላለማዊ የሆነ የሕያውነት ሀውልት ለትውልድ እና ለሀገር ማቆም ይቻለን ዘንድ መልካሙን አጨራረስ በጸሎት እየተመኘሁላችሁ ጌታ በነገር ሁሉ በፍቅር የምንገለጥበትን የጸጋ ጉልበት እንዲያበዛልን እየተማጸንኩ ልሰናበት፡፡
#ከንባብ_ማስታወሻ!!
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
👉👉👉 @NeosKtizo 👈👈👈✌
👉👉👉 @NeosKtizo 👈👈

የክርስቶ ሰላም!!
"ሰላምን እተውላችኋለሁ፥ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ፤ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም። ልባችሁ አይታወክ አይፍራም።”(ዮሐንስ 14፥27)
ከላይ ያለው የጌታ ቃል ዓለም የሚሰጠው አንድ ሰላም እንዳለ ነገር ግን ኢየሱስ የሚሰጠን ሰላም አለም ከሚሰጠው የተለየ እንደሆነ ያሳየናል። ለምሳሌ ዓለም በደረሰበት የሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርምር ሰዎች የሚፈልጓቸውን ነገሮች በማቅረብ ተረጋግተው እንዲኖሩ ለማድረግ ብዙ ጥረት ቢያድረግም ሰላምን ፍጹም ማድረግ አልተቻለም።
ዛሬ በዓለም ላይ ብዙዎች ሰላምን ከቤታቸው፣ከኑሮአቸው፣ከገንዘባቸው፣ከእውቀታቸው፣ከመንግስት ወዘተ ከጌታ ውጭ ከብዙ ስፍራ ይፈልጋሉ። ነገር ግን ሰው የሚያስፈልገውን ፍጹም ሰላም የሚሰጥ እርሱ(ክርስቶስ) ብቻ ነው። ይህ ሰላም በተቃወሱ ነገሮች ላይ የሚያረጋጋ ሀይል ነው፤ ይህ ማለት በማዕበል፣ በተግዳሮት እና በሕይወት ተቃውሞዎች መካከል ሳንናወጥ ደስታ እና ሀሴት እንድንሞላ የሚያደርገን ነው።
ሰው ራሱን መርዳት አይችልም፤ በምድር ላይ ትርጉም ያለው ሕይወት ለመኖር ጌታ ያስፈልገናል። የሚያስፈልገን ክርስቶስ ብቻ መሆኑን ስንረዳ ሕይወት የሚያስደንቅ እና ለመኖር የተጋባ ይሆናል። እርሱ የሰላም አለቃ/ ልዑል ነው (ኢሳይያስ 9፥6)።እርሱ የሚሰጣችሁ ሰላም ከሰው መረዳት ያልፋል (ፊልጵስዩስ 4፥7)፤ከተለመደው በላይ ከሆነ ከልቀት፣ ከጽናት፣ ከእረፍት እና ጸጋ ጋር ወደ ሕይወታችን የመጣል። በዕብራይስጥ “ሻሎም” በሚል ቃል ነው የመጣው ይህም የደህንነትን ሙሉነት ነው የሚያሳየን። ስለዚህ ጌታን “ጀሆቫህ ሻሎም” ብለን ስንጠራው ጌታ የሰላማችን፣ የእረፍታችን እና የመኖሪያችን አካል እንደሆነ እየተናገርን ነው። " እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት።"(1 የጴጥ5፥7)፤በዚህ በሚያልፍ አለም ውስጥ የማያልፍበትን ስላሙን የተወልን ጌታ ስሙ ብሩክ ይሁን " ጃሆቫህ ሻሎም " ብያለው ቅዱሳን።