Sostkilo Podcast 📻 | 2021 Wrapped: 3K plays - 100+ subscribers -11 episodes - 14 countries. Merci 🙌 #2021PodcasterWrapped #SpotifyWrapped
ቡዲዝምን በዲንዴን'ግ ተቀበልኩ
ማስታወሻ | July 24 -19
[ ልዑል ፡ ዘወልደ ]
ወደ ነፃይቱ ምድር በመሄጃዬ ቀን የትም ሳሽኳልል ቆየሁና እንደማንኛውም አበሻ በሰዓቴ መዳረሻ መጣደፍ ጀመርኩ ። ቦሌ ስደርስ ፥ መንገደኛው ቼኪ'ን የሚያደርግበት ሰልፍ የኢሮብ ነዋሪዎች አብይን ለመቃወም ከወጡት ቀጫጫ ሰልፍ ይረዝማል ።
እንዳማራጭ ፥ በማሽን ቼኪ'ን ማድረግ ይቻል ስለነበር ይለፈኝ ብዬ ወደ ማሽኑ ሄድኹ ። እንደደረስኩ አንድ ሰውዬ የአያቱን ስም አላልፍልህ ብሎት ሳንቲም እንደዋጠበት ስልክ ሲደበድበው ደረስኩ ። ትካይ ማሽኑን ልገላግል ከመሀል ስገባ ደብዳቢው የኔው ጉድ ነው ።
የለየሁት ከአገጩ ከፍ ብላ በበቀለች ደማቅ ሸንጎበት ነው ። አይ ጌታዬ ፥ ምን ባደርግህ ነው ከቡድሃ ጉተማ በፊት ግራማ ጉተማን ያሳየኸኝ ፥ ሃሃ
ከግርምሽ- አባ ጨብሳ ጋር ትንሽ አወራን ፥ ያው ዶክተሩን ቦጨቅን ብል ይቀላል (መሰለኝ) ። በወቅቱ ወደ ጅጅጋ ይበር ነበር ፤ የበረረበትን ምክኛት በቅጡ ሳልጠይቀው በችኮላ ተለያየን ።
ነገር ሁሉ ሆነና ከምድረ-ታይ በግዜ ገባኹ ። እንደደረስኩ ቀድሞ የገባልኝ የአገሪቷ ጠረንና እንዲህ የማይሉት ወበቅ ነው ። ሽታውን መግለፅ አስቸጋሪ ቢሆንም ለ'ሎንችን መጋረጃ ቅርናት ይቀርባል ።
እንደባላገር መንገደኛ ሰው አጠያይቄ ወደ መሀል አገር ባቡር ተሳፈርኩ ። ባቡሩ ዘመናዊ ባቡር ለመባል እራሱ ብዙ ይዘምናል ። ጋሽ አበራ ሞላ የለገሃር ፉርጎ ላይ ተንጠልጥሎ ሸከተፍ - ሸከተፍ እያለ ስለመዝፈኑ እያሰብኩ ሀሳቤን ሳልጨርስ ደረስኩ ፥ ግነት - ወ - ፍጥነት ሃሃ
ቡክ ያደረግሁት ሆቴል ያለው በስድስተኛው ስቴሽን ላይ እንደመሆኑ ደውል ቆጥሬ አወራረዴ በአምስተኛው ሆነ ። ከሆቴሉ በጠዋት ስለገባሁ ተመልሶ ለመውጣት ገላዬን መታጠብ ጀመርኩ ። ነገሩ የሚጀምረው ከዚህ እጥበት ነው ...
ከፊት ያገኘሁትን ተመትቼ እየታጠብኩ ድንገት ፀጉሬ ውልቅ ውልቅ እያለ ይነቃቀል ገባ ። ተደናግጬ ዉሃውን በመዝጋት ወደ ጎመ'ው መስታወት ሄድኩና አየሁ ። አናቴ ፍንጭት ፈላ የጋጠው አካት መስሏል ።
መስታወቱ ላይ ብዙ ከተከዝኩ በኋላ ሙሉ ዞማዬን በደንበኛው አዳርሼ ላጨሁት ፥ መለጥኩ ። እንዳበቃሁ የሎርድ ኦፍ ዘሪንጉ ጎለም በመተጣቢያ ቤቱ መስታወት አየሁት ፥ እርሱ ይየኝ አይየኝ እርግጠኛ አይደለሁም ።
ወበቅ ቤቴ አልጋ ላይ ያገኘሁትን ቀይ ሽርጥ እንዳሸርጥ አስገድዶኝ ፥ ለብሼ ወደ ሎቢ ቦታው ወረድኩ ። በመውረድ ላይ ሳለሁ ነበር የታጠብኩበትን ፈሳሽ ምንነት አገላብጬ ያየሁት ። ፀጉሬን ስፈትግበት የነበረው ሻምፑ ጭገር ማርገፊያ ክሬም ነበር ..ሃሃ
ከመኝታ ቤቱ ሰገነት ስወርድ ያዩኝ ቢልቦዮች ማስቲካቸውን እየተፉ " ዋይ ዋይ " አሉኝ ። የጉድ አገር ቶሎ አይመሽም ፥ ለመርዶም በረፈደ ሰዓት እንደ ሙሾ አውራጅ ዋይ-ዋይ በማለታቸው ግራ ተጋበሁ ። በዋይታው በርግጌ እንደተገተርኩ አንገታቸውን ሰብረው ደግሞ ሰላም አሉኝ ።
ቆይቶ ሲገባኝ "ዋይ" ታዮች ለታላቅ ሠውና ለመነኩሴ የሚሰጡት የስግደት ሰላምታ መሆኑ ነው ። ከተራ ሰው በአንዴው የቡድሃ ልዑል ከሆኑ በኋላ መፎገር የለም ፥ መደናበሬን ተውኩ ። ከትከሻዬ አንስቶ ያሰመርኩትን ቀይ ሽርጥ እያሰማመርኩ መልሼ እጅ ነሳሁ ። እንደው ግን ፥ ጥቁር ቡዲስት ኖሮ ያውቅ ይሆን ?
ውስጤ በጥያቄ ቢናጥም ፥ የትም ያላገኘሁት ጌትነት ግትነት ግን ተሰምቶኛል ፤ ያልነበረ አይነት ጌትነት ። ደራሲ ስብሓት (ነብስኄር) ለትምህርት ወደ አሜሪካ በሄደ ግዜ የሚቀበለው ሰውዬ በአባቱ ስም " ሚስተር እግዛቤር " ሲለው ፥
- እንዴ ? ለካ እግዚያብሔር ነኝ ! እንዳለው አይነት ጌትነት ሃሃ
------------------------------------
ክፍል - 01 - Land of free.

ማስታወሻ ፥ ወይ ጡቷ | July 26 - 19.
[ ልዑል ዘወልደ ]
በሁለተኛው ቀኔ ገበያ ላረግ ወጣሁ ። በገበያው ከነበሩ አሻንጉሊቶች ቀድሞ ከአይኔ የገባው ጡት የያዘ እጅ ነበር ። ጡት እንዲህ ሸንጉልቶ አደባባይ መውጣቱ ገርሞኝ ቆምኹ።
ነገርዬው ወሲብ መቀስቀሻ ይሁን ጣዖት ግራ ገብቶኝ ብዙ ሳየው ቆየሁና በስተመጨረሻ አባባኝ። መባባቴ ሸንጎሊቱ ትንሽ ቢጠቁር የአኖሌ'ን ሀውልት ቁርጥ በመምሰሉ ነው - Harkaafi Harma Muraa Aanolee ። ሰው ስሜቱን በሚቀሰቅስበት መጫወቻ መባባቴ አናዶኝ ገበያውን ጥዬ ወጣሁ ሃሃ።
በባዶ ሆዴ ባዮኬ ስር ስንሸራሸር መንገድ ዳር ቺክን ሲጠበስ ከሩቅ አየሁ ። ሀላል ምግብ ተብሎ ካልተለጠፈበት ምግብ ቤት በቀር አልበላም ያልኩ ሰው ሆዴ ተላወሰብኝ ። እግዜር በታይ እንደሌለ ወላ ፆሜን ገደፍኩ ። በርግጥ ክንፍ-ክንፉን ብቻ ነው የበላሁት ሃሃ ።
የገረመኝ የምች ከአገር ውጭ አለመኖር ነው ። አገር ቤት ቡና ላይ ጤና አዳም አበዛህ ብሎ የሚያጣፋኝ ከይሲ ባቡር መንገድ ላይ የዶሮ ዳሌ እንደሸንኮራ ስግጥ እንዴት ዝም አለኝ ?
ብቻ ሆዴ ትንሽ ተንፈስ አለች ። ስጠግብ የጠባሹን ሰውዬ መልክ ታየኝ ፥ ሽበታም ሞንጎላይ ነው ። አመሰገንኩ - ካፑን ኽራብ ! ። ያጠለቀው ጋወን ላይ በራሪ ትሁን ቀዛፊ ፥ የሆነች እንስሳ ታትማለች ። ቀና ስል ፥ ከአናቱ በላይ በሜንጦ የተንጠለጠሉ አራት ዳክዬዎች ተዘቅዝቀው አየሁ ፥ ... ፈ ...ጣ ... ሪ ...ዬ ... !
ለምን አስበላኸኝ አልልህም ፤ ምን ይሁን ብለህ ቀና አረከኝ ሃሃ ። የተጣባኝን አጋሰስነት እየረገምኩ ካሁን-አሁን አስታወከኝ ብዬ በጉልበቴ ተደፋሁ ። እንደ ኮብል አንጣፊ አጎንብሼ ብጠብቅ የለም ፤ ብጠብቅ የለም ። ከነባር ምግቦች ጋር ሲብላላ ቆየ መሰለኝ ፥ ጭራሹን አስጋሳኝ ...ኧረ'ረረረ
ሆዴን እንደነገሩ እያሸሁ ካጎነበስኩበት ስነሳ ቁምጣ አድርጋ የምትሸጥ ቢጫ ኮረዳ ታየቺኝ ። የፈጣሪ ስራ በምክንያት ቀና ያረጋል ፥ በምክንያት ያስጎነብሳል ።
ቁምጣ የሚባል ጥብቆ እንደሌለኝ ትዝ ያለኝ ቢጫ ገላዋን እንዳየሁ ነው። ከሱቋ ገብቼ መዟዟር ጀመርኩ ፥ ልጅት ከስልኳ ላይ እንደተደፋች ነው ። ከቶፗ ሊያፈረግጥ የሚታገለው ጡቷ እንደመንግስት ግማሹ ወርዷል ። ጡቷን እያየሁ ብቆይ እንደቅድሙ አሻንጉሊት ልሆን ሆነ ። ድጋሚማ አልባባትም ሃሃ
ወሬ ለመጀመር ያህል ሸምቀቆ ያለው ቁምጣ ስቤ ፥ ሃው ማች ? አልኩ ። እሷ ሰው ጤፏ እቴ ፥ ከስልኳ ቀና ሳትል በእጇ ወደመደብሩ አናት ጠቆመቺኝ ። የመደብሩ አናት ላይ 300 ተሰርዛ #200 ONLY የሚል ካርቶን ተለጥፏል ። እንግሊዘኛ በከንቱ አባክኜ ሳላስወራትማ አሌድም ብዬ ወደ ኪሴ ገባሁ ። ጊቭ ሚ ሃሃ
ቁምጣውን ልታወርድ ስትንጠራራ ያጠለቀችው ቫንስ ሸራ ከአይኔ ገባ ። የእግር ቁጥሯ ርዝመት ከቁመቷ ይስተካከላል ቢባል ማጋነን አይሆንም። የሰው ልጅ ዘሩ እንዲህ በመለያየቱ እየተገረምኩ ከፈልኩ ። ፈገግ ብላ በለዘዘ አፍ ፥
- ታንኪ'ዩዩ ፎ ባይይይንግ ! አለች ።
ከምስጋናዋ ጋር ግን የፈነዳ ፈንጂ ነበር ። ፍንዳታው በእንግሊዘኛ መኮላተፉ አደለም ። ብቻ ... ፈንጂ ለመጀመሪያ ግዜ ከድምፅ ተዳብሎ ከአፍ ሲወጣ አየሁ ። ጎርናና የወንድ ድምፅ ... ታንኪ'ዩዩ ፎ ባይይይንግ ! ቡ... ም !
በእታባ ሞት ፥
ምኔ እንደሮጥኩ ፥ ምኔ ከሆቴሌ እንደገባሁ ፥
ምኔ ክፍሌን እንደቆለፍኩ ፥
ምኔ ድርሳነ ሚካዔል እንዳወጣሁ ፥ ምኔ ... ሃሃሃ
-------------------------------------
Land of the free - ክፍል 2

ዘ ፍ ጥ ረ ት
[ ልዑል ዘወልደ ]
- አባ
የልጁ ድምፅ ነው ። ሁሌም ሲጠራው እንደተለኮሠ ኩራዝ ፊቱ በርቶ ከሌላው ይዳርሳል ። በትከሻው ይዞት የነበረን ፋስ አውርዶ ከቤት ሳይገባ ከበሩ መደብ ተቀመጠ ። ከቤት ተንደርድሮ የወጣው ልጁን እንደታቀፈ አድንኖ መሀል አናቱን ሳመው ።
- አባዬ
- ወዬ ፥ የኔ ልጅ ?
አፍ ከፈታ አመታት ቢሆንም ከርሱ ማውራት አልሰለችህ ብሎታል ። ሆድ ባይኖርና እርሻ ሳይሄድ ከርሱ ሲጫወት ቢውል ፥ እሱን ይመርጣል ። የበኩር ልጅ መርማሪ ነው ይሉትን ሰምቶ የባጥ የለ የቆጡን ሳይታክት ያስረዳል ። ልጁም እንደነገሩ መርማሪ ነው ፥ እስኪደክመው ወይ እስኪረካ መጠየቁን አይተውም ። መሀላቸው ሰው አይገባም ። እታፈራሁ ፥ የባሏን መምጣት እንዳየች የእግር ውሃ ልትጥድለት ወደ ማጀት ገባች ።
ቀጠለ ፤
- እንተ ነክ እንዴ የወለድከኝ አባዬ?
- ሃሃሃ አዎና ! አይ አንተ ሂሂ ፥ እናትህ እታታ'ም ግን አለችበት ።
እታታ እሳቱ ተያይዞላት ፥ አንዴ ከሳቋ አንዴ ከጭሱ ወደውስጥ እየማገች ቀድማ ተንተከተከች ። እርሷ የማያልቁ የልጆቿን ጥያቄ የምትገታበት ግላዊ መላ አላት ። ግራዋ አውልላ በስንት ያስተወችውን ጡቷን መልሳ መወተፍ ። ያኔ ከልቧ ወርዶ ጡቷን መጥባት ይጀምራል። የቸገረ የሆነበት ለአባቱ ነው ። አያጠባው ነገር ደረተ መኻን ነው ። ቀን የበሬው እንዳይበቃው ምሽት-ምሽት በልጁ ጥያቄዎች ይወዘወዛል ።
- እናንተንስ ግን ?
- እኔና እታፈራው ?
- እ ፥ እናንተን ማን ወለዳቹ ነው?
- እኛንም እንዲሁ ፥ እናት አባቶቻችን ናቸዋ ። ባለፈው እስከ ምንጅላት ያስቆጠርኩህን ረሳህ እንዴ ?
- ኧረ አረሳሁም ።
- በል እስኪ ፥
- ደምስ አየለ ፥ አየለ መኩሪያ ፥ መኩሪያ ደረጄ ፥ ደረጄ ቢሰጥ ፥ ቢሰጥ ...
- አዬ የኔ ምላጭ ፥ ና በል ተሳም
- እና እዝጋቤር ሳይሆን አየለ ነው የወለደህ?
- አሃ ሁለቱም ፥ እርሱም እግዚያብሔርም ነው እንጂ ። ሁሉንም እኮ አንድዬ ነው የፈጠረው ።
- ቆይ እሺ እሱንስ ?
- እሱን ምን ?
- እሱንስ ማን ፈጥሮት ነው?
- ማንን ?
- እዝጋቤርን
- እ ?
- እ
- ይኸውልህ አንበሳዬ ፥ እርሱን ደግሞ ...እ....ፈጣሪ በመጀመሪያ ....እ...አለም ሳይፈጠር...እ...ከሁሉ አስቀድሞ...እ...እ...እታ ...እታፈራሁ ነይ ልጅሽን ውሰጅልኝ !

❤1🔥1
ቃሲምና የፈረንሳይ ሽቱ
[ ልዑል ዘወልደ ]
ሣምንት ብንጠፋፋ ጓደኛዬ ቃሲም ከጁምኣ መልስ የተቃውሞ ሰልፍ ሲያስተባብር በዩቲዩብ አየሁት ። ከፊት ሆኖ "ፌዳ ነብሲ - ፌዳ ነብሲ" ይላል ። ቃሲም ደሞ ምን ገጠመው ብዬ ፌስቡክ ብከፍት ፕሮፋይሉ ላይ በሱፍ ቂቅ ያለ ሰውዬ ተዘቅዝቋል ። ተዘቅዝቆ ከማየት ስልኬን መዘቅዘቁ ስለሚቀል ስልኬን አዙሬ አየሁ ። የተዘቀዘቀው ሰውዬ የፈረንጅ ጠቅላይ ነው ።
እንዴ? ቃሲም ደሞ ከኢማኑዔል ማክሮ ጋር ምን አገናኘው ብዬ አሰብኩ ። ደህና ምክንያት ግን አልመጣልህ አለኝ ። ማለቴ ፥ ከሳምንት በፊት ሳቃቸው ደህና ነበሩ -ሃሃ ። ዛሬ በጠዋት ደወልኩለት ።
- ቃሲሞ
- ወዬ
- ትላንት እኮ በዩቲዩብ አየቼህ ...
- ኧረ ተወኝ ይሄ ውሻ ፥
በመጨረሻ ቀን ስንገናኝ አፉ ላይ የተውኩት ጥያቄ የስልጤ ክልልነት ጉዳይ ስለነበር የአፉን ይዤ አሰር-ገባውን እተረተር ጀመር ። አጀማመሬን ሁላ በተረት ፥
- ህጲ በዳለህ አርበ በዳላህ ! ይሄ ነጫጭባ ። ፈረንሳይ ደሞ በስልጤ ክልል መሆን ምን አገባት? ሁሉም ላይ ጥልቅ ካላልኩ ይባላል እንዴ? ነውር እኮ ነው ። አይደለም ስልጤን ወለኔን ክልል ከመሆን የሚያግደው የትኛው ምድራዊ ሀይል ነው ? ...
ስልኩ ዝም ሲልብኝ ብዙ እንደለፈለፍኩ ገብቶኝ አዙሬ አየሁት ፥ ተዘግቷል ። የቀደመው ቅሌት እንዳይበቃኝ መልሼ ደወልኩ ።
- ቃሲሞ
- ያረቢ ፥ አልትራከቤን ! ምኑን የምለፈልፍብኝ?
- እና አትናገርም ፥ ምንድነው እሺ ? ማክሮን ምን አረገ ?
- ምን የማያረገው አለ? ከማይረባ የርዳታ ስንዴ ቲም ያለው ኢማን ይበልጣል ። ይሄ የሸይጣን ቁራጭ ጭራሽ ብሎ ብሎ በሀይማኖቴ ይምጣ ? አለኝ ።
የጀመረውን ጥያቄ ራሱ ይለጥቀዋል ብዬ ብጠብቅ እንዳንጠለጠለው ቀረ። ለማዳመቅ ማን ቀድሞኝ ፥ ምናባቱ አለ ደሞ ? አያልኩ አጋጋልኩ ። ነገር ግን ፥ ኧረ ተወኝ ! እያለ ከመራገም በቀር የረባ ነገር አልወጣው አለ ።
ኋላ ላይ እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ባገሩና በማተቡ ስለማይደራደር ነው እንጂ ማክሮ ምን እንዳለ አለመስማቱ ገባኝ ፥ ሃሃሃ
ያም ሆኖ ወሬ ካልሟሸ ደግ ስላልሆነ ፥ የባጡን እያወረድኩ አረጋጋው ገባሁ ። ቀናዒነቱ ግን ገዝቶኛል ፥ በፓሪስ እንደ ኢተሰዮጵያ ያለ ዲሞክራሲ እንዲሰፍን ከመፈለግ አንፃር ነው ። ፕሬዚደንት ማክሮ እንደ ኡስታዝ አብይ መውሊድ ቢደኣ ነው ሳይል ሶስት ገፅ ቢፅፍ ይሄኔ መከራከሪያው ሌላ ነበር ።
- አይዞን በቃ ቃሲሞ ፥ ፈረንሳዮች አጣሀቸው እንዴ ? ከድሮም የባለጌ ፊልም እየሰሩ እነሱ አደሉ እንዴ ወግ ባህላችንን የበከሉት ፥ እነሱ ሲወርዱ አብሮ ከነሱ ጋር አብሮ መውረድ አያስፈልግም ! አንተ ብቻ በኢትዮጵያዊነት ከፍታ ፣ በዳዕዋና በዲንህ ፅና።
- ወላሂ አቦ ! ሐቂቃ አለህ ። እኔ ከዚህ ወዲህ የኚህን ከፊሮች እቃ መጠቀም አይደለም ቋንቋቸውን ራሱ ላለመስማት ወስኛለው ። ይኸው ፥ ዛሬ ጠዋት ፍሬንች ቁርጤን አስነስቼ ፥ አላኋክበር ፥ የሀጂ ተጓዥ መስያለው ።
- ሃሃሃ ፥ ደገ አረግህ ፥ ምናቸውም አያስፈልገንም።
- እሱ ብቻ መስሎህ ነው ?
- እህ?
- ትላንት ከመስጂድ ስወጣ ዲዮር የፈንሳይ ነው ብለውኝ የባለቤቴን ሽቶ አንስቼ አመድ አረኩት ። የታባቱ ፥ ከአራት ሺ ብርና ከኢማን የቱ ይበልጣል ?
- እሱስ ልክ ነህ ። ላለፈው ዒድ ገዛሁት ያልከኝስ ሽቶ ግን?
- እ....
- ያ እንደውም ስምንት ነው ዘጠኝ ሺህ ገዛሁት ያልከኝ ፥
ድምፁ ዘገየ ። ከመሳቢያ አውጥቶ ሜዲኑን እያየ መሆኑ ገብቶኛል ። ማርኩን ሲፈልግ በመሀል "Eau de toilette" የሚል ፅሁፍ ከሽቶው ላይ አምልጦት አነበበ ። ጮክ ብሎ ፥
- አላህዬ አረቢኛ ነው በለኝ ሃሃ