Sost Kilo
5.09K subscribers
998 photos
45 videos
7 files
107 links
Stories | ሦስት ኪሎ

@leoulz
Download Telegram
1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
𝚂𝚊𝚍𝚕𝚢, 𝚍𝚞𝚎 𝚝𝚘 𝚜𝚞𝚙𝚎𝚛𝚜𝚝𝚒𝚝𝚒𝚘𝚗 𝚊𝚗𝚍 𝚏𝚘𝚕𝚔𝚕𝚘𝚛𝚎, 𝚋𝚕𝚊𝚌𝚔 𝚌𝚊𝚝𝚜 𝚊𝚛𝚎 𝚕𝚎𝚜𝚜 𝚕𝚒𝚔𝚎𝚕𝚢 𝚝𝚘 𝚐𝚎𝚝 𝚊𝚍𝚘𝚙𝚝𝚎𝚍 𝚝𝚑𝚊𝚗 𝚘𝚝𝚑𝚎𝚛 𝚌𝚊𝚝𝚜, 𝚊𝚜 𝚝𝚑𝚎𝚢'𝚛𝚎 𝚜𝚞𝚙𝚙𝚘𝚜𝚎𝚍𝚕𝚢 "𝚋𝚊𝚍 𝚕𝚞𝚌𝚔." 𝙻𝚒𝚔𝚎𝚠𝚒𝚜𝚎, 𝚖𝚘𝚜𝚝 𝚜𝚑𝚎𝚕𝚝𝚎𝚛𝚜 𝚠𝚘𝚗'𝚝 𝚎𝚟𝚎𝚗 𝚊𝚍𝚘𝚙𝚝 𝚘𝚞𝚝 𝚝𝚑𝚎𝚒𝚛 𝚋𝚕𝚊𝚌𝚔 𝚌𝚊𝚝𝚜 𝚏𝚘𝚛 𝚒𝚗𝚌𝚛𝚎𝚍𝚒𝚋𝚕𝚢 𝚍𝚒𝚜𝚝𝚞𝚛𝚋𝚒𝚗𝚐 𝚛𝚎𝚊𝚜𝚘𝚗𝚜 . 𝙷𝚊𝚙𝚙𝚢 𝚋𝚎𝚕𝚊𝚝𝚎𝚍 𝙱𝚕𝚊𝚌𝚔 𝙲𝚊𝚝 𝙰𝚠𝚊𝚛𝚎𝚗𝚎𝚜𝚜 𝚖𝚘𝚗𝚝𝚑 🖤
Black cat awareness month
<unknown>
Listen to the most recent episode of Sostkilo podcast: የ አ ረ መ ኔ ፡ ክ ር ስ ት ያ ኖ ች ፡ ዘ ር ፡ ማ ጥ ፋ ት | Black cat awareness month ••• https://anchor.fm/sostkilo/episodes/ep-e19if5j
1
የሲያትሏ ማርያም ምን አረኩሽ ?

[ ልዑል ፡ ዘወልደ ]

ልጃቸውን ለማረስ እናት ወደ አገረ አሜሪካ ይበራሉ። ከአገሩ ልጃቸውና የልጃቸው ባል አበባ ይዘው ተቀበሏቸው ። ሰላም በመግባታቸው ቢደሰቱም አንድ ፍፁም ያልጠበቁትን ነገር አይተዋል ። የልጃቸው ባል በስልክ እንደሰሙት ፈረንጅ ሳይሆን ከዳካ የጠቆረ ግዙፍ ሰውዬ ነው ።

- አበስ'ገበርኩ
ልጄን ሰድጄ ፥ ከባርያ ተዛመድኩ ...

እያሉ ሰውየውን ካንገት በላይ የነገር ሰላም አሉት ። ወደ ቤት ሲወስዷቸውም እንደ እዝን ተጓዥ ተለጉመው ብቻቸውን እየተብሰለሰሉ ነበር ። ከ'አገርቤት ሳሉ ቡና ለጠራቸው ሁሉ " ልጄ ፈረንጁን ነው ያንበረከከችው ፥ የልጅ-ልጄ ከመልአክ መለስ ያለ ክልስ ነው" እያሉ ያወሩት ቅሌት ሁሉ ተንዣበባቸው።

ልጃቸውን ማረስ ከጀመሩ ወዲያም ሊያዋራቸው ሲሞክር " ወይድልኝ ፥ ልጥልጥ ባርያ !" እያሉ ፊት ይነሱት ጀመር ። ልጃቸው የገዛ እናቷ ላይ ብትፈርድም ከሰው አገር ጠርታ ላለማስቀየም ዝምታን መረጠች ። ጥቁር አሜሪካዊው ጉድ ሞሪንግ ባለ ቁጥር በንቀት ከሚመልሱለት ቃላት 'ባርያ' በመደጋገሙ በልቦናው ተቀረፀችበት ።

አንድ ቀን ከስራ ሲመለስ እግረመንገዱን የአበሻ ኮሚኒቲ የሚበዛበት ሰፈር ሄዶ ትርጓሜውን ያጠያይቃል ። የቃሉ ፍቺ " የግዢ ሻግያ ፥ ከተራ ሰው ያነሰ " መሆኑን በሰማ ግዜ እሳት ጎርሶ እሳት ለብሶ ወደ ቤት ተመመ ። ከቤት እንደገባ ሚስቱ ተኝታ እርሳቸው ደግሞ ከአፓርታማው በረንዳ ላይ ሆነው የፀሀይዋን አገባብ እያዩ ነበር ።

ቀጥታ ወደሳቸው በመሄድ ከመቀመጫቸው አንስቶ ሰጥ አርጎ አንጠለጠላቸው ። እንዴት አውሬ እንደሆነ ባዩ ግዜ ንቅሳታቸው እስኪለቅ በረገጉ ። በመጠጥ ጢቅ ብሎ ጠንዝቶ አፉ ጠጅ ከላሰ ጋን ይጠነባል ።

አይናቸውን ከማቁለጭለጭ በቀር የሚናገሩት ቃል ጠፋባቸው ። የማይሰሙትን ብዙ የፈረንጅ ቃላት በሀይል እየወረወረ ሻሻቸው እስኪፈታ ጮኸባቸው ። ይባስ ብሎ በእግራቸውን ጠፍሮ ከፎቁ ወደታች ዘቀዘቃቸው ። በሰው አገር ንፋስ ተገላለቡ አረንጓዴ ውስጥ-ልብሳቸው በአሜሪካ አየር ተንቦለቦለ ።

በኮሰመነ ልባቸው የወይበለዋ ማርያም እንዲ ልታቀይኝ ነው ካገሬ የሰደድሽኝ እያሉ አማረሩ ። አማረው ሲጨርሱ ፥ አሁንም አየር ላይ እንደሆኑ ልብ አሉ ፥ ልብ ብለውም ፥ በይ የሲያትሏ ማርያም አንቺ ደግሞ ነብሴን ተቀበያት ብለው ወደ እዬዬ ገቡ።

ሰውየው ምንም ቢሆን የልጁ አያት እንደሆኑ ተገለጠለት መሰለኝ ከሞት አፋፍ መልሶ በእግራቸው አቆማቸው ። ትንሽ ከተጉረጠረጠባቸው በኋላም ከልብ ምታቸው ጋር ጥሏቸው ወጥቶ ሄደ ።

ባርያ የምትለውን ቃል ከእንግሊዘኛው ስድቦቹ መሀል ስለሰሟት ጥፋታቸው ምን እንደሆነ ገብቷቸዋል ። ሙሉ ለሊቱን በፍርሃት ከአራስ ልጃቸው ጋር በአንድ አልጋ አደሩ ። አይነጋ የለም ሲነጋ... ምንም እንዳልተፈጠረ ... በእጁ ጁስ እየጠጣ ...

- ጉድ ሞርኒግ ኢማማ ... አላቸው ። በትላንቱ አተያየት አይን አይኑን እያዩ ...

- ደህና አደርክ ቀዮ ...ሃሃሃ
2
አሁን ምን ያደርጋል የሴት ወየው ባይ፣
ወሎ የመጣው ሞት ሸዋ የለም ወይ?

[ ልዑል ፡ ዘወልደ ]

ምክንያት ይሰጡት እንጂ ፥ ሞት አይቀርም ። ተዘጋጅተው አይጠብቁት ነገር ደግሞ እንግዳ እንጂ ሙሽራ አይደለም ። በጦርነት ግፎች እንደሚሞት ሁሉ በሰላም ውስጥ ተኹኖም ይሞታል ። በረሃብ አረንቋ እንደሚሞት ፥ በጥጋብና አለቅጥ ውፍረትም ይሞታል ። ኤሊያሶች አይደለን አንዳናርግ ፥ ሮሙለስ አይደለን አንሠወርም ። ለማን እንደራራው - ለማን እንደሳሳው ይተወናል ?

በአንድ ወቅት የሸዋረጋ ምኒሊክ ፥ የንጉሥ ሚካኤል ባለቤት ፥ ከወሎ አገር መከተሟን ሸዋዎች አልወደዱም ነበር ። ይህ አለመውደዳቸው ከወሎና ሸዋ ባላንጣነት ፥ ማለትም ከልጅ እያሱ መፈንቀለ መንግስት ጋር ይገናኛል ።

ታዲያ እመቤቲቱ በጠና ይታመሙና ይሞታሉ ። ያን ግዜ ታዲያ ሸዋ ሙሾ አውራጅ ከወረኢሉ ይሰዳል ። ሴቲቱም ...

በቀረብሽ ምነው ፥ ከወሎ ጋብቻ ፥ በወሎ ግዛት ፤
ወጣ እንዳለች ቀረች የሸዋ እመቤት ።

እያለች ህዝቡን ታስለቅስ ገባች። ለዚህ መልስ ፥ በለቅሶው ላይ የነበረ ወለየ ፥ የመግቢያዬን ርዕስ ተቀኘ -

አሁን ምን ያደርጋል የሴት ወየው ባይ፣
ወሎ የመጣው ሞት ሸዋ የለም ወይ?

ተይ አንቺ ሴትዮ ነገር አታጥብቂ ፣
እኛ አልገደልናትም እግዜርን ጠይቂ ።

ሰው ፥ ከሞት በኋላ ባለው ሕይወት አመነ አላመነ ከመሞት አይቀርም ። ከመካከለኛው ምስራቅ የፈለቁ ሀይማኖቶች የሞት ምክንያት ከዕፀ በለስ ጋር ሲያቆራኙ ያ ወለየ ግን እስኪ ምናልባት እስኪ እግዜርን ጠይቁ ብሏል ። እንጠይቅ ?

ብቻ ጠየቅን አልጠየቅን ፥ ሞት ይመጣል ሃሃ ። ማድረግ የምንችለው ፥ ቢያንስ መልዓከ ሞትን ማዝናናት ነው ። በAppointment in samarra - ኢራቃዊው የነጋዴ ተላላኪ ኒቃብ ያደረገች መልዓከ ሞት በባግዳድ አይቶ ወደ ሣማራ ሄዶ ይደበቃታል ። ይሄ ያየች መልዓከ ሞት ታዲያ በዚህ ተዝናናች ፥ ደስም አላት ። በመዝናናት ውስጥ ሆና እንዲህ የተቀኘች ይመስለኛል ፥

ከነጋዴው ፈረስ ፥ የተበደርከው
ሣማራ የለም ወይ ፥ ከባግዳድ ያለው ?
1
Forwarded from Sost Kilo
ᵀʰᵉʳᵉ ʷᵉʳᵉ ᵃˡˡ ᵏⁱⁿᵈˢ ᵒᶠ ˢᵗᵒʳⁱᵉˢ ᵗᵒˡᵈ ᵃᵇᵒᵘᵗ ᵗʰᵉ ʷᵃʳ ᵗʰᵃᵗ ᵐᵃᵈᵉ ⁱᵗ ˢᵒᵘⁿᵈ ᵃˢ ⁱᶠ ⁱᵗ ʷᵃˢ ʰᵃᵖᵖᵉⁿⁱⁿᵍ ⁱⁿ ᵃ ᶠᵃʳᵃʷᵃʸ ᵃⁿᵈ ᵈⁱᶠᶠᵉʳᵉⁿᵗ ˡᵃⁿᵈ° ᴵᵗ ʷᵃˢⁿ'ᵗ ᵘⁿᵗⁱˡ ʳᵉᶠᵘᵍᵉᵉˢ ˢᵗᵃʳᵗᵉᵈ ᵖᵃˢˢⁱⁿᵍ ᵗʰʳᵒᵘᵍʰ ᵒᵘʳ ᵗᵒʷⁿ ••• | 𝙸𝚜𝚑𝚖𝚊𝚎𝚕 𝙱𝚎𝚊𝚑 | 𝙰 𝙻𝚘𝚗𝚐 𝚆𝚊𝚢 𝙶𝚘𝚗𝚎: 𝙼𝚎𝚖𝚘𝚒𝚛.
1
See you in December. Stay safe !
Sostkilo Podcast 📻 | 2021 Wrapped: 3K plays - 100+ subscribers -11 episodes - 14 countries. Merci 🙌 #2021PodcasterWrapped #SpotifyWrapped