አላህ ፥ አሏህ
[ ልዑል ዘወልደ ]
ካቻምና የታላቁን ዋትፍራይ ቤተመቅደስ ስጎበኝ የሰማሁትን ዛንታ ላጫውታችሁ ፤ አርብም አይደል ። የጨዋታው ገድል ለቡድሃ ቢያደላም ፤ በሮማ ስትሆን እንደሮማውያን ነውና በግዜው ቡድሃን ወግኜ ስቄያለሁ ። የተቀረውን የፓታያ ቆይታ ሌላ ግዜ እየቀነጫጨብኩ እፅፈዋለሁ ። አሁን ፥ ጁምኣ ሙባረክ ብዬ እቺን ዛንታ ላውራ ...
አንድ ወቅት ላይ እስላም ፣ ክርስትያንና ቡዲስት በፈጣሪያቸው ትክክለኛነት አብዝተው ይከራከራሉ ። ይሄ ክርክራቸው መቋጫ አጥቶ ይሰነባብትና በስተመጨረሻ በአንድ ፈተና ይስማማሉ ። ፈተናው ራሳቸውን ከተራራ አፋፍ ላይ በመወርወር ፈጣሪያቸው ሲታደጋቸው ማሳየት ነበር። ቱማንክ ከሚባል ገደልማ ተራራ ጫፍ ወጥተውም ተደረደሩ ።
ክርስትያኑ ቀልቃላ ቢጤ ነበር ፥
- የኔ እየሱስ አድህኖቱና ከልጁ ከኔ ይጀምር ብሎ ታበየ ። ለጥቆም ፥
- እነሆ ተዓምራትህን በኔ ግለፅ አለና ራሱን ወረወረ ። በመንገዱም ...
- እ የ ሱ ስ
እ የ ሱ ስ
እ የ ሱ ስ ...
እያለ በመጮህ ተምዘገዘገ ።
መጨረሻው ግን ያማረ አልነበረም ። እንዳሰበው እየሱስ አልተራዳውም ። ሲምዘገዘግ ሄዶ አግጦ ከጠበቀው አለት ላይ አጥንቱ እንዳይተርፍ ሆኖ ተፈጠፈጠ ። አማሟታችሁ ያሳምርላችሁ ፥ የቻይና ፊደል መስሎ ሞተ ሃሃ
የቀሩት በአሟሟቱ በጣም ተደናገጡ ። ሆኖም ቡዲስቱ መነኩሴ ለመወርወር ልብሰ ተክህኖውን አጣጥፎ ተዘጋጀ ። ከዘለለ ኋላም ጌታውን ተጣራ ...
- ቡ ድ ሃ
ቡ ድ ሃ ...
ልክ በሁለተኛው ጥሪ አንዳች መለኮት አስፍፎ እንደወፍ ላባ አባብሎ አከብክቦ በግርማ ከመሬት አሳረፈው ። ከአለቱ ላይ ሆኖ ወደ በማንጋጠጥ ፥ አሁንስ በቡድሃ ታምናለህ ወይንስ እንደሱ ዘለህ ትፈርጣለህ ? አለው ።
ሙስሊሙ ሰውዬ የከፋ አጣብቂኝ ውስጥ ገባ ። በዚህ ሉቅማን ላይ ያለው የአላህ ቃል "ልጄ ሆይ በአላህ ላይ ሌላ አታጋራ" የሚለው ሲይዘው በዚህ ስጋው ትጎትተው ገባች ። ጥቂት ዱዓ አርጎም ዘለለ ...
- አላህ
አሏህ
አሏህ
ነገር ግን የእድሜው ሙሉ ኢባዳ አልሰራም ። ጥሪው ተሰምቶ ከአላህ ቤት የተላከለት አንድም መሊክ የለም ። አይኑ እያየ አጥንቱ ሊፈርጥ ሆነ ። እየተምዘገዘገ ትንሽ እንደማሰብ አለና በሰለለ ድምፅ
ቡድሃ ሃ ሃ... ሃሃሃ

❤1
Intala mootti
<unknown>
ሦስት ኪሎ ፖድካስት: Bonus episode - Intala mootii | https://anchor.fm/sostkilo/episodes/Intala-mootii-e15pl0o
❤1🔥1