ኢትዮጵያዊ ወጎች #Ethiopian
1.36K subscribers
314 photos
3 videos
18 files
50 links
Download Telegram
4.5K ቤተሠብ አፍርተኛል ፡፡
እናመሠግናለን ዛሬም ነገም ሁሌምለእናንተ ይመጥናሉ የምንላቸውን እያጋራናችው አብረን እንዘልቃለን ፡፡

#ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ልጆችዋን ይባርክ CORONAንም ከምድራችን ላይ ያንሳልን
#ወይኩን_ፍቃድከ

በወዝጋባ ዕለት ውዝግብግብዋ ዕኔ
ግራ በሆነ ሀሳብ መልኩ በወየበ
እንባ ያነፈረው ዕርጥብ ጉንጬን ይዜ
ከእግዜር ደጃፍ ቆምኩኝ እለምነው ብዬ።

ልቤ ከህሊናዬ መንታ ሀሳብ ይዞ
ቅጭም ፈካ ይላል መልኬ ተበርዞ።

ጸሎቴ ውል አጣ
ምኞት አናወዘኝ
ሁለት ሀሳብ ናጠኝ።

እጄን አመሳቀልኩ
መላ አካሌን ባረኩ
ወደኩ ;ተንበረከኩ
መጽናናትን ናፈኩ።

ያሳብ ማዕበል አይምታኝ
ያሠብኩትን ሳይሆን
ያንተን ፍቃድ ስጠኝ።

ህሌና
#ሠናይ ውሎ
~~~~መልሱልኝ ልጄን
=============
ይድረስ ለአባ ገዳ~ለጎሳ መሪዎች
ላገር ሽማግሌ~ለእምነት አባቶች
~
መንግስትን አምኜ~ወግ አያለሁ ብዬ
ልጄን ልኬ ነበር~ ተማሪልኝ ብዬ
ተምራ መምጫዋን~ቀኗን እያሰላሁ
ናፍቃኝ ቻል አድርጌ~ማየት እንደጓጓሁ
ልጅሽ ታግታለች~የሚል መርዶ ሰማሁ
~~
ትማርልኝ ብዬ
ያይን ማረፊያዬን~ተስፋዬን ሰድጄ
ትኑር ትሙት አላውቅ~እጄን በላሁ በእጄ
እናም አሸማግሉኝ~ይቅርባት ትምህርቷ
ልጄን መልሱልኝ~ካለች በህይወቷ

#ህሊና ደሣለኝ ©


#የረሣናቸው_የእህቶቻችን_ጉዳይስ
#ስለሷ_ዝም_አንበል
#ፍትህ_ከወዴት_ነሽ
ከ Covid 19 በላይ ስቃይ ለኢትዮጵያ ህዝብ ይዞ እየመጣ ያለው የሀገር አቀፍ ምርጫ ጉዳይ ነው ይህ ምርጫ ዘንድሮ ይካሄድ አይካሄድ እናንተ ምን ታስባለችሁ የሽግግር መንግስትስ ያዋጣል ?
public poll

አይካሄድ – 30
👍👍👍👍👍👍👍 49%

ይካሄድ – 24
👍👍👍👍👍👍 39%

የሽ/መንግስት ይመስረት – 7
👍👍 11%

👥 61 people voted so far.
በኢትዮጵያ በመጪው ሰኔ ወር አጋማሽ የፀሃይ ግርዶሽ ይከሰታል!

በኢትዮጵያ በመጪው ሰኔ ወር አጋማሽ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ እንደሚከሰት የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት አስታውቋል።

ግርዶሹ ከምዕራብ እስከ ሰሜን ምስራቅ ኢትዮጵያ የሚታይ ሲሆን ክስተቱም ወለጋ፣ ከፊል ጎጃምና ጎንደር፣ በወሎ በተለይ ላሊበላ አካባቢ ቀኑ #የሚጨልም ይሆናል ተብሏል።

በተቀረው የአገሪቱ ክፍል ደግሞ በዕለቱ በከፊል ጨለማ ሊሆን እንደሚችል የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሰሎሞን በላይ ተናግረዋል።

ግርዶሹ ስድስት ሰዓታት የሚፈጅ ሲሆን እንደ ኢትዮጵያውያን አቆጣጠር የፊታችን ሰኔ 14 እሁድ ቀን ከጠዋቱ 12፡45 እስከ ቀኑ 6፡33 የሚቆይ ይሆናል።

#ENA
©TIKVAH-ETH
#Ethiopia : "የምናውቀው የመረመርነውን ነው ፤ የመረመርነው ደግሞ ትንሽ ነው። ትክክለኛ ትምህርትና እርምጃ ለመውሰድ በብዙ ቁጥር መያዝ ፣ በብዙ ቁጥር መሞት የለብንም”

ዶ/ር ሊያ ታደሰ ፤ የጤና ሚኒስቴር
#የምፃተኛው_ኑዛዜ
(በእውቀቱ ስዩም)

ካ’ገር ጫፍ እስከጫፍ በጥላህ ከልለህ
ተራራው የኔ ነው ለምን ትለኛለህ?
ወንዙ ድርሻዬ ነው ለምን ትለኛለህ?
እንኳንስ መሬቱ አንተም ያ’ንተ አይደለህ።
እኔ መጻተኛ አንተ ኗሪ ነኝ ባይ
እኔ እግሬን ስከተል ርስትህን ስታይ
ስቀርብህ ገፋኸኝ ስትገፋኝ ቦታ አጣሁ
ድንኳን ብትተክል፣ ነፋስ ሆኜ መጣሁ።
ያ’ባትህ ያ’ባቴ
ጠበኛ ስማቸው
ጠበኛ ሕልማቸው
በሕይወት ተጣሉ፣ ታረቁ ባፅማቸው
ባፈር ተቃቃሩ፣ አፈር አስማማቸው
በዙሪያቸው በቅሎ ከቧቸው ሞት ደኑ
መተቃቃፍ መርጠው ማማና ወይን ሆኑ።
ይችላል ይሉሃል ፍልሚያ ማዘጋጀት
ያ’ባት አጥንት ወስዶ ስሎ ጦር ማበጀት
አንተው ጦር ወርውረህ አንተው ቀድመህ ወድቀኽ
አካሌ ደረቴ መኾንኽን መች አወቅኽ ??? !!!

#ውብ ቀን
‹‹ነገ ሌላ ቀን ነው››
--------------------
ከዕለታት በዚች ቀን፣
በልዩ አጋጣሚ፤
እንድትሆኝ ጋበዝሁሽ፣
የቤቴ ታዳሚ።

አንቺ ግን ሰበባም፣
ምክንያት ደርድረሽ፣
ግብዣዬን አቃለሽ፣
እምቢ ብለሽ ቀረሽ።

በይ ከእንግዲህ ወዲያ፣
አንቺ ከኔ ጋራ፤
ፈፅሞ እንዳያምርሽ፣
ጊዜ እንድንጋራ።

እርሱ በፈቃዱ፣
ቢመርጥም ባይመርጥም፤
ዛሬዬን ለናቀ፣
ነገዬን አልሰጥም።

አየሽ በኔ ዓለም፣
ዛሬ ልዩ ቀን ነች፤
ነገ የማትመጣ፣
ትናንት ያልነበረች።

ጊዜን ትርጉም ሰጥቶ፣
ተግባር ለሚከውን፤
ቀን ማለት ዛሬ ነው፣
ጊዜ ማለት አሁን።

‹‹ነገ ሌላ ቀን ነው››
ትርጉሙ ይሄው ነው።
--------------------------
መላኩ አላምረው
📙 ነፍጠኛ ስንኞች

#ሠናይ ምሽት
#ውብ ለሊት
#ጥንቃቄ ማድረግ አይዘንጉ ለእርስዎ ለቤተሰብዎ ደህነንት ሲሉ
እህ እንዴት ነው ገዳዎ!
(በእውቀቱ ስዩም)
በጥንታዊ የጋርዮሽ ስርአት የመጀመርያው የሰው ልጆች ስራ
አደንና ፍራፍሬ መልቀም ነበር፤ አንድ ወንድ እና ሴት ተጣምረው
ዱር ለዱር ይንከራተታሉ:: እንጆሪ ለቅመው ወይም የዱር ፍየል
አድነው በጋራ ይበላሉ፤ከእለታት አንድ ቀን ሴቲቱ ታረግዛለች፤
ሆዷ ገፍቶ እንደ ድሮው ዛፍ መውጣት ወይም መስክ በሩጫ
ማቋረጥ በሚሳናት ጊዜ ባልየው አንድ ዋሻ ውስጥ ጥሏት ወይም
አስጠልሏት ይሄዳል፤ ገራም ከሆነ ዞሮ ዞሮ ይመለሳል ፤ የተረገመ
ከሆነ እንደወጣ ይቀራል፤ ቀስ በቀስ ሴቷ ባንድ ቦታ ልትረጋ
የተፈጠረች መሆኑን ትረዳለች፤ ጎጆም ትቀልሳለች::
ባንድ ቦታ ረግቶ መቀመጥ በሴት ሆርሞን ውስጥ ያለ ነገር
እንደሆነ ሁሉ ፤ መቅበዝበዝ በወንድ ልጅ ደም ውስጥ ያለ ነገር
ነው:: ሲሄድ ውሎ ሲሄድ የሚያድር ወንድ እንጂ ወንዝ
አይደለም፤ ወንድ ልጅ የእመቤቶች ለማዳ እንስሳ ከመሆኑ በፊት
ባንዲት ጣራ ስር እሺ ብሎ እሚቸከል ፍጡር አልነበረም፤
እንዲያም ሆኖ ፤ሰበብ እየፈጠረ፤ወታደር፤(ዋትቶ- አደር) ሲራራ
ነጋዴ፤ ፖስታ አመላላሽ ፤ አሳሽና ሀዋርያ አድርጎ ራሱን እየሾመ
የመሄድ ሱሱን ሲያረካ ኑሯል::
ቤት መስራትና መንደር ምስረታን የጀመሩት ሴቶች ሲሆኑ
ድልድይና ጎዳናን መስራት የጀመሩት ደሞ ብጤዎቼ ይመስሉኛል
፤ ስራ ላይ ራሱ ተመልከቺ ፤ አሁን ወንድ ልጅ ምንም ቢገደድ
ሁለት ሰአት ሙሉ ብቅል ሊፈጭ ይችላል? ራሱን በወፍጮው ልጅ
ፈጥፍጦ ቢገል ይቀለዋል፤ ታይፒስት መሆን ይችላል? ወንድ ልጅ
ባንድ ቦታ ቁጭ ብሎ የሚሰራው ስራ አለ? እንጃ! ምናልባት
ልብስ ሰፊነት ? እሱንም ቢሆን ታግሶ የተቀበለው ከታች እግሩን
ማንቀሳቀስ ስለሚችል ነው፤ ልብ ብለን ካየነው የሽመና ስራም
የቅምጥ ስራ አይደለም ፤ሰውየው ባይንቀሳቀስ ቆለጡ እሱን
ወክሎ ወድያ ወዲህ ይላል ፤
ምን ልል ፈልጌ ነው? ቀሳው በዚህ ከቀጠለ ወንዶች
ከነጨርቃችን እናብዳለን ፤ሴቶች እንደነበሩት ይቀጥላሉ፤ግፋ ቢል
ወንዱ አብዶ ሲፈነዳ ፍንጣሪው ቢነካቸው ነው፤
እኔኮ በራሴ አየዋለሁ፤ እግሬ ቢታሰር አእምሮየ ይንቀዠቀዣል፤
ሁለት የዩቲውብ ሳንዱቅ ከፍቼ አንዱን ሳላይ ወደ ሌላው
እዘልላለሁ:: ልደቱ አያሌውን መስከረም ሰላሳ ላይ አስደግፌ ወደ
ባህሩ ቃኘ የሄድኩበት ፍጥነት ጉግልን ራሱ ሳያሳስበው
አልቀረም:: what is the attention deficient
hyperactivity disorder የሚል እርእስ ያለው ሌክቸር
ሪኮመንድ አደረገኝ፤
በነገራችን ላይ እያንዳንድሽ እግዜር ባያይሽ ጉግል ያይሻል፤
ባለፈው፤ ባለንጀራየ በየነ ገላውን ታጥቦ፤ መቸም ብቻየን ነኝ
ብሎ፤ ላፕቶፑን ሳይዘጋ ታችኛውን ላጨ:: ከዛ ዩቲውብ ገብቶ
ባህላዊ ዜማ እየሰማ እያለ Recommended for you እሚል
መጣለት፤ እና ጎግል የመረጠለትን ቢድዮ ርእስ ሲሾፈው ምን
ይላል፤ How to enlarge your penis without a medical
aid .
አርፌ ባህሩ ቃኘን ባዳምጥስ ?
እህ እንዴት ነው ገዳ-ዎ
እንዴት ነው ገዳ-ዎ
እንዴ? ባህሩ ቃኘ ስለገዳ ስርአት መዝፈናቸውን እንዴት
እስከዛሬ ልብ ሳልል ቆየሁ?
#የማንቂያ ደውል ይሁነን!

"ሳል፣ ትኩሳት፣ ለመተንፈስ መቸገርና የራስ ህመም የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ምልክቶች ቢሆኑም አንዳንድ ሰዎች ምንም አይነት ምልክት ሳያሳዩ #ፖዘቲቭ ሊሆኑና ወደ ሌሎች ሰዎች የማስተላለፍ ዕድል ሊኖራቸዉ ስለሚችል ምልክቶች ታዩም አልታዩ የሚደረጉ መሰረታዊ የጥንቃቄ መመሪያዎችን መተግበር አማራጭ የሌለዉ ተግባር ነው" - አቶ አለማየሁ አልዬ (የሀላባ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊ)

#Stayhome
#staysafe
“ብትችል ብረር፤ መብረር ካልቻልክ ሩጥ፣ መሮጥ
ካልቻልክ ተራመድ፣ መራመድ ካልቻልክ ተንፏቀቅ ግን ምንም
ቢሆን መሄድህን አታቁም”
ማርቲን ሉተር ኪንግ

#ሠናይ ቀን ከሙሉ ጤና ጋር
""" "እናቴ"" """
ፀጉርሽን አይቼ የኔን ፀጉር ሳየው
እንደ ወንድ ፀጉር ገባ ገባ ያለው
እሳት እንደነካው የተኮማተረው
----ለካ ለፍቅር ነው
የፊትሽ ላይ ቆዳ የተሸበሸበው
እንደ ወየበ ልብስ እንዲህ የገረጣው
እንደ ቼዙ ሜዳ የተዥጎረጎረው
--ለካ ለፍቅር ነው
በጉብዝናሽ ወራት በወጣትነትሽ
እነዚያ ውብ አይንሽ
ጎላ ጎላ ያሉት
ከለሊት ጨረቃ ደምቀው የሚታዩት
አሁን ደም ለብሰዋል
አንቺ ለእኔ ብለሽ በጪስና አቧራ
ሰውተሻቸዋል
---ይሄም ለፍቅር ነው
አንቺ የፍቅር አምድ
ተምሳሌት የመውደድ
አንቺ የፍቅር ማዕድ
ልክ እንደከዘራ ጀርባሽ የጎበጠው
አሁን ነው የገባኝ እኔ ቀና እንድል ነው
------አንቺ እንዲህ የሆንሺው ለካ
ለፍቅር ነው
መዳፍሽን ሳየው
አሻራ እንኳን የለው
ድህነት በልቶታል
ሸክም አጥፍቶታል
-----እናም ውዷ እናቴ
ዝምብየ ሳስበው
ምን አይነት ፍቅር ነው
ይሄን ሁሉ የሆንሺው
አንዴት በትወጂኝ ነው።
እማ ዛሬ ፍቅርሽ ገባኝ!!!

#መልካም ቀን
Dear members when u think to leave the channel it's better to leave us the reasons too😉
Inbox us here
👉 @Simetin_Begitimbot/
@Haile_melekot

So we are going to work on it.
በመጠንቀቅ ያተረፈ እንጂ የተጎዳ የለም!

(በዶክተር ኃይለልዑል መኮንን)

የዛሬ ሁለት እና ሶስት ሳምንት አካባቢ የፋሲካው ግርግር ምን ሊያስከትል እንደሚችል በተለያዩ ሚድያዎች ስንሰማ ቆይተናል።

ነገር ግን 'ጆሮ ዳባ ልበስ' ብለን ፤ ሰምተን እንዳልሰማን ሆነን "ኮሮና እኛን አይነካም" በሚል የባለሙያዎችን ትእዛዝ ሳንተገብር ቆየን።

ይባስ ብሎ ደግሞ ቁጥሩ በጣት የሚቆጠር ሲሆን "አይ ፈጣሪ ይጠብቀናል፤ ችግር የለም" እያልን ከኛ የሚጠበቀውን ጥንቃቄ ረስተን ብዙ ተዘናጋን።

የዛሬ ሶስት ሳምንት ገደማ "ለመጠንቀቅ የሞት ዜና አንጠብቅ" ብዬ ከፋሲካ ዋዜማ በስትያ የታዘብኩትን እና ሊመጣ ስላለው ከባድ ጊዜ አያይዤ ፅፌ ነበር። ይኸው ጊዜ ደጉ አሁን ላይ አየነው፤ አሁንም አረፈደብንም ለመጠንቀቅ ጊዜው አለን። እባካችሁ በቁጥር ከፍ እና ዝቅ ማለት ጥንቃቄያችን እና ስሜታች ከፍ ዝቅ አይበል።

ከፍ ሲል"በቃ አለቀልን!!" ዝቅ ሲል ደግሞ" የት አባቱ ኮሮናን ድባቅ መታነው" እያልን ቁጥር ላይ መሰረት አናድርግ።

አሁን ከምን ግዜውም በላይ የምንጠነቀቅበት ሰዓት ላይ ነን ፤ የትላንቱን ስህተት አንድገመዉ።

እባካችሁን እንጠንቀቅ!!

የዛሬዋ የሴኮንድ ስህተት ዘመን ተሻግሮ ጠባሳ እንዳያሳርፍብን እንጠንቀቅ፤ ይሄን ከባድ ጊዜ አሳልፈን ነገን በደስታ እንየው።
እምዬ ኢትዮጵያ ፣ ብትደላም ብትከፋም
ምላስ ናት ለህዝቧ ፣ ከአፋችን አትጠፋም።
።።።
አፍ በሚባል ዋሻ...
ምላስን የሚያህል ፣ ስጋ ተሸክሞ
ስጋ ባለመብላት ፣ ማንስ ያውቃል ፆሞ?!
:::::::::
ፍስክ ምላስሽን ፣ ባፍሽ ተሸክመሽ
ከዋናው የደም ምንጭ ፣ ልቤ ላይ ታትመሽ
ፆመኛ ነኝ ስትይ ፣ ታስገርሚኛለሽ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ወደ ነፍሴ ገዳም ፣ ስትገቢ መንነሽ
ዓለም በቃኝ ስትይ ፣ የኔው ዓለም ሆነሽ
ታስገርሚኛለሽ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
መልካም የፆም ወቅት !!!
(በላይ በቀለ ወያ )

@Simetin_Begitim
ቀለል ያሉ የጠቅላላ እውቀት ጥያቄዎችን እየተጠያየቅን ዘወትር ምሽት ከ2-3:00 እምናሳልፍበትን ሁኔታዎች እያመቻቸን ነው ይቀረብ አይቅረብ የሚለውን ከእናንተው እንረዳ
ይቅረብ👍
አይቅረብ👎
" እናትህ ጠፋች " ይላሉ አማርኛ መምህራችን ጌቱን።
በየሳምንቱ ወላጅ አምጣ ሲባል ለመዷቸው!
የጌቱ እናት፡ ቆንጆ ነበሩ መሰለኝ።
ጌቱ እንዲያጠፋ የሚገፋፉት መምህራንም ነበሩ፡
" የፊደል "ፖ" ን እግር ማነው የዘረጠጠው? "
" ተፈጥሮዋ ነዋ "
" ሴት ናትንዴ? "
" እኔንጃ ቲቸር "
" የመማር ፍላጎትህ ቀንሷል "
ወላጅ እንዲያመጣ " ይጋበዛል " ማለት ነው።
የጌቱ እናት በንቅሳት ብዛት የአለላ ሙዳይ የመሰሉ ነበሩ።
ደልደል ያሉ ናቸው።
ያኔ ታዲያ ቲቸር ይልማ፡
" ልጅዎ ጎበዝ ቢሆንም ከሰነፍ ተማሪዎች ጋር ገጥሟል "
ይሉና ሻይ ለማዘዝ ክበብ ይሄዳሉ።
ጌቱን ጎበዝ አሉት?......ጌቱን?
የጌቱ ስንፍናኮ ነገረኛ ነው።
" How old are you? "...እንግሊዝኛ ትምህርት ላይ
ዓይኑን ጣራው ላይ ሰክቶ......
" ደብተሬ ጠፍቶብኛል ቲቸር "
" ዋናው አንተ መትረፍህ "
አንድ ቀን Class activity ለግሬድ አሪፍ ነው ብለነው፡
ሳይቸግረው እጁን ያወናጭፋል
" እሺ የጌጥዬ ልጅ " አሉ እንግሊዝኛ መምህራችን እናቱን የናፈቁ
አይነት አይናቸው ቡዝዝ እያለ...
" እፉዬ ገላ በእንግሊዝኛ ምንድነው? "
" ቧልት ጀመርክ? "....አሉና እኔ ብቻ በሰማሁት ድምጽ
" እሷን ብየንጂ ፈስህን ነበር የማስረጭህ "
አንድ ቀን እንደተለመደው ወላጅ አምጣ ይባልና፡ አባቱ ከ ፊልድ
መጥተው እረፍት ላይ ስለነበሩ ይዟቸው ይሄዳል።
እናትየዋን የሚጠብቁት ቲቸር በለጠ፡ ጺማቸውን ተላጭተው፡ ሽቶ
ተለቅልቀው ይጠብቃሉ።
የጌቱ አባት ጋሽ ጓንጉል፡ እንደ ኮባ እየተዘናጠፉ ገቡ።
ቲቸር በለጠ በጣም ደነገጡ፡ ንዴት ተጨምሮባቸው፡
" ልጅዎ በጣም ረባሽ፣ አርፋጅ ስንፍናው ለከት የሌለው ነው።
ሌሎችንም ልጆች ያበላሻል....አንድ ቀን የሲጋራ ቁራጭ
ይዞ........."
የጌቱ አባት ልጃቸውን እንደ ዶሮ ዘቅዝቀው መያዝ ጀመሩ!
ከፍ አድርገው እንደ እቃ ጣሉት!
ጌቱ እንደዚያ ቀን አየር ላይ አልበዛብኝም።

Fikre Z Bhere Ethiopia
የመጀመርያ ዙር ቀለል ያሉ የጠቅላላ እውቀት ጥያቄዎች መልሱን @EthiopianFirst_bot ይላኩልን መልካም ዕድል

1) በኢትየጵያ የመጀመርያው ዘመናዊ ትምህርት ቤት ማን ይባላል ?

2) ኢትዮጵያ የአፍሪካን ዋንጫ መች ነው ያነሳችው ?

3) The Father of History በመባል የሚታወቅ ሰው ስሙ ማን ይባላል ?

4) ከአፍሪካ ሀገራት ውስጥ ብቸኛዋ የእራሷን ፊደል ያላት ሀገር ማን ናት?

5)እግርኳስን ለዓለማችን ያበረከተች ሀገር ማን ናት?


ለመጀመር ያህል በእነዚህ ጥያቄዎች አብረን እናምሽ መልካም ዕድል
እስካሁን ድረስ አንድም መላሽ አላገኘንም 😭😭😭