ኢትዮጵያዊ ወጎች #Ethiopian
1.43K subscribers
314 photos
3 videos
18 files
50 links
Download Telegram
"... [አለቃ ገብረሐና] የሚጠሉት አንድ ፉንጋ ቄስ ነበር፡፡ ታዲያ ቄሰ ሆዬ የአባ ገብረሐናን ሸፋፋነት ያውቅ ኖሮ ‹‹አባ ሽፍን ጫማ በሸዋ በኩል መጥቷል ይባላልና እንዳያመልጥዎ›› ሲል ያሽሟጥጣቸዋል፡፡ [አለቃ ገብረሐናን] በነገር የሚቀድማቸው የለም፣ ‹‹አንተ ፊት ግዛና›› ብለው ኩምሽሽ አደረጉት፡፡”

“[አለቃ ገብረሐና] ብቸኝነቱ ቢጫጫናቸው … ሴት ማዘውተር ጀመሩ፡፡ ሆኖም ጠላቶቻቸው ይከታተሏቸው ኖረው አንድ ቀን ሴት ቤት አድረው ሲወጡ ያያቸው ካህን ሲገሰግስ ራጉኤል ሄዶ ጉዳያቸውን ነገረባቸው፡፡ አለቃ አገር ሰላም ብለው ቤተክርስቲያን ሊገቡ ሲሉ ተከለከሉ፡፡
‹‹ለምን?››
‹‹ሴት ስለነኩ››
‹‹አይ ጥሩ›› ብለው አለቃም ተመለሱና ሳይታዩ የሴቶች መግቢያ በር ላይ ቆመው የመጡትን ሴቶች ሁሉ ‹‹መግባት ተከልክሏል›› ብለው መለሷቸው፡፡ ካህናቱ አንዲት የሔዋን አምሳል እንኳን በግቢ ውስጥ ቢያጡ ተደናግጠው ሁኔታውን ሲያጣሩ አለቃ ሁሉንም መመለሳቸውን ሰሙ፡፡
ካህናቱ ወዲያውኑ ንጉሡ ዘንድ ሄደው ከሰሷቸው፡፡ ‹‹ሴት ቤት አድረው ከመምጣታቸውም በላይ ሴቶችን ሁሉ ቤተክርስቲያን አትሳሙ ብለው መልሰዋል›› ሲሉም ወነጀሏቸው፡፡
‹‹ለምን እንዲህ አደረግህ ገብረሐና?››
‹‹እንዴ ጃንሆይ! እኔ ነካህ ተብዬ ስከለከል እነሱ ይዘውት ይግቡ እንዴ?›› ብለው ምኒልክን አሳቋቸው፡፡”

(“አለቃ ገብረሐና እና አስቂኝ ቀልዶቻቸው” ከሚለው የአረፈዓይኔ ሐጎስ መጻሕፍ የተወሰደ)

@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
# ነፃ_አውጪ

ሰደድ እሳት ሆኖ
ነገር ባገር ላይ ከመጣ፣
ያፈገፈገው ነው
ሌላውን ነፃ የሚያወጣ !!!

# ሀብታሙ_ወዳጅ

@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
ለፈገግታ
ግን ምን ተሻለ
@Simetin_Begitim
#ኢትዮጵያዊ ወጎች
ህዝብ ማለት ግለሰብ በጅምላ ማለት ነው!
(አሌክስ አብርሃም)
እንደምን አደርክ የትግራይ ህዝብ? (ከሰሜን ልጀምር)
እንደምን አደርክ የአማራ ህዝብ ?
እንደምን አደርክ የኦሮሞ ህዝብ ?
እንደምን አደርክ የአፋር ህዝብ ?
እንደምን አደርክ የአዲስ አበባ ህዝብ?
እንደምን አደርክ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ህዝብ ?
እንደምን አደርክ የሃረሪ ህዝብ ?
እንደምን አደርክ የቤኒሻንጉል ጉምዝ ህዝብ?
እንደምን አደርክ የሱማሌ ህዝብ?
እንደምን አደርክ የጋምቤላ ህዝብ ?
እና አንተ ሁሉ ህዝዝዝዝዝዝዝዝዝዝዝዝብ ለነገር ለግጭት ለጸብ ሲባል<<ህዝብ>> ተብለህ የሆነ የሚያስፈራ የሚመለክ ዓይነት ነገር ትሆናለህ ! ሌሎችን ማሸማቀቂያ ማስፈራሪያ ትሆናለህ ! ምን ዋጋ አለው ወንድምህ ቢፈራህ ? ርሃብ አይፈራህ ፣ በሽታ አይፈራህ ? ድህነት አይፈራህ ! አንዱ ካንዱ አይሻል ዘጠኝ ክልል ሙሉ ያጣ የነጣ ድሃ ! አንዱ ክልል ቢቸገር ሌላው ለማበደር የማይበቃ ! ሁልጊዜ የውጭ እርዳታ ብድር! ደግሞኮ ህዝብ ሲባል በቃ የሆነ ያብሮነት መንፈስ እንጂ ራሱ እጅ እግር ያለው አንድ ግዙፍ ፍጥረት ነገር አይደልም! የሆነች አለሚቱ ፣ ጫልቱ ፣ጉርሜሳ፣ ኡጅሩ ፣ ሰጥ አርጌ ፣ ገብረመድን ፣በድሩ፣ ወለላ አያልነሽ፣ ብርጣሉ የሚባሉ ሰዎች ተሰብስበው ህዝብ ይባላሉ !
ይታይህ ጫልቱና አያልነሽ ፣ ሰጥ አርጌና ኡጅሩ ፣ገብረመድህንና ጉርሜሳ እየተሰዳደቡ ፌስቡክ ላይ ጥንብርኩሳቸውን እየተወጣጡ ሲመቻቸው ምድር ላይ እየተፈነካከቱ ባደባባይ <<ህዝብ ማክበር >> ይሉሃል ህዝብ ማስፈራሪያ !! ባጭሩ ምን መሰልህ አንተ ይሄን ጽሁፍ የምታነበው በችርቻሮ ህዝብ ስትሆን ሰብሰብ ስትል ደግሞ በጅምላ ህዝብ ትባላለህ! አንድን ሰው ካላከበርክ ህዝብን በምንም ሒሳብ አታከብርም ! ህዝብ ግለሰቦች ምሰሶ ሁነው ያቆሙት ከፍ በሎ ይሚታይ ጉልላት ነው! ምሰሶውን በገጀራ እየጨረገድክ ጉልላቱን ማቆም የማይሆን ነገር ነው! ምሰሶውን እያዋረድክ እየዘለፍክ ጉልላቱን ማሞካሸትም ከንቱ ነው ! በህዝብ አታስፈራራ ! ጭራሮውን ንቆ በችቦ በዓል ላድምቅ አይባልም!!

@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
ባይገጥምም ይገጥማል
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
ሚታገላት ልቤ ፣ የሚጥላት ኪሱ
የፍቅር ጥያቄ
ያቀረብኩት እኔ ፣ ምትመልሰው ለሱ
አለመገጣጠም ፣ ግጥም ነው በራሱ።

@Simetin_Begitim
ለፈገግታ

ጥበብ ጠራችኝ😂😂😂
@Simetin_Begitim
©ፊደል Life Hack
😊አይበልና😂
.
.

እኔ፣ ሚስቴ፣ የሚስቴ እህት
ተቀምጠን በአንድ ምሽት
አይበልና እና እኔ ብሞት
እንደው ሌላ ታገቢያለሽ ስል ጠየኳት
ውዷ ሚስቴን ልገምታት ••
ምን ሊሆነኝ ካንተ ወዲያ አገባለሁ
እስካለልኝ ከህቴ ዘንድ እኖራለሁ
መልሳልኝ ብላ እንደዚህ •••
አንተስ ውዴ አይበልና እኔ ብሞት
ታገባለህ ሌላ እመቤት?
ጠየቀችኝ በተራዋ ልትገምት
እኔም አልኳት•••
ምን ሊሆነኝ ካንቺ ወዲያ አገባለሁ
እስካለልኝ ከህትሽ ጋር እኖራለሁ።
😂😂😂😂😂😂😂

@Simetin_Begitim
ሠላም ውድ የኢትዮጵያዊ ወጎች ቤቸሠብ እንደምን ቆያችሁን? ሁሌም እንደምንለው ሠላማችሁ የበዛ ይሁን!!
እስቲ ኢትዮጵያ ስለሚለው ስም ትርጉም እምታውቁትን ያህል አካፍሉን፡፡ እኛ ደግሞ ከ Prof ፍቅሬ ቶሎሳ አንደበት የሠማነውን በቅርብ ቀን ወደ እናንተ እናደርሳለን ፡፡ እስከዛው በ @Simetin_Begitimbot እናንተም አካፍሉን፡፡
ያወቁትን ማሣወቅ ትልቅነት ነው!
ሠላም ለኢትዮጵያ

@Simetin_Begitim
ስም እና Bio....😂😂😂
++ሰለሞን ሳህለ++

ትናንት...
እንደ ከሰረ ሰዉ
ወዘናዬ ጠፍቶ ጭዉ ብዬ ነጣሁ
በደበኞች ደባ
አንገቴን ደፍቼ ግፍ እንደ ዉሃ ጠጣሁ
ዝም ብዬ ተቀጣሁ...
ጮክ ብዬ ተቆጣሁ...
ልክ አንቺን ሳገኝሽ
ከሲኦል ሆድ ወጣሁ

ዛሬ...
የዛሬዉን ትርጉም የዛሬዉን ፍቺ
እንዲህ ነሽ ይልሻል ተቀበይዉ እንቺ
ዉስብስብ ቋጠሮን ስቀሽ የምትፈቺ
ቀና እምታደርጊ ቀና ሰዉ ነሽ አንቺ
ምንም እንዳይገርምሽ!!!

@Simetin_Begitim
ሠላም ሠላም ውድ የቻናላችን ቤተሠቦች እንደምን ቆያችሁን ?? እኛ ሁሌም እንደምንለው ሠላማችሁ ይብዛ፡፡
ሠላሙ የበዛና ውብ እሁድ ተመኘንላችሁ፡፡
ሠናይ የዕረፍት ቀን ይሁንላችሁ ፡፡
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ተከብራ ትኑር
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
@Simetin_Begitim
#ላ’ንዲት የገጠር ሴት

ስትፈጭ የኖረች ሴት፣
መጁ በመጠኗ፣ ወፍጮውም በልኳ፣
ጓያ ትፈጫለች
ጓያ ሽሮ ሲሆን ያበቃል ታሪኳ !!

አስባው አታውቅም…
ወደ ኦናው ምድር ለምን እንደመጣች፣
ከ’ለታት አንድ ቀን፣ ከና’ቷ ሆድ ወጣች፣
ከ’ለታት አንድ ቀን፣ ጡት አጎጠጎጠች፣
ከ’ለታት አንድ ቀን፣ ለባሏ ተሰጠች……

ተዚያን ቀን ጀምራ፣
ተዚያን ቀን ጀምሮ፣
ድንግል ድንጋይ ወቅራ፣
ትፈጫለች ሽሮ……

አታውቅም፣
ማን እንደሚባሉ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣
አታውቅም፣
ሹማምንት በ’ሷ ስም፣ ምን እንደሚሠሩ፣
አነሳኹት ‘ንጂ፣ እኔም ለነገሩ፣
ፖለቲካ ጥበብ ራስን ማራቀቅ፣
ምን ይጠቅማትና ጓያዋን ለማድቀቅ

ከቶ ማንም የለ, አበባ ‘ሚሰጣት፣
ከቶ ማንም የለ፣ ከተማ ‘ሚያወጣት፣
ከቶ ማንም የለ ፣ በዳንኪራ መላ፣ ወገቧን የሚያቅፋት፣
ልፋቷም፣ ዕረፍቷም፣
ወደዚህ መጅ መሳብ
ወደዚያ መጅ መግፋት……
እንደ ዓባይ ፏፏቴ፣
ሽህ ዓመት ቢንጣለል፣
ቢጎርፍም ዱቄቱ፣
እንደ ሲኦል ወለል፣ ጫፍ የለውም ቋቱ!

ከዘመናት ባንዱ
መስተዋት ፊት ቆማ፣ በተወለወለው፣
ራሷን ለማየት፣
ከጸጉራ ላይ ያለው
ዱቄት ይኹን ሽበት ሲያቅታት መለየት፣
ያኔ ይገባታል
የተሰጣት ዕጣ፣
ከማድቀቅ ቀጥሎ፣ መድቀቅ እንዲመጣ…

የመጅ አጋፋፏ - አምሳለ ሲሲፈስ፣
ከቋት ሥስት እንጅ፣ ሢሳይ አይታፈስ፣
ትቢያ ‘ሚተነብይ ዱቄት በዙሪያዋ፣
ከባርኔጣ አይሰፋም፣ የኑሮ ጣሪያዋ፣
"ስትፈጭ የኖረች ሴት"
ይህ ነው መጠሪያዋ!

© በእውቀቱ ስዩም
@Simetin_Begitim
ለፈገግታ
😂😂😂😂
©ዝንቅ
#ቡና_አማረኝ_ብትይ ...

ደክሞኝ ቢሆን እንኳን
መች እኔ ሰንፋለሁ
ብቻ አንቺ ከቆላሽ
ለመውቀጡ አለሁ

🗣😂😂

@Simetin_Begitim
አገኘውሽ😂😂😂
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
አንቺ ስትቀሪ
የትላንቱ ሣቄ እንኳ
ታሪክ ሆኖ ቀረ፣
አንቺ ስትቀሪ
ሁሉም ተቀየረ፣
እኔነቴ ጠፍቶ
ባዲስ ተዋቀረ፣
ደሣሣው ቤት እንኳ
ሆነ እንዳል ነበረ፣
አንቺ ስትሄጂ
ብቻ ምን አለፋሽ፣
የነበረው ፈርሶ
ሁሉም ተቀይሮ፣
ኦና ሁኖልሻል
ተደሠች የኔ ኑሮ፡፡

😭😭😭😭😭
ሀይለ መለኮት
27/5/11
@Simetin_Begitim
ለላይኛው መልስ
(ከመዓዛ ተበጀ ለሀይለመለኮት)

የኔ መቅረት ሳይሆን
ሳቅህ ቢያሳስብሕ
የኖረው መፍረሱ ያለው
መቀየሩ ቢሆንም ጥያቄሕ
ባለፈ ነገር ላይ
አልቦ ትርጉም ላይኖር
የብሉይ አዝመራ
የሀዲስም መከር ካንተ ዘንድ ባይኖር
ሁሌም ስትጎተት
ሁሌም ቀስቅሱኝ ባይ
ውሀ ብትቸልስ የሞቀው አልጋሕ ላይ
ብርዱ ቢበርደኝ
ዘልቆ እስከ አጥንቴ
ብቸኝነት ገብቶ ዘልቆ ከጅማቴ
ትቼው የወጣሁት
ኦና ያረከውን ቤት
እቃ ረስቼ ነው
ለቀጣዩ ቤትሕ
እሳት መማገጃ
ለአዲሱዋ ጎጆሕ
ለብርዱ ማብረጃ
ክብሪቴን ጥያለው
በትዝታሕ ውስጥ
ፈልገህ አግኝተሕ
ምናል ብትለወጥ፡፡
@Simetin_Begitim
Forwarded from Deleted Account
https://t.me/joinchat/JBksVRXVfXG_wxJ9-eCy1A

ምርጥ እና ለየት ያለ አዲስ Group አንድ አንቺ
ተቀላቀሉን አን አንቺ አንድ ሐሣብ አንስተን እንወያይበታለን፡፡
No ስድብ
No ዘረኝነት

100 Add ለሚያደርጉ admin ysetal
መልስ 2 ከ Helen Tsegaye
........----------..........
መቅረቴን አስበህ
መሄዴን ብቻ አዉቀህ ጥፋተኛ አረከኝ
መቅረቴን አስበህ አለመመለሴን
ያንተን ስሜት ብቻ ጉዳትህን ነገርከኝ
ኑሮዬንና አንተን ትቼ የሄድኩ ዕለት
ዘግቼ ስወጣ ከዉጭ ቆልፌዉ እንደዉ እንደዘበት
እንዴት ተሄደልሽ? ምን ተሰምቶሽ ይሆን? ብለህ መች ጠየከኝ?
የአይኖቼን እንባ, የልሂድ አልሂድ የአዕምሮ ሙግቴን መቼ ተረዳኸኝ?
እንኳን ትቼው ልቀር ለአንድ አፍታ ወጥቼ የማላምነው ቤቴን
አስችሎ ያስቀረኝ,አርቆ ያቆየኝ ምን ብሆን እንደሆን እርም ያስባለኝ ደጄን
እስኪ አንዴ ጠይቀኝ ምንስ ቢያነሳሳኝ,ምን ቢከፋኝ እንደሁ እወቅ ምክንያቴን
ምን ተሰማሽ በለኝ??
አንተን ትቼ ስሄድ
አካልህ ሲርቀኝ
ሳቅህ ሲናፍቀኝ
ፍቅርህ ውል ሲለኝ
ጎጇችን ሲጠራኝ
ምን ተሰማሽ በለኝ...
ህመምክን ስትነግረኝ
እኔን እንደ-ደላኝ አርገህ አታስበኝ
ደጋግመህ ጠይቀኝ
ምን እንደጎደለኝ
ምንን እንዳጣሁኝ.....
ሄለን ፀጋዬ
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
መልስ 3
ሀይለ መለኮት

ብሉይን ከሀዲስ
የአንድዬን ቃሉን ጠቅሰሽ፣
ጥፋቴን ለማጉላት
የአዞ እንባ አንብተሽ፣
ባዶ ቤት ትተሽኝ
ጨለማን አስታቅፈሽ፣
የገነባነውን ንደሽ
የሞላነውን አጉድለሽ፣
ከሄድሽ በዋላ
ለቀጣዩ ቤትህ
ላስተምርህ ነው ፣
ለብቻ የተውኩህ
እንድትለወጥ ነው
ትዝታ ያስታቀፍኩህ,፣
ብትይ ማን ሊሠማሽ
በብሉይ በሀዲስ
ቃሉ እንኳ የሚለው
ሸሽታችሁ አፍርሱ
ሣይሆን፣
ችላችሁ ገንቡ ነው፡፡

@Simetin_Begitim