ኢትዮጵያዊ ወጎች #Ethiopian
1.34K subscribers
314 photos
3 videos
18 files
50 links
Download Telegram
ለፈገግታ 😂😂😂😂😂

ሠናይ ቅዳሜ ሠናይ ውሎ
Forwarded from Debonairs Pizza Official (King T'Chala) via @like
ተቀበል እስኪ

በባሌም በቦሌ ይሸጣል እንጀራ፣
የዘመኑ ወዳጅ አይበቃም ለአደራ፡፡

Credit - ሀይለ መለኮት

@ZiniQ ዝንቅ ይናገራል
Forwarded from Debonairs Pizza Official (Mr. Nobody) via @like
ተቀበል እስኪ

ስልኬን ያስወደደኝ ከ ደብተሬ በልጦ
ስለመሠጠኝ ነዉ በ ደም ስሬ ገብቶ
የዝንቅን ነገር እንዴት አወራለዉ
ባነበብኩት ቁጥር ሁሌ እስቃለው
😂😁😁🤣😂😅👏👏👏👏

Credit - Bamlak

አኸይ ዘመድዬ 👏👏👏

@ZiniQ ዝንቅ በማሲንቆ
His majesty imperial Haile silase
የቀዳማዊ ሀይለሥላሤ ሀውልት በመሠረቱት የAfrica አንድነትጠያሁኑ የአፍሪካ ህብረት ቅጥር ግቢ ውስጥ ዛሬ ይመረቃል ፡፡
የካቲት 3 የአፄ ሀይለስላሴ ሀውልት በይፋ ተመረቀ
//ላጣህ አቅም አጣሁ//

ዓለማዊ ልቤ ለበሰልህ ዳባ ምናኔ ተመኘ
በናቴ ቀብር ላይ የጠፋብኝ እንባ ፊቴ ላይ ተገኘ
ላጣህ አቅም አጣሁ፤

የሳምሶንን ገድል
ያላዛርን እድል
ያቡየን ተአምር
ተቀብዬ ነበር ቄስ እንዳስተማረኝ
አንተን አጣሁ ብየ ማመኑ ቸገረኝ

ክረምቱ ጨከነ
ጨላለመ ጋራው
በረዶና ጭፍራው
ከዋሻቸው ወጡ
ዛፎች ተመለጡ
ከምልአት ጎደሉ
ላባቸውን ያጡ
አሞሮች መሰሉ፤

ልረሳህ አልቻልኩም ልረሳህ እልና
ፊትህን አትመህ በየብስ በደመና
ከንፈርህ ያውና
ፈገግታህ ያውና
ውብ ዓይንህ ያውና ።

በዕውቀቱ ሥዩም

@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
ሠላም ለኢትዮጵያ 🇪🇹
ሠላም ለህዝቦቿ 🇪🇹
ሠለም ለምድሪቷ 🌍
ሠላም ለሠው ዘር በሙሉ🕊


መልካም እና ሸጋ የሥራ ቀን ተመኘንላችሁ
@Simetin_Begitim
<<በላይ በቀለ ወያ>>
ሥራ በሌለበት
ሥለ ሥራ ቋንቋ ፣ የሚነታረኩ
የትውልድ ልብ ላይ
ቂምን ለመጋገር ፣ ጥላቻ ሚያቦኩ
በነፃነት ምድር
ነፃ አውጪ ነን ብለው ፣ ባርነት ሚሰብኩ
ትውልዶችን ፈጥሮ ፣ ዝም ሲል ፈጣሪው
"ትናገር አደዋ"
እያልሽ በድፍረት ፣ ምታንጎራጉሪው
ምን ነክቶሽ ነው እቴ?
።።።
ከኔ ቋንቋ በቀር ፣ ለማይናገሩ
መግባባት አይኖርም ፣ መስማማት ኢንጅሩ
ገለመሌ እያለ
ቋንቋ ተከፋፍሎ ፣ ሲፎክር ሀገሩ
ሀገር መንደር ሲሆን ፣ ውቅያኖሱ ኩሬ
አንቺ ባለማወቅ
"ትናገር አደዋ ፣ ትናገር ሀገሬ"
ብለሽ የምትዘፍኚው
ወይ ደሞ በድፍረት ምታቀነቅኚው
ምን ነክቶሽ ነው እቴ?
።።።
አዋቂ ነኝ ባዮች
ፍቅርን አቀጭጨው ፣ ጥላቻን ሲያሰቡ
ተማሪ ነን ባዮች
"ቋንቋ መግባቢያ ነው "
በሚል አስተምሮት ፣ ብለው አልግባቡ
ትናገር አደዋ
ብለሽ የምትዘፍኚው ፣ መምህራቸውን ለሚደበደቡ
ምን ሆነሻል እቴ?
።።።
ለብዙ ሺህ ዘመን
እጇን ወደ አምላኳ ፣
ዘርግታ ስትኖር ፣ ሰርቀዋት ፀሎቷን
የቆጡን ለማውረድ ፣ ጥላ የብብቷን
የፉክክር ሀገር
የሚዘጋት አጥቶ ፣ እያደረች ክፍቷን
ሌባና ቀማኛ ፣ ለጉድ ተንሰራፍቶ
ዘረኛ መምህር
የቤት ስራ ሲሰጥ ፣ የሀገር ስራን ትቶ
ፍቅር ያግባባቸው
ያያት ቅድም አያቶች ፣ ታሪክን አንስቶ
ቋንቋ ላያግባባን
እውነት እየሰቀልን ፣ ለምንፈታ በርባን
ትናገር አደዋ
የሚል አጉል ቅኔ ፣ ከምትደረድሪ
አደዋ ዝም ብላ ፣ አንቺ ተናገሪ።
አለበለዚያ ግን
ብሔር ተከፋፍሎ ፣ ለሚጣላ ሀገር
ትናገር አደዋ
ትናገር ሀገሬ ፣ የምትይው ነገር
ለእሳት ልጅ አመዶች ፣ ነገር ነው ሚጭረው
ልናገር ብትልስ
ቆይ በማን ቋንቋ ነው ፣ የምትናገረው?
ራስሽ ተናገሪ።
@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
ለፈገግታ😂😂😂
Join and share
@Simetin_Begitim
🌹🌹ሳብድ ግን ዝም በይኝ📝

..........................

ብዬሽ ነበር የኔ
አንቺ እየሳቅሽ እያለቀስኩ እኔ
ሳብድ ዝም በይኝ
በበርሽ ስገባ በመስኮት ወተሻል
አንቺን ስጠብቅሽ አንቺ ግን ቀርተሻል

እኔማ

ፍቅር ሳይኖረኝ ስለ ፍቅር ዘፍኛለሁ
ተስፋ ሳይኖረኝ ስለ ተስፋ ገጥሜያለሁ
ሳላገኝ ስለ ማግኘት ጽፌያለሁ
አንቺ ሳታስቢኝ ስለ አንቺ አስቤያለሁ

እናማ

ድንገት ካገኘሺኝ መንገድ ላይ አብጄ
ባላየ እለፊኝ ግድ የለም ወዳጄ
ምንም ቅር እንዳይልሽ በሰራሺው ስራ
ብቻ ዝም በይኝ ሳብድልሽ አደራ።

🙉Via ፦ቃረማ
♥️Share ለወዳጅዎ

@endenaendena
@endenaendena
Share it share it
@Simetin_Begitim
@Abebe Haregewoin
የዩጎዝላቪያው አርቲስት ሳቫ ቦትዛሪስና የጃንሆይ ሀውልት።

@Simetin_Begitim
የካቲት 12 በታሪክ ሲታወስ🇪🇹

፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
©Eyob Zeleke
ቂም- ባንይዝም-አንረሳውም!!!!
የየካቲት 12 ሰማእታት ሲታወሱ
# ኢዮብ ዘለቀ
ምስሉ የሚያሳየን በ 1929 ዓ.ም በስደት ለንደን ላይ በየካቲት
ጭፍጫፋ ያለቁትን ኢትጲያውያን ስማዕታትን ለማሰብ በተዘጋጀ
አንድ ዝግጅት ላይ ብላቴን ጌታ ህሩይ ወልደስላሴ ፣ሀኪም
ወርቅነህ ፣ልዑል ራስ ካሣ ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ በጋራ
የተነሱትን ፎቶ ነው።
በነገራችን ላይ እነዚህ አራቱም ታላላቅ ሰዎች ልጆቻቸውን በግፍ
አጥተዋል ።
1. ብላቴን ጌታ ህሩይ ወልደስላሴ.. .
ፈቃደ ስላሴ ህሩይ የተባለው ልጃቸው ከ የካቲት 12 ጥቃት ጋር
በተያያዘ በፋሺስቶች ብዙ ስቃይ ደርሶበት ተገድሏል ፡፡
ሌላዋ የብላቴን ጌታ ህሩይ ወልደስላሴ ልጅ ላቀች ህሩይ
በተለያዩ ግንባሮች በመዘዋወር ለአርበኛች ስንቅ ታቀብል ነበር ፤
ሁላም ሱሉልታ አካባቢ በፈሺስቶች ተገላለች ።
2.ሀኪም ወርቅነህ.. ..
.ቢኒያምና እና ዮሴፍ የተባሉት ሁለቱም የአውሮፓን የዘመናዊ
ትምህርትን የቀሰሙ ፤ ከየካቲት ጥቃት ጋር በተያያዘ በፋሺስቶች
ብዙ ድብደባ ከደርሶባቸው በሁዋላ በጥይት ተገድለዋል።
3. የልዑል ራስ ካሣ ልጆች.. ...
ደጃዝማች ወንደወሰን ፣ደጃዝማች አበራ ፣ደጃዝማች አስፋ
ወሰን.. ..ሶስቱንም ልጆቻውቸን ፋሺስቶች ፈጅተዋቸዋል
/ከየካቲት ጥቃት ጋር በተያያዘ ባይሆንም /
4. የግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ልጅ ልጅ ልዕልት ሮማን
ወርቅ በኢጣሊያ ሀገር በእስር ቤት ህይወቷ አልፏል

፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
የአራቱም የኢትዮጵያ በለውለታዎች ምስል 👇👇👇👇

ኢንዲ ለሀገራቸው የልጆቻቸውን ስጋና ደም ብሎም እራሣቸውን የሠጡትን የዘመናዊዋን ኢትዮጵያ አባቶች አለመዘከር ከንቱነት ነው፡፡

@Simetin_Begitim
©Dagmawi Dagmawi
የእኔ ቫላንታይን እኒህ ናቸው። እኔ በነፃነት እንድኖር በአደባባይ
በጥይት ተደብድበው የወደቁ... በደማቸው ነፃነትን
ያወረሱኝ በሞታቸው ፍቅርን ያሰተማሩኝ! ቫላንታይን የሚባል
ነገር ካለ ከአቡነ ጴጥሮስ ውጪ ቫላንታይን የሚባል ነገር
አላውቅም!

@Simetin_Begitim
ሀገሬ ብዙ ለነፃነት ሲሉ ለህዝብ ፍቅር ሲሉ የቆሠሉ የደሙ ብዙ ጀግኖች አሏት ስለ እነርሱ ባወቅነው በገኘነው መጠን ሁሌም እንሰብካለን ፡፡ እኛ በፍቅር ስም ሴሰኝነትን ለወጣቶች አንሠብክም ፡፡ ፍቅር እንደሆነ ሁሉም ቀን የእርሱ ነው ፡፡

የኛን ውድ ታሪክ ትተን በነጮች ታሪክ አንታሠርም፡፡

ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ተከብራ ትኑር፡፡

🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
@Simetin_Begitim
ለፈገግታ😂😂😂
የቀኑ አስቂኝ Post

@Simetin_Begitim
ኢትዮጵያዊ ወጎች #Ethiopian
ግጥሞች በጀማሪና በተዋቂ ገጣሚያን
አጫጭር ወጎች በጀማሪና ተዋዊ ፀሐፊያን
የዕለቱ መልዕክቶች አነቃቂ ፅሁፎች
ከSurprise gift ጋር

ሁሉን በአንድ ላይ በአንድ ቦታ በ ኢትዮጵያዊ ወጎች ያገኛሉ ፡፡

ወጋችን ኢትዮጵያ ብቻ ናት

t.me/Simetin_Begitim