ኢትዮጵያዊ ወጎች #Ethiopian
1.45K subscribers
314 photos
3 videos
18 files
50 links
Download Telegram
ለፈገግታ😂😂😂

በጣም አስቀያሚ ነህ
ማግኔት ብትውጥ እንኳን አትስበኝም አለችኝ 😂😭
ልክ ነሽኮ ማግኔት ዱቄት አይስብም 😜
ምርጥ 10(Top 10) የተሠኘ በአለማችን ብሎም በሀገራችን የተከናወኑ የመዝናኛ የፖለቲካ እንዲሁም ሳይንሳዊ ወሬዎችን አጠር ባሉ ቃላት እጥር ምጥን አርገን አዘጋጅተን ለእናንተ ለወድ ቤተሰቦቻችን ለማቅረብ ዝግጅት እያደረግን እንገኛለን ፡፡ ዝም ብለን ከምናቀርብ በትንሹ 50 ሰው ያክል ሀሣባችንን ከደገፈልን በሳምን 3 ቀን የምናቀርብ ይሆናል ፡፡ ስለዚህ ይቅረብ👍 አይቅረብ👎

በዛውም ሀሳብ አስተያየት ከለዎት ወይም አድሚን ወስደው ከኛ ጋር መስራት ከፈለጉ በ @EthiopianFirst_bot ይናግሩን ፡፡

ያለውን እውቀት ትንሽ ይሁን መካፈል ትልቅነት ነው የሀገራችን ሰውም እንዲህ ይላል የጋን ውስጥ መብራት አትሁን ፡፡
እንማማር ያለንን እናካፍል ኢትዮጵያዊነት ማለት ይህ ነው ፡፡

መልካም ጊዜ
የዛሬ ጥያቄዎች 🔥🔥🔥🔥
👇👇👇👇👇👇👇👇👇

1) የpop ንጉስ በመባል የሚታወቀው እውቁ ጥቁር አሜሪካዊ አቀንቃኝ ማን ይባላል ?

2) በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ ውስጥ የማይረሳ የራሳቸውን አሻራ ከኖሩ ሰዎች መካከል ትልቁን ድርሻ የሚይዙ አንድ አርመናዊ ሰው አሉ ስማቸው ማን ይባላል ?

3) ባሳለፍነው ሳምንት አንዲት አውሮፓዊት ሀገር በcovid-19 ምክንያት የቆመችውን ሊግ ድጋሜ ጀምራለች ይች ሀገር ማን ናት ሊጓስ ምን ይባላል ?

4) አንዲት ደግ ሴት የብዙ ኢትዮጵያውያን ሴቶችን ከሚሰቃዮበት የፌስቱላ ህመም በራሷ ጥረት ለብዙ አመታት ስትታደግ እኔ ሳትታክት ስታገለግል ከርማ በ2012 ዓ.ም ከዚህ አለም በሞት አተናታል ይህቺ እንስት ማን ናት?

5) Oromo - Geda
Sidama- Luwa
Gedeo-???????


Bonus ***______________

* Just we need your participation participate?

መልሱን በ @EthiopianFirst_bot ይላኩልን
ምንም ተሳታፊ አላገኘንም 😭😭😭😭😭
እስካሁን አንድ ተሳታፊ ነዉ ያገኘነው😭😭😭😭
We miss u guys participate😢😢😢
እነ #Endash , #Biruk Girma , #Ame , #Emuye , #whocares ,#jobbir Galanna ,#menen የዘወትር ተሳታፊዎቻችን ዛሬ ጠፍታችዋል😢😢😢 የት ናችሁ
ኢትዮጵያዊ ወጎች #Ethiopian
የዛሬ ጥያቄዎች 🔥🔥🔥🔥 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 1) የpop ንጉስ በመባል የሚታወቀው እውቁ ጥቁር አሜሪካዊ አቀንቃኝ ማን ይባላል ? 2) በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ ውስጥ የማይረሳ የራሳቸውን አሻራ ከኖሩ ሰዎች መካከል ትልቁን ድርሻ የሚይዙ አንድ አርመናዊ ሰው አሉ ስማቸው ማን ይባላል ? 3) ባሳለፍነው ሳምንት አንዲት አውሮፓዊት ሀገር በcovid-19 ምክንያት የቆመችውን ሊግ ድጋሜ ጀምራለች ይች ሀገር ማን…
የትናንቱ ጥያቄዎች መልስ🔥🔥🔥
👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏
(ብዙ መላሾች ስላላገኘን በትንሹ ከጥቂት ማብራሪያ ጋር መልሱን ጀባ እንላቸዋለን )
1) የpop ንጉስ በመባል ሚታወቀው አፍሮ አሜሪካዊው ማይክል ጃክሰን ነው ፡፡

2) ነርስስ ናርባንዲያን ሲሆን በኢትዮጵያ ዘመናዊ የሙዚቃ ታሪክ ውስጥ የማይነጥፍ አሻራውን አሳድሯል፡፡ በ1959 የኢትዮጵያን ዜግነት አግኝቷል ፡፡ ለኢትዮ-ጃዝ መፈዘርም የአንበሳውን ድርሻ ይይዛል ፡፡

3) ጀርመን ስትሆን የሊጓም መጠርያ ቡንደስሊጋ ይባላል ፡፡

4) ካትሪን ሀምሊን አውስትራሊያዊት ስትሆን ከ60,000 ኢትዮጵያውያን ሴቶችን በፌስቱላ ህመም የሚሠቃዩትን አክማለች፡፡


5) Oromo- ባህላዊ የአስተዳደር ስነስርዓቱ Geda ሲሆን በየ8አመቱ የስልጣን ሽግግር ይኖራል ምርጫውም 9 አባገዳዎች ይመረጣሉ ይህም Salgan ya’ii Borana በመባል ይታወቃል ዘጠኑ የቦረና ተወካዮች እንደማለት አንድ አባ ገዳ ለ8 አመት ብቻ በስልጣን ላይ ይቆያል ፡፡ ካንዱ የገዳ ወደ ሌላኛው የገዳ አስተዳደር የሚደረገው ሽግግር Baallii በመባል ይታወቃል ፡፡

Sidama- Luwa በመባል የሚታወቅ ባህላዊ የአስተዳደር ዘዬ አላቸው ፡፡ በየ8 አመቱ በየእድሜ እርከን ይሸጋገራል ፡፡ በLuwa ውስጥ 5 የሽግግር ደረጃዎች አሉ እነሱም ደራራ፣ ፉላሳ፣ ሂሮቦራ፣ ዋሳሳ እና ሞጊሳ በመባል ይታወቃል ፡፡

Gedeo- ልክ እንደ ኦሮሞው ሁላ ጌዲኦ Geda የሚባል ባህላዊ የአስተዳደር ስነስርዓት ያለው ሲሆን አባ ገዳውም ባሌ በሚባል ስነስርዓት በየ8አመቱ ለተተኪው አባ ገዳ ስልጣኑን ያስረክባል፡፡


እናመሰግናለን አብረውን ስለሆኑ!
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
መላሾች

#Walove 4/5 🥇

#Ame
#Yilugnal Wube
#Nigist t
#Firdewsa
#liwam &
#NeverGiveup
#Tekee man ለተሳትፎአችሁ ሁላችሁንም እናመሠግናለን!!!
#LatinAmerica

የዓለም ጤና ድርጅት /WHO/ ላቲን አሜሪካ አዲሷ የኮሮና ቫይረስ /ኮቪድ-19/ ወረርሽኝ #ማዕከል መሆኗን አሳውቋል - #AFP
Top-10© ምርጥ 10

📩ምርጥ 10ን እንሆ ጀባ እንበላችሁ📩

ምርጥ 10ችን ዛሬ ትኩረቱን የሚያደርገው በኛው በሰው ልጆች ብዛት ከ 1-10 ደረጃን የያዙ ሀገራትን ለመዳስ እንሞክራለን ፡፡ ይህ ቁጥራዊ አሃዝ በmarch 3 2020 እንደ ጊሪጎርያን አቆጣጠር የተወሰደ ነው ፡፡

1) ቻይና- 1,439,323,776
2)ህንድ- 1,380,004,385
3)አሜሪካ - 381,002,651
4)ኢንዶኔዥያ - 273,523,615
5)ፓኪስታን - 220,892,340
6) ብራዚል -212,559,417
7) ናይጄሪያ -206,139,589
8) ባንግላዴሽ -164,689,383
9)ሩሲያ -145,934,462
10) ሜክሲኮ - 128,932,753

👉የተቀረው የዓለም ህዝብ ቁጥር 3,293,613,339 ሲሆን በአጠቃላይ የዓለም ህዝብ ቁጥር ደግሞ 7,796,615,710 ነው ተብሎ ይገመታል ፡፡

Source:- Miniwatts Marketing Group.
WWW.internetworldstats.Com

ለሀሳብ አስተያየት / መረጃ ለመስጠትበ @Haile_melekot Or @EthiopianFirst_bot ይጠቀሙ
🔥🔥🔥🔥👍🔥🔥🔥🔥👏🔥🔥🔥
የዛሬ ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥👇👇👇
1) የጀርመን ዋና ከተማ ማን ናት?
ሀ) በርሊን
ለ) ለንደን
ሐ) አንካራ

2) Pentagon ስንት ማዕዘን አለው?
ሀ)5
ለ)6
ሐ) 7

3) ስንት ሴንቲሜትሮች አሉ በ 1ሜትር ውስጥ?
ሀ) 100
ለ) 150

4) የኤርትራ የስልክ መለያ country code ቁጥር ስንት ነው?
ሀ)+253
ለ)+291
ሐ)+251

5) የየትኛው ሀገር ብሔራዊ መዝሙር ነው እጅግ ረጅሙ?

ሀ) ግሪክ
ለ) ቻይና
ሐ) ቱርክ

መልሱን በ @EthiopianFirst_bot ይላኩልን መልካም ዕድል!!
ይሳተፉ መልካም ምሽት መልካም ዕድል!!!
እንኳን ለ 1441ኛው የኢድ አል ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ! ውድ የቻናላችን የእስልምና እምነት ተከታዮች
በዓሉ የሠላም እና የጤና እንዲሆንላችሁ እንመኛለን ፡፡

የጤና ባለሙያዎችን ምክር በመከተል የኮሮና ቫይረስን እንዲከላከሉ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን።
#We wish you a Happy Eid
°°°°°°°°°°°°°
የሰፈራችን አባቶች የገዙት በሬ አንድ አይን አልነበረውም!
የት ዘምቶ እንደሆነ እንጃ!
እንደ ጭቃ ሹም ታጅቦ መጣ።
አረማመዱ መቼም የጤና አልነበረም። ልክ የሰፈራችን የቆሻሻ
ገንዳ አጠገብ ሲደርስ ደነበረ!
ተፈነጣጠረ!
አባቶቻችን እንደ ዝምብ መንጋ ዝዝዝዝ..ብለው ተበተኑ!
" ያዘው! ያዘው! "
ከወኔ ውጪ ሰውነት የሌላቸው ጋሽ ብሩ ቁልቁል የሚንደረደረውን
በሬ በሩጫ ተከተሉት
...ግን ተሳሳቱ--- ፈጠኑ....በጣም!
በሬው ቀጥ ብሎ ሲቆም ጋሽ ብሩ ፍሬናቸውን በጥሰው እግሩ ስር
እንደ ሊስትሮ.....
በሬው በቀኟ ዐይኑ እንደ መሽኮርመም አለና!
በቀንዱ ዘገናቸው! ( የምሬን ነው )
እንደ ጀላቲ ቀንዱ ጫፍ ላይ ሰክቷቸው ሲታይ የፈረንጅ አጋዘን
ይመስል ነበር።
ዘቅዘቅ ሲሉ፡ ነጯ ኮፍያ ጠብ አለች!
" በህግ አምላክ! "....አሉ አየር ላይ ( ማንን ይሆን? )
በሬው ጋሽ ብሩን አንጠልጥሎ ወደገንዳው ተመለሰና ገንዳው
ውስጥ ጨመራቸው!( አስቀመጣቸው ልበል? )
ተረኛ የሚዘገን ሲፈልግ፡ ሰዉ ተተራመሰ!
ዞሮ ዘሎ ሲመጣ ጋሽ ብሩ ከገንዳው ብቅ አሉ!
አልጋ ስር የተረሳ ጫማ መስለው..
" ኮፍያዬን አላያችሁም? "
" አላየንም "
" ያችኋትናኮ አቀብሉኝማ "
" ሌላ ቀን ይውሰዷት "....በዚያ ላይ
" ቢወጋንስ? "
" እኔ አባታችሁ እንዴት ልውጣ ታዲያ? "
እንዳይወጡ ቆሟል ፊት ለፊት
" ኧረ ጠነባሁ ጎበዝ "
መቼስ ብዙ ስቀናል ያኔ። በስንት መከራ ተሸነፈ!
ታርዶም ጣጠኛ ነበር
የታረደ ቀን ጠዋት ቅርጫው ላይ ጫጫታ ይሰማል
ጨጓራው ተሰረቀ!
ያው ከሮቤል ውጪ መቼም ማንም አይሆንም!
የነሮቢ በር በሃይል ተንኳኳ!...ሮቢ ከፈተ
" ጨጓራውን መልስ! "
" ኧረ ጋሼ! የምን ጨጓራ? "
" ዛሬ ፊኛህን ተሰናበት! ልቆምበት ነው "
" እኔ አላየሁምኮ "
" ምንድነው በመዘፍዘፊያው ያስቀመጥከው "
" የባቢ ሽንት ጨርቅ ነው "
" እያጠብክለት? "
" አዎ "
" በፈርስ ነው የምታለቀልቀው? "

Fikre Ze Bhere Ethiopia
#የመልስሽ #ጥያቄ

#እኔ #ምልሽ
የእንባችን ገንቦ ~ ሳይሰበር በፊት
ይፈስ ነበር አይደል ~ በሳቃችን ግፊት
የተፈጥሮስ ሂደት ~ እንዲህ ሳይጓደል
ከልብ እየሳቁ ~ ማልቀስ ነበር አይደል ?

#እኮ
#እኛ #እኮ #ነን
ሀዘንን በደስታ _ እያነሳን ልንጥል
ስሜታችን ቆርጠን _ ስሌት ልንቀጥል
በአንድ ወገን ስለነው ~የተፈጥሮን መቀስ
በየተራ ሆኗል ~ መሳቅና ማልቀስ
===||===
ከሙሉቀን ሰ•
ለፎቶ የተዋስናቸው የልደት ለስላሳዎች ከኛ በላይ celebrate
ይደረጉ ነበር....
የዘንድሮው ወላጅ፡
" ኧረ ቀስ ልጆች እንዳትደፉት! "
ያኔስ?
" ቀስ! ዋ! እንዳትከፍቱት! በሰንበቱ አትነጅሱኝ".
.....ተመላሽ ነዋ!.....
ሙስጤ በሩን ያንኳኳል ( ባለሱቁ )
ሲከፈት፡
" መልሱንጂ "
" ቆይ አዩ ይምጣ! "....አዩ ፎቶ አንሺ ነው ...የሰፈራችን።
ሙስጤ አምስት ኮካና ምሪንዳ አውሶን፡ የጌቱን ልደት አድምቀን
ልንመልስለት ነበር ውሉ...
" አስር ደቂቃ ብቻ! "
" ወላሂ! ካሁን በኋላ ግን አላውሳችሁም "
***
አንድ ቀን ሃያ ብር ወድቆ አገኘሁ! አቤት ደስታዬ!
ሰው ፈንክቼ ካሳ መክፈል ሁሉ አማረኝ!
ቀጥታ ሙጤ ጋር ሄድኩ
" ሙስጤ እስኪ ሁለት ምሪንዳ ስጠኝ! "....ለራሴ ነውኮ
" ፍቅርሻ ለልደት አውሸዋለሁ! "
.....እርሜን ገንዘብ ብይዝ!?.......
" በቃ ተወው! ዳኜ ጋር እሄዳለሁ " ስለው፡
" ቆይንጂ! ካላመንከኝ ና ይዤህ ልሂድ " ብሎ ወንድሙን
'መጣሁ አደራ' ብሎት አብረን ሄድን
ልደቱ የጩና ነበር። ኮካው አልተከፈተም። አዩ ፎቶ ያነሳል።
" ያውልህ! አንዱን አንስተህ ጠጣ! " አለኝ
......አዝማሪ በሰው ሰርግ ይዳራል ይልሃል ይሄ ነው!....
ተንደርድሬ ብድግ ላደርግ ስል፡ የጩና አባት፡ አንገቴን እንደ
ብርሌ ሲጥ አድርገው፡
" እናትህ ወልዳሃለች ዛሬ! "...አሉኝ
ሙስጤ፡ መጥቶ አረጋጋቸውና
" ገዝቶታል ጋሼ! "
" እና!? "
" ልጠጣ? " አልኩ ጣልቃ ቀብቼ
" ልደቱኮ የጩና ነው! እሷ ሳትጠጣ በሰው ልደት እዚህ
ሊጨልጥ? "
መቼስ የልደቴ ቀን ባልጠጣ የጩና ላይ ይመርብኝንጂ!
ጩና እየተቁለጨለጨች፡ እኔ የሷን ምሪንዳ ፉት እያልኩ
አስቡት!......( መቃብሬ ላይ ትቆማለች? )
በነገራችን ላይ ጨዋታውን አልኩንጂ እኛ ሰፈር ልደታቸውን
የሚያከብሩት ጥቂቶቹ ናቸው
ሶስት ወይም አራት ይሆናሉ። ሁለቱ በቋሚነት የሚያከብሩ
ደምበኞች ሲሆኑ፡ ሌሎቹ ሲኖር የሚደረግላቸው ናቸው።
ታዲያ የኛ የራሳችን ልደት እስኪመስለን እናከብርላቸው ነበር።
የኛን ሳናውቅ የነሱን!
የሆነው ሆኖ ሃያ ብሬን ሆጭ አድርጌ ጩና እና ሌሎቹን
ለለስላሳው ከፍዬ አንበሻበሽኳቸው!
አባቷም ያን ያህል አላወጡ
" ፍቅርሻ! በሰፈሯ ለመጀመሪያ ጊዜ የልደት ኮካ አስከፈተች!
".......ብሏል ሃበሻ!

Fikre Ze bhere Ethiopia
መርዶ
[በዕውቀቱ ሥዩም]
____________
ተምትም አሻግሬ የሚባል ጓደኛ ነበረኝ ። አይ ተምትም አሻግሬ !
ባሰብሁት ቁጥር ሳቄ ዝም ብሎ ይመጣል ።
ተምትም ንግግር በማስረዘም ተወዳዳሪ የለውም ። ለምሳሌ
አብረን አምሸተን ስንለያይ እኔ ''ቻው!'' እለዋለሁ። እሱ ግን
'' ....ደህና አምሸተህ ሌሊቱን በሰላም ታሳልፍ ዘንድ
እመኝልሃለሁ!'' ይላል ።
ቁርስ ልንበላ ስናዝዝ '' ቋንጣ ፍርፍር!'' ብሎ እንዳይገላገል ''
''እስቲ እባክሽ የኔ እመቤት ፣ ሽንኩርት ሳይታይ ፣አንድ ጥሩ የሆነ
ከቋንጣ የተሰራ የእንጀራ ና የልዩ ልዩ ነገሮች ፍርፍር አምጭልኝ
....'' ይላል ።
ተምትም እና እኔ አንድ ቀን የጓደኛችን የደመቀ ባይከዳኝን
ወንድም ሞት ሰማን። መርዶውን ለመናገር የታጨን ሁለታችን
ነበር። ''እኔ ቀስ ብዬ ብነግረው ይሻላል !....አንተ ታስረዝማለህ!''
አልኩት። እሱ ግን የንግግር ሱስ ስላለበት ተቃወመኝ።
''ምን ነካህ!....መርዶ እንዲህ ቀላል ነገር ነውንዴ ?....እኔ ነኝ
በዘዴ ልነግረው የሚገባ ....ይልቅ ራሱን የሳተ እንደሁ አንተ
ትደግፈዋለህ!'' አለኝ ።
ከብዙ ጭቅጭቅ በኃላ እሱ አሸነፈኝ ። በማግስቱ ሌሊት ወደ
ደመቀ ቤት ስንሄድ ''አደራ እንግዲህ እንዳታንዛዛው....ወንድምህ
በመኪና አደጋ ስላረፈ ርምህን አውጣ ! ማለት ብቻ ነው'' አልኩት
።።
እሺ ብሎኝ ገባን።
ደመቀ ከእንቅልፋ ተነስቶ በር ከፈተልን በኃላ {ምነው በደህና?}
አለን ። ምልክት ሳሳየው ተምትም ንግግሩን ለቀቀው ''ውድ
የተከበርከው ወንድማችን ደመቀ ባይከዳኝ....ወንድምህ ከሁለት
ቀናት በፊት እናቱን ለመጠየቅ መኪናውን እየነዳ መውጣቱን
ሳታስታውስ የምትቀር አይመስለኝም....ያን ቀን ከሌሎች ቀን
የከበደ ቀን ነበር ....ሰማዩ ርጉዝ አህያ መስሏል ።ወንድምህ
ምነው ዛሬ ቀፈፈኝ እያለ ለራሱ በመናገር መኪናውን በአባይ
ጎዳና ማሾር ጀመረ ...ጸጥ ያለ መንገድ ነበረ ...ምነው የሆነ
መልአክ ተመለስ ብሎ ሹክ ባለው !...ዋ! .....ጎደሎ ቀን ! ዋ
የተሰበረ ዕድል ....ምንኛ ያሳዝናል! ....በአባይ ሽለቆ ውስጥ
ሲገባ የመኪናውን ፍጥነት አልቀነሰም ፤ እናም ወደ ግራ
እዞራለሁ ሲል መኪናው እንደ ኳስ ነጠረች !... ከዚያም ሙሽራ
ሙሽሪትን እንደሚስም ሁሉ መኪናዋ ባቅራቢያው ካለ ቋጥኝ ጋር
ተሳሳመች....ግው! ጓ!
ወንድምህ ! ያ! ቅን ወንድምህ ከዚህ የጨቀየ ዓለም ወደ
ብርሃናዊውና የማይከስመው ዓለም የተሸጋገረው በዚህ ጊዜ
ነው !'' አለና ትንፋሹን ዋጠ።
ደመቀ ግን '' አልገባኝም !'' ብሎ ወደ እኔ ተመለከተ ።
'' ወንድምህ አርፏል !'' አልኩት በፍጥነት ። እሱም በፍጥነት
ወደቀ ።
#stayHome
#Staysafe
#Fact
ኢትዮጵያ” ማለት በአይሮግሊፊክ አትኦፕቢያ “የበላይኛው
የእውነት አገር” ማለት ነው፡፡
“ሳባ” ማለት “የመንፈስ ልጅ” ማለት ነው፡፡
“ጋላ” ማለት ለቧልት እንደሚባለው “ሃይማኖት የሌለው” ማለት
ሳሆን ካራ “የእግዚአብሔር ፀሐይ ፋና” እንደማለት ነው፡፡
“ዐማራ” ማለት በሻዕቢያ ቧልት እንደተባለው “ወፈፌ” ወይም
“ፉዞ” ማለት ሳይሆን “ዓም ሀራ” ወይም “የካም ሰራዊት ፀሐይ”
እንደማለት ነው፡፡
“ሃማ ሴን” “የካምን ወገን ዝርያ” እንደማለት ነው፡፡
“አጋሜ” ማለት በቧልት እንደሚባለው “ለማኝ” ወይም “ቆሻሻ”
ማለት ሳይሆን “አጋ ሃሜ” “ታላቅ የካም ወገን” እንደማለት ነው፡፡
“እግዚአብሔር” ማለት “እግ-ዘ-አብሔር” “ታላቁ የምድር አባት”
ማለት መሆኑን፣ “ጋዳ” ማለት “ካ አዳ” “የእግዚአብሄር ሥርዓት”
ማለት ነው ፡፡
ፀጋዬ ገ/መድህን
ምንጭ፡- ጢቢያ መፅሄት ቅጽ 5፣ ቁጥር 11፣ 1990
#ከFb የተመነተፈ
መልካም ቀን
ʟօʋɛʀs ɛʍքɨʀɛ :
"እኔ_ደግሞ …."
(አሌክስ አብርሃም)

ምንድነው እንደዚህ - ፊቴን በብረሃን
ከንፈሬን በውብ ሳቅ - የሚያጥለቀልቀው፣
ምንድነው ከልቤ - ኮለል ያለ ሰላም - በጧት የሚፈልቀው?።
እያልኩ አስባለሁ ……

እኔ ደግሞ …..
ምንድነው ሰው ሁሉ- ነጫጭ ክንፍ አብቅሎ - መ,ላክ የመሰለው፣
ምንስ ነው ሰማዩ - እንዲህ ተጠቅልሎ -
በጀ የምይዘው - መሃረም ያከለው።

ኧረ ምን ታምር ነው - መሬት መዞር ትታ - በፎይታ ያቆማት፣
ምንድነው ጨረቃን - ከሰማይ አወርዶ - ምድር -ያሳረፋት?።
እያልኩ አስባለሁ

እኔ ደግሞ …..
የጠሉኝን ሁሉ - ድንገት የመውደዴ፣
መሬቱን ለቅቄ - ባየር ላይ መንጎዴ።

ምንድነው ሚስጥሩ-ቆይ ውስጤን ምን ነካው፣
አለም እንዲህ ጠቦ - በርምጃ ሚለካው።

ውቂያኖስ በፍኘ - ተጨልፎ የሚደርቅ፣
ተራራው በክንዴ - ተጎሽሞ ሚደቅ።

ማነው በመንገዴ - ሳልፍ እልል የሚለው አበባ ነስንሶ፣
ማነው ግማሽ ልቤን - ሸርፎ የወሰደው -በትልቁ ቆርሶ?።
ኧረ ምን ታምር ነው ?
እያልኩ አስባለሁ

እኔ ደግሞ …..
መንገዳኛው ሁሉ - የተከፋ ፊቱን -
በማን ተነጠቀ፣
ከጨፍጋጋ ፊቶች - የዚህ አይነት ብርሃን - እንዴት ፈነጠቀ።

ሚሊየን ህፃናት - ቀልብ በሚነሳ -
ስርቅርቅ ድምፃቸው፣
የት ቢዘምሩ ነው - ልቤ ሚሰማቸው።

በምን ተአምር ነው - ዛፎች የሚያረግዱት፣
በምን ጉድ አስማት ነው - የሰማይ ከዋክብት
ቁልቁል የሚበሩት።
እያልኩ አስባለሁ ….

እኔ ደግሞ ….
ቤሳ ቤስቲን ፍራንክ - ኪሴ ሳይጨመር፣
አመት የለበስኩት - ልብሴ ሳይቀየር።

የዘወትር ጉርሴ - ጣሙ ሳይነካ፣
እኔነት እኔ ውስጥ - ተቀይሯል ለካ።

እኮ በምን ምክንያት - እኔ ተቀየርኩኝ፣
እንዴት እኔ ነኝ ስል - እኔ ሌላ ሆንኩኝ።
እያልኩ አስባለሁ ……..
ለ ካ ስ ……………………..አፍቅሬሽ ነው!!!
#StayHome
#StaySafe
ሰሞኑን በአንዳንድ የግል ችግር ምክንያት ጥያቄዎችን እና መረጃዎችን አዘጋጅተን ማቅረቦ አልቻልንም ለዚህም ይቅርታ እንጠይቃለን በቅርቡ ከSurprise Gift ጋር እንመለሳለን እስከዛው አብሮነትዎ አይለየን ፡፡ መልካም ጊዜ!!

#Share these link to your friends
https://t.me/joinchat/AAAAAE1DeWswU2W9sUd-rA