ኢትዮጵያዊ ወጎች #Ethiopian
1.36K subscribers
314 photos
3 videos
18 files
50 links
Download Telegram
ሀገራችን አሁንም ጀግኖች አሏት!

( በዶ/ር ኤልያስ ገብሩ )

መሐመድ አል አሩሲ ይባላል። አረብኛና እንግሊዘኛ ቋንቋዎችን አቀላጥፎ ይናገራል። እንደ አል-ጀዚራ ባሉ ሚዲያዎች ላይ ቀርቦ አገሩን መክቷል። ዐባይ ላይ ኢትዮጵያ መወሰን አትችልም የሚሉ የግብጽ ተከራካሪዎችን አፍ አዘግቷል። የኛን እውነት በዓለም አቀፍ ሚዲያዎች አሳይቷል።

ረመዳንን እየጾመ እንኳን እናት አገሩን ወክሎ ለመሟገት ወደ ኋላ አላለም። ለሚሰራው ድንቅ ሥራ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ደውለው ምስጋናቸውን አድርሰውታል። ቆፍጣና፣ አንደበተ ርቱዕ፣ የጀግናው ቢላል የልጅ ልጅ - በርታልን።
ይህቺ ሀገር ዘርፈ ብዙ ጀግኖች ያስፈልጓታል፤ አሏትም። ግድባችንን ሠርተን የናቁንን ሁሉ እንድናሳፍር እሱ ይርዳን።

#የኔትውልድ
#ItIsMyDam
©tikvahethmagazine
R u ready for today's competition?
ለዛሬው ጥያቄዎች ዝግጁ ናችሁ ?
sport , ታሪክ , geography እና ሌሎችም አሉን
የዛሬ ቀለል ያሉ ጥያቄዎች🔥🔥🔥
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
1) በአፍሪካ ብሎም በኢትዮጵያ ብቸኛው የአንድነት ፖርክ መች ነው የተመረቀው ?
ሀ) ጥቅምት 29 2012 ዓ.ም
ለ) መስከረም 29 2011 ዓ.ም
ሐ) መስከረም 29 2012 ዓ.ም

2) ቻምፒየንስ ሊግን በብዛት ያነሳው ክለብ የየት ሀገር ነው ?

ሀ) እንግሊዝ
ለ) ጀርመን
ሐ) ስፔን

3) የአለማችን ትንሿ ሀገር ማን ናት?

ሀ) ቫቲካን ሲቲ
ለ) ኤርትራ
ሐ) ሰለሞን አይስላንድ

4) ብዙ ጓል ያለው ከ ሁለቱ ማን ነው?

ሀ) ሊዮኔል መሲ
ለ) ክርስቲያኖ ሮናልዶ

5) በሀገራችን ብዛት ያለው ታናጋሪዎች ያለው ቋንቋ የቱ ነው )

ሀ) አማርኛ
ለ) ኦሮምኛ
ሐ) ትግርኛ

Bonus Question just Say true or false .
#There are McDonald’s one every continent
except one.

መልካም ዕድል!!

መልሱን እንደተለመደው በ @EthiopianFirst_bot ያድርሱን!!
ደስ የሚልና ውብ ምሽት ተመኘንላችሁ ተሳተፉ ወዳጅዎን ይጋብዙ መልካም ዕድል
ዛሬም እንደተለመደው አዳዲስ ተሳታፊዎች እያገኘን ነው ይሳተፉ ይዝናኑ መልካም ምሽት
የሁለተኛ ክፍል በሮች
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
" ይሄ ክፍል መረጨት አለበት!....ሰላቢ በዛ! "
" ምነው መምህር? "
" ለሽንት ወጥቼ ስመለስ ጭር ይልብኛል "
ከዋናው መንገድ የሚዋሰነው የክፍላችን ግድግዳ ቆርቆሮ ነበር።
ከኋላ ጥግ ያለችውን ቆርቆሮ፡ ሚስማሮቿን አርቆ አሳቢ
ፎራፊዎች አላልተውት በ shortcut ይፎርፋሉ!
" 4 X 3 = ? ስለው ያለቀሰው ልጅ የት ሄደ? "
" አላየነውም ቲቸር "
" ቅድም ሲነፋረቅኮ ቁጥሮቹ የሞቱበት መስሎኝ "
እንስቃለን
" አስታወሳችሁት? "
" አዎ "
" አሁን ወጣ ከማለቴ፡ የት ሄደ? "
" አላየነውም "
" ተባይ ሁላ!! "
ያሬዶ እሳቸው ወጣ ሲሉ፡ ሚስማር የሚያላላ ኮሚቴ ተዋቅሮለት፡
ሾልኮ ሄዷል!
*
በጣም የሚደነግጡት ግን መንገደኞች ነበሩ!
" ሰሃሊትነ!..." አሉ አንዲት ጠና ያሉ ሴት፡ ማሞ ድንገት
ፍልቅ ሲልባቸው ከክፍሉ።
" ምነው ልጄ? በስኳሬ ላይ? ".......
ማሞ እድለ ቢስ ነበር። የደረጃ ተማሪ ቢሆንም፡ አባቱ ግን
ውጤቱን አይቀበሉትም ነበር
ሰኔ ሰላሳ ማሞ ሲገረፍ፡-
" እንዴት 2 ብቻ ታመጣለህ!? "....እየዠለጡ
" አባዬ ላስረዳህ ቆይ! "
" መምህርህን አስረዳ! "
" ኧረ አባዬ! "
" ዝምበል! የአጉኔ ልጅ 71 ሲያመጣ አንተ ሁለት? "
" ኧረ ደረጃችን ነው አባዬ? "
" የምን ደረጃ? "
" እኔ ሁለተኛ ነው የወጣሁትኮ! "
" ምን ያንቀዠቅዥሃል? ረጋ ብትል 71ዱን ትዘግን ነበር! "
**
አንድ ቀን ግን ያቺ መፎረፊያ ተባነነች
ደምሴን ለመስወጣት በተደረገው ኦፕሬሽን የላሉት ሚስማሮች
ወልቀው ጠፉ!..ዝም ብለን አስደገፍናት!
ቲቸር ግስላ ዳኒን ለመኮርኮም ሲንጠራሩ፡ የውጪው ንፋስ
በሃይል ገፍትሯት አናታቸው ላይ ተኛች!
...ሙሴ የተማራችሁ አስታውሱ!.....
መንገደኞች በተከፈተው በኩል እያሰገጉ ቲቸርን በንቀት እያዩ
" አስተማሪም ይፎርፋል?? "

Fikre Z Bhere Ethiopia

#ሠናይ ቀን ከሙሉ ጤና ጋር ተመኘንላችሁ
#Staysafe
የሙት ሐሳብ ጣዕም(ልዑል ኃይሌ)
'የአባ ሎራ' ሐሳብ
የሮሚዮና ዡሊየት ጣፋጭ ህልም ፈቺ፤
ከክፉ ዕድል አዳኝ
ያ'ሰት ሞት ነሽ አንቺ፤
ድልድይ ነሽ ለሮሚዮ
በፍርደ ገምድል ፍርድ መንገዱ ለጠፋው፤
ይኸው ዕድሜ ላንቺ!...
በቁሙ ያጣውን
የታረደ ፍቅሩን በሞት ፅዋ ሰፋው፤
.
እኔም ባንቺ መላ
ብሞት መች ሊቆጨኝ ደጋግመሽ ግደይኝ፤
የሞት ሐሳብ ሆነሽ
ልትጎጂኝ ተነሺ ዡልየቴ ላይ ጣዪኝ፤
.
እኔም እጓዛለሁ!
አንቺ ባቀናሽው የሙት ቃል ጎዳና፤
ካንቺ ሐሳብ ባሻገር
ቆማ ምትጠብቀኝ ሙት ሴት አለችና፤
.
ግንቦት 12, 2012 ዓ.ም.
#StaySafe
ለመላው የኢትዮጵያ ማህበረሰብ እና ለሲዳማ ህዝብ እንኳን ለሲዳማ ህዝብ የዘመን መለወጫ ባዓል ፊቼ ጨምበላላ በሰላም አደረሳችሁ ፡፡

መልካም በዓል!!
በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ5 ሚሊዮን በላይ ሆነ!

በርካታ ሰው በበሽታው የተያዘባት አገር ኃያሏ አሜሪካ ስትሆን ሩሲያ በሁለተኝነት ትከተላለች፤ ብራዚል ደግሞ ሦስተኛ ደረጃ ላይ ሆና በወረርሽኙ በከፍተኛ ሁኔታ ልትጠቃ እንደምትችል እየተነገረ ነው።

በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ያለባቸው አገራት
1 - 1,551,853 አሜሪካ
2 - 308,705 ሩሲያ
3 - 291,579 ብራዚል
4 - 249,619 ዩናይትድ ኪንግደም
5 - 232,555 ስፔን

Via BBC
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የ12ኛ ክፍል ፈተና ዕጣ ፈንታ!

(በአሃዱ ቴሌቪዥን)

የዚህ ዓመት የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ዕጣ ፈንታ ምን ይሁን፣ ፈተናው በተያዘው ዓመት ይሰጥ ወይስ ይተላለፍ የሚለው ውሳኔ ከፌደራሉ መንግሥት ውሳኔ እየተጠበቀ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ መግለጹን አሐዱ ቴሌቭዥን ዘግቧል።

እንደሥራ ኃላፊዎቹ መረጃ ውሳኔው በ15 ቀናት ውስጥ ይታወቃልም ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው መመሪያ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎቻቸውን እንደቴሌግራም ባሉ የማኅበራዊ ትስስር ገፆች ማስተማር እንዲቀጥሉ ቢልም ስኬታማ ሆኖ አልቀጠለም፡፡

ከዚህም አልፎ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የሰዎች መሰብሰብ መከልከልም ተማሪዎች ቢዘጋጁ እንኳን ፈተናው በምን አግባብ ይሰጣል የሚለውን ምላሽ አልባ አድርጎታል፡፡
የዕለቱ ቀለል ያሉ የናንተን የበዛ ተሣትፎ የሚጠይቅ ጥያቄዎች 🔥🔥🔥🔥
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

1) በ corona virus በዛሬው ቀን WHO ያወጣው መግለጫ ስንት ሚሊየን ሰው በአለም ላይ ተይዟል ይላል?


2) የአለም ዋንጫ ለመጀመርያ ጊዜ ያነሳችው ሀገር ማን ናት ?

3) Corona virus ሳይበግራት ምርጫ ያካደችው የአፍሪካዊት ሀገር ማን ናት?

4) የመጀመሪያዋ ሴት አፍሪካዊት አትሌት የኦሎምፒክ ወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ ማን ናት?

5) የFacebook መስራች ማን ይባላል ?

መልሱን በ @EthiopianFirst_bot ይላኩልን!
መልካም ዕድል ተሳተፉ መልካም ምሽት
ተሳተፊዎቻችን የትናችሁ😢😢😢
ብዙ ተሣታፊ ስላላገኘን እስከ ነገ ከቀኑ 8 ሰአት ድረስ ይሞክሩ ?
ግብዣ
{በዕውቀቱ ሥዩም}
_________________________
እትዬ ፀሐይ ቤት ከተከራየሁ ከሁለት ሳምንት በኃላ የገና ዋዜማ
ሆነ ።
''አንተ ልጅ ብቻ መሆን ጥሩ አደለም ተጎረቤቶችህ ጋር
ተቀላቀል!'' አሉኝ እትዬ ፀሐይ ።
እሺ ብዬ ተከተልኳቸው።
ቤታቸው በእንግዶች ተጨናንቋል። ያስተዋውቁኝ ጀመር ። ''ይሄ
ከግራ ጎንህ ያለው ዶክተር ምትኬ ነው ።
ይሄን ቤት ከተከራየው አራት ዓመት ሆኖታል ። ባሁኑ ጊዜ እጅግ
የተከበረ ሐኪም ከመሆኑም ባሻገር ወደ ውጭ ሀገር አሁንም
አሁንም ይመላለሳል። ውጭ ሀገር ማለት ለእሱ ሶደሬ ሄዶ
እንደመመለስ ነው። ለነገሩ ሶደሬ ብርቅ የሆነባቸው ሰዎች እንዳሉ
ሳላውቅ ቀርቼ አይደለም ። ለምሳሌ አንተ ሶደሬን ታውቃለህ ?''
''አውቀዋለሁ''
''ማወቅማ...ያው በስም ሲጠሩት መስማትህ የት
ይቀራል ?....ሄደህ ታውቃለህ ወይ ማለቴ ነው ?''
''ሄጄ አላውቅም!''
'' እኮ ! ....አየህ ሄድሁ ብትለኝ ማን ወሰደህ ብዬ ላፋጥጥህ
ነበር!!...ይሄ ጎረቤትህ ግን ውጭ ሀገር ይመላለሳል ።
አውሮፕላን ለሱ አንተ የምትመላለስበት 64 ቁጥር አውቶብስ
ማለት ነው ። ታዲያ ሄዶ ሲመለስ በእጅ አንድ ነገር
ሳያንጠለጥልልኝ አይመለስም። መከራየት ማለት ሺህ ብር
ከፍለው በሰው ቤት መፈንጨት ብቻ አለመሆኑን የተረዳሁት በእሱ
ነው እንግዲህ ....'' አሉኝ ።
ዶክተር ምትኬ ራሱን አወዛወዘልኝ። { እኔ ነኝ እወቀኝ እንግዲህ
እንደማለት }
''ይህች ደግሞ !...'' አሉኝ ''ሶፋው ላይ ከፊት ለፊቴ
የተቀመጠችዋን ማለፊያ ሴት በአገጫቸው እየጠቆሙኝ ''ይቺ
ደግሞ በቀኝህ በኩል ያለችው ተከራይ ናት ። ቆንጆ መሆኗ
የማይካድ ቢሆንም እጮኛ ግን አላት ። ለዚህ ነው ዕቃ ለመዋስ
ስትፈልግ እኔን ጠይቀኝ እያልኩ የምጨቀጭቅህ። የወንዶችን
አመል እኔ መች አጣሁት....ነገር የሚጀምሩት ስኒ በመዋስ ነው
።ትንሽ ቆይተው ቢራ ልጋብዝሽ ይላሉ። ስኒ ሳይኖርህ እንዴት ቢራ
ልትጋብዝ ትችላለህ ? የማይመስል ነገር እኮ ነው ....ሆሆ
....የወንዶችን አመል እኮ አብጠርጥሬ ነው የማውቀው ።
እንግዲህ ስኒ በመዋስ ይገቡና በኃላ የሚፈልጉትን ሲያገኙ ጀበና
ይሰብራሉ። ለማንኛውም ይች ውብ መዓዛ ነሽ ትባላለች ።
እንደነገርኩህ ምን የመሰለ በደምግባቱም በሀብቱም የተሳካላት
እጮኛ አላት። አይ ፀባይ ! አይ ልግስና ....ኑሮው ፊልድ
መውጣት ነው። ከዚያ ሲመለስ ሽንኩርቱን፣ ከሰሉን፣ ፍራፍሬውን፣
ማሩን አስጭኖ ይዞልኝ ይመጣል...አይኔ ይፍሰስ...አይ የሰው
መለያየት !....ሰው ዝጉርጉር ነው ። አንዳንዱ እጁን ኪሱ ጋር
ሰፍቶ ይፈጥረዋል ። አንዳንዱን እንዲያውም ወይ ከኪሱ ወይ
ከእጅ አንዱ የጎደለበት ነው ። ሌላው እንደመአዛነሽ እጮኛ ያለው
ደግሞ ..."
''ይሄ ደግሞ '' አሉ ወደኔ እየጠቆሙ ምን ብለው ሊያስተዋውቁ
እንደሆነ በመጠበቅ አንገቴን ደፋሁ። ''ይሄ ደግሞ ...''ብለው
ቆሙ ። ቀና ብዬ አየኋቸው። ''ይሄ ደግሞ ...ያው ተከራይ ነው
...!'' አሉና ወደ መስተንግዶው ሄዱ ።
ብፌ ነው ።
ብፌውን እየዞርን እህል ማንሳት ጀመርን ።
የእትዬ ፀሐይን ንግግር እያብሰለሰልኩ ድብል እንጀራውን ሳነሳ፣
ክትፎውን ፣ቆስጣውን፣ ስጋውን ፣አይቡን ሳነሳ ሳላስበው ሰሃኔ
ትንሽ ጉድባ መስሎ ኑሯል ።''
ወደ ቦታዬ ስመለስ የሁሉም ዓይን ወደኔ መጣ ። እንዴት ያለ ነገር
ነው ? ...አልኩና ቶሎ ቶሎ ንጄ ልቀንሰው እጄን ስሰድ....የእትዬ
ፀሐይ ትንሽ ልጅ ቱር ብሎ ከጓዳ መጣ ።
''እማማ እራቴን!'' አለ ።
'' ሂድና አንሳ!'' አሉና ሰሃን ሰጡት ።
ልጅ ግን የማይረሳ ነገር ተናገረ ።
'' ከዚህ ነው ከዚያኛው ? ከየትኛው ላንሳ?'' አለ የኔን ሰሃን እና
የብፌውን ጠረጴዛ እያፈራረቀ እያየ ።

#መልካም ቀን
የኔ ቁመት ማጠር የጠቀመው ልብስ ሰፊዎችን ነው!
" ፍቅርሻ! ጨጓራ አሰፊንጂ! "...ጂንስ ማለታቸው ነው።
" ለምን? "
" ሁልጊዜ በጨርቅ ሱሪ?....ደላላ ይመስል "
ለምን መሰላችሁ? ጂንስ ከገዛሁ ግማሹን ማስቆረጤ የማይቀር
ነው እነሱ ጋር.......
አሁን መቼስ ለጌትየው ምስጋና ይድረስ፡ ወፈርኩንጂ ያኔ 40ዎቹ
ላይ ኪሎዬ ስታሽቃብጥ፡ የማላስጠብበው ልብስ ቢኖር ካልሲዬን
ነበር...እሱንም አፍሬ ነውንጂ....
ሰፍቶ..ሰፍቶ ወደታች ይወርድና የጫማዬ ቆብ መስሎ ቁጭ!
**
አንድ ልብስ ሰፊ ነበሩ፡ መንጥቅ ነው ስማቸው!
የአፍንጫ ጁስ ( ንፍጥ ) ያበዛሉ። የሚናፈጡበትን የማያጡ
አዛውንት፣ እድሜ ለኛ!
ሴቶችን ሲለኩ በጣም ይቆያሉ፡ ሴቶቹ ሲነጫነጩ ትዝ ይለኛል።
አንድ ቀን አቦነሽን ልትለካ መጣች፡ እኔ ከሷ ቀጥዬ።
ጋሽ መንጥቅ እንደለመዱት በአቦነሽ ዛቢያ ዞሩ
.....አስር ደቂቃ!
" ኧረ በቃ ምነው...አቦነሽ! "....ትላለች
" አይ እንግዲህ!...ወበራሽ ደግሞ! "
" ወገብ ለመለካት መዋል አለብዎትንዴ? "
" አሄሄ! ገና አላዳረስኩምኮ...."
እዚህ ላይስ እውነታቸውን ነው!
የአቦነሽን ወገብ አንተ አንለውም " እነ ወገብ " ነውንጂ!
አቦነሽን ታዘብኳት!...በኪነጥበቡ ሴት አደረጋትንጂ ወንድ ብትሆን
ኖሮ ከአንጀት የተሰራ ቀበቶ ነበር ልኳ!
የአቦነሽን ጨርሰው ዘወር ሲሉ ለጉድ የዶለኝ አለሁ
" ያንተን ነገ እጨርስልሃለሁ "
" ሳይለኩኝ? "
......ከላይ እስከ ታች ገርመም አደረጉኝ.....
ምን ከላይ እስከ ታች እላለሁ!? ከታች እስከ ታች ነውንጂ
" በግምት አውቀዋለሁ "
" የበግ ዋጋ ነውንዴ "
" አይ እንገዲህ " ክፍ " ካላሉህኮ! ትግማማለህ "
ይላሉ ፍንጃል ሙሉ እየተናፈጡ!
በአቦነሽ ጨርቅ ጠረግ ጠረግ....እያደረጉ!

©Fikre Ze Bhere Ethiopia

ሠናይ ውሎ መልካም ቀን!!!