ኢትዮጵያዊ ወጎች #Ethiopian
1.44K subscribers
314 photos
3 videos
18 files
50 links
Download Telegram
የመላሾች ስም
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥

1ኛ🥇 5/5

# Bethelihem @Emusha21
#Hermi
#Ame @Darfeto
#Eyu @Ambesaye87
# @BAFYT
# @Idlaous

2ኛ🥈 4/5

#Love is
#Rasu jone
#auser (Zion D)
#matias
# @Bentemariam
# Tekee @lmTeke
# @Eyyoba (New season...)
3ኛ 🥉 3/5

#አዲስ ከደብረዘይት



#እና በጣም ብዙ ስማችሁ ያልተጠቀሰ ተሳታፊዎች መልሱን መልሰዋል ቀድመው የመለሱ ጥቂቶችን ብቻ ነው የገለፅነው ሁላችሁም ምርጦች ናችሁ አብሮነታችሁ አይለየን፡፡

እናመሠግናለን ለዛሬው በዚው አጠናቀናል!!
#DrLiaTadesse

ኮሮና ቫይረስ ሁሉንም የእድሜ ክልል ነው የሚያጠቃው!

(በዶክተር ሊያ ታደሰ - የጤና ሚኒስትር)

በሀገራችን በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎችን የእድሜ ስብጥር ብንመለከት እስካሁን በቫይረሱ ከተያዙት 272 ሰዎች ከህፃናት እስከ አረጋዊያን ድረስ በሁሉም የእድሜ ክልል ያሉ ተይዘዋል።

ትልቁ ቁጥር 99 ሰዎች ከ15-24 የእድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ናቸው ፤ ከዛ የሚቀጥለው ከ25-34 የእድሜ ክልል ውስጥ (75 ሰዎች) የሚገኙ ሲሆን ከ60 ዓመት በላይ የሆኑ ሰዎች ቁጥርም 19 ነው። በህፃናት ላይ አነስተኛ ቁጥር ቢታይም ህፃናትም በሽታው እንደሚይዛቸው ያሳያል።

ይህ በሽታ የማያጠቃው የእድሜ ክልል የለም። በዓለም አቀፍ ደረጃ #ወጣቶች አይጠቁም የሚል #የተሳሳተ ግንዛቤ አለ ፤ በተለይ በእኛ ሀገር ያለው ስርጭት ትልቁ ቁጥር በወጣቶች ላይ የታየ ነው። ስለዚህ እያንዳንዳችን የምንወስደው ጥንቃቄ እጅግ አስፈላጊ ነው።

የዚህ በሽታ ስርጭት #እየጨመረ የሚሄድ ሊሆን ቢችልም ምን ያህል ይጨምራል የሚለውን የምንወስነው በየዕለቱ በምንወስናቸው ውሳኔዎች ፣ በየዕለቱ በምንመርጣቸው ምርጫዎች እንዲሁም በምንወስዳቸው እርምጃዎች ነው።
" አስቸገርኩህ መቼስ!...ጎሽ የኔ ልጅ....አምጣታ!? "
አያቴ ናት። ጠዋት የጀመረቻትን ማንጎ፡ እስከ አራት ሰአት!
" ስድስቴ ወደቀብሽኮ "
" ለቅለቅ አርጋትንጂ...."
ማንጎ ያጃጅላታል፡ ከአፏ በወደቀ ቁጥር፡ አንስቶ እያለቀለቀ
የሚሰጥ ተቀያሪ እስከማገኝ፡ ጲርርር እያለ የሚፈናጠርባትን
የማንጎ ፍሬ አባርራለሁ!
" የት ለመሄድ ነው የምትፎገላው!.....ውይ ወደቀች! "
" አሁንስ በቃሽ! "
" አንት ከርከዴ! አዞልሃላ "
አያቴ በገበያ፡-
...." ስንት ነው? " የሆነ ቅድ ጨርቅ
" 200 ብር "
" አይ አንተ ደግሞ 40 ብር ይበቃሃል ከምርቃት ጋር "
" ኧረ እማዬ እንደሱ አይሸጥም "
" ቅዘንህን የቻለ ሽንት ጨርቅ ነበር ያኔ " ብላኝ ቁጭ
.........ሰው ፊት! ......
ድሮ ቀረ፡ የአያቴ ጥቅስ
" ቆየህንዴ ከጀመርክ? " አለቺኝ ድንገት
" ምን እማማ? "
" መንዘላዘል ነዋ "...ግራ መጋባቴን ስታይ
" የከንፈር ወዳጅ፣ አጎጠጎጤ የለይም? "
" ፍቅረኛ ማለትሽ ነው?"
" አዎ " አለች በትዝታ እየተሳበች.......
" ፍቅር ድሮ ቀረ መቼስ! ያንተን ተወው። ወንድ ልጅ ጭን ስር
ገብቶ ካልቆነጠጠ፣ የውሃ እንስራ ካልሰበረ፣ ሎሚ ካላስሸተተማ
አንተን ሆነ ማለት ነው "
ኮስተር ብላ
" ብብትህ አራስ አራስ ከሸተተ ወንድ ነኝ እንዳትል "
" እንዴ እና ሳልታጠብ? "
" አሁንስ ውሃ እርሙ አይደለህ? "
አሰብ ታደርግና፡
" ለመሆኑ ወዳጅህን ቆንጥጠሃት ታውቃለህ? የኔ ጀፈል "
" ምን አጥፍታ? "
" አይ በቃ እሷ ትቆንጥጥህ እንግዲያው! "
" ኧረ እማማ "
" ሴት ሁነህ እየዋ የቁንጥጫውን ወግ "
አንድ ጊዜ አሸዋ የተጫነ አህያ ግቢያችን ገብቶ ስናወርድ፡
አህያው ፈሳ! መሳቅ ጀመርን
አያቴ አዘነች፡
" አሁን እንግዲህ ተፈሳ ማለት ነው! አበስኩገበርኩ! "
" ምነው እማማ "
" ኤዲያ! የድሮ አህያኮ አይፍሳ እናቴ! አንዴ የለቀቀው እንደሁ፡
የተሰጣ ልብስ ያደርቃል "
" የዛሬውስ? "
" አይይ! የዘንድሮ አህያማ ወጉን ትቶታልኮ! "
አህያውን ፍዝዝ ብላ እያየች፡
" በዚህስ እናንተ ትጎብዛላችሁ! "

Fikre Z Bhere Ethiopia
ስለ ዘገየን ይቅርታ የዛሬው ጥያቄዎች
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
የዛሬ ጥያቄዎች ትንሽ ለየት ይላል
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥

1) እውነት / ሀሰት

ንግስት ኤልሳቤጥ ሁለተኛ በነገስታት የአገዛዝ ታሪክ ውስጥ ረጅም ዕድሜ ስልጣን ላይ በመሆን የሚወዳደራት የለም፡፡

2) እውነት / ሀሰት
አልበርት አንስታይን እንደ ግሪጎሪያን ዘመን አቆጣጠር በ1952 የእስራኤል ፕሬዝዳንት እንዲሆን ታጭቶ ነበር ፡፡

3) የ 2011 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ያነሳው ክለብ ማን ነው?

4) ሊዮናርዶ ዲያቬንቺ የሚታወስበት ዝነኛ የስዕል ስራው ምንይባላል?

5) ኦሮሚኛ - ኩሸቲክ
አማርኛ - ሴሜቲክ
ወላይትኛ - ?????

መልሱን በ @EthiopianFirst_bot ይላኩልን መልካም ዕድል!!!
ብዙ መላሾች እንደምናገኝ ተስፋ እናደርጋለን Good luck!
ተሳተፉ መሞከር አይከፋም
ኧረ ዛሬ ቀዘቀዛችሁብን ተሣተፉ😭😭😭
በሚገርም ሁኔታ ሁሉም ተሣታፊዎች ማለት ይቻላል መልሡን በትክክል እየመለሡ ነው ያሉት ተሳተፉ ሞክሩ
ተሳትፎ ቀዝቅዟል ስለዚህ ከፍቶናል የታላችሁ😭😭😭😭
ድሮ ተማሪዎች ሆነን፡ ከሚያዝናኑኝ ነገሮች አንዱ ቅጣታችን
ነበር።
" አየለ! "
" አቤት ቲቸር "
" ና ውጣ! "
" ምን አጠፋው? ቲቸርዬ "
" እሁድ በሰፈራችሁ ሳልፍ በሴት ድምጽ ' ጊሽጣው ' ብለኸኛል
"
" ኧረ....እኔ "......
ቲቸር ማሩ ባገኙት ነገር ነው የሚማቱት። ጊዜ አይሰጡም!
ቷቷ ጧጧ ግው ጭው ድው...ካደረጉ በኋላ አራግፈን ስንነሳ ለኛ
ብለው እየመከሩን እንደሆነ ይነግሩናል።
አየለ ዘለግ ስለሚል በዱላ ነው የሚስተናገደው
ዧዧ...ጀርባውን
እውነቱን ለመናገር አየለ እንዳይገረፍ ጸሎታችን ነው
በተዠለጠ ቁጥር፡ ከጃኬቱ የሚነሳው አቧራ ተዉት!
" አንት ጅምር አህያ! " እያንከባለሉ...አባሱት ጭራሽ!
°°°°°°°°°°
አንድ ቀን የቲቸር ምስራቅ ወንበር ላይ የሞተ እንቁራሪት
ያስቀመጠውን መጠቆም ስላልቻልን በመደዳ እንድንገረፍ
መምህርቷ ሃሳብ አቀረቡ
በ75 ተቃውሞና በሳቸው ድጋፍ ጸደቀ!
" ማነው ስምህ? "
" ፍቅሬ "
" መምህር ሙላቱ ጋር ሂድና 4ኛ C ዎችን ልገርፍ ስለሆነ
ከቢልልኝ ጋር ሆናችሁ አግዙኝ ብላችኋለች ምስራቅ "
በላቸው!......እኔንኮነው የሚልኩት!
እሺ ብዬ ሄድኩ
" ቲቸር! " አልኳቸው መምህር ሙላቱን
" ምንድነው? "
" አይ፡ ቲቸር ምስራቅን እንዲያግዟቸው ነው "
" ምን እየሰራች? !
" ሊገርፉን ስለሆነ አግዙኝ ብለዋል "
ቲቸር ሙላቱ ሳቅ አፈናቸው
" ጥሩ!..... አለንጋ ብቻ ነው ያላት ማቴሪያል? "
.....ሙያ አደረጉትንዴ?......
" ለማንኛውም ያንን ጉማሬ አለንጋ ያዝ "
አሉና ትላልቅ አጣና ይዘው ተከተሉኝ።
አረማመዳችንና የተሸከምነውን ለሚያይ ገራፊና ተገራፊ
አንመስልም።
ለክፍላችን መገረፊያ የተሸከምኩትን ጭነት ክፍላችን አመጣነው።
ስንደርስ ቢልልኝ የተባለው ጥበቃ ቀድሞ ደርሶ፡ አዳሜን
ሰባብሯታል።
ክፍላችን የሰልስት ለቅሶ አይነት በስሱ ሲለቀስባት ሰማሁ፡፡
ለካ ዱላው ሲበዛ እኔ በሌለሁበት፡ በኔ ላይ ተደፍድፏል!
" ሙላቱ እንዳትለቀው! እራሱ ነው! ያዝ! "
.......ተበላሸሽ ፍቅርሻ!..........
እንደሮኬት ተወነጨፍኩ!
ዞር ስል ቲቸር ሙላቱ በንዴት አጣናውን እንደያዙ ያባርሩኛል
" ሙላቱ አጣናውን ጣል! " ይላል ቢልልኝ በጩኸት
ቲቸር ሙላቱ ገዋናቸው በንፋስ ወደኋላ እየተወጠረ ዞሬ ሳያቸው
ሳቄ መጣ።
" ሌባ ! ሌባ! ሌባ! ".....ሲሉ ደነገጥኩ!
ጥበቃዎቹ ከያሉበት እንደ ግሪሳ ከበው እላዬ ላይ!....
" አለንጋ ከአስተማሪ ይሰረቃል? "
እጄ ላይ ነበር!
Fikre Z Bhere Ethiopia

#ሠናይ ውሎ ውብ ቅዳሜ ተመኘንላችሁ

#StaySafe
ዓለም ዋዣቂ ናት ። ከፍና ዝቅ ስትል አትደናገጥ ፤ ፀሐይ ዝናብን ተከትላ ትፈነጥቃለች ። ከመከፋትም በኋላ ትልቅ መፅናናት ይሆናል ። ከሌሊት በኋላም ሌሊት አይመጣም ። ከሀዘን በኋላ
ደስታ ይሆናልና በርታ!
# ካነበብኳቸው_ገጾች
ከሮማን ጋር ጨርሼ ስልኩን እንደዘጋሁ ሌላ ጥሪ ወዲያውኑ
ተከትሎ መጣ። ፊያሜታ ጊላይ ነበረች።
< ከማን ጋር ነው ለግማሽ ሰዓት ስታወራ የቆየኸው አታግናይ? >
አለችኝ።
< ከማን ጋር ይመስልሻል? >
< ከእጨኛህ ጋር... >
< ልክ ነሽ... >
< ምን ነበር የምትለው? ምን ትፈልጋለች? ለእሷ ስልክ ለመደወል
ነው እኔን ዝም ብለህ ወደ ቤቴ ያመጣኸኝ? አባቴ ይሙት ፥
የሠራሁት ግፍ ሳይሆን አይቀርም እንዲህ የሚያዋርደኝ። ቅሌት
ነው... ቅሌታም ሆንኩ አባቴ ይሙት > እያለች ነገር ትፈልገኝ
ጀመር።
< እንሂድ ብዬሽ ነበር’ኮ። አንቺው ነሽ ቤቴ ውሰደኝ ያልሺኝ ፥
አይደለም እንዴ? > አልኳት።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በፊት የማላውቀው አዲስ ጠባይ
ይታይባታል። ከእኔ ጋር እደሪ ስላት እሺ አትልም። በፈቃዷ
መሠረት ወስጄ ሳደርሳት ደግሞ ታኮርፈኛለች።
< ብልህስ ታዲያ! >
< እሺ ምን አድርግ ነው የምትይኝ? >
< እንጃ አባትህ ፤ ደደብ ! >
< እሺ አሁን ልምጣና ልውሰድሽ... >
< አልመጣልህም ! >
< እሺ ምን ይሁን? >
< እንጃልህ! >
< እሺ ለምነኝ የምትይ ከሆነ አሁን ልለምንሽ... >
< ቤቴ ወስደህ እንደ ዕቃ ከጣልከኝ በኋላ? እውይ ብሞት ! >
ብላ ስልኩን ዘጋችብኝ።
መልሼ ልደውልላት ፈልጌ ስልኩን ካነሳሁ በኋላ ተውኩት። ኩራቴ
ታገለኝ። ተሟገትኩት ፤ አሸነፈኝ። ጥሪዬን እንደምትጠብቅ
ቢገባኝም ጨክኜ ተኛሁ። ግን እንቅልፍ አልወሰደኝም። ምን
እንደነካኝ አላውቅም ፤ እንዲህ አልነበርኩም።
ድንገት ለራሴ ባዶ እንደሆንኩ ተሰማኝ። የፍቅር ሰመመን አባዜ
ይዞኝ ይሆናል እንዳልል ዕድሜዬ እንዲህ ዓይነቱን ነገር የሚፈቅድ
አልመሰለኝም። የአሥራ ስምንት ዓመት ጎረምሳ አይደለሁም ፥
ወይስ ሰመመን የዕድሜ ክልል የለውም? አላውቅም። ግን የያዘኝ
አባዜ ሰመመን አልመሰለኝም። ገረመኝ ፥ መከረኛው ልቤ ሁለት
ሴቶች እንዴት ብሎ እኩል ሊወድ ይችላል? ብዬ ተገረምኩ።
ሕይወት እንግዳ ነገር ነው። ብዙውን ቀልድ ነው። አንዳንድ ጊዜ
ቀልዱ ይመራል። በሁለቱ መካከል መወሰን አልቻልኩም። ለደግም
ሆነ ለክፉ መወሰን አለመቻል ስቃይ ነው። ልቤ ሲደማ ተሰማኝ።
ያሰርኩት ቃልኪዳን እንደሾህ ወጋኝ።በዘንባባዎች ጥላ ሥራ አዲስ
ያገኙት ፍቅር እና ደስታ እንዲህ በቀላሉ የሚርረሰ ባለሞሆኑ
የሚደማውን ልቤን የባሰውኑ ጨመቀው።
ከፍቅርም ሌላ በፊያሜታ ሕይወት ላይ የሚያንዣብበው የአደጋ
ጥላ ፥ ይሉኝታ ፈጠረብኝ። አሁን ልለያት አልችልም። እንዴት
ብዬ? ሰው ወዶ ፣ ወዶ ድንገት በቃሽኝ ወይም በቃኸኝ ለማለት
እንዴት ይቻላል? እንዲህ ለማድረግ የሚችሉት የታደሉ ብርቱዎች
ናቸው። እኔ በዚህ አልታደልኩም። በዚህ ረገድ ደካማ ነኝ።
ተዋውቆ መለየት ያቅተኛል ፥ አንጀቴ አይችልም። ትዝታዬን መርሳት
ያስቸግረኛል። ስቃይ ይሆንብኛል።
የማደርገው ነገር ሁሉ ስሜቴን ስለሚነካ የኔ የራሴ ፥ የግሌ
አድርጌ ላስቀረው እፈልጋለሁ። እና እንዲህ ዓይነቱ ነገር ደሞ
ጅልነት ነው።
ምን ላድርግ? ጅል ነኝ !
______________
ደራሲ - # በዓሉ_ግርማ
ርእስ - # ኦሮማይ
1975 ዓ.ም
#የነበባችሁ ደግማችሁ አንብቡት
#ያላነበባችሁ ፈልጋችሁ አንብቡት

ሠናይ ቅዳሜ ከሙሉ ጤና ጋር ተመኘንላችሁ
ኢትዮጵያዊ ወጎች #Ethiopian
የዛሬ ጥያቄዎች ትንሽ ለየት ይላል 🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥 1) እውነት / ሀሰት ንግስት ኤልሳቤጥ ሁለተኛ በነገስታት የአገዛዝ ታሪክ ውስጥ ረጅም ዕድሜ ስልጣን ላይ በመሆን የሚወዳደራት የለም፡፡ 2) እውነት / ሀሰት አልበርት አንስታይን እንደ ግሪጎሪያን ዘመን አቆጣጠር በ1952 የእስራኤል ፕሬዝዳንት እንዲሆን ታጭቶ ነበር ፡፡ 3) የ 2011 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ያነሳው ክለብ ማን ነው? …
የትትናን ጥያቄዎች መልስ🔥🔥🔥
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
1) እውነት
2) እውነት
3) መቀለ 70 ዕንደርታ
4) ሞናሊዛ
5) ኦሞቲክ ሲሆኑ መላሾች ደግሞ🔥🔥🔥🔥
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

1ኛ 5/5🥇

#Matias 👏👏👏
#Samuel Mulugeta👏👏👏
#Endash👏👏👏
#Eyu @Ambesaye87👏👏👏

2ኛ 4/5🥈

#YEAB @Itsyeabsera 👏👏
# @SelamMebratuTadese 👏👏

3ኛ 3/5 🥉

#Tewulgn @Bemnetf👏
#Tekee man👏
#Bethelhem @Emusha21👏
#Bahilu Mola 👏


#ሳማችሁ ያልተገለፀ ብዙ ተሳታፊዎች ለተሳትፎችሁ እናመሠግናለን አብሮነታችሁ አይለየን ፡፡
#Share
ይቅርታ ለዛሬ ጥያቄዎች አይኖሩንም!!
አንድ ጀለስ አለ እና ሁሌ ይቋጥራል። ቺክ ከሆነች ግን ተበድሮም ቢሆን 😂 ያደርጋል። እና አንድ ቀን ምሳ በልተን ስንነሳ ሂሳብ አዋጣ ሲባል "ይቅርታ ዝርዝር ስለሌለኝ ለዛሬዉ እናንተ ክፈሉ" ብሎ ላሽ ሊል ሲል አንዱ ተናዶ ምን ቢለዉ ጥሩ ነዉ...
.
.
አታመንዝር እንጂ አትመንዝር አልተባለምኮ ሂሳብ አምጣ🤣🤣🤣
አምስቱ የስሜት ህዋሳት ስንት ናቸው?
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
እኔና እሷ ሳንፋቀር..
ስለ ስሜት ህዋሳቶች ፥ የምናውቀው አምስት ነገር
በአይናችን እናያለን
በእጃችን እንዳስሳለን
በምላሳችን እንቀምሳለን
በጆሯችን እንሰማለን
ባፍንጫችን እናሸታለን ፣ የሚል ነበር፡፡
።።።
እኔና እሷ ስንፋቀር..
ካንደበቷ ቃል ሳይወጣ ፣ በዝምታ ስትናገር
የከንፈሯን ንቅናቄ
እያየሁኝ የምሰማት ፣ ያለችኝን አንዳች ነገር.
አይን ማለት
በዚያ ሰአት ፥ መስሚያ ነበር፡፡
።።።
እኔና እሷ ስንጣላ
ስለጃችን ከተማርነው ፤ ከመዳሰስ ስሜት ሌላ
ሌላ ስሜት ተፈጥሮብኝ ፥ ያንደበቴን ቃል ሰስቼ
አነዳች ነገር ስናገራት ፤ የመሀል ጣቴን አውጥቼ
ስድብ መሆኑ ሲገባት
ምላሷን ስታወጣብኝ
ስላቅ መሆኑ ሚገባኝ
እጅ ማለት ሌላ ስሜት ፥ ምላስ ማለት ሌላ ነገር
መቅመስ መዳበስ ያልሆነ ፥ ያልተማርነው ነገር ነበር፡፡
ብቻ
ብቻ
እኔና እሷ ስንጣላ ፥ እኔና እሷ ስንፋቀር
ስለ ስሜት ህዋሳቶች ፥ ብንማርም አምስት ነገር
እኛ ኖረን ያሳለፍነው ፥ ቁጥር አልባ ስሜት ነበር፡፡

ሠናይ ቀን ውብ ውሎ
ዛሬ ቀለል ያሉ ጥያቄዎች ይኖሩናል ይሳተፉ እየተዝናኑ እውቀትዎን ያሳድጉ ፡፡ ለሀሳብ አስተያየት ወይም አብሮ ለመሥራት በ @EthiopianFirst_bot ያናግሩን፡፡
ዛሬ ቀለል ያሉ ጥያቄዎች ይኖሩናል ይሳተፉ እየተዝናኑ እውቀትዎን ያሳድጉ ፡፡ ለሀሳብ አስተያየት ወይም አብሮ ለመሥራት በ @EthiopianFirst_bot ያናግሩን፡፡
የዛሬ ቀለል ያሉ ጥያቄዎች 👇👇👇👇
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥

1) የአለማችን እረጅሙ ተራራ ማን ይባላል ?

ሀ) ራስ ዳሽን
ለ) ሂማሊያ
ሐ) ኤቨረስት

2) ለአድዋ ጦርነት መነሻ የሆነው ውል ምን በመባል ይታወቃል ?

ሀ) የአድዋ ውል
ለ) የውጫሌ ውል
ሐ) የሂወት ውል

3) ውሃ በስንት ዲግሪ ሴንቲግሬድ ቴምፕሬቸር ነው የሚፈላው ?

ሀ) 37
ለ) 72
ሐ) 100

4) የባርባዶስ ዋና ከተማ ማን ይባላል ?

ሀ) ካራካሽ
ለ) ብሪጅታወን
ሐ) ባርባዶስ

5) በየትኛው የተክል ክፍል ነው ፎቶሲንተሲስ የሚካሄደው ?

ሀ) ቅጠል
ለ) ስር
ሐ) አበባ

🔥🔥🔥Bonus questions🔥🔥🔥

# What does GIF stand for?

# Who is the current chairman of WHO?

መልካም ዕድል Good luck !

መልሱን በ @EthiopianFirst_bot ያድርሱን፡፡
ተሳታፊዎች ደስ ይላል ብዙ አግኝተናል