ኢትዮጵያዊ ወጎች #Ethiopian
1.44K subscribers
314 photos
3 videos
18 files
50 links
Download Telegram
በላይ በቀለ ወያ

በልክሽ ተሰርቶ፤ ቀልዴ ቁምነገሬ
ከተውሽኝ በኋላ…..
አንቺን ለመርሳት ስል ፤
ከብዙ ሴቶች ጋር፤ ልላመድ ሞክሬ
ለማንም አልሆንኩም!
ላንዷ እጠባታለሁ፤
ላንዷ እሰፋታለሁ፤
ላንዷ እረዝማታለሁ፤ ላንደኛዋ አጥሬ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ይኸው በቀደም ለት…..
ሳቅሽን የሚመስል ፤
ሳቋን የምትስቅ ፤ አንዲት ሴት ወድጄ
ሳቋን ለማፅናት ስል..
አንቺን ባሳቅሁሽ ቀልድ፤ እንድትስቅ ቀልጄ
ቀልዴ አላስቅ ብሏት ...
ያንቺን የሚመስለው ፤ ያ ሳቋ ቢጠፋ
በቅፅበት ጠላኋት…
አንቺን ባሳቀሽ ቀልድ፤ ሳያት እሷ አኩርፋ፡፡
።።።።።።።፣፣፣፣፣፣፣።።።።።።።።።።።፣።።
ባለፈው ለት ደሞ…
ያንቺን የሚመስል፤
ኩርፊያ ካኮረፈች፤ ከአንዲት ሴት ጋራ
ላንች የነገርሁሽን...
አስኮራፊ ታሪክ ፣
ኩርፊያዋን ለማፅናት፤ አኩርፌ ሳወራ
ያንቺን የሚመስል ፣
ኩርፊያዋ እስኪጠፋ ፣ ሳቋን ብትለቀው
ድንገት አስጠላችኝ….
እሷ ማን ሆና ነው?
አንቺን ባስኮረፈሽ ፤ ታሪክ የምትስቀው!?
።፣፣፣፣፣።።።።፣።፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣።፣።።።፣፣፣፣
ሰሞኑን ደግሞ አንዷን…
የዋናውን መንገድ፤ ትንሽ ገባ ብላ
አራቴ ወደ ቀኝ...
ሶስቴ ወደ ግራ፤ ከታጠፈች ኋላ
ወደ ሌላ ሚወስድ
ሌላ ዋና መንገድ
ከማግኘቷ በፊት...
ያለው ድልድይ ጋር ፣ እንገናኝ ስላት
አንቺ ከምትወጂው...
አንቺ ከምትቀጥሪኝ፤ ቦታ ላይ ስቀጥራት
‹‹እንዲህ ያለ ቦታ...
በጭራሽ አላውቅም›› ፣ የሚል ነበር መልሷ፤
ዘልዓለም ጠላኀት!
አንቺ ምትወጂውን
ቦታ የማታውቀው ፤ ማን ሆና ነው እሷ?!
፣፣፣፣፣፣።።።።።፣፣፣፣፣፣።።።።፣፣፣፣፣፣፣፣፣፣
ብቻ ምን ልበልሽ….
በልክሽ ተሰርቶ፤ ቀልዴ ቁምነገሬ
ከተውሽኝ በኋላ…..
አንቺን ለመርሳት ስል ፤
ከብዙ ሴቶች ጋር፤ ልላመድ ሞክሬ
ለማንም አልሆንኩም!
ላንዷ እጠባታለሁ፤
ላንዷ እሰፋታለሁ፤
ላንዷ እረዝማታለሁ፤ ላንደኛዋ አጥሬ፡፡
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ይኸው ደሞ ዛሬ…
የሌላ እንዳልሆን ፤በልክሽ ሰርተሸኝ
ከተውሽኝ በኋላ…….
ምትወርጂውን መንገድ ፣
እኔ እወጣሁት፤ ድንገት አግኝተሸኝ
‹‹እንዴት ነህ? ››ስስትዪኝ ...
እንዴትም እስክሆን ፣ ግራ አጋባሽኝ
አንቺ ነሽ? እኔን ነው? እንዴት አናገርሽኝ?
እንዴት ነኝ ልበልሽ?
እንደዚያው ነኝ በቃ!
እንደዚህ አድርገሽ ፣ያኔው እንደተውሽኝ፡፡
አንቺ ግን እንዴት ነሽ?
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡

#ውብ ቀን
#የምፃተኛው_ኑዛዜ
(በእውቀቱ ስዩም)

ካ’ገር ጫፍ እስከጫፍ በጥላህ ከልለህ
ተራራው የኔ ነው ለምን ትለኛለህ?
ወንዙ ድርሻዬ ነው ለምን ትለኛለህ?
እንኳንስ መሬቱ አንተም ያ’ንተ አይደለህ።
እኔ መጻተኛ አንተ ኗሪ ነኝ ባይ
እኔ እግሬን ስከተል ርስትህን ስታይ
ስቀርብህ ገፋኸኝ ስትገፋኝ ቦታ አጣሁ
ድንኳን ብትተክል፣ ነፋስ ሆኜ መጣሁ።
ያ’ባትህ ያ’ባቴ
ጠበኛ ስማቸው
ጠበኛ ሕልማቸው
በሕይወት ተጣሉ፣ ታረቁ ባፅማቸው
ባፈር ተቃቃሩ፣ አፈር አስማማቸው
በዙሪያቸው በቅሎ ከቧቸው ሞት ደኑ
መተቃቃፍ መርጠው ማማና ወይን ሆኑ።
ይችላል ይሉሃል ፍልሚያ ማዘጋጀት
ያ’ባት አጥንት ወስዶ ስሎ ጦር ማበጀት
አንተው ጦር ወርውረህ አንተው ቀድመህ ወድቀኽ
አካሌ ደረቴ መኾንኽን መች አወቅኽ ??? !!!

#ውብ ቀን
‹‹ነገ ሌላ ቀን ነው››
--------------------
ከዕለታት በዚች ቀን፣
በልዩ አጋጣሚ፤
እንድትሆኝ ጋበዝሁሽ፣
የቤቴ ታዳሚ።

አንቺ ግን ሰበባም፣
ምክንያት ደርድረሽ፣
ግብዣዬን አቃለሽ፣
እምቢ ብለሽ ቀረሽ።

በይ ከእንግዲህ ወዲያ፣
አንቺ ከኔ ጋራ፤
ፈፅሞ እንዳያምርሽ፣
ጊዜ እንድንጋራ።

እርሱ በፈቃዱ፣
ቢመርጥም ባይመርጥም፤
ዛሬዬን ለናቀ፣
ነገዬን አልሰጥም።

አየሽ በኔ ዓለም፣
ዛሬ ልዩ ቀን ነች፤
ነገ የማትመጣ፣
ትናንት ያልነበረች።

ጊዜን ትርጉም ሰጥቶ፣
ተግባር ለሚከውን፤
ቀን ማለት ዛሬ ነው፣
ጊዜ ማለት አሁን።

‹‹ነገ ሌላ ቀን ነው››
ትርጉሙ ይሄው ነው።
--------------------------
መላኩ አላምረው
📙 ነፍጠኛ ስንኞች

#ሠናይ ምሽት
#ውብ ለሊት
#ጥንቃቄ ማድረግ አይዘንጉ ለእርስዎ ለቤተሰብዎ ደህነንት ሲሉ