ኢትዮጵያዊ ወጎች #Ethiopian
1.46K subscribers
314 photos
3 videos
18 files
50 links
Download Telegram
~~~~መልሱልኝ ልጄን
=============
ይድረስ ለአባ ገዳ~ለጎሳ መሪዎች
ላገር ሽማግሌ~ለእምነት አባቶች
~
መንግስትን አምኜ~ወግ አያለሁ ብዬ
ልጄን ልኬ ነበር~ ተማሪልኝ ብዬ
ተምራ መምጫዋን~ቀኗን እያሰላሁ
ናፍቃኝ ቻል አድርጌ~ማየት እንደጓጓሁ
ልጅሽ ታግታለች~የሚል መርዶ ሰማሁ
~~
ትማርልኝ ብዬ
ያይን ማረፊያዬን~ተስፋዬን ሰድጄ
ትኑር ትሙት አላውቅ~እጄን በላሁ በእጄ
እናም አሸማግሉኝ~ይቅርባት ትምህርቷ
ልጄን መልሱልኝ~ካለች በህይወቷ

#ህሊና ደሣለኝ ©


#የረሣናቸው_የእህቶቻችን_ጉዳይስ
#ስለሷ_ዝም_አንበል
#ፍትህ_ከወዴት_ነሽ