ኢትዮጵያዊ ወጎች #Ethiopian
1.46K subscribers
314 photos
3 videos
18 files
50 links
Download Telegram
አድዋ
GIGI (Ejigayehu Shibabaw)
🎙• እጅጋየሁ ሽባባው
🎧 • አድዋ|Adwa

►Join Us, @Mudenyaz
Amazing poem by Laureate Yetnebersh Nigussie
የሎሬት የትነበርሽ ንጉሴ ማራኪ ግጥም፡ አማረኝ
ገጣሚ እና አንባቢ :- ሎሬት የትነበርሽ ንጉሴ ርዕስ - አማረኝ @getem @getem
@getem
መለያየት ማለት
(ኤፍሬም ስዩም)

ይኸው ትላንትና ከትላንትም በስትያ
ያዩሽ ሰዎች ሁላ ከእቅፌ ጉያ
ዛሬን ተራርቀን ብቻዬን ቢያዩኝ
ከድታዋለች ብለው ከንፈር መጠጡልኝ
እባክሽ የኔ አለም!! ፈጥነሽ ንገሪያቸው
ሴትን ማፍቀር እንጂ ማባበል አይችልም ብለሽ አስረጃቸው።

ለኔ ና ላንቺ እኮ መለያየት ማለት
በሩቅ መፋቀር ነው ያለመተያየት... ያለመተያየት
መፋቀርም ማለት
በምናልባት ተስፋ የምትቆም ህይወት
ዘወትር....
ዘወትር ምናልባት......... ምናልባት እያለች የምትኖር ህይወት በተስፋዋ መሀል ጥቂት ደስታ አላት

በታስፋችን መሀል መፋቀሩ ካለን
ናፍቆት አካል ገዝቶ እንተያያለን
ብለሽ ንገሪያቸው....
ልቤና ልቦናው ተጣብቀዋል በያችቸው
እንጂ በኛ መሀል መለያየት ማለት
በሩቅ መፋቀር ነው ያለመተያየት....
በሩቅ መሰማማት በድምፅ አልባ ቃላት።

@Simetin_Begitim
ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች በግል ችግር ምክንያት በየዕለቱ መልዕክቶችን ለእናንተ ማድረስ አልቻልንም ለዚህም ከልብ ይቅርታ እየጠየቅን በአዲስ አቀራረብ ከአዳዲስ መሠናዶዎች ጋር በቅርቡ እንደምንመጣ ከወዲሁ ለመግለፅ እንወዳለን ፡፡ አብሮነታችሁ አይለየን ፡፡

ለወዳጅዎ ቻናላችሁን ያጋሩ t.me/Simetin_Begitim

ለሀሳብ አስተያየት @Simetin_Begitimbot ያግኙን
የኮሮና ቫይረስ በሽታ መከላከያ መንገዶች፦

- የኮሮና ቫይረስ በሽታ ምልክት ከሚያሳዩ ሰዎች መራቅ

- ባልታጠበ እጅ አይን፣ አፍንጫ እና አፍን አለመንካት

- እጅን በንፁህ ውሃ እና ሳሙና በደንብ መታጠብ

ይህን መልዕክት ለምታውቁት ሁሉ አጋሩ!
#CoronavirusEthiopia በውሃን ቻይና በኮሮና ቫይረስ የተፈጠረውን ወረርሽንለመዋጋት በስፍራው ከሚንቀሳቀስ ግብረሃይል ጋር ለመስራት ከተሰማራ ወጣት ተመራማሪ የተገኘና ኮሮና ቫይረስ ማለት ምን ማለት እንደሆነ፣ እንዴት ከሰው ወደ ሰው እንደሚተላለፍ እንዴት በዕለት ተዕለት የህይወት እርምጃ ውስጥ የቫይረሱን ስርጭት ማስቆም እንደሚቻል የተሰጠ መረጃ!

ከሮና ቫይረስ የአፍንጫ እርጥበት እና አክታ የሚያስከትል ሳል ያለው
አይደለም፡፡ በተቃራኒው አፍንጫ የማያረጥብ እና ደረቅ ሳል የሚያስከትል በመሆኑ በቀላሉ ልንረዳው የምንችለው ነው፡፡

ቫይረሱ ከ26-27 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ያለውን ሙቀት መቋቋም የማይችል በመሆኑ ይሞታል፡፡ ስለዚህ እንደ ሻይ፣ ሾርባ ፣ ትኩስ ውሃ
...ወዘተ ያለትን ትኩስ ነገሮች በየቀኑ ደጋግሞ መጠጣት ቫይረሱን ይገድበዋል፡፡ ትኩስ ነገሮችን መጠጣት ደግሞ ከባድ አይደለም፡፡

በጣም የቀዘቀዘ ውሃ አትጠጡ፣ የበረዶ ኩቦችን ወይም አመዳይ/Snow አትመገቡ!

የምትችሉ ሁሉ የጸሐይ ሙቀት ተቀበሉ፡፡

1. ኮሮና ቫይረስ ከ400-500 ናኖሜትር ዳያሜትር ርዝመት ያለው ትልቅ ቫይረስ በመሆኑ ለመከላከል የሚያስፈልገው ጭምብል ወይም ማስክ
በተለየ መንገድ የተሰራ መሆን የለበትም፡፡ ማንኛውንም አይነት ጭምብል መጠቀም ይቻላል፡፡

በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች በሚገኙባቸው ተቋማት የሚያክሙ የጤና ባለሙያዎች ግን የተለዩ የመከላከያ መንገዶችን መጠቀም አለባቸው::

አንድ በቫይረሱ የተጠቃ ሰው ከፊት ለፊታችሁ ከ3 ሜትር ርቀት ላይ ቢያስነጥስ ቫይረሶቹ ወደ ምድር የሚወድቁ በመሆናቸው በቫይረሱ
ተጠቂ አትሆኑም፡፡

2. ቫይረሱ ብረትነት ባላቸው ገጾች/አካሎች ላይ ካረፈ በኋላ ለ12 ሠዓታት በህይወት ሊኖር ይችላል፡፡ ስለዚህ ከብረት የተሰሩ እንደ እጀታዎች፣ በሮች፣ የቤት ዕቃዎችን፣ የአውቶቡስ የባቡር ወይም የትራም መደገፊያ እጀታዎችን ወይም ምሰሶዎችን ከነካችሁ በኋላ እጃችሁን በደምብ በሳሙና መታጠብ ይገባል፡፡

3. ቫይረሱ በልብስ እና በጨርቆች ውስጥ ተሰግስጎ ከ6-12 ሰዓታት ሊኖር ይችላል፡፡ ስለዚህ መታጠብ የሚችሉትን ልብሶች በሙሉ ዘወትር
በምንጠቀምባቸው ሳሙናዎች ብናጥባቸው ቫይረሱን ይገድለዋል፡፡ በየእለቱ መታጠብ የማይችሉ ልብሶችን ጸሐይ ላይ ብታሰጡዓቸው
ቫይረሱን የጸሐይ ሙቀት ይገድለዋል፡፡ በቫይረሱ የመጠቃት ምልክቶች #ምን ምንድን ናቸው?

1. ቫይረሱ መጀመሪያ መቀመጫውን ጎሮሮ ላይ በማድረግ የጉሮሮ ብግነት እና የጎሮሮ ድርቀት ስሜት ያስከትላል፡፡ ይህ የህመም ስሜት
ከ3-4 ቀን በሰው ላይ ሊቆይ ይችላል::
2. ቫይረሱ በመተንፈሻ ቱቦ ውስጥ ያለውን እርጥበት በመጠቀም ወደ ትራኪያ ከወረደ በኋሊ መቀመጫውን ሳምባ ውስጥ ያደርጋል፡፡ ሳምባን
በማጥቃት ኒሞንያ/ የሳምባ ብግነት ያስከላል፡፡ ይህ ምልክት የሚታይባችሁ ሁሉ በፍጥነት ወደ ህክምና ሂዱ!! በቫይረሱ ላለመያዝ ምን ማድረግ ይገባል?

1. የቫይረሱ ስርጭት በአብዛኛው ቀጥታ ከንክኪ ጋር የተያያዘ ሲሆን ቫይረሱ ያረፈባቸውን ቁሳቁሶች እና ልብሶች ወዘተ... መጠቀም ዋነኛ
መተላለፊያው መንገዱ ነው፡፡ ይህም ማናቸውንም ነገር ከነኩ በኋላ በተደጋጋሚ እጅን በደምብ መታጠብ ዋነኛ መከላከያ መሆኑን
ያስገነዝበናል፡፡

< ቫይረሱ በሰው እጅ ላይ በሕይወት መቆየት የሚችለው 10 ደቂቃ ያህል ነው፡፡ ይሁን እንጂ በአስር ደቂቃዎች ውስጥ ብዙ ነገር ሊከናወን
ይችላል፡- አይንን ማሸት፣ አፍንጫን መንካት፣ ጣቶችን ወደ አፍ መውሰድ ወይም [እንደ ጥፍር የመመጥመጥ ክፉ ልማድ] ቫይረሱን በቀላሉ ወደ
ጉሮሮ እንዲሄድ ሊያደርገው ይችላል፡፡
< ስለዚህ ለራሳችሁና ለባልንጀራችሁ (ለሌላው ሰው) ደህንነት ስትሉ በጣም በተደጋጋሚ እጆቻችሁን ታጠቡ፡፡

2. አፍ እና ጉሮሮን ጸረ-ተሕዋስ መድሀኒቶችን በመጠቀም መጉመጥመጥ ቫይረሱን ሊያስወግድ ወይም ወደ ጉሮሮ የሚሄዱትን መጠን ሊቀንስ ይችላል፡፡ አፍን መጉመጥመጥ ወደ ጉሮሮ ወደ ትራኪያ አልፎም ወደ ሳምባ ቫይረሱ የሚያደርገውን ጉዞ ሊያግደው ወይም
ሊቀንሰው ይችላል፡፡

3. የኮምፒውተራችሁን ኪ-ቦርድ እና ማውዝ በጸረ- ተህዋስ በሚገባ አጽዱ።

© ምንጭ : ዶ/ር ቤዛ አያሌዉ የቴሌግራም ገፅ
መደናገጥ እና አጉል ፍራቻ፣ ከበሽታው እኩል አደገኛ ሊሆኑ ይችላሉ!

ጠቃሚ ምክሮች፦

- ሳል ወይም ትኩሳት ካለው ግለሰብ ቢያንስ ሁለት የአዋቂ እርምጃ ርቀት ያህል መራቅ
- እጅዎን በአግባቡ ሳይታጠቡ አይንና አፍንጫዎን አይንኩ
- ከሰዎችጋር አይጨባበጡ፣
- እጅን በንጹህ ውሃና ሳሙና አዘውትረው ይታጠቡ፣
- ሰዎች ወደ በሚበዙባቸው ቦታዎች በተለይም የህመም ስሜት ካልዎት አይሂዱ፣
- በሚያነጥሱበት እና በሚያስሉበት ጊዜ አፍና አፍንጫዎን በሶፍት ወይም ክርንዎን አጥፈው በመጠቀም ወደ ሌሎች እንዳያስተላልፉ ይጠንቀቁ፣ የተጠቀሙበትን ሶፍትና ተመሳሳይ ነገሮች በቆሻሻ ክዳን ባላቸው ማጠራቀሚያ ያስወግዱ፣
- በስራ ቦታ፣በትራንስፖርት እና መኖሪያ ወይም የመኝታ ክፍል መስኮት በመክፈት በቂ አየር እንዲኖር ያድርጉ፣
- መረጃዎችን ከአስተማማኝ ምንጮች ብቻ በመቀበል፣ የተሳሳቱ መረጃዎች የሚያስከትሉትን መደናገር እና ፍርሀት እርሶም ይከላከሉ!

#ሼር #SHARE

#ጤናሚኒስቴር
የጠቅላይ ሚኒስትሩ መልዕክት፦

በአገራችን በዛሬው እለት አንድ ኮሮና ቫይረስ ያለበት ሰው የተገኘ በመሆኑ ህብረተሰቡ እነዚህን ምክሮች በመከተል እራሱን እና ቤተሰቦቹን ከበሽታው እንዲከላከል አሳስባለሁ።

- እጃችንን በውሃ እና በሳሙና አዘውትሮ መታጠብ

- የጉንፋን ምልክት ከታየብን ከቤት አለመውጣት፣ ሰው የሚበዛብት ቦታ አለመሄድ

- ንክኪ የሚያስፈልጋቸው የሰላምታ መንገዶችን መተው

- ሰው በብዛት የሚሰበሰብባቸው ቦታዎች ላይ የሚገኙ ከሆነ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ

- ህብረተሰቡ ሳይደናገጥ በንቃት የራሱን እና የቤተሰቡን ጤና መጠበቅ

#DrAbiyAhmed

#Share
የፊት ማስክ አጠቃቀም እና አወጋገድ

- የፊት ማስኮን ከማድረግ በፊት እጅም በሳሙና መታጠብ።

- በማስኩ አፍና አፍንጫን መሸፈን ምንም ክፍተት ሳይኖረው።

- ማስኩ አፍንጫዎ ላይ እንደተመጠ እንዲቆይ የአፍና የአፊንጫዎን ጠርዝ በጣቶ መጫን።

- ማስኩን በሚያወልቁበት ወቅት ክዳን ባለው ቆሻሻ መጣያ ውስጥ ይጣሉት ወይንም ያቃጥሉት።

- ማስኩን አድርገው እያለ ማስኩን በእጆ ባይነኩ ይመረጣል። ለመንካት ከፈለጉም እጆን በሳሙና ታጥበው መሆን አለበት


#ሼር ያድርጉ
#Share it
Forwarded from Chunisha@
Forwarded from ግጥም ብቻ 📘 (👋ገብርዬ)
Corona Ebook.pdf.pdf.pdf.pdf
724 KB
Everything you need to know about the corona virus.
የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክ (face mask) አጠቃቀምና እነማን መጠቀም እንዳለባቸው ልብ ይበሉ!

የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ (face mask) አጠቃቀሙና እነማን መጠቀም እንዳለባቸው በቅጡ ባለመረዳት ሰዎች ለአላስፈላጊ ወጪና እንግልት ሲዳረጉ ይስተዋላል፡፡ ስለሆም ማስክ የሚከተሉት ሰዎች እንዲጠቀሙት ይመከራል፡፡

1. የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማስክ መጠቀም የሚያስፈልገን በበሽታው የተያዘ ወይም የተጠረጠረ ሰው አጠገብ ወይም እየተንከባከብን ከሆነ ብቻ፣

2. ሳልና ትኩሳት ካለብን ለሌላው ጥንቃቄ በማድረግ ስያስለን ወይም ስያስነጠሰን፣ እንዲህ ከሆነ ደግሞ ሌሎች ተጨማሪ ጥንቃቄዎችን ማድረግ ያስፈልጋል ለምሳሌ ሰው የሚበዛበት ቦታ ከመሄድ ራስን መቆጠብ ፣ እጅ በደንብ መታጠብ ፣ መጨባበጥ ማቆም እና ማስኩን በስርዓት ማስወገድ እና ለባለሙያ ማሳወቅ ያስፈልጋል::

3. የማስክ አጠቃቀምም ውጤታማ የሚሆነው እጅን በንጹህ ውሃና ሳሙና አዘውትሮ መታጠብ ሲቻል እና አወገገዱም ጥንቃቄ የተሞላበት ስሆን ብቻ ነው፡፡ ህብረተሰባችን መረጃዎችን ከአስተማማኝ ምንጮች ብቻ በመቀበል፣ የተሳሳቱ መረጃዎች የሚያስከትሉትን መደናገር እና ፍርሀት እርሶም ይከላከሉ።

የበለጠ መረጃ ሲያስፈልግ ነጻ በሆነው 8335 የስልክ መስመር ላይ መደወል ይቻላል።

Via FBC
( በላይ በቀለ ወያ )

.
አንጥሴ
አንጥሴ
በማለት ባስነጥስ ፣ ሁሉም አገለለኝ
ቀና ብየ ባየው ፣ ሰማዩም ቀለለኝ
"እግዚአብሔር ይማርህ"
ማያባብል ዘመን ፣ መጥቶ ነው መሠለኝ!

@Simetin_Begitim
Forwarded from yirgalem post (Mesge D)
ተጠንቀቁ እንጂ አትፍሩ!

አንድ ጊዜ አንድ ንጉስ ከጦር አጃቢዎቹ ጋር ሆኖ ወደ ሌላ ሃገር ጉዞ ሲደርግ አንድ እጅግ አጥፊ የሆነ አውሎ ነፋስ ወደ እሱ አገር አቅጣጫ በመገስገስ ላይ እንዳለ ተመለከተና ባለው የጦር ኃይል አውሎ ነፋሱን አስቁሞ፣ “ወደ እኔ ሃገር አቅጣጫ በመሄድ ላይ ነህ፡፡ ከእኔ ሃገር ሰው ማንንም እንዳማታጠፋ ቃል ካልገባህ አታልፍም አለው” አውሎ ነፋሱም፣ “በእርግጥ ነው ወደዚያ አቅጠጫ ነው የምሄደው፤ ነገር ግን የአንተን ሃገር ሕዝብ በፍጹም እንደማልነካ ቃል እገባልሃለሁ” አለው፡፡

ንጉሱ ከጉዞው ሲመለስ ከሃገሩ ሰዎች በርካታዎቹ እንደሚቱ ሰማ፡፡ በጣም በመቆጣት አውሎ ነፋሱን ተከታትሎ ደረሰበትና፣ “ማንንም እንደማትነካ ቃል ገብተህልኝ ለምንድን ነው ብዙ ሰው የገደልከው?” አለው፡፡ አውሎ ነፋሱም እዲህ ሲል መለሰ፣ “እኔ በሃገርህ አጠገብ አለፍኩኝ እንጂ የሃገርህን ህዝብ አንዱንም አልነካሁም፡፡ እንደሰማሁት ከሆነ ግን ከባድ አውሎ ነፋስ መጣ የሚል ወሬ ተወርቶ በፍርሃትና በድንጋጤ አንዳንዱ በልብ ድካም፣ አንዳንዱ ሲሯሯጥ እርስ በርሱ ተረጋግጦ ነው የሞተው”፡፡

አንዳንዴ በሃገራችን ከሚከሰተው ችግር ይልቅ በችግሩ ላይ ያለን አመለካከት፣ የሚወርሰን ፍርሃት፣ የምንሰጠው ተገቢ ያልሆነ ምላሽና የፍርሃትና የድንጋጤ ስሜታችን ከማየሉ የተነሳ አዋቂዎቹ የሚነግሩንን መመሪያ በአአምሯችን አስበን አለመከተላችን ነው የሚያጠፋን፡፡

አንባቢዎቼ በወቅቱ በደረሰብን አስጊ ሁኔታ ስለራሳችንና ስለቤተሰቦቻችን የማሰባችን ጉዳይ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ በምክንያት የለሽ ፍርሃት ከመተራመስና ራስን ለከፋ ነገር ከማጋለጥ እንጠበቅ፡፡

ፈጣሪ እናንተንና የእናንተ የሆኑትን ሁሉ ይጠብቅላችሁ፡፡

@yelakehiwet
@yelakehiwet
@yelakehiwet
👆👆👆👆👆
እንደምትወዳት ንገራት!

(በእውቀቱ ስዩም)

ህይወት -የብድር በሬ፤ መቼ ሁሌ ይጠመዳል?
ለጊዜው ብቻ የመጣ ፤ ጊዜው ሲደርስ ይሄዳል
የተሰጠህ ፀጋ ሁሉ፤ ደሞ ካንተ ይወሰዳል፤

ቀለበት ፤ አምባር አይደሉም
እጅህ ላይ፤ ሁል ጊዜ የሉም-
-ቀናት ፤ሳምንታት፤ ወራት
ዛሬውኑ ፤ አሁንኑ ፤ እንደምትወዳት ንገራት ፡፡

አበቦች ሁሉ ሳይረግፉ
ምኡዝ ሽታዎች ሳይጠፉ
ያፀድ በሮች ሳይቆለፉ
በንቦች ጎዳና ላይ ፤ተርቦች ሳይሰለፉ
በንፋስ ክንፍ ሳይመታ
ህይወት- የላምባ መብራት
አሁንኑ ዛሬውኑ፤ እንደምትወዳት ንገራት::


ርቃ ሳትገሰግስ
ገና ስንቋን ስትደግስ
እንዲሁ እንዳማረባት
ቀልብህ እንደቀረባት
መቃብር በመዳፉ
እንደ ጠጠር ሳይቀልባት
አፈሩን ሳትዛመድ
ወደ እማትቀባው አመድ
ወደ እማትስበው አየር
ሳትቀየር
አንተም አንደበት ሳለህ ፤ እሷም ጆሮ ሳያጥራት
ዛሬውኑ ! አሁንኑ! እንደምትወዳት ንገራት!!

@Simetin_Begitim
@Simetin_Begitim
⁉️

ይሄ የአንድ ጣልያናዊ ሰው ታሪክ ነው፡፡ እጅግ በጣም ረዘም ኣርጎ ዛሬ በሙሉ
የለይቶ ማቆያ ሁናቴ ውስጥ ያለችው ሀገሩ ከየት ተነስታ የት ደረሰች የሚለውን
ይናገራል፡፡ እንደወረደ ነው የተረጎምኩት፡፡ በየመሃሉ ስብር ስብር ማለቱን ችለህ
አንብብና ፍረድ፡፡

ዛሬም እንደትናንቱ ከጓደኞችህ ጋር ፈታ እያልክ ከሆነ፣ በሰው የተጨናነቁ ክለቦች ውስጥ ስትጨፍር እያነጋህ ከሆነ፡፡ ራስህን በመስታወት ተመልከትና ስርዓትህን መያዝ ጀምር፤ በሽታ በካልቾ እየጠለዘ ቤትህ ሳያስቀምጥህ፡፡ አለም ምን እየመጣባት እንደሆነ ገና ፍንጩም የላትም!!!" መቼም በዜና ሰምተሃል፣ ሙሉ ሀገሪቷ- ጣልያን-ራሷን በለይቶ ማቆያ ውስጥ
ከትታ፣ ከአለም ተገልላ ተቀምጣለች፡፡ በኮሮና ምክንያት፡፡ ሁኔታው በጣም መጥፎና አሳዛኝ ነው፡፡ ይበልጥ ልብ የሚሰብረው ግን፣ ቀሪው ኣለም " አይ እኔን አይነካኝም " በሚል ሀሳብ እጁን አጣጥፎ መቀመጡ ነው፡፡
ይሄንን የቀሪውን አለም ሀሳብ የማውቀው፣ እኛም ከሁለት ሳምንታት በፊት እናስበው ስለነበር ነው፡፡
ነገሮች ከየት ተነስተው የት እንደደረሱ፣ አሁን ምን ላይ እንዳለን፣ በየት በኩል
እንዳለፍን ደረጃ በደረጃ እንየው፡፡
ደረጃ አንድ... ኮሮና የሚባል ቫይረስ የሆነ ቦታ መኖሩን ሰምተሃል፡፡ አለ ብቻ፡፡ ከዛ የመጀመሪያዎቹ ተጠቂዎች በሀገርህ ብቅ ብቅ ማለት ይጀምራሉ፡፡ አንተ ግን ለትንሽዬ ጉንፋን ምንም ሀሳብ አይገባህም፡፡ "ገና ወጣት ነኝ፡፡ እድሜዬ ከ75 አልገፋ፡፡ ምን እሆናለሁ? ምንም!!!" " እኔን ምንም አያገኘኝ፡፡ ሰዉ ያለቅጥ
እያካበደ ነው፡፡ አሁን እኔ የፊት ማስክ እና የሽንት ቤት ሶፍት ልገዛ የሚገባኝ ሰው
ነኝ??? ኧረ በጭራሽ!!" " ከፈለገ ሰዉ ይነፋ እንጂ፣ እኔ ኑሮዬን እቀጥላለሁ፡፡"

ደረጃ ሁለት...

አንድና ሁለት እየተባለ የሰማኸው የበሽተኞች ቁጥር፣ እየጨመረ እየጨመረ ይሄዳል፡፡ መንግስትህ " አደገኛ ክልሎች" ብሎ የመጀመሪያዎቹ በሽተኞች ያሉባቸውን ጥቂት፣ ትናንሽ ከተሞች ይዘጋል- ለይቶ ማቆያ፡፡ ያገልላል፡፡ እነዚህ ከሌሎች ከተሞች የበለጠ የህመምተኛ ቁጥር ያለባቸው ናቸው፡፡
እንዲሄ ስትል ትሰማለህ፡፡ " ውይ ሰዎቹ በቃ ተገለሉ? ሲያሳዝን፡፡" ትንሽ ትንሽም
ቢሆን ያስጨንቅሃል፡፡ "ግን መንግስት ጉዳዩን ስለያዘው መደናገጥ
አያስፈልግም" የተወሰኑ ሰዎችን ህልፈት ትሰማለህ፡፡ ግን በእድሜ የገፉና በሞት አፋፍ ላይ የደረሱ ሰዎች ናቸው ብለህ ትፅናናለህ፡፡ እንደውም፣ ሚዲያው ለትርፍ እና ለእይታ ሲል ያሳያቸው ናቸው ፣ እነዚህ ወራዶች ብለህ ትወቅሳለህ፡፡
ህይወት መልኳን ሳትቀይር ትቀጥላለች፡፡ "ከጓደኞቼ ጋር እየተገናኘሁ ፈታ
ማለትማ አልተውም፡፡ እኔ!?? ኧረ በደንብ፡፡ ያለንበት አካባቢ ሰላም ነው፣ እኔን ኮሮና ከሚይዘኝ፣ ፍቅር ቢይዘኝ ይቀላል" እያልኽ ትቆያለህ.

ደረጃ ሶስት

የበሽተኞች ቁጥር መመንጠቅ ይጀምራል፡፡ በአንድ ቀን ውስጥ ብቻ በሁለት እጥፍ አድጎ ያድራል፡፡ የሟቾች ቁጥርም እንደዛው፡፡ የአደጋ ክልሎች ይታወጃሉ፡፡ በሀገራችን በሽታው በጣም የገነነባቸው ኣራት ክልሎች- የሀገሪቱ 25% የሚሆነው- ከሌሎች እንዲለዩና እንዲገለሉ ተወሰነ ( የካቲት-29)፡፡ በነዚህ ክልሎች ውስጥ ትምህርት ቤቶችና ዩኒቨርሲቲዎች ቢዘጉም፣ መጠጥ ቤትች፣ ሆቴሎችና የስራ ቦታዎች ክፍት ነበሩ፡፡ አንድ ውስጥ አዋቂ ነኝ የሚል ሀላፊነት የጎደለው ጋዜጣ፣ የመንግስትን ውሳኔ መንግስት ከመዘጋጀቱና ለህዝብ ከማሳወቁ በፊት ለህዝብ ይፋ አወጣው፡፡
በዚህም በተፈጠረው መደናገጥ፤ አደገኛ ተብለው ከተለዩት አራት ክልሎች
ውስጥ 10ሺ ሰዎች አምልጠው ወደ ቀሪው የጣልያን ክፍል ተበታተኑ- በአንድ
ለሊት ብቻ፡፡ የቀረው 75% የሀገሪቱ ህዝብ፣ ከዘወትር ተግባሩ አንዳች እንኳን ሳይስተጓጎል ኑሮውን ይመራል- ኮሽም አይልበት፡፡ በሀገሬ፣ አብዛኛው ህዝብ ገና የጉዳዩን ከባድነት አልተረዳም፡፡ በየመገናኛ ብዙሃኑ- እጃችሁን ታጠቡ፣ ህዝብ የሚበዛባቸው ቦታዎች መሄድ ቀንሱ፣ በብዛት እየሆናችሁ አትሰብሰቡ እየተባለ በየአምስት ደቂቃው ይነገራል፡፡ ጆሮ የሚሰጥ የለም፣ ከልቡ የሚያስቀምጥ
አልተገኘም፡፡

ደረጃ አራት

በሽታው እንደ ክፉ ወሬ እየተዛመተ ነው፤ የበሽተኛው ቁጥር ደግሞ ሀገሪቱን
እንደ ድንገተኛ ደራሽ እያጥለቀለቃት፡፡ በየክልሉ የሚገኙ ትምህርት ቤቶችና
ዩኒቨርሲቲዎች ቢያንስ ለ1 ወር ያህል እየተዘጉ ነው፡፡ መንግስት በሀገር ደረጃ
የድንገተኛ የጤና አደጋ ቀውስ ውስጥ መግባታችንን አውጇል፡፡ ሆስፒታሎች
በሙሉ አቅማቸው ህዝብ ያስተናግዳሉ፡፡ ሌሎች አገልግሎቶች ሁሉ ተዘግተው፣
የኮሮናን ታማሚዎች ብቻ እያስተናገዱ ነው፡፡ በቂ ሀኪምና ነርስ በሀገሪቱ የለም፡፡
በጡረታ የተገለሉና ትምህርታቸውን ለሁለት አመታትና ከዛ በላይ የተከታተሉትን ሁሉ እየቀጠሩ እየሰሩ ነው፡፡ በዚህ ወቅት፣ የማታ የቀን ተረኛ ነኝ ብሎ ነገር የለም፡፡ ሀኪም ከሆንክ መቆም የቻልክበትን ያህል ቆመህ ስራህን ትሰራለህ፡፡ ካለረፍት የሚያገለግሉት ሀኪሞች፣ በሽታው ይተርፋቸዋል፡፡ ወደ ቤተሰቦቻቸውም ይወስዱታል፡፡ በመተንፈሻ ህመም የሚሰቃዩ ፣ ነፍስ ውጪ ነፍስ ግቢ ውስጥ ያሉ ሌሎች በሽተኞች ቢኖሩም፣ ለሁሉም የሚበቃ መታከሚያ ቦታ የለም፡፡ እዚህ ጋ ስትደርስ፣ በቃ ይህ ሁኔታ ልክ እንደ ጦር ሜዳ ነው፡፡ ሀኪሞቹ የሚያክሙት የመዳን እድሉ የየትኛው ከፍ ያለ ነው በሚለው ላይ ብቻ ተመስርተው ነው፡፡ ይህ ማለት፣
አዛውንቶች፣ በእድሜና በጤና ሁኔታቸው የገፉ ሰዎች ይረሳሉ፣ ይተዋሉ፡፡
ቅድሚያ ለኮሮና ህመምተኞች፡፡
ለሁሉም የሚበቃ ሀኪምም የህክምና መገልገያም የለም፡፡ በቃ፡፡ ይሄ ሁሉ ጨዋታና ተረት አይደለም፡፡ በሀገሬ ሲከሰት ቆሜ የታዘብኩት እንጂ፡፡
ሰዎች በኮሮናም ይሁን በሌላ በሽታ ተይዘው፣ የመታከሚያ ቦታ በማጣት ብቻ
እየሞቱ ነው፡፡ አንድ ሀኪም ጓደኛዬ እጅግ በተሰበረ ልብ ሆኖ " ዛሬ ብቻ ሶስት
ሰዎች ሞቱብኝ " ብሎ ደውሎልኛል፡፡ ነርሶቹ ዘወትር እንባ እንዳፈሰሱ ነው፡፡
ምክንያቱም፣ ለህመምተኞች የተወሰነ ኦክስጅን ከመስጠት ውጪ ምንም እርዳታ የሚሰጡበት አቅም የላቸውምና፡፡
ትናንት አንድ የጓደኛዬን ዘመድ በሞት አጣን- በቃ የሚያክመው አላገኘም፡፡
ቀውስ ላይ ነን፡፡ ቀውስ፡፡ የገነባነው ስርዓት ወደ መፈራረስ ተቃርቧል፡፡
በምትሄድበት ሁሉ፣ የሚሰማውም የሚታየውም የኮሮና ቫይረስ ወሬ ነው፡፡ በቃ!!

ደረጃ አምስት

እነዛ 10ሺ ሰዎች ትዝ አሉህ፣ ከተለዩት ክልሎች ያመለጡት? በነሱ ምክንያት
ሙሉ በሙሉ ሀገሪቱ ራሷን በለይቶ ማቆያ ውስጥ ትከትት ዘንድ- ከቀሪው አለም ትቆራረጥ ዘንድ ግድ ሆኖባታል፡፡ ( የካቲት 30) የመለየቱ አላማ፣ የቫይረሱን ስርጭት መቀነስና መቆጣጠር ነው። ኣሁን... ዛሬ ሰዎች ወደ ስራ ይሄዳሉ፡፡ ገበያ ወጥተው ሸመታ ያከናውናሉ፡፡
መድሀኒት ይገዛሉ፡፡ የንግድ ቦታዎች ሁሉ ክፍት ናቸው፡፡ ያ ባይሆን የሀገሪቱ
ኢኮኖሚ ሽባ ይሆን ነበር፡፡( አሁንም ኢኮኖሚው እየተጎዳ መሆኑን የሚያሳዩ
ምልክቶች ቢኖሩም)፡፡ እንዲህም ቢሆን ግን አሳማኝ ምክንያት ሳይኖርህ ከቦታ
ቦታ መንቀሳቀስ አትችልም፡፡
የት ደረስን? በቂ የሆነ ፍርሀት ላይ ደርሰናል፡፡ ብዙ ሰዎችን የፊት "ጭምብል" እና የእጅ ጓንት አጥልቀው ታያቸዋለህ፡፡ ግን ደግሞ፣ "አይበገሬ" ነን የሚሉ የጅል ጀግኖች አሁንም እየተሰበሰቡ ወደ ሬስቶራንቶች ይሄዳሉ፡፡
ቀጥሎሳ? ከሁለት ቀናት በኋላ ሁሉም አይነት የንግድ እንቅስቃሴዎች እንዲቋረጡ ታዘዘ፡፡ መጠጥ ቤት የለ፣ ምግብ ቤት፣ ሱቅ... ምንም፡፡ ከመድሃኒት ቤቶችና ከሱፐርማርኬቶች በቀር ሁሉም ተዘጉ፡፡ አንተ እንኳን መንቀሳ
ቀስ የምትችለው የይለፍ ወረቀት ይዘህ ስትገኝ ነው፡፡ ደረጃ ስድስት... የይለፍ ወረቀቱ፣ ከመንግስት የሚሰጥ ሲሆን፤ ስምህን፣ ከየት እንደመጣህ፣ ወደየት እንደምትሄድና ጉዳይህ ምን እንደሆነ ይገልጻል፡፡ ቅርብ ለቅርብ የተሰደሩ የፖሊስ ኬላዎች አሁንም አሁንም ይፈትሹሃል፡፡ ያለ ፍቃድ ከተያዝክ 206ዩሮ ( 8000ብር አካባቢ) ትቀጣለህ፡፡ ያለፍቃድ የተያዝክ ህመምተኛ ከሆንህ ደሞ፣ ነፍስ ማጥፋት ወንጀል ተከስሰህ ከ1-12 አመት የእስር ግዜ ይጠብቅሃል፡፡
ዛሬ ሀገሬ እዚህ ደረጃ ላይ ደርሳለች፡፡
.
ወሬኣችንን ስንደመድም
ሀገራት በቸልተኝነት በግዴለሽነት ዜጎቻቸውን ከመጠበቅ ሲፎርሹ ማየት ያማል፡፡ የሚችሉትን ሁሉ ያላረጉ እንደሚቀጡበት ግልጽ ነው፡፡
ይህንን እያነበብክ ከሆነ ተለመነኝ፣ ለጤናህ ስትል የተነገረህን የጥንቃቄ እርምጃ ሁሉ ውሰድ፡፡ ስለጉዳዩ አላወራህም፣ ረስተኸዋል ማለት እሱ ረስቶሃል፣ በራሱ ግዜ ብን ብሎ ይጠፋል ማለት አይደለም፡፡ ማመን ያለብኝ አንድ ነገር፣ የጣልያን መንግስት-መንግስቴ- ይህንን በሽታ ለመቆጣጠር እጅግ የሚያስመሰግነው ስራ መስራቱን ነው፡፡ የተወሰዱት እርምጃዎች፣ ከልክ ያለፉና፣ ያልተመጣጠኑ ቢሆኑም፣ እጅግ አስፈላጊ ነበሩ፡፡ ስርጭቱን ለመቀነስ ያለው ብቸኛ መንገድ ይኸው ብቻ ነው፡፡ ቻይናን ጠቅሟታል፡፡ ለእኛም ይጠቅመናል ብለን እናስባለን፡፡ መጀመሪያ ወደ ማግለያ በገቡት የእኛም ክልሎች ላይ ውጤት እየተገኘ እንደሆነ ሰምተናል፡፡ የሀገሪቱ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ በመቆሙ ምክንያት፣ መንግስት ድጎማ እያደረገ
ይገኛል፡፡ የቤት ተከራይ ዜጎቹን፣ ሱቃቸውን በኪራይ የያዙ ነጋዴዎችን ወጪ እየሸፈነ ይገኛል፡፡ ይሄንን በሌሎች ሀገራት ማስፈጸም ከባድ እና የማይታሰብ ሊመስል ይችላል፡፡ ሁኔታውን ከሀገሬ ድንበር አሳልፌ ሳየው ግን እጅግ እሰጋለሁ፡፡ ውስጥ እጅ የሚያልብ ድንጋጤ ይወርሰኛል፡፡ የማህበረሰባችንን አኗኗር ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ የሚቀይር መዓት መጣብን ይሆንን? እላለሁ፡፡ ይሄንን ብቻ ስማኝ
ባለህበት አካባቢ በበሽታው የተያዘ ሰው ከተገኘ፣ ቫይረሱ እየተስፋፋ ነው ማለት
ነው፡፡ አሁን የእኔ ሀገር ያለችበት ለመድረስ ሁለት ሳምንት ይበቃሃል፡፡ ዞሮ ዞሮ የእኛ እጣ እጣህ ነው፡፡
የምትችለውን ሁሉ ተጠንቀቅ፡፡
ከሁሉ በላይ ደግሞ እኔን አይነካኝም ብለህ አትበጥ፡፡ ከቻልህ ቤትህን ዘግተህ ተከርቸም፡፡

©ወግ ብቻ
#biniam teshome
TIKVAH-MAGAZINE:
ወጣት መሀመድ እቢኑ መሀመድ አል አሩሲ

ነዋሪነቱ እዚሁ ኢትዮጵያ ሲሆን በሳዑዲ ዓረቢያ መካ ተወልዶ እዛው ትምህርቱን ተከታትሏል። መሀመድ የመንግስት ሰራተኛም፣ ዲፕሎማትም፣ ባለስልጣንም፣ አምባሳደርም አይደለም። ስልጠናም አላገኘም፣ ከመንግስትም ምንም አይነት ልዩ መረጃም አልተሰጠውም።

ነገር ግን በቅርቡ በህዳሴ ግድብ ዙሪያ በቲዊተር ገፁ፣ BBC Arabic ፣ Aljazeera Arabic፣ Asharq ከሚባሉት በዓለማችን በተለይም በዓረቡ ዓለም ታላላቅ ሚዲያዎች ላይ በራሱ ተነሳሽነት በመቅረብ የአፍ መፍቻው በሆነው በዓረበኛ ቋንቋ እጅግ በሚያስገርም ሁኔታ ሀገራችን በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ያላትን አቋም ለዓረቡ ዓለም በማስረዳት ላይ ይገኛል።

ከተሳተፈባቸው ውይይቶች መካከል:
https://youtu.be/o8vQ3ktvXYE
https://youtu.be/LQQf0w0j4SM
https://www.facebook.com/Tateknegni1/videos/847187225706269/
https://youtu.be/6i3ZX_GczQQ
https://youtu.be/JvcaPKvgSBA

[ Sultan Aba Gissa ~ Elias Meseret ]
Forwarded from ዝንቅ መዝናኛ (Mr. Nobody) via @like
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
😂😁😁😂

Credit - Selamina (ቡቢዬ)

@ZiniQ ዝንቅ መዝናኛ