ኢትዮጵያዊ ወጎች #Ethiopian
1.34K subscribers
314 photos
3 videos
18 files
50 links
Download Telegram
3.3K ቤተሠብ ስለ ኢትዮጵያዊነት እና ስለኢትዮጵያ ብቻ ወጋቸው ያደረጉ አባላት አፍርተናል ፡፡ ወጋችን ኢትዮጵያ ብቻ ናት ስለ ኢትዮጵያ ኑ አብረን እንስበክ ፡፡ ኢትዮጵያ እንደ ተራ የመንደር አጥር ምትፈርስ ሳይሆን ከፀና አለት የተሠሰራች ግንብ ናት ፡፡ አናፂዋም ስለ ኢትዮጵያ መቼም አያንቀላፋም ፡፡

ለወዳጅዎ #share በማድረግ ብዙ ወዳጆችን አብረን እናፍራ፡፡ ግጥም ፣ አስተማሪ ፅሁፎች ካላችሁ በ @Simetin_Begitimbot እና @Haile_melekot ይላኩልን፡፡

ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ተከብራ ትኑር 🇪🇹🇪🇹🇪🇹

@Simetin_Begitim
መውደቅን ሳይሆን አለመነሳትን ፍራ ፡፡ አለም ላይ ሀያል እሚባሉ ሀገሮች ሰዎች ሁላ ብዙ የውድቀት ታሪክ አላቸው ፡፡ ነገር ግን ውድቀትን እንደ ጥሩ አጋጣሚ ተጠቅመው ስህተታቸውን አርመው አንቱ ለመባል በቅተዋል ፡፡ እኛ ኢትዮጵያውያን ግን ከውድቀት ወደ ውድቀት እያመራን በስንፍና እና በሞቀ ድህነት ውስጥ ተጠቅልለን እየተኛል የ3000 ዓመት ታሪክ ባለቤት ነን እያልን እንኩራራለን ፡፡ ወዳጄ ሆይ ንቃ አንቺም እህቴ ንቂ አሁን እያመራን ያለነው ወደ ቁልቁለት ነው ሳላማችን ቁልቁል እየሄደ ነው ጨዋነታችን ቁልቁል ተመዘግጎ ገደል ገብቷል ወድቆ መነሳት ከታሪካችንም እሚከብደን ስለሆን እንንቃ የኢትዮጵያ ቤዛ አዲሱ ትውልድ ነው ከታሪክ ተምሮ እና መርምሮ ካለንበት የውድቀት ጎዳና እሚሻግረን የአዲሲቱ ኢትዮጵያ ቤዛ ወጣቶች ናቸው ፡፡
🇪🇹ኢዲሲቷ ኢትዮጵያ እኔ ነኝ🇪🇹
🇪🇹ወድደቅ መሸነፍ አይደለም🇪🇹
🇪🇹የኢትዮጵያ ቤዛ እኔ ነኝ 🇪🇹🇪🇹

#ኢትየጵያ ለዘለዓለም ተከብራ ትኑር!
#ይህን መልክት #Share በማድረግ ለወዳጅዎ የጋሩ
@Simetin_Begitim
#ኢትዮጵያዊ
#ወጎች
👌ግጥም
👌ወግ
👌ትምህርታዊ ፅሁፎች
እና ስለ ኢትዮጵያዊነት ብቻ እምናወጋበት Channel ወጋችን ኢትዮጵያ ብቻ ናት በቅንነት ለወዳጅዎ #Share ያድርጉ ፡፡

@Simetin_Begitim
ውድድሩ ሊያልቅ የቀረው 28 ደቂቃዎች ብቻ ነው የውጤት ለውጥ እንዲኖር #Share ያድርጉ፡፡

@Simetin_Begitim
ለውብ ቀን💚💛❤️
የሙላ ናስሩዲን ጫወታ

ናስሩዲን አንዳንዴ እንደ ሞኝ ይቁጥሩት የለ ፤ አንድ ቀን
የሚያውቁት ሰዎች መንገድ ዳር ቆመው " ነስሩ የፍርድ
ቀንኮ ከሳምንት በኃላ ነው .. እ ለምን ንብረት ሁሉ
የማይጠቅምህ ከሆነ ከፍየሎችህ አንድ ሁለቱን አርደህ
አትጋብዘንም " ይሉታል :: "መርሃባ" አለ ነስሩዲን :: ቤት
ወሰዳቸው ::
ወቅቱ ይወብቅ ነበርና ከቀሚስ ውጪ የደረቡትን ካባ እና
ጥምጣም አንደኛው ክፍል አስቀምጠና ወደ ኸልዋ አመሩ
፤ ፍየሎቹ ተገፈው ተጠብሰው ማዕዱ እስኪመጣ ሊጠብቁ
..
ተበላ ፥ ተጠጣ .. ሊሄዱ ፈለጉ ካባቸው ቢፈለግ የለ ፥
ጥምጣም የለ .. ናስሩዲንን ጠየቁት
"እሳቱን ለማቀጣጠል ከእንጨትጋ ጨምሬዋለሁ"
"ለምን ??" ተበሳጭተው
"የፍርድ ቀንኮ ከ
ሳምንት በኃላ ነው .. ካባ አይጠቅም ወላ
ጥምጣም "::
ሠናይ ውሎ ውብ ቀን
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ተከብራ ትኑር

@Simetin_Begitim #Share
#ለሰላም_የምችለውን_ሁሉ_አደርጋለሁ!

1ሚሊዮን ተከታይ የለኝም። ቢያንስ እያንዳንዳቸው 1000 ጓደኛ ያላቸው እስከ 5000 ጓደኞች ግን አሉኝ።

#ከዛሬ_ጀምሮ_በሃገሬ_ጉዳይ_ዳር_ቁጭ_ብዬ_ተመልካች_ላለመሆን_ቃል_እገባለሁ

እናንተስ?

#ሰላምለኢትዮጲያ
#PeaceForEthiopia

#ሼር #share
አብዛኛዎቹ የዓለም ሀገራት ወደ ቻይና የሚያደርጉትን በረራ አቁመዋል፡፡ የኛው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግን እስከዛሬዋ ቀን ድረስ አላቆመም ፡፡ ይህ ገዳይ ቫይረስ ወደ ኢትዮጵያ ቢገባ ተጠያቂው አንድና አንድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ነው ፡፡ ሀገራችን እያጋጠማት ያለው የፖለቲካ ቀውስ ሳያንስ ደህና ጤና ጠቢያ እንኳን የሌላት ሀገራችን እንዲህ አይነት ወረርሽኝ ገባ ማለት በታሪካችን የማንወጣው በችግር ላይ ችግር በሀዘን ላይ ሀዘን በቀውስ ላይ ቀውስ ነው የምናየው እሡንም በህይወት ከተረፍን ፡፡ እናም እንደኔ እይታ ከሆነ አየር መንገዳችን በቶሎ እርምጃ መውሰድ አለበት ፡፡
#Share
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
#ሼር #SHARE

የኮሮና ቫይረስ ምልክቶች፦

COVID-19 በትኩሳት እና ደረቅ ሳል ይጀምራል። ከሳምንት በኋላ የመተንፈስ ችግር ያጋጥማል። በበሽታው የተያዘ ሰው እስከ 14 ቀናት ምንም አይነት ምልክት ላያሳይ ይችላል። አንዳንድ ሰዎች የበሽታ ምልክት ሳያሳዩ በሽታውን ሊያስተላልፉ ይችላሉ።

ኮሮና ቫይረስ መድሃኒት አለው?

ቫይረሱን ከሰውነት ውስጥ የሚያስወግድ መድሃኒት የለም። ሃኪሞች በሽተኞችን እያከሙ የሚገኙት የታማሚዎችን የበሽታ የመከላከል አቅምን ከፍ በማድረግ ነው።
ለመተንፈስ የሚረዱ ቁሶችም ጥቅም ላይ ይውላሉ።

እራሴን ከቫይረሱ እንዴት ነው መጠበቅ የምችለው?

የዓለም ጤና ድርጅት የሚከትሉትን እንዲያደርጉ ይመክርዎታል፦

- እጅዎን ይታጠቡ- ቫይረሱን ሊገድሉ በሚችሉ ሳሙናዎች

- በቫይረሱ የተበከሉ ነገሮችን ሊነኩ ስለሚችሉ፤ በእጅዎ ዓይን፣ አፍ እና አፍንጫዎን ከመነካከት ይቆጠቡ።

- ወደ የሚያስነጥሱ፣ የሚያስሉ እና ትኩሳት ወዳለባቸው ሰዎች አይጠጉ። ቢያንስ የ1 ሜትር እርቀት ይፍጠሩ።

- ሲያስሉ እና ሲያስነጥሱ አፍ እና አፍንጫዎን ይሸፍኑ - ከዚያም እጅዎን ይታጠቡ። ይህን ማድረግዎ በቫይረሱ ተይዘው ከሆነ የማሰራጨት ዕድልዎን ያጠባሉ።

በቫይረሱ እርሶ ወይም ሌሎች መያዛቸውን ከተጠራጠሩ፦ እራሰዎን ያግልሉ፤ በቤትዎ ይቆዩ ሌሎችም ተመሳሳይ እንዲያደርጉ የበኩልዎን ይወጡ። 8335 ላይ በመደወል ለማሕብሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በፍጥነት ያሳውቁ።

ምንጭ፦ BBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
መደናገጥ እና አጉል ፍራቻ፣ ከበሽታው እኩል አደገኛ ሊሆኑ ይችላሉ!

ጠቃሚ ምክሮች፦

- ሳል ወይም ትኩሳት ካለው ግለሰብ ቢያንስ ሁለት የአዋቂ እርምጃ ርቀት ያህል መራቅ
- እጅዎን በአግባቡ ሳይታጠቡ አይንና አፍንጫዎን አይንኩ
- ከሰዎችጋር አይጨባበጡ፣
- እጅን በንጹህ ውሃና ሳሙና አዘውትረው ይታጠቡ፣
- ሰዎች ወደ በሚበዙባቸው ቦታዎች በተለይም የህመም ስሜት ካልዎት አይሂዱ፣
- በሚያነጥሱበት እና በሚያስሉበት ጊዜ አፍና አፍንጫዎን በሶፍት ወይም ክርንዎን አጥፈው በመጠቀም ወደ ሌሎች እንዳያስተላልፉ ይጠንቀቁ፣ የተጠቀሙበትን ሶፍትና ተመሳሳይ ነገሮች በቆሻሻ ክዳን ባላቸው ማጠራቀሚያ ያስወግዱ፣
- በስራ ቦታ፣በትራንስፖርት እና መኖሪያ ወይም የመኝታ ክፍል መስኮት በመክፈት በቂ አየር እንዲኖር ያድርጉ፣
- መረጃዎችን ከአስተማማኝ ምንጮች ብቻ በመቀበል፣ የተሳሳቱ መረጃዎች የሚያስከትሉትን መደናገር እና ፍርሀት እርሶም ይከላከሉ!

#ሼር #SHARE

#ጤናሚኒስቴር
የጠቅላይ ሚኒስትሩ መልዕክት፦

በአገራችን በዛሬው እለት አንድ ኮሮና ቫይረስ ያለበት ሰው የተገኘ በመሆኑ ህብረተሰቡ እነዚህን ምክሮች በመከተል እራሱን እና ቤተሰቦቹን ከበሽታው እንዲከላከል አሳስባለሁ።

- እጃችንን በውሃ እና በሳሙና አዘውትሮ መታጠብ

- የጉንፋን ምልክት ከታየብን ከቤት አለመውጣት፣ ሰው የሚበዛብት ቦታ አለመሄድ

- ንክኪ የሚያስፈልጋቸው የሰላምታ መንገዶችን መተው

- ሰው በብዛት የሚሰበሰብባቸው ቦታዎች ላይ የሚገኙ ከሆነ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ

- ህብረተሰቡ ሳይደናገጥ በንቃት የራሱን እና የቤተሰቡን ጤና መጠበቅ

#DrAbiyAhmed

#Share