#Meron_Getnet
በሜሮን ጌትነት
"አበበ በሶ በላ
ጫላ ጩቤ ጨበጠ
ጨቡዴ ጣሳ አጠበ"
ሲሉን መምህራችን
ያንን መድገም ነበር ዋና
ተግባራችን
ከዓረፍተ ነገሩ ስኬት የዘለለ
ጠያቂም ተማሪ መሀላችን የለ
ፈተናም ሲመጣ...
ያችኑ ከመድገም የለም ሌላ
ጣጣ
አበበ ዳሽ በላ ዳሽ ጩቤ
ጨበጠ
ቢበዛ ቢበዛ ዓረፍተ ነገሩ
የተገለበጠ
ኋላ ግን ተማሪ ያሉትን
ከመድገም ከመከትል ወጥቶ
መጠየቅ ሲጀምር የሀሳቡን
መሰረት ይዘቱን አጥንቶ
አበበም ጨቡዴም ጠፉ ደግነቱ
ጫላንም ሰረዘው ስርዓተ
ትምህርቱ
እንጂ በዚያ ክፍል ለነበር
ተማሪ
የጊዜው ፈተና ሆኖ አደናጋሪ
"አበበ በላ የሚለው
በቀን ስንት ጊዜ ነው?
ሶስት ጊዜ ከበላ ምርታማ
ሆኗል ገበሬ
ማዳበሪያ ተጠቅሞ ገቢ
ጨምሯል ሀገሬ
እንዴት አድርጎ ነው የበላ?
ጭብጦዎቹ ስንት ናቸው?
ክልሎችን የሚወክል ይሆናል
ወይ ብዛታቸው?
በሶው ራሱ ሲታይ ገና
ከአፈጫጨቱ
ልሟል ወይስ ሽርክት ነው?
በደንብ ይጠና ዱቄቱ
አስፈጪዎችን ገምግሙ ...
የአፈፃፀም ችግርም ይኖረዋል
ወፍጮ ቤቱ
ጫላ ጩቤ ሲጨብጥ ዝም
ይባላል ወይ ታይቶ?
ወይስ በሽብር ይከሰሳል
ከወይህኒ ቤቱ ገብቶ
የትምክት ነው የጠባብነት
ጩቤውን አጨባበጡ?
ብለው ነበር እኚያ ሰውዬ
'በሳንጃ ይወጋ ቂጡ'
ርዝራዥ ነው የቀድሞ የሳቸው
ስርዓት ናፋቂ
ልማቱን አደናቃፊ የሽብር
ጩቤ ነቅናቂ!
ጨቡዴስ የሚያጥበው ጣሳ
ምንድነው አገልግሎቱ?
ጠላ ሊሸጥበት ነው? ውሃ
ሊቀዳ ልፋቱ?
ወጣም ወረደ ያተርፋል ስንት
ይክፈል ግብር በወቅቱ?"
ይልና በጥያቄ ውስጥ ምላሹን
ራሱ አብራርቶ
ተማሪውን ይሞግታል
በመደምደሚያው ፀንቶ
አበበን ለበሶ ጠርቶ
ለምግብ ለጥጋብ አጭቶ
ጫላን ጩቤ ማስጨበጥ
ጨቡዴን አጣቢ ብሎ
ህገ መንግስት ይፃረራ ይባላል
የብሄር መድሎ!
. . .
አበበ በሶ በላ
ጫላ ጩቤ ጨበጠ
ጨቡዴ ጣሳ አጠበ"
ሲሉን መምህራችን
ያንን መድገም ነበር ዋና
ተግባራችን
ከዓረፍተ ነገሩ ስኬት የዘለለ
ጠያቂም ተማሪ መሀላችን የለ
ግና በዚያ ሰሞን የነበር ተማሪ
የጊዜው ፈተና ሲሆን አስቸጋሪ
ጥያቄ አስቀይሮ መልስ
እንደማቃናት
ስህተቱን ሊያርም በሌላ
ስህተት
የምናብ እውነቱን ከሃቁ
ደባልቆ
መምህር ይሞግታል ከተፈታኙ
ፊት ፈተናውን ሰርቆ
"አበበ በላ" ለሚለው...
"ከየት አምጥቶ ይበላል? ረሀብ
ገብቶ በሀገሩ
አደግን ሊሉን ነው እንጂ አሀዝ
እየጨመሩ
አበበማ እንዴት ይበላል በሶውን
የት አስፈጭቶ?
አንድ ወር አለፈው አሉ
መብራት ከቀረ ጠፍቶ
የወፍጮ ቤቱን ወርፋ ሲጠብቅ
ሲጠብቅ ከርሞ
አልደርስ ሲል ጨረሰው
ጥሬውን እህል ቆርጥሞ
በዚህ ምክንያት አበበ ስለተኛ
ሆዱን ታሞ
መብት አስጠባቂ ድርጅት
ያጣራ ጉዳዩን ቀርቦ
ጫላ ጩቤ ጨበጠ
ምድር ተገለበጠ
ጨቡዴ ጣሳ እያጠበ የዕለት
ጉርሱን ከሸፈነ
ከጠላ ጠጪ ተወዳጀ ከባለጊዜ
ወገነ"
በሚል የፅንፍ ሃሳብ መልሱን
አዘጋጅቶ
ይወድቃል ተማሪ ከአስር ዜሮ
አምጥቶ
. . .
አበበ በሶ በላ
ጫላ ጩቤ ጨበጠ
ጨቡዴ ጣሳ አጠበ"
ሲሉን መምህራችን
ያንን መድገም ነበር ዋና
ተግባራችን
ዘንድሮ ትምህርቱ በኖረ ፖሊሲ
መምህሩን ቀይሮ
ፈተና ያደቆነው ተማሪ ደርድሮ
ሊያስተምር ይተጋል የየኔታን ሀ
ሁ በፍቅር ቀምሮ
ተማሪውም ነቅቷል!
ደርዝ ያለው ጥያቄ ስንል ደርሶ
ይበዛል
አልፈተን ባዩ ቀድሞ መምህር
ያዛል
'በአንድነት ተባበር የቤት ስራ'
ሲባል በትር ይማዘዛል::
"አበበ በሶውን ቋጥሮ ...ጫላም
ጬቤ እንደጨበጠ
ጨቡዴም በባዶ ጣሳ
በህብረት ለለውጥ ይነሳ!"
ተብሎ በሶ ለመብላት የጋራ
ገበታ ቀርቧል
ትልቅ መዳፍ አለኝ ባይ....
ሳህን ሙሉ በሶ ዱቄት በአንድ
ጭብጥ ይተምናል
ሌላው በሌላ በኩል...
'ጭብጦዬን ቀሙኝ' ብሎ
በተራው ጨባጭ ይከሳል
የባሰበት 'ብላ' ሲሉት በመብቱ
መጠጥ ይመርጣል
ከዱቄቱ እፍኝ ወስዶ በሶውን
ይበጠብጣል
በዚህ ሁሉ መሀል...
በፅንፈኞች ሀሳብ በግራና በቀኝ
አጉል ተወጥሮ
ሊዛመድ በማይችል; ምርጫ
ባልተሰጠው ጥያቄዎች ታጥሮ
'እውነት/ውሸት' የሚል
አማራጭ ሲፈልግ ከሞኝ
ተቆጥሮ
ጠያቂ ተማሪ በሁለት ጥይት
ሞተ ከመሀል ቤት ሰፍሮ
የአበበ በሶ የጫላ ጬቤና
የጨቡዴ ጣሳ
በየፖለቲካው እየተጣመመ
ሲወድቅ ሲነሳ
"ትምህርት" ይሉት ነገር...
ይኸው ሆኖ አረፈው ለመምህር
ፈተና ለተማሪ አበሳ!
©kinchebchabi
@Simetin_Begitim
በሜሮን ጌትነት
"አበበ በሶ በላ
ጫላ ጩቤ ጨበጠ
ጨቡዴ ጣሳ አጠበ"
ሲሉን መምህራችን
ያንን መድገም ነበር ዋና
ተግባራችን
ከዓረፍተ ነገሩ ስኬት የዘለለ
ጠያቂም ተማሪ መሀላችን የለ
ፈተናም ሲመጣ...
ያችኑ ከመድገም የለም ሌላ
ጣጣ
አበበ ዳሽ በላ ዳሽ ጩቤ
ጨበጠ
ቢበዛ ቢበዛ ዓረፍተ ነገሩ
የተገለበጠ
ኋላ ግን ተማሪ ያሉትን
ከመድገም ከመከትል ወጥቶ
መጠየቅ ሲጀምር የሀሳቡን
መሰረት ይዘቱን አጥንቶ
አበበም ጨቡዴም ጠፉ ደግነቱ
ጫላንም ሰረዘው ስርዓተ
ትምህርቱ
እንጂ በዚያ ክፍል ለነበር
ተማሪ
የጊዜው ፈተና ሆኖ አደናጋሪ
"አበበ በላ የሚለው
በቀን ስንት ጊዜ ነው?
ሶስት ጊዜ ከበላ ምርታማ
ሆኗል ገበሬ
ማዳበሪያ ተጠቅሞ ገቢ
ጨምሯል ሀገሬ
እንዴት አድርጎ ነው የበላ?
ጭብጦዎቹ ስንት ናቸው?
ክልሎችን የሚወክል ይሆናል
ወይ ብዛታቸው?
በሶው ራሱ ሲታይ ገና
ከአፈጫጨቱ
ልሟል ወይስ ሽርክት ነው?
በደንብ ይጠና ዱቄቱ
አስፈጪዎችን ገምግሙ ...
የአፈፃፀም ችግርም ይኖረዋል
ወፍጮ ቤቱ
ጫላ ጩቤ ሲጨብጥ ዝም
ይባላል ወይ ታይቶ?
ወይስ በሽብር ይከሰሳል
ከወይህኒ ቤቱ ገብቶ
የትምክት ነው የጠባብነት
ጩቤውን አጨባበጡ?
ብለው ነበር እኚያ ሰውዬ
'በሳንጃ ይወጋ ቂጡ'
ርዝራዥ ነው የቀድሞ የሳቸው
ስርዓት ናፋቂ
ልማቱን አደናቃፊ የሽብር
ጩቤ ነቅናቂ!
ጨቡዴስ የሚያጥበው ጣሳ
ምንድነው አገልግሎቱ?
ጠላ ሊሸጥበት ነው? ውሃ
ሊቀዳ ልፋቱ?
ወጣም ወረደ ያተርፋል ስንት
ይክፈል ግብር በወቅቱ?"
ይልና በጥያቄ ውስጥ ምላሹን
ራሱ አብራርቶ
ተማሪውን ይሞግታል
በመደምደሚያው ፀንቶ
አበበን ለበሶ ጠርቶ
ለምግብ ለጥጋብ አጭቶ
ጫላን ጩቤ ማስጨበጥ
ጨቡዴን አጣቢ ብሎ
ህገ መንግስት ይፃረራ ይባላል
የብሄር መድሎ!
. . .
አበበ በሶ በላ
ጫላ ጩቤ ጨበጠ
ጨቡዴ ጣሳ አጠበ"
ሲሉን መምህራችን
ያንን መድገም ነበር ዋና
ተግባራችን
ከዓረፍተ ነገሩ ስኬት የዘለለ
ጠያቂም ተማሪ መሀላችን የለ
ግና በዚያ ሰሞን የነበር ተማሪ
የጊዜው ፈተና ሲሆን አስቸጋሪ
ጥያቄ አስቀይሮ መልስ
እንደማቃናት
ስህተቱን ሊያርም በሌላ
ስህተት
የምናብ እውነቱን ከሃቁ
ደባልቆ
መምህር ይሞግታል ከተፈታኙ
ፊት ፈተናውን ሰርቆ
"አበበ በላ" ለሚለው...
"ከየት አምጥቶ ይበላል? ረሀብ
ገብቶ በሀገሩ
አደግን ሊሉን ነው እንጂ አሀዝ
እየጨመሩ
አበበማ እንዴት ይበላል በሶውን
የት አስፈጭቶ?
አንድ ወር አለፈው አሉ
መብራት ከቀረ ጠፍቶ
የወፍጮ ቤቱን ወርፋ ሲጠብቅ
ሲጠብቅ ከርሞ
አልደርስ ሲል ጨረሰው
ጥሬውን እህል ቆርጥሞ
በዚህ ምክንያት አበበ ስለተኛ
ሆዱን ታሞ
መብት አስጠባቂ ድርጅት
ያጣራ ጉዳዩን ቀርቦ
ጫላ ጩቤ ጨበጠ
ምድር ተገለበጠ
ጨቡዴ ጣሳ እያጠበ የዕለት
ጉርሱን ከሸፈነ
ከጠላ ጠጪ ተወዳጀ ከባለጊዜ
ወገነ"
በሚል የፅንፍ ሃሳብ መልሱን
አዘጋጅቶ
ይወድቃል ተማሪ ከአስር ዜሮ
አምጥቶ
. . .
አበበ በሶ በላ
ጫላ ጩቤ ጨበጠ
ጨቡዴ ጣሳ አጠበ"
ሲሉን መምህራችን
ያንን መድገም ነበር ዋና
ተግባራችን
ዘንድሮ ትምህርቱ በኖረ ፖሊሲ
መምህሩን ቀይሮ
ፈተና ያደቆነው ተማሪ ደርድሮ
ሊያስተምር ይተጋል የየኔታን ሀ
ሁ በፍቅር ቀምሮ
ተማሪውም ነቅቷል!
ደርዝ ያለው ጥያቄ ስንል ደርሶ
ይበዛል
አልፈተን ባዩ ቀድሞ መምህር
ያዛል
'በአንድነት ተባበር የቤት ስራ'
ሲባል በትር ይማዘዛል::
"አበበ በሶውን ቋጥሮ ...ጫላም
ጬቤ እንደጨበጠ
ጨቡዴም በባዶ ጣሳ
በህብረት ለለውጥ ይነሳ!"
ተብሎ በሶ ለመብላት የጋራ
ገበታ ቀርቧል
ትልቅ መዳፍ አለኝ ባይ....
ሳህን ሙሉ በሶ ዱቄት በአንድ
ጭብጥ ይተምናል
ሌላው በሌላ በኩል...
'ጭብጦዬን ቀሙኝ' ብሎ
በተራው ጨባጭ ይከሳል
የባሰበት 'ብላ' ሲሉት በመብቱ
መጠጥ ይመርጣል
ከዱቄቱ እፍኝ ወስዶ በሶውን
ይበጠብጣል
በዚህ ሁሉ መሀል...
በፅንፈኞች ሀሳብ በግራና በቀኝ
አጉል ተወጥሮ
ሊዛመድ በማይችል; ምርጫ
ባልተሰጠው ጥያቄዎች ታጥሮ
'እውነት/ውሸት' የሚል
አማራጭ ሲፈልግ ከሞኝ
ተቆጥሮ
ጠያቂ ተማሪ በሁለት ጥይት
ሞተ ከመሀል ቤት ሰፍሮ
የአበበ በሶ የጫላ ጬቤና
የጨቡዴ ጣሳ
በየፖለቲካው እየተጣመመ
ሲወድቅ ሲነሳ
"ትምህርት" ይሉት ነገር...
ይኸው ሆኖ አረፈው ለመምህር
ፈተና ለተማሪ አበሳ!
©kinchebchabi
@Simetin_Begitim