፮ ኪሎ ግቢ ጉባኤ
2.43K subscribers
2.86K photos
42 videos
355 files
172 links
ይህ የ፮ ኪሎ ግቢ ጉባኤ ህጋዊ የቴሌግራም ቻናል ነው።
This is the official Channel of 6 kilo Gibi Gubae.
በግቢ ጉባኤው ላይ ያለዎትን አስተያየት ወይም ጥያቄ በ @fesehatsion12 ወይም @Hoping7 ላይ ይላኩልን።
Download Telegram
Forwarded from Addisu Teshome
የማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና ለደግ ሚድዋይፍሪ ኮሌጅ ግቢ ጉባኤያት ያስተማራቸውን 1088 ተማሪዎች አስመረቀ።

በውብሸት መገርሳ
++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++

የማኅበረ ቅዱሳን አዲስ አበባ ማእከል በአራዳ ጉለሌ ወረዳ ማእከሉ ስር በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 4ኪሎ፣ 5ኪሎ፣ 6ኪሎ እንዲሁም የማታ እና ለደግ ሚድዋይፍሪ ኮሌጅ ግቢ ጉባኤያት ያስተማራቸውን 1088 የግቢ ጉባኤ አባላት በዛሬው ዕለት በመንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ ቤ/ክ አስመርቋል፡፡

ተመራቂዎቹ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ቆይታቸው በግቢ ጉባኤ የሚሰጡትን መንፈሳዊ ትምህርቶች በሚገባ የተከታተሉ መሆናቸው የተጠቆመ ሲሆን ከ1088ቱ ተማሪዎች ውስጥ 59ኙ የማዕረግ ተማሪዎች መሆናቸውም ተገልጿል፡፡

በምረቃት መርሐ ግብሩ ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ የምዕራብ ካናዳ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ተገኝተው ለተመራቂ ተማሪዎች የእንኳን ደስ አላችሁ እና የአደራ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
@mahibere kidusan Broadcast service
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!

ውድ የግቢ ጉባኤያችን ልጆች እንዴት ናችሁ?🙏🙏

ግቢ ጉባኤያችን ከማህበረ ቅዱሳን ጋር በመሆን በክረምቱ ቤተሰብ መሄድ ለማይፈልጉ(አዲስ አበባ መቆየት ለሚፈልጉ) ተማሪዎች ልዩ የሆነ እድል አዘጋጅቷል::
እድሎችም

👉 አብነት ትምህርት ማስተማር ለምትችሉ
👉 ስነ ምግባር ማስተማር ለምትችሉ (የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፣ክርስቲያናዊ ስነ ምግባር……
👉 መዝሙር ማስጠናት ለምትችሉ

ከላይ👆 በተዘረዘሩት በእያንዳንዳቸው ሶስት(3) ሰው ይፈልጋል

‼️‼️የሚያስፈልጉ ነገሮችና የስራ ሁኔታ
👉 የስራ ጊዜ:- ክረምቱን
👉ሲገቡ interview ይኖረዋል
👉ከአገልግሎት በተጨማሪ የተወሰነ ክፍያ ይኖረዋል
👉 የምዝገባ ቦታ:- ማህበረ ቅዱሳን 4ኛ ፎቅ የልማት ተቋማት/አዲስ አበባ ማዕከል ጽ/ቤት
👉 የምዝገባ ቀን ከ03/11/2016 ጀምሮ እስከ 05/11/2016

ሌሎች መረጃዎች በቦታው ተገኝታችሁ መጠየቅ ትችላላችሁ

ቀድሞ ለሚመዘገብ እድሉ ሰፊ ስለሆነ ቀድሞ መመዝገብን አትዘንጉ!!!

©፮ ኪሎ ግቢ ጉባኤ
🌹እንኳን ለብርሃናተ ዓለም ቅዱስ ጴጥሮስ ወቅዱስ ጳውሎስ ሰማዕት ለሆኑበት ዕለት በሰላም አደረሰን!🌹
ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ

ልደቱ በገሊላ ባሕር ዳር በቤተሳይዳ ሲሆን አባቱ ከሮቤል ነገድ የሆነ ዮና የሚባል ሰው ነው። ሪዛምና በማናቸውም ነገር ፈጣንና ቀልጣፋ የነበረ ይህ ሰው የመጀመሪያ ስሙ ስምዖን ይባላል፣ ይህም በእናቱ ነገድ ስም የወጣለት ነው። በጐልማሳነቱ እድሜም ከወንድሙ ከእንድርያስ ጋር በገሊላ ባሕር ዓሳ በማሥገር ያሳልፍ ነበር።

ከዕለታት በአንዱ ቀንም በገሊላ ባሕር አጠገብ ዓሳ በማጥመድ ላይ ሳሉ ጌታችን "ሰው አጥማጆች አደርጋቹ ዘንድ ተከተሉኝ" አላቸው። እነሱም መረባቸውን ትተው፣ ታንኳቸውን ጥለው ተከተሉት [ማቴ ፬ ÷ ፲፰]። በዚህ ጊዜ ስምዖን እድሜው ፶፭  ነበር።

ስምዖን በቂሳርያ ከተማ መድኀኒታችን "ማን ትሉኛላችሁ?" ብሎ በጠየቀ ጊዜ "አንተ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ" ብሎ በመመስከሩ ጌታችን አንተ ጴጥሮስ ነህ አለው፣ ይህም በግሪክ ቋንቋ ዐለት ማለት ሲሆን፤ በአርማይክ ደግሞ ኬፋ ይባላል [ማቴ ፲፮ ÷ ፱፰]።

ቅዱስ ጴጥሮስ ከአዕማድ/የምሥጢር ሐዋርያት አንዱ ነው። ይህ ሐዋርያ «ከደቀ መዛሙርቱ ሁሉ ቀደም ቀደም የማለት ባሕርይ አለው፣ እንዲሁ ሐዋርያቱንም ወክሎ ይናገር ነበርና» የሐዋርያት አፈጉባኤ ተባለ [ማቴ ፲፬፥፳፪-፴፫ ፣ ዮሐ ፮፥፷፮-፷፰ ]። «መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የአብ የባሕርይ ልጁ መሆኑን መስክሯልና» የመንግስተ ሰማይ ቁልፍ ተሰጠው

ቅዱስ ጴጥሮስ በአራቱም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ላይ በተቀመጡት የሐዋርያት ዝርዝር ቀዳሚውን ሥፍራ ይዞ ይገኛል። ይህም፤ በሽምግልና አባትነቱ፣ ጌታ በቂሳርያ በሰጠው ቃል ኪዳን፣ የሐዋርያት አፈ ጉባዔ ሆኖ ይናገር ስለነበር፣ በጥብርያዶስ ባሕር በተሰጠው ቃል መሠረት ነው። በቤተ ክርስቲያን ታሪክ መሠረት ቅዱስ ጴጥሮስ በፍልስጥኤም፣ በሶርያ፣ በጳንጦን፣ በገላትያ፣ በቀጰዶቅያ፣ በቢታንያ እና በሮሜ ሰብኳል። እንዲሁም ሁለት መልእክታትንም ጽፏል።
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ

የኪልቂያ ዋና ከተማ በሆነች በጠርሴስ፣ ከዕብራዊያን ዘር፣ ከብንያም ነገድ ተወለደ። የመጀመርያ ስሙ ሳውል ነው። በአባቱ ሮማዊም ነበር [አባቱ የሮም ሰራተኛ ሲሆን፣ ሮማውያን ደግሞ ለሚሰሩላቸው ዜግነትን ይሰጡ ነበርና]። በወጣትነቱም በኢየሩሳሌም ከነበረው የታወቀው የገማልያል ትምህርት ቤት ገብቶ፣ የአይሁድን ሕግና ሥርዓት ጠንቅቆ ተምሯል። በዚህም በ፴ ዓመቱ የአይሁድ ሸንጎ አካል ሆነ። ለኦሪት ከነበረው ቅናት ይተነሳ ክርስቲያኖቸን እጅግ አምርሮ ይጠላ፣ ያሳድዳቸውም ነበር።

በ፴፪ ዓመቱ ከሊቀ ካህናቱ እጅ ክርስቲያኖቸን ሊያጠፋ የሚያስችለውን ደብዳቤ ተቀብሎ፣ ወደ ደማስቆ በመሄድ ሳለ በታላቅ ብርሃን ተመታ። መድኃኒታችንም በብርሃኑ መሃል ተገልጦለት "...አንተ የምታሳድደኝ እኔ የናዝሬቱ ኢየሱስ ነኝ። የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ለአንተ ይብስብሃል" ብሎ ተናገረው [ሐዋ ፱፥፩]። በዚያም የሐዋርያው ዓይኖች ማየት ስላልቻሉ እየተመራ ወደ ደማስቆ ገባ ። በሶስተኛው ቀን ሐናንያ የሚባል ደቀ መዝሙር በጌታ ትዕዛዝ ወደሱ መጥቶ ዐይኑን ፈወሰው፣ አጠመቀውም። ከዚያን ጊዜ አንስቶ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ «በአሕዛብም በነገሥታትም በእሥራኤልም ልጆች ፊት የጌታን ስም ይሸከም ዘንድ የተመረጠ ዕቃ» ሆነ [ሐዋ ፱፥15]። ብረሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ የኦሪትም የወንጌልም ሊቅ የነበር፣ ምድርን ሙሉ ዞሮ ወንጌልን የሰበከ፣ እስከ ሶስተኛው ሰማይ መነጠቅ የቻለ፣ ዐስራ አራት መልእክታትን የጻፈ ድንቅ ሐዋርያ፣ የክርስቶስ አገልጋይ ነው።
ዕረፍታቸው

በ ፶፬ ዓ.ም ኔሮን በሮም ነገሠ። በ፷፬ ዓ.ም ይህ ንጉስ በጥጋቡ የሮማ ከተማ ስትቃጠል ምን እንደምትመስል ማየት እፈልጋለሁ ብሎ አቃጠላት። የሮም ሕዝብ በከተማው መቃጠል በማዘኑና በማመፁ ነገሩን ሁሉ በክርስቲያኖች ላይ አሳበበ። በዚህም የተነሣ ክርስቲያን የተባለ ሁሉ መሰደድ፣ መሠየፍ፣ መታረድ እጣ ፈንታው ሆነ። ቅዱስ ጳውሎስ በዚህ ሰዓት በእሥር ነበርና ሐምሌ ፭ ቀን ፷፯ ዓ.ም ተሠይፎ ዐረፈ። ይህን የሰሙት የአግቢኖስና የአግሪጳ ሚስቶች "አንተ ትረፍልን" ብለው ቅዱስ ጴጥሮስ ሮማን ለቅቆ እንዲወጣ አደረጉት። ቅዱስ ጴጥሮስ በመንገዱ እያዘገመ ሳለ አንድ ጐልማሳ መስቀል ተሸክሞ ወደ እርሱ ሲመጣ አየ። እየቀረበ ሲመጣ ጌታችን መሆኑን ተረዳ። እርሱም "ጌታዬ ወዴት እየተጓዝክ ነው?" አለና ጠየቀው። "ዳግም በሮም ልሰቀል" አለው። በዚህ ሰዓት ቅዱስ ጴጥሮስ አዘነና እንደገና ወደ ሮማ ተመለሰ። በዚያም እኔ እንደ ጌታዬ ልሰቀል አይገባኝም በማለት ቁልቁል ተሰቅሎ ሐምሌ ፭ ቀን ፷፯ ዓ.ም ዐርፈ።

የአባቶቻችን ረድኤት እና በረከት ይደርብን🙏

፮ ኪሎ ግቢ ጉባኤ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
ከሐምሌ 22 እስከ ሐምሌ 28 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ በሁሉም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ገዳማት የሚፈጸመውን የምሕላ ጸሎት አስመልክቶ ከቋሚ ሲኖዶስ 
              የተሰጠ መግለጫ

‹‹ተማሕለሉ ወሰአሉ ኃበ አቡክሙ ሰማያዊ እስመ አብ ይሁበክሙ ኵሎ ዘሰአልክሙ…አባታችሁ የምትለምኑትን ሁሉ ይሰጣችኋልና ወደ ሰማይ አባታችሁ ለምኑ፣ ምሕላንም አውጁ›› ኢዩኤል 1፤14 ቅዱስ ያሬድ 
በሀገር አስተማማኝ ሰላም ሲጠፋ በጾም በጸሎት በመወሰን፣ምሕላን በማወጅ ልባዊ በሆነ ተማሕጽኖ ሁሉን ማድረግ ወደሚችለው አምላካችን አግዚአብሔር ምልጃን ማቅረብ የሚያስፈልግ መሆኑን ከሀገራችን ሊቃውንት መካከል የመጀመሪያ የሆነው ቅዱስ ያሬድ ከሰማያውያን ዐውደ ማህሌት ሰምቶ በቀሰመው ጣዕመ ዜማ አበክሮ ይነግረናል፡፡
በመሆኑም ውሎ ማደር፣ ወጥቶ መግባት በአንዳንድ የሀገራችን አካባቢዎች ስጋት ከሆነ ሰነባብቷልና በእውነት የሚለምኑትን ሁሉ የሚሰማ እግዚአብሔር መተላለፋችንን ይቅር እንዲለን፣ ለሀገራችን ዘላቂ ሰላም፣ ለቤተ ክርስቲያናችን ፍቅር አንድነት፣ ለሕዝባችን ደኅንነት እንዲሰጥልን ከአንድነት ገዳማት ኅብረት በቀረበው ጥያቄ መነሻነት ምሕላ ማወጅ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ በሁሉም የሀገራችን ክፍልና በሌሎችም አህጉራተ ዓለም የምትገኙ መነኰሳትና መነኰሳይያት ከሐምሌ 22 እስከ ሐምሌ 28 ቀን 2016 ዓ.ም. ድረስ ለሰባት ተከታታይ ቀናት በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ሃይማኖታዊና ቀኖናዊ ትውፊት መሠረት የገዳማት ኅብረቱን ጥሪ ተቀብላችሁ የምሕላ ጸሎት እንድታደርሱ፣ በጤና ችግር ምክንያት ካልሆነ በስተቀር እስከ ዕርበተ ፀሐይ በመጾም ሱባኤ እንድትይዙ፣ ቋሚ ሲኖዶስ በኅብረተ መንፈስ ቅዱስ ከአደራ ጋር ያሳስባል፡፡
ሁሉም የቤተክርስቲያናችን አገልጋዮችና ምእመናን ሀገራዊ ሰላምን፣ መረጋጋትንና ፍቅር አንድነትን ለማስፈን ጾምና ጸሎት በታወጀበት የምሕላ ሳምንት ለገዳማውያኑ ፀጥታ ሲባል ወደ ገዳማት የምታደርጉትን ጉዞ ለጊዜው እንዲቆይ አድርጋችሁ መደበኛ ሥራችሁን በያላችሁበት ቦታ እየሠራችሁ እግዚአብሔር የገዳማውያኑን ጸሎት ሰምቶ ለሀገራችንና ለሕዝባችን ምሕረትን እንዲሰጥ በኅሊና ዝግጅት፣ በሐሳብ አንድነት ሆናችሁ በጾም በጸሎት እንድተጉ ቋሚ ሲኖዶስ መንፈሳዊ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
Forwarded from Ayni ጌታ ሆይ እኔን ከእኔ ጠብቀኝ..አባ አትናቲዮስ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከምሁር እየሱስ ገዳም 1:30 ገደማ ርቀት ላይ የምትገኘው የነጎጀ ( የነጌጃ) ደብረ ምሕረት ወዳጆች ሁላችሁ አደራ አለብን በተለይ ጊቢያት 6,5,4 ኪሎ ጊቢ ጉባኤ ወዳጆቼ ከአባታችን ጎን ሆነን የኛን ትንሽ ( ጥቂት) ሀላፊነት እንወጣ promotion በተለያዩ የ Social Media በመጠቀም ለሁሉም ኦርቶዶክሳውያን ተደራሽ በማድረግ ከታሪክ ተወቃሽነት እንዳን ትኬት ለመግዛት 📞0913850267 ይደውሉ
Online ይቁረጡ
"ጌታ ሆይ እርሻውን አቃጥለህ ሰብሉን ብትባርክ ምን ይጠቅማል? ዛፉንስ ቆርጠህ ቅርንጫፉን ብትባርክ ምን ይረባል? እናቴ እርሻ ናት እኔ ሰብል ነኝ:: እናቴ ዛፍ ናት እኔ ቅርንጫፍ ነኝ:: እባክህን እናቴ ብትክድ እኔ ባምን ምን ይጠቅማል:: ጌታ ሆይ የእናቴን ልብ በሃይማኖት አጽናልኝ"

(ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ ስለ እናቱ ቅድስት ኢየሉጣ የጸለየው ጸሎት)

ቅዱስ ቂርቆስ ሆይ አንተ ሕፃን ሆነህ ትልቅ ነበርክ:: ትልቅ ሆነን ሕፃን የሆንን እኛን በምልጃህ አስበን!

"የእግዚአብሔር ምስክር የታመነ ነው፤ ሕፃናትን ጠቢባን ያደርጋል" መዝ 19:7

(#ከዲያቆን_ሄኖክ_ኃይሌ_የተወሰደ)
††† እንኳን ለቅዱሳኑ ገብርኤል ሊቀ መላእክት: ቂርቆስ ወኢየሉጣ: በጥላን ጠቢብ እና ሰማዕታተ እስና ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ቅዱሳን ቂርቆስ ወኢየሉጣ: ወቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት †††

††† ቅድስት ኢየሉጣ እናታችን በዘመነ ሰማዕታት ከነበሩና በዚህ ስም ከሚጠሩ ቅዱሳት አንዷ ናት:: በወቅቱ ቅዱስ ቂርቆስ የሚባል ደግ ልጅ ወልዳ ባሏ ባለመኖሩ በመበለትነት ትኖር ነበር:: የዚያ ዘመን ክርስቲያኖች ለክርስቶስ የነበራቸው ፍቅር ከመነገር በላይ ነው:: በዛው ልክ ደግሞ መከራው በጸጉራቸው ቁጥር ልክ ነበር::

ከሮም ግዛት በአንዱ ከቅዱስ ልጇ ጋር የምትኖረው ቅድስት ኢየሉጣ የስደቱ ዘመን ሲመጣ እርሷም እንደ ሌሎቹ ክርስቲያኖች ተሰደደች:: እስክንድሮስ የተባለው ከሃዲ ንጉሥ ግን ያለችበት ድረስ ተከትሎ እንድትያዝና እንድትቀርብ አደረገ::

ወዲያውም "ስምሽ ማን ይባላል?" ቢላት "ክርስቲያን እባላለሁ" አለችው:: ንጉሡ ተቆጣ:: "መዋቲ ስሜን ከፈለክ ኢየሉጣ ይባላል" አለችው:: ንጉሡ መልሶ "አሁን ለጣዖት ካልሠዋሽ ሲጀመር ስቃይ: ቀጥሎም ሞት ይጠብቅሻል" ቢላት ቅድስቲቱ መልሳ "በከተማ ውስጥ የሦስት ዓመት ሕፃን አለና እርሱን አምጣው:: ማንን ማምለክ እንዳለብን ይነግረናል" አለችው::

አስፈልጐ ቅዱስ ቂርቆስን አስመጣው:: "ስምህ ማን ይባላል?" አለ ንጉሡ:: "ከማይደፈርስ ከንጹሕ ምንጭ የተቀዳ ጥሩ ምንጭ ስሜ ክርስቲያን ይባላል:: መዋቲ ስሜን ከፈለግህ ግን ቂርቆስ ይባላል" አለው::

ንጉሡ ሊያታልለው "ደስ የተሰኘህ ሕፃን" ቢለው ቅዱሱ ሕፃን "ትክክል ተናገርክ: ለእኔ በሰማያት ደስታ ይጠብቀኛል:: አንተ ግን እውነተኛው አምላክ ይፈርድብሃል" አለው:: በሦስት ዓመት ሕፃን አንደበት ዘለፋ የገጠመው ከሃዲ ተቆጣ::
እናትና ልጅን በብዙ መክፈልተ ኩነኔ አሰቃያቸው::

ሰውነታቸውን ቸነከረ: አካላቸውን ቆራረጠ: ዓይናቸውን አወጣ:: ሌላም ሊናገሩት የሚጨንቅ ስቃይን አሰቃያቸው:: በዚህች ቀን ግን ትልቅ ድስት አሰርቶ ባሩድ: አረር: ስብና የመሳሰሉትን ጨምረውበት በእሳት አፈሉት::

የእሳቱ ወላፈን አካባቢውን በላው:: በድስቱ ውስጥ ያለው ነገር እየፈላ ሲገላበጥ እንደ ክረምት ነጐድጓድ ይጮህ ነበር:: የስድስት ሰዓት የእግር መንገድ ድረስም ተሰምቷል:: ቅድስት ኢየሉጣ ይሔኔ ነበር ልቧ ድንግጥ ያለው:: ሕፃኑ ቂርቆስ የእናቱን ፍርሃት ሲመለከት ጸለየ::

"ፈጣሪዬ! ፍሬው ያለ ግንዱ አይቆምምና እኔን እንዳጸናሕ እናቴንም አጽናት" ሲል ለመነ::
"እግዚኦ ትፈቅድኑ ለፍሬሁ ተአልዶ:
እንዘ በእሳት ታውኢ ጉንዶ" እንዲል::
በዚያች ሰዓት ቅድስት ኢየሉጣ ዓይኖቿ ተከፍተው ሰማያዊ ክብርን ተመለከቱና ልቧ ወደ ድፍረቱ ተመለሰ::

ልጇንም "አንተ አባቴ ነህ: አንተን የተሸከመች ማኅጸኔ የተባረከች ናት" አለችው:: ከዚያም ሁለቱንም ወደ ፈላው ድስት ውስጥ ቢጨምሯቸው ፍጡነ ረድኤት ቅዱስ ገብርኤል ከሰማይ ወረደላቸው:: በበትረ መስቀሉ ባርኮ የፈላውን አቀዘቀዘው:: የነደደውን ውኃ አደረገው:: ቅዱሳኑ ቂርቆስና ኢየሉጣ ከብዙ መከራ በኋላ በሰማዕትነት አልፈዋል::

††† ቅዱስ በጥላን ጠቢብ †††

††† ቅዱሱ ከአሕዛብ ወላጆቹ ተወልዶ: ያደገውም በጣዖት አምልኮ ነው:: በሙያው እጅግ የተመሠከረለት ሐኪም ነበር:: የሃገሩ ሰዎች "ጠቢብ" እያሉም ይጠሩታል:: በጥላን ምንም ጣዖት አምላኪ ቢሆን በተፈጥሮው ተመራማሪና ቅን ነበር::

አንድ ካህንም በጐረቤቱ ነበርና ዘወትር ስለ ሃይማኖት ይከራከሩ ነበር:: ካህኑ ሌሊት ሌሊት ስለ በጥላን ተግቶ ይጸልይ ነበርና ተሳክቶለት አሳመነው::

አንድ ቀን በጥላን መንገድ ሲሔድ እባብ ሰው ነድፎ ለሞት ደርሶ አየውና ጸሎት አድርሶ ስመ ክርስቶስን ቢጠራ የተነደፈው ድኖ እባቡ ሞተ::

በዚህ ተዓምር ደስ ብሎት ወደ ካህኑ ሒዶ ተጠመቀ:: ከዚያም ጾም ጸሎትን ጀመረ:: በየቦታው እየዞረ ሕሙማንን እንደ ቀድሞው በመድኃኒት ሳይሆን በጸሎት ያድናቸው ነበር:: ስላዳናቸውም በርካቶቹ ወደ ክርስትና መጡ::

የአካባቢው ሰው: ወላጆቹን ጨምሮ ክርስቲያኖች ሆኑ:: በመጨረሻም ቅዱስ በጥላን: ቤተሰቦቹ: ካህኑና ከደዌ የዳኑት ወገኖቹ በአካባቢው ጣዖት አምላኪ ንጉሥ ፊት ቀርበው ክርስቶስን ሰብከው በሰማዕትነት ዐርፈዋል::

††† ቅዱሳን ሰማዕታተ እስና †††

††† እስና ማለት ግብጽ ውስጥ የምትገኝ የቀድሞ አውራጃ ናት:: በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን በከተማዋ በርካታ ክርስቲያኖች ይኖሩ ነበር:: የእንዴናው መኮንን መጥቶ "ክርስቶስን ካዱ: ለጣዖት ስገዱ" አላቸው:: ሕዝቡ በአንድ ድምጽ መለሱ:- "ይሕማ ፈጽሞ ሊደረግ አይችልም::" መኮንኑ ተቆጥቶ "ሁሉንም ግደሉ" አለ::

ወታደሮቹ ሰው አልመረጡም:: ከታዘለ ሕፃን አልጋ ላይ እስካለ ሽማግሌ: ከጤነኛ እስከ ሕመምተኛ: ሁሉንም ጨፈጨፏቸው:: ከተማዋ በደም ተነከረች:: ከከተማዋ ክርስቲያኖች ወሬ ለመንገር አንድ ሰው እንኳ አልተረፈም:: ሁሉም ስለ ክርስትና ደማቸውን አፈሰሱ::

††† ጌታችን ስለ ሰማዕታቱ ብሎ: ደማቸውንም አስቦ በሃይማኖታችን ያጽናን:: ከመከራም ይሰውረን:: በረከታቸውንም ያድለን::

††† ሐምሌ 19 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት
2.ቅዱስ ቂርቆስ ወእሙ ኢየሉጣ
3.ቅዱስ በጥላን ጠቢብ ሰማዕት እና ማኅበሩ
4.ቅዱሳን ሰማዕታተ እስና

††† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ኤስድሮስ ሰማዕት
2.አቡነ ዓቢየ እግዚእ ጻድቅ
3.አቡነ ስነ ኢየሱስ
4.አቡነ ዮሴፍ ብርሃነ ዓለም

††† "ከክርስቶስ ፍቅር ማን ይለየናል? መከራ: ወይስ ጭንቀት: ወይስ ስደት: ወይስ ራብ: ወይስ መራቆት: ወይስ ፍርሃት: ወይስ ሰይፍ ነውን?
'ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን:: እንደሚታረዱ በጐች ተቆጠርን::' ተብሎ እንደተጻፈው ነው::
በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን::" †††
(ሮሜ. ፰፥፴፭-፴፯)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††