✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞
✞✞✞ እንኩዋን ለአባቶቻችን ቅዱሳን "12ቱ ሐዋርያት" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞
+"+ ቅዱሳን 12ቱ ሐዋርያት +"+
=>በቅድስት ቤተ ክርስቲያን አስተምሕሮ ከእመቤታችን በቀር ከቅዱሳን ሐዋርያት የሚበልጥ አልተነሳም:: "ሐዋርያ" ማለት "ፍንው: ልዑክ: የተላከ: የጽድቅ መንገደኛ" እንደ ማለት ነው:: በምሥጢሩ ግን "ባለሟል" ብለው ሊቃውንቱ ተርጉመውታል::
+ይህስ እንደምን ነው ቢሉ:-
¤የፍጥረታት ሁሉ ጌታ: የክብር ባለቤት መድኃኔ ዓለም ከድንግል ማርያም ተወልዶ: አድጐ: ተጠምቆ: ጾሞ: ከገዳመ ቆረንቶስ ሲመለስ ቀዳሚ ሥራው ያደረገው ደቀ መዛሙርቱን መጥራት ነበር::
+ከተከተሉት የ5 ገበያ ሕዝብ መካከል "ወሐረየ እምሰብአ ዚአሁ አሠርተ ወክልኤተ ሐዋርያተ" እንዲል በመጀመሪያ 12ቱን ሐዋርያት መረጠ::
+እሊህም:-
1.ዼጥሮስ የተባለ ስምኦን
2.እንድርያስ (ወንድሙ)
3.ያዕቆብ ወልደ ዘብዴዎስ
4.ዮሐንስ (ወንድሙ)
5.ፊልዾስ
6.በርተሎሜዎስ
7.ቶማስ
8.ማቴዎስ
9.ያዕቆብ ወልደ እልፍዮስ
10.ታዴዎስ (ልብድዮስ)
11.ናትናኤል (ቀናተኛው ስምዖን) እና
12.ማትያስ (በይሁዳ የተተካ) ናቸው:: (ማቴ. 10:1)
+እነዚህን 12 አርድእቱን ከጠራ በሁዋላ ለ3 ዓመታት ከ3 ወራት ከዋለበት ሲማሩ ይውሉ ነበር:: ሌሊት ደግሞ ምሥጢር ሲያስተረጉሙ ያድሩ ነበር::
+ጌታ እንደሚገባ ካስተማራቸው በሁዋላ ከፍ ያለ ኃላፊነትን ሾማቸው:: ለዓለም እረኞች: የእርሱም ባለሟሎች ሆኑ:: እጅግ ብዙ መከራ እንደሚገጥማቸው ነገራቸው:: (ማቴ. 10:16, ዮሐ. 16:33) በዚያው ልክ ክብራቸውንም አከለላቸው:: (ማቴ. 19:28)
+ሥልጣናቸው ደግሞ እስከዚህ ድረስ ሆነ:: "በምድር ያሠራችሁት በሰማይ የታሰረ ይሆናል: በምድር የፈታችሁት በሰማይ የተፈታ ይሆናል::" (ማቴ. 18:18) "ይቅር ያላችሁዋቸው ኃጢአታቸው ይቀርላቸዋል: ያላላቹሃቸው ግን አይቀርላቸውም::" (ዮሐ. 20:23)
+የመንግስተ ሰማያትን መክፈቻ (ማቴ. 16:19): እረኝነትን (ዮሐ. 21:15) ተቀበሉ:: ጌታ በንጹሕ አንደበቱ ሐዋርያቱን እጅግ ሲያከብራቸው "ጨው: የዓለም ብርሃናት" (ማቴ. 5:13) አላቸው:: ወንድሞቹም ተባሉ:: (ዮሐ. 7:5) ከዚህም በሚበልጥ በሌላ ክብር አከበራቸው::
+ከዚህ ሁሉ ነገር በሁዋላ በጌታ ሕማማት ጊዜ ገና ነበሩና አንዳንዶቹ ፈርተው ተበተኑ:: ተመልሰው ግን በጽርሐ ጽዮን ሲጸልዩ ሰንብተው የጌታን ትንሳኤ ተመለከቱ:: እጆቹን: እግሮቹንም ዳስሰው ሐሴትን አደረጉ::
+ለ40 ቀናት መጽሐፈ ኪዳንን: ትምሕርተ ኅቡዓት: ሌላም በፍጡር አንደበት የማይነገር ብዙ ምሥጢራትን ተምረው: ጌታ ሊቀ ዽዽስናን ሹሟቸው ዐረገ::
+ለ10 ቀናት በእመ ብርሃን ሥር ተጠልለው ሲጸልዩና በአንድ ልብ ሲተጉ ሰንብተው መንፈስ ቅዱስ ወረደላቸው:: በአንዴም ከፍርሃት ወደ ድፍረት ተመልሰው ፍጹማን: ብርሃናውያን ሆኑ:: 71 ልሳናትን ነስተው በአንዲት ስብከት ብቻ 3ሺ ነፍሳትን ማረኩ:: (ሐዋ. 2:41)
+ቅዱሳን ሐዋርያት በኅብረት ለአንድ ዓመት ያህል በኢየሩሳሌምና በዙሪያዋ እየተመላለሱ አስተምረው ብዙ እሥራኤላውያንን ወደ ክርስትና ማርከዋል:: ከዚህ በሁዋላ ግን እንደ ትውፊቱ በዚህች ቀን ዓለምን በእጣ ለ12 ተካፈሏት::
+ይህ ሲሆን መንፈስ ቅዱስ አብሯቸው ነበርና ለእያንዳንዳቸው እንደሚገባቸው አሕጉረ ስብከቶች ደረሷቸው:: እነርሱም ደቀ መዛሙርቶቻቸውን አስከትለው ለታላቁ መንፈሳዊ ዘመቻ ወረዱ::
+በሔዱበት ቦታም ከተኩላ: ከአንበሳና ከነምር ጋር ታገሉ:: በጸጋቸውም አራዊትን (ክፉ ሰዎችን) ወደ በግነት መልሰው ለክርስቶስ አስረከቡ:: በየሃገሩ እየሰበኩ ድውያንን ፈወሱ:: ለምጻሞችን አነጹ:: እውራንን አበሩ:: አንካሶችን አረቱ:: ጐባጦችን አቀኑ:: ሙታንንም አስነሱ:: እልፍ አእላፍ አሕዛብንም ወደ መንጋው ቀላቀሉ::
+ስለዚህ ፈንታም ብዙዎቹ በእሳት ተቃጠሉ:: ቆዳቸው ተገፈፈ:: በምጣድ ተጠበሱ:: ደማቸው በምድር ላይ ፈሰሰ:: ከአንድ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ በቀር ሁሉም ይህችን ዓለም በሰማዕትነት ተሰናበቱ:: ጨው ሆነው አጣፍጠዋልና: ብርሃንም ሆነው አብርተዋልና እናከብራቸዋለን:: "አባቶቻችን: መምሕሮቻችን: ጌቶቻችንና ሊቆቻችን" እንላቸዋለን::
=>+"+ በዚያን ጊዜ ዼጥሮስ መልሶ:- 'እነሆ እኛ ሁሉን ትተን ተከተልንህ:: እንኪያስ ምን እናገኝ ይሆን?' አለው:: ጌታ ኢየሱስም እንዲህ አላቸው:- 'እውነት እላቹሃለሁ! እናንተስ የተከተላችሁኝ በዳግመኛ ልደት: የሰው ልጅ በክብሩ ዙፋን በሚቀመጥበት ጊዜ እናንተ ደግሞ በአሥራ ሁለቱ የእሥራኤል ነገድ ስትፈርዱ በአሥራ ሁለት ዙፋን ትቀመጣላችሁ:: +"+ (ማቴ. 19:27)
አምላከ ቅዱሳን ሐዋርያት ቸርነቱን: ምሕረቱን ያብዛልን:: በምልጃቸው ሃገራችንን ከክፉ ጠብቆ ከበረከታቸው ይክፈለን::
፮ ኪሎ ግቢ ጉባኤ ትምህርት እና ሐዋርያዊ አገልግሎት ክፍል

ሰላም ለናንተ ይሁን ውድ የግቢ ጉባኤያችን ልጆች እንደተለመደው ሳምንታዊው የጥያቄና መልስ ውድድር ዛሬ ምሽት ከ2:50-3:30 ይካሄዳል ሽልማቱ 21 የእመቤታችን እለት ይካሄዳል ሰናይ ምሽት https://t.me/SidistKiloGibiGubae
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
"ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ!" መዝ.122:1
💐💐 እንኳን ደህና መጣችሁ💐💐
የከፍተኛ ትምህርታችሁን ልትከታተሉ ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የተመደባችሁ ኦርቶዶክሳውያን በሙሉ ፮ ኪሎ ግቢ ጉባኤያችን እናንተ አዳዲስ ልጆቿን ለመቀበል ወገቧን ታጥቃ ያማሩ የተዋቡ ለነፍስ የሚበጁ የግቢን ሕይወት የሚያበጁ መርሐግብሮችን አዘጋጅታ በእግዚአብሔር ፍቅር "እንኳን ደህና መጣችሁ" ትላቹሃለች።
ነገ ማለትም ረቡዕ የአዲስ ተማሪዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ መርሐግብር ስለተዘጋጀ ሁላችሁም የ1ኛ ዓመት ተማሪዎች ትገኙ ዘንድ ተጋብዛችኋል‼️
⛪️ቦታ: 5ኪሎ ማኅበረ ቅዱሳን ሕንፃ 3ኛ ፎቅ
⏰ ሰዓት: ረቡዕ ምሽት 11:20
✅ማሳሰቢያ: ቦታው ከጠፋባችሁ በዚህ ስልክ ቁጥር ይደውሉ!
0956399936
0911658643
©፮ኪሎ ግቢ ጉባኤ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን‼️
"ኑ! ንጹሑን የዝናም ውሃ የተሸከመችልን የብርሃን ደመና እርሷን እናግናት እናትነት ከድንግልና አስተባብራ የያዘች እርሷን ኑ እናመስግናት!!" መጽሐፈ አርጋኖን
የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ወርሐዊ ዝክር ነገ ማለትም ሐሙስ ከምሽቱ 12:45 ጀምሮ ስለተዘጋጀ ኑ አብረን እስከዘለዓለሙ ድረስ ለአብርሃም ልጆች መመኪያ የሆነች እርሷን ክብሯንና ገናንነቷን እንናገር!!
⛪️ቦታ: ቅዱስ ማርቆስ ቤተክርስቲያን መጠለያ
⏰ሰዓት: ሐሙስ ምሽት 12:45
©፮ ኪሎ ግቢ ጉባኤ