፮ ኪሎ ግቢ ጉባኤ
2.49K subscribers
2.87K photos
42 videos
355 files
186 links
ይህ የ፮ ኪሎ ግቢ ጉባኤ ህጋዊ የቴሌግራም ቻናል ነው።
This is the official Channel of 6 kilo Gibi Gubae.
በግቢ ጉባኤው ላይ ያለዎትን አስተያየት ወይም ጥያቄ በ @fesehatsion12 ወይም @Hoping7 ላይ ይላኩልን።
Download Telegram
ከመቀበል በፊት

አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ
ርኲስ ከሆነች ከቤቴ ጠፈር በታች ትገባ ዘንድ የሚገባህ አይደለህም። እኔ በዚህ ዓለም አሳዝኜሃልሁና በፊትህም ክፉ ሥራ ሥርቻለሁና፣ በአርኣያህና በአምሳልህ የፈጠርከው ነፍሴንና ሥጋዬን ትእዛዝህን በማፍረስ አሳድፌኣለሁና፣ ሥራ ምንም ምን የለኝምና፣ ነገር ግን ስለ መፍጠርህና እኔን ለማዳን ሰው ሰለመሆንህ፣ ስለክቡር መስቀልህም ማሕየዊ ስለሚሆን ስለሞትህም፣ በሦስተኛው ቀን ስለመነሣትህ፣ ጌታዬ ፈጣሪዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ከበደልና ከመርገም  ሁሉ ከኃጢያትና ከርኲሰትም ሁሉ ታነጻኝ ዘንድ እለምንሃለሁ፣ እማልድሃለሁም። የቅድስናህንም ምሥጢር በተቀበልሁት ጊዜ ለወቀሳና ለምፈራረጃ አይሁንብኝ፣ ማረኝ ይቅርም በለኝ እንጂ።
የዓለም ሕይወት ሆይ በርሱ የኀጢያቴን ሥርየት የነፍሴንም ሕይወት ስጠኝ እንጂ። በሁለት ወገን ድንግል በምትሆን በወለደችህ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም በመጥምቁ በዮሐንስ አማላጅነት ክቡራን በሚሆኑ በመላእክት፣ በሰማዕታት ለበጎ ነገር በሚጋደሉ በጻድቃን ሁሉ ጸሎት እስከዘላለሙ ድረስ አሜን።

በሚቀበሉ ጊዜ የሚጸለይ ጸሎት

ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ይህ ምሥጢርህ በእኔ በደል አይሁንብኝ ሥጋዬንና ነፍሴን ለማንጻት ይሁንልኝ እንጂ። ወይም ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ሥሉስ የሚለውን ምሥጋና በቃል ይዞ ማመስገን ነው።

ከተቀበሉ በኋላ የሚጸለይ ጸሎት

ጌታዬ አምላኬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ቅዱስ ሥጋህንና ክቡር ደምህን እነሆ ተቀበልሁ። ለኀጢያቴ ማስተሥረያ ይሁንልኝ ስለ በደሌም ሁሉ።
ሰውን የምትወድ ውልድ ዋሕድ ሆይ ምስጋናህን በአንደበቴ ሙላ። ምስጋናህን አመሰግን ዘንድ ቀድሞ አንተ ሰው የሆንክ በሱም የተግለጽህ አስከዘላለሙ ታድነኝ ዘንድ ነውና፣ ስለቅዱስ ስምህም ለዘላለሙ አዳንከኝ። ጌታዬ አምላኬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ በአግልጋይህ በዚህ ካህን እጅ ሥጋህንና ደምህን አንድ አድርገህ ስለሰጠኸኝ ለአንተ ምስጋና ይገባሃል፤ አመሰግንሃለሁ፤ እለምንህማለሁ። 
ከምዕመናን ጋር አንድ እሆን ዘንድ ከወዳጆችህም ጋር ትቆጥረኝ ዘንድ ተቀበለኝ አሁንም ኀጢያቴን አትቁጠርብኝ፤ ለኔ ስለሰጠኸኝ ፀጋህና በኔ ስላለችው ረድኤትህ አመሰግንሃለሁ።https://youtube.com/@6Kilogbigubae?si=JPyZjTwMFI-i2HxR
ጸሎተ ሐሙስን ከግቢ ጉባዔያችን ጋር

ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እንኳን ለጸሎተ ሐሙስ አደረሳችሁ እያልን ግቢ ጉባኤያችን ልዩ የሆነ መርኃ ግብር አዘጋጅቷል!

በዕለቱ የሚኖሩ መርኃ ግብራት
➡️ መዝሙር
➡️ ትምህርተ ወንጌል
➡️ ሥነ -ጽሑፍ
➡️ ሕጽበተ እግር
➡️ ጉልባን

ስለሆነም ነገ ሐሙስ ሚያዚያ 24:2016 ዓ.ም ማኅበረ ቅዱሳን 3ኛ ወለል ምሽት 11:00 ጀምሮ ተገኝው የመርኃ ግብሩ ተካፋይ እንዲሆኑ ተጋብዘዋል!

የ፮ ኪሎ ግቢ ጉባዔ

ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን የተወደዳችሁ የግቢ ጉባዔያችን አባላት እንደምን ናቸሁ።



የቅዳሜ ስዑር ዕለት የምታከፍሉ የግቢ ጉባዔያችን ዓባላት በሙሉ የቅዳሜ ምሳችሁን ለነድያን ለማውጣት እና ለማስፈሰክ ስለታሰበ የምታከፍሉ ተማሪዎች በዚህ @Mi121919
➡️ ስም
➡️ መመገቢያ ቁጥር እና
➡️ ካፌ
በመላክ እንድትመዘገቡ እናሳስባለን ።

©የ፮ ግቢ ጉባዔ ሙያና በጎ አድራጎት ክፍል
ጸሎተ ሐሙስን ከግቢ ጉባዔያችን ጋር

ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እንኳን ለጸሎተ ሐሙስ አደረሳችሁ እያልን ግቢ ጉባኤያችን ልዩ የሆነ መርኃ ግብር አዘጋጅቷል!

በዕለቱ የሚኖሩ መርኃ ግብራት
➡️ መዝሙር
➡️ ትምህርተ ወንጌል
➡️ ሥነ -ጽሑፍ
➡️ ሕጽበተ እግር
➡️ ጉልባን

ስለሆነም ነገ ሐሙስ ሚያዚያ 24:2016 ዓ.ም ማኅበረ ቅዱሳን 3ኛ ወለል ምሽት 11:00 ጀምሮ ተገኝው የመርኃ ግብሩ ተካፋይ እንዲሆኑ ተጋብዘዋል!

የ፮ ኪሎ ግቢ ጉባዔ
ሰላም ለናንተ ይሁን በክርስቶስ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን  በዛሬው እለት በምስካዬ ህዙናን ተገኝታችሁ በእግዚአብሔር ቸርነት ከክርስቶስ ምሥጢረ ቁርባን የተሳተፋችሁ ሁላችሁም አፋችሁን ሳታድፉ እንዳትወጡ ቦታ ትንሿ ክርስትና ቤት ምስካዬ ህዙናን ቦታው ከጠፋባችሁ 0912920081ደውላችሁ እንድትጠይቁ በትህትና እናሳውቃለን

ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን የተወደዳችሁ የግቢ ጉባዔያችን አባላት እንደምን ናቸሁ።



የቅዳሜ ስዑር ዕለት የምታከፍሉ የግቢ ጉባዔያችን ዓባላት በሙሉ የቅዳሜ ምሳችሁን ለነድያን ለማውጣት እና ለማስፈሰክ ስለታሰበ የምታከፍሉ ተማሪዎች በዚህ @Mi121919
➡️ ስም
➡️ መመገቢያ ቁጥር እና
➡️ ካፌ
በመላክ እንድትመዘገቡ እናሳስባለን ።

©የ፮ ግቢ ጉባዔ ሙያና በጎ አድራጎት ክፍል
ወየው ወየው ወየው

❖  "አዳምን የፈጠሩ እጆች በመስቀል ቀኖት ተቸነከሩ ፡ #ወዮ

❖  በገነት የተመላለሱ እግሮች በመስቀል ቀኖት ተቸነከሩ ፡ #ወዮ

❖ በአዳም ፊት የህይወት መንፈስን እፍ ያለ አፍ ከሃሞት ጋራ የተቀላቀለ የኮመጠጠ መፃፃን ጠጣ ፡ #ወዮ

የወልድን መከራውን የሚናገር ምን አፍ ነው? ምን ከንፈር ነው? ምን አንደበት ነው? የፍቅር ጌታ ሕማማት በተነገረ ጊዜ ልብ ይለያል ፡ ህሊናም ይመታል ፡ ነፍስም ትንቀጠቀጣለች ፡ ስጋም ይደክማል፡፡

የማይሞተው ሞተ ፡ ሞትን ይሽረው ዘንድ ሞተ ፡ ሙታንን ያድናቸው ዘንድ ሞተ ፤ የምትወዱት ሰወች ፈፅሞ አልቅሱለት ፤

❖ ወየው ወየው ወየው አማኑኤል አምላካችን፡፡

❖ ወየው ወየው ወየው መድሃኒታችን ኢየሱስ ፤

❖ወየው ወየው ወየው ንጉሳችን ክርስቶስ ፤

❖ ወየው ወየው ወየው ፃድቃን ከእንጨት አወረዱት ስጋውንም ለመገነዝ ከርቤ የሚባል የጣፈጠ ሽቱንና ንፁህ በፍታን አመጡ፡፡

ሞተም ተቀበረም ፤ ሙስና ሳይኖርበት ከሙታን ተለይቶ ፈፅሞ ተነሳ ፤ ከሃጢአት ቀንበርም ነፃ አደረገን ፤ በዚያች ስጋ በመለኮት ሃይል ወደ ሰማይ ወደ ቀደመ አኗኗሩ አረገ፡፡"

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

አንጋፋው ግቢ ጉባኤያችን የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የትንሣኤ በዓል በታላቅ ድምቀት በትንሳኤ ዋዜማ ሚያዝያ 26 በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ሥላሴ በታላቅ ድምቀት ለማክበር ዝግጅቱን አጠናቋል።

በመርሐግብሩም ላይ

ሰባኪያነ ወንጌል

፩. ቀሲስ ዶ/ር መዝገቡ ካሳ
፪. ቀሲስ ዐብይ ሙሉቀን

ዘማርያን

፩. ዘማሪ ሀብታሙ
፪. ዘማሪት ወርቅነሽ ተፈራ

እንዲሁም የተለያዩ ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ያከብራል

በዕለቱ የሚኖሩን መርሃ ግብሮች

፩. ፀሎተ ወንጌል በቅዱስ ማርቆስ አባቶች እና በግቢው ዲያቆናት

፪. መዝሙር በተጋባዥ ዘማርያን

፫. ትምህርተ ወንጌል

፬. ስነ ፅሁፍ

፭. ወረብ በማኅበረ ካህናት እና በመዝሙር ክፍል

፮. ቅኔ

፯. ጭውውት

፰. ቃለምዕዳ

በዕለቱም የሚወጣ እጣ ያዘጋጀ ሲሆን እጣውን በመቁረት ግቢ ጉባኤያችሁንም እንድትደግፉ ከበረከቱም ተሳታፊ እንድትሆኑ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን!

1ኛ    በገና                        
2ኛ    Smart phone
3ኛ    Air pod                     
4ኛ    ድርሳነ ቅዱስ ሚካኤል
5ኛ    ነጠላ
                  
በተጨማሪም

ማስተዛዘኛ ለ 5 ሰው ወርሃዊ Voice package
             
ይሄ ሁሉ በ20ብር ብቻ 

ቦታ:- በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ሥላሴ

ሰዓት ⌚️ ከቀኑ 10:00 - 4:30

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን

፮ ኪሎ ግቢ ጉባኤ
ሰላም ለኩልክሙ

ገብረ ሰላመ በመስቀሉ ።
በመስቀሉ ሰላምን አደረገ

ትኩረት የሚሻ መልዕክት

እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው ዋይዜማ  በሰላም አደረሳችሁ

እግዚአብሔር ቢፈቅድ የትንሣኤው መርሐግብራችን ለማክበር አጭር 
ሰዓታት ቀሩን። 

የዘንድሮው መርሐግብራች ከሌላው ዓመት በተለየ ቀደም ተብሎ 
ከቀኑ 10:30 ላይ የሚጀመር !


ይህም የሆነበት ምክንያት መርሐግብራችንን ቶሎ ጨርሰን ወደ አገልግሎት  ለመግባት እና ቅዳሴ ለማስቀደስ በሚል እሳቤ ነው።

ቦታ:መንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ አዳራሽ
ሰዓት:10:30  ( አደራ ሰዓት ይከበር  የሚጀመረው ontime ነው።) ለሚመለከተው ሁሉ share አድርጉ! እና ተቀሳቅሳችሁ ተገኙ!

፮  ኪሎ ግቢ ጉባኤ
✥✥ መቃብሩን አትክፈቱ❗️❗️❗️❗️ ✥✥✥

👉 በብዛት የክርስቶስን ትንሣኤ ለመግለጽ የሚሣሉ ሥዕላት መቃብሩን ከፍቶ(ፈንቅሎ) ሲነሣ ወይም መላእክት የመቃብሩን ደጃፍ ከፍተውለት ሲነሣ ኣድርገው ነው የሚሣሉት ይህ በመጽሓፍ ቅዱስ ከተገለጸው ጋር የሚጋጭ ነው።

👉 ጌታችን የተነሣው መግነዝ ፍቱልኝ፥ መቃብሩን ክፈቱልኝ ሳይል ነው።

➛ ቅዱስ ማርቆስ በወንጌሉ እንደገለጸልን እሑድ በማለዳ ወደ ጌታ መቃብር ሽቱ ለመቀባት የሄዱት ሴቶች «ድንጋዩን ከመቃብሩ ደጃፍ ማን ያንከባልልልናል?» የሚል ጥያቄ ኣሳስቧቸው እንደነበር ይገልጽልናል።

➛ ይህን ጥያቄ ያቀረቡት “ ድንጋዩ እጅግ ትልቅ ነበርና ” በማለት የጥያቄያቸው መነሻ የሆነውን ምክንያት ያስረዳናል። {ማር ፲፮÷፩-፮፡፡}

➛ የእነዚህ ቅዱሳን ኣንስት (ሴቶች) ላሳሰባቸውን ጥያቄ መፍትሔ እንዴት እንዳገኘ ሌላኛው ወንጌላዊ ማቴዎስ በወንጌሉ እንዲህ ባለ መልኩ ይገልጽልናል፦

➛ «በሰንበትም መጨረሻ ( ሰንበት ያለው ቅዳሜን ነው) የመጀመሪያው ቀን (የመጀመሪያ ቀን ያለው የሥነፍጥረት መጀመሪያ የሆነች እሁድ ነው) ሲነጋ፥ መግደላዊት ማርያምና ሁለተኛይቱ ማርያም መቃብሩን ሊያዩ መጡ፡፡ እነሆም የጌታ መልአክ ከሰማይ ስለወረደ ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ ቀርቦም ድንጋዩን ኣንከባሎ በላዩ ተቀመጠ፡፡ መልኩም እንደ መብረቅ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ነበረ፡፡ ጠባቆቹም እርሱን ከመፍራት የተነሣ ተናወጡ፡፡ እንደ ሞቱም ሆኑ፡፡ መልኣኩም መልሶ ሴቶቹን ኣላቸው፥ እናንተስ አኣትፍሩ፤ የተሰቀለውን ኢየሱስን እንደምትሹ ኣውቃለሁና፤ እንደ ተናገረ ተነሥቶአልና በዚህ የለም፤ የተኛበትን ስፍራ ኑና እዩ። » {ማቴ ፳፰÷፩-፮፡፡}

➛ ጌታችን መቃብሩ ከፍቶ ተነስቶ ቢሆንስ ኖሮ መልኣኩ ሴቶቹ ወደ መቃብሩ ውስጥ እንዲመለከቱ መቃብሩን ከፈተው ባልተባለ ነበር። ጌታችን በዝግ መቃብር ከተነሣ በኋላ ባዶ የነበረውን መቃብር የከፈተው ይህ የጌታ መልአክ ነው፡፡

➛ መልኣኩ መቃብሩን ለምን ከፈተው ቢሉ፦ የመጡ እነዚህ ሴቶች የጌታችንን መነሣት እንዲያውቁ እና ትንሣኤውን እንዳይጠራጠሩ ነው፡፡ ኋላም ደቀ መዛሙርቱ ትንሣኤውን ያመኑት መልኣኩ ወደ ከፈተው መቃብር ገብተው መግነዙን ካዩ በኋላ ነው። ዮሐ ፳፥፯።

➛ ጌታችን መቃብሩን ክፈቱልኝ ሳይል ለምን ተነሣ ቢሉ፦ ሞቱ በፈቃዱ እንደሆነ ትንሣኤውም በሥልጣኑ መሆንን ለማስረዳት ነው።

ኣንድም፦ ሥግው ቃልን በርቀቱ ቢያጸናው ነው። ይኸውም በኅቱም ድንግልና መወለዱ፣ በባህር ላይ መራመዱ፣ በተዘጋ ደጃፍ ሳይከፈት መግባቱ፣ መቃብርም ክፈቱልኝ ሳይል መነሣቱ ጌታ ምንም እንኳን ግዝፍ የሆነ ሥጋን ቢነሣም በመለኮትነቱ ግን ረቂቅ ነው በተዋሕዶ የቃል ርቀቱ ለሥጋ ገንዘቡ በመሆኑ (ሥግው ቃልን በርቀቱ ቢያጸናው ) በድንግልና ለመወለድ የማይከልክለው፣ ባህር የማያሰጥመው፣ ደጃፍ ለመግባት የማይከለክለው፣ ለትንሣኤውም መቃብር መክፈት የማያስፈልገው መሆኑን ኣስረዳ።

👉 ስለዚህ ቅዱሳን ሥዕላት በመሣል ቤተክርስቲያንን የምታገለግሉ ይህንን መጽሓፍ ቅዱሳዊ ትምህርትን መሠረት ኣድጋች ብትሥሉ (መቃብሩን ኣትክፈቱ)፤ ምዕመናንም ይህን በመረዳት በቤታችንም ሆነ ወደ ቤተክርስቲያን የምናመጣቸውን ሥዕላትን ትክክለኛ መልእክት የሚያስተላልፍ ከቤተክርስቲያን ትምህርት ጋር የማይጋጭ መሆኑን በማገናዘብ ቢሆን ፤ እንዲሁም በሶሻል ሚዲያ የምናቀርባቸው ሥዕላትንም ይህን ያማከለ ሊሆን ይገባል። ይቆየን

መልካም በዓል ይሁንላችሁ ❗️❗️❗️
ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን፡
በዓቢይ ኃይል ወስልጣን ።
አሰሮ ለሰይጣን፡ አግዓዞ ለአዳም ።
ሰላም፡ እምይእዜሰ ።
ኮነ ፡ፍስሐ ወሰላም፡፡
እነሆ ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩር ሆኖ ከሙታን ተነስቷል፡1ኛ ቆሮ 15÷20።

እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤዉ በሰላም አደረሳችሁ እያልን በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የትንሳኤ ሎተሪ ትናንት ምሽት በይፋ መውጣቱ የታወሳል። በስፍራው ተገኝተው መካታተል ላልቻሉ አባላትም እድለኛ ቁጥሮችን እነሆ ብለናል።

1ኛ እጣ 1143 በገና
2ኛ እጣ 0265 Smart phone
3ኛ እጣ 3565 Air pode
4ኛ እጣ 1303 ድርሳነ ሚካኤል
5ኛ እጣ 0112 ነጠላ
የማስተዛዘኛ እጣዎቸ
6ኛ እጣ 0697
7ኛ እጣ 4026
8ኛ እጣ 0141
9ኛ እጣ 2286
10ኛ እጣ 0650

ከ6-10 ያሉት ሁሉም የወርሃዊ የድምጽ ጥቅል እድለኞች ናቸው።

እድለኞች እንኳን ደስ አላችሁ።
@Mi121919 ላይ በማሳወቅ ሽልማቱን መቀበል ትችላላችሁ።

ትኬቱን በመሸጥና እና በመግዛት ለመርኃ ግብሩ መሳካት ላበረከታችሁች ተሳትፎ በግቢ ጉባኤው ስም ከልብ እናመሰግናለን።

የ2016 ዓ.ም የትንሳኤ በዓል አዘጋጅ ኮሚቴ


https://t.me/SidistKiloGibiGubae
https://t.me/SidistKiloGibiGubae
https://t.me/SidistKiloGibiGubae
ከትንሳኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ፡-

#ሰኞ
#ማዕዶት_ይባላል፡- ማዕዶት ማለት መሻገር፣ ማለፍ ማለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን፡፡

#ማክሰኞ
#ቶማስ_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ፤ ጌታዬና አምላኬ ብሎ መመስከሩ ይዘከራል፡፡ ዮሐ. 20፡27-29

#ረቡዕ
#አልአዛር_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታ ኢየሱስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን፡፡ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ፡ በድልም ያረገ ንጉሥ መሆኑን እንመሰክራለን፡፡

#ሐሙስ
#አዳም_ሐሙስ_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው ተስፋ እና የተገባለት ኪዳን እንደተፈጸመ አዳምና ልጆቹ ነጻ እንደወጣን እናስባለን፡፡

#አርብ
#ቅድስት+ቤተክርስቲያን_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ስለመመስረቷ ይሰበካል፡፡ ክርስቶስ ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል፡፡ ቤተክርስቲያን ስንል ሕንፃውን ሳይሆን አማኞችን ነው፤ ክርስቶስ ለሕንፃ አልሞተምና፡፡

#ቅዳሜ
ቅዱሳት_አንስት_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን አካል ሽቶ ለመቀባት ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውና ትንሣኤውንም ቀድመው ማየታቸው ይሰበካል፡፡

#እሁድ
#ዳግም_ትንሳኤ_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሦስተኛ ጊዜ ለደቀመዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል፡፡
የእመቤታችንን ልደት  ከግቢ ጉባኤያችን ጋር 

  ልደተ እግዝእትነ ማርያም

መዝ. 86፥1
“መሠረታቲሃ ውስተ አድባር 
ቅዱሳን" መሠረቶቿ የተቀደሱ ተራሮች ናቸው

ዮም ፍሥሐ ኮነ በእንተ ልደታ 
ለማርያም   |በእመቤታችን ልደት ምክንያት ዛሬ ደስታ ሆነ|


ውድ የግቢ ጉባኤያችን ተማሪዎች በመጀመሪያ ​​እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያልን  የእናታችንን በዓለ ልደት በማሰብ ነገ በዕለተ ሐሙስ ከቀኑ 11:00 ጀምሮ በመንበረ ልዑል ቅዱሰ ማርቆሰ ወሚካኤል ቤተክርሰቲያን አውደምህረት እናት ግቢ ጉባኤያችን  መርሐ ግብር አዘጋጅታ ልጆቸ ኑ  እያለች መልዕክቷን ታሰተላልፋች።

ልደትሽ ልደታችን ነው!

ሰዓት ፡ 11:00 ጀምሮ
ቦታ : መንበረ ልዑል ቅዱሰ ማርቆሰ ወሚካኤል  አውደምህረት

የ፮ ኪሎ ግቢ ጉባዔ
Forwarded from ወይኩን ፈቃድከ
"ዘወትር በንፁሕ ሕሊና እየሆናችሁ ወደ እግዚአብሔር ጸልዩ።" መ.ቀሌሜንጦስ 12:25

የተወደዳችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ዘወትር ዓርብ በጋራ ተሰብስበን የአንድነት ጸሎት የምናደርስበት መርሐግብራችን ነገም እንደተጠበቀ ነው‼️

ስለዚህም ሁላችንም ከጓደኞቻችን ጋር ተቀሳቀሰን በመገኘት የጸሎት መርሐግብሩ ተሳታፊሆች እንሆን ዘንድ የእግዚአብሔር መልካም ፈቃዱ ይሁንልን!

👥ቦታ: ቅዱስ ማርቆስ ወሚካኤል ቤተክርስቲያን ሰንበት ትምህርት ቤት አዳራሽ
ሰዓት: ጠዋት 11:50

፮ ኪሎ ጊቢ ጉባኤ
ሰላም የ6ኪሎ ግቢ ጉባዔ ተማሪዎች

እንደሚታወቀው ይህ ጥንታዊ የሆነ ግቢ ጉባዔ የራሱ የሆነ የ YouTube channel መክፈቱን በይፋ ገልጿል። ስለሆነም ለጓደኞቻችሁ ፣ ለምታቁት ሰው ሊንኩን በመላክ #SUBSCRIBE እንዲያደርጉ ንገሯቸው። ይህንንም በማረግ ያሳደገችንን ግቢ ጉባዔ እናግዛት።

📌ኦርቶዶክሳዊ ትምህርተ ወንጌሎችን፣
📌የበዓላት ወረቦችን፣
📌ዝማሬዎችን፣
📌ምክረ አበውን እንዲሁም ሌሎች በስድስት ኪሎ ግቢ ጉባኤ የሚዘጋጁ ምስል ወ ድምፆችን ያገኙበታል።

ስለዚህ YouTube ላይ ገብታችሁ @6kilogbigubae ብላችሁ Search ማድረግ ወይም ደሞ ይህንን https://youtube.com/@6Kilogbigubae?si=JPyZjTwMFI-i2HxR መጠቀም ትችላላችሁ።

፮ ኪሎ ግቢ ጉባኤ
                   
@SidistKiloGibiGubae
                   
እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የልደት በዓል እና የማኅበረ ቅዱሳን ፴፪ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል በሰላም አደረሰን!

"ግቢ ጉባኤያት የአገልግሎት መሠረት" በሚል መሪ ቃል እሑድ ግንቦት 4 ቀን 2016 ዓ.ም ከ7፡00 ሰዓት ጀምሮ በጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ በመገኘት የማኅበራችንን የምሥረታ በዓል በጋራ እናክብር።
መቅረት ፈጽሞ የተከለከለ ነው።