ጥያቄ ፦
፩ . በስሙነ ሕማማት ማማተብ ፣ ማዕድ መባረክ ፣ መልክዐ መልክ መድገም አይፈቀድምን?
፪ . ሰሙነ ሕማማት ከገባ ጊዜ ጀምሮ ማማተብ ፣ ማዕድም ሲቀርብ ባርኮ መቁረስና ስለ እነሱ ብሎ ቡራኬ መስጠት የተከለከለ ነው ይባላል፡፡ ትክክል ነውን? ለምን?
፫ . በተጨማሪም መልክዐመልኮች አይደገሙም ፣ የሃይማኖት ጸሎት ሲደገም "ስለኛ ተሰቀለ በጴንጤናዊው በጲላጦስ ዘመን እርሱ መከራን ተቀበለ ሞተ ተቀበረ በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ..." እስከሚለው ድረስ ከሰኞ እስከ ሐሙስ አይደገምም ይዘለላል ምክንያቱ ምንድን ነው?
-----------------------------------------------
[ ምላሽ ]
- ማማተብ !
ይህ የሚያመለክተው በጉባዔ ፣ በአደባባይ ፣ በይፋ የሚደረገውን ነው፡፡ በብዙኃን ፊት ቡራኬ መስጠት ፣ የሞተ መፍታት ፣ መስቀል ማሳለም አይፈቀድም፡፡ ይህም ፭ ሺህ ፭ መቶ ዘመን ዓለም በማእሠረ ሰይጣን እንዳለ ፣ በግዞት በመርገም ውስጥ እንደነበረ ለማስታወስ ነው እንጂ ማዕዳችሁን አትባርኩ የሚል ሥርዓት አልተደነገገም፡፡
በግሉ አንድ ሰው ፊቱን በትእምርተ መስቀል አማትቦ መጸለይ ይችላል፡፡ ምክንያቱም አንድ ሰው ካላማተበ የአጋንንትን ውጊያ ድል መንሣት አይችልም፡፡ ስለዚህ በግል ጸሎት አታማትብ አይባልም፡፡ አይከለከልም፡፡
- ጸሎት !
የሃይማኖት ጸሎትም ሲደገም ፦ "ስለ እኛ ተሰቀለ ፣ በጴንጤናዊው በጲላጦስ ዘመን እርሱ መከራን ተቀበለ ፣ ሞተ ፣ ተቀበረ ፣ በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ" እስከሚለው ድረስ ከሰኞ እስከ ሐሙስ አይደገምም "ሐመ" ብለው ይተውታል፡፡ ይሄ ታሪኩን ለማስታወስ ነው፡፡ ጸሎቱ የሚከለከል ሆኖ አይደለም፡፡ ወቅቱን እየጠበቅን ድርጊቱን ለማስተማር ነው፡፡ ይኸውም ሰኞ ፣ ማክሰኞ ፣ ረቡዕ ፤ ሐሙስ መከሩ ከሐሙስ እስከ ዓርብ ሌሊት መከራውን ተቀበለ ፤ ዓርብ ስድስት ሰዓት ላይ ተሰቀለ እንላለን ፤ ከዘጠኝ ሰዓት ጀምሮ "ሞተ ተቀበረ" ይባላል፡፡ "ተነሣ" የምንለው ደግሞ ቅዳሜ በሌሊት ስድስት ሰዓት ነው፡፡ ያንን በየሰዓቱ የተደረገውን ታሪክ ለማስታወስ ፣ ለመግለጽ ፣ ለማስተማር ነው፡፡
መልክዐ መልኮች አለመደገማቸው ደግሞ ወደ ነገረ መስቀሉ ለማድላት ነው፡፡ ነገረ መስቀሉ ከሁሉ በላይ ነውና፡፡ ዓለም የዳነው በጌታችንና በአምላካችን በኢየሱስ ክርስቶስ ካሳነት ነው ፤ ይህንን የምናስታውስበት በስሙነ ሕማማት የእርሱን ካሳነት በፍጹም ተመስጦ እናስባለን እንጸልያለን፡፡ በዚህ ወቅት በቂ ጊዜ ስለማይኖር ወደ ቅዱሳን ገድል ትሩፋት ድጋም [ጸሎት ፣ ንባብ] አንሄድም፡፡
ነገር ግን ጊዜ ከተገኘ በሕማማት ቢሆን የቅዱሳንን ገድሎች እናነባቸዋለን፡፡ የሰዓት ቁጠባ ነው እንጂ ሌላ ምንም ምክንያት የለውም፡፡ ግብረ ሕማማቱ እራሱ በየሰዓቱ የተዘጋጀ የራሱ ጸሎት አለው፡፡ በእረፍት ሰዓት ግን ገድሎችንም ሆነ ስንክሳርን እናነባለን፡፡ ከሰዓት አንጻር የሚታይ ነው፡፡ ወደ ነገረ መስቀሉ ለማድላት ሕማሙን ሞቱን መከራውን ለእኛ ያደረገውን ካሳ በስሙነ ሕማማት በፍጹም ልቡና ለማሰብ ቅድሚያ ለእርሱ እንዲሰጥ ነው፡፡
የ፮ኪሎ ግቢ ጉባኤ
📲Join & Share👥
👇👇👇
Telegram @SidistKiloGibiGubae
YouTube https://youtube.com/@6Kilogbigubae?si=JPyZjTwMFI-i2HxR

#ማክሰኞ
#የጥያቄ_ቀን_ይባላል፦
ሰኞ ዕለት በቤተመቅደስ ሲሸጡ እና ሲለውጡ የነበሩትን ሁሉ እየገረፈ በማባረሩ ምክንያት ለሰው ልጅ ሹመትንና ስልጣንን የሰጠ ጌታ “በምን ስልጣን ይህንን ታደርጋለህ?” ማቴ ፳፩፥ ፳፫ ተብሎ በፈሪሳውያን ተጠይቋልና የጥያቄ ቀን ይባላል።
#የትምህርት_ቀን_ይባላል፡-
በዚህ ዕለት በቤተመቅደስ ረጅም ትምህርት ስላስተማረም የትምህርት ቀን ይባላል። ሉቃ ፳፩ ፥፳፰ ፣ ማር ፲፪፥፪።

፮ ኪሎ ግቢ ጉባኤ
በ2016_ዓ_ም_ለመጽሔት_የተመለመሉ_ተማሪዎች.pdf
ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን ከላይ በዝርዝሩ ላይ የተመዘገባችሁ ተመራቂ ተማሪዎች በሙሉ ነገ ማክሰኞ ሚያዚያ 22:2016 ዓ.ም ከሰዓት 7 ሰዓት ጀምሮ እና ረቡዕ ሚያዚያ 23:2016 ዓ.ም ጠዋት 3 ሰዓት ጀምሮ ፎቶ እንድትነሱ እያሳሰብን
‼️‼️‼️‼️ፎቶ ለመነሳት የሚከተሉትን ማሳሰቢያዎች መተገበር ይጠበቅባችኋል።‼️‼️‼️‼️
➡️ ፎቶ የምትነሱት ምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም ፊት ለፊት አለው ትልቁ ሕንጻ 4ኛ ፎቅ ፍቃዱ ፎቶ ቤት ነው
➡️ ለፎቶ እና ለመጽሔት በአጠቃላይ 120 ብር መክፈል ይጠበቅባችኋል።
➡️ፎቶ ከተነሳችሁ በኋላ የፎቶ ኮድ መቀበል እና መያዝ ስትጠየቁ ማቅረብ ግዴታ ነው።
➡️ ከላይ ከተቀመጠው ዝርዝር ውስጥ ስማችሁ ከሌለ አሳማኝ ምክንያት በመያዝ ቅሬታ ማቅረብ ትችላላችሁ። ከዛ ውጪ ፎቶ ብትነሱም መጽሔት ላይ አትገቡም።
➡️ ለፎቶ የሚያገለግል ጋውን፣ ነጠላ እና መስቀል እዛው የሚኖር ይሆናል።
ማሳሰቢያ በተጠቀሱት ሁለት ቀናት ፎቶ ተነስቶ የፎቶ ኮድ ማቅረብ ለማይችል ተማሪ ኮሚቴው ኃላፊነቱን አይወስድም!
ከላይ ካለው ዝርዝር ውስጥ የሌለ ተማሪ ረቡዕ ጠዋት ከ4:00-6:30 ወይም ሐሙስ ከ3:30- 5:00 ቅዱስ ማርቆስ ቤተክርስቲያን በሚገኘው 6 ኪሎ ግቢ ጉባኤ ጽ/ቤት የቅሬታ ወረቀት ማስገባት ትችላላችሁ።
በተጨማሪም
ዋና ግቢ +251920009082
FBE ግቢ +251967015381 በማንኛውም ሰዓት በመደወል ቅሬታ ማስገባት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
የ፮ ኪሎ ግቢ ጉባኤ የG.C ኮሚቴ

ረቡዕ
የምክር ቀን
ምክንያቱም የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍትጌታን እንዴት መያዝ እንደሚገባቸው ምክር ያጠናቀቁበት ቀን ነውና፡፡ በዚህ ምክራቸው ላይ በጣም ትልቅ ጭንቀት ነበር፡፡ ምክንያቱም ወቅቱ የፋሲካ በዓላቸውን የሚያከብሩበት ቀን የተቃረበ በመሆኑ ብዙው ሕዝብም በጌታችን ትምህርት የተማረኩ ተአምራቱንም የሚያደንቁ ስለ ነበር ሁከት እንዳይፈጠር ነው፡፡ በዚህ ጭንቀት ሳሉ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ በመካከላቸው በመገኘት የምክራቸው ተባባሪ ሆኖ ጭንቀታቸውን አስወግዶላቸዋል፡፡ (ማቴ. 26÷1-14፣ ማር. 14÷1-2፣ ሉቃ. 22÷1-6) የሐዲስ ኪዳን ካህናትና ምእመናን በዚሁ ዕለት በቤተ ክርስቲያን ተሰብስበው መላ ሰውነታቸውን ለእግዚአብሔር አስገዝተው የሞት ፍርዱን በማሰብና በማልቀስ ሐዋርያት ከጌታችን መያዝ በኋላ በኀዘን በፍርሐት እንደነበሩ እያሰቡ መጻሕፍትን በማንበብ በጾም በጸሎትና በስግደት ተወስነው ይቆዩና ከአሥራ ሁለት ሰዓት በኋላ ወደ ቤታቸው ይሄዳሉ፡፡
የመልካም_መዓዛ_ቀንም_ይባላል
ምክንያቱም ጌታችን በዚህ ዕለት በቤተ ስምዖን ዘለምጽ ተቀምጦ ሳለ መላ ሕይወቷን ለዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ እፍረት "ከእንግዲህ ወዲህ በኃጢአት ተበላሽቶ ይኖር የነበረውን ሕይወቴን እንደዚህ መልካም ሽቱ የሚያጣፍጥ ኃጢአትን ይቅር የሚል አምላክ መጣ" ስትል ዋጋው እጅግ በጣም ውድ የሆነ ከሦስት መቶ ዲናር በላይ የሚያወጣ በአልባስጥሮስ ብልቃጥ የተሞላ ሽቱ ይዛ በመሔድ በጠጉሩ ላይ በማርከፍከፍ ስለቀባችው ረቡዕ የመዓዛ ቀን ይባላል፡፡
የእንባ_ቀንም_ይባላል
ማርያም እንተ እፍረት በጌታችን እግር ላይ ተደፍታ መላ ኃጢአቷን ይቅር እንዲላት በእንባዋ እግሩን አጥባዋለችና በጠጉሯም በእንባዋ ያጠበችውን እግሩን አብሳዋለችና። (ማቴ. 26÷6-13፣ ማር. 14÷9፣ ዮሐ. 12÷8)

📣📣📣✨አዋጅ!✨📣📣📣
🔔 "እንግዲህ ከቅዱስ ቁርባን ተሳትፈን፤
እሳት እንደሚያገሳ አንበሳ ለዲያብሎስ አስፈሪ ሆነን እንመለስ።"🥰
(ቅ/ዮሐንስ አፈወርቅ)
እግዚአብሔር ቢረዳን በመንፈስ ቅዱስ አጋዥነት ቅዱስ ቁርባን የመቀበል መርሐግብራችን እነሆ ደረሰ!🥰
📌መቼ?:- ነገ የጸሎተ ሐሙስ/የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ/አረንጓዴው ሐሙስ/ትዕዛዘ ሐሙስ እየተባለች ለምትጠራዋ ክርስቶስ አምላካችን ምስጢረ ቁርባንን በመሰረተባት ዕለት
🔔"ዛቲ ዕለት እንተ ገብረ እግዚአብሔር ንትፈሣሕ ወንትሐሰይ ባቲ"
🍁 የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ጉዳዩ አዲስ እንደሆነ አናስብ እናታችን ቤተ ክርስቲያን ሁሌም የምታደርገው ጥሪ ነው! የሚበላ የሚጠጣ ብታጣ እንኳን የማትተወው ግብዣ ነው! ሙሽራው የሚታረድበት ብቸኛው ሠርግ ነው !
ቦታ:- ምስካዬ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም
ሰአት:- ከቀኑ 5:00 ጀምሮ
በዕለቱ :ስጋወደሙን ተቀብለው ለሚወጡ ልጆች አፋቸውን አፍነው ወደ ግቢ እንዳይመለሱ ግቢ ጉባኤው ያዘጋጀው ማቁረሪያ ስላለ ሁሉም በዕለቱ የተዘጋጀውን እየቀመሰ ወደ ግቢ መምጣት ይችላል!!!
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
ክርስቲያን የሚጀምር ብቻ ሳይሆን የሚፈጽም ነው! አደራ ወደኋላ እንዳንል🙏
🔔 “እኔ የነገርኋችሁ ቃል መንፈስ ነው ሕይወትም ነው።”ዮሐ 6፥63
🤲 እግዚአብሔር እንዲያከናወንልን ጸሎትን አናስታጉል።
፮ኪሎ ግቢ ጉባኤ

ከመቀበል በፊት
አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ
ርኲስ ከሆነች ከቤቴ ጠፈር በታች ትገባ ዘንድ የሚገባህ አይደለህም። እኔ በዚህ ዓለም አሳዝኜሃልሁና በፊትህም ክፉ ሥራ ሥርቻለሁና፣ በአርኣያህና በአምሳልህ የፈጠርከው ነፍሴንና ሥጋዬን ትእዛዝህን በማፍረስ አሳድፌኣለሁና፣ ሥራ ምንም ምን የለኝምና፣ ነገር ግን ስለ መፍጠርህና እኔን ለማዳን ሰው ሰለመሆንህ፣ ስለክቡር መስቀልህም ማሕየዊ ስለሚሆን ስለሞትህም፣ በሦስተኛው ቀን ስለመነሣትህ፣ ጌታዬ ፈጣሪዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ከበደልና ከመርገም ሁሉ ከኃጢያትና ከርኲሰትም ሁሉ ታነጻኝ ዘንድ እለምንሃለሁ፣ እማልድሃለሁም። የቅድስናህንም ምሥጢር በተቀበልሁት ጊዜ ለወቀሳና ለምፈራረጃ አይሁንብኝ፣ ማረኝ ይቅርም በለኝ እንጂ።
የዓለም ሕይወት ሆይ በርሱ የኀጢያቴን ሥርየት የነፍሴንም ሕይወት ስጠኝ እንጂ። በሁለት ወገን ድንግል በምትሆን በወለደችህ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም በመጥምቁ በዮሐንስ አማላጅነት ክቡራን በሚሆኑ በመላእክት፣ በሰማዕታት ለበጎ ነገር በሚጋደሉ በጻድቃን ሁሉ ጸሎት እስከዘላለሙ ድረስ አሜን።
በሚቀበሉ ጊዜ የሚጸለይ ጸሎት
ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ይህ ምሥጢርህ በእኔ በደል አይሁንብኝ ሥጋዬንና ነፍሴን ለማንጻት ይሁንልኝ እንጂ። ወይም ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ሥሉስ የሚለውን ምሥጋና በቃል ይዞ ማመስገን ነው።
ከተቀበሉ በኋላ የሚጸለይ ጸሎት
ጌታዬ አምላኬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ቅዱስ ሥጋህንና ክቡር ደምህን እነሆ ተቀበልሁ። ለኀጢያቴ ማስተሥረያ ይሁንልኝ ስለ በደሌም ሁሉ።
ሰውን የምትወድ ውልድ ዋሕድ ሆይ ምስጋናህን በአንደበቴ ሙላ። ምስጋናህን አመሰግን ዘንድ ቀድሞ አንተ ሰው የሆንክ በሱም የተግለጽህ አስከዘላለሙ ታድነኝ ዘንድ ነውና፣ ስለቅዱስ ስምህም ለዘላለሙ አዳንከኝ። ጌታዬ አምላኬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ በአግልጋይህ በዚህ ካህን እጅ ሥጋህንና ደምህን አንድ አድርገህ ስለሰጠኸኝ ለአንተ ምስጋና ይገባሃል፤ አመሰግንሃለሁ፤ እለምንህማለሁ።
ከምዕመናን ጋር አንድ እሆን ዘንድ ከወዳጆችህም ጋር ትቆጥረኝ ዘንድ ተቀበለኝ አሁንም ኀጢያቴን አትቁጠርብኝ፤ ለኔ ስለሰጠኸኝ ፀጋህና በኔ ስላለችው ረድኤትህ አመሰግንሃለሁ።https://youtube.com/@6Kilogbigubae?si=JPyZjTwMFI-i2HxR

✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝
ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን የተወደዳችሁ የግቢ ጉባዔያችን አባላት እንደምን ናቸሁ።
✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝
የቅዳሜ ስዑር ዕለት የምታከፍሉ የግቢ ጉባዔያችን ዓባላት በሙሉ የቅዳሜ ምሳችሁን ለነድያን ለማውጣት እና ለማስፈሰክ ስለታሰበ የምታከፍሉ ተማሪዎች በዚህ @Mi121919
➡️ ስም
➡️ መመገቢያ ቁጥር እና
➡️ ካፌ
በመላክ እንድትመዘገቡ እናሳስባለን ።
©የ፮ ግቢ ጉባዔ ሙያና በጎ አድራጎት ክፍል

Forwarded from 2ኛ ዓመት የ፮ኪሎ ግቢ ጉባኤ ተማሪዎች
ሰላም ለናንተ ይሁን በክርስቶስ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን በዛሬው እለት በምስካዬ ህዙናን ተገኝታችሁ በእግዚአብሔር ቸርነት ከክርስቶስ ምሥጢረ ቁርባን የተሳተፋችሁ ሁላችሁም አፋችሁን ሳታድፉ እንዳትወጡ ቦታ ትንሿ ክርስትና ቤት ምስካዬ ህዙናን ቦታው ከጠፋባችሁ 0912920081ደውላችሁ እንድትጠይቁ በትህትና እናሳውቃለን
✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝
ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን የተወደዳችሁ የግቢ ጉባዔያችን አባላት እንደምን ናቸሁ።
✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝
የቅዳሜ ስዑር ዕለት የምታከፍሉ የግቢ ጉባዔያችን ዓባላት በሙሉ የቅዳሜ ምሳችሁን ለነድያን ለማውጣት እና ለማስፈሰክ ስለታሰበ የምታከፍሉ ተማሪዎች በዚህ @Mi121919
➡️ ስም
➡️ መመገቢያ ቁጥር እና
➡️ ካፌ
በመላክ እንድትመዘገቡ እናሳስባለን ።
©የ፮ ግቢ ጉባዔ ሙያና በጎ አድራጎት ክፍል
ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን የተወደዳችሁ የግቢ ጉባዔያችን አባላት እንደምን ናቸሁ።
✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝✝
የቅዳሜ ስዑር ዕለት የምታከፍሉ የግቢ ጉባዔያችን ዓባላት በሙሉ የቅዳሜ ምሳችሁን ለነድያን ለማውጣት እና ለማስፈሰክ ስለታሰበ የምታከፍሉ ተማሪዎች በዚህ @Mi121919
➡️ ስም
➡️ መመገቢያ ቁጥር እና
➡️ ካፌ
በመላክ እንድትመዘገቡ እናሳስባለን ።
©የ፮ ግቢ ጉባዔ ሙያና በጎ አድራጎት ክፍል
ወየው ወየው ወየው
❖ "አዳምን የፈጠሩ እጆች በመስቀል ቀኖት ተቸነከሩ ፡ #ወዮ
❖ በገነት የተመላለሱ እግሮች በመስቀል ቀኖት ተቸነከሩ ፡ #ወዮ
❖ በአዳም ፊት የህይወት መንፈስን እፍ ያለ አፍ ከሃሞት ጋራ የተቀላቀለ የኮመጠጠ መፃፃን ጠጣ ፡ #ወዮ
የወልድን መከራውን የሚናገር ምን አፍ ነው? ምን ከንፈር ነው? ምን አንደበት ነው? የፍቅር ጌታ ሕማማት በተነገረ ጊዜ ልብ ይለያል ፡ ህሊናም ይመታል ፡ ነፍስም ትንቀጠቀጣለች ፡ ስጋም ይደክማል፡፡
የማይሞተው ሞተ ፡ ሞትን ይሽረው ዘንድ ሞተ ፡ ሙታንን ያድናቸው ዘንድ ሞተ ፤ የምትወዱት ሰወች ፈፅሞ አልቅሱለት ፤
❖ ወየው ወየው ወየው አማኑኤል አምላካችን፡፡
❖ ወየው ወየው ወየው መድሃኒታችን ኢየሱስ ፤
❖ወየው ወየው ወየው ንጉሳችን ክርስቶስ ፤
❖ ወየው ወየው ወየው ፃድቃን ከእንጨት አወረዱት ስጋውንም ለመገነዝ ከርቤ የሚባል የጣፈጠ ሽቱንና ንፁህ በፍታን አመጡ፡፡
ሞተም ተቀበረም ፤ ሙስና ሳይኖርበት ከሙታን ተለይቶ ፈፅሞ ተነሳ ፤ ከሃጢአት ቀንበርም ነፃ አደረገን ፤ በዚያች ስጋ በመለኮት ሃይል ወደ ሰማይ ወደ ቀደመ አኗኗሩ አረገ፡፡"
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
✝አንጋፋው ግቢ ጉባኤያችን የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የትንሣኤ በዓል በታላቅ ድምቀት✨ በትንሳኤ ዋዜማ ሚያዝያ 26✨ በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ሥላሴ በታላቅ ድምቀት ለማክበር ዝግጅቱን አጠናቋል።
በመርሐግብሩም ላይ
ሰባኪያነ ወንጌል
፩. ቀሲስ ዶ/ር መዝገቡ ካሳ
፪. ቀሲስ ዐብይ ሙሉቀን
ዘማርያን
፩. ዘማሪ ሀብታሙ
፪. ዘማሪት ወርቅነሽ ተፈራ
እንዲሁም የተለያዩ ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ያከብራል
በዕለቱ የሚኖሩን መርሃ ግብሮች
፩. ፀሎተ ወንጌል በቅዱስ ማርቆስ አባቶች እና በግቢው ዲያቆናት
፪. መዝሙር በተጋባዥ ዘማርያን
፫. ትምህርተ ወንጌል
፬. ስነ ፅሁፍ
፭. ወረብ በማኅበረ ካህናት እና በመዝሙር ክፍል
፮. ቅኔ
፯. ጭውውት
፰. ቃለምዕዳ
በዕለቱም የሚወጣ እጣ ያዘጋጀ ሲሆን እጣውን በመቁረት ግቢ ጉባኤያችሁንም እንድትደግፉ ከበረከቱም ተሳታፊ እንድትሆኑ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን!
1ኛ በገና
2ኛ Smart phone
3ኛ Air pod
4ኛ ድርሳነ ቅዱስ ሚካኤል
5ኛ ነጠላ
በተጨማሪም
ማስተዛዘኛ ለ 5 ሰው ወርሃዊ Voice package
ይሄ ሁሉ በ20ብር ብቻ
ቦታ:- በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ሥላሴ
ሰዓት ⌚️ ከቀኑ 10:00 - 4:30
ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን

ሰላም ለኩልክሙ
ገብረ ሰላመ በመስቀሉ ።
በመስቀሉ ሰላምን አደረገ
ትኩረት የሚሻ መልዕክት
እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው ዋይዜማ በሰላም አደረሳችሁ
እግዚአብሔር ቢፈቅድ የትንሣኤው መርሐግብራችን ለማክበር አጭር
ሰዓታት ቀሩን።
የዘንድሮው መርሐግብራች ከሌላው ዓመት በተለየ ቀደም ተብሎ
ከቀኑ 10:30 ላይ የሚጀመር !
ይህም የሆነበት ምክንያት መርሐግብራችንን ቶሎ ጨርሰን ወደ አገልግሎት ለመግባት እና ቅዳሴ ለማስቀደስ በሚል እሳቤ ነው።
ቦታ:መንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ አዳራሽ
ሰዓት:10:30 ( አደራ ሰዓት ይከበር የሚጀመረው ontime ነው።) ለሚመለከተው ሁሉ share አድርጉ! እና ተቀሳቅሳችሁ ተገኙ!

✥✥✥ መቃብሩን አትክፈቱ❗️❗️❗️❗️ ✥✥✥
👉 በብዛት የክርስቶስን ትንሣኤ ለመግለጽ የሚሣሉ ሥዕላት መቃብሩን ከፍቶ(ፈንቅሎ) ሲነሣ ወይም መላእክት የመቃብሩን ደጃፍ ከፍተውለት ሲነሣ ኣድርገው ነው የሚሣሉት ይህ በመጽሓፍ ቅዱስ ከተገለጸው ጋር የሚጋጭ ነው።
👉 ጌታችን የተነሣው መግነዝ ፍቱልኝ፥ መቃብሩን ክፈቱልኝ ሳይል ነው።
➛ ቅዱስ ማርቆስ በወንጌሉ እንደገለጸልን እሑድ በማለዳ ወደ ጌታ መቃብር ሽቱ ለመቀባት የሄዱት ሴቶች «ድንጋዩን ከመቃብሩ ደጃፍ ማን ያንከባልልልናል?» የሚል ጥያቄ ኣሳስቧቸው እንደነበር ይገልጽልናል።
➛ ይህን ጥያቄ ያቀረቡት “ ድንጋዩ እጅግ ትልቅ ነበርና ” በማለት የጥያቄያቸው መነሻ የሆነውን ምክንያት ያስረዳናል። {ማር ፲፮÷፩-፮፡፡}
➛ የእነዚህ ቅዱሳን ኣንስት (ሴቶች) ላሳሰባቸውን ጥያቄ መፍትሔ እንዴት እንዳገኘ ሌላኛው ወንጌላዊ ማቴዎስ በወንጌሉ እንዲህ ባለ መልኩ ይገልጽልናል፦
➛ «በሰንበትም መጨረሻ ( ሰንበት ያለው ቅዳሜን ነው) የመጀመሪያው ቀን (የመጀመሪያ ቀን ያለው የሥነፍጥረት መጀመሪያ የሆነች እሁድ ነው) ሲነጋ፥ መግደላዊት ማርያምና ሁለተኛይቱ ማርያም መቃብሩን ሊያዩ መጡ፡፡ እነሆም የጌታ መልአክ ከሰማይ ስለወረደ ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ ቀርቦም ድንጋዩን ኣንከባሎ በላዩ ተቀመጠ፡፡ መልኩም እንደ መብረቅ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ነበረ፡፡ ጠባቆቹም እርሱን ከመፍራት የተነሣ ተናወጡ፡፡ እንደ ሞቱም ሆኑ፡፡ መልኣኩም መልሶ ሴቶቹን ኣላቸው፥ እናንተስ አኣትፍሩ፤ የተሰቀለውን ኢየሱስን እንደምትሹ ኣውቃለሁና፤ እንደ ተናገረ ተነሥቶአልና በዚህ የለም፤ የተኛበትን ስፍራ ኑና እዩ። » {ማቴ ፳፰÷፩-፮፡፡}
➛ ጌታችን መቃብሩ ከፍቶ ተነስቶ ቢሆንስ ኖሮ መልኣኩ ሴቶቹ ወደ መቃብሩ ውስጥ እንዲመለከቱ መቃብሩን ከፈተው ባልተባለ ነበር። ጌታችን በዝግ መቃብር ከተነሣ በኋላ ባዶ የነበረውን መቃብር የከፈተው ይህ የጌታ መልአክ ነው፡፡
➛ መልኣኩ መቃብሩን ለምን ከፈተው ቢሉ፦ የመጡ እነዚህ ሴቶች የጌታችንን መነሣት እንዲያውቁ እና ትንሣኤውን እንዳይጠራጠሩ ነው፡፡ ኋላም ደቀ መዛሙርቱ ትንሣኤውን ያመኑት መልኣኩ ወደ ከፈተው መቃብር ገብተው መግነዙን ካዩ በኋላ ነው። ዮሐ ፳፥፯።
➛ ጌታችን መቃብሩን ክፈቱልኝ ሳይል ለምን ተነሣ ቢሉ፦ ሞቱ በፈቃዱ እንደሆነ ትንሣኤውም በሥልጣኑ መሆንን ለማስረዳት ነው።
ኣንድም፦ ሥግው ቃልን በርቀቱ ቢያጸናው ነው። ይኸውም በኅቱም ድንግልና መወለዱ፣ በባህር ላይ መራመዱ፣ በተዘጋ ደጃፍ ሳይከፈት መግባቱ፣ መቃብርም ክፈቱልኝ ሳይል መነሣቱ ጌታ ምንም እንኳን ግዝፍ የሆነ ሥጋን ቢነሣም በመለኮትነቱ ግን ረቂቅ ነው በተዋሕዶ የቃል ርቀቱ ለሥጋ ገንዘቡ በመሆኑ (ሥግው ቃልን በርቀቱ ቢያጸናው ) በድንግልና ለመወለድ የማይከልክለው፣ ባህር የማያሰጥመው፣ ደጃፍ ለመግባት የማይከለክለው፣ ለትንሣኤውም መቃብር መክፈት የማያስፈልገው መሆኑን ኣስረዳ።
👉 ስለዚህ ቅዱሳን ሥዕላት በመሣል ቤተክርስቲያንን የምታገለግሉ ይህንን መጽሓፍ ቅዱሳዊ ትምህርትን መሠረት ኣድጋች ብትሥሉ (መቃብሩን ኣትክፈቱ)፤ ምዕመናንም ይህን በመረዳት በቤታችንም ሆነ ወደ ቤተክርስቲያን የምናመጣቸውን ሥዕላትን ትክክለኛ መልእክት የሚያስተላልፍ ከቤተክርስቲያን ትምህርት ጋር የማይጋጭ መሆኑን በማገናዘብ ቢሆን ፤ እንዲሁም በሶሻል ሚዲያ የምናቀርባቸው ሥዕላትንም ይህን ያማከለ ሊሆን ይገባል። ይቆየን
መልካም በዓል ይሁንላችሁ ❗️❗️❗️

ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን፡
በዓቢይ ኃይል ወስልጣን ።
አሰሮ ለሰይጣን፡ አግዓዞ ለአዳም ።
ሰላም፡ እምይእዜሰ ።
ኮነ ፡ፍስሐ ወሰላም፡፡
እነሆ ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩር ሆኖ ከሙታን ተነስቷል፡1ኛ ቆሮ 15÷20።
እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤዉ በሰላም አደረሳችሁ እያልን በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የትንሳኤ ሎተሪ ትናንት ምሽት በይፋ መውጣቱ የታወሳል። በስፍራው ተገኝተው መካታተል ላልቻሉ አባላትም እድለኛ ቁጥሮችን እነሆ ብለናል።
1ኛ እጣ 1143 በገና
2ኛ እጣ 0265 Smart phone
3ኛ እጣ 3565 Air pode
4ኛ እጣ 1303 ድርሳነ ሚካኤል
5ኛ እጣ 0112 ነጠላ
የማስተዛዘኛ እጣዎቸ
6ኛ እጣ 0697
7ኛ እጣ 4026
8ኛ እጣ 0141
9ኛ እጣ 2286
10ኛ እጣ 0650
ከ6-10 ያሉት ሁሉም የወርሃዊ የድምጽ ጥቅል እድለኞች ናቸው።
እድለኞች እንኳን ደስ አላችሁ።
በ @Mi121919 ላይ በማሳወቅ ሽልማቱን መቀበል ትችላላችሁ።
ትኬቱን በመሸጥና እና በመግዛት ለመርኃ ግብሩ መሳካት ላበረከታችሁች ተሳትፎ በግቢ ጉባኤው ስም ከልብ እናመሰግናለን።
የ2016 ዓ.ም የትንሳኤ በዓል አዘጋጅ ኮሚቴ
https://t.me/SidistKiloGibiGubae

ከትንሳኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ፡-
#ሰኞ
#ማዕዶት_ይባላል፡- ማዕዶት ማለት መሻገር፣ ማለፍ ማለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን፡፡
#ማክሰኞ
#ቶማስ_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ፤ ጌታዬና አምላኬ ብሎ መመስከሩ ይዘከራል፡፡ ዮሐ. 20፡27-29
#ረቡዕ
#አልአዛር_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታ ኢየሱስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን፡፡ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ፡ በድልም ያረገ ንጉሥ መሆኑን እንመሰክራለን፡፡
#ሐሙስ
#አዳም_ሐሙስ_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው ተስፋ እና የተገባለት ኪዳን እንደተፈጸመ አዳምና ልጆቹ ነጻ እንደወጣን እናስባለን፡፡
#አርብ
#ቅድስት+ቤተክርስቲያን_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ስለመመስረቷ ይሰበካል፡፡ ክርስቶስ ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል፡፡ ቤተክርስቲያን ስንል ሕንፃውን ሳይሆን አማኞችን ነው፤ ክርስቶስ ለሕንፃ አልሞተምና፡፡
#ቅዳሜ
ቅዱሳት_አንስት_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን አካል ሽቶ ለመቀባት ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውና ትንሣኤውንም ቀድመው ማየታቸው ይሰበካል፡፡
#እሁድ
#ዳግም_ትንሳኤ_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሦስተኛ ጊዜ ለደቀመዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል፡፡