የሸዋ ልጆች/Shoa
7.37K subscribers
271 photos
12 videos
18 files
125 links
እንኳን ደህና መጡ‼️
✔️ ቻናሉን ለመቀላቀል join
https://t.me/Shoaost
ከልብ አመሰግናለሁ♥️🙏
Download Telegram
እምዬ ምኒልክ ጥቁር የነጮቹ ጌታ! "Menelik is a king today and forever."
182ኛ አመት እንኳን ተወለዱልን አባትነት👑🎉🎊❤️‍🩹 ለበለጠ መረጃ
ቻናሉን ለመቀላቀል join
https://t.me/Shoaost
28🔥6🥰4👏2
መንዝ ሸዋ!
ለበለጠ መረጃ
ቻናሉን ለመቀላቀል join
https://t.me/Shoaost
5🔥4
በዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና 563 ሺ 960 ተማሪዎች ተመዝግበው 550 ሺ 210 ተማሪዎች ፈተናውን ወስደዋል።

ፈተናውን ከወሰዱት ውስጥ 12.8 በመቶ የሚሆኑት ተማሪዎች 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ ማምጣት ችለዋል።

በአጠቃላይ ፈተናውን ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል ማለፍ የቻሉት 70 ሺ 544 ናቸው።

ካለፉት መካከል በተፈጥሮ ሳይንስ 16.5 በመቶ ሲሆኑ በማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ 8.33 በመቶ ናቸው።

ከፍተኛ ውጤት በተፈጥሮ ሳይንስ ወንድ 591.6 ከ600 ተመዝግቧል። ተማሪው የኦዳ ስፔሻል ቦርዲንግ - አዳማ ተማሪ ነው።

ከሴት ደግሞ 583 ከ600 ሲሆን ከእንጅባራ አገው ምድር ትምህርት ቤት ነው።

በማኅበራዊ ሳይንስ ወንድ 576.2 ከዶዶላ ኢፋ ቦሩ ት/ቤት ተመዝግቧል።

በሴት 569.1 ከቦሌ ሱፐር ሆሊሴቪየር ት/ቤት ተመዝግቧል።

ተማሪዎች #ውጤታቸውን ከሰኞ ጠዋት ወይም ማክሰኞ ከሰዓት ጀምሮ መመልከት ይችላሉ።

በውጤታቸው ላይ ቅሬታ የሚኖራቸው ከሆነም 5/6 ቀናት ቅሬታ የማቅረቢያ ጊዜ የሚሰጣቸው ይሆናል።
ለበለጠ መረጃ
ቻናሉን ለመቀላቀል join
https://t.me/Shoaost
2🔥1🥰1😨1
የ12ኛ ክፍል ውጤት ለማየት ከታች ባለው ቴሌግራም ይቀላቀሉ። ሰኞ ይለቀቃል!
ቻናሉን ለመቀላቀል join
https://t.me/Shoaost
👏3🥰1
በአገው ምድር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ28 ዓመታት ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበችው ተማሪ ቤተ መጻሕፍት በስሟ ተሰየመላት

#Ethiopia | በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር እንጅባራ ከተማ በሚገኘው የአገው ምድር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ባለፉት 28 ዓመታት ከተመዘገቡት ሁሉ በላጭ የሆነ የትምህርት ውጤት ተመዝግቧል።

የኢትዮጵያ ሚሊኒየም በገባበት በ2000 ዓ.ም የተወለደችው ተማሪ ህዳሴ ዘመኑ በ11ኛ ክፍል የትምህርት ዘመኗ 99.67 በመቶ ያመጣች ሲሆን ይህም በትምህርት ቤቱ ታሪክ ውስጥ የመጀመሪያው ከፍተኛ ውጤት ነው።

በአሁኑ ወቅት የ12ኛ ክፍል ተማሪ የሆነችው ህዳሴ ያስመዘገበችውን ድንቅ ውጤት እና ጥረት ለማስከበር ትምህርት ቤቱ ቤተ መጻሕፍቱን በስሟ ህዳሴ ቤተ መጻሕፍት በማለት ሰይሞላታል።

ተማሪ ህዳሴ የተደረገላት እውቅና ለቀጣይ ጥረቷ ትልቅ የመንፈስ ጥንካሬ እንደሆናት ገልጻ ወደፊት በሶፍትዌር ቴክኖሎጂ ዘርፍ በመሰማራት ሀገሯን የማገልገል ትልቅ ራዕይ ሰንቃ በመማር ላይ ትገኛለች።

በሌላ በኩል በትምህርት ሚኒስቴር ይፋ በተደረገው የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገራዊ ፈተና ውጤት ከአገው ምድር ትምህርት ቤት በተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ በሴቶች 583 ከ600 እንዲሁም በወንዶች 591.6 ከ600 በመመዝገብ ከፍተኛ ውጤት ከተመዘገበባቸው ትምህርት ቤቶች አንዱ ለመሆን ችሏል።

#Education #AcademicExcellence #InspiringStudents #Injibara
የ12ኛ ክፍል ውጤት ለማየት ከታች ባለው ቴሌግራም ይቀላቀሉ። ሰኞ ይለቀቃል!
ቻናሉን ለመቀላቀል join
https://t.me/Shoaost
17👏4🥰3
ባለፈው የኢራኑ ፕሬዚዳንት የነበረው አህመዲን ነጃት ከፕሬዝዳንት ሲለቅ በባቡር ከህብረተሰቡ ጋር ተሳፍሮ እየሄደ ባቡር ላይ ታየ ተብሎ አድናቆት እና ግርምት ተፅፎ አይተን ነበር።
ክቡር ፕሬዚዳንት
ክቡር ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
ክቡር የጠቅላይ ሚኒሴተሩ አማካሪ
የሆኑት እጅግ በሳል ሰው አቶ ገዱ አንዳርጋቸው አለነ
የኢትዮጵያ ልጅ ፣የአማራ ልጅ፣ዕንቁ የወሎ ልጅ ናቸው።
እሳቸው 98 ቢሊዮን በተዘረፈባት ኢትዮጵያ እጃቸው ቢዘረጋ ልባቸው ቢፈልግ በእውነት ቦሌ ላይ 1000 ካሬ ሜትር እና 1 ቢሊዮን የኢትዮጵያ ብር ያጡት ነበር??

አትዘባበቱ ቀን ጣለው ብላችሁ፤
ከፊታችሁ ቀድሞ ታገኙታላችሁ።

በነገራችን ላይ ሰዎችን ለመኮንን ለማሸማቀቅ ሲታሰብ ፈጣሪ ከፍ ያደርግሃል ።
ቻናሉን ለመቀላቀል join
https://t.me/Shoaost
10👍4👏1
እውነት መልክ ቢኖራት ክቡር ገዱን ትመስላለች። 🙏
We remember all your genuine leadership.
ቻናሉን ለመቀላቀል join
https://t.me/Shoaost
🥰32👍1
የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤት

ተፈታኞች ውጤታችሁን ከምሽቱ 1:00 ጀምሮ ማየት ትችላላችሁ

አዲስ አበባ — የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2018 ትምህርት ዘመን የሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) ተፈታኞች ውጤታቸውን ማየት የሚችሉበትን አማራጮች ይፋ አድርጓል።

በዚህም መሠረት ተፈታኞች ዛሬ ነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ.ም ከምሽቱ 1:00 ሰዓት ጀምሮ የተመቻቹትን ዲጂታል አማራጮች በመጠቀም ውጤታቸውን መመልከት ይችላሉ።

ውጤት መመልከቻ አማራጮች፡

1ኛ በድረ-ገጽ (Website): https://result.eaes.et

2ኛ.በቴሌግራም ቦት (Telegram): https://result.eaes.et/telegram

3ኛ በአጭር የጽሑፍ መልዕክት (SMS): https://result.eaes.et/sms

የቅሬታ ማቅረቢያ ጊዜና መንገድ አገልግሎቱ አያይዞ እንዳሳወቀው፣ በውጤቱ ላይ ቅሬታ ያላቸው ተፈታኞች በአካል መምጣት ሳይጠበቅባቸው በኦንላይን ማቅረብ ይችላሉ።

ቅሬታ ለማስገባት https://result.eaes.et/complaint የሚለውን ማስፈንጠሪያ መጠቀም የሚቻል ሲሆን፣ ማመልከቻው ከዛሬ ነሐሴ 19 እስከ ነሐሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ሰዓት ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆያል። የተሰጠውን ምላሽም በተመሳሳይ ሊንክ መከታተል ይቻላል።

©️የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
ቻናሉን ለመቀላቀል join
https://t.me/Shoaost
4👏2
የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ።

የ2018 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ተደርጓል። ተፈታኞችም ውጤታቸው ማየት ጀምረዋል።

ውጤት ለማየት ፦
👉 በድረ ገጽ ፡ https://result.eaes.et
👉 ቴሌግራም፡ https://result.eaes.et/telegram
👉 አጭር የጽሑፍ መልዕክት፡ https://result.eaes.et/sms

በአንድ ጊዜ በርካታ ተማሪዎች ውጤታቸውን ለማየት ስለሚሞክሩ የኔትዎርክ መጨናነቅ ሊያጋጥም ስለሚችል ደጋግሞ መሞከር ይገባል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ተፈታኞች ቅሬታ ሲኖራቸው በአካል መምጣት ሳያስፈልጋቸው

https://result.eaes.et/complaint

የሚለውን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም ቅሬታቸውን ከነሐሴ 19 እስከ 26/2018 ዓ/ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብና ምላሹንም በዛው ማስፈንጠሪያ መከታተል እንደሚችሉ ተገልጿል።
ቻናሉን ለመቀላቀል join
https://t.me/Shoaost
4🥰1
UG_Regular_Program.pdf
2.2 MB
ለሁሉም ለአለፋ ለምታውቋቸው ለአካባቢው ተማሪዎች አሳውቋቸው ማመልከት ትናንት ተጀምሯል
በሁለቱ እንዲያመለክቱ ንገሯቸው 1.ፕሬዜዳንሻል ስኮላርሽፕ (Entrance result 500+(including
2.ገቨርንመንት ስኮላርሽፕ(300+(including
Inform all passed their Entrance exam
መልካም ዕድል ! ለበለጠ መረጃ
ቻናሉን ለመቀላቀል join
https://t.me/Shoaost
1👍1
#ታላቅ_የበረከት_ጥሪ!
#ድንጋይ_ለበስ_ማርያም!

በሰሜን ሰዋ ሀገረስብከት መንዝ ቀያ ገብርኤል ቆላቆ ቀበሌ የምትገኘው ድንጋይ ለበስ ማርያም ገዳም የማስፋፊያ እና እድሳት ስራ እየተሰራ መሆኑ ይታወቃል። በመሆኑም ብዙ ደጋግ ወገኖችም በገንዘባቸው፣ በእውቀታቸው፣ በጉልበታቸው እየተባበሩ ይገኛሉ። ነገር ግን አሁንም በቂ ስላልሆነ ስራው ገና መጀመሩ ስለሆነም፣ በሀገር ውስጥም ከሀገር ውጭም የምትገኙ ውድ የቤተክርስቲያን ወዳጆች እና ልጆች አቅማችሁ የቻለውን የበረከት ትብብር ታደርጉ ዘንድ በእግዚአብሔር ስም እንጠይቃችኋለን።

1000259781365 ኢ.ን.ባ የአሰሪ ኮሚቴው አካውንት ነው።

እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ምልጃና ጥበቃዋ አይለየን 🙏
አሜን፫
ለበለጠ መረጃ
ቻናሉን ለመቀላቀል join
https://t.me/Shoaost
21🥰5👍3👏2