የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል በሪፎርም ስራዎች ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ
ሸካ ዞን፤ግንቦት4/2018(መ.ኮ.ጉ)በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል በሪፎርም ስራዎችና በመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ማስጀመሪያ ለባለድርሻ አካላት ስልጠና መስጠት ተጀመረ።
መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሸካ ዞን ፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ደበበ እንደሻው እንደገለፁት ስልጠናው እውቀታችንን ለማሳደግ፣ ልምዶቻችንን ለመለዋወጥ፣ እንዲሁም በተቋማትና በህብረተሰቡ ውስጥ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የሚያስችሉ አዳዲስ ሀሳቦችንና ክህሎቶችን ለመቅሰም እንደሚያግዝ ገልፀው መረጃ መቀበል ብቻ ሳይሆን አመለካከትን ለማሻሻል፣ የስራ ባህልን የማጎልበት ብቃትን ወደ ከፍተኛ ደረጃ ለማሸጋገር ያግዛል ነው ያሉት።
አክለውም ሰልጣኞች ከስልጠናው የሚያገኙትን እውቀት በወረቀት ላይ ብቻ የሚቀር ሳይሆን ወደ ተግባር ተቀይሮ በስራ ላይ ለውጥ ማምጣት አለበት ብለዋል።
አሁናዊ የአለም ሁኔታ ፈጣን ለውጦች እየተመዘገበ ባሉበት ጊዜ እራስን በእውቀትና በክህሎት ማዘመን እንደሚገባ ገልፀው ይህንን ስልጠና እንደ ትልቅ ዕድል በመውሰድ በሙሉ ትኩረት እንዲሳተፉ ጠቁመዋል።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የፐብልክ ሰርቪስ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳምሶን መለሰ የስልጠናው ዓላማ ተግባርን በዕውቀት ለመምራት፣ የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄን ለመመለስ እንዲሁም ከአሰራርና አደረጃጀት አንጻር ወቅቱ የሚፈልገውን ተልዕኮ የመፈጸም አቅም ካለመገንባታቸው ጋር ተያይዞ የሚስተዋለውን ቀልጣፋና ውጤታማ የአገልግሎት አሰጣጥ ተደራሽነት ችግሮችን በመቅረፍ የዜጎችን የአገልግሎት እርካታ ማሳደግ የሚያስችል ተቋማዊ የሪፎርም የአሰራር ስርዓት ለመዘርጋት ያለመ እንደሆነ አብራርተዋል ።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የሲቪል ሰርቪስ የተቋማት አቅም ግንባታ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተዘራ ታደሰ በሰነድ ላይ እንደገለፁት የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥን በማሻሻል ቀልጣፋ፣ ጥራት ያለውና የህብረተሰቡን እርካታ ለማሳደግ መሶብ አንድ ማዕከል ወደ ትግበራም መግባት እንዳለበት በአጽንኦት ገልፀዋል።
ሪፎርሙ የመንግስት አስተዳደርን በማሳለጥ ለአገልግሎት ፈላጊው ከብልሹ አሰራር የፀዳ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል መሳሪያ መሆኑም ገልፀው ስልጠናው ለሁለት ተከታታይ ቀን እንደሚቆይ ተናግረዋል ሲል የዘገበው ቴፒ ከተማ ኮሙኒኬሽን ነው።
ለተጨማሪ መረጃዎች በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ይከታተሉን 👇
📌በፌስቡክ። https://www.facebook.com/profile.php?id
📌በቴሌግራም https://t.me/Shekazonecom
📌 በዋትስአፕ: https://whatsapp.com/channel/0029Vb5H4XMDzgTEyOsVsw2z
📌በኢንስታግራም: https://www.instagram.com/shekazonecommunication?igsh=YzljYTk1ODg3Zg==

Telegram
Sheka Zone Communications
ወቅታዊ ዜናዎችና መረጃዎችን ለህዝቡ ተደራሽ ለማድረግ የተከፈተ የቴሌግራም ቻናል 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ኢኮኖሚ በሚያመነጨው ሀብት ልክ ገቢን በአግባቡ በመሰብሰብ የክልሉን የልማት ፍላጎት ማሳካት እንደሚገባ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) አሳሰቡ
የክልሉ የ2018 የእስካሁን ገቢ አፈፃፀምና ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ የባለድርሻ አካላት የውይይት መድረክ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በተገኙበት በቦንጋ ከተማ ተካሂዷል።
በክልሉ የልማት ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ በመሆኑ ይህን የመልማት ፍላጎት በአግባቡ መመለስ የሚቻለው ኢኮኖሚ በሚያመነጨው ሀብት ልክ ገቢን መሰብሰብ ሲቻል ብቻ በመሆኑ የገቢ አሰባሰብ ስራ በቅንጅትና በኃላፊነት መንፈስ ልፈፀም ይገባል ብለዋል።
ገቢ አሰባሰብ ወቅት የሚታዪ ማጭበርበሮችን ለመከላከል በተለይ ዘርፉን በቴክኖሎጂ ማስደገፍና የኦዲት ስርዓትን ማጠናከር እንደሚገባም ጠይቀዋል። የባለሙያዎችን የስነምግባር ችግር ለመቅረፍ ጥብቅ እርምጃዎችን መውሰድ እንደሚገባና አቅማቸውን ለማሳደግ ተከታታይ ግንዛቤዎችን መስጠት እንደሚገባም ገልፀዋል።
በበጀት ዓመቱ ከማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት፥ታክስ ያልሆኑ ገቢዎችና የገጠር መሬት መጠቀሚያ ግብር አፈፃፀም ዝቅተኛ በመሆኑ የበጀት ዓመቱን እቅድ ለማሳካት በልዩ ቁርጠኝነት ልሰራ ይገባል ብለዋል።
በኦዲት የተገኘውን ታክስና ውዝፍ እዳዎችን በተቀመጠው አጭር ጊዜ በማስፈፀም የገቢ ጉድለቶችን መሙላትም ትኩረት ልደረግበት እንደሚገባ ርዕሰ መስተዳድሩ በአፅንኦት ጠይቀዋል።
የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ህይወት አሰግድ በበኩላቸው ቢሮው የግብር ህግ ተገጂነትን ለማስከበርና የሰራተኞችን አቅም በማሳደግ የክልሉን ገቢ አቅም ለማሳደግ አልሞ እየሰራ ይገኛል ብለዋል። የባለሙያዎች የአቅም ክፍተትና የአሰራር ብልሹነትን ለማወቅ ልዩ የግምገማ ስርዓት ተዘጋጅቶ የስነምግባር ጉድለት የገጠማቸው ባለሙያዎችን አስተዳደራዊና ህጋዊ እርምጃዎችን የሚወስድ ስራ ተጠናክሮ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
የገቢ አሰባሰብ ስርዓትን በቴክኖሎጂ ለማስደገፍ የካሽ ሪጅስተር ማሽኖችን የማቅረብ ስራ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የጠቆሙት ኃላፊዋ ማሽኑ በተለይ ከተጨማሪ እሴት ታክስ የሚገኘውን የገቢ አቅም ከማሳደግ አንፃር ትልቅ ድርሻ ይኖረዋል ብለዋል። ተጨማሪ እሴት ታክስ አፈፃፀም ላይ የሚታየውን ክፍተት ለመሙላት በተለይ ተገልጋዮች ከሆቴሎች፣ ከአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ደረሰኝ ጠይቆ የመቀበል ልምድ ማደግ እንዳለበት ጠይቀዋል።
SWC