ሰው ሲኖር-Sew Sinor
Photo
Dude ማሰብ አትችልም የኦርቶዶክስ ቤቱ ክርስቲያንን ጥልቀት ኢየሱስን ላስተምርሽ ልትላት ቀርቶ። ሳምንቱን ሙሉ አንተ ቀደህ ማትጨርሰውን ስንትና ስንት ገጽ ግብረ ሕማማት መጽሐፍ ስታነብ በጸሎት በስግደት ኢየሱስን እና ኢየሱስን ብቻ እያሰበች ቆይታ ዛሬ በስቅለት ቀን ጸሐይ መጨለሟን ጨረቃ ደም መልበሷን እያሰበች መጋረጃዋን ቀድዳ፣ መቅደሱን ዘግታ ሁሉን ንዋያተ ቅድሳት ከውጪ እንዲታይ ታደርጋለች። መቅደስ ተቀደደ ጸሐይ ደም መሰለች ስትል እንዲሁ ሳይሆን ታሳያለች። ማዕጠንቱ ሁሉ ወግ አለው። ሞቱን መግነዝ አድርጋ አምላኳን እያሰበች። ሁሉ ሲያበቃ ነፍስና ስጋን በሚያላቅቅ ዜማ
አምንስቲቲ ሙኪርያ አንቲ ፋሲልያሱ
አምንስቲቲ ሙአግያ አንቲ ፋሲልያሱ
አምንስቲቲ ሙዳሱጣ አንቲ ፋሲልያሱ
ትላለች። ያኔ ነው እርጥብ ወረት የመላው እኔነቴ ከጌታ ጋር ነህ ዛሬ የሚለኝ። ማርያምን ያችን ቅጽበት ዘጠኝ ሞት ቢመጣ!
ለከ ኃል ክብር ወስብሐት ወዕዘዝ ለዓለመ ዓለም፣
አማኑኤል አምላኪየ ለከ ኃይል ወስብሐት ወዕዘዝ ለዓለመ ዓለም፣
ኦ እግዚእየ ኢየሱስ ክርስቶስ ለከ ኃይል ክብር ወስብሐት ወዕዘዝ ለዓለመ ዓለም፣
ለአምላክ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ ለዓለመ ዓለም
ለሥሉስ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ ለዓለመ ዓለም
ለማሕየዊ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ ለዓለመ ዓለም
ለመንግሥቱ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ ለዓለመ ዓለም
ለዕበዩ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ ለዓለመ ዓለም
ለእዘዙ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ ለዓለመ ዓለም
ለሥልጣኑ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ ለዓለመ ዓለም
ለምኩናኑ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ ለዓለመ ዓለም
ለኢየሱስ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ ለዓለመ ዓለም
ለክርስቶስ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ ለዓለመ ዓለም
ለሕማሙ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ ለዓለመ ዓለም
ለመስቀሉ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወእዘዝ ለዓለመ ዓለም
ለከ ይደሉ ኃይል ለከ ይደሉ ስብሐት ወለከ ይደሉ አኮቴት ኦ እግኢእየ ኢየሱስ ክርስቶስ ለዓለመ ዓለም
ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ
እንኳን አደረሰን!
❤️
© ዮሀንስ ሞላ

❤2
ጌታችን ሲሰቀል ፀሐይ ለምን ብርሃኗን ከለከለች
“ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተሰቀለ ጊዜ ከስድስት ሰዓት እስከ ዘጠኝ ሰዓት በምድር ላይ ጨለማ የኾነው ለምንድን ነው?” ብለህ ትጠይቀኝ ይኾናል፡፡ እኔም እንዲህ ብዬ እመልስልሃለሁ፡- ፀሐይ ብርሃኗን የከለከለችው፣ ጨረቃ ደም የለበሰችው፣ ከዋክብትም የረገፉት አይሁድ አስቀድመው “ከአንተ ምልክት ልናይ እንወዳለን” ባሉት ጊዜ “ዐመፀኛዪቱና አመንዛራዪቱ ትውልድ ምልክትን ትሻለች፡፡ ምልክት ግን ከነቢዩ ዮናስ በቀር አይሰጣትም” ብሎ በነገራቸው መሠረት የስቅለቱን፣ ወደ መቃብር የመውረዱንና የትንሣኤውን ምልክት ሲያሳያቸው ነው፡፡
ዳግመኛም በሌላ ጊዜ የስቅለቱን ነገር በተናገረ ጊዜ፡- “የሰውን ልጅ ከፍ ከፍ ባደረጋችሁት ጊዜ እኔ እንደ ኾንሁ ያን ጊዜ ታውቃላችሁ” ብሏቸው ነበር (ዮሐ.8፡28)፡፡ ይኸውም እንዲህ ሲላቸው ነው፡- “በሰቀላችሁኝ ጊዜ ድል እንደነሳችሁኝ ታስባላችሁ፡፡ ነገር ግን መለኮታዊ ኃይሌን ታውቃላችሁ፡፡”
ጌታችን ከተነሣ በኋላ ከተማይቱ ተደምስሳለችና፤ እስራኤልም እንደ አገር ጠፍታለችና፤ ከግዛታቸውና ከሉዓላዊ አገራቸው ወድቀዋልና፡፡ ወንጌል ግን ተስፋፍታለችና፤ ቃለ እግዚአብሔር እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ - በባሕርም በየብስም ተሰብኳልና፤ ሰው የሚኖርበትም ምድረ በዳም ኹሉ የቃሉን ኃይል ምስክር ናቸውና፡፡
ስለዚህ “እኔ እንደ ኾንሁ ያን ጊዜ ታውቃላችሁ” ሲላቸው ይህንንና በስቅለቱ ሰዓት የኾነውን የተደረገውን ሲነግራቸው ነው፡፡ በምድር በላይ እየተመላለሰ ካደረጋቸው ይልቅ በመልዕልተ መስቀል ላይ ሳለ የተደረጉት እጅግ ይበልጣልና፡፡
ተአምራቱ እንደዚህ ግልጽ የኾነው ግን በዚህ መንገድ ብቻ አይደለም፤ እነርሱ በዓይናቸው ያዩትና በላይ በሰማይም ተድርጓል፡፡
ይህ በምድር ኹሉ ላይ ሲከናወንም አንድ ጊዜ ብቻ በግብጽ ምድር በፋሲካው ዕለት ከተደረገው በቀር መቼም ቢኾን መች ተደርጎ አይታወቅም፡፡ በግብጽ ጨለማ የኾነውም የዚህ በዛሬው ዕለት ለተፈጸመው ምሳሌ ስለ ነበር ነው፡፡
ምድር ጨለማ የኾነችው በየትኛው ጊዜ ላይ እንደ ኾነም ተመልከቱ፡፡ እኩለ ቀን ላይ! ለምን? በምድር ኹሉ የሚኖሩት ሰዎች ይህን ያውቁት ዘንድ! ስለዚህ አይሁድ ወደ አሚነ ክርስቶስ ይመለሱ ዘንድ ተአምራቱ እጅግ ታላቅ ከመኾኑም ባለፈ ጊዜውም ቀትር ላይ ኾነ፡፡ ከሰደቡት፣ ከገረፉት፣ እጅግ ቁጣቸውን ከገለጡ፣ በእርሱ ላይ መሳለቃቸውን ከጨረሱ፣ ካፌዙበት፣ በልባቸው የነበረውን ክፋት ኹሉ ከተናገሩ በኋላ ቢያንስ ተአምራቱን ተመልክተው እንኳን ይመለሱ እንደ ኾነ ምድር ኹሉ ጨለማ እንድትኾን አደረገ፡፡
“ከመስቀል ላይ ይውረድ፤ እኛም እናምንበታለን” ብለው ይናገሩ ነበርና ከመስቀል ከመውረድ በላይ ይህ እጅግ ዕፁብ ድንቅ ነበርና፤ እዚያ መስቀል ላይ ኾኖ እነዚህን ማድረጉ ከሕሊናትም የሚያልፍ ነበርና፡፡ እርሱ ራሱ እነዚህን አደረጋቸው ቢሉ ፈርተው እንዲያምኑበት፣ እርሱ ሳይኾን አባቱ እነዚህን ተአምራት አደረጋቸው ቢሉም ባደረጉት ክፋት ኹሉ ተቆጥቶ ምድር ኹሉ ጨለማ እንድትኾን እንዳደረጋት ዐውቀው አዝነውም እንዲመለሱ ለማድረግ ነበር፡፡ ምክንያቱም የተደረገው የፀሐይ ግርዶሽ አይደለም፡፡ እንዲመለሱ ለማድረግ ቢኾንም ቅሉ የተገለጠው የእግዚአብሔር ቁጣም ነው፡፡ የጨለማው ቆይታም ይህን የሚያስረዳ ነው፤ ምድር ኹሉ ጨለማ የኾነችው ለሦስት ሰዓታት ነውና፡፡ ግርዶሽ ግን የሚቆየው ለተወሰኑ ደቂቃዎች ብቻ ነው፡፡
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ - አምስቱ የንስሐ መንገዶች)

#ቀዳም_ሥዑር
✝️✝️✝️
ቅዳሜ፡–#ቀዳም ሥዑር ይባላል፡፡ በዚች ዕለች ከድሮው በተለየ መልኩ የጌታችንን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትውል የተሻረችው ቅዳሜ ትባላለች፡፡
✝️✝️✝️
#የማትጾመዋ ቅዳሜ ስለምትጾም ስዑር /የተሻረች/ ተብላለች በዓል መሻርን አይመለከትም በቀዳም ሥዑር ሌሊት ሥርዓቱ የሚጀመረው በመኀልየ ሰሎሞን ምንባብ ነው፡፡ ማኀሌቱም እዝሉ እየተቃኘ እየተመጠነ፣ እየተዘመመ እየተመረገደ እየተጸፋ ያድራል፡፡ ጠዋት አቡን መዋሥዕት ውዳሴ ማርያም ዜማ ተደርሶ ወለመልአከ ሕይወትሰ ሰቀልዎ በሚለው ሰላም ይጠናቀቃል፡፡በዚህ ዕለት ልብሰ ተክህኖ የለበሱ ካህናትና ዲያቆናት ቄጤማ ተሸክመው ቃጭል ሲያቃጨሉ መታየታቸው ዕለተ ትንሣኤውን ለሚናፍቅ ምእመን ትልቅ ብስራት ነው፡፡
✝️✝️✝️
#ለምለም ቅዳሜ፡- ካህናቱ ለምእመናን ለምለም ቀጤማ የሚያድሉበት ዕለት ስለሆነ በዚህ ተሰይሟል፡፡ ቀጤማውንም ምእመናን እስከ ትንሣኤ ሌሊት በራሳቸው ላይ ያስሩታል፡፡
✝️✝️✝️
#በቀዳም ስዑር ቀሳውስቱና ዲያቆናቱ ቃጭል /ቃለዓዋዲ/ እየመቱ ገብረ ሰላመ በመስቀሉ ትንሣኤሁ አግሃደ የሚለውን ያሬዳዊ ዜማ በመዘመር፤ ጌታ በመስቀሉ ሰላምን እንደሰጠን እና ትንሣኤውንም እንደገለጠልን በማብሰር፤ ቄጤማውን ለምእመናን ይሰጣሉ፡፡ ምእመናኑም በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚውል ገጸ በረከት ያቀርባሉ፡፡ ቄጤማውንም በራሳቸው ያስራሉ፡፡ ይህም አይሁድ ጌታችንን እያሰቃዩ ሊሰቅሉት ባሉ ጊዜ የእሾህ አክሊል ጭንቅላቱ ላይ ያሠሩበትን ድርጊት የሚያስታውስ ነው፡፡
✝️✝️✝️
#የቀጤማው አመጣጥና ምስጢርም ከአባታችን ከኖኅ ታሪክ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ምድር በማየ አይኅ /በጥፋት ውኃ/ በጠፋችበት ወቅት የኖኅ ታማኝ መልእክተኛ ርግብ የውኃውን መጉደል ያበሰረችው ቀጤማ ይዛ በመግባት ነው፡፡
✝️✝️✝️
#ዛሬም ለሐዲስ ኪዳን ክርስቲያኖች የኃጢአት ውኃ ጐደለ፣ የኃጢአት ውኃ ጠፋ በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ነጻነት ተሰበከ ታወጀ በማለት ካህናት ቄጠማ ይዘው ምእመናንን ያበሥሩበታል፡፡
✝️✝️✝️
#ቅዱስ ቅዳሜ ይባላል፡፡ ቅዱስ ቅዳሜ መባሉ ቅዱስ የሆነ እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ፍጥረታትን አከናውኖ ከፈጠረ በኋላ በዚህ ቀን ከሥራው ሁሉ ያረፈበት ነው፡፡ በዘመነ ሐዲስ ደግሞ የማዳን ሥራውን ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው በመቃብር ሲያርፍ፣ በነፍሱ ሲዖልን በርብሮ ባዶዋን አስቀርቷታል፡፡ በዚያ ለነበሩት ነፍሳትም የዘለዓለም ዕረፍትን ያወረሰበት ዕለት ስለሆነ ከሌሎቹ ዕለታት የተለየ ዕለት ለማለት ቅዱስ ቅዳሜ ተብሏል፡፡
✝️✝️✝️
#ምእመናን ሆይ፣ በአጠቃላይ ሥርዓተ ሕማሙን፤ ሰሙነ ሕማማት ብለው የተለየ ሥርዓት አውጥተው አባቶቻችን ተግተው ያቆዩልንን ሥርዓተ መላእክት ልንጠብቀውም ልንጠቀምበት ይገባል፡፡ የዕለታቱን ክብርና ስያሜ ከማወቅና ከመረዳት ጋር በዕለታቱ የታዘዙትን ሃይማኖታዊ ግዴታዎችን መወጣት ከሁላችንም ይጠበቃል፡፡

❤1🕊1
ም ን : ያ ህ ል : አ ል ቅ ሳ : ይ ሆ ን !?
በዕለተ ዓርብ በቤተ መቅደስ ዲያቆናት በሚያሳዝን ውርድ ንባብ በሚያነቡት የግብረ ሕማማት ክፍል ላይ እመቤታችን በዚያን ዕለት ስለተሰማት ነገር እንዲህ ተጽፎ እናገኝዋለን ፡-
‹‹ ዓለም ድኅነትን በመቀበሉ ደስ ይለዋል ፤ ልጄ ሆይ!ፈጣሪዬና መድኃኒቴ ስለ ሁሉ ሕይወት ብለህ ወደ ታገሥካት ወደ ስቅለትህ በተመለከትሁ ጊዜ አንጀቴ ተቃጠለ ! ›› (ግብረ ሕማማት ዘዓርብ 9 ሰዓት)
በቤተልሔም በግርግም በወለደችው ጊዜ በጨርቅ ጠቅልላ ያስተኛችውን ልጅዋን በዚያች ዕለት በአደባባይ ልብሱን ሲገፍፉትና ዕርቃኑን ሲያቆሙት ምን ያህል አልቅሳ ይሆን ?
በደረትዋ አስጠግታ በጀርባዋ አዝላ ያሳደገችውን አንድ ልጅዋን አጥንቱ እስከሚቆጠር ሥጋው እስከሚነጭ ደሙ እንደ ውኃ እስከሚፈስ ድረስ ሲገርፉት ቆማ ስታይ ምን ያህል አልቅሳ ይሆን ?
በንጉሥ ሄሮድስ ሰይፍ እንዳይሞትባት ወደ ግብፅ በረሃ እንደ ወፍ የተንከራተተችለት ልጅዋን ሰይፍና ጎመድ ይዘው ሲከብቡት ከሄሮድስ ወደ ጲላጦስ እያዳፉ ሲወስዱት ወታደሮችም ከብበው ሲደበድቡት ምን ያህል አልቅሳ ይሆን ?
ድንግልናዊ ወተትዋን አጥብታ ያሳደገችው አንዱን ልጅዋን ሐሞትና ከርቤን ሲያጠጡት ምን ያህል አልቅሳ ይሆን ?
እንደ ልጅነቱ አቅፋ ይዛው ልትሸሽ በማትችልበት በዕለተ ዓርብ ብዙ መከራ ያየችበትን ልጅዋን በወደቀበት ሲረግጡት ፣ ሲተፉበትና ሲደበድቡት ያቺ የግብፅ በረሃዋ ስደተኛ ምን ያህል አልቅስ ይሆን ?
እጆቹን በእጆችዋ ይዛ የመጀመሪያዎቹን የሕጻንነት እርምጃዎቹን በእግሮቹ እንዲራመድ የመራችው ልጅዋን እጆቹና እግሮቹን በሚስማሮች ሲቸነክሩት ቆማ በዓይኖችዋ ስታይ ምን ያህል አልቅሳ ይሆን ?
እንደ ሕጻናት ሲያለቅስ ዕንባውን የጠረገችለት ልጅዋን የእሾህ አክሊል በደፉበት ጊዜ ፊቱ በደም ተጠምቆ ስታይ ምን ያህል አልቅሳ ይሆን ?
ለሦስት ቀናት ብቻ ጠፋብኝ ብላ ለምን አስጨነቅህኝ ያለችው ድንግል በፊትዋ በአሰቃቂ ሁኔታ ሲገድሉት ምን ያህል እጥፍ ተጨንቃ ይሆን?
የኢየሩሳሌም ሴቶች እንኳን ባይወልዱትም በሰብአዊነት ብቻ ራርተው ልቅሶና ሙሾ ካወጡለት ብቻዋን ያለ አባት የወለደችው እናቱ ምን ያህል አልቅሳ ይሆን?
እስራኤላውያን የሥጋ ዝምድናን እንደሚገልጹበት አገላለጽ የአጥንትዋ ፍላጭ ፣ የሥጋዋ ቁራጭ የሆነ ልጅዋ መስቀል ተሸክሞ ሲወድቅ ሲነሣ ስታይ ምን ያህል አልቅሳ ይሆን ?
በእርግጥም : የልብ : ዓይን : ኖሮት : ካልተገኘ :በቀር የእመቤታችን : የዕለተ : ዓርብ : ኀዘንዋን : ሊያስብ : የሚቻለው : የለም ፡፡
ከሕማማት መጽሐፍ የተወሰደ

ሶርያዊው ቅዱስ ኤፍሬም ስለ ጌታ ትንሣኤ በተናገረበት ድርሳኑ እንዲህ አለ፦
አቤቱ ገነትንና በውስጧ ያሉትን የሚገልጽልኝ ሕግህ መርከቤ ነው፤ መስቀልህ ይህንን ገነት የሚከፍትልኝ የገነት መክፈቻ ቁልፍ ነው። ከለመለመው ስፍራ፣ ከገነትም አበባ፣ ጽጌረዳ እና ሽታው ጣፋጭ የሆኑን በእቅፌ ሰብስቤ አመጣሁ። እነሆ የትንሣኤህን በዓል ስናከብር እነዚህን አበባዎች ጎዘጎዝንልህ። ይኸውም ልብን ደስ የሚያሰኙ ማኅሌትና ዝማሬዎች ናቸው። አክሊላትን ለሚያቀዳጅ ለእርሱ ምስጋና ይገባል።
በዚህ በዓል ላይ በደስታ የተሞሉ የሴቶችና የወንዶች፣ የወጣቶች ድምጾች እንደ መለከት፤ የሕፃናት መዝሙሮችም እንደ በገና ድርድር ነው። ድምጻቸውም የጌታቸውን ምስጋና ይዞ ወደ ሰማይ ይወጣል። ዝምታውም ከመባርቅት በላይ ለሚሰማ ለእርሱ ምስጋና ይገባል።
እነሆ መሬት ከታች ድምጽዋን አሰማች፤ ሰማያትም ከላይ ከመባርቅት ድምጽ ጋር ጉርምርምታን አሰሙ። ሚያዝያ ሁለቱን ድምፆች አንድ ላይ አፈለቀች። እነዚህ ድምጾችም ከላይ የተሰሙ እና ከታች የተደመጡ ናቸው። ከቤተ መቅደስ የሚሰማው ምስጋናም ከመለኮታዊው ድምጽ እና ከመልካም መቅረዞች በሚንቦገቦጉት መብራቶች፣ እንደ ዝናብ ከሚፈስ ዕንባ ጋር የፋሲካውን በዓል እናከብራለን።
( #ድርሳነ_ቅዱስ_ኤፍሬም_ሶርያዊ - ገጽ 275-276 ትርጉም ዲ/ን መዝገቡ ከፍያለው)

🙏3
ወቅቱ የጋብቻ ወቅት አይደል ይነበብ፦
ማግባት ስትፈልግ አስቀድመህ ጸልይ፤ አሳብህን ለእግዚአብሔር ንገረው፡፡ እግዚአብሔር መርጦ እንዲሰጥህ ለምነው፡፡ ጭንቀትህን ኹሉ በእርሱ ላይ ጣለው፡፡ አንተ እንደዚህ እርሱ እንዲመርጥልህ የምታደርግ ከኾነም፥ አክብረኸዋልና እርሱም ለአንተ በጎ የትዳር አጋርን በመስጠት ያከብርሃል፡፡ ስለዚህ በምታደርገው ነገር ኹሉ ሽማግሌህ እርሱ እግዚአብሔር እንዲኾን ዘወትር ጠይቀው፡፡
አስቀድመህ እንደዚህ ካደረግህም፥ ወደ ትዳር ከገባህ በኋላ ፍቺ አይገጥምህም፡፡ ሚስትህ ሌላ ሰውን አትመኝም፡፡ በሌላ ሴት እንድትቀናም አታደርግህም፡፡ በመካከላችሁ [ለክፉ የሚሰጥ] ጠብና ክርክር አይኖርም፡፡ ከዚህ ይልቅ ታላቅ የኾነ ሰላምና ፍቅር በመካከላችሁ ይሰፍናል፡፡ እነዚህ ካሉ ደግሞ ሌሎች በጎ ምግባራትን፣ ትሩፋትን ለመፈጸም አትቸገሩም፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

❤9🥰1
ሰው ሲኖር-Sew Sinor pinned «ወቅቱ የጋብቻ ወቅት አይደል ይነበብ፦ ማግባት ስትፈልግ አስቀድመህ ጸልይ፤ አሳብህን ለእግዚአብሔር ንገረው፡፡ እግዚአብሔር መርጦ እንዲሰጥህ ለምነው፡፡ ጭንቀትህን ኹሉ በእርሱ ላይ ጣለው፡፡ አንተ እንደዚህ እርሱ እንዲመርጥልህ የምታደርግ ከኾነም፥ አክብረኸዋልና እርሱም ለአንተ በጎ የትዳር አጋርን በመስጠት ያከብርሃል፡፡ ስለዚህ በምታደርገው ነገር ኹሉ ሽማግሌህ እርሱ እግዚአብሔር እንዲኾን ዘወትር ጠይቀው፡፡…»
የሰርግ ወቅት ስለሆነ...
"ባልና ሚስት ሆይ! ስሙ፦
ባል ሆይ ሚስትህን ክርስቶስ ቤተክርስቲያንን እንደወደዳት ውደዳት። ክርስቶስ ስለ ቤተክርስቲያን ራሱን አሳልፎ እንደሰጠ፣ አንተም ስለ ሚስትህ ስትል መሞት ቢያስፈልግህ እንኳ ወደኋላ አትበል። ስድብን፣ መገፋትንና መከራን ሁሉ ስለ እርሷ ታገሥ። ክርስቶስ ቤተክርስቲያንን ወደ እርሱ የቀረባት በዛቻና በማስፈራራት ሳይሆን በፍቅርና በቸርነት ነው። አንተም ሚስትህን በፍቅር እንጂ በኃይል አታስገዛት። በፍርሃት የምትገዛ ሚስት ከጥቂት ጊዜ በኋላ ትሰለችሃለች፤ በፍቅር የምትገዛ ግን እስከመቃብር ታምንሃለች።
ሚስት ሆይ! አንቺም ለባልሽ ተገዢ፤ መገዛት ሲባል ግን እንደ ባሪያ መሆን ሳይሆን እንደ አካል መሆን ነው። አካል ለራስ እንደሚታዘዝ አንቺም ለባልሽ ታዘዢ። እርሱ ራስሽ ነውና። ባልሽ ባልደረባሽ እንጂ አገልጋይሽ አይደለምና ክብሩን ጠብቂ።
በቤታችሁ ውስጥ 'የእኔ' እና 'የአንተ' የሚሉ ቃላትን አጥፉ። እነዚህ ቃላት የጠብ ምንጮች ናቸው። ይልቁንም 'የእኛ' በሉ። ሀብቱ የእኛ፣ ልጆቹ የእኛ፣ ሕይወቱ የእኛ ነው በሉ። ባል ለሚስቱ እንዲህ ይበላት፦ 'እኔ አንቺን ከመውደዴ የተነሳ ዓለምንና መንግሥትን ሁሉ ብታጣ እንኳ ግድ የለኝም፤ አንቺ ከእኔ ጋር ከሆንሽ ብቻ ይበቃኛል።'
ሚስት ለባሏ እንዲህ ትበለው፦ 'የአንተ መኖር ለእኔ ከወርቅና ከብር ይበልጥብኛል።' እንዲህ ዓይነት ንግግር ባለበት ቤት ውስጥ ሰይጣን መግቢያ ቀዳዳ አያገኝም። ጸሎታችሁም አይሰናከልም።
ልጆችን በምግባርና በሃይማኖት አሳድጉ። ቤታችሁን ቤተክርስቲያን አድርጉት። መዝሙር ዘምሩ፣ መጽሐፍ ቅዱስን አብራችሁ አንብቡ። ባል ለሚስቱ፣ ሚስት ለባሏ በመንፈሳዊ ሕይወት መበርታት ምክንያት ይሁኑ። አንዱ ሲደክም አንዱ ያንሳው። በምድር ላይ በፍቅር የኖራችሁ እንደሆነ፣ በሰማያዊው መንግሥትም ለዘላለም አብራችሁ ትኖራላችሁ።"
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅን በኤፌሶን መልእክት ምዕራፍ ፭ (5) በተረጎመበት ድርሳኑ)

❤2🥰2
ጩኸቱ ኹሉ አንድ አይደለም።
የኢያሪኮ ግንብ የፈረሰው በጩኸት ነው። አንተ ግንቡን ከኾንህ ያ ኹሉ ጩኸት አይሰማህም። ውጤቱን እንጅ ድምፁን አትረዳውም። ስትፈርስ ግን ይገባሃል።

አንድን በክፉ ምግባር የተያዘን ሰው ወደ መልካም ነገር ልትመልሰው ብትወድድ መጀመርያ ሰላሙን እንዲያገኝ አድርገው፡፡ በፍቅር ቃል ከፍ ከፍ አድርገው። እንዲህ ያለን ሰው ከክፉ ስራው እንዲመለስ ለማድረግ ከዚህ የተሻለ ዘዴ የለምና። ሰው በተግባር የሚያደርገው ፍቅር ሰዎችን የመለወጥ ፍጹም ሀይል አለውና።
ቀጥለህ በፍቅር አንድ ሁለት ቃልን ንገረው፣ በቁጣ አትንገረው። በእርሱ ላይ አንዳች የጠላትነት ስሜት አታሳይ። ፍቅር ሰዎችን ለመለወጥ መንገዱን እርሱ ያውቅበታል። ብቻ እንተ እድሉን ስጠው። የፍቅር ሰውም ሁን።
(መክስምያኖስ ባህታዊ ዘሶርያ - የበረሃ ፈርጦች)

❤4
Forwarded from Orthodox Tewahdo
" የአባቶቻችን ትምህርት እናስተምራለን ፤ ተስፋቸውንም ተስፋ እናደርጋለን ፤ የተማርናት ፤ ተስፋ የምናደርጋት ሃይማኖት ይህች ናት:: እንኖርባታለን ፤ እንሞትባታለን ፤ በእግዚአብሔር ፍቃድ እንነሣባታለን "
ሃይማኖተ አበው
እንቁ መምህራችን የሆኑት እዮብ ይመኑ ትምህርቶች ለማግኘት ከታች ናለድ ሊንክ ይግቡ❤️
የይቱብ ቻናላችን ሰብስክራይብ ያድርጉ
👇👇👇
https://youtu.be/yI-3Sl9NB5c?si=1fCKjnh4FjRC2OJ9

👍1
Forwarded from Orthodox Tewahdo
Forwarded from Orthodox Tewahdo
💍ከጋብቻ በፊት ድንግልናን (ንጽኅናን) እንዴት መጠበቅ አለብን⁉️
በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ንጽሕት ሃይማኖት ውስጥ አንድ ሰው በእግዚአብሔር ፊት የተወደደ ጋብቻን ለመፈጸም በድንግልና መኖር አለበት ብዙዎቻችን በድንግልና ሆኖ ድንግል ሴት ማግባት ያለበት በክህነት የተሾመ ዲያቆን ብቻ ነው ብለው ያስባሉ!... ሙሉውን ለማንበብ
📜ሥርዓተ ቤተከርስቲያን⛪️
👇🏽👇🏽👇🏽
https://t.me/serate_beta_krstian

❤1