ስንክሳር
7.09K subscribers
830 photos
4 videos
37 files
243 links
በስንክሳር channal ስንክሳሩ ተገልጦ ቅዱሳን ይዘከራሉ፣ ወቅቱን የጠበቁ መረጃዎችን ያገኛሉ፡፡ ይከታተሉን!
Download Telegram
ዓርገ ሰማያተ በዓምደ ደመና፥
ለድንግል ተፈትሐ ማኅፀና፥
ለደቂቀ እስራኤል ዘአውረደ መና፥
ዓርገ ሰማያተ በአምደ ደመና።

ውርስ ትርጉም

በድንግል ማኅፀን፥
ያን ሥጋ አዳምን፥
ወደ አምላክነት ልዕልና ያሳረገ፥
በአምደ ደመና ወደ ሰማይ አረገ፥
ለእስራኤል ልጆች ያወረደ መና፥
ዐረገ በስብሐት በዐምደ ደመና።

ዚቅ

እንኳን ለብርሃነ ዕርገቱ በሰላም አደረሳችሁ!

____
t.me/andkelem
t.me/andkelem
እም መልክዐ አማኑኤል

ሰላም ለቀሚስከ ምስሌከ ዘልህቀ፥
እንዘ ከመ ሕፃን ትልህቅ በበሕቅ ሕቀ፥
ውስተ ብሔረ ባዕድ ክርስቶስ ኢታኅጥአኒ ሥንቀ፥
ከዊነከ ከመ ሕፃን መንክር ጥቀ፥
ዘትሰፍር በሕፍንከ ማየ ባሕር ጥቀ።

___
t.me/andkelem
t.me/andkelem
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሰኔ ዐሥራ አምስት በዚች ቀን የሰማይ ጭፍራ የተባለ የቅዱስ ሚናስ ቤተ ክርስቲያኑ መርዩጥ በተባለ አገር የከበረችበት ነው ።

ከዚህ አስቀድሞ የቅዱስ ሚናስ ሥጋ ተሠውሮ ይኖር ነበር ። ጌታችንም ሊገልጠው በወደደ ጊዜ ምክንያት አደረገ ይኸውም እንዲህ ነው ፥ የቅዱስ ሚናስ ሥጋው ተደፍኖ በሚኖርበት ኮረብታ አቅራቢያ በጎችን የሚያረባ አንድ ሰው በጎቹን እየጠበቀ ይኖር ነበር ።

ከዚያ እረኛ በጎች ውስጥ ደዌ ያለበት አንዱ በግ በዚያ በኮረብታው አጠገብ ባለ የጉድጓድ ውኃ ተጠምቆ ወዲያውኑ ከደዌው ዳነ ። እረኛውም አይቶ አደነቀ ሌሎችንም ደዌ ያለባቸውን አመጣ በዚያ ውኃም በታጠቡ ጊዜ ሁሉም ዳኑ ።

ከዚህም በኋላ ይህ በቦታው ሁሉ ታወቀ፡ደዌ ያለባቸውም ሁሉ እየመጡ አፈሩን ከውኃው ጋር አንድ አድርገው ለውሰው በመቀባት ወዲያውኑ ይድኑ ነበሩ ምክንያቱን ግን አላወቁም ።

በዚያ ውኃና በአፈሩ በሽተኞችን እንደሚያድን የዚያ በግ ጠባቂ ወሬው በሮሙ ንጉሥ ዘንድ ተሰማ ። ለንጉሡም የቁስል ደዌ የታመመች ልጅ ነበረችው ። ወደ በግ ጠባቂውም ላካት እርሱም በጎቹን እንደ አዳናቸው አዳናት ።

እርሷም በተፈወሰች ጊዜ በዚያ ቦታ ፈውስ የሚደረግበትን ምክንያት ታውቅ ዘንድ ወደደች ።
ከዚህ በኋላ ቅዱስ ሚናስ በሕልም ተገለጸላትና ሥጋዬ በዚህ ቦታ ተደፍኖ ስለሚኖር እነሆ አስቆፍረሽ ታወጪው ዘንድ እግዚአብሔር አዞሻል አላት ።
ከእንቅልፍዋም በነቃች ጊዜ ቅዱስ ሚናስ እንዳዘዛት አደረገች ። የከበረ ሥጋውንም አወጣች በዚያም ውብ የሆነች ቤተ ክርስቲያን ሠራችለት ንጉሡም በዚያ ቦታ ከተማ እንዲሠሩ መኳንንቱንና ሹሞቹን አዘዛቸው ታላቅ ከተማም ተሠራች ሰሟም መርዩጥ ተባለች ።

በረከቱ ይደርብን!
___
t.me/Andkelem
t.me/Andkelem
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የአባ ለትጹን ድንቅ የምልጃ ታሪክ / ዘሰኔ 17

በአንዲት ዕለትም ወደዚያ ገዳም ሔደ አበ ምኔቱንም ታሞ ለሞት ደርሶ አገኘው መነኰሳቱም በዙሪያው ሆነው ያለቅሱ ነበር ።

አባ ለትጹንም የሰይጣን ሠራዊትን ከበውት ደስ ሲላቸው አያቸው ።

አባ ለትጹንም አባት ሆይ በአንተ ላይ የሆነው ምንድን ነው ብሎ አበ ምኔቱን ጠየቀው እርሱም መነኰሳቱን ከአጠገቡ እንዲርቁ አዘዛቸው ።

ከዚህም በኋላ ያደረገውን በደሉን ሊነግረው ጀመረ እንዲህም አለው ከእኔ አስቀድሞ እንደርሱ ያለ ማንም ያልሠራው ኃጢአትን ሠርቻለሁና አባቴ ሆይ በጸሎትህ አትርሳኝ እኔ ቅስና ልሾም ፈልጌ ባልሾሙኝ ጊዜ ወደ ሌላ አገር ሔድሁ ኤጲስቆጶሱም ቅስና ሹሞኛል ብዬ በድፍረት በቁርባኑ ላይ የምቀድስ ሆንኩ ። ለጠላሁትም በቍርባኑ መሥዋዕት ውስጥ መርዝ አድርጌ አሰጠዋለሁ እርሱም ይሞታል ከእናቴም ጋራ ዐሥር ጊዜ ተኝቼ አለሁ ከእኔም ፀንሳ ለመውለድ በደረሰች ጊዜ ሥራይ አጠጥቼ ሕፃኑን በሆድዋ ውስጥ ገደልሁት ኃጢአቴ ብዙ ነው ተነግሮ አያልቅም ። ከበጎ ሥራም ምንም ምን የሠራሁት የለም ነገር ግን በጸሎትህ አትርሳኝ ከዚህ ከኃላፊው ዓለም መውጫዬ ደርሷልና ወዲያውም በክፉ አሟሟት ሞተ ነፍሱንም አጋንንት ሲቀበሏትና በየራሱ በሆነ ሥቃይ ሲአሠቃይዋት አባ ለትጹን አያት ። አባ ለትጹንም ልቅሶን አለቀሰ ።

አባ ለትጹን “ስለ ወዳጆቹ ነፍሱን አሳልፎ የሚሰጥ ያለ ከሆነ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር የለም” የሚለውን የቅዱስ ወንጌልን ቃል አሰበ ።
ሙሴ ጸሊም ኢትዮጵያዊ

1 (፩) አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሰኔ ሃያ አራት በዚች ቀን አባ ሙሴ ጸሊም በሰማዕትነት ሞተ ።

2 (፪) ሰዎች ከገድሉ የተነሣ ይህን ቅዱስ ያደንቁታል እርሱ አስቀድሞ መንግሥተ ሰማያትን ገፍቷት ነበረና እርሱ በሥጋው ጠንካራ በሥራውም ኃይለኛ ነበር ይበላና ይጠጣ ይቀማና ያመነዝር ነበር ይገድልም ነበር ማንም ሊቋቋመው አይችልም ነበር ።

3 (፫) አንድ በግ በአንድ ጊዜ ጨርሶ እንደሚበላና አንድ ፊቀን ወይን ጠጅ እንደሚጠጣ ስለ እርሱ ተነግሮአል ።

4 (፬) እርሱም ፀሐይን ለሚያመልኩ ሰዎች አገልጋይ ነበረ ብዙ ጊዜም ወደ ፀሐይ እያንጋጠጠ ፀሐይ ሆይ አንተ አምላክ ከሆንክ አነጋግረኝ ይል ነበር ደግሞም በልቡ የማላውቅህ ሆይ ራስህን አሳውቀኝ ይል ነበር ።

5 (፭) ከዚህም በኋላ በአስቄጥስ ገዳም ያሉ መነኰሳት እግዚአብሔርን ያውቁታል ያዩታልም እያሉ ሲነጋገሩ ሰዎችን ሰማቸው ።

6 (፮) ያን ጊዜም ተነሣ ሰይፉንም ታጥቆ ወደ አስቄጥስ ገዳም ሔደ በደረሰም ጊዜ አባ ኤስድሮስን አገኘው ። አባ ኤስድሮስም ፈራው....

ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ
👇👇👇👇👇👇👇
------------------
t.me/andkelem
t.me/andkelem
እመልክዐ መድኃኔ ዓለም

ሰላም ለቆምከ ዘዐቀምዎ በዐውድ፥
ተጋቢኦሙ ደርገ በቀራንዮ አይሁድ፥
መድኃኔ ዓለምክርስቶስ ኢተሃበኒ ለባዕድ፥
እንዘ እስእለከ አነ በልሣነ ሥጋ ክቡድ፥
እስመ አልቦ ዘከማከ በቋዒ ዘመድ።

ውርስ ትርጉም

ሰላም ለእግሮችህ ለቆሙ አደባባይ፥
በቀራንዮ ደብር በአይሁድ ለሥቃይ፥
መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ አትስጠኝ ለባዕድ፥
እያልኩኝ ለመንኩህ በአፌ ትሰማኝ ዘንድ፥
እንዳንተ የለምና የሚጠቅም ዘመድ።
___
t.me/andkelem
t.me/andkelem
እመልክዐ ኪዳነ ምሕረት

ሰላም ለአዕዛንኪ እለ ተበሥራ እለ ተበሥራ ኪዳነ፥
እም አፈ ፈጣሪ ወልድኪ ዘባሕርየኪ ተከድነ፥
አምሕለኪ ማርያም ከመ ኢታርእዪኒ ደይነ፥
እንበለ ምግባር ባሕቱ እመ ኢይጸድቅ አነ፥
ቦኑ በከንቱ ኪዳንኪ ኮነ?


ውርስ ትርጉም
ሰላም ለዦሮዎችሽ ኪዳንን ለተበሠረ፥
ፈጣሪሽ በሆነ ልጅሽ ባሕርይሽን ነሥቶ ባደረ፥
አምልሻለሁ ማርያም መከራ አታሳይኝ ብዬ፥
በምግባር ትሩፋት ብቻ ባልጸድቅ በቸሩ በጌታዬ፥
ለከንቱ ነው ሊባል ነው ወይ ጽኑ ኪዳንሽ ፣ ኪድዬ?

__
t.me/andkelem
t.me/andkelem
የሐምሌ 19 ሰላም

እንዘ ሕፃን አዕበዮ እግዚአብሔር
ወፈነዎ ብሔረ ጽልመት
ኢያውዓዮ ውኂዘ እሳት
ለሕፃን ወሀቦ ሞገሰ
ሆረ ወገብአ በሰላም::

+++++++++++
ሕፃን ሳለ እግዚአብሔር ከፍ አደረገው
ወደ ጨለማ ሃገር ላከው
የእሳትም ፈሳሽ አላቃጠለው
ለሕፃኑ ሞገስን ሰጠው
በሰላምም ገባ ወደ ማደሪያው::
____
t.me/andkelem
t.me/andkelem
እመልክዐ ዑራኤል

ሰላም ለቆምከ ወለመልክእከ በጕጕዓ፥
ለዕዝራ ሱቱኤል እንተ አስተይኮ ጽዋዓ፥
ዑራኤል ክቡር መልአከ ውሳጤ ወአፍአ፥ማኅሌተ እንተ አፉየ እንዘ ትሠምር ነሢአ፥
ለናዝዞትየ በረዊጽ ነዓ።
__
t.me/andkelem
t.me/andkelem
መርቆሬዎስ ገላግለን

"መርቆሬዎስ አብ ይደልወከ ፍሥሐ፥
ሃይማኖትከ ወልድ አምጣነ ለፈረስ በጽሐ።"
የተባልከው መርቆሬዎስ፥
ልማልድህ እንደ ባስልዮስ።

ኢትዮጵያዊው ዑልያኖስ፥
ለጦር ወጥቷል፥
በእኛም ዝቷል፥
ኧረ ሰማዕቱ ገላግለን ያ ስል ጦርህ ዛሬ የታል?
አሁን አቅና ፣ አድን አሁን!
ውጋት የተወጋ ይሁን!!!!!!!

✍️ከሣቴ ብርሃን
ዕለተ መርቆሬዎስ ፣ ሐምሌ 25 ፣ 2016 ዓ.ም።
ነሐሴ 15 (፲፭) በዚችም ቀን የአንድ ክርስቲያናዊ ባለጸጋ ሰው ልጅ ቅድስት እንባመሪና አረፈች ።

16 (፲፮) የዚችም ቅድስት የእናቷ ስም ማርያም ይባላል ሕፃንም ሁና ሳለች እናቷ ሞተች አባቷም አድጋ አካለ መጠን እስከምታደርስ መልካም ትምህርትን እያስተማረ አሳደጋት ።

17 (፲፯) አባቷም እሷን አጋብቶ እርሱ ወደ አንድ ገዳም ሒዶ ይመነኲስ ዘንድ ወደደ ። እርሷም አባቷን ያንተን ነፍስ አድነህ የኔን ነፍስ ታጠፋለህን አለችው ። እርሱም ስለ አንቺ እንዴት አደርጋለሁ ከገዳም ውስጥ ሴትን አይቀበሉምና አላት እርሷም እንዲህ አለችው አባቴ ሆይ የሴቶችን ልብስ ከላዬ አስወግደህ የወንዶችን ልብስ አልብሰኝና ከአንተ ጋራ ውሰደኝ ።

18 (፲፰) የልቧንም ጽናት አይቶ የወንድ ልብስ አልብሶ ከእርሱ ጋር ወሰዳት የቀድሞ ስሟ መሪና ነበር እርሱ ግን ስሟን ለውጦ እንባመሪና ብሎ ጠራት ገንዘቡንም ሁሉ ለድኆችና ለጦም አዳሪዎች በተነ ልጁንም በወንድ ስም እየጠራ ከእርሱ ጋራ ወስዳት ወደ አንድ የመነኰሳት ገዳምም ደርሰው በዚያ እየተጋደሉ ኖሩ ።

19 (፲፱) ከዚህም በኋላ አባቷ ታመመ ለሞትም በቀረበ ጊዜ አበ ምኔቱን ጠርቶ እርሷን ልጁን አደራ ሰጠው ስለ ገዳም አገልግሎት ከገዳም እንዳትወጣ ከዚያም በኋላ አረፈና ቀበሩት ።

20 (፳) የከበረች እንባመሪናም ከአባቷ ተለይታ ብቻዋን ቀረች በጾም በጸሎት በስግደት ከቀድሞዋ ዕጥፍ አድርጋ ተጋድሎ ጀመረች ።

21 (፳፩) ከዚህም በኋላ የገዳሙ መነኰሳት ይህ ወጣት መነኰስ ከእኛ ጋራ ለገዳሙ አገልግሎት ለምን አይወጣም ብለው ተቃወሟት እንዲህም አበምኔቱን በአሰጨነቁት ጊዜ ከእርሳቸው ጋራ ሰደዳት ።

ይቀጥላል።
_
t.me/andkelem
t.me/andkelem
​​​​🌼የሩፋኤል ጠበል ከልጅነት እስከ ጅልነት🌼

በዲ/ን ከሣቴ ብርሃን ገብረኢየሱስ

በመዋዕለ  ንጽሕ ..
ልጅ ሳለሁ ፤ እንደ ልጅ፤
ጤና ሆኜ ሳለ..
በንዕማን ልማድ፤በውሃ ተጠምቄ፤ ጤንነቴን ሳውጅ፤
በርኅወተ ሰማይ፤
ሲዘንም የምሕረት ማይ፤
በሩፋኤል ጠበል በ“አሳድገኝ” ጬኸት፤
በጋን እንድባጀው እንደ ከረምኩ ክረምት፤
ከልቤ ለምኜ፤
ስብራት ሳይኖረኝ በወግ ተጠግኜ፤
ፀአዳ ብራና ሳልዳመጥ ዳግም፤
በጥምቀት ሳልሸኘው ዘመን አልፎ አያውቅም::

እነሆ ልጅነት እንደ ጥላ አለፈ፤
በዚያ ብራና ገጽ እልፍ ኃጢአት ተጻፈ፤
ሰውነት ይሁዳ ከድቶ ሽፍታ ኖሮ፤
ባበቀለው ጫካ ጠብ መንጃ ሰውሮ፤
ጠብ ክብሪት ሲላኮስ፤
ከጽድቅ ሲታኮስ፤
እኔ ሕመምተኛ፤ የጦር ቁስለኛ፤ መፈወሻ ጠበል የምፈልግ ሳለሁ፤
ጥግ ይዤ ቆሜያለሁ::

ያ ጠለ በረከት፤
የንስሐ እጥበት ዓመቱን ጠብቆ ይኸው ዛሬ መጣ፤
የከተማው ደቂቅ ልብሱን አወላልቆ በነቂስ ሲወጣ፤
እኔ ግን ከቤቴ በለበስኩት ቁምጣ፤
በለበስኩት ሱሬ ፤
በሥራዬ ሳይሆን በኃፍረቴ አፍሬ ፤
ራቁት ከኃጢአት ልጅነቴን ሽሬ:: 
 
ጳጉሜን 3 ፣ 2008 ዓ.ም።

___
t.me/andkelem
t.me/andkelem
ከ፭ ዓመታት በፊት በዲ/ን ዶ/ር አብነት ተስፉ አዘጋጅነትና በእኔ አርታዒነት ይኽ የ፳ ገጽ ብዛት ያለው የነገረ መንፈስ ቅዱስ Article በዳረጎት ዲጂታል መጽሔት ላይ ወጥቶ ነበር።
ሙሉ የዳረጎት ዲጂታል መጽሔቶች(Editions) በቅርቡ በአንድ ቀለም ኘሬስ ለንባብ ሲውሉ ያነቡታል። እስከዚያው ዌብሳይቱን ይጎብኙ! Sign up አድርገውም አባል ይሁኑ!

www.andkelempress.com

ወቡሩክ መንፈስ ቅዱስ መጽንዒ ወመንጽሔ ለኵልነ!

___
t.me/andkelem
t.me/andkelem
ጌታን ለሞት ያበቃው ሕማማተ መስቀል የቱ ነው?
(ከመጽሐፈ መሠረት ለጥያቄዎች መልስ ከተሰጠበት ምእራፍ የተወሰደ)

የጌታ ሕማማት ሁሉም አስጨናቂዎች ናቸው። ጌታ ከተቀበላቸው ጽዋትወ መከራ አንዱን ከሌላው ለይቶ “ይህ ያንሳል ፣ ይህ ይበልጣል” ለማለት አይቻልም። እነዚህን ሕማማት ባሰብናቸው ቁጥር ሕዋሳተ አፍኣና ሕዋሳተ ውስጥ ይንቀጠቀጣል። ስለዚህ የሊቁን የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ቅዳሴ ይመለከቷል። ነገር ግን አንዱን የጌታ ሕማመ መስቀል ከሌሎቹ ሕማማተ መስቀል ለይቶ ለሞት ያበቃው የመጨረሻው ይህ ነው ብሎ ለመናገር ያዳግታል። ምሳሌ እንውሰድ።

አንድ ሌሊት በረዶና ዝናም(ውኃ) ቀላቅሎ ዘነመ እንበል። በዚህም ወጀብ ውስጥ ሰው ሞተ እንበል። “የገደለው የትኛው የበረዶ ጠብታ ነው? የወሰደውስ የየትኛው የዝናም ጠብታ ነው?” የሚል ጥያቄ ይቅረብልን። የምንመልሰው ወይም የሚመለስልን መልስ “የበረዶ ዝናም ገደለው ከሚል አልፎ ከዚያ ሁሉ የበረዶ ክምር አንዱን አንኳር አንሥቶ “ይህቺ ገደለችው” ወይም አንዲት ጠብታ ውሃ ፈንጥቆ “ይህች ወሰደችው” ለማለት እንደማይቻልና የሁሉም በረዶና ዝናም ጠብታ ስብስብ ሙላት ወሰደው ገደለው እንደሚባል የጌታም ሕማማት የዚሁ አምሳል ነው። በመጨረሻ በመስቀል ላይ የተቀበለው ፣ ለሕማማቱ ክፍል አንዱ ስተየ ሐሞት ነው። ሐሞቱን እንደጠጣ “ሁሉም ተፈጸመ” ሲል አበሳችንን ደምስሶታል። ሆኖም ታዲያ በሐሞት መጠጥ ሕመም ብቻ ለሞት በቃ አንልም። የማይሞት መለኮት በሥጋ ሞተ። ቅድስት ነፍሱ ከቅድስት ሥጋው ተለየች። መለኮት በሕማማት ምክንያት ወይም በሞት ከሥጋውም ከነፍሱም አልተለየም።

ሙሉ መጽሐፉን ለማንበብ
👇👇👇👇👇👇👇
www.andkelempress.com
_
t.me/andkelem
t.me/andkelem
በቅርብ ቀናት ይጠብቁ! በቅድመ ትእዛዝ ብቻ የሚሸጥ በመሆኑ መጽሐፉን መግዛት የምትፈልጉ ከታች ያለውን ሊንክ ተጠቅመው ወደ "የትንሣኤው ብርሃን ገዢዎች" group ይቀላቀሉ

https://t.me/+p8xAXG85vYtjMTRk
https://t.me/+p8xAXG85vYtjMTRk