Seid Social
11K subscribers
2.58K photos
463 videos
6 files
1.7K links
አለም አቀፋዊ መረጃዎች ምልከታዎችና ታሪካዊ ክስተቶች ይቀርቡበታል
Download Telegram
ሁቲዎች ባለፉት ጥቂት ወራት ብቻ በየመን አቅራቢያ ይበሩ የነበሩ ሶስት የአሜሪካ ድሮኖችን መትተው ጥለዋል ።
ከትላንት በስቲያም ሁቲዎች የየመንን የአየር ክልል ጥሶ የገባን አሜሪካ አለኝ የምትለውን Predator የተሰኘውን ድሮን መትተው ጥለዋል ።

ሁቲዎች ከአሜሪካ ጋር የሚያደርጉትን ግብግብ አጠናክረው ቀጥለዋል።

t.me/Seidsocial
የሁለት ልእለሀያላን ወግ !

በነ አሜሪካ የተዘጋጀው የዩክሬን የሰላም ኮንፈረንስ ሰሞኑን በስዊዘርላንድ ይካሔዳል ። እናም በዚህ ስብሰባ ላይ ቻይና እንድትገኝ የተጋበዘች ቢሆንም ቻይና ግን አልገኝም ብላለች ። ለምን ቢባል የጋዛ ጉዳይ ከዩክሬን ይልቅ አሳሳቢ ነው በማለቷ ነው ።

እናም የቻይናው ፕሬዚዳንት ዢ ጂንፒንግ የጋዛ የሰላም ኮንፈረንስ እንዲካሔድ ጥሪ አቅርበዋል።
ፕሬዚዳንት ዢ ለአረብ ሀገራት መሪዎች ባቀረቡት ጥሪም " የእስራኤል ግፍ ካለገደብ መቀጠል የለበትም" ብለዋል። በመሆኑም ሁሌም ፍትህ ጠፍቶ መኖር የለበትምና ሰላም ወዳድ ሀገራት የጋዛን የሰላም ኮንፈረንስ በማካሔድ ለፍልስጤማውያን መድረስ አለብን ብለዋል ፕሬዚዳንት ዢ !

ፕሬዚዳንት ዢ የአረብ ሀገራት እርስበርስ እንዲዋሀዱና በአካባቢው ያለውን ሰቆቃ እንዲያስቆሙ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን ሳኡዲ አረቢያና ኢራን እንዲነጋገሩና ድፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን እንዲያድሱ በማድረግ ፕሬዚዳንቱ ታሪካዊ ስራ ሰርተዋል ሲል የዘገበው አልጀዚራ ነው።

እንዳለመታደል ሆኖ ግን ይህንን ጥሪ የሚሰማ የአረብ ሀገር አይኖርም !!

👉 t.me/Seidsocial
ዝነኛው መሪ ማህሙድ አህመዲነጃድ ለኢራን ፕሬዚዳንትነት ይወዳደራሉ !

ኢራንን ከ 2005-2013 የመሯት ያኔ አሜሪካና እስራኤል እንድሁም ምእራባውያን ጋር በሚያደርጉት እልህ አስጨራሽ ትግል የሚታወቁትና ከአለማችን ተፅዕኖ ፈጣሪ መሪዎች አንዱ የነበሩት ሀይለኛው ፕሬዝዳንትነት ለመወዳደር ተመዝግበዋል
ፕሬዚዳንቷን ከሳምንት በፊት በሄሊኮፕተር አደጋ ያጣቺው ኢራን ተተኪ መሪዋን ልትመርጥ እየተዘጋጀች ነው።

የኢራንንም የአለምንም ፖለቲካ ጥንቅቅ አድርገው የሚያውቁትና ከምእራባውያን ጋር በሚገባ የሚተዋወቁት አህመዲነጃዲ ወደ ስልጣን ከመጡ የኢራንና የምእራባውያን ጡዘት የበለጠ የሚጨምር ይሆናል። ማህሙድ አህመድነጃዲ የኢራንን ኢኮኖሚ ለማንሰራራትና ሙስናን ሙሉ ለሙሉ ለማጥፋት እንደሚሰሩ ተናግረዋል

ማህሙድ አህመዲነጃድ በመሪነታቸው ዘመን በተመድ በተናገሩት ንግግር እንድህ ብለው ነበር
" አሜሪካ የመስከረም 11 ጥቃትን በራሷ ዜጎች ላይ ፈፅማለች ይህንን ያደረገቺው ደግሞ አፍጋኒስታንን መውረሪያ ምክንያት ለማግኘት ነበር ፤ ሳዳም ሁሰይን ኢራንን እንዲወር ገፋፍታ እሳት የማገደቺው አሜሪካ ነች ፤ አሜሪካ ኦሳማ ቢን*-ላደንን የገደለቺው የሰራቺው በደልና ሸፍጥ እንዳይታወቅባት ለመሸፋፈን ነው ያ ባይሆን ኖሮ ኦሳ*ማን ፍርድቤት ታቆመው ነበር ፤
የአውሮፓ ሀገራት ለሆሎከስት ጭፍጨፋ ለእስራኤል ካሳ ይከፍላሉ ለመሆኑ ሀቀኛ ከሆኑ በአፍሪካ ለፈፀሙት ባርነትና ቅኝግዛት ለምን ካሳ አይከፍሉም ፤
ለፍልስጤማውያን ጭፍጨፋና ስደት ፂዮናዊነትና ምእራባውያን ተጠያቂ ናቸው፤
መከላከል በማይችሉ ንፁሀን ላይ የኑክሌያር ቦንብን ካርከፈከፈ ሀገር ሞራልና ሰብአዊነ አንማር " እያሉ ምእራባውያንን ያኮማትሯቸው ነበር ።
ማህሙድ አህመዲነጃዲ ዳግም እንዲመሩ ምኞቴ ነው ።

t.me/Seidsocial
NO THANKS !

ትላንት አንድ ሱፐርማርኬት ገባሁ እና ለመግዛት ፈልጌ የሆነ እቃ አነሳሁ ! የሱቁን ባለቤት ''ይኼ እቃ እንዴት ነው ?'' ብየ ጠየቅኩት ። ጥሩ ነው እንዴት ነው ? ለማለት ። ሰውየው ከእጄ ተቀብሎ ወሰደ እና ሞባይሉን አውጥቶ የእቃውን ባር ኮድ ስካን ካደረገ በኋላ ''አትግዛው ሌላ አማራጭ እቃ ፈልግ '' አለኝ ። እኔም ''ለምን አልኩት '' እሱም ይህን የሚያምርተው ካምፓኒ የኤስራኤል ደጋፊ ነው ህጻናትን እንድትጨርስ በገንዘቡ የሚደግፍ ስለሆነ ነው '' ብሎ ስካን ያደረገበትን አፕ አሳየኝ ። NO ! THANK YOU የሚል አስገራሚ አፕ በጀግና ዴቨሎፐሮች ተዘጋጅቷል ። ማንኛውንም እቃ ስካን ስታደርጉ የኤስራኤል ደጋፊ የሆነውን ''NO '' እንዳትገዛ ይላችኋል ። ችግር የሌለበት ከሆነ ግዙት ችግር የለውም የሚል ጽሑፍ ያሳያል ።

ሰውየው የራሱ ሱቅ ሁኖ ቆራጥ ሁኖ ይህን ማድረጉ ሲገርመኝ ''እነዚህን እቃዎች ከመደርደሪያ ላይ አነሳቸዋለሁ ካሁን በኋላም አላመጣቸውም '' አለኝ ። ድንቅ ተግባር !

እኔም አፑን ዳውንሎድ አደረኩኝ ። ስካን ማድረግ ጀመርኩኝ ። በሉ እናንተም አፑን ዳውንሎድ አድርጉ እና ልትገዙ የምታስቡትን እቃ ባር ኮዱን ስካን ስታደርጉት ያመጣልችኋል !

ቢያንስ ለፍልስጤም ህጻናት ማድረግ የሚጠበቅብንን እንኳን ማድረግ ባንችል ቢያንስ ገዳዮቻቸውን አናፈርጥምም ።

© Abdurahim Ahmed
የ No thanks አፕሊኬሽንን ማውረድ የምትፈልጉ በዚህ ሊንክ ማውረድ ትችላላችሁ ።

አፕሊኬሽኑ የትኛውንም ምርትና አገልግሎት ከእስራኤል ግንኙነት ይኑረው አይኑረው የሚነግራችሁ ሲሆን ከናንተ የሚጠበቀው ባርኮዱን ስካን ማድረግ ብቻ ነው።
ከዚያ በተጨማሪ መተግበሪያው እስራኤልን የሚያግዙ ታላላቅ ካምፓኒዎችን ዘርዝሮ ይዟል።

Check out "No Thanks"
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.bashsoftware.boycott
ስለጋዛ የተሰሙ አዳድስ መረጃዎች
የተኩስ አቁም ስምሜነቱ ተስፋና ቀቢፀተስፋዎች
ዛሬ በነበረው የጦርነት ውሎ ምን አዳድስ ነገሮች ተከሰቱ ?
ሁሉንም መረጃዎች ተከታተሉ
https://youtu.be/0Od8J8P6X7g?si=Jm16DSDk_ClcsBfH
የዩክሬን ጦርነት መከሰት ፋታና አንፃራዊ እፎይታ ከሰጣቸው ህዝቦች ውስጥ ሶሪያዊያን ወንድምቻችን ዋነኞቹ ናቸው።
ሩሲያ ከአምባገነኑ የበሽር አልአሳድ ጎን ተሰልፋ በሶሪያ ንፁሀን ላይ የፈፀመቺው ጭፍጨፋ ከሰቅጣጭ ግፎች አንዱ ነው። ሩሲያ አሊፖና ሆምስን አፈራርሳ ኢድሊብን አውድማ በሶሪያዊያን ላይ ከፍተኛ ግፍ ፈፅማለች።

የበሽር አልአሳድ መንግስት አፈር ልሶ እንዲነሳ ከኢራንም በላይ ሩሲያ ቀዳሚውን ቦታ ትይዛለች። ሩሲያ በሶሪያዊያን ላይ በአለምአቀፍ ህጎች የተከለከለውን የክላስተር ቦንብ ጭምር ተጠቅማለች።

አሁን ላይ ሩሲያ በዩክሬን ጦርነት ስለተወጠረች በተቃዋሚዎች ቁጥጥር ስር በሚገኙ የሶሪያ ግዛቶች የሚኖሩ ሶሪያዊያን አንፃራዊ ሰላም አግኝተዋል።

👉 t.me/Seidsocial
ሳኡዲ አረቢያ የፍልስጤምን ካርታ ከመማሪያ መፅሀፎቿ ላይ መፋቋ ተገለፀ ።
በሳኡዲ አረቢያ አዲሱ የትምህርት ካሪኩለም መሰረትም ፍልስጤም የምትባል ሀገር እንደሌለች ተገልጿል ። ሳኡዲ ለተማሪዎቿ የአለም ካርታ ላይ ፍልስጥኤም የምትባልን ሀገር ማግኘት እንዳይችሉ አድርጋለች። እናም የፍልስጤም ግዛት ባዶ ቦታ እንዲሆን ተደርጓል።

ሳኡዱ አረቢያ ከዚህ በተጨማሪ እስራኤልን በጠላትነት የሚፈርጁ ገለፃዎችን በሙሉ ከማስተማሪያ መፅሀፎቿ ማውጣቷም ታውቋል። በፊት የነበሩ እስራኤልን " ጠላት " "ፅዮናዊት ጠላት " የመሳሰሉ ቃላትም በሳኡዲ የመማሪያ መፅሀፍ ውስጥ ከእንግዲህ አይገኙም። በአጠቃላይ እስራኤልን በክፋትና ቀጠላትነት የሚገልፁ ከቀድሞው መማሪያ መፅሀፍት ላይ የነበሩ 21 ገለፃዎች መወገዳቸውን the New Arab የዜና ወኪል ዘግቧል።

ሳኡዲ አረቢያ ከዚህ በተጨማሪ በሀገሪቱ እስራኤልን የሚያወግዙ ድርጊቶችን ማገዷ ይታወቃል። ለዚህ የሳኡዲ ለውጥም የአሜሪካ ጥረት በሰፊው እንዳለበት ይታመናል። ሳኡዲ አረቢያ ከእስራኤል ጋር ወዳጅነታቸውን ይፋ እንዲያደርጉ እየሰራች የምትገኘው አሜሪካ ሳኡዲ አረቢያ እስራኤልን የሚያስቀይሙ ገለፃዎች እንድታስወግድ በመጠየቋ ሳኡዲም የአሜሪካን ትእዛዝ ገቢር አድርጋለች።

👉 t.me/Seidsocial
እስራኤል ከአሜሪካ 25 ሀያ አምስት F-35 የጦር ጄቶችን ቀ 3 ቢሊዮን ዶላር ለመግዛት ጥያቄ አቅርባለች ።
የሚገርመው ግን የጦር በጀቷን የምትሸፍንላት ራሷ አሜሪካ ናት ። አሜሪካ በቅርቡ ብቻ ያፀደቀቺላት የጦር እርዳታ የእስራኤልን የሁለት አመት የጦር በጀት የሚዘጋ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ አሜሪካ በየአመቱ ለእስራኤል የ 4 ቢሊዮን ዶላር የጦር እርዳታ ታደርጋለች።

እናም እስራኤል በአሜሪካ ገንዘብ የአሜሪካ ጦርጄቶችን ትገዛለች ማለት ነው ።

ቀላል ሙድ ይይዙብናል እንዴ 🤔

t.me/Seidsocial
የአፄ ቴዎድሮስን ርእዮተአለም ተከትሎ የሚገኝ ድል አይኖርም !
አፄ ቴዎድሮ የስኬትም የድልም የለውጥም ተምሳሌት ሊሆን የሚችል መሪ በፍፁም አይደለም !

ሌላው ካልጠፋ እኔ አልኖርም አይነት ቴዌድሮሳዊ አካሔድ ውጤቱ እንደ ቴዎድሮስ የሽንፈትን ፅዋ ተጎንጭቶ ከንቱ ውጤት አልባ መስዋዕትነት መክፈል ነው ።

በኢትዮጵያ ውስጥ ምንም ነገር ሳያሳኩ ምንም ከይነት አሻራ ሳያሳርፉ ከሽፍትነት ውጥተው በሽፍትነት በመሰዋት ከቴዎድሮስ በፊት የሚጠቀስ መሪ የለም።
ሰርቆ ዘርፎ የዘረፈውን ንብረት ለወራሪዋ እንግሊዝ አስረክቦ ነው የተሰዋው ።
ገና ለገና ነጭ ስለሆኑ የጦር መሳሪያ ይሰራሉ ብሎ የጊዜዋን ልእለሀያል ሀገር የእንግሊዝን ድፕሎማቶች ማሰርና ማገት ማንም የማይዳፈረው ሞኝነት ነው። እንግሊዝ ለክብሯ ስትል ባዘመተቺው የህንድ ጦር ምንም መስዋዕትነት ሳይከፍሉ ነው ቴዎድሮስን የገደሉት ወይንም ራሱን የገደለው ።

ሲጀመር ቴዎድሮስ ወድቆ መቅደላ ተራራ ላይ መሽጎ ነበር ። ምክንያቱም በየሄደበት ሁሉ ባደረሰው ወደር አልባ ጭካኔና ዝርፊያ ሁሉም እያሳደደው ስለነበር።

እንግሊዝ ትልቅ የኢትዮጵያ ሰራዊት እገጥማለሁ ብላ 30,000 አብዛኛው ከህንድ የተውጣጣ ጦር ብታዘምትም መቅደላ ስትደርስ ያገኘቺው የቴዎድሮስ ጦር ግን 3,000 አካባቢ ብቻ የተዳከመ ሰራዊት ነበር ። እናም የአንድ ቀን ኦፕሬሽን አድርጋ መስዋዕትነት ሳትከፍል ታጋቾቿን አስለቅቃ ነው የተመለሰቺው። ልትዋጋበት ይዛው የመጣቺውን መሳሪያም ከፊሉን ለአፄ ዮሐንስ ሰጥታው ነው የተመለሰቺው ።

እና ይሄን አይነቱን በትርክትና ተረት ካላቅሙ የተቆለለ መሪ ሌጋሲን እከተላለሁ ብሎ መንጀፋጀፍ የርሱን ፍፃሜ ያመጣል።
የቴዎድሮስን አይነት ህልም ተሸክሞ የተሳካለት በአለም ላይ አንድም መሪ የለም።

t.me/Seidsocial
"ኢትዮጵያኒስቶቹ" እውነተኛ ህልምና መሻታቸው የኢትዮጵያ ልእልናና ሀያልነት ቢሆን ኖሮ የሚከተሉት ሌጋሲ የቴዎድሮስ ሳይሆን የልጅ ኢያሱን በሆነ ነበረ።

አፄ ቴዎድሮስ የህፃኑን የልጅ ኢያሱን 1/100ኛ እንኳ የሚሆን የኢትዮጵያ የታላቅነት ህልም አልነበራቸውም።
የልጅ ኢያሱን የታሪክ መዝገብ ያገላበጠ ሰው ያንን ያክል የአሁኑ መሪዎቻችን እንኳ ሊያስቡት ያልተቻላቸውን ህልም የሰነቀው ያ ህፃን ልጅ ነበር ? ብለው በግርምት መጠየቃቸው አይቀርም !!

ኢትዮጵያን እንደት ትልቅ ማድረግ ፤ ኢትዮጵያን እንደት የሁሉ ማድረግ ፤ ኢትዮጵያን እንደት የቀጠናው Hegemonic force ማድረግ ፤ ኢትዮጵያን እንደት የስልጣኔ የሰላም የሁሉም ዜጎቿ እናት ማድረግ እንዳለበት የገባው በታሪክ ብቸኛው የኢትዮጵያ መሪ ህፃኑ ልጅ ኢያሱ ብቻ ነው !
በዚያ ህፃንነት እድሜ በዚህ ልክ እንደት Mastermind መሆን እንደቻለ ሳስበው እደነቃለሁ!

ያው እንዳለመታደል ኢትዮጵያ ከሊሂቃን ፖለቲከኞች ይልቅ ደናቁርት ፖለቲከኞች የሚዘውሯት ተገር ነች ። እናም ደናቁርቶቹ ኢያሱን " ሰልመሀል " ብለው ከእንግሊዝና ፈረንሳይ እገዛ ጠይቀው ከስልጣኑ ገልብጠው ገደሉት። ያኔ የገደሉት የኢትዮጵያን ህልም ነበር ። እንግሊዝና ፈረንሳይ እንዲረዷቸው " ኢያሱ ከጀርመንና ከቱርክ ጎን ተሰልፎ ሊወጋችሁ ነው " በማለት ቀጥፈው ባለራእዩን ኢያሱን አስቀጠፏቸው።

t.me/Seidsocial
ሳኡዲ አረቢያ ባለፉት ሶስት ወራት ብቻ ከ 400 በላይ ኢትዮጵያዊያንን ወደ ሀገሯ ሲገቡ መግደሏ ተገለፀ።
ሳኡዲ አረቢያ በኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ላይ የምታደርገው ግድያ በአሳሳቢ ሁኔታ ቀጥሏል በማለት Human rights watch ዛሬ አለምኘቀፉ ማህበረሰብ ሳኡዲን ተጠያቂ እንዲያደርግ ተማፅኗል።

Middle east eye በርካታ አለምአቀፍ ተቋማትንና ከቦታው መረጃ ወስዶ ዛሬ ይፋ ባደረገው ዘገባው የሳኡዲ አረቢያ ወታደሮች በኢትዮጵያ ስደተኛ ሴቶች ላይ የአስገድዶ መድፈር ጥቃት እየፈፀሙ መሆኑንም አሳውቋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባወጣው መግለጫ ደግሞ አንድት እድሜዋ ከ 13-14 የምትገመት ኢትዮጵያዊት ስደተኛ በሳኡዲ ወታደሮች በጋራ መደፈሯን ይፋ አድርጓል።

ለስደተኞች መብት የሚታገለው MMC ወይንም Mixed migration center ይፋ ባደረገው መረጃ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በጅምላ መገደል መደፈርና መሰቃየት እየደረሰባቸው ነው ብሏል።

ሳኡዲ አረቢያ የምታደርሰውን የሰብአዊ መብት ጥሰትም ለመጠየቅ ሀገራትና ተቋማት ፍላጎት አለማሳየታቸው ጉዳዩን እጅግ አሳዛኝ አድርጎታል ሲሉ HRW እና MMC ገልፀዋል ።
አምና በቪዲዮ የተለቀቀው የሳኡዲ አረቢያ የስደተኞች ጭፍጨፋ ብዙዎችን ማሳዘኑ አይዘነጋም ።

በዚህ ሁሉ ሰቅጣጭ ጉዞ ውስጥ ግን ኢትዮጵያዊያን እጅግ አደገኛውን ስደት አሁንም ቀጥለዋል ።

t.me/Seidsocial
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በርግጥ አብዛኞቻችሁ ከሚገደሉት ንፁሀን ይልቅ የሳኡዲ አገዛዞች ስም መጥፋት እንደሚያሳስባችሁ አውቃለሁ ።
ቢሆንም ብትወዱም ብጠሉም እውነትን ማድረሴን አልተውም !
ይህ የኢትዮጵያዊያን ስደተኞች የሬሳ ክምር ነው !
ይህንን እንኳንስ በሀገሬ ልጆችና በማንም ላይ ተፈፅሞ ባየው እንኳ እጅጉን አዝናለሁኝ !

እናንተ ግን ይብላኝላችሁ ትንሽ እንኳ ነግበኔ አትሉም ???