Seid Social
9.14K subscribers
2.26K photos
332 videos
6 files
1.43K links
አለም አቀፋዊ መረጃዎች ምልከታዎችና ታሪካዊ ክስተቶች ይቀርቡበታል
Download Telegram
እነሆ ኢራን አድስ ፊት አሳይታናለች !

በኢራን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ተራማጅ የሚባሉት ዶክተር መስኡድ ፔዜሽኪያን አሸንፈዋል ። ፕሬዝዳንቱ ወግአጥባቂውንና የኢራንን የኑክሌር ተደራዳሪ ሰኢድ ጃሊሊን አሸንፈው ነው ለኢራን ፕሬዝዳንትነት የበቁት።

እንግድህ ፕሬዚዳንቱ ኢራን ለአለም ክፍት ትሆናለች ብለዋል። ከአለም ሀያላን ጋር ተደራድረን ማእቀቡን እናስነሳለን ሲሉም ለመራጮቻቼው ቃል ገብተዋል ። ከእንግድህ የፆታ እኩልነት የተረጋገጠባትና ሴቶች የማይጨቆኑባት ኢራንን ትመለከታላችሁ ብለዋል ። ፕሬዝዳንቱ ሴቶች ሂጃብ መልበስ ከፈለጉ በፍላጎታቸው ይለብሳሉ እንጅ ተገደው ወይንም ደግሞ በቅጣት አይሆንምም ብለው ቃል ገብተዋል። ኢኮኖሚውን ማሻሻል ከአለም ጋር መዋሀድ ተቀዳሚ አጀንዳየ ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ ማህበራዊ ፍትህና እኩልነት መርሄ ይሆናል ብለዋል።

ፕሬዚዳንቱ ይህን ሁሉ ቃል ይግቡ እንጅ በኢራን አመራር ውስጥ ፍፁም ውሳኔ ሰጪ ከሆኑት ከኢማም አያቱሏህ አሊ ኻምንኢ የተጣረሰ ውሳኔ ማሳለፍ እንደሚከብዳቸው አያጠያይቅም። ኢማሙ ያላፀደቁት ነገር በኢራን ተፈፃሚ አይሆንምና !

ቴሌግራም
👉 t.me/Seidsocial
ከአቡ ኡበይዳ የተላለፈ መግለጫ !

የአልአቅሳ ጎርፍ ዘመቻ ከተከፈተ 9 ወራቶችን አሳለፍን ። ህዝባችን በአሜሪካ-እስራኤል ጥምረት የተከፈተበት የማጥፋትመቻ እንደቀጠለ አለ ። መሬት አልባ ሀገር አልባ ሊያደርጉን ራሳችንን መከላከላችንን እንደ ሽብርተኝነች ቆጥረው ሊያጠፉን የከፈቱት ጦርነት እነሆ እንደቀጠለ ነው !
በዘጠኙ ወሩ ጦርነት አለም እንዲያውቅልን የምንፈልገው ነገር ቢኖር ጦርነቱ ያኔ አልተጀመረም ። የኦክተበር 7 ጦርነት ለዘመናት የተራቀመ ግፍ ማሳደድ ማጥፋት ውጤት ነው ። ያ ጦርነት ድንገት በፊት ላይ እንደፈነዳ ፍንዳታ ነው ። በህዝባችን ላይ በመሬታችን በቅዱሳን ቦታዎቻችን ላይ በደረሰ የዘመናት ግፍና በደል የተጠራቀመ ፍንዳታ ነው።
ይህን ጦርነት የጀመርነው ወራሪው ሀይል ፍልስጤሞችን ከምድራቸው አፅድቶ መሳጅዶችን ሁሉ አስወግዶ ከጋዛ እስከ ዌስት ባንክ ጠቅልሎ ለመውሰድና አልአቅሷን ወደ ብተአምልኳቸው ለመቀየር በወሰነ ጊዜ ነው።

አዎ ዘጠኝ ወራት አለፉን ! ግና ትግላችን አልተዳከመም ! አልቀነሰም አልተጓደለምም !!
ከውጭ የመሳሪያና የቁሳቁስ እርዳታ ባናገኝም ፤ ከጎናችን የሚቆም ባይኖርም ሳንበረከክ በፅናት እየታገልን እንቀጥላለን ። ህዝባችን ረሀብና ጥሙን ተቋቁሞ እየቀጠለ ነው። የሚደርስብንን ጭካኔ መታገላችንን እንቀጥላለን !

ጋዛ የታሪክ ምእራፍ ከፍታለች! ለነፃነት ለሰብአዊነት ለክብርና ልቅና ስለሚደረግ ክቡር ትግል ጋዛ ለነፃነት አቀንቃኞች ሁሉ ትልቅ ትምህርት ቤት ሆናለች !

በአሜሪካ እንግሊዝና አጋሮቻቼው የሚታጠቀው ወራሪው ሀይል ከላይ በአየር ከስር በመሬትና በባህር በሚወነጨፉ ቦንቦችና ሚሳኤሎች እየተሸፈነ ቢዋጋንም ንፁሀንና ህዝብን ምሽግ አድርግ ቢፋለመንም ከአጋሮቹ ጋር ጭምር ተሰልፎ እየተዋጋነው እየጣልነው እየገነደስነውም ነው ። ቃል እንደገባንላችሁ ወራሪው ጋዛ ላይ ሞት እንጅ ሌላ አይጠብቀውም ። ሙጃሂዶቻችን በየቀኑ የወራሪውን አመራሮችና ወታደሮች እየመቱ መጣላቸውን ቀጥለዋል።

እናንተ ቤተሰቦቻችን ሆይ ! እናንተ ህዝቦቻችን ሆይ ! እናንተ ኡመቶቻችን ሆይ ! እናንተ ነፃነት ወዳድ ነፃ የአለም ህዝቦች ሆይ !
- ሙጃሂዶቻችን በፅናትና በአስደናቂ ታክቲክ እየታገሉ ነው ። በኢማን ፅናታቸው ልክ በነዚያ ከውዱ ነብያችን ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም ሶሀቦች ዘመን ያሉ ያክል በፅናት እየታገሉ ነው ። አላህም በቅዱስ ቃሉ " እነዚያ በኛ መንገድ የታገሉትን ትክክለኛውን መንገድ እንመራቸዋለን አላህም ከአሳማሪዎች ጋር ነው " ይላልና !!

የወራሪዎቹ ህዝቦች ሆይ ! ኔታኒያሁ የሚላችሁ ነገር ሁሉ ውሸት ነው ! ፍፁም በኛ ላይም ድል አይቀዳጅም ! በአላህ ፈቃድ ይህ አይሆንም ! እርሱ ድል የሚለው ተፎካካሪ ፖለቲከኞችን አጥፍቶ ስልጣኑን በማናለብኝነት መቆጣጠሩን ነው። መቼም ቢሆን በጋዛ ላይ ያሰበውን አያሳካም።

በሙጃሂዶቻችን ፅናት እናሸንፋለን ። ለህዝባችን ክብርና ልእልና የሚያጎናፅፍን ስምምነት እንጅ አንስማማም ! ህዝቦቻችን ሆይ እኛ ከናንተው ወደናንተው ለናንተው ነን ! የአብራካችሁ ክፋይ የሆንን እኛ ስለህዝናችንና እምነታችን በፅናት እንታገላለን !
አላህም በነገራቶች ሁሉ አሸናፊ ነው ።ግና አብዛኛዎቹ አያውቁም !
ይህ ጅሀድ ነው ወይ ድል አልያም ሸሂድነት !!!!!

👉 t.me/Seidsocial
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሙስሊሞች እንደዚህ የጠላት መጫወቻ የጭካኔያቸው መለማመጃ በሆኑበት ፤ ወንድም ወንድሙን ገድሎ ተክቢር እያለ ጠላት ሲሆን መስለሀና መፍሰዳ እያለ በሚልመጠመጥበት በዚህ የሙስሊሞች የዝቅታ ዘመን ባልፈጠር ምንኛ ደስ ይለኝ ነበር !
በዚህ ከገለባም በቀለልንበት ከባህር አረፋም በበነንበት የማንም መጫወቻ በሆንበትና ህፃናት ሳይቀሩ ሙስሊም ሆነው በመወለዳቸው ብቻ ይህን ሁሉ ስቃይ እንዲያዩ በሆነበት በዚህ አሳዛኝ ዘመን ምናለ ባልተፈጠርኩ ኖሮ !!

የውስጤን መቃጠልና ማዘን ማን ያቀልልኛል ???
ብቻ ምንም አልልም
የምለምነው አንደውኑ ተፈጥሪያለሁ ቢያንስ የነዚህን ግፉንን ደስ ሳያሳይ እንዳይገድለኝ ብቻ ነው 😢
አንድት የጋዛ እናት " ነብያችንን ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም አሁን ብታገኛቼው ምን ትያቸዋለሽ " ተብላ በጋዜጠኞች ተጠየቀች ። እርሷም ሳግ እየተናነቃት እንደዚህ ስትል መለሰች
" ነብያችንንማ ባገኛቸው የአላህ መልእክተኛ ሆይ አቅም እያላቸው ገንዘብ እያላቸው ሁሉ ነገር እያላቸው ለጠላት አሳልፈው የሰጡንን የከዱንን ያዋረዱንን አረቦችን ሸፈአ አይሆኗቸው ብየ እጠይቃቸው ነበር " ስትል መለሰች ።

ፍልስጤማዊያን ከአረቦች ያገኙት ነገር ቢኖር መከዳትን ብቻ ነው ! የዚህች እናት ቁስል እንድህ እንድትል አስገደዳት !

👉 t.me/Seidsocial
ሳኡዲ አረቢያ የእንግሊዝ እና አሜሪካን የጦር ጥምረት መቀላቀሏ የሁቲዎችን ግስጋሴ ይገታው ይሆን ?
ሳኡዲ ለምን በዚህ ወቅት የጦር ጥምረቱን መቀላቀል ፈለገች ?
ሁቲዎችስ ለዚህ አፀፋ በሳኡዲ ላይ ምን እርምጃ ሊወስዱ ይችላሉ ?
ለመሆኑ የአንሷሩሏህ ሁቲዎች ወታደራዊ አቅምስ ምን ይመስላል ?

ሁሉንም ዳስሻለሁ ዝግጅቱን እንድትከታተሉ ጋበዝኳችሁ !


https://youtu.be/ESWqT4yfQ5s?si=8KP0sggevPkmbgq4
ኢራን በቴህራን የሚገኘውን የቱርክ አየር መንገድ ቢሮ ዘጋች ።
ኢራን የቱርክ አየር መንገድ ሶስት ሴት ኢራናዊ ሰራተኞች ሂጃብ አንለብስም በማለታቸው የቱርክ አየር መንገድ ቢሮን ዘግታለች ። በቴህራን የነበረው የቱርክ አየር መንገድ ቢሮ ሴት ሰራተኞች በቴህራን ሀላፊዎች ሂጃብ እንዲለብሱ ቢጠየቁም አሻፈረኝ ብለዋል ። በመሆኑም በሂጃብ አልደራደርም ያለቺው ኢራን ግዙፉን የአለማችን አየር መንገድ የሆነውን የቱርክ አየር መንገድ ቢሮን ለመዝጋት ተገዳለች ።

ሂጃብ አንለብስም ያሉት የቱርክ አየር መንገድ ሰራተኞች ኢራናዊ ሲሆኑ ኢራን በሚገኘው ቢሮው የቀጠራቸው ናቸው። እነዚህ ኢራናዊ ሴቶች በቱርክ አየር መንገድ ውስጥ መቀጠራቸውን እንደ ማምለጫ በመጠቀም ነው ሂጃብ አንለብስም ብለው የነበሩት።

በኢራን ውስጥ ማንኛዋም ሴት ሂጃብ እንድትለብስ ትገደዳለች። ይህንን አለማድረግም የሚያስቀጣ ወንጀል ተደርጎ የተደነገገባት ሀገር ነች ። መረጃው የ ABC News ነው ።

👉 t.me/Seidsocial
ሳኡዲ አረቢያዊው መምህር ማህበራዊ ሚዲያ ላይ በፖሰተው ፖስት የ 20 አመት እስራት ተፈረደበት ።

ሳኡዲ አረቢያዊው መምህር አሰድ አልጋምዲ የሳኡዲን ጉዞ የሚተችና ከኢስላም አስተምህሮ እየተንሸራተተች ነው የሚል ፖስት በመፖሰቱ ነው ሌሊት ላይ በሳኡዲ የደህንነት ሀይላት ታፍኖ ከተወሰደ በሗላ የ 20 አመታት እስራት የተፈረደበት።


አሰድ አልጋምዲ ላይ የተመሰረተው ክስም የሽብርተኝነት ክስ ሲሆን " የአልጋወራሽ ሙሀመድ ሰልማንን ሀይማኖት ጥርጥሬ ላይ እንዲወድቅ አድርገሀል የሳኡዲን ጉዞም ኢስላማዊ አይደለም ብለሀል ይህ ደግሞ የሙሀመድ ቢን ሰልማንን ክብር የሚነካ ነው " በሚል ነው በፖስቱ የ 20 አመት ፅኑ እስራት የተፈረደበት ።

አሰድ አልጋምዲ የ 47 አመት እድሜ ያለው መምህር ሲሆን አላህ ካለ ከእስርቤት ከወጣ የ 67 አመት እድሜ ሆኖት ይሆናል ። ይሁን እንጅ የሳኡዲን ንጉስ በመተቼት የታሰሩ ኡለሞችና ተቆርቋሪዎች የእስር ጊዜያቸውን ቢጨርሱም የማይፈቱ በመሆናቸው የአሰድ አልጋምዲም እጣፈንታ ተመሳሳይ እንዳይሆን ያስፈራል።

👉 t.me/Seidsocial
ሂጅራ ባንክ ትልቅ አብዮት ላይ ነው !

በዘንድሮው እለት በታሪኩ ሪከርድ የሆነን ትልቅ ትርፍ ማግኘት የቻለው ባንኩ የቅርንጫፍ ብዛቶቹን ከ 100 በላይ አድርሶ ሌሎች በርካታ ቅርንጫፎችን አዘጋጅቶ ጨርሶ ወደ ትልቅነት ምእራፍ ያደረገውን ጉዞ በታላቅ እመርታ ያጠናቀቀበት አመት ሆኖ አልፏል።
ያሉትን ክፍተቶች አርሞ ከፍተኛ ቴክኖሎጂና ብቁ ባለሙያዎችን ወደ ተቋሙ በመሳብ አብዮት ላይ ያለው ሂጅራ ባንክ Omni channel የተሰኘውን በሀገራችን ምናልባት ከሂጅራ ውጭ አንድ ወይንም ሁለት ባንክ ብቻ ያለውን የባንክ ኮር ቴክኖሎጂም ባለቤት ለመሆን ችሏል።

ሆኖም የባንኩ ባለቤትነትን የሚፈልጉ በርካታ ማህበረሰቦች በመኖራቸውና ባንኩም ባለቤትን ማብዛትና ካፒታሉን የበለጠ ማግዘፍ ለታላቅነት ለሚያደርገው ግስጋሴ አንዱ ስትራቴጂ አድርጎ በመውሰዱ የዚህን የባለቤትነት እድል ዳግም በውጭና በሀገር ውስጥ ለሚኖረው ማህበረሰባችን እንካችሁ ብሏል።
በመሆኑም የትም መሄድ ሳይጠበቅባችሁ የሂጅራ ባንክ ባለቤት መሆን  የሚትችሉበትን እጅግ ቀላል አማራጭ አቅርቦላችሗል። በቴሌግራም መተግበሪያ የሚከተለውን ሊንክ በመጫን ብቻ አክሲዮን የመግዛት ጉዟችሁን መጀመር ትችላላችሁ ፡፡
https://t.me/hijra_share_bot?start=DIEISOC በመጠቀም ጥያቄዎቹን በመሙላት እና ደረሰኙን በመጫን የሂጅራ ባንክ አክሲዮኖችን ከ15 ሺህ ጀምሮ እስከ 300 ሚሊዮን ድረስ በማንኛውም ጊዜ ከየትኛውም ቦታ መግዛት ትችላላችሁ።

ኢትዮጵያ ለባንኩ ዘርፍ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ከውጭ ሀገር ሳይቀር ባንኮች ወደ ሀገራችን እንዲገቡ የፈቀደች በመሆኑ እናንተም ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም ወደዚህ ዘርፍ መቀላቀልና ኢስላማዊ ባንኮችን ፈርጣማ እንድታደርጉ መልእክቴን ለማስተላለፍ እወዳለሁ።
https://t.me/hijra_share_bot?start=DIEISOC በመጠቀም አሁኑኑ የሂጅራ ባንክ ባለቤት ይሁኑ !
ጋዛ ወደ 2 ሚሊዮን የሚጠጋ ህዝብ አላት ። ከዚህ ከሁለት ሚሊዮን ህዝብ ውስጥ ከ 200 ሺህ እስከ 300 ሺህ የሚጠጉት ቁርአን ሀፊዞች ናቸው ። ያ ማለት ከመቶ የጋዛ ሰው 15ቱ ሀፊዝ ናቸው ማለት ነው ።
በእያንዳንዱ የጋዛ ቤትም አንዳንድ የቁርአን ሀፊዝ አለ ። ይህም በአለም ጋዛን በቁርአን ቀዳሚ ያደርጋታል።

ስለዚህ እስራኤል 100 ጋዛዊያንን በገደለች ቁጥር 15 የቁርአን ሀፊዞችን አብራ ትገድላለች። እስካሁን ኦፊሴላዊ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የተገደሉት ፍልስጤማዊያን ንፁሀን 39,000 ገደማ እንደሆኑ ቢነገርም ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ግን ከ 180,000 በላይ ንፁሀን ጋዛዊያን በጦርነቱ ሙተዋል ። ከጋዛ ህዝብ 10% ገደማ እንደማለት ነው። እጅግ ልብ አይሰብርም ???

ወደ ቁርአን ሀፊዞቹ ስንመጣ በቅድሙ ስሌት በእስካሁኑ ጦርነት ወደ 27,000 ቁርአን ሀፊዞች ተገድለዋል ማለት ነው ። ይህ ህይወት ባለው ኡማ ውስጥ ቢደረግ አንድ ሙስሊም እንኳ ተኝቶ ያድር ነበር ወይ?

በየማማ ጦርነት ጊዜ 360 የቁርአን ሀፊዞች ሲገደሉ በአቡበክር ሲዲቅና በሶሀቦቻቼው ላይ የደረሰው ድንጋጤና ስብራትን ሲራን የሚያውቅ ያውቀዋል ። ዛሬ ላይ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሀፊዞች ጋዛ ላይ በጅምላ ሲጨፈጨፉ እንኳንስ ሊያስደነግጠን ሊያሳስበንም አልቻለም !
ዛሬ ላይ በዚያች ጋዛ ምድር ብቻ ከ 1,000 በላይ ጥንታዊ መስጅዶች በመሰቀል ጦረኞቹና በፅዮናዊያኑ ጥምረት ሲወድም ሊያመን አልቻለም ። የራሳቼው ጉዳይ ብለን ጋዛዊያንን ክደናቸዋል !!

ይሄ ረሱላችን ፊት ስንቀርብ የሚያሳፍረን አይመስላችሁም ? ሸፈአቸውን ለመከጀል አንገታችንን ቀና ማድረግ ይቻለን ይሆን ??
ሲያዩን የሚያፍሩብን አይመስላችሁም ???

👉 t.me/Seidsocial
ከፍተኛ የጦር መሳሪያ እጥረት ስለገጠማትና ወታደሮቿም ካለ በርካታ የጦር መሳሪያ ውርጅብኝ ስኬታማ ውጊያ ስለማያደርጉ በጀኔራሎቿ ጉትጎታ እስራኤል ከሀማስ ጋር ተኩስ እንዳቆም ተባበሩኝ ስትል ጥሪ አቅርባ ነበር ። ይህንንም ኔታኒያሁ በአንደበቱ ተናግሮ ድርድርም ተጀምሮ ነበር ።

ይህ እስራኤልን ተሸናፊ የሚያስመስል የተኩስ አቁም ጥሪ ሲደረግ ታድያ አሜሪካን የሚዘውሩ አይሁዳውያን ፖለቲከኞች እና የእስራኤል ወዳጅ አሜሪካዊያን ፖለቲከኞች ዶናልድ ትራምፕን ጨምሮ በባይደን ላይ ወረዱበት ። ምክንያቱም የእስራኤል ጦር እየተፍረከረከ የመጣ አሜሪካ ወደ እስራኤል የምታጓጓዘውን መሳሪያ በጊዜያዊነት በማቆሟ ነበር።

በዚህ የተበሳጨው ዶናልድ ትራምፕ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደንን " አስቀያሚ ፍልስጤማዊያ" በማለት ጭምር ሰደበው። እናም የባይደን አስተዳደር ይህን ቁጣ መቋቋም ተስኖት ወደ እስራኤል የጦር መሳሪያዎችን ማጓጓዙን ቀጠለ።
በጥቂት ቀናት ብቻ አሜሪካ 500 ፓውንድ የሚመዝኑ በርካታ ሚሳኤሎችን ጅምላ ጨራሽ ቦንቦችን ጭና ወደ እስራኤል አጓጓዘች። እናም ኔታኒያሁ በዚህ የሀይል ሀይል ተሰማው ። አሜሪካ እያስታጠቀችኝ ከቀጠለችማ ለምን ተኩስ አቆማለሁ ወደሚል ሀሳብ ተቀየረ ። እናም አቅርቦት የነበረውን የተኩስ አቁም ጥሪ አጥፎት ተኩስ መቀጠልን መርጧል።

አዎ ጋዛን በቀጥታ እየተዋጋቻት ያለቺው አሜሪካ ነች ። እስራኤል የአሜሪካን ድጋፍ እስካገኘች ድረስ አሜሪካ ከተትረፈረፋት የጦር መሳሪያዋ በገፍ እስካስታጠቀቻት ድረስ እስራኤል ብዙ አመት እየተዋጋች ትቀጥላለች ። ምናሻት ከላይ የሚያዘንቡት የአሜሪካ F-16 እና F-35 የጦር ጄቶች ፤ የሚዘንበው የአሜሪካ ጅምላ ጨራሽ ሚሳኤልና ቦንቦች ስለዚህ ይህ ፍልስጤማዊያንን እስከጨረሰላት ድረስ በደስታ ትቀጥልበታለች ።


👉 t.me/Seidsocial
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የሙጃሂዶቹ ጀብድ !
የማይሰበሩት ፅኑዎች ! የማይንበረከኩት ብርቱዎች!
የማይፍረከረኩት ባለኢማነኞች በዛሬው እለት የፈፀሙትን ጀብዱ እነሆ ተመልከቱ !
ለሙጃሂዶቱ ወዳጆችም ላኩላቸው
ዛሬ አንድ መስጅድ ውስጥ ጁሙአ እየሰገድኩ አንድ ዳኢ ነኝ ባይ ውሸታም " የአሹራ ቀን የሀዘን ቀን አይደለም አዝናችሁ እንዳትውሉ የደስታ ቀን ነው ። እከሌ ሞተ እያሉ በሀዘን የሚውሉት ጠማ**ማዎቹ ሺአዎች ናቸው እነርሱ ናቸው ገድለው መልሰው የሚያለቅሱት እና እንዳታዝኑ አላህ ሙሳን ነፃ ያወጣበት የደስታ ቀናችን ነው ። ሀገራችን ላይ ስለተገደሉት ሰዎች እናዝናለን የሚሉ ብቅ ብቅ እያሉ ነው እርሱ ሺአዎች ናቸው እንዳትታለሉ ተጠንቀቋቸው" ወዘተ እያለ አፉን ይከፍታል ።

ይህ ሰው የተገደሉት እያለ ስማቸውን ለመጥበስ እንኳ የተፀነፋቸው የነብያችን አደራ የሆኑትን የጀነት ወጣቶች አለቃ የውዱ ነብያችን ሽታና በውዱ ነብይ ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም አንደበት" ቁርአንና ቤተሰቦቼን ትቼላችሁ ሂጃለሁ የቤተሰቦቼን ነገር አደራ " የተባልነውን ውዶቹን የነብያችንን ቤተሰቦች ነው ። ስማቼውን መጥራት ተፀይፎ ስለነርሱ ማዘንንም አፈንጋጭነት አድርጎ ሲጮህ ነበረ።

ያው ከዚያም አልፎ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚፅፉ ሺአዎች በማለት እኛንም በነገር ሲያሽሟጥጥ ነበር ። አግኝቼ ለመሞገት ጊዜውም ሁኔታውም ስላልፈቀደልኝ ትቼዋለሁ።

ለማንኛውም እነዚህ ኡመውዮች አፋቸውን ስለከፈቱና ሰለነቢ ቤተሰቦች እልቂት አታውሩ አትናገሩ አትዘኑ ብለው ስለጮሁ የምንተወው ነገር የለም ።

የሙሳ ህዝቦች ወይንም እስራኤላውያን በመትረፋቸው ከምንደሰተው በላይ የውዱ ነብያችን ንፁህ ቅዱስ ብፁአን ቤተሰቦች በግፈኞችና ሙጅሪሞች በማለቃቸው እናዝናለንና ያንን እናስተጋባለን !
የነብያችን ቤተሰቦች ስለሀቅ የከፈሉትን መስዋዕትነትም አጉልተን እናሳያለን !
እንኳን በሺአነት መፈረጅ ቢያከፍሩኝ ደንታ የለኝም !

👉 t.me/Seidsocial
#ጋዛ_እንደ_ከርበላእ ! ታሪክ ራሱን ሲደግሞ !

በሙጅሪሙ በየዚድ ቢን ሙአዊያና በቅዱሱ በሁሰይን እና ቤተሰቦቻቼው መካከል የተደረገው ፍልሚያ የሀቅና የባጢል ፍልሚያ ነበረ ። በርግጥ ሁሰይን የነብያችንን 70 የሚጠጉ ቤተሰቦች ይዘው ነው በየዚድ ቢን ሙአዊያ በ አስር ሺህ የሚቅጠር ጦር ከርበላእ ምድር ላይ የተከበቡት ።
መቼስ የረሱሉ ትንፋሽ ናቸው ! የጀግኖቹ ጀግና የአሊ የአብራክ ክፋይ የቅድስቷ የጀነቱ ዋና የፋጢመቱ ፍሬ ተወዳጁ ነቢ የሚሳሱላቸው የአይኔ ማረፊያ የሚሏቸው ቅዱሱ የጀነቱ ሙሽራ ሁሰይን !!! እርሳቸው ከአያታቸው ከሙሀመድ ቢን ከብዱሏህ ከአባታቸው ከአሊ ቢን አቢጧሊብ ከእናታቸው ከፋጢመቱ ዘህራ ቢንት ሙሀመድ የተማሩት የወሰዱት በሀቅ ላይ መሰዋትን እንጅ በፍረሀት ከሀቅ ማፈግፈግን አይደለም ። ደግሞም ውዱ ነብይ ናፈቀዋቸው የለ በሞቱ ወደርሳቸው ነው የሚሄዱት ። ፋጢመቱ ያቺ የሴቶች ጀግና በመካ ምድር ላይ ያኔ ሁሰይንን ለመግደል የከበቡት ወላጆች የሆኑት ቁረይሾች በነብያችን ላይ የእንሰሳት ፈርስ በላያቸው ላይ ደፍተው ለመነሳት ቢሞክሩ ባቃታቸው ጊዜ ያንን የቁረይሽ ሙጅረም መሪ ሁሉ ሳትፈራ ሂዳ ያንን ቆሻሻ ነገር ከውዱ ነብይ ከቅዱሱ ነብይ ከአዛኙ ነብይ ከንፁሁ ነብይ ላይ ያነሳችላቸው እነዚያን ሙጅሪሞች የጋፈጠችው ጀግና በርግጥ ለሁሰይን የጡት ወተቷን ሳይሆን ጀግንነት ፅናቷንም ነው አስተላልፋላቸው የሄደቺው ።

እናም ልክ ዛሬ እስራኤልና አጋሮቿ ምእራባውያን እና አረቦች ጋዛን ከብበው እንደሚፈጩት ሁሉ ያኔም የሙጅሪሙ የየዚድ ቢን ሙአዊያ ጦር የነብያችንን ቤተሰቦች ከቦ ጨረሳቸው ።
ዛሬ ላይ ጋዛን ሁሉም ሙስሊም እንደካዳቸው ሁሉ የነብያችንም ቤተሰቦች ተካዱ ። አለን ያሏቸው ኩፋዎች ነበሩ ። የኩፋ ህዝቦችን የዚድ ጦሩን ልኮ ዋናዎቻቼውን ሁሉ ሲጨርስባቸው ለነብያችን ቤተሰቦች ማን ይድረስላቸው !!???

ያኔ የዚድ በነብያችን ቤተሰቦች ላይ ረሀብን ውሀ ማስጠማትን እንደ መሳሪያ ተጠቅሞ ነበር ልክ ዛሬ ጋዛ ላይ እንደሚሆነው!
ኢማም ሁሰይን ልጃቸውን ከፍ አድርገው " እባካችሁ ይህን ህፃን ልጄን አንዴ ብቻ ውሀ እንዳጠጣ ፍቀዱልኝ ብለው የሙጅሪሞቹን ጦር በጠየቁ ጊዜ ሙጅሪሞቹ በሁሰይን ህፃን ልጅ ላይ ቀስት ነበር ያርከፈከፉበት ! ልክ እንደ አሁኑ እንደ ጋዛ ያውም ከዚያም በላይ !

አዎ ዛሬ ጋዛ ላይ ከምናየው ግፍ በላይ በከርበላእ ሙሉ የነብያችን ቤተሰቦች ዘራቸው ተጠፋ ። የሁሰይን አንገት ተቆርጦ ለየዚድ ቢን ሙአዊያ ስጦታ ተላከለት !!

በርግጥ የነብያችን ቤተሰብ ገዳዮች ሁላቸውም የእጃቸውን እያገኙ ነው ። አላህ ይበቀላል !!
ዛሬ ጋዛን የከዱት የነዚያ የበኑ ኡመውዮች የመንፈስ ተጋሪዎች ናቸው !

ሁላቸውንም ለአላህ ብየ ለነብዩ ብየ ለቤተሰቦቻቼው ብየ እጥላቸዋለሁ ! ከነዚህ ጨካኞች ጋርም ለአንድት ቅፅበት እንኳ አብሮ እንዳያኖረኝ !!!

👉 t.me/Seidsocial
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የሀማስ ሙጃሂዶች ወደ ፍልሚያ ከመግባታቸው በፊት የተገኘቺውን ነገር ይቀማምሱና ይተጣጠባሉ ውዱእ ያደራርጉና ያላቸውን ንፁህ ልብ ይለብሳሉ። ከዚያም ሽቶ ይቀባባሉ ። ፀጉራቸውን ፂማቸውን ያስተካክላሉ።
ባላቸው ነገር ይዋቡና ሶላት ሰግደው ዱአ አድርገው ለሞት እንደሚከፈን ሬሳ ራሳቸውን አበጃጅተው ወደ ጅሀድ ይገባሉ ። ሸሂድ ለመሆን አላህ ለመገናኘት ናፍቀው !ይህ እንግድህ የኢኽላስ ጥግ ነው።

ሙጃሂዶቹ ሲናገሩ በጣም በጣም ይገርማል ።
በቃ በዚህ ህይወት ውስጥ በዚህ አሳዛኝ ትግል ውስጥ ሆነው ደስተኛ ናቸው። ደግሞ ያላቸው የቂን !
በነገራችን ላይ ይህ የቴሌግራም ግሩፕ አሁን ካለው የአባል ቁጥር እኩል የሆነ ሰው በብሎክ አሰናብቻለሁ። ይህን የምለው ብሎክ በማድረጌ ለመመፃደቅ አይደለም ። አብዛኛው ብሎክ ያደረኩት ሰው ተሳዳቢ ለማወቅ ምንም አይነት ፍላጎት ሳይኖረው ሳያነብ በጭፍን የሚሳደብ የሚያከፍር ፅንፍ የረገጠ ፊርቀኛ ነው። እንደዚህ አይነት ሰው ጋር መዳረቅ ስለማያስፈልግ አብሬ አላስቀጥልም።

እኔ follower ደንታየ አይደለም ። ሲጀመር ሶሻል ሚዲያ ለኔ Cost እንጅ Benefit አይደለም ። የሚጠቅመኝ አንዳች ነገርም የለም። እውነት ያልኩትን መረጃዎች አስተላልፋለሁ ለአንባቢ ሰው ከጠቀመ ። ከዚያ ውጭ እየተከፈለህ ተላላኪ ምናምን ቅብጥርሶ የምትሉ ክሳችሁን ከቁምነገርም አልቆጥረውም።
እና በሀሳብ ልዩነት ውስጥ በሀሳብ የሚሞግተኝ ብቻ ጋር አብሬ እቀጥላለሁ ። ተሳዳቢና አክፋሪን ግን ታግሼ ከማስቀጥል ቻናሉን ደልቼው ብወጣ እመርጣለሁ። ተሳዳቢን ሙስሊምን የሚያከፍርን መአሰላማ ብሎ ማሰናበት አስፈላጊ ነው
በዛሬው እለት እስራኤል በአል መዋሲ የስደተኞች ካምፕ በላይ በፈፀመቺው የሚሳኤል ውርጅብኝ በሰአታት ውስት ከ 100 በላይ ተፈናቃይ ፍልስጤማዊያን አልቀዋል።

ጥቃቱ ፍልስጤማዊያንን ከጋዛ ምድር በሙሉ ለማጥፋት የሚደረገው የዘር ማጥፋት አካል ነው ። ሰሞኑን ከአሜሪካ ለቁጥር የሚታክት የጦር መሳሪያ ያገኘቺው ጨካኟ ሀገር እስራኤል ያለ ምንም እርህራሄ የታጠቀቺውን መሳሪያ ንፁሀን ላይ አርከፍክፋዋለች።ንፁሀንና ህፃናትም በእሳት እየተቃጠሉ መሞት እጣፈንታቸው ሆኗል።

ምእራባውያንም በስራቸው ተደስተው የፍልስጤማውያን ንፁሀንን የሲቃ ድምፅ ልክ እንደ ሞዛርት ሙዚቃ እያጣጣሙት ነው። የንፁሀኑ ለቅሶ ሲቀንስ እስራኤልን ሀይል ይጨምሩላትና እንደገና ሌላ ለቅሶ እያዘጋጁ ይሄ በአለም ፊት አለም አይኑ እያየ አንድ ህዝብ በሀያላን ትብብር እየጠፋ ነው።

👉 t.me/Seidsocial