Seid Social
23.2K subscribers
4.68K photos
980 videos
7 files
3.18K links
አለም አቀፋዊ መረጃዎች ምልከታዎችና ታሪካዊ ክስተቶች ይቀርቡበታል
Download Telegram
የቱርኩ የልድሪም ኻን አህጉር አቋራጭ ሚሳኤል ቱርክን በአለም ላይ ካሉ ጥቂት የሚሳኤል ሀያላኖች ጎራ ማለትም ከነ ሩሲያ ፣ አሜሪካ ፣ ቻይና ፣ ሰሜን ኮሪያ ጋር የሚቀላቅላት ብቻ አይደለም።
ይልቁንስ ይህ ሚሳኤል 3,000 ኪሎግራም የፍንዳታ ሀይል በመሸከም በአለም ላይ 4 ሀይለኛ ሚሳኤሎችም አንዱ የሚያደርጀው ነው።
ሚሳኤሉ 6,000 ኪሎሜትር የሚምዘገዘግ በመሆኑ አብዛኛውን የአለም ክፍል ማካለል ይችላል። ይህም ማለት ከአሜሪካ እስከ ቻይና ሊደርስ የሚችል ረጅም እርቀት ተጓዥ ሚሳኤል ነው። ጠቅላላ አውሮፓን አፍሪካን ሩሲያን እስከ ሩቅ ምስራቅ ኤዢያ ድረስ ማካለል ይችላል።

ሚሳኤሉ ሌላው ሀያል የሚያደርገው ፍጥነቱ ነው ። የልድሪም ኻን ከድምፅ ከ 9 እስከ 25 እጥፍ የሚፈጥን ሀይፐርሶኒክ ሚሳኤል በመሆኑ በአየር መከላከያ የመመታት እድሉ በጣም የጠበበ ነው ።
ሚሳኤሉ 3 ቶን ፍንዳታ ከመሸከሙ በተጨማሪ ብቻውን 7.2 ቶን እንደሚመዝን ይነገራል።

ይህ ሚሳኤል የኑክሌያር ሚሳኤል ባይሆንም ከኒክሌየር ሊቀራረብ የሚችል የፍንዳታ ሀይል ያለው ሚሳኤል ነው።
ሚሳኤሉ በቀጣይ የኑክሌያር አረርም እንዲሸከም ተደርጎ እንደተሰራ ይነገራል።
ቱርክ ካለ ብዙ ጩኸትና አለምአቀፍ ፍጭትም ከባባድ መሳሪያዎችን እየታጠቀች ትገኛለች።

ሚሳኤሉ በአራተኛው የኦቶማን ሱልጧን ቤይዚድ ቢን ሙራድ ወይንም በቅፅል ስሙ የልድሪም የተሰየመ ነው። የልድሪም ማለት ነጎድጓድ ማለት ሲሆን ለሱልጧን ብይዚድ ሀይለኛነትና ጀግንነትና ጠላትን አንበርካኪነት የተሰጠው ማእረግ ነበር።

ቴሌግራም
👉 t.me/Seidsocial
121👍34👏12🔥4🥰1
ሱልጧን ብይዚድ የልድሪም ማን ነው ካላችሁ እርሱ ጠላቶቹ በእጅጉ የሚፈሩት ስሙንም የልድሪም ወይንም ነጎድጓዳማው ያሉት አራተኛው የኡስማኒያ ሱልጧን ነበር።
ሱልጧን ቤይዚድ በልጅነቱ ከአባቱ ሙራድ ጋር በመሆን በጦር ልምድ ጥንቅቅ ብሎ ያደገ በኡለሞች ተኮትኩቶ ለመሪነት የወጣ ተወዳጅም ተፈሪም ሱልጧን ነበር። እርሱ የአርቱግሩል አምስተኛ ትውልድ የኡስማን አራተኛ ትውልድ የኦርሀን የልጅ ልጅ ልጅ የሙራድም ልጅ ነበረ።

ጦሩን ከአናቶሊያ እስከ ስራቅ አውሮፓ በሚያስደንቅ ፍጥነት የሚያንቀሳቅስ በመሆኑ መብረቅ ወይንም ነጎድጓድ የሚል ስም ተሰጠው።

ሱልጧን ቤይዚድ የመስቀል ጦረኞችን በሙስሊሙ አለም ላይ ከማሸነፍም አልፎ ተከታትሎ አውሮፓ ድረስ በመግባት ኒኮፖሊስ ላይ በ 1396 ከፈረንሳይ እንግሊዝ ጀርመን እና ሌላውም የአውሮፓ ክፍል የተውጣጣውን የአውሮፓ መስቀል ሀይል በመደምሰስ ደቡብ ምስራቅ አውሮፓን ለመጀመሪያ ጊዜ የኢስላማዊው ኦቶማን ግዛት አድርጎታል። በዚህም የባልካን ግዛት የኡስማኒያ ግዛት ሆነ። ዛሬ ላይ በአውሮፓ የምናውቃቸው ሙስሊም ሀገራት እነ አልባኒያ ፣ ቦስኒያ ፣ ኮሶቮ የመሳሰሉት ከያኔው መከፈት ጋር የተያያዙ ናቸው።

ቤይዚድ ሀያል ጦሩን እየመራ ኮንስታንትኖፕልን ለመጀመሪያ ጊዜ ከበበ። በዚህ ከበባ ላይ እያለ የቱርኮ ሞንጎሉ መሪ አሚር ቲሙር በቤይዚድ ላይ ጦርነት አወጀበት። አሚር ቲሙር ወይንም ቲሙር ኻን አልያ ታመርሌንም ይሉታል የቱርክ እና ሞንጎል ቅልቅል ሲሆን ኢስላምን ተቀብያለሁ በማለት አሚርነትን የተጎናፀፈ መሪ ነበር።
አሚር ቲሚር እጅግ ሀይለኛ በአለም ታሪክ ከታዩ የጦር ታክቲሻኖች ከእጅግ አስደማሚዎቹ አንዱ ነው። የቲሙር ቅፅል ደግሞ ነበልባል ይባል ነበር። በጊዜው ባደረገው ጦርነት ከ 17 ሚሊዮን በላይ ህዝብ እንደጨረሰ ይነገራል። እናም ቤይዚድ ነጎድጓዱ እና ቲሙር ነበልባሉ በአንካራ ግዙፉን ጦራቸውን እየመሩ ተላተሙ። ምድር ቃጤ ሆነች።

በርካታ ኡለምች አሚር ቲሙር ሙስሊም የመሰለው ለፖለቲካው ነው በማለት በቲሙር ላይ ጂሀድ ቀሰቀሱ። ግና ድል የአሚር ቲሙር ወይንም ታመርሌን ነበረች።
በአንካራ ጦርነት የኦቶማን ሱልጧኔት በቲምሩድ ሀይል ተሸነፈና ሱልጧን ቤይዚድ ተማረከ።
ሱልጧን ቤይዚድ ከነባለቤቱ ተማርኮ በአሚር ቲሙር ጋር ካሳለፈ በሗላ ሚስቱ አገልጋይ ሆና እንዲያት በማድረግ ከፍተኛ ቁጭት ከከተተው በሗላ አሚር ቲሙር በመጨረሻም ቤይዚድን ሊገድለው ችሏል።

ሱልጧን ቤይዚድ በመገደሉ ኮንስታንትኖፕልን መክፈቱ ሲቋረጥ የኦቶማን ሱልጧኔትም ተበታተነ። ከዚያ በሗላ ነው የሱልጧን ቤይዚድ ልጅ ሙሀመድ የተበታተነው ሱልጧኔት እንደገና መልሶ ዳግም ኦቶማንን የወለደው።

የሙሀመድ የልጅ ልጅ ሙሀመድ አልፋቲህም የቅድመ አያቱን የቤይዚድን ህልም በማሳካት ኮንስታንትኖፕልን ወይንም ኢስታንቡልን ሊከፍታት ችሏል።
ሱልጧን ሙሀመድ አልፋቲህ የሱልጧን ቤይዚድ የልጅ ልጅ ልጅ ነበረ።

ሱልጧን ቤይዚድ ከፍተኛ ዲስፕሊን ያለው ኡለማኦችን በከፍተኛ ደረጃ የሚወድ ሙስናና ማጭበርበርን በፍፁም የማይታገስ መሪ እንደነበር ይነገራል። ሱልጧን ቤይዚድ ለወታደሮቹ ቋሚ መደበኛ ደመወዝ መክፈል የጀመረ እንደሆነም ይነገርለታል።

እናም ቱርክ የመጀመሪያውን አህጉር አቋራጭ ሚሳኤል የሰየመቺው በዚህ ታሪካዊ መሪዋ ስም ነው።

ቴሌግራም
👉 t.me/Seidsocial
91👍19👏4🥰2🤔2
የእስራኤል ወታደር ዛሬ በሊባኖስ የድንግል ማርያምን ሀውልት ካዋረደ በሗላ ሁለት ሲጋራ ይዞ አንዱ ለርሱ እያጨሱ አንዱን የእርሷ ሀውል አፍ ላይ ሲሰካ መታየቱ አዲስ ቁጣን ቀስቅሷል።

በደቡባዊ ሊባኖስ ወረራ እየፈፀመ የሚገኘው የእስራኤል ጦር በክርስትና ገዳማት አብያተ ክርስቲያናት እና ሀውልቶች ላይ ከማፍረስ እስከ መፀዳዳት ከዚያ አልፎም በቤተክርስቲያን ውስጥ የወንድ ለወንድ ጋብቻ እስከማድረግ የደረሰ ማዋረድ እየፈፀመ ይገኛል።
እስራኤል ለይምሰል መግለጫ ብታወጣም ድርጊቱ ተባብሶ ቀጥሏል።

ቴሌግራም
👉 t.me/Seidsocial
😁13726👍18🤔7🤯5
መንግስትም ትምህርትን እየገደለው ነው!
አማፂያንም ትምህርትን እየገደሉት ነው!
የሀይማኖት ሰባኪ ነን ባዮችም ትምህርትን እየገደሉት ነው!
የማህበራዊ ሚዲያ ተፅእኖ ፈጣሪዎችም ትምህርትን እየገደሉት ነው!
በአጭር አቋርጠው የከበሩ ባለሀብቶችም ትምህርትን እየገደሉት ነው።
ሀገሪቱ አጠቃላይ ትምህርትን ጥናትና ምርምርን ጠላት አድርጋ ይዛለች።

መሃይምነት በእጅጉ ተንሰራፍቷል። ህዝቡ የሀይማኖት ጠንቋዮች ገባሪ ሆኖ አሜንን እያለ በመጮህ ለመለወጥ እየሞከረ ነው የሚገኘው። ድሮም መሀይም ህዝብ የጠንቋዮች መጫወቻ ነው።
አሁን ላይ ትምህርትን አማራጭ አድርጎ የሚወስድ ትውልድ እየጠፋ ነው።
ወይ ፈምሶ ወይ ሸፍቶ ወይ የሀይማኖት ጠንቋይ ሆኖ ወይንም ካድሬ ሆኖ ነው ለመለወጥ እየተመመ ያለው።

ሀገሪቱ ለትምህርት የምትበጅተውን ገንዘብ እየቀነሰች ሳይሆን እያቆመች ነው ማለት ይቻላል። አሁን ላይ ለመንግስት ትምህርት የሚባል ሲያዩት የማያምር ነገር ትኩረቱም ደንታውም አይመስልም።
ከ 10 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች በመላ ሀገሪቱ ከትምህርት ገበታ ውጭ ናቸው። ዩኒቨርሲቲዎች ለመዘጋት ተቃርበዋል።ተማሪዎቻቼውን የሚመግቡት ምግብ እንኳ የላቸውም ለምን? በጀት ስለተቋረጠ።

እናም አበበ ጅብ ሆነ ብሎ የሚገድል ፤ ማሪያም ቆላድባ ተከሰተች ብሎ እልልታውን የሚያቀልጥ ፤ አካውንቱ ላይ ገንዘብ እንዲገባለት የቅዱሳንን😁 ውሀ የሚያስረጭ ፤ መገዳደልና መጫረስ ቀላሉ የሆነለት መሀይም ህዝብ እየተፈጠረ ነው።
የአለም ህዝብ በምክንያታዊነት ወደፊት እየሄደ እየሰለጠነ በሄደ ቁጥር የኢትዮጵያ ትውልድ ግን በአስደናቂ መልኩ ወደሗላ ወደ መሀይምነት እየተጓዘ ነው። እዚህች ሀገር ላይ በትክክለኛው የትምህርት ስርአት ድግሪ የያዙ ሰዎች እያነሱ ድግሪ እና ዶክትሬት ገዝተው የሚያጠልቁ የሚበዙባት ሀገር እየሆነች የመሄዷ ነገር ያስፈራል!

መንግስት ትኩረት የነፈገውን የትምሀርት ዘርፍ ዳግም የትኩረት ዋነኛ አቅጣጫው አድርጎ ትውልዱን ካልታደገ እንደ ሀገር እንወድቃለን።

ቴሌግራም
👉 t.me/Seidsocial
👍6641😢8👏6🤔3👌2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"እንደት ፋኖን የትምህርት ጠላት አድርገህ ታስቀምጠዋለህ ፋኖኮ የአማራን ህዝብ ነፃ አውጭ ነው" የሚሉ አስተያየቶች ከቀደመው ፖስት ጋር ተያይዞ ደርሰውኛል።
እንደውም በኔ እምነት በኢትዮጵያ ውስጥ የፋኖን ያክል የትምህርት ጠላት ፤ የተማሩ ሰዎች ጠላት ያለ አይመስለኝም።
መማርም ማስተማርም የማይወድ የሰነፎችና የመሀይማን ስብስብ መሆኑን ቅንጣት አልጠራጠርም።

ይህ ሀይል "እንደት እኛ እየታገልን እናንተ ትማራላችሁ? በማለት በርካታ ተማሪዎችን የገደለ
" እንደት እኛ እየታገልን ታስተምራላችሁ በማለት በዚያ ጦርነት ውስጥ እንኳ እያስተማሩ የነበሩ መምህራንን አንበርክኮና አዋርዶ የረሸነ
በርካታ ትምህርት ቤቶችን አውድሞ የተቀሩትን መመሸጊያው ያደረገ
የለየለት የትምህርት ጥራት መሆኑ የሚያጠራጥር አይደለም።

ይህ ሀይል ውንብድናውን እንደ ነፃነት ትግል እየደሰኮረ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የአማራ ልጆችን ከትምህርት ገበታ ውጭ ያደረገ ትምህርት በዞረበት ያልዞሩ ወያላዎችና ማጅራት መችዎች ስብስብ ነው።

ይህ ከታች ያለው ቪዲዮ የዚህ ቡድንን ማንነት የሚያሳይ አንድ ማሳያ ነው። እናም ይሄ ቡድን በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ የትምህርት ገዳዮች ዋነኛው ነው።

መንግስትን እንደት የትምህርት ገዳይ ትላለህ ለሚሉ በቀጣይ ብልፅግና እንደት ትምህርትን እየገደለ መሆኑን እመለስበታለሁ!

t.me/Seidsocial
💯4136👍11🤔5
መንግስት የትምህርት ሴክተሩን ያክል ጦርነት ያወጀበት የገደለው ሌላ ሴክተር ያለ አይመስለኝም። በብልፅግና 8 የስልጣን አመታት የትምህርትን ያክል ትኩረት የተነፈገው በፊት ይበጀትለት የነበረው በጀት የተቋረጠበት ሴክተር የለም።

ለምሳሌ ዩኔሴፍ በ 2024 ይዞት የወጣው መረጃ እንደሚያሳየው ኢትዮጵያ ለትምህርት የምትበጅተው በጀት ከኢኮኖሚዋ አንፃር በከፍተኛ ሁኔታ እያሽቆለቆለ መሆኑን ያሳያል። 2020 ላይ ኢትዮጵያ 4% ኢኮኖሚዋን ለትምህርት ታውል የነበረ ሲሆን በ 2024 ይህ አሀዝ ወደ 2.3% አሽቆልቁሏል ። ይህም ኢትዮጵያን በአለም ደረጃ ከኢኮኖሚ ጥቅል ምርታቸው አንፃር ዝቅተኛ በጀትን ለትምህርት ከሚመድቡ 21 ሀገራት አንዷ ያደርጋታል። በአለም ላይ ከኢትዮጵያ በታች ለትምህርት የሚመድቡት ኤርትራ ሱዳን እና ደቡብ ሱዳንን የመሳሰሉ መናጢ ጎረቤቶቻችን ናቸው።
በአሁኑ ሰአት ኢትዮጵያ በአለም በትምህርት ደረጃ ከ 193 ሀገራት 182 ደረጃ ላይ ትገኛለች። ይህ የዩኒስኮ መረጃ ነው። የምንበልጠው 10 ሀገራትን ብቻ ነው ማለት ነው። እንዴ ሀገር ወዴት እየሄደች ነው ተብሎ አይጠየቅም እንዴ?!!

አንድት ከፍተኛ ያልተማረ ህዝብ ያለባትና ህዝቧም በከፍተኛ ደረጃ እያደገ ያለባት ከፍተኛ የተማረ የሰው እጥረት ያለባት ሀገር ትልቁ በጀቷ ትልቁ ኢንቨስትመንቷ ሊሆን የሚገባው ትምህርት ነበር። እንዳለመታደል ግን እኛ በተቃራኒው ነው እየተጓዝን ያለነው።

ታዲያ መንግስት ለትምህርት የሚሰጠውን በጀት በከፍተኛ ደረጃ ቀንሷል ማለት ምን ማለት ነው? ጉዳቱስ ምንድነው ? ካልን እንደው በደፈናው ሀገር ቀንጭራ ትቀራለች ማለት እንችላለን። ትንሽ እናብላላው።

1 ለትምህርት የሚሰጠው በጀት በመቀነሱ ሀገሪቱ ባለፉት 8 አመታት አዳዲስ ዩኒቨርሲቲዎች እና የምርምር ማእከላትን መገንባት እንድታቆም አድርጓታል። ካለነዚህ ተቋማት በምንም ተአምር አንዲት ሀገር አትለወጥም አታድግም!

2 ያሉት ዩኒቨርሲቲዎች የቅበላና የማስተማር አቅማቸው በከፍተኛ ሁኔታ ተጎድቷል። የሚለቀቅላቸው በጀት በመቀነሱ ዩኒቨርሲቲዎች ለተማሪዎቻቼው የሚያቀርቡትን ግብአቶች በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሰዋል። ከካፌ ምግብ አቅርቦት ጀምሮ በአሁኑ ሰአት ዩኒቨስቲ መማር እጅግ ከባድ ሆኗል።

3 ትምህርት የጥቂቶች እንዲሆን ተደርጓል። ዩኒቨርሲቲዎች ድጎማ ስለተነሳባቸውና ራሳችሁን ቻሉ ስለተባሉ እያስከፈሉ ወደ መማር የንግድ ማእከልነት ተሸጋግረዋል። በዚህም መክፈል የማይችሉ የድሀ ልጆች በሀገሪቱ ታላላቅ ዩኒቨርስቲዎች መማር እንዳይችሉ እየተደረጉ ነው። ታላቅ የትምህርት ብቃት ያላቸው ተማሪዎች እንዲህ እንዲሆኑ መፈረዱ አሳዛኝ ነው። ይህ ሂደት በሀገሪቱ አደገኛ ውጤት ይኖረዋል።

4 ደካማ የመማሪያ ከባቢ ተፈጥሯል። ከደረጃ በታች የሆኑ በቂ የቴክኖሎጂ ግብአት የሌላቸው እንዲሁም ፅዱ ኢንቫይሮሜንት የሌላቸው ዩኒቨርስቲዎችና ትምህርት ቤቶች በእውቀት የታጠቀ ከዘመኑ ጋር አብሮ መጓዝ የሚችል ትውልድ ያፈራሉ ብሎ ማሰብ ላም አለኝ በሰማይ የሆነ ህልም ነው!

5 የመማር መንፈስ ተሰብሯል። አሁን ትውልዱ መማር አይፈልግም። ቅድመ ምረቃም ሆነ ድህረ ምረቃ ያሉት ሁኔታዎች ለትምህርት የሚጋብዙ አይደሉም።

6 መንግስት የሰነፍ ፕሮፓጋንዳ እየሰራ ነው። ፈትኖ ትንሾ ተማሪ ማሳለፍን እንደ ትልቅ ስኬት በመቁጠር አብዛኛውን ተማሪ ብቁ እንዳይሆንና ከፈተና ጥራት ይልቅ የትምህርት ጥራት ላይ እንዳይሰራ አድርጓል።

7 ይህ ሁኔታ ከቀጠለ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ፣ እድገት ከፍተኛ አደጋ ይደቀንበታል።

8 ትምህርት የጥቂቶች ብቻ የሚሆንበት ሁኔታ እየተፈጠረ ነው። ይህቺን ለመቀባባት ምሳ እየመገብኩ እያሰሰተማርኩ ነው የሚለው የመንግስት ማስተባበያ ህመሙን አያክመውም።
9 መምህራኖች በቂ ክፍያ የማይከፈላቸው በመሆኑ የመማር ማስተማርን ሞራል በከፍተኛ ሁኔታ ይጎዳዋል። የስራ አጥነትም ይስፋፋል። የሀገሪቱን ፍላጎት ማሟላት የሚችሉ ብቁ ዝጎች እንዳይወጡ ያደርጋል።

በመሆኑም መንግስት ለትውልድ ካሰበ ትኩረት የነፈገውን የትምህርት ዘርፍ ትኩረት ይስጥ። የዩኒቨርስቲ ድጎማዎችን ይቀጥል። ለትምህርት ያልሆነ በጀት ለምርምር ያልሆነ ገንዘብ ለምን ሊሆን ነው???

እኔ በዚህ ጉዳይ ስለ ሀገሩ እንደ ሚቆረቆር አንድ ኢትዮጵያዊ መወትወቴን እቀጥላለሁ።

ቴሌግራም
👉 t.me/Seidsocial
54👌12👍9🤔4😢2👏1
ቻይና ሁለት መከላከያ ሚኒስትሮቿ ላይ የሞት ፍርድ ወስናለች።
በሙስና ምክንያት ከሁለት አመት በፊት ከስልጣን የተነሱት መከላከያ ሚኒስትሩ ወይ ፈንጌ እና ሌላኛው የቀድሞው መከላከያ ሚኒስትር ሊ ሻንግፉ በተጠረጠሩበት የሙስና ወንጀል ጥፋተኛ መባላቸውን ተከትሎ ሁለቱም ላይ የቻይና ፍርድ ቤት የሞት ፍርድ በይኗል።

የሞት ፍርዱ ለሁለት አመት የሚዘገይ ሲሆን በሁለት አመት ውስጥ ተጨማሪ ወንጀል ካልተገኘባቸው ወደ እድሜ ልክ እስራት ሊቀየር ይችላል።
ከሞት ፍርዱ በተጨማሪ የሁለቱ መከላከያ ሚኒስትሮች ሀብትም ሙሉ ለሙሉ ተወርሷል።

በቻይና ሙስና በሞት የሚያስቀጣ እጅግ አደገኛ ወንጀል ነው። ቻይና የትኛውም ባለስልጣን ሙስና ውስጥ ገብቶ አገኘሁት ካለች የሚጠብቀው ሞት ነው።

ቴሌግራም
👉 t.me/Seidsocial
👍9529👏9🔥5🥰1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አሜሪካ እና ኢራን ዳግም ጦርነት ጀምረዋል።
የኢራን አየር መከላከያ በቴህራን እና ሌሎችም የኢራን አካባቢዎች የመከላከል እርምጃ እየወሰደ ሲሆን በደቡባዊ ኢራን ፍንዳታ ተሰምቷል።

አሜሪካ ጥቃቱን እንደፈፀመች ገልፃ ነገር ግን የተኩስ አቁም ስምምነቱን ማፍረስ አይደለም ብላለች።

ኢራን በበኩሏ አሜሪካ የተኩስ አቁም ስምምነቱን መጣሷን በመግለፅ የአፀፋ እርምጃዋን እንደምትጀምር ገልፃለች።

ኢራን ወደ ሆርሙዝ ሊገቡ ያሉ ሶስት የአሜሪካ ጦር መርከቦችን ማጥቃቷንም ገልፃለች ።

t.me/Seidsocial
121🤔17👍7👀5😁4🥰1👏1🕊1
አሜሪካ ከማታው ሚከራዋ ዳግም አፈግፍጋለች።
የአሜሪካ ጦር መርከቦች ወደ ሆርሙዝ ሰርጥ ለመግባት ያደረጉት ሙከራም በኢራን የሚሳኤል ጥቃት ምክንያት ከሽፎ መርከቦቿ ወደ ሗላ መመለሳቸውን አሜሪካ አስታውቃለች።

በኢራን ዋና ግዛት ላይ የተፈፀሙ የአየር ጥቃቶችንም የኢራን አየር መከላከያ ማክሸፍ በመቻሉ ውድመት ሳይደርስ ቀርቷል።

አሜሪካ ጥቃቱን የፈፀምኩት በጦር መርከቦቼ ላይ ለተፈፀመው ጥቃት አፀፋ ነው ብትልም እውነተኛ ምክንያቱ ግን ኢራንን ወደ ድርድሩ ለማስገደድ እና የአሜሪካ ፍላጎቶች እንዲትቀበል ለማስገደድ ነበር። ሆኖም ሁሉም ሳይሳኩ አሜሪካ ጦጦርነቱን አቁማለች።

ቴሌግራም
👉 t.me/Seidsocial
102👍38😁4🕊2🤔1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ይህ እንግዲህ ለአማራ ህዝብ ሲባል ነው¡
እንኳን ነፃ ሊያወጡ ነፃነት ምን እንደሆነ እንኳ የማያውቁት የመሀይማን ስብስብ በነፃነት ስም ላዘሮፉት ከዘመቱበት የአማራ ህዝብ ላይ እንደዚህ በሬውን እያረዱ የስጋ አምሮታቸውን እየተወጡ ነው።
እነዚህ ሽፍታዎች የአማራን ገበሬ ካለ በሬ አስቀርተው መሬቱን ጦር አሳድረው ለረሀብ እየዳረጉት ይገኛሉ።
ጠላ እያስጠመቁ እንጀራ እያስጋገሩ ከዚያ እንዲህ እያረዱ ዘልዝለው አለማቸውን እየቀጩ ነው።
የአማራ ህዝብ እንዲህ ያለ ጠላት በታሪኩ ገጥሞት አያውቅም!

ቴሌግራም
👉 t.me/Seidsocial
57😢22👍15🤔4😭2🤯1
ከ 2013 እስከ 2022 በ 9 አመት ውስጥ ብቻ ኢትዮጵያ በሙስና 25 ቢሊዮን ዶላር አጥታለች። ይሄ የሀገሪቱን አጠቃላይ ኢኮኖሚ 25% ይሸፍናል። ከ 2022 በሗላ ደግሞ የሙስና ፍጥነቱ በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ በአመት ወደ 5 ቢሊዮን ዶላር እየደረሰ መሆኑን የአፍሪካ ልማት ባንክ ያወጣው መረጃ ያሳያል።
በትንሹ 3 ቢሊዮን ዶላር ወስዳችሁ ከላይ ካለው ቁጥር ላይ ብትጨምሩበት አጠቃላይ ኢትዮጵያ ከ 2013 ጀምሮ በሙስና ያጣቺው ገንዘብ 34 ቢሊዮን ዶላር ይደርሳል።
ይሄንን አሀዝ ወደ ብር ብትቀይሩት 5 ትሪሊዮን 440 ቢሊዮን ብር ይደርሳል።
ይሄ የተወሰደ ብር የት ነው የሄደው ካላችሁ እንደ አፍሪካ ልማት ባንክ መረጃ ከሆነ አብዛኛው በባለስልጣናት እና በባለሀብቶች አማካኝትት ከኢትዮጵያ ወጥቷል።

የአፍሪካ ልማት ባንክ መረጃ አክሎም በኢትዮጵያ የውጭ ገቢ ንግድ በትክክል ሪፖርት የሚደረገው 35% ብቻ ሲሆን 65% ሪፖርት የውሸት ሪፖርት ነው።

የኢትዮጵያ 15 የኢትዮጵያ ቢሊየነሮች በስዊዝ ባንክ እና በካሪቢያን ወስጥ በምትገኘው ካይማን ደሴት በሚገኝ ባንክ አካውንት ከፍተው ገንዘባቸውን ወደዚያ ያስወጣሉ- ከባለስልጣናት ጋር በመተባበር።
የኢትዮጵያ የወርቅ 30% ከኢትዮጵያ በሱዳን በኩል ብሎ ኢማራት ይደርሳል እንጅ የኢትዮጵያ ባንኮችን ንክች አያደርግም።

ይሄ ሁሉ ሀብት ከዚህ ድሀ ህዝብ ላይ ከዚህች ድሀ ሀገር ላይ የተቀማ የተሰረቀ ነው።
ይሄ እጅ ከወርች የሚያሳስር ሙስና ባለበት ተጨባጭ ሀገር በፍፁም በፍፁም አታድግም።

የደለቡት ሳይጠግቡ ሌሎች አዲስ ረሀብተኛ ሙሰኞችም እየመጡ ሀገሪቷ እንዲህ ሆና መቅረቷ ያሳዝናል።
ይህ ሙስና የኢትዮጵያ ህዝብ የኑሮ ሁኔታ ያቃወሰ ፤ የዋጋ ንረቱን ባለፉት ጥቂት አመታት ከ 400%
በላይ እንዳደርስ ያደረገ ፤ የብርን የመግዛት አቅም ባለፉት ስምን አመታት ብቻ በ 500% እንዲወድቅ ያደረገ አሳዛኝ ሰባሪ ክስተት ነው።

ይህን በሙስና የሚጠፋውን ገንዘብ ለማሟላት ሀገሪቱ በነ IMF የብድር ማነቆ ውስጥ ገብታለች ፤ ህዝባችን ላይ ከአቅም በላይ የሆነ ግብር ተቆልሎበታል እንዲሁም በርካታ ሀገር የሚለውጡ ፕሮጀክቶች ታጥፈዋል።
በዚህ ሙስና ምክንያት ሀገሪቱ የጦር አውድማ ሆና መረጋጋት የተሳናት ሆና ቀጥላለች!

ኡኡኡኡ የሚያስብል ሁኔታ ላይ ነው ያለነው!

ቴሌግራም
👉 t.me/Seidsocial
58💔21🤔16😭7👍2😢1
ትራምፕ የኢራን ጦርነት ቢለው ቢለው አልገፋው ብሎ ስልችት ድብር እንዳለው ዘ አትላንቲክ ይዞት የወጣው መረጃ ያሳያል።
ኢራንን በጦርነቱም በከበባውም እጅ ለማሰጠትና ለስምምነት ለማንበርከክ የሚያደርገው ጥረት ሁሉዐዋጋ አልባ ሆኖበታል።
በአሀኑ ሰአት በጦርነቱ የተሰላቸው ትራምፕ ከሁሉም በላይ የሚፈልገው ጦርነቱ እንዲቆም ቢሆንም የእስራኤል ፍላጎትና ጦርነቱን በምን መልኩ ማጠናቀቅ እንዳለበት በመቸገሩ አሰልቺ የሆነ ጉዞ ቀጥሏል።

ይሄ የአለም ጦስ የሆነ መሪ ይሄው በእርሱ ጦስ ምክንያት እኛንም እያሰቃየን ይገኛል።

የፅዮናዊያን ፕሮጀክትን ያክል በ21ኛው ክፍለዘመን አለም ትልቅ ዋጋ ያስከፈለ የለም።

ቴሌግራም
👉 t.me/Seidsocial
106👏24👍11💯6😁4🤔3🕊1
የምክንያታዊነት ድርቅ በመታውና የፖለቲካ ሀይሎች በጥናት የተደገፉ የፖሊሲ አቅጣጫዎችን ለማቅረብ በሚሰንፉበት የኢትዮጵያ ፖለቲካ መድረክ የራሱን ሁሉን አቀፍ የፖሊሲና ስትራቴጂ አቅጣጫ አመታትን በፈጀ ጥናት ቀርፆ የመጣው የነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ ነእፓ በዛሬው እለት በአዲስ አበባ የምርጫ ቅስቀሳ ሲያደርግ ውሏል።

የነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ ነእፓ ለታመመው የሀገራችን ኢኮኖሚ ፣ ለተቃወሰው ማህበራዊ መስተጋብራችኝ ፤ ለተበላሸው የፖለቲካ ምህዳራችን ፤ እንዲሁም ከፍተኛ የእርስበርስ እልቂትን እያስተናገደ ላለው የሀገራችን ሰላምና መረጋጋት ችግር የመፍትሄ አቅጣጫ ይሆናሉ ያላቸውን ፖሊሳዎቹን እና ሶትራቴጂዎቹን አዘጋጅቶ በሰላማዊ ትግል ስለ ህዝብ ስለ ሀገር ለመስራትና ህዝቡ ይሁንታውን ከሰጠው ለማገልገል የተዘጋጄ የፖለቲካ ፓርቲ ነው።

የነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ በእድሜ ከሌሎች ፓርቲዎች አንፃር ዘግይቶ የተመሰረተ ቢሆንም በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ አባሎችን ይዞ የራሱን የፖለቲካ ቀለም ፈጥሮ በከፍተኛ ተነሳሽነት እየተንቀሳቀሰ ያለ ፓርቲ ነው።

ፓርቲው ለአካታች ፣ ምክንያታዊ ፖለቲካ ቅድሚያ በመስጠት የሀገራችን ችግሮች የመፍትሄ አካል ለመሆን ዝግጅቱን አጠናቆ አላማውን ለህዝብ እያስተዋወቀ ይገኛል።

ነእፓ የምርጫ ምልክቱ ብእር ሲሆን ለተሻለ የፖለቲካ ምህዳር ነእፓን እንዲትመርጡ ጥሪየን አቀርባለሁ።

ቴሌግራም
👉 t.me/Seidsocial
129👍34😁9🤯4🤷‍♂3🤔3💔1
የኢትዮጵያን ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ አስመልክቶ ምርጫ ቦርድ ባዘጋጀው ፕሮግራም ላይ ያደረግነው የክርክር መድረክ በሀገሪቱ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ምሽት 2:30 ላይ ይቀርባል።
በኢቲቪ እና ፋና ብሮዲካስቲንግ ኮርፖሬትን ጨምሮ በሁሉም የሀገሪቱ ቴሌቪዢኖች 2:30 ላይ ተከታተሉን።

ትላልቅ የፖለቲካ አካላትና በርካታ መገናኛ ብዙሀን በተገኙበት ያደረኩት የመጀመሪያ የክርክር መድረክ እንደመሆኑ ሀሳብ አስተያየታችሁን እጠብቃለሁ!
በፅሁፍ የምታውቁኝ የንግግር ድስኩሬንም ምን እንደሚመስል ታዩት ዘንዳ ጋበዝኳችሁ።

t.me/Seidsocial
93👍34🥰3😁2
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
"በአንድ በኩል ገና ለሚመሰረቱ ቢዝነሶች የታክስ እፎይታ እንሰጣለን ትላላችሁ በሌላ በኩል ታላላቅ ፕርጀክቶችን እናስኬዳለን ትላላችሁ ። ባልሰበሰባችሁት የገቢ ግብር ከየት አምጥታችሁ ነው ስለ ፕሮጀክት የምታወሩት" በሚል ከብልፅግና ፓርቲ ለቀረበልን ጥያቄ በዚህ መልኩ ምላሽ ሰጥተናል
👏11549💯13🏆11👌10🥰2
ሙሀመድ ቡአዚዝ ደስተኛ ብሩህ ተስፋ ያለው ለቤተሰቦቹና ዘመዶቹ የሳቅ ምንጭ የሆነ ወጣት ነበር። ሙሀመድን ሰዎች "በስቡስ" ብለው ነበር የሚጠሩት። ማሳቅ ቀልድ የማያልቅበት እንደ ማለት ነው።

ሙሀመድ አባቱ በልጅነቱ ስለሞተበት እናቱን እና ስድስት ወንድምና እህቶቹን ማገዝ የእርሱ ድርሻ ሆነ። ኑሮ እየከበደ የመንግስት ብልሹ አሰራሮች የበለጠ እየተንሰራፉ በመጡባት ቱኒዚያ ለሙሀመድ ኑሮ ቀላል አልሆንለት አለች። ደስታ እየራቀው ያ የማያልቅበት ቀልዱ እየደበዘዘ መጣ። ቢሆንም ሙሀመድ ብርቱ ወጣት ነው። ተስፋ የማይቆርጥ የቤተሰቦቹ ምሰሶ የሆነ ወጣት።

በጧት ይነሳና ጋሪውን ያስነሳና ከጅምላ አከፋፋዮች አትክልትና ፍራፍሬዎችን ገዝቶ በችርቻሮ ሲሸጥ ይውላል ከጧት እስከ ማታ! ከዚያ ቤቱ ሂዶ ትንሽ ይተኛና መልሶ ተነስቶ ሲንከራተት ይውላል። ባገኛት ገንዘብ የቤተሰብ አስቤዛውን ይገዛል ከዚያ ብድር ተበድሮ እንደሆነም ይከፍላል። ለ 26 አመቱ ሙሀመድ ህይወት እንደዚህ ነበረች።

ግና ሙሰኞች የሚመሯት ጋጠወጥ የፀጥታ ሀይሎች የሚርመሰመሱባት ቱኒዚያ እንዲህ እየተንከራተተ እንዲኖር እንኳ ልትፈቅድለት አልቻለች። ፖሊሶችና የፀጥታ አስከባሪዎች አንተ ህገወጥ ነህ ብለው አትክልቱን ከነጋሪው ቀምተው ፖሊስ ጣቢያ ወሰዱበት። ያች የሚገፋት ጋሪ እነዚያ አትክልቶች የሙሀመድ ብቻ ሳይሆን ከጀርባው ያሉት የእናቱና የ 6 ወንድም እህቶቹ ህይወት መሆኗ ለነርሱ ደንታ አይሰጣቸውም።

ለመናቸው ተማፀናቸው ግና ፖሊሶቹ እምቢ አሉት። ህይወት ያደከመቺው የ 26 አመቱ ለግላጋ ታታሪ ወጣት ሁሉንም ቢያማትር ተስፋ የሚያደርግበት አጣ። መተንፈስ ተሳነው። እናም አንድ ያልተጠበቀ ውሳኔ በራሱ ላይ ወሰነ - በአደባባይ ላይ ራሱ ላይ ነዳጅ አርከፍክፎ ማቃጠል!

ሙሀመድ አደረገው። አደባባይ ላይ ራሱን አቃጠለ። የአደጋ ጊዜ ሰዎች መጥተው ሊያድኑት ሞከሩ። ሆስፒታል ገባ እዚያው ከሳምንት በሗላ ህይወቱ አለፈች። ቪዲዮውን አጎቱ አሊ ፌስቡክ ላይ ፖሰተው። መገናኛ ብዙሀን ተቀባበሉት። የቱኒዚያ ህዝብ ድርጊቱን ሰማ ። አዘነ እጅግ ተቆጣ። በሙሀመድ ውስጥ ሁሉም የራሱን ኑሮ አየው። እናም አደባባይ ወጣ። በሙሰኛ ባለስልጣናቱ ላይ አመፀ። ለሙሰኞች አልገዛም ብትገድሉኝም ይሄው የሙሀመድ መንገድ መኔገዴ ኑሮውም ኑሮየ ስቃዩም ስቃየ ነው አለ።
እናም ያ አብዮት ተቀጣጥሎ ለ 25 አመት ቱኒዚያን ረግጦ የገዛውን የዘይኑልአቢዲን ቢን አሊ ን አገዛዝ ገረሰሰ። ዘይኑልአቢዲንም ከቱኒዚያ አምልጦ ሳኡዲ አረቢያ በመግባት ሸሸ።

ግና የሙሀመድ ቡአዚዝ መስዋዕትነት በቱኒዚያ ብቻ አልተገደበም። መላ የአረብ ሀገራትን አቀጣጥሎ በአብዮት እና ነውጥ ናጣቸው። እነ ግብፅ ፣ ሊቢያ ፣ ሶሪያ ፣ የመን ፣ ባህሬይን ምን የቀረ አለ በተቃውሞ ንዳድ በአብዮት ማእበልም ተናወጡ። ሚሊዮኖች ሞቱ። እነ ሶሪያና ሊቢያ ፈራረሱ። በርካታ ሀገራት እንዳልነበር ሆኑ።

ይህ ሙሰኛና አምባገነን ጨካኝ አገዛዞች ህዝብን ተስፋ ሲያስቆርጡ የሚፈጠር ውድመት ነው። ውድመቱ ደግሞ እነርሱንም ሳይምር ያጠፋል። ሀገርም ያፈርሳል።

ለብልፅግና መንግስት የማስተላልፈው ማሳሰቢያም
የህዝብን ብሶት ይስማ ፤ የዲሀን ለቅሶ ይስማ ፤ተስፋ የቆረጠ ህዝብ እስኪነሳ አይጠብቅ ያኔ ውድመቱ ማንንም አይምርምና ነው!
እንደዚህ ያሉ በሙስና ከራሳቸው እስከ እግራቸው የተነከሩ ባለስልጣናትን ይዞ አይደለም ለውጥና እድገት ይቅርና ሀገር ማስቀጠልም ይቸግረዋል።

ብልፅግና ተናጋሪ ብቻ አይሁን። የህዝብ ድምፅ ይስማ!
ያ ለሁሉም ይጠቅማል።

ቴሌግራም
👉 t.me/Seidsocial
👍6935💯25🔥3🥰1
ህወሀት ለትግል ሲነሳ ሀይማኖት አልባውንና ለሰው ልጆች ሁሉ እኩልነት የሚያቀነቅነውን የማርኪሲዝም ሶሻሊዝምን ወይንም ኮሚኒዝምን ርእዮተ አለም አንግቦ ነበር የተነሳው።
ያኔ በብሔርና ሀይማኖት ጭቆና ፍዳዋን በምትበላው ኢትዮጵያ የዚህን የመደብ ጭቆናና ሀይማኖት የተቀባ አንዱ ፀያፍ አንዱን ቅዱስ አገዛዝ የተማረሩ ሰዎች የመሰረቱት ህወሀት በርግጥ አነሳሱ መብትና ነፃነትን ለመጎናፀፍ ነበር። ያ ግቡ ሀገር መገንጠልም ያለበት ቢሆንም!

በህወሀት ውስጥ የነበሩት በሳልና በትግል የተፈተኑ አመራሮችም ህወሀት የህዝብ ልጅ እንዲመስል አድርገው መላ የትግራይን ህዝብ ሀይማኖት ሳይለይ አሰልፈው ከዚያም በርካታ የአማራና የኦሮሞ እንዲሁም የሌላውን ህዝብ ከጎናቼው በተጨቁነሀል ስም አሰልፈው የደርግን መንግስት ጥለዋል። በርግጥ ደርግ የብሔር ጨቋኝ ነው ማለት ያስቸግራል።

የሆነው ሆኖ ህወሀት ፌድ እያደረገ መጥቶ አሁን ላይ ሁሉንም ካርዶችን ጨርሶ በርእዮተ አለም መመራቱን ትቶ ሀይማኖታዊ ፅንፈኝነት ውስጥ የተሸጎጠ ሀይል ሆኗል።

ተስፋ የቆረጠና ለሀገርና ህዝቡ የሚሸጠው ሀሳብ የሌለው የፖለቲካ ሀይል ሁሌም ሀይማኖትና ብሔር ውስጥ ተወሽቆ ነው መጨረሻውን የሚያደርገው።
በዚህች ሀገር በዚህ ሰአት በዘርፈ ብዙ ችግርና መከራ ውስጥ የሚገኘው የትግራይም ህዝባችንም ሆነ በአጠቃላይ የሀገራችን ህዝብ የተጠማው እና ህልሙ ሀይማኖታዊ ስርአትና ቅድስና አይደለም።
እንደውም ይሄን የህዝብ የሀይማኖት መሪ ነን ባይ የተበረዙ ጥቅም አሳዳጅ መሪዎች አሰልችተውታል አባልተውታል አዳክመውታል።

ለትግራይ ወገኖቻችን የሚጠቅመው ህዝቡ ካለበት ሁለገብ ኢኮኖሚያዊ እና ሰብአዊ ችግር የሚወጣበት ከጦርነትና ስደት እፎይ የሚልበት ሁኔታ እንጅ ከተሞችን ቅዱስ አድርጎ ሌላውን ህዝብ የሚያረክስ አድርጎ ለ 3,000 አመታት አብሮ የኖረን አብሮ ክፉ ደግ ያሳለፈን ህዝብ መጤ የሚል ታፔላ ለጥፎ እርስበርስ የሚያባላ ሁኔታ አይደለም።

ቁሞቀር የህወሀት አመራሮች ከጥቅመኛና ዘረኛ የሀይማኖት መሪዎች ጋር ተጣምረው በአክሱም ሙስሊሞች ላይ የሚፈፅሙትን አፓርታይዳዊ አፈና ሊያቆሙ ይገባል።
ይህ ለነርሱም ለትግራይ ህዝብም ይጠቅማል!

ቴሌግራም
👉 t.me/Seidsocial
👍5323🥰1