Seid Social
10.2K subscribers
2.5K photos
418 videos
6 files
1.61K links
አለም አቀፋዊ መረጃዎች ምልከታዎችና ታሪካዊ ክስተቶች ይቀርቡበታል
Download Telegram
የዩክሬን ጦርነት መከሰት ፋታና አንፃራዊ እፎይታ ከሰጣቸው ህዝቦች ውስጥ ሶሪያዊያን ወንድምቻችን ዋነኞቹ ናቸው።
ሩሲያ ከአምባገነኑ የበሽር አልአሳድ ጎን ተሰልፋ በሶሪያ ንፁሀን ላይ የፈፀመቺው ጭፍጨፋ ከሰቅጣጭ ግፎች አንዱ ነው። ሩሲያ አሊፖና ሆምስን አፈራርሳ ኢድሊብን አውድማ በሶሪያዊያን ላይ ከፍተኛ ግፍ ፈፅማለች።

የበሽር አልአሳድ መንግስት አፈር ልሶ እንዲነሳ ከኢራንም በላይ ሩሲያ ቀዳሚውን ቦታ ትይዛለች። ሩሲያ በሶሪያዊያን ላይ በአለምአቀፍ ህጎች የተከለከለውን የክላስተር ቦንብ ጭምር ተጠቅማለች።

አሁን ላይ ሩሲያ በዩክሬን ጦርነት ስለተወጠረች በተቃዋሚዎች ቁጥጥር ስር በሚገኙ የሶሪያ ግዛቶች የሚኖሩ ሶሪያዊያን አንፃራዊ ሰላም አግኝተዋል።

👉 t.me/Seidsocial
ሳኡዲ አረቢያ የፍልስጤምን ካርታ ከመማሪያ መፅሀፎቿ ላይ መፋቋ ተገለፀ ።
በሳኡዲ አረቢያ አዲሱ የትምህርት ካሪኩለም መሰረትም ፍልስጤም የምትባል ሀገር እንደሌለች ተገልጿል ። ሳኡዲ ለተማሪዎቿ የአለም ካርታ ላይ ፍልስጥኤም የምትባልን ሀገር ማግኘት እንዳይችሉ አድርጋለች። እናም የፍልስጤም ግዛት ባዶ ቦታ እንዲሆን ተደርጓል።

ሳኡዱ አረቢያ ከዚህ በተጨማሪ እስራኤልን በጠላትነት የሚፈርጁ ገለፃዎችን በሙሉ ከማስተማሪያ መፅሀፎቿ ማውጣቷም ታውቋል። በፊት የነበሩ እስራኤልን " ጠላት " "ፅዮናዊት ጠላት " የመሳሰሉ ቃላትም በሳኡዲ የመማሪያ መፅሀፍ ውስጥ ከእንግዲህ አይገኙም። በአጠቃላይ እስራኤልን በክፋትና ቀጠላትነት የሚገልፁ ከቀድሞው መማሪያ መፅሀፍት ላይ የነበሩ 21 ገለፃዎች መወገዳቸውን the New Arab የዜና ወኪል ዘግቧል።

ሳኡዲ አረቢያ ከዚህ በተጨማሪ በሀገሪቱ እስራኤልን የሚያወግዙ ድርጊቶችን ማገዷ ይታወቃል። ለዚህ የሳኡዲ ለውጥም የአሜሪካ ጥረት በሰፊው እንዳለበት ይታመናል። ሳኡዲ አረቢያ ከእስራኤል ጋር ወዳጅነታቸውን ይፋ እንዲያደርጉ እየሰራች የምትገኘው አሜሪካ ሳኡዲ አረቢያ እስራኤልን የሚያስቀይሙ ገለፃዎች እንድታስወግድ በመጠየቋ ሳኡዲም የአሜሪካን ትእዛዝ ገቢር አድርጋለች።

👉 t.me/Seidsocial
እስራኤል ከአሜሪካ 25 ሀያ አምስት F-35 የጦር ጄቶችን ቀ 3 ቢሊዮን ዶላር ለመግዛት ጥያቄ አቅርባለች ።
የሚገርመው ግን የጦር በጀቷን የምትሸፍንላት ራሷ አሜሪካ ናት ። አሜሪካ በቅርቡ ብቻ ያፀደቀቺላት የጦር እርዳታ የእስራኤልን የሁለት አመት የጦር በጀት የሚዘጋ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ አሜሪካ በየአመቱ ለእስራኤል የ 4 ቢሊዮን ዶላር የጦር እርዳታ ታደርጋለች።

እናም እስራኤል በአሜሪካ ገንዘብ የአሜሪካ ጦርጄቶችን ትገዛለች ማለት ነው ።

ቀላል ሙድ ይይዙብናል እንዴ 🤔

t.me/Seidsocial
የአፄ ቴዎድሮስን ርእዮተአለም ተከትሎ የሚገኝ ድል አይኖርም !
አፄ ቴዎድሮ የስኬትም የድልም የለውጥም ተምሳሌት ሊሆን የሚችል መሪ በፍፁም አይደለም !

ሌላው ካልጠፋ እኔ አልኖርም አይነት ቴዌድሮሳዊ አካሔድ ውጤቱ እንደ ቴዎድሮስ የሽንፈትን ፅዋ ተጎንጭቶ ከንቱ ውጤት አልባ መስዋዕትነት መክፈል ነው ።

በኢትዮጵያ ውስጥ ምንም ነገር ሳያሳኩ ምንም ከይነት አሻራ ሳያሳርፉ ከሽፍትነት ውጥተው በሽፍትነት በመሰዋት ከቴዎድሮስ በፊት የሚጠቀስ መሪ የለም።
ሰርቆ ዘርፎ የዘረፈውን ንብረት ለወራሪዋ እንግሊዝ አስረክቦ ነው የተሰዋው ።
ገና ለገና ነጭ ስለሆኑ የጦር መሳሪያ ይሰራሉ ብሎ የጊዜዋን ልእለሀያል ሀገር የእንግሊዝን ድፕሎማቶች ማሰርና ማገት ማንም የማይዳፈረው ሞኝነት ነው። እንግሊዝ ለክብሯ ስትል ባዘመተቺው የህንድ ጦር ምንም መስዋዕትነት ሳይከፍሉ ነው ቴዎድሮስን የገደሉት ወይንም ራሱን የገደለው ።

ሲጀመር ቴዎድሮስ ወድቆ መቅደላ ተራራ ላይ መሽጎ ነበር ። ምክንያቱም በየሄደበት ሁሉ ባደረሰው ወደር አልባ ጭካኔና ዝርፊያ ሁሉም እያሳደደው ስለነበር።

እንግሊዝ ትልቅ የኢትዮጵያ ሰራዊት እገጥማለሁ ብላ 30,000 አብዛኛው ከህንድ የተውጣጣ ጦር ብታዘምትም መቅደላ ስትደርስ ያገኘቺው የቴዎድሮስ ጦር ግን 3,000 አካባቢ ብቻ የተዳከመ ሰራዊት ነበር ። እናም የአንድ ቀን ኦፕሬሽን አድርጋ መስዋዕትነት ሳትከፍል ታጋቾቿን አስለቅቃ ነው የተመለሰቺው። ልትዋጋበት ይዛው የመጣቺውን መሳሪያም ከፊሉን ለአፄ ዮሐንስ ሰጥታው ነው የተመለሰቺው ።

እና ይሄን አይነቱን በትርክትና ተረት ካላቅሙ የተቆለለ መሪ ሌጋሲን እከተላለሁ ብሎ መንጀፋጀፍ የርሱን ፍፃሜ ያመጣል።
የቴዎድሮስን አይነት ህልም ተሸክሞ የተሳካለት በአለም ላይ አንድም መሪ የለም።

t.me/Seidsocial
"ኢትዮጵያኒስቶቹ" እውነተኛ ህልምና መሻታቸው የኢትዮጵያ ልእልናና ሀያልነት ቢሆን ኖሮ የሚከተሉት ሌጋሲ የቴዎድሮስ ሳይሆን የልጅ ኢያሱን በሆነ ነበረ።

አፄ ቴዎድሮስ የህፃኑን የልጅ ኢያሱን 1/100ኛ እንኳ የሚሆን የኢትዮጵያ የታላቅነት ህልም አልነበራቸውም።
የልጅ ኢያሱን የታሪክ መዝገብ ያገላበጠ ሰው ያንን ያክል የአሁኑ መሪዎቻችን እንኳ ሊያስቡት ያልተቻላቸውን ህልም የሰነቀው ያ ህፃን ልጅ ነበር ? ብለው በግርምት መጠየቃቸው አይቀርም !!

ኢትዮጵያን እንደት ትልቅ ማድረግ ፤ ኢትዮጵያን እንደት የሁሉ ማድረግ ፤ ኢትዮጵያን እንደት የቀጠናው Hegemonic force ማድረግ ፤ ኢትዮጵያን እንደት የስልጣኔ የሰላም የሁሉም ዜጎቿ እናት ማድረግ እንዳለበት የገባው በታሪክ ብቸኛው የኢትዮጵያ መሪ ህፃኑ ልጅ ኢያሱ ብቻ ነው !
በዚያ ህፃንነት እድሜ በዚህ ልክ እንደት Mastermind መሆን እንደቻለ ሳስበው እደነቃለሁ!

ያው እንዳለመታደል ኢትዮጵያ ከሊሂቃን ፖለቲከኞች ይልቅ ደናቁርት ፖለቲከኞች የሚዘውሯት ተገር ነች ። እናም ደናቁርቶቹ ኢያሱን " ሰልመሀል " ብለው ከእንግሊዝና ፈረንሳይ እገዛ ጠይቀው ከስልጣኑ ገልብጠው ገደሉት። ያኔ የገደሉት የኢትዮጵያን ህልም ነበር ። እንግሊዝና ፈረንሳይ እንዲረዷቸው " ኢያሱ ከጀርመንና ከቱርክ ጎን ተሰልፎ ሊወጋችሁ ነው " በማለት ቀጥፈው ባለራእዩን ኢያሱን አስቀጠፏቸው።

t.me/Seidsocial
ሳኡዲ አረቢያ ባለፉት ሶስት ወራት ብቻ ከ 400 በላይ ኢትዮጵያዊያንን ወደ ሀገሯ ሲገቡ መግደሏ ተገለፀ።
ሳኡዲ አረቢያ በኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ላይ የምታደርገው ግድያ በአሳሳቢ ሁኔታ ቀጥሏል በማለት Human rights watch ዛሬ አለምኘቀፉ ማህበረሰብ ሳኡዲን ተጠያቂ እንዲያደርግ ተማፅኗል።

Middle east eye በርካታ አለምአቀፍ ተቋማትንና ከቦታው መረጃ ወስዶ ዛሬ ይፋ ባደረገው ዘገባው የሳኡዲ አረቢያ ወታደሮች በኢትዮጵያ ስደተኛ ሴቶች ላይ የአስገድዶ መድፈር ጥቃት እየፈፀሙ መሆኑንም አሳውቋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባወጣው መግለጫ ደግሞ አንድት እድሜዋ ከ 13-14 የምትገመት ኢትዮጵያዊት ስደተኛ በሳኡዲ ወታደሮች በጋራ መደፈሯን ይፋ አድርጓል።

ለስደተኞች መብት የሚታገለው MMC ወይንም Mixed migration center ይፋ ባደረገው መረጃ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በጅምላ መገደል መደፈርና መሰቃየት እየደረሰባቸው ነው ብሏል።

ሳኡዲ አረቢያ የምታደርሰውን የሰብአዊ መብት ጥሰትም ለመጠየቅ ሀገራትና ተቋማት ፍላጎት አለማሳየታቸው ጉዳዩን እጅግ አሳዛኝ አድርጎታል ሲሉ HRW እና MMC ገልፀዋል ።
አምና በቪዲዮ የተለቀቀው የሳኡዲ አረቢያ የስደተኞች ጭፍጨፋ ብዙዎችን ማሳዘኑ አይዘነጋም ።

በዚህ ሁሉ ሰቅጣጭ ጉዞ ውስጥ ግን ኢትዮጵያዊያን እጅግ አደገኛውን ስደት አሁንም ቀጥለዋል ።

t.me/Seidsocial
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በርግጥ አብዛኞቻችሁ ከሚገደሉት ንፁሀን ይልቅ የሳኡዲ አገዛዞች ስም መጥፋት እንደሚያሳስባችሁ አውቃለሁ ።
ቢሆንም ብትወዱም ብጠሉም እውነትን ማድረሴን አልተውም !
ይህ የኢትዮጵያዊያን ስደተኞች የሬሳ ክምር ነው !
ይህንን እንኳንስ በሀገሬ ልጆችና በማንም ላይ ተፈፅሞ ባየው እንኳ እጅጉን አዝናለሁኝ !

እናንተ ግን ይብላኝላችሁ ትንሽ እንኳ ነግበኔ አትሉም ???
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሂዝቡላህ በትላንትናው እለት የእስራኤልን የአየር መከላከያ የሆነውን Irone Domeን ማውደሙ በአለምአቀፍ ደረጃ ትልቅ መነጋገሪያ ሆኗል። ሂዝቡላህ የእስራኤል የአየር መከላከያ Irone dome ያወደመበትን ቪዲዮ ጭምር በመልቀቁ እስራኤል ተደናግጣለች ።

እስራኤል ዛሬ በሰጠቺው መግለጫ ስለጉዳዩ ዝርዝር መረጃ አልሰጥም ከአየር መከላከያው ጋር የነበረ ወታደርም ተገድሎብናል ለእኛ ትልቅ ኪሳራ ነው ሲል የእስራኤል ጦር ቃልአቀባይ ኮሎኔል ፒተር ለርነር ተናግሯል።

ሂዝቡላህ የእስራኤልን አየር መከላከያዎች እንደት ማለፍ ሲቻልም እንደት ማውደም እንደሚቻል ተደጋጋሚ ሙከራዎችን እያደረገ የከረመ ሲሆን አሁን ላይ እየተሳካለት ይመስላል።
በመሆኑም እስራኤል ከየትኛውም የአየር ጥቃት ትከላከልበት ዘንዳ ከአሜሪካ የተሰጣትን የ Irone dome ቴክኖሎጂ ሂዝቡሏህ በስኬት ማውደም ችሏል። ሂዝቡላህ ከዚህ በተጨማሪ የእስራኤል የስለላ ፋሲሊቲውችን እያወደመ ይገኛል ።

👉 t.me/Seidsocial
ቭላዲሚር ፑቲን ምእራባውያንን ማጥቃት ለሚፈልጉ ሀይሎች አህጉር አቋራጭ ሚሳኤሎቻችንን እናስታጥቃቸዋለን አሉ ።

ፕሬዚዳንት ፑቲን ዛሬ በሰጡት መግለጫ ምእራባውያን ድንበራቸውን እያለፉ ነው በመሆኑም የአውሮፓ እና የአሜሪካ ከተሞችን መምታት የሚችል ረጅም ርቀት ተምዘግዛጊ ሚሳኤሎቻችንን ለምእራባዊያን ጠላቶች እናስታጥቃቸዋለን ብለዋል ።

ምእራባውያን ዩክሬይንን ማስታጠቃቸውን ከቀጠሉ እኛ የነርሱን ጠላቶች የማናስታጥቅበት ምን ምክንያት አለን ? ሲሉም ተደምጠዋል።

ይህ የፑቲን መግለጫ ድንጋጤ የፈጠረባት አሜሪካም ለዩክሬይን ሩሲያን ዘልቃ በአሜሪካ መሳሪያዎች እንዳታጠቃ ትእዛዝ አስተላልፋለች ።
በሁለቱ ሀያላን ጎራዎች መካከል ያለው ፍጥጫ ተፋፍሞ ቀጥሏል።

👉 t.me/Seidsocial
ይህ የአስክሬን ክምር እስራኤል የጨፈጨፈቻቼው የጋዛዊያን አስክሬን አይደለም !
ይህ የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሀይል በራሱ ዜጎች ላይ ያደረሰው እጅግ ሰቅጣጭ ጭፍጨፋ ነው።
የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሀይል በአንድ ቀን ብቻ 140 ሱዳናዊያንን በመግደል ጠበሳ ታሪክ ፅፏል።
ሱዳኖች እጅግ አሳዛኝ ሁኔታ ውስጥ ናቸው።

የሙስሊም ሀገራት ጦር በተለይም የአረብ ሀገራት ጦር ጀግንነቱ እንደዚህ ምንም ያልታጠቁ ዜጎቻቼውን ለመግደል ነው። እንጅ በጠላት ላይማ እንኳንስ የጥይት የቃል ጥቃት እንኳ ለመፈፀም ብርክ ይይዛቸዋል።

አላህ በግፍ የተገደሉትን በጀነት ይካሳቸው። ገዲዮቹንም የእጃቸውን ይስጣቸው!

👉👉 t.me/Seidsocial
ይህ የምታዩት ልኡክ የሳኡዲ አረቢያው የኡለሞች ሊግ ፕሬዚዳንት ሸይኽ ሙሀመድ ቢን አብዱልከሪም አልኢሳ በጀርመን ጭፍጨፋ የተፈፀመባቸውን የአይሁዶች መታሰቢያን የሳኡዲ ኡለሞችን እየመራ የጎበኘበት ክስተት ነው ።
ሸይኽ ሙሀመድ አልኢሳ ሳኡዲ አረቢያ ለአይሁዶች ያላትን አጋርነት ለማሳየት ነው ልኡካኑን እየመራ አይሁዶች የተጨፈጨፉበትን ቦታ የጎበኘው ። ሸይኹ ቀድሞ የሳኡዲ የፍትህ ሚኒስትር ሲሆን አሁን ላይ የሳኡዲ የአለም ሙስሊሞች ሊግ ፕሬዚዳንት ተደርጎ ኡለሞችን እንዲመራ ተመርጧል ። ያው በሳኡዲ ላይ በጣም ከሚደመጡ የነገስታት አሊምች አንዱ ነው።

ሳኡዲ አረቢያ በአሁኑ ሰአት አይሁድነትንና እስራኤልን የሚያጥላሉ አስተምህሮዎችን ኡለሞቿ እንዳያስተምሩ አድርጋለች። እንኳን ኡለሞቿ ማንኛውም ሳኡዲያዊ ታዋቂ ግለሰብ በአሁኑ ሰአት እስራኤልን የሚያወግዝ ስለፍልስጤም ድምፅ የሚያስተጋባ ነገር ማስተላለፍ አይፈቀድለትም ። በግብፅም ያለው ሁኔታ ተመሳሳይ ነው ።

ሳኡዲ አረቢያ ከትምህርት ካሪኩለሟ ላይ እስራኤልን የሚያጥላሉ ፅሁፎችን ከትምህርት ገበታዋ ማውጣቷ ይታወቃል። የፍልስጤምንም ካርታ ከአለም ካርታዋ ላይ ፍቃ ግልፅ ማንነቷን አሰያሳየች ነው።

ይህንን አስመልክቶ የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ፖሊሲዎች ሀላፊ ኒምሮድ ጎሬን ለ THE TIMES OF ISRAEL በሰጡት መግለጫ የሳኡዱ አረቢያ ጅምር ጥሩ ቢሆንም በጣም አነስተኛ ነው ገና ብዙ መስራት ይጠበቅባታል ብለዋል።
ዋና ላፊው " ይህ ሳኡዲ እስራኤል የተሳለችበትን ስእል ለመቀየር ያደረገቺው ገና ትንሽ እርምጃ ነው ከዚህም በላይ ብዙ መስራት ይጠበቅባታል እስራኤልን ማክበር እና ለእስራኤልም ክፍት መሆን ላይ ገና ብዙ ነገር ማድረግ ይጠበቅባታል " በማለት የእስራኤሉ የውጭጉዳይ ፖሊሲዎች ሀላፊ ኒምሮድ ጎሬን አሳስበዋል።

ዋና ሀላፊው አክለውም " ሳኡዲ አረቢያ የእስራኤል የልብ ወዳጅ መሆን ከፈለገች ዩናይትድ አረብ ኤሚሬትስ የተከተለችውን መንገድ መከተል አለባት ልክ እንደ ኢማራት ስለ ሀይማኖት መቻቻል አይሁድም እስላምም የአብረሀም ሀይማኖቶች መሆናቸውን ኡለሞቿ እንዲያስተምሩ በማድረግ የተሻለ መቀራረብ እንዲፈጠር ማድረግ አለባት " በማለት ጎሬን ተናግረዋል። የሳኡዲ እና የእስራኤል የወዳጅነት ጅምርም ዛሬ የተጀመረ አለመሆኑን በመጠቆም ከበርካታ አስርት አመታት በፊት የተጀመረ ቀስበቀስ እያዘገመ የመጣ ወዳጅነት ነው ብለዋል።

በተለይም ሳኡዲ አረቢያ አይሁዶችን የሚያጥላላውን የቁርአን አስተምህሮ እንድታጤነው የእስራኤል ሀላፊ አሳስበዋል ።
ሳኡዲ በትምህርት ካሪኩለሟ ላይ ከቁርአን ላይ የተጠቀሰውን " አይሁዶችን በወንጀላቸው ወደ ዝንጀሮና ከርከሮ ቀየርናቸው " የሚለውን አስወግዳለች።
የእስራኤሉ የውጭጉዳዮች ሀላፊ ኒምሮድ ጎሬን ሳኡዲ የፍልስጤም ካርታን ከአለም ካርታ ላይ ማንሳቷን በማሞገስ ግና ፍልስጤምን ካነሳች በሗላ የእስራኤልን ካርታ በቦታው ላይ ማስገባት ነበረባትም ብለዋል።

ይህ እየሆነ ያለው እውነታ ነው። ብዙዎች ይህ ውሸት ወይንም ጥላቻ ይመስላቸዋል ። ላ !!! ወላሂ ውሸት አይደለም። ማንም እውነት ፈላጊ ማረጋገጥ ይችላል!!
እኔ ሳኡዲ በሙስሊሙ አለም ላይ ይህን ሁሉ ሸፍጥ ባትሰራ ኖሮ ለምን አገዛዟን አጥላላለሁ ! በግሌ ያደረሰችብኝ በደል የለ !!

ለማንኛውም ሙስሊሙ ማን ጠላቱ ማን ወዳጁ እንደሆነ ያውቅ ዘንድ የበኩሌን ማሳወቄን እቀጥላለሁ።
ሸኹ የአይሁዶችን መታሰቢያ የሚጎበኝበትን ምስል ግሩፑ ላይ አስቀምጥላችሗለሁ !

t.me/Seidsocial
ሶማሊያ የፀጥታው ጥበቃ ምክርቤት አባል በመሆን በታሪክ ትልቁን የፖለቲካ ድል ተቀዳጀች።

ምስራቅ አፍሪካዊቷና በእርስበርስ ጦርነትና ረሀብ የምትታወቀው ሀገር ሶማሊያ የአለም ፖለቲካ በሚዘውረው የፀጥታው ጥበቃ ምክርቤት አባል ሆናለች። በዚህም መሰረት ከ 15ቱ የአለም የፖለቲካ ውሳኔ ሰጭ ሀገራት አንዷ ለመሆን ችላለች። ይህ ሶማሊያ በአለምአቀፍ ፖለቲካ ያላትን ድርሻ የሚያጎላው ሲሆን ፖለቲካዊ ጥቅሞቿን በአለምቀፍ መድረክ እንድታስጠብቅ እድሉን ያጎናፅፋታል።

የፀጥታው ጥበቃ ምክርቤት 15 አባል ሀገራት ያቀፈና የተመድ ከፍተኛው የውሳና ሰጭ አካል ሲሆን ከ 15ቱ አምስቱ ሀገራት ማለትም አሜሪካ ሩሲያ ቻይና እንግሊዝ እና ፈረንሳይ ቋሚና ድምፅን በድምፅ የመሻር መብት ያላቸው ሀገሮች ናቸው። አስሩ ደግሞ ተለዋጭ አባል ሀገራት ናቸው።

ከኢትዮጵያ ጋር ከፍተኛ ፖለቲካዊ ውዝግብ የገባቺው ሶማሊያ የኢትዮጵያ ጦር ከሀገሯ ሙሉ ለሙሉ ለቆ እንዲወጣ ቀነገደብ አስቀምጣለች።

👉 t.me/Seidsocial
እስራኤል በዛሬው እለት በጋዛ በስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ላይ በፈፀመቺው ጭፍጨፋ 210 ለፍልስጤማውያን በአንድ ጀንበር ተገድለው ውለዋል።

እስራኤል በማእከላዊ ጋዛ በኑሰይራት የስደተኞች መጠለያ ላይ ከሰማይ ከምድር ባወረደቺው የቦንብ ውርጅብኝ ከመጠጠለያው ካሉ ተፈናቃዮች ውስጥ 210 የሚሆኑትን ጨፍጭፋለች። አለምም ይህንን ጭፍጨፋ በዝምታ ማለፍን መርጧል።

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታኒያሁ ጭፍጨፋውን " ታሪክ ሁሌም ሲያስታውሰው የሚኖረው የእስራኤል ገድል " ሲል አሞካሽቶታል።

ዛሬ እስራኤል ይህን ሁሉ ጭፍጨፋ የፈፀመቺው ከአሜሪካ ጋር በቀጥታ በመተባበር ነበር። አሜሪካ እና እስራኤል ምርኮኞቹን ለማስለቀቅ በመሩት ዘመቻ ነው የኑይሰራትን መጠለያ ያወደሙት።

በዛሬው እለት አሜሪካና እስራኤል ባደረጉት ዘመቻም አራት ምርኮኞችን ማስለቀቅ የቻሉ ሲሆን ሌሎች የእስራኤል ምርኮኞች ግን ከእስራኤል በተተኮሰ መሳሪያ ተገድለዋል።

ሀማስ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አሜሪካ በጦርነቱ ቀጥታ መግባቷን በማውገዝ ዛሬ አራት ምርኮኞችን ማስለቀቅ ቢችሉም ገና በመቶዎች የሚቆጠሩ ምርኮኞች በእጃችን ናቸው ብሏል። እንደዚህ አይነት ዘመቻ የሚቀጥሉ ከሆነ ግን ምርኮኞቻቼውን በህይወት ማግኘት ይከብዳቸዋል ብሏል።
እስራኤል አንድም ምርኮኛዋን ያለማስለቀቅ ውርደቷን ለማካካስ ዛሬ ከአሜሪካ ጋር በመተባበር የፈፀመቺው የጦር ወንጀል እጅግ ዘግናኝ ነበር ።

t.me/Seidsocial
ከቀናት በፊት የግሪኩ ጠቅላይ ሚኒስትር ኪርያኮስ ሚትሶታኪስ ቱርክን ጎብኝተው ነበር።
ታዲያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚትሶታኪስ ከኤርዶጋን ጋር የጋራ መግለጫ እየሰጡ በነበረበት ወቅት ሀማስን ለመውቀስ እየዳዳቸው ነበርና ኤርዶጋን ንግግራቸውን ያዝ አድርጎ መናገር ጀመረ

" ሀማስ ለእኛ የነፃነት ታጋይ ነው ሀማስ ስለህዝቡ ህልውና ስለፍልስጤምም ህልውና ሁሉን ሰውቶ እየተፋለመ የሚገኝ የነፃነት ፈርቀዳጅ ነው ። ሀማስ ለእኛ የቱርክን ህልውና ለማትረፍ እንደተዋደቁት እንደነዚያ የቱርክ አርበኞች ነው። እናም ሀማስን በክፉ የሚያነሳብን ሰው እኛን ያስቀይመናል ! ሀማስን በሽብርተኝነት መፈረጅም አሳፋሪ ነው እናንተ ምእራባውያን እኛም ለነፃነታችን በምንታገል ወቅት አሸባሪ እንደምትሉን አንጠራጠርም ። እናም ሀማስን በክፉ እንዳያነሱ " በማለት ለግሪኩ መሪ ይናገራል ።

የግሪኩ ጠቅላይ ሚኒስትርም የኤርዶጋንን ንግግር ከሰማ በሗላ " መልካም ከፊታችሁ ሀማስን አናወግዝም ግና በዚህ ጉዳይ ላይ ባለመስማማት እንስማማ " በማለት ጉዳዩን ቋጭቷል።

በመግለጫው ወቅት ኤርዶጋን " ቱርክ 1,000 የሀማስ ቁስለኞችን በሀገሯ እያከመች ነው " በማለት መናገሩ ትልቅ መነጋገሪያ ሆኖ ነበር ።
በዛሬው እለትም የቱርክ የደህንነት መሪ ከሀማስ አመራሮች ጋር በኳታር ዶሀ በምስጢርእየመከሩ ይገኛሉ። የሚደርሱበትን ነገር ወደፊት የሚታይ ይሆናል።
ቱርክ በእስራኤል ላይ የንግድ ማእቀብም መጣሏ የሚታወቅ ነው ። በዚህም በእስራኤል ላይ ማእቀብ የጣለች ብቸኛዋ ሀገር ያደርጋታል። የቱርክ ማእቀብ የእስራኤልን ኢንዱስትሪ በከፍተኛ ሁኔታ እየፈተነው መሆኑም ተረጋግጧል። እስራኤል ቱርክ የጣለቺውን ማእቀብ እንዲታነሳ ብትወተውትም ቱርክ ግን እስራኤል ጭፍጨፋዋን እስከቀጠለች ድረስ ማእቀቡ እንደሚፀና ተናግራለች ።

ቱርክ ለፍልስጤም እያደረገች ያለቺው ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ድጋፍ ከፍተኛ ቢሆንም ግና የምትችለውንና ማድረግ የሚገባትን ያክል እያደረገች እንዳልሆነ በኩሌ አምናለሁ። ቱርክ ለፍልስጤም ከዚህ በላይ መስራት ይገባታል !

👉 t.me/Seidsocial
የእስራኤሉ የትላንት ዘመቻ ምርኮኞችን ማስመለስ አልነበረም በፍፁም !
ከዚያ ይልቅ የወደቀባትን የውርደት ማቅ በትንሹም ገፈፍ የማድረግ ህልም ነበረው። ይህንን ለማድረግ ነው አሜሪካ በቀጥታ የተሳተፈችበትን ኦፕሬሽን ትላንት የከፈተቺው። ኦፕሬሽኑንም " operation Arnon " በማለት ነበር የሰየመቺው።

የትላንቱ ዘመቻ በአሜሪካ የስለላ ተቋም CIA ይመራ ነበር ። እናም ምርኮኞቹ ያሉበትን ቦታ አሜሪካ ከጠቆመች በሗላ አሜሪካ ሰራሽ ጄቶች ከሰማይ የቦንብ ዝናብ ያዘንቡ ነበር። ከስር ያማም የተሰኘው የእስራኤል ልዩ ኮማንዶ ተልእኮውን ሊወጣ በእስራኤል አየር ወለድ እየታጀበ አካባቢውን አፈራረሱት።

በዚህ ኦፕሬሽን የሞተው ምርኮኛ ሞቶ ትንሽም ቢሆን ነፃ መውጣት እንዳለባቸው ኔታኒያሁ ቀጭን ትእዛዝ አስተላልፏል። ምክንያቱም አለምአቀፍ ማህበረሰብና የእስራኤል ህዝብም የእስራኤልን ጦር " የጋዛ ንፁሀንን ከመጨፍጨፍ የዘለለ ያሳካችሁት ነገር የት ነው ?" ሲባሉ መልስ ስለጠፋ !

እናም ትላንት እስራኤል በገዛ ምርኮኞቿ ላይ ጨከነች ። በርካታ ምርኮኞችን ገድላም አራት ምርኮኞችን ብቻ አስጣለች። ኔታኒያሁም የመንተፍረቱን " ታሪካዊ ድል " በማለት ተቦተረፈ።
ግና አለም የእስራኤልን ገድል ከማሞገስ ይልቅ የበለጠ ቁጣውን ገለፀ። አራት ምርኮኞችን ለመግደል እንደት 274 ንፁሀን ይሰዋሉ ? እንደትስ በሌሎች የራሷ ምርኮኛ ዜጎች ላይ ትጨክናለች ? የሚል ውግዘት።
ቢጠቅምም ባይጠቅምም ከክስተቱ በሗላ አውሮፓ ህብረት የእስራኤልን ድርጊት "ጭፍጨፋ" በማለት ሲያወግዝ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በበኩሉ እስራኤል "ለህፃናት አደገኛዋ ሀገር " በማለት በጥቁር መዝገብ ላይ ስሟን አስፍሯታል። ባይጠቅምም ለታሪክ መፋረጃ ይሆናል።

በሀማስ እጅ ከ 100 በላይ የወራሪዋ ምርኮኞች ይገኛሉ

👉 t.me/Seidsocial