Seid Social
11K subscribers
2.58K photos
463 videos
6 files
1.7K links
አለም አቀፋዊ መረጃዎች ምልከታዎችና ታሪካዊ ክስተቶች ይቀርቡበታል
Download Telegram
በአሁኑ ሰአት አሜሪካ በአፀፋዊ እርምጃ በሶሪያ የኢራን ይዞታዎች ላይ ድብደባ እየፈፀመች ትገኛለች !

ይህ እየሆነ ባለበት ቅፅበት ደግሞ ባግዳድ የሚገኘው የአሜሪካ ኢምባሲና ኢራቅ የሚገኙ የአሜሪካ ጦር ሰፈሮች በኢራን መራሽ ታጣቂዎች በሚሳኤል እየተደበደቡ ይገኛሉ ።

ሶሪያና ኢራቅን የአሜሪካና የኢራን ሚሳኤሎች እያጓሩበት ይገኛል ።

መካከለኛው ምስራቅ ወደየት እየሄደ ነው ?
አስፈሪው ጦርነት ይከሰት ይሆን ?
ሁሉንም ጊዜ ይነግረናል !
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አሜሪካና ኢራን በሌላ ሀገር በዚህ መልኩ ነው ሲታኮሱ ያደሩት ።
እስካሁን በቁጥር የተገለፀ ሞት ወይንም ጉዳት ባይኖርም አሜሪካ ከ 85 በላይ ኢላማዎችን በኢራቅ እና ሶሪያ መምታቷን አሳውቃለች ።
በኢራን የሚታገዙት ታጣቂዎችም አፀፋውን ሲመልሱ አድረዋል ።
አሜሪካ ግን አሁንም ከኢራን ጋር በቀጥታ የማያላትማትን መንገድ እየመረጠች ነው እየተዋጋች የሚገኘው ። ለዚህም ነው ድብደባዋን በሶሪያና ኢራቅ ብቻ የወሰነቺው ።
ሳኡዲ አረቢያና ኢማራት በየመኖች ጥቃት የመርከብ ጉዞዋ ለተቋረጠው እስራኤል ድንበራቸውን ክፍት በማድረግ ሊታደጓት ነው ።
እስራኤል በጋዛ ፍልስጤማዊያን ላይ የጀመረቺውን የዘርማጥፋት ጦርነት ተከትሎ ወደ እስራኤል ምንም አይነት መርከብ አናሳልፍም ባሉት የየመን ሁቲዎች ዘመቻ መርከቦች ቀይ ባህርን ማለፍ ማቆማቸው ይታወቃል ። ታዲያ ይህ የሁቲዎች ዘመቻ የእስራኤልን ኢኮኖሚ እያቃወሰ መሆኑ ይታወቃል ።

እስራኤልን ከዚህ ቀውስ ለመታደግም አሜሪካና እንግሊዝ በተደጋጋሚ የመንን ቢደበድቡም የመኖቹ ግን "እንኳንም እንደጋዛ ተደበደብን እንኳንም የወንድሞቻችንን ህመም እኛም ታመምነው " ብለው ከመደሰት ውጭ ከዘመቻቼው ሊያቋርጧቸው አልቻሉም ። እንደውም አባሷቸውና መርከቦችን እያሳደዱ ማደባየት ተያያዙት ።

ታድያ በዚህ ሁሉ አማራጭ አጥታ ስትዋልል ለነበረቺው እስራኤል አሁን ሳኡዲ አረቢያ እና ኢማራት ደርሰውላታል ። በዚህም መሰረት የእስራኤል ግዚፉ የመርከብ ድርጅት Trucknet enterprise ltd ሳኡዲ አረቢያና ኢማራት ላይ መስመሮቹን በመዘርጋት ከኢማራት ወደብ ተረክቦ የሳኡዲን ግዛት አልፎ ወደ እስራኤል ለማድረስ መስመሮቹን ዘርግቶ እየተንቀሳቀሰ ነው ። Trucknet የእስራኤልን ኢኮኖሚ የሚታደገው ከኢማራት አድርጎ ሳኡዲን በዋናጰመስመርነት ከተጠቀመ በሗላ በዮርዳኖስ ወይንም ጆርዳን ( ኡርዱን) አድርጎ እስራኤል ይገባል ።

ድሀዎቹና ኢማነኞቹ የመኖች ለፍልስጤምን ለመታደግ ይህን ሁሉ መስዋዕትነት ሲከፍሉ ሀብታሞቹ የአረብ ሀገራት ሳኡዲ አረቢያ ኢማራትና ዮርዳኖስ ደግሞ እስራኤልን ለመታደግ ይህን አድርገዋል ።

ታሪክ መቼም ይቅር የማይለው የአረቦች ኺያና !!!

👉 t.me/Seidsocial
👉 t.me/Seidsocial
ሀማስ ዳግም እያንሰራራ ከተሞችኔ እየተቆጣጠረ ነው ።
የጋዛዊያን ስቃይና መከራ ተባብሶ ቀጥሏል ። ዝብርቅርቅ ስሜቶች በጋዛ ሰማይ !

ሀማስ በሰሜን ጋዛ ዳግም እያንሰራራ ከተሞች ላይ አስተዳደሩን እየዘረጋ ሲሆን በሌሎች ቦታዎችም የእስራኤልን ጦር እያጠመደ ማሳደዱን ቀጥሏል ። ጦሩንም ዳግም እያደራጀ ነው ። እስራኤል የሀማስ የምድር ውስጥ ዋሻዎችን በውሀ የመሙላት ትግል ላይ ብትሆንም ሀማስን አላንበረከከቺውም ።
ይህ ግን በቀላል መስዋዕትነት የሚከናወን አይደለም ። ከላይ በሚዘንብ ከምድር በሚነድ የእሳት ነበልባል ውስጥ ተሹለክልኮ የሚፈፀም ጀብዱ እንጅ ። በትላልቅ መስዋእትነት የሚቀጥል ትግል እንጅ !

የተኩስ አቁም ስምምነት ንግግሩ እንደቀጠለ ቢሆንም ሀማስ የማይቀበላቸው መስፈርቶች በመካተታቸውና እስራኤልም ሀማስን በደንብ ካዳከመች በሗላ ለመደራደር በማሰቧ አስተላላቂው ጦርነት ቀጥሏል ። እነሆ አራት ወር ሞሉት ።

የጋዛዊያን ስቃይና መከራ ግን አይወራ አይነገር ። ረሀቡ እልቂቱ መፈናፈኛ ማጣቱ ስንቱ ተነግሮ ይዘለቃል ።
ብቻ ወይ መስዋዕትነት ወይ ድል ነውና ትግሉ ቀጥሏል !

ድልም ለፅኑዎች ናትና !!
ይህ የአቢሲኒያ ባንክ አንድ ቅርንጫፍ ማኔጀር የፈፀመው ድርጊት አንድም ከሃላፊነቱ ውጪ ሲሆን ሁለትም ለሙስሊሞች ያለውን ጥላቻ ይፋ ያደረገ ነው።
ኡስታዝን በስልክ አግኝቸ ባገኘሁት መረጃ መሰረት በዚሁ ቦታ በዚሁ ቀን ከደቂቃዎች በፊት የሌላ እምነት ሰባኪዎች ያውም ለረጅም ደቂቃ የመንገድ ላይ ስብከት ሲያደርጉ ማኔጀሩም ሆነ ጥበቃው አንዳችም ያሉት ወይም የወሰዱት እርምጃ ሳይኖር ኡስታዝ ሙሃመድ ሲጀምር ግን ለመከልከል ሙሉ ደቂቃ እንኳን አልፈጀባቸውም።

ይህ ድርጊታቸው ብቻውን የሰውየውን ጭፍን ጥላቻ ለማሳየት በቂ ነው። ሲቀጥል አቁም ከማለት አልፎ ስፒከሩን እዘጋለቡ ብሎ መገልገሉ ፈፅሞ መብቱን እና ሃላፊነቱን እንደማያውቅ የግል ፍላጎቱን በባንኩ ስም ለማስፈፀም መሞከሩን አጉልቶ ያሳያል።
የግል ፈላጎቱን የምንለው ባንኩ በሚመለከተው አካል በዚህ ግለሰብ ላይ እርምጃ ከወሰደ እና ለተሰራው ስህተት ህዝበ ሙስሊሙን ሆነ የምንወደውን ኡስታዛችን በግልፅ ይቅርታ ከጠየቀ ብቻ ነው።

ይህን ካላደረገ እና በዝምታ ለማለፍ ከሞከረ ግን የሰውየው ፍላጎት የባንኩም እንደሆነ በማመን ሌላ ማድረግ ባንችል ደንበኝነታችን ግን ለማቋረጥ እና ሌሎች ወንድም እና እህቶቻችን ተመሳሳይ እርምጃ በሁሉም ቅርጫፎች ላይ እንዲወስዱ ለማነሳሳት የሚከለክለን አንዳች ሃይል አይኖርም።
ባንኩ የህዝብ ነው ብለን እንደምናምነው መንገዱም የህዝብ ነው።ባንኩ ሁሉንም ሰው በእኩል አስተናግዳለሁ እንደሚለው በመንገዱም ላይ ሁሉም ህዝብ ሁሉም ሃምኖት እኩል መብትአለው።

ይህን አስነዋሪ ድርጊት የፈፀምክ ማኔጀር ከቻልክ እና ጎበዝ ከሆንክ አለቆችህንም ሳትጠብቅ ቀድመህ ይቅርታ ጠይቅ ።ወይም የቅርንጫፍህ ደንበኞችን ዝርዝር ጊዜ ሰጥተህ ቁጭበል እና ተመልከት ። ምን ያህል ደንበኛ በተሳሳተ ድረወጊትህ ምክንያት እንደምታጣ ከወዲሁ አጢን።
@dinu ali
አለቅጥ አታብዙት !
ድንበር አለፋችሁኮ ! በቃ ሚዛናዊነት የሚባል ነገር የለም እንዴ ? አንድ የቅርንጫፍ ማናጄር ስህተት ስለሰራ አቢሲኒያ ባንክ ላይ አጠቃላይ ዘመቻ መክፈት አላማችሁን ሌላ አስመሰለባችሁኮ !
አቢሲኒያ ባንክ በባንኩ የውስጥ ደንብ መሰረት የእርምት እርምጃ ይወስድ ይሆናል ያም በአንድ ቀን የሚደረግ አይደለም ። ሰውየው ጥፋተኛ ከሆነ ተቋማዊ አሰራሩን ጠብቆ የማስተካከያ እርምጃ ይወስዳል ያንንም ለህዝብ ያሳውቃል ።

ከዚያ በዘለለ ግን አቢሲኒያ ባንክን ከሌሎች በተለየ የሙስሊም ጠላት አድርጎ በመሳል እንደዚህ አይነት ዘመቻ መክፈት የለየለት ሸፍጠኝነት ነው ።
እኔ እስከማውቀው አቢሲኒያ ባንክ የደንበኞቹን እሴት በማክበር ቀዳሚ ባንክ ነው ። በየቅርንጫፎቹ መስገጃና ማረፊያ አዘጋጅቶ ደንበኖቹ ቤታቸው እንዲመስላቸው በማድረግ ከቀዳሚዎቹ ባንክ ነው ።

በብሔር ካባ ተወሽቆ ሀይማኖታዊ ጀብደኝነት መጫወት አጉል ግብዝነትና ማስመሰልም ነው ። በበኩሌ የባንኩ ማናጄር ያደረገው ነገር ትክክል እንዳልሆነ አምናለሁ ። ትክክል ያልሆነውም በዋናነት ሌሎቹ ሲሰብኩ ዝም ብሎ ኡስታዙ ሲሰብክ ለማስቆም መሞከሩ ነው ። ከዚያ ውጭ ልክ ያለፈው የጎዳና ላይ ስብከት ለሁሉም ሀይማኖት ሰባኪዎች ቢከለከል በፅኑ እደግፋለሁ ።

ከዚያ ባለፈ ግን ከወራት በፊት ያሁሉ መስጅድ በኦሮሞ ብልፅግና ሲፈራርስና ያሁሉ ሰው ቤቱ በግፍ ፈርሶበት ሲያለቅስ ፀጥ ብሎ የነበረው ሁሉ ያሸንፈከውን በል በል ቢሉት እንዲሉ ጊዜ ያግዘኛል ብሎ አጉል አርበኝነት መጫወት ለማንም አይጠቅምም ።

አቢሲኒያ ባንክ ይህችን ክፍተት አስተካክሎ ከደንበኞቹ የቀረበበትን ቅሬታ እንደሚመልስ ተስፋ አደርጋለሁ ። ለደንበኞቹ ትልቅ ክብር ያለው ባንክ እንደሆነ ስለማምን !

👉 t.me/Seidsocial
👉 t.me/Seidsocial
መረን የለቀቀው የጎዳና ላይ ስብከት ሊቆም ይገባል !

መቼስ ይህቺ ሀገር ሁሉ ነገር መረን የለቀቀባት ሆናለች ። የሀይማኖት ሰባኪያን ገሪ አጥተው በመነገድም በአደባባይም በስራ ቦታም አላስቀምጥ አላላውስ ካሉ አስርት አመታት ተቆጠሩ ። ከጩኸት ውጭ ጠብ የሚል ልብን የሚያረጥብ ነገር ለማውጣት አንደበታቼው ያልታደለው ጯሂዎች ህዝባችንን አስመርረውታል ። በጪከትና እርበሻ የድምፅ ብክለት እንጅ የነፍስ ቀለብ አይገኝምና እነዚህ ጯሂዎች በቃችሁ ሊባሉ ይገባል ።

እንደ ሰውኮ ነፃነቱን ተገፈፈ ። መኪና እንኳ በሰላም መሰለፍ ተቸገረ ። አሁንማ በመኪና ስፒከር ላይ ደቅነው ከተማውን ሁሉ በሚያናጋ ድምፅ እየናጡት ነው ። አለቅጥ መረን ተለቀቀና ወደሌላ አቅጣጫ ሳይሄድ እንዲቆም ቢደረግ መልካም ነው ።

ሰው ሀይማኖቱን ማስተማር ከፈለገ በየሀይማኖት ተቋሙና በየሚዲያዎቹ ያስተምር እንጅ ሴኩላር የሆነና ብዝሀ ሀይማኖት ባለበት ህዝብ መካከል እየመጡ ይሄንን ካልተቀበልክ ከስረሀል ጠፍተሀል እያሉ መጮህ ሌላ የብጥብጥ ስጋትን ይደቅናል ።

አሁንማ ሆስፒታል አልቀረ የትምህርት ማእከላት አልቀሩ በቃ የሰበካ ወይንም የጩኸት ዘመቻ ተከፍቶ ህዝባችን እየተሳቀቀ ነው ።

መንግስት ይህንን መረን የለቀቀ ሰበካ ማስቆም አለበት ። እየተደረጉ ያሉ ትንኩሳዊ ስብከቶች በሗላ ከቁጥጥር የወጣ ቀውስን እንዳያመጡ እሰጋለሁ ።

#Seid_Mohammed_Alhabeshiy

👉 t.me/Seidsocial
👉 t.me/Seidsocial
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
አሏሁ አክበር !!!!
አሏሁ አክበር !!!
አሏሁ አክበር !!!!

የዛሬው ደግሞ እጅግ እጅግ እጅግ ይለያል !!!
ዛሬ እስራኤል ከጋዛ ምድር 540 ቁስለኞቿንና 15 አስክሬኗን ሰብስባ ሂዳለች !!! 540 ቁስለኛኮ ነው ያልኩህ ያ አኺ !!!
ከነዚህ ውስጥ 27ቱ ሞት አፋፍ ላይ ናቸው ስልህ ያረጁል !!
ደግሞ መረጃህ ምንድነው አልከኝ አይደል እንግድያውስ መረጃየ የእስራኤሉ መገናኛ ብዙሀን Israel TV 12 ነው ። እንደው ሌሎቹ ሚዲያዎች የዘገቡትንማ ተወው !

በቀን 540 ወታደር በድንገት በተፈፀመ የተቀናጄ ጥቃት ቆሰሉብን ብሏል የእስራኤሉ የዘና አውታር ። ይህን ያክል ወታደር ማቁሰል የቻሉትኮ ባዶ እግራቸውን እየተዋጉ ያሉት ሙጃሂዶቹ ናቸው ።

በነዚህ የሙጃሂዶች ተአምራዊ ጀብዱ ዝምብለህ ተደነቅማ !!!
እዚህ ፔጄ ውስጥ ገብታችሁ አስፀያፊ አስፀያፊ ስድብ የምትሳደቡ ወንድሞችና እህቶች እኔ የማቀርባቼው ሀሳቦችና መረጃዎች ይህን ያክል የሚያበሳጫችሁ ከሆነኮ ፔጁን ለቆ መውጣት ይቻላል ። ስድብን ምን አመጣው ? የወንድምን ክብር መንካት ምን አመጣው ? ኧረ ከሁሉም በላይ ማክፈርን ምን አመጣው ? አይደረግም !
ነብያችን ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም እንደነገሩን ሙስሊም ተሳዳቢም አነዋሪም አይደለም ! እነዚዚህ ባህሪዎች ከሙስሊም ጋር በጭራሽ አብረው አይሄዱም ። ሙስሊም የማይወደውን ሀሳብ እንኳ ሲያይ በአክብሮት ይሞግታል እንጅ አይሳደብም ! ስድብ ነውር ነው ወንጀልም ነው ። አንድን ሰው ብትሰድቡትኮ አውፍ እስካላላችሁ ድረስ አላህ ፊት ከመጠየቅ አታመልጡም !
ኢማሙ ሻፊኢይ ረህመቱሏሂ አለይህ ሁሌም ክርክርና ውይይት ሲኖርባቸው " አላህ ሆይ ሀቁን ከተከራካሪዎቼ አንደበት አድርገው " ይሉ ነበር ። ምክንያቱም ሀቁ ከኔ ከሆነ ተከራካሪዎቼ ላይቀበሉት ይችላሉ ብለው በመፍራት ነው ። የሙእሚን ባህሪ ይህ ነው ።

እኔ አንድ ወንድማችሁ ነኝ እሳሳታለሁ አንዳንዴም ትክክል ልፅፍ እችላለሁ ግና ስህተት በመሰላችሁ ወቅት ሁሉ ልብ የሚያጠልሽ ስድብ መስደብ የሙስሊም አደብ አይደለም ።

ወላሂ ከምትሳደቡ ብሎክ እያደረጋችሁኝ ውጡ ምንም ጣጣ የለብኝም ። ፎሎወር የሚያሴጨንቀኝ ሰው አይደለሁም ።
መረጃ አይናቅምና ቢጠቅማችሁ ብየ እንጅ የማጋራችሁ አልሃምዱሊላህ የማንንም ተልእኮ ተቀብየ የምንቀሳቀስ አይደለሁም ።
አቢሲኒያ ባንክ ይቅርታ በመጠየቅ ዳግም ታላቅነቱን አሳይቷል ። ይቅርታ ብቻ ሳይሆን ይህንን ጥፋት ባጠፋው ሰራተኛው ላይም ጥብቅ እርምጃ ወስዷል ።
ይህንን እንደሚያደርግ እርግጠኛ ነበርኩ ።
የዚህ ባንክ መርህ " እሴትዎን ያከበረ " ነው ። አቢሲኒያ ይህንን በመርህ ብቻ ሳይሆን በተግባርም በመፈፀም የሚታወቅ ነው ።
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
መንግስት ስርአት ያስከብር

መረን የለቀቀው የጎዳና ላይ ስብከት በጊዜ ካልተገታ የሚደርስብንን የማንወጣው የእርስበርስ ግጭትን በቅርብ ታዩታላችሁ !
የሀይማኖት ጦርነት መቼም መብረጃ የሌለው ነውና ሳይረፍድ መፍትሔ ይበጅለት !
የጎዳና ላይ የጩከት ስብከቶች ይታገዱልን
ዛሬ በቱርክ የተፈጠረው ነገር ምንድነው ?

ቱርክ ዛሬ የሽብር ጥቃት አስተናግዳለች ። በዚህም ሁለት ቱርካዊያን ተገድለዋል ። ጥቃቱ የተፈፀመውም በኢስታንቡል በሚገኝ አንድ ፍርድቤት ፊትለፊት ሲሆን ከሞቱት ሁለት ቱርካዊያን በተጨማሪ ስድስት ሌሎችም ተጎድተዋል ።

የሽብር ጥቃቱን የፈፀሙትን ሁለት አካላት ፖሊስ ወዲያው የገደላቸው ሲሆን ከዚህ ድርጊት ጋር ግንኙነት አላቸው ያላቸውን ሁሉ የቱርክ ደህንነት ምርመራ ጀምሯል ።

ጥቃቱን የፈፀመው DHKP-C የተባለ የሽብር ቡድን ነው ። ይህ ቡድን የማርኪሲዝም-ሌኒኒዝምን ሶሻሊዝም ርእዮተ አለም በቱርክ ለማስረፅ የሚታገል ቡድን ሲሆን ይህንን አይዶሎጂውን ለማስፋፋትም የሽብር ጥቃትን እንደዋነኛ መሳሪያ ይጠቀማል ።
ይህ ድርጅት በቱርክ ከተመሰረተ 50 አመታት ያለፉት ሲሆን በዚህ ታሪኩም የቱርኩን የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ኒሀት ኢሪምን ጨምሮ በርካታ የቱርክ ባለስልጣናትን እና የደህንነት ሀላፊዎችን ሲገድል ኖሯል ። በተለይም ምእራባውያንን አምርሮ የሚጠላውና የቱርክን የኔቶ አባልነት አጥብቆ የሚኮንነው ይህ ሶሻሊስታዊ ድርጅት በአሜሪካ ሰዎች ላይም ተደጋጋሚ ግድያ በመፈፀም ይታወቃል ። ይህ ድርጅት ከ PKK ጋርም አብሮ በመስራት ይታወቃል ።

ባለስልጣናትን አሳዶ መግደል ወይንም Assassination የተጀመረው በኢስማኢሊያ ሺአዎች ሲሆን እነዚህ ሺአዎች የአባሲድ ኸሊፋንና የሰልጁቅ ሱልጧኔት ባሀስልጣናትን እዚያ ተደብቀው በመግደል እንደዚህ አይነቱን የግድያ ስልት ለአለም አስተዋውቀዋል ። በዋናነት በዚህ አይነት የግድያ ስልት ስሙ ቀድሞ የሚጠራው የባጢኒያው መሪ የነበረው ሀሰን ሳባህ ነው። ሀሰን ሳባህ ታላቁን የኢስላም ፖለቲካዊ መሪ ኒዟም አልሙሉክን በማስገደል የታሪክ ጥቁር ጠባሳ ጥሎ ያለፈ ሰው መሆኑ ይታወቃል።

t.me/Seidsocial
ሁለት ዜናዎች የየመን ሁቲዎችን በተለመለከተ

1 የመኖች በዛሬው እለት ሁለት የአሜሪካና የእንግሊዝ መርከቦችን በሚሳኤልና ድሮኖች ቅንጅት ደብድበዋል ። አሜሪካና እንግሊዝ በየመን ላይ የአየር ድብደባቸውን አጠናክረው ቢቀጥሉም ሁቲዎችን ግን ማስቆም አልቻሉም ። የመኖችም እኛ ጥቃታችንን የምናቆመው የፍልስጤም ወንድሞቻችን ጥቃት ሲቆም ብቻ ነው በማለት ትግላቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል ። በዛሬው እለትም ሁለት የእንግሊዝ እና የአሜሪካ መርከቦችን በሚሳኤሎቻቼው ደብድበዋል ።

2 የየመን ሁቲዎች አሜሪካና እንግሊዝ በየመን ላይ የሚያደርጉትን ድብደባ ካላቆሙ የአለም የመገናኛ ኢንተርኔት መስመርን እንደሚቆርጡት አስጠንቅቀዋል ። ይህ ምስራቁን ከምእራቡ አለም የሚያገናኘው የኢንተርኔት መስመር የተዘረጋው በቀይባህር እና ህንድ ውቅያኖስ ስር ሲሆን መስመሩም ሁቲዎች እንደፈለጉ የሚንቀሳቀሱበት መስመር ነው ። እናም ሁቲዎች ይህንን መስመር ከቆረጡት የአለም የኢንተኔት ግንኙነት ሊቋረጥ ይችላል ።
ከ 90% በላይ የሚሆነው የበይነመረብ መስመሮች የተዘረጉት በባህር ውስጥ መሆኑ ይታወቃል ።

#Seid_Mohammed_Alhabeshiy

ቴሌግራም
👉 t.me/Seidsocial
ለአለም መርገምትን አውርሰው ያለፉት የባጢኒያ ሺአዎች !! Assassination and Mafia መነሻቸው !
የሀሰን ሳባህ በደም የተጨማለቁ እጆች ሲታወሱ !

ጊዜው በአባሲድ ኸሊፋና በሰልጁቅ ሱልጧኔትነት ጊዜ ነው ። በአባሲድ ኸሊፋ ስር ሱልጁቅ ሱልጧኔት አለመል ኢስላምን ሲመራ በነበረበት ወቅት ። ታላቁ አሊም አንነይሳቡሪይ ሶስት ሰዎችን ጠሩና ለታላቅ ኢስላማዊ ሀላፊነት አጯቸውና ቃል አጋቧቸው እነርሱም ኒዟመል ሙሉክ ፣ ሀሰን ሳባህና ታላቁ ሊቅ ኡመር ኻያም ነበሩ ።

ግና ሀሰን ሳባህ በኒዟመልሙሉክ ይቀና ነበርና እርሱን ለመግደል መንቀሳቀስ ጀመረ ። በይፋ ሙስሊም መስሎ በድብቅ ደግሞ ባጢኒያ ሆኖ የሰልጁቅና የአባሲድ ባለስልጣናትን ማሳደድ አሳዶ መግደልም ተያያዘው ። ባጢኒያነት ስውርነት ነው ። ባጢኒያዎች ቁርአን ሁለት ትርጉም አለው ብለው ያምናሉ አንዱ የዟሂር ትርጉም ሲሆን ይህም ቁርአን ከላይ በቀጥታ ያለው ትርጉም ነው ። ሌላኛው ትርጉሙ ደግሞ የባጢን ትርጉም ነው ። ይህ ለባጢኒ ኡለሞች እንጅ ለማንም ያልተገለጠ ማንም ምንም ቢደክም የማያገኘው ከፈጣሪ በቀጥታ በሚደረግ ግንኙነት የሚገኝ ብቻ ። ልክ እንደ አሁኑ የፕሮቴስታንት ሀሰተኛ ነብያት በሏቸው ።

እናም በባጢኒ ሀራሞች ሁሉ ሀራም ሀላሎች ሁሉም ሀላል አይደሉም ። አንድ መጥፎ ነገር መጥፎ የሚባሉ ለተመልካቹ ሊሆን ይችላል በባጢን ግን የተፈቀደ ይሆናል ። ሌላው መገለጫቸው አንድ ሰው የባጢኒ ኢስማኢሊያን ለማስፋፋት ተልእኮውን ለመወጣት ምንም ማድረግ ምንም መሆን ይችላል ። ክርስቲያን መሆን ይችላል ፓጋን መሆን ይችላል ሱኒ መሆን ይችላል ግና ብቻ የተባለለትን አላማ ተመሳስሎ መግደል አለበት ኸላስ !

በኢስላም ታሪክ ከታዩ አስቀያሚ ግሩፖች ውስጥ ናቸው እነዚህ ባጢኒዮች ። እናም እነ ኒዟሙል ሙሉክን ጨምሮ በርካታ የኢስላም ስብእናዎችን መግደል ተሳካላቸው ኢስላሙ አለምን አዳከሙት ሰልጁቅ ኢምፓየርን ገዘገዙት ። ሱልጧን መሊክሻህ ሊያጠፋቼው ቢሞክርም ፍፁም ከማንም ጋር ተመሳስለው በመኖራቸው ጭራሽ አስቸጋሪ አደረገበት። መሊኽ ሻህ ሲሞት ልጁ አህመድ ሳንጃር ዋና መቀመጫቼውን አላሙትን አፈራርሶ ሀሰን ሳባህን ሊገድለው ሲል የሳንጃርን አገልጋይ ሴት አንገቷ ላይ ስለት በመደገን ከተንቀሳቀስክ አንገቷን እቆርጠዋለሁ በማለቱ እሷን መያዦ አድርጎ አምልጧል ።

#Assassins !

በሀሰን ሳባህ የሚመሩት ባጢኒዎች ለአለም ካበረከቱት ነገር አንዱ እራስን አጥፍቶ ማጥፋት ነው ። ለዚህም ባጢኒዎች መግደል የማፈልጉትን ባለስልጣን ገድለው ራሳቸውን ይገድላሉ ። አንዳዴም ምስጢር እንዳያወጡ ምላሳቸውን ተቆርጠው ወደ ተልእኮ ይዘምታሉ ። ከሀሰን ሳባህ ለዚህም ጀነት ቃል ይገባላቸዋል ። የውሸት የቅጥፈት ጀነት !!
ታድያ ሀሰን ሳባህ ይህን አይነት ጭካኔ እንድሂ እንዲወስኑ አያደርጋቸውም ። ከፍተኛ የሆነ ሀሽሽ ያስወስዳቸዋል ። በሀሽሽ ከደነዘዙ በሗላ የፈለገውን ነገር ያሰራቸዋል ። ፈንጆችም ባጢኒያዎችን Hashashin ሲሉ ጠሯቸው ። Hashashin ከሚለው ቃልም Assassin የሚለው የእንግሊዝኛ ቃል ተፈጠረና የእነርሱን ተግባር መፈፀም Assassination ተብሎ ተጠራ ። አይገርማችሁም ??!!
እናም ራስን ሰውቶ የፈለጉትን ዝነኛ ሰው አዋቂና ባለስልጣን መግደል ከነርሱ ተወሰደ ማለት ነው ።

#Mafia

ሌላው ባጢኒያ ሺአዎች የፈጠሩት ነገር ማፊያነትን ነው ። ታላቁ ሱልጧን ሰላሂድን አልአዩቢ ፋጢሚዶችን አሸንፎ ግብፅን ሲቆጣጠር የባጢኒ ሺአዎች ወደ ጣሊያኗ የሲሲሊ ከተማ ፈለሱና እዚያ በድብቅ የራሳቸውን የምስጢር እንቅስቃሴ ፈጠሩ ። ያም መግደልን መዝረፍን ማገትን እና ሌሎችም ዘግናኝና አስፈሪ እርምጃዎችን ይወስዱ ነበር ። እንቅስቃሴያቸውንም #መህፊያ ብለው ጠሩት ። በአረብኛ ምስጢር እንደማለት ነው ። እናም መህፊያ ከሚለው ቃል ማፊያ ተወለደ ማለት ነው ። ጣሊያንም ከዚያ ጀምሮ ማፊያዎች የተወለዱባት ሀገር ሆነች ። እናም በሱሰኝነት የማነዳው ማፊያ በዚህ መልኩ አለምን ተዋወቀ ።

ባጢኒዮች አብዛኛው ኢላማቸው ሙስሊሞች ነበሩ ። ለዚህም ከመስቀል ጦረኞች ጋር አብረው ይሰሩ ነበር ። የመስቀል ጦረኞች በባጢኒያዎች በጣም ይደነቁና ይገረሙ ነበር ። ብዙ የጭካኔ ተግባሮቻቼውንም ኮረጄው ወስደዋል ።
ባጢኒያ ወታደሮች ተአማኝነታቸውን ለሰይዳቸው ሀማሳየት የራሳቸውን አንገት ጭምር ይቀሉ ነበር ። ለሀሰን ሳባህ ታማኝነት መተኪያ የሌለው መስፈርት ነው ። ሀሰን ሳባህ ሁለት ልጆቹን ሳይቀር የገደለ ጉድ ያለው ሰው ነበረ ።

ባጢኒያዎችን ከፍተኛ ውድመት አድርሶ የበታተናቸው የሞንጎል ጦር ነበር ። በሁላጉ ኻን የሚመራው የሞንጎል ጦር ባጢኒዎችን ደምስሶና በታትኖ የተረፉት ጥቂቶች ወደ አዘርባጃን እና አናቶሊያ እንዲሰደዱ አድርጓቸው ነበር ።

የኢራኑን ሳፋቪድ ዳይናስቲን የመሰረተው ኢስማኢልም አስተምህሮቱን የወሰደው ከነዚህ ከሞት ከተረፉ ባጢኒዎች ነበር ። ባጢኒዎች ከኢስላም ያፈነገጡ ቡድኖች ነበሩ ።

#Seid_Mohammed_Alhabeshiy

ቴሌግራም
👉 t.me/Seidsocial
ሀማስ ዛሬ ምላሹን ሰጥቷል ።

በኳታር አሜሪካና ግብፅ አርቃቂነት በተዘጋጄው የተኩስ አቁም ሀሳብን ሀማስ ምላሹን ለአለም አሳውቋል ። በዚህም መሰረት ሀማስ የተኩስአቁም ረቂቅ ሀሳቡን በአዎንታዊ መልኩ እንደሚመለከተው ገልጿል ።
ሀማስ የተኩስ አቁም እንዲደረግ የአደራዳሪነት ሚና እየተጫወቱ ያሉትን ኳታርን ግብፅንና ሌሎችንም ሀገር ለሚያደርጉት ጥረት እውቅና ሰጥተን እናመሰግናለን ብሏል ።
" ህዝባችንን በእጅጉ እናደንቃለን ! ላሳዩት ታሪክ የማይፍቀው ፅናት ላደረጉት የማይሰበር ተጋድሎ ለፈፀሙት ወድቆ የመነሳት ጥንካሬ በእጅጉ እናመሰግናለን ! ህዝባችንን ይዘን ከሌሎች ሀይሎችም ጋር አብረን ወራሪውን ከመሬታችን ከህዝባችን እስክናፀዳና ነፃ እስክንወጣ ድረስ ትግላችን ይቀጥላል " ብሏል ሀማስ በመግለጫው ።

ኳታር የሀማስን መግለጫ ተከትሎ አዎንታዊ ምላሽ አግኝተናል ስትል ገልፃለች ። የአሜሪካው ውጭጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ተኩስ አቁሙን ለማስፈፀም መካከለኛው ምስራቅ ይገኛሉ ።