AYA Media || አያ ሚዲያ
1.85K subscribers
398 photos
35 videos
7 files
587 links
AYA Media || አያ ሚዲያ

ስለ ቻናላችን ያሎትን ሀሳብና አስተያየት በ @Haicrosoft ይላኩልን! እናመሰግናለን!

★ ኢስላማዊ መልዕክቶች
★ ማህበራዊ ጉዳዮች
★ ጠቃሚ መረጃዎች
የሚቀርቡበት ቻናል!

#አያ_ሚዲያ

https://m.youtube.com/user/haiderrkedirtv
Download Telegram
እንቅፋት አይሁንባችሁ!

ወላጆች ሆይ! ለልጆቻችሁ ያላችሁ ፍቅር፣ እዝነትና ርህራሄ ትለክክለኛውንና ቀጥተኛውን ጎዳና ለማመላከት እንቅፋት አይሁንባችሁ!

ልጆቻችሁ ዛሬ በመልካም ስታዟቸው ከመጥፎ ስትከለሏቸው ልጅነት ይዟቸውና በህይወታቸው ጣልቃ የገባችሁ መስሏቸው ጥላቻ ቢያሳይዋችሁ ቢከፉባችሁም!

ነገ እነርሱን ለማሳደግ ያያችሁትን ፍዳና መከራ፤ እነርሱን የተሻለ ሰው ለማድረግ የከፈላችሁትን ዋጋና ያደረጋችሁትን ጥረት በመረዳት ያመሰግኗችኋል!

ነገ ደግሞ ሩቅ አይደለም! … የሚመጣ ነገር ሁሉ ቅርብ ነው!

ለውድ ስጦታችሁ! ለመልካም ወላጅነታችሁ በዱኒያ ተንከባካቢያችሁ፤ ከህልፈት በኋላም በመልካም ዱዓቸው አስታዋሽ ይሆኗችኋል!

﴿ ... رَبَّنَا هَبْ لَنَا مِنْ أَزْوَاجِنَا وَذُرِّيَّاتِنَا قُرَّةَ أَعْيُنٍ وَاجْعَلْنَا لِلْمُتَّقِينَ إِمَامًا﴾
[ الفرقان: 74]

#የሂዳያ_ትውልድ #ለወላጆች  #ምክር_ለተርቢያ

📮 የመጪው ትውልድ ሃላፊነት የጋራችን ነው! መልዕክቱን ሼር በማድረግ ለብዙዎች እናድርስ!

💫 https://t.me/HidayaTerbiya 💫
የምስራች ከሂዳያ ተርቢያ

ሰላቴ ሕይወቴ መጽሐፉ  በድጋሚ ገበያ ላይ ዋለ!

ለልጆች በልጆች ቃና የተዘጋጀ! ድንቅ መጽሐፍ!

መጽሐፉ ከ5 ዓመት ጀምሮ ላሉ ልጆች የተዘጋጀ ሲሆን

ስለ ዉዱእ አደራረግ ስርዓትና ጥቅሞች
ሰላት ለምን እንደሚሰግዱ
የሰላት አሰጋገድ ስርዓትና ጥቅሞች
ሰላትን የሚያበላሹ ነገሮችን እና
ከሰላት በኋላ የሚባሉ አዝካሮችን
አካቶ ይዟል በተጨማሪም

ልጆችን አሳታፊ የሆኑ አዝናኝና አስተማሪ ጥያቄዎችን! እንዲሁም ሰላት ለመለማመድ የሚረዳቸው የሁለት ወራት የሰላት ወቅቶች መቆጣጠሪያ ያለው ነው!

ለልጆችዎ የሚያወርሱት ድንቅ የእስልምና ማዕዘን መማሪያ!

* ወላጆች ልጆቻችሁን ቤት ውስጥ ለማስተማር
* የተርቢያ ማዕከላትና መድረሳዎች በኮርስ መልኩ ለመስጠት ምቹ ሆኖ የተዘጋጀ! 

ጥራታቸውን ጠብቀው በከለር የታተሙ ኮፒዎችን ለልጅዎ በስጦታ ያበርክቱ!

አድራሻችን: ቤተል ተቅዋ መስጂድ ፊት ለፊት አልመሻን ሕንጻ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 205 ያገኙናል!

ስልክ: 0921 014449

ወይም በተከታዩ ሊንክ ጻፉልን!

@HidayahTerbiya

#የሂዳያ_ትውልድ #የተርቢያ_መጽሐፍ

💫 https://t.me/HidayaTerbiya 💫
እናት

እናት በልጆች ልብና ነፍስ ውስጥ ትክክለኛውን የአስተዳደግ ዘር በመዝራትና ተክሉን በማጠጣት ረገድ የመጀመሪያዋ ሰው ነች!

የእናት ባህሪ፣ የተርቢያ ዘይቤና የአስተሳሰብ መንገድ ሳይቀር በልጆች ስብዕናና የወደፊት ማንነት ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳድራል።

እናት ሆይ! የምትፈልጊው ዓይነት መልካም ልጆች ለማፍራት ያለሽበትን ቁመና ዘወትር መገምገም አትርሺ!

#የሂዳያ_ትውልድ #ለወላጆች  #ምክር_ለተርቢያ

📮 ሼር ያድርጉ!

💫 https://t.me/HidayaTerbiya 💫
10ቱ የዙልሒጃ ወርቃማ ቀናት Hidaya Terbiya.pdf
3.6 MB
🕋 አስርቱ የዙልሒጃ ወርቃማ ቀናት

📌 በሂዳያ ተርቢያ

🗓 ዙልሒጃ 01/12/1445

📮 #HidayaPublication

⭐️ https://t.me/HidayaTerbiya ⭐️
📌 እይታችሁን ጠብቁ — ኢማናችሁንም ጠብቁ!

ከኢብራሂም ቢን አድሃም (አላህ ዘንላቸው) የተገኘ ዘመን ተሻጋሪ ድንቅ ማስታወሻ

"ሐሰትን አብዝቶ መመልከት የእውነትን ዕውቀትና ግንዛቤ ከቀልብ (ከልብ) ያስወግዳል።"

📖 ሒልየቱል-አውሊያእ (2/8)

ዛሬ ላይ ማህበራዊ የትስስር ገጾች በሐሰት ተሞልተዋል፤ ነውር እየተፈላፈሉ መዘክዘክ፣ ሙዚቃ፣ ፊልም፣ ሐሜት፣ ብልግና እና ኢስላምን የሚቃወሙ አስተሳሰቦች እንደ አሸን ፈልተዋል።

እኛም ሆነ ልጆቻችን እነዚህን ነገሮች ላይ ደጋግመን  ስናፈጥባቸው ጊዜያችንን ማባከን ብቻ ሳይሆን ቀልባችንን እየገደሉብን፤ ኃጢዓትና አመፆችን እንድንላመድ እያደረጉን ይገኛሉ።

🛑 አንድ ሰው ዓይኖቹን ለኃጢዓት ባጋለጠ ቁጥር ቀልቡ ከእውነት እየተጋረደና እየታወረ ይሄዳል። ምክርን መጥላት፣ ቁርኣንን መርሳት፣ ሱናን ማቃለል እና ከአላህ መራቅ ይጀምራል። እውነትን በእውነትነቱ መቀበል፤ ውሸትን በውሸትነቱ መራቅ እየተሳነው ይሄዳል!

🔒 ዓይኖቻችንን እንጠብቅ፤ የቀልቦቻችን በር ናቸውና።

ዓይኖቻችንን፣ ጆሮዎቻችንና  ቀልቦቻችንን በቁርኣን፣ በሐዲስ እና በዚክር እንሙሏቸው ሕያው እናድርጋቸው።

ያለ ዓላማ ለሚደረግ ስክሮሊንግ 'ይብቃ' በሉ።  ዓላማ ላለው ሕይወት 'ነቃ' በሉ።

📌 እይታችሁን ጠብቁ — ኢማናችሁንም ጠብቁ!

#የሂዳያ_ትውልድ #ለወላጆች  #ምክር_ለተርቢያ

📮 የመጪው ትውልድ ሃላፊነት የጋራችን ነው! መልዕክቱን ሼር በማድረግ ለብዙዎች እናድርስ!

💫 https://t.me/HidayaTerbiya 💫
በልጆች ልብ ውስጥ የአላህን ውዴታ ማስረፅ

የሰው ልጅ ነፍስ መልካም ለዋለለት አካል ውዴታና ፍቅር እንዲኖረው ሆኖ ተፈጥሯል።

ልጆችም የዚህ ተፈጥሮ ድርሻ ተካፋይ እንደመሆናቸው መልካም ወደሚያደርግላቸው አካል በጣም የማዘንበል ባህሪ አላቸው

ታዲያ ልጆችን ከለጋ ዕድሜያቸው ጀምሮ  አላህ ስለዋለላቸው የተለያዩ ፀጋዎች በመዘርዘር የአላህን ውዴታ በልባቸው ውስጥ የማስረፅ ሥራ ይጠበቅብናል።

ሁሉም ፀጋዎች ከአላህ የተሰጡን መሆናቸውና ማስረዳት ይኖርብናል። አላህ እንዲህ ብሏል፦

﴿ وَمَا بِكُم مِّن نِعْمَةٍ فَمِنَ اللَّهِ ﴾

"ማንኛውም በእናንተ ላይ ያለው ፀጋ ከአላህ ነው፡፡" [አን-ነሕል ፡ 53]

አላህ እንዲህ ብሏል፦

﴿هُوَ الَّذِي خَلَقَ لَكُم مَّا فِي الْأَرْضِ جَمِيعًا ﴾

"እርሱ ያ በምድር ያለውን ሁሉ ለእናንተ የፈጠረ ነው፡፡" [አል-በቀራ ፡ 29]

ስለዚህ ወላጆች ለልጆቻቸው የአላህን ፀጋዎች ያለማቋረጥ  መንገር ያስፈልጋቸዋል፤ ከእነዚህም መካከል፦

አላህ ነው የፈጠረን
አላህ ነው የምናይባቸውን ዓይኖች የሰጠን
አላህ ነው የምንሰማበትን ጆሮ የሰጠን
አላህ ነው የምንበላባቸውን ጥርሶች የሰጠን
አላህ ነው የምንራመድባቸውን እግሮች የሰጠን

እንዲህ እያልን የአላህን ፀጋዎች እንቆጥራለን፤ ፀጋዎቹ ሊቆጠሩና ሊዘረዘሩ እንደማይችሉም እንነግራቸዋለን።

﴿ وَإِن تَعُدُّوا نِعْمَةَ اللَّهِ لَا تُحْصُوهَا ﴾

"የአላህንም ፀጋ ብትቆጥሩ አትዘልቋትም።" [አን-ነሕል ፡ 18]


#የሂዳያ_ትውልድ #ለወላጆች  #ምክር_ለተርቢያ

📮 የመጪው ትውልድ ሃላፊነት የጋራችን ነው! መልዕክቱን ሼር በማድረግ ለብዙዎች እናድርስ!

💫 https://t.me/HidayaTerbiya 💫
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ወርቃማዎቹን ቀናት በንቃት!

ያለነው አላህ የመረጣቸው፣ ከሌሎች ቀናት ሁሉ በላይ ከፍ ያደረጋቸውና ወደር በሌላቸው የዙልሒጃ የመጀመሪያዎቹ አስር ቀናት ነው።

በእነዚህ ቀናት ሚዛኖች ይለወጣሉ! ምንዳዎች ይነባበራሉ!

አላህ በእነዚህ ቀናት ምሏል!

"በንጋትም እምላለሁ፤ በአስር ሌሊቶችም፡፡" [አል-ፈጅር 1-2]

እነዚህ አስር ቀናት እንደወትሮው ተራ ቀናት አይደሉም፤ ይልቁንም አላህ የወደዳቸው የባረካቸውና ምንዳዎች እጥፍ ድርብ የሚሆኑበትን እድል ያመቻቸበት ወርቃማ ቀናት ናቸው።

ነቃ በልና ቅድሚያ የምትሰጣቸውን ጉዳዮች እንደ አዲስ አስተካክል።

ከንቱ ወሬን ቀንስና አላህን ማውሳትን (ዚክርን) አብዛ።

የስክሪን ጊዜህን አጥፋና የቁርኣንን ብርሃን አብራ።

ጠዋትህን በተክቢራዎች ጀምር፤ ምሽትህን በዱዓዎች ደምድም።

በእያንዳንዱ ቀንም ፈገግታ ወይም መልካም ቃል ቢሆን እንኳ ሶደቃ አድርግ።


እነዚህ አስር ቀናት የሚባክኑበት ጊዜ አይደሉም፤ ይልቁንም ፍሬያማ የሚደረጉ ጊዜያት ናቸው።

ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦

“ከእነዚህ (የዙልሒጃ) አስሩ ቀናት የበለጠ መልካም ስራዎች አላህ ዘንድ ይበልጥ ተወዳጅ የሆነባቸው ቀናት የሉም።”

አላህ ያንቃን!

#የሂዳያ_ትውልድ #ለወላጆች  #ምክር_ለተርቢያ

📮 የመጪው ትውልድ ሃላፊነት የጋራችን ነው! መልዕክቱን ሼር በማድረግ ለብዙዎች እናድርስ!

💫 https://t.me/HidayaTerbiya 💫
አደራ!

አላህ ልጆችን ለወላጆች በትክክለኛ እምነትና በመልካም ስነ ምግባር ኮትኩተው እንዲያሳድጉ አደራ ሰጥቷቸዋል፤ ግዴታቸውን እንዲወጡም ደንግጎባቸዋል። 

እንዲሁም በወላጆች ላይ ሙከራና ፈተናም አድርጓቸዋል።  አላህ ባዘዘው መልኩ (አደራቸውን) ኃላፊነታቸውን ከተወጡ አላህ ዘንድ ታላቅ ምንዳንና ብዙ ሽልማቶችን ሲያገኙ፤ በተቃራኒው ኃላፊነታቸውን ችላ ካሉ ደግሞ በቸልተኝነታቸው ልክ ራሳቸውን ለቅጣት ይዳርጋሉ። 

አንዳንድ ዑለማኦች (የኢስላም ሊቃውንት) እንዲህ ብለዋል፦

"አላህ የቂያማ ዕለት ልጆችን ስለ ወላጆቻቸው ከመጠየቁ በፊት ወላጅን ስለ ልጁ ይጠይቀዋል ፤ ምክንያቱም (አባት) ወላጅ በልጁ ላይ ሐቅ (መብት) እንዳለው ሁሉ ልጅም በወላጁ (አባቱ) ላይ መብት አለውና ነው።"


#የሂዳያ_ትውልድ #ለወላጆች  #ምክር_ለተርቢያ

📮 የመጪው ትውልድ ሃላፊነት የጋራችን ነው! መልዕክቱን ሼር በማድረግ ለብዙዎች እናድርስ!

💫 https://t.me/HidayaTerbiya 💫
ወላጆች ሆይ!

የልጅ አስተዳደግ መሠረታችሁ በእናንተና በልጃችሁ መካከል ፍቅርና የጋራ መተሳሰብ ላይ የተመረኮዘ ይሁን፤ በማስፈራራትና በማስጨነቅ ላይ የተመሠረተ አይሁን፤ ምክንያቱም እነዚህ ሁለቱ ዘላቂ አይደሉምና ነው።

ልጆቻችሁን በጉልበታችሁ የምትቆጣጠሩት ከሆነ፣ እናንተ እንደምትደክሙ እነርሱ ደግሞ አድገው እንደሚጠነክሩ አስታውሱ፤ ያኔ በእናንተና በእነርሱ መካከል ፍቅር ከጠፋ እንዴት ትቆጣጠሩታላችሁ?

ፍቅር ፍቅርን ይወልዳል፤ ልጅም ከተቀበለው ይገነዘበዋል፣ ለሰጠውም በተመሳሳይ ይመልሳል። ፍቅርን ከተቀበለ በምላሹ ሌሎችን እንደሚወድ ሆኖ ያድጋል፤ ጭካኔንና ግዴለሽነትን ከተቀበለ ግን ጠበኛና ጨካኝ ሆኖ ያድጋል።

እያስተዋልን!

#የሂዳያ_ትውልድ #ለወላጆች  #ምክር_ለተርቢያ

📮 የመጪው ትውልድ ሃላፊነት የጋራችን ነው! መልዕክቱን ሼር በማድረግ ለብዙዎች እናድርስ!

💫 https://t.me/HidayaTerbiya 💫
በልጆቻችሁ ውስጥ በራስ የመተማመን መንፈስ አሳድጉ፤ ማንኛውንም ነገር ለመፈፀም አቅም የሌላቸው ሁል ጊዜ በሌሎች ላይ ጥገኛ አታድርጓቸው።

💫 https://t.me/HidayaTerbiya
ጉዞና ስንቅ

ልጆችን ማሳደግ ትዕግስት፣ ዕውቀትንና ጥበብ የሚፈልግ በዋነኝነት ደግሞ የማያቋርጥ ዱዓን የሚጠይቅ ረጅም ጉዞ ነው።

ቁርኣንና ሱንና ደግሞ በዚህ ጉዞ ላይ ብርሃን የሚሆኑን መመሪያዎቻችንና የጉዟችን ስንቅ ናቸው።

የልጆቻችንን ልብ በእምነት እናንፀው!
በተግባራችን አርአያ እንሁናቸው!
በፍቅርና በእዝነት እንንከባከባቸው!

በእጆቻችን የያዝናቸውን የአደራ ፍሬዎች በመልካም ተርቢያ እናስጊጣቸው።

ከሁሉም በላይ ደግሞ፣ ጥረታችንን እንዲያሳምርልንና ልጆቻችንን ለኛ የዓይን ማረፊያ እንዲያደርግልን አላህን እንለምነው።

"እነዚያም «ጌታችን ሆይ! ከሚስቶቻችንና ከዘሮቻችን ለዓይኖች መርጊያን ለእኛ ስጠን፡፡ አላህን ለሚፈሩትም መሪ አድርገን» የሚሉት ናቸው፡፡" (ሱረቱል ፉርቃን 25:74)

#የሂዳያ_ትውልድ #ለወላጆች  #ምክር_ለተርቢያ

📮 የመጪው ትውልድ ሃላፊነት የጋራችን ነው! መልዕክቱን ሼር በማድረግ ለብዙዎች እናድርስ!

💫 https://t.me/HidayaTerbiya 💫
ጥበብ ከቁርኣን፡

የልጅ አስተዳደግ ጥበብ ከቁርኣን

ልጆች ከአላህ የተሰጡን ውድ ስጦታና ታላቅ አደራ (አማና) ናቸው። ይህን አደራ በአግባቡ መጠበቅና ለነገው ዓለም የሚጠቅም ሷሊሕ (ደጋግ) ትውልድን መፍጠር የእያንዳንዱ ሙስሊም ወላጅ ትልቁ ኃላፊነት ነው። ቁርኣን ይህንን ከባድ ኃላፊነት እንዴት መወጣት እንዳለብን የሚያመላክቱን በርካታ መመሪያዎችንና አስተማሪ ታሪኮችን ይዟል።

ከእነዚህም መካከል ጥቂቶቹን በማስተንተን ለልጆቻችን አስተዳደግ የሚረዱ ጠቃሚ ቁምነገሮችን ለማየት እንሞክራለን።

1. የእምነት መሰረት መጣል (ተውሒድ)


የልጅ አስተዳደግ ትልቁ ግብ ልጁን ከፈጣሪው ጋር ማስተዋወቅ ነው። ጥበበኛው ሉቅማን ለልጃቸው የመከሩት የመጀመሪያው ምክር ይህንኑ ያሳያል፦

"ሉቅማንም ለልጁ እርሱ እየገሰጸው «ልጄ ሆይ! በአላህ (ጣዖትን) አታጋራ፡፡ ማጋራት ታላቅ በደል ነውና»፡፡" (ሱረቱ ሉቅማን 31:13)

ከዚህ አንቀጽ የምንማረው፡-

ቅድሚያ ለተውሒድ፡

ለልጆቻችን ከምንም ነገር በፊት ማስተማር ያለብን የአላህን አንድነትና ብቸኛ ተመላኪነት፤ ከእርሱ ውጪ ማንም ሊመለክ እንደማይገባው ነው። ይህ የእምነታቸው መሰረትና የህይወታቸው መመሪያ ይሆናል።

በፍቅር የተሞላ ምክር፡

ሉቅማን ልጃቸውን "ልጄ ሆይ!" (ያ ቡነየ) በማለት በፍቅርና በእዝነት እንደመከሩ እናስተውላለን። ልጆችን ስናስተምር በጩኸትና በዛቻ ሳይሆን በፍቅርና በጥበብ መሆን ይኖርበታል።

#የሂዳያ_ትውልድ #ለወላጆች  #ምክር_ለተርቢያ

📮 የመጪው ትውልድ ሃላፊነት የጋራችን ነው! መልዕክቱን ሼር በማድረግ ለብዙዎች እናድርስ!

💫 https://t.me/HidayaTerbiya 💫
ልጆችን የጠዋትና ማታ እንዲሁም ሌሎች ዚክሮችን ማስተማር ልክ እንደ መንፈሳዊ ክትባት ነው፤ ከማይታዩ አደጋዎች ሁሉ ይጠብቃቸዋል።

💫 @HidayaTerbiya
ወላጅ ልክ እንደ አትክልተኛ መሆን አለበት። አትክልተኛ ችግኙን ውሃ እንደሚያጠጣው ሁሉ ወላጅም ልጁን በፍቅርና በርህራሄ ሊያረሰርሰው ይገባል።

በሌላ በኩል ደግሞ ችግኙ ቀጥ ብሎ እንዲያድግ ደጋፊ እንደሚያስቀምጥለት ሁሉ ወላጅም ልጁ ከስነ-ምግባር መስመር እንዳይወጣ በጥበብ የተሞላ ቁጥጥርና ዲሲፕሊን ሊያደርግለት ይገባል።

💫 @HidayaTerbiya
ለወላጆችና ለመድረሳዎች በሙሉ ታላቅ የምስራች!

ከሂዳያ ተርቢያ

ልጆቻችሁን በኢስላማዊ ስነ-ምግባርና አዳብ ማነፅ ፈታኝ ሆኖባችኋል?

በዘመናችን ያሉ የቴክኖሎጂ እና የባህል ተፅዕኖዎች ልጆቻችንን ከእምነታቸው እና ከመልካም ባህሪያቸው እንዳያርቃቸው ሰግተዋል?

መድረሳዎችና የተርቢያ ማዕከላትስ ተማሪዎቻችንን ለክረምት ምን  እናስተምር ብላችሁ ተጨንቃችኋል?

እንግዲያውስ በአላህ ፈቃድ መፍትሄ ይዘን መጥተናል!

📖 "አዳብ ለልጆች" 📖
የሙስሊም ልጆች የሥነ-ምግባር መማሪያ!

በቅርቡ ይጠብቁን…

አድራሻችን:
📞  0921 014449
💬 በቴሌግራም: @HidayahTerbiya
📍 ቤተል ተቅዋ መስጂድ ፊት ለፊት አልመሻን ሕንጻ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 205 ያገኙናል!
የልጅዎን ክብር እንደ ዓይን ብሌን ይጠብቁ! በተለይም በጓደኛ፣ በጎረቤት፣ በዘመድ ወይም በባዕድ ፊት ክብራቸውን የሚነካ፣ የሚያዋርድ ወይም የሚያሳንስ ቃል ከመናገር ወይም ድርጊት ከመፈጸም ፍፁም ይቆጠቡ።

💫 @HidayaTerbiya
ለልጆቻችሁ ያላችሁ ፍቅር ሚዛኑን የጠበቀ መሆኑን አረጋግጡ፤ የሚያቀብጥ ሳይሆን የሚያንጽ ይሁን። ፍቅራችሁን ግለጹላቸው ነገር ግን ከልክ አልፎ የመሞላቀቅ የባህርይ እንዲያደርሳቸው አትፍቀዱ፤ ጥንካሬያቸውን እንዳያሳጣቸው ተጠንቀቁ።

💫 @HidayaTerbiya
ልጆችን ማድነቅ እና ማመስገን ልጆች በራስ የመተማመን መንፈስ እንዲኖራቸው፤ ምቾት እንዲሰማቸው እና በወላጆቻቸው ላይ አዎንታዊ አመለካከት እንዲኖራቸው የሚረዱ የተርቢያ መሳሪያዎች ናቸው።
#ተርቢያ

💫 @HidayaTerbiya
በሌሎች ሰዎች ፊት ስለ ልጃችሁ ስሞታ አታብዙ፤ ስህተቶቻቸውንም አትናገሩ፤ በተለይም ደግሞ በፊት ለፊታቸው!
#ተርቢያ

💫 @HidayaTerbiya