ሳሙኤል አለሙ-Samuel alemu
584 subscribers
78 photos
1 video
3 links
ሌላ መገኛዬ...
facebook.com/samialemu
Download Telegram
ተገልጋዩን በተመለከተ የምናገረው በጣም አጭር ነው፤

ሲጀመር ጉንዳንን የምናውቀው በታታሪነቱ እንጂ በድህነቱ አይደለም፤ ጉንዳን የቺስታ ምልክት ሆኖ አያውቀም፤ ጠቢቡ ሰለሞንም “አንተ ታካች ወደ ገብረጉንዳን ሂድ “ ሲል ባተሌነቱን ፥አርአያ አድርግ ማለቱ መሰለኝ፤

“ሁላችንም ራቁታችንን ነው የመጣነው” እምትለዋ የቸከች አባባል ትምጣብኝ፤

እውነት ነው፤ ሱፍ ገበርዲን ለብሶ የተወለደ የለም፤ ይሄ ማለት ፥ በዚች ምድር ለሁሉም ሰው ኑሮውን የሚያሸንፍበት አንድ አይነት መወዳደርያ ሜዳ አለው ማለት አይደለም፤ ራቁታችንን መምጣታችን አይደለም ችግሩ፤ የሚቀበሉን ወላጆች ርቃናችንን የመሸፈን አቅም አላቸው ወይ ? በእራፊ ጨርቅ የሚጠቀለል አለ፤ በሀር ጨርቅ የሚጠቀለል አለ፤ የአላሙዲ ልጅ እና ጎዳና ላይ የሚወለደው ያንዲት የኔ ብጤ ልጅ እኩል ናቸው፤? የመጀመርያው ሁለተኛውን ቀድሞት ቢከብር ፥ ሁለተኛው "ባመሉ እና ባመዱ"ምክንያት ደኸየ ሊባል ነው?

በዚህ አገር ላይ ስንፍና እና ስለታታሪነት ማውራት ያለባቸው በትክክል በልፋታቸው የሚኖሩ ሰዎች ናቸው ፤ ገበሬው፥ ጠረፍ ጠባቂው፥ ሀኪሙ መምህሩ ነጋዴው ፤ ሾፌሩ፤ ግንበኛው ፤ አናጢው ወዘተረፈ፥

በአንጻሩ “ እግዚአብሄር ነገረኝ “ በማለት እየተበረነነ በአማኝ ህዝብ ድጋፍ ደልቶት የሚኖር ሰው ፥ ስለ ስለትጋትና ስለስንፍና የማውራት ሞራል የለውም፤

የሀይማኖት መሪዎች ሰባኪዎች ህብረተሰቡ ብዙ መስዋእትነት እንድትከፍሉለት አይጠብቃችሁም! ሀብታሞች ለእናንተ ከሚሰጡት መባና ስጦታ ቆንጥረው በብዙ ምክንያት ለተቸገረ እንዲረዱ ካሳሳባችሁ ትልቅ ውለታ ነው፤

#Bewketu_seyoum🙏
#መልካም_ሰንበት

@Samuelalemuu
3
እራሷን ካደች--ልክ እንደ ሕይወት ...
አ ን ገ ዳ ገ ዳ ት
መንገድ ናት ፊትም....ማን እመኝ ኣላት ?
እ ን ደ ም ወ ዳ ት

ድንገት ስትነቃ .... 'ምትል ተነስታ
'አል ተ ወ ደ ድ ኩ ም'
ባልገፋት ነፋስ....ምስክር ጠርታ
(ለ)'አልተሰበርኩም.!!']
[ለ)'አልተወሰድኩም.!!'...
በራሷው መርዶ....ምትወርድ እስክስታ
ዘ መ ዳ--እ ሪ ኩ ም
"ወደድኩሽ..(..!" እንጂ...."እወድሻለሁ..!.)"
እኔም አ ላ ል ኩ ም !!!
____
🎼 "እሪኩም ዘመዳ .....


        [ ይስሃቅ (ካፒቴን ግራ) ]


@Samuelalemuu
🤔3👏1
የእኩለ-ሌሊት ሀሳብ
(በእውቀቱ ስዩም)

ቀኑ ተሰናብቶ
ጀንበር ከነጭፍራው፥ እስከ ነገ ሞቶ
እንቅልፌ ኮብልሎ
ለካ አልጋ ሸክም ነው፤ የሚሸከም መስሎ ::

"ያለ ረፍት ልጋደም?
ወይስ አንጋጥጨ ጠፈሩን ልራገም ?"
እያልሁኝ ስሟገት
ትዝ አልሽኝ በድንገት፤

ደስ ትይኝ ነበር
ደስ ደስ
ደስ ደስ
እድሌ ነው ማፍቅር፤ እጣሽ ነው መወደስ፥
የፈገግታሽ መጠን
የብርሀን አውራ
ጠፈሩ ሲወጠን
ከግዜር አፍ የበራ  ::

ቁጣሽ አይበረክት
ሰላምሽ አይታክት
ውጊያሽ ሰው አይገድል
አካል አያጎድል
ብጥልሽም  ገድል
ብወድቅልሽም ድል ::

እቅፍሽ ገራገር
ክንድሽ ለማዳ ርግብ
ያጣጣምሽ ነገር
የጦም  መዝጊያ ምግብ::
ብዙ ጸጋዎች ነሽ
የጸጋ ስብስብ
ታድያ ይህን ሳስብ
መራራ ምሾየን ፥ በዘፈን ለወጥኩት
ርግማኔን ዋጥኩት፥

              [ በዕውቀቱ ስዩም ]



@Samuelalemuu
👍31
ከሩቅ ያሳውዳል
ስሟ የመቅደስ ዕጣን
ተብረከረከላት
የኔው ድኩም ሰይጣን
ተንዘፈዘፈላት
እሷ የቄስ ጥምጥም
መፃበሏ እንጂ
መፋቀሯ አይገጥም

ምን ይሉት ታምር ነው
ከሰይጣን መቆንጀት
ስምሽን ለሚጠሩ
ኡኡታን ማበጀት
ምን ይሉት ገቢር ነው
በምን አጠመቅሽኝ
አብም ወልድም ሳሉ
ባንቺ ስም ወለድሽኝ

ከየት አመጣሽው
እንደ ሄሮድስ መክፋት
በነካሽኝ ቁጥር
የጣትሽ አሻራ ስጋዬን ሲልፋት
በተጠራሽ ቁጥር
ተቃጠልኩ እያልኩኝ
ሁሌ ስብከነከን
ከየት ነው የተማርሽው
እንደ አይሁድ መጨከን
አበድሪኝ ስምሽን
"ወየሁ" ልበልበት
አንድም እንደ አቤት
አንድም እንደ ጩኸት

                 [ ቶማስ ትግስቱ ]


@Samuelalemuu
🥰3
¹
ገና ወጣት ንፁህ ነበር .....
ያለ  ግብሩ  ወነጀሉት ፤
ይግባኝ  ቢልም አልገባቸው
ግራ ቀኝ ሳይሉ ገ ደ ሉት ።
ከመሬት አጋድመው
አፈ ሙዝ ደግነው እየፎከሩበት
እሳት ያዘለ እርሳስ አርከፈከፉበት ።
²
የእሱስ ይሁን አንዴ ሄደ
እንደ ንፋስ ....ነፍሶ (ደርሶ)
አተረፈው ከሕይወቱ
(ከስቃይ አዳነው ሞቱ !)
ይብላኝ ለኗሪ እናቱ ።
³
ያኔ ፊትለፊቷ....
ልጇን  በመስቀል ላይ የቸነከሩት ለት
ያሰረችበትን የወላድ አንጀቷን
አላቀበለቻት ማርያም መቀነቷን ።
ውስጥ ውስጡን ተከፍታ በሀዘን ዝላለች
ስዕሏ ፊት ቆማ እንዲህ ትላታለች

“ለደረሰበት ምኑ ሊነገር ?
ታውቂው የለም ወይ የልጅን ነገር !?
የልጅን ነገር ታውቂው የለም ወይ ?
አይተሽ የለም ወይ?
ወስደው ሲያዳፉት
አስረው ሲገርፉት
በምስማር ፊትሽ ሲቸነክሩት
አካል ገላውን በደም ሲነክሩት
አይተሽ የለም ወይ?
ታመሽ የለም ወይ?
.
.
.
«ያንቺስ ተነስቷል በሦስት ቀኑ
የኔ ግን ይሄው ስንት ዘመኑ
በአካል በስጋ መች ይገለጣል
ትዝታው ብቻ በሌት ይመጣል ።
እስኪ ንገሪኝ ?
እነዛ አይሁዶች አንቺን
እንደ
ኔ በድለውሻል?
ልጅሽን ገድለው
አታልቅሽ ብለው
ከልክለውሻል?»

የታወቀ ነው.....
ደስታ ቢታሰር በሳቅ ያመልጣል
ሀዘን ፈንቅሎ በእንባ ይወጣል
(እሷ ትላለች ....)
«አልበቃ ብሎ ልጄን የነሱኝ
ባዋጅ በሕጉ እየመለሱኝ
እንደው በወጉ አላስለቀሱኝ »

ብዙ ቀን ሄዶ....ብዙ ቀን አልፎ
ከሕይወት ዛፍ ላይ ዘመን ረግፎ
ጎረቤቶቿ አብረው ሚኖሩ
በየሰርጉ ዳስ በየማ
በሩ
ድግስ ሲጠሩ
ትታደማለች ፤
እንደ ተፅናና ፈገግ ትላለች ።
ሀዘኗ ሳይሽር አውልቃው ማቋን ፤
ዕምባ ዕምባ ይላል ቢቀምሱት ሳቋን ።
እየዋሸች ነው እያስመሰለች
"እንደ ሚኖሩት ልኑር" እያለች ።
(አልተፅናናችም )

ተፅናናች እንዴ?
ፀኣዳ ቢሆን ከላይ ቀሚሷ
የሀዘን ማቋን ካልጣለች ነፍሷ
ውስጧ እንዳዘነ....
ልቧ ተከፍቶ ዘቅዝቆ ጥለት
‘ሞቶ መኖር’ ነው ....
“መፅናናት” ማለት ?
------
By #Bekalu_shumye
ነሃሴ 23 — 2016 ዓም


@Samuelalemuu
7
ልቡ ለከነፈ ፥ ለናፈቀ ወዳጅ
ምን ያደረጋል ታክሲ ?
ምን ያደረጋል ባጃጅ ?
ወራጅ !
የመኪናው ጎማ ፥ ሺ ጊዜ ቢፈጥን
መውደዴን ላያክል
ጉጉቴን ላይመጥን !
ወራጅ !
ወራጅ !
ናፍቆቷ እንዳልደክም ፥ ይሆነኛል ነዳጅ ።

ጫማዬን አስሬ ፥ ወደ ቤቷ ላዝግም
አጋዥ አልፈልግም ።

መኪናም ይቅርብኝ ፥ ፈረስም አልጋልብ
እግር ይቀርባል ላሳብ
እግር ይቀርባል ለልብ ።

መነሻ ሀሳብ - "ስለምቸኩል በእግሬ ብሄድ ይሻለኛል" ብሎ "ወራጅ!" ያለው የራያ ሰው ታሪክ


#Hab_HD

@Samuelalemuu
👍2😁2
ብርሃን ስላየሁ ብቻ
ሩህ አቅሌን ማሰንበቻ
ቃል ሚስጥሬን መተረቻ
መንገድ ያዝኩኝ ለመሄጃ

ተነሳሁ
ስለሳሳሁ
ተጣደፍኩ
ስለቀለልኩ
እንደልቤ ለመራመድ
ከጎዳናው
ከሰው ዳናው
ለመዛመድ

አቅጣጫ
አካሄድ
ማንጠቁሞኝ
ከፈለኩት እደርሳለሁ
በመሻቴ ልክ አቁሞኝ

ማሰስ ማፈላለግ
በነብስያ ቀንዲል ፈለግ

መንገድ
መንገዳገድ
ላዩት ማርገድ
( አልታከተኝ )

መሄድ መጓዝ
በጋን ኩራዝ

ደጅ ደጁን
የአፍ የጁን
የሆድ መጁን

ከሰማይ
ከንፋስ
ከቃል
ከእስትንፋስ
ከአፈር
ከምድር
ከስጋ
ከድድር

የሆነ አይነት ታምር
የሆነ አይነት ምግባር
ቀን ከለሊት መዋብ
እለት ተለት ማማር

( አያለው )

               [ አዲብ ]


@Samuelalemu
3
እንኳን ለ1446ኛው የዒድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል አደረሳችሁ!

ኢድ ሙባረክ!

@Samuelalemuu
2
'ለዛ ለዛ' ይላል ቃልህ
'ሀሴት ሀሴት 'ትሸታለህ
ጥንጁት ጥንጁት ጤና አዳሙን
አደስ አደስ የደስደሱን
ትለኛለኛለህ
-ቀለም ቀለም ትታያህ
ማማር ማማር ትለኛለህ

እንደመኖር አትከረፋም
እንደመዋል አታለምጥም
ሳትኖር እንኳን አትጎድልም

እንደ ከርቤ እንደሽቶ
መአዛህስ እየቆየ መቼ ጠፍቶ

ትለኛለህ ለዛ ለዛ
እሸቴ ነህ ፥ያልደረቀ ያልጠነዛ
ፈለጌ ነህ ደብዛ ደብዛ
እንደ ግጥሜ..
የማታንስ የማትበዛ...!

             [ሳሚያ ጧሀ]

@Samuelalemuu
3
_ተናፋቂ_እንባወች_

በርግጥ
ከኔ ጎጆ ምንም የለም
እንባዬን ነው ያበደርኳት እንባዋን ነው የሰጠችኝ
ተስፋዬን ነው የነገርኳት ህልሞቿን ነው ያወራችኝ

በኋላ ግን
ከኔ መሸሽ ያድን መስሏት
ሕይወት ገፍቶ ሞት ሸኝቷት

ሄደች ሄደች ትዬው ብዬ ይሁን አልኳት
የትም ስትሄድ የትም ኖሬ በትዝታ ስላሰርኳት

ብዙ ለፋች
አንዱን ባንዱ እያነሳች
በዬ'ለቱ ውብ ቀሚሷን አሰጣችው
አልሞተችም አልዳነችም መሃል ላይ ነው የቀረችው
በቀኑ ነው ቀጭን ሻማ ያበራችው

በጎዳናው ስመላለስ
ይሰማኛል የይመሰል ሳቅ የሷ እንደሆን አውቀዋለሁ
[[ አንዱ ቀሽም ልቧን ፋቀው ብዬ አልፋለሁ ]]

አውቀዋለሁ የሳቅ ልኳን
አውቀዋለሁ የሳቅ መልኳን
ካንጀት ልቧ ስትፈነድቅ አይሰማም ለራሷ'ንኳ
ፍስስ ነው እንደ ዜማ ሰመም ነው እንደታንኳ

ከዚያ ሁሉ ድካም ኋላ
የድዷን ደም በሳቋ ጨርቅ መሸፈኑ ሲሰለቻት
የትም ስትሄድ  መንገድ ሁሉ ባይመቻት

ድክም አለች
ት...ክ....ዝ አለች ስስ ልቧ ተሰበረ
ሌላ ሰው ጋ ከሳቀችው
ከኔ ጋራ ያነባችው ናፍቋት ቀረ
.
.
.
ያሳዝናል።


       [ አማረ ዘውዱ ]

@Samuelalemuu
3🔥1
ከአበቦች ጠረን ፥ ቀለም ቀማሚ
ከገላሽ ምትሐት ፥ ውበት ለቃሚ
እኔን የሚያስንቅ ፥ ምርጥ ገጣሚ !

ያገኘሽ እንደሁ ...

ፀጉርሽን አይቶ ፥ ቅኔ ዘራፊ
ሳቅሽ ሲነካው ፥ ውበት ለፋፊ
እንደኔ ያለ ፥ ጎበዝ ጸሐፊ !

ያገኘሽ እንደሁ ...

በድሮ አድናቆት ሳያሰለችሽ
አዲስ ቃል ፈጥሮ የሚያቆነጅሽ
ካለ ?
ይመችሽ !

ወደ እሱ ብትሄጅ ፥ ወይ ብንለያይ ?
በእርግጥ ያ አይደለም ፥ ትልቁ ጉዳይ !

ብቻ ልንገርሽ !
እሱም አይለካሽ ፥ እኔም አልሆንሽ
ግጥም ብቻ ነው ፥ የሚመጥንሽ ።

📌 የሶሪያው ባለቅኔ ኒዛር ቃባኒን ግጥም #Hab_HD እንደተረጎመው

@Samuelalemuu
🔥31
ይህ ሁሉ የሆነው...
ትላንት ነው ስልሽ
አመታት አልፎታል ፥ ብለሽ ያወራሽው
ያለፉትን ቀናት ፥ እንደምን ቆጠርሽው ?
ጨለማ ብርሃን የተፋለሱብን
ወንዝ ላቦቻችን የተፋሰሱብን
አዋሽ ላብ...
ተከዜ ላብ...
ዮርዳኖስ ላብ...
የተጠመቅነው
የተቀመጥነው
የተደረደርነው ፥ የጠቢብ ስሜት
ተነጠልን ፥ ከወል ቤት።

ቤቴ ሆንሽ ማደሪያዬ
ቤቴ ሆንሽ መክረሚያዬ
ሱባኤ የምገባልሽ
ጉባኤ የምረታልሽ
ታዲያ...
ትላንት ነው ስልሽ
አመታት አልፎታል ፥ ብለሽ ያወራሽው
ያለፉትን ቀናት ፥ እንደምን ቆጠርሽው?
አለፉ ነው ያልሽው ?
ትዝታ ነው ያልሽው ?

ሰው መሆን እንደው...
ላዩን ልውስ ልውስ
ነበር ማለት ብቻ ፥ ናፍቆትን ላይፈውስ።
አመታት ነው ያልሽው ፥ እንደሻረ ቁስል
ቆይቷል የምትይ ፥ እኔ ትላንት ስል።

ትላንት መቼ ነው ?
    
           [ ኤልያስ ሽታኹን ]

@Samuelalemuu
👍4🔥1
ሀገር ሲሰርቅ

ጀግኖቹ ዘማቾች!
በገደል፣ በደኑ፤
ሌባ ሲያሳድዱ፣ ቀማኛ ሲያድኑ።

ጀግኖቹ ዘማቾች!
ከጫካው፣ ከዱሩ፤
ነጣቂ ሲያስሱ፣ ሽፍታ ሲያባርሩ።

ከዘመቻው ብዛት፣
ከዘማቹ ብዛት − አንድ ‘ዕውቀት’ ተረፈን፤
ለካስ!
ሽፍቶች መሀል በቅሎ ‘ጫካው’ ነው ‘ሚዘርፈን።
------
በረከት በላይነህ


@Samuelalemuu
👍2
ብዙ ሳይጣጣር
        እምብዛም ሳይለፋ
  ከዓይን የራቀ
                ከምናብ የሰፋ
                ይህን ዓለም ሠራ
                        ያለ ጭንቀት ጥበት
                ሆነለት “ሁን” ሲለው
                                እንዲሁ በዘበት
                      …
ሕዋውን በሙሉ
               ግዑዙን ተፈጥሮ
         በቃሉ ትዕዛዝ
                 እንዲህ አሳምሮ
                     ለድንጋዩ ራርቶ
                    የንብ መንጋ መርቶ
                     አበባን አፍክቶ
                           ወፊቱን አብልቶ
                  …
እኔ ትንሽ ነገር
          ከሕይወት ቢጨንቀኝ
            አደራህን ብለው
               “እሺ ቆይ” እያለ
             ይህን ሁሉ ዓመት
                            የሚያጠባብቀኝ
         እንዴት ብከብደው ነው
                  ወይ እንዴት ቢንቀኝ ?
              ….

By henok bekele


@Samuelalemuu
1
Sami Alemu
https://t.me/literatureandPoetryy
ግጥም ለምቶዱ ወደ ዚህ ቤት ጉራ በሉ🙏
2
የቀንድ ሀገር ታሪክ

(ደሱ ፍቅርኤል)

ዕልፍ አዕላፍ ጊደሮች
ደጋግ እናት ላሞች ባለፉባት አገር
የበሬውን ውጊያ ታሪኬ ነው ብሎ ነጥሎ መናገር
እጅግ ያሳቅቃል
እጅግም ያስቃል

አዎ በዚች አገር
ወይፈን በሬዎችን በፍቅር የጣሉ እጅጉን የሚያምሩ
ለዓይን የሚያሳሱ ጊደሮች ነበሩ

አዎ በዚች አገር
'ሚዋጉት በሬዎች ለውጊያ እንዲደርሱ
ለወተት ሳይሳሱ
በእናትነት ምላስ ፀጉር እየላሱ
ያሳደጉት ላሞች ሜዳ ላይ እያሉ
'ታሪክ ይህ ነው' ተብሎ
'በሬ ውጊያ' ብቻ ተመዝግቧል አሉ

አልተፃፈም እንጂ
የሞተ ከብትን ፈርስ በክብ እየዞሩ
በሀዘን እየጮሁ በሀዘን እያጓሩ
ለሞተ 'ሚያለቅሱ ደጋግ ኮርማዎች ሜዳ ላይ ነበሩ

አልተፃፈም እንጅ
ሽል ያነሳች ጊደር እየተከተሉ
ሽንት እየቀመሱ እየኮለኮሉ
የተፈጥሮን ውበት ለፍቅር ያደሩ
ውጊያ የሚጠሉም በሬዎች ነበሩ

ዳሩ ያሳዝናል
የጊደር የእናት ላም የጨዋ በሬዎች ዕልፍ ፍቅር ቢያልፍም
በቀንድ ሀገር ታሪክ
ተዋጊው አውራ እንጅ መንጋው አይፃፍም?

@Samuelalemuu
5
ንጉስ ሲጨንቀው

የአንዲት ደሃ ሀገር፣ ዜጎቿ በሙሉ
መሄጃ ቢያሳጡት፣ 'ተራብን' እያሉ
ምስኪን ንጉሳቸው፣ እንዲህ ፀለየ አሉ፡-

‘’እባክህ አምላኬ!
የተራበ ህዝቤን፣ ሲያሻህ በነጠላ
ካሰኘህ በጅምላ፣
ከፊቴ አርቅና፣ ባህር ክተትልኝ
ከሐይቅ ጣልልኝ፡፡
ከዚያማ!
ያልቻሉት ሲሰምጡ፤
የቻሉት ለማምሻ፣ ዓሣ ይዘው ይውጡ!”

By bereket belayneh


@Samuelalemuu
5
የባከነ ሌሊት!!!!


ወይ ሮንድ አላደርኩ
ወይ ኮኮብ አልቆጠርኩ
ወይ ደልቶኝ አልጨፈርሁ
ወይ ውስኪ አልተዳፈርሁ
የባለጌ ወንበር :ኮርቻ አልተሳፈርሁ
ወይ ሰአታት ቁሜ
ቤተክስያን ስሜ
ሰይጣን አላሳፈርሁ::
ሌቦች ደብድበውት
አንዱን ምስኪን ላሥር
ባምቢስ ድልድዩ ሥር
ቆስሎ የወደቀ
ገላው በላዩ ላይ :እንደጨርቅ ያለቀ
ፊቱ ተሸፍኖ : በደምና አቧራ
"በኡራኤል ርዱኝ " ብሎ የሚጣራ
ምስኪን አባወራ
ብብት ሥር ገብቼ
አፋፍሼ አንስቼ
ተሸክሜ አድኜ
ስፈልግ አምቡላንስ :ሲሻኝ ዶክተር ሁኜ
ወይ ምግባር አልሠራሁ
ወይ ጀብድ አልፍፀምኩኝ : ወይ ፅድቅ አላፈራሁ::
አንድ በትረ-ሙሴ
ሁለት ስስ አሎሎ
ከጭኔ መሀከል ሲያመሽ ተንጠልጥሎ
ሲባክን ዝምብሎ
" እሸኝ የኔ ጀግና እንደሰነፍ ቆሎ"
የምትል መለሎ
ልቤን ሳትሰውረው
አልጋየን ሳትሰብረው::
ወግ ቢጤ ሞንጭሬ: ፌስቡክ ላይ ሳለጥፍ
" እናትዋን ጨረቃ" የሚል ግጥም ሳልጥፍ::
አንዲት ሴት- አዳሪ :ቺቺንያ ምንገድ ላይ
እድሉዋ ሰባራ :ሰውነቱዋ አማላይ
ካፍያውና እንባዋ : ተጋግዞ ሚያረጥባት
ደምበኛ ስትጠበቅ :ደመኛ ጥሎባት
አምስት ደፋሪዎች : ከበው ሲያዋክቧት
ሲገፉ ሲስቧት
" እረ በናታችሁ በወላድ ማህፀን
እህት የላችሁም?" ብላ ስትማፀን
ልመናዋ ስቦኝ
እንዳበጀ በለው : በደሏ አንገብግቦኝ
ከሁዋላ ደርሼ
ነበልባል ለብሼ: ነበልባል ጎርሼ
እንደብሩስሊ: እንዳየሩ ጋኔን
እግሬን ወንጨፍ ወንጨፍ
ወዝወዝ ወዝወዝ ጎኔን
በማረግ ቃኝቼ
ከሁዋላ ነው ሲሉኝ ከፊት ተገኝቼ
ካምስቱ መከከል አራቱን ነጥየ
ከቻልኩ በካራቲ ካልቻልኩ በሳቅ ጥየ::
ድል ሳላስመዘግብ
ውጥረት ሳለረግብ
ወይ ታሪክ ሳልሰራ -ወይ ታሪክ ሳልዘግብ
ያለምንም ጣጣ : ያለምንም ፀጋ
አለሰበብ መሽቶ አለሰበብ ነጋ::

By bewuketu seyoum

@Samuelalemuu
👍86😁4👎2