Sam Tech
7K subscribers
409 photos
27 videos
50 files
106 links
Welcome to our tech family! 🚀 Here's what you’ll get
የቴክ መረጃዎች
ጠቃሚ የስልክ አፕልኬሽኖች
Tech tips
✅️Airdrops

Buy ads: https://telega.io/c/SamInTeck
Download Telegram
chatGPT ስለእናንተ ማንነት መዝግቦ የያዘውን ማየት እንደምትችሉ ታውቃላችሁ?

chatGPT ከፈቱና profile ላይ ግቡ።
ከዛ Personalization — memories — manage memories
chatGPT save ያደረጋቸው የተለያዩ መረጃዎች ታገኛላችሁ።
የተዘረዘሩትን አንድ በአንድ በመምረጥ እንዲረሳው የምትፈልጉትን delete ማድረግ ትችላላችሁ። ወይም delete all በማለት ሁሉንም በ1 ጊዜ ማጥፋት ትችላላችሁ።

በነገራችን ላይ ይህ መረጃ more personalized የሆኑ search result እንዲያመጣላችሁ ያግዛል።

የምትነግሩትን መረጃ እዚሁ ውስጥ እንዲመዘግበውና ለቀጣይም እንዳይረሳው ከፈለጋችሁ "save this........", "Don't forget this......."  ወይም "Memorize this........" እያላችሁ ከፃፋችሁ ከዛ በኋላ አይረሳውም።

እስከዛሬ የነበራችሁን chat history ሙሉ በሙሉ ማጥፋት ከፈለጋችሁ ደግሞ profile ላይ ገብታችሁ Data controls - clear chat History
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
5
✉️በEmail እና📧 Gmail መካከል ያለው ልዩነት።

ብዙ ሰዉ በEmail እና Gmail መካከል ልዩነት ያለ አይመስለውም። ስማቸውን interchangeably የሚጠቀሙም ብዙ ናቸው።

E-mail (electronic mail) ማለት ሲሆን የተለያዩ digital መልዕክቶችን በኢንተርኔት ላይ የምንላላክበት መንገድ ነው።

G-mail (google mail) በgoogle የተቋቋመ እና የe-mail አገልግሎት የሚሰጥ platform ነው። ይህም ተጠቃሚዎች በgoogle አካውንታቸው አማካኝነት email እንዲልኩ እና እንዲቀበሉ ያስችላል።

E-mail የግንኙነቱ አጠቃላይ መጠሪያ ሲሆን Gmail ግን ከኢሜል ፕላትፎርሞች ውስጥ አንዱ ነው፡፡

emailን ከgmail ውጭ እንደ yahoo mail, Apple mail, Microsoft outlook, Proton mail, AOL mail, mail.com በመሳሰሉ email ፕሮቫይደሮች መጠቀም ይቻላል።

ከእነዚህ ውስጥ በጣም የታወቀውና ብዙ የገበያ ድርሻ ያለው gmail ነው፡፡
ለአጠቃቀም ምቹና ቀላል መሆኑ እንዲሁም ባሉት ጥሩ ፊቸሮች ምክንያት ከ1 ቢልዮን በላይ ተጠቃሚ በማፍራት ከሁሉም email providers አንደኛ ደረጃን ይዟል።

አንድ ሰው email ፅፎ ወደ ሌላ ሰው በሚልክበት ጊዜ የላኪው SMTP (Simple Mail Transfer Protocol) ስርቨር ከተቀባዩ ሰርቨር ጋር connect ያደርጋል።
የተቀባዩ ሰርቨር የላኪውን አድራሻና የመረጃውን አይነት እንዲሁም ደህንነት ካጣራ በኋላ ትክክል ከሆነ ወደ መረጃ ቋቱ ያስገባዋል።

©bighabesha
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
2
Meta Instagram📹 ላይ የpremium subscription💼 ሙከራ ጀመረ።

Meta Instagram ላይ Instagram plus የተሰኘ premium subscription ወይም ክፍያ ሙከራ መጀመሩን የገለፀ ሲሆን ይህም ይህንን ክፍያ ለከፈሉ ሰዎች ልዩ features መጠቀም ያስችላል።

ከነዚህም features መካከል ከ24 ሰዓት በኋላ በሚጠፋ photo ወይም ቪድዮ ላይ post ያደረገው ሰው ሳያውቅ ማየት፣ የራሳቸውን Story ለተጨማሪ 24 ሰዓት ማራዘም የመሳሰሉ features ይጠቀሳሉ።

ይሁን እንጂ ሙከራው ለጊዜው የተጀመረው የተወሰኑ ሀገራት ላይ ብቻ ነው።

ቴሌግራምም ከጥቂት አመታት በፊት telegram premium የተሰኘ ልዩ features ያሉት premium subscription መጀመሩ አይዘነጋም።

ምንጭ TechCrunch
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
3
💬😎Telegram_update

ቴሌግራም ሰሞኑን ባስተዋወቀው update አንዳንድ features ያካተተ ሲሆን ከነዚህም መካከል👇:

AI Text Editor ✍️🤖

ይህ feature telegram ላይ ረዘም ያለ መልእክት በምንፅፍበት ጊዜ Translate ማድረግ🌐፣ በተለያዩ Style መፃፍ እና Grammer fix ማድረግ ያስችላል የተባለም ሲሆን የፃፍነውንም text እንደ formal, Short, Tribal, Corp በመሳሰሉ ስታይሎች style ማድረግ እንደሚያስችልም ተገልጿል።

ይህንንም feature ለመጠቀም የቴሌግራም መተግበሪያን Update ካደረግን በኋላ 3 እና ከዚያ በላይ መስመር message bar ላይ ስንፅፍ የሚመጣውን የAi ምልክት መንካት📱

New Features for Polls 📊

Pools ላይ እንደ ፎቶ 📷 እና ቪድዮ 📹 ያሉ medias ወይም location 📍 Attach ማድረግ/ማያያዝ፣ Active በሆኑ polls ላይ ᝒርጫዎችን ሰዎች suggest እንዲያደርጉ ማስቻል💡፣ምርጫዎቹ ለየሰው random እንዲኖራቸው ማድረግ የመሳሰሉ features ተካተዋል🆕

@Saminteck
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
3👍2
Samsung ዋና የሚሴጂንግ መተግበሪያውን ወደ Google Messages ሊቀይር ነው።

ሳምሰንግ በዩናይትድ ስቴትስ ለሚገኙ ደንበኞቹ የSamsung Messages መተግበሪያ አገልግሎትን እንደሚያቆም በይፋ አስታውቋል። ከjuly 2026 ጀምሮ የጉግል ሜሴጅ (Google Messages) የሳምሰንግ official የጽሑፍ መልዕክት መተግበሪያ ይሆናል።
ይህ ለውጥ በአንድሮይድ 12 እና ከዚያ በላይ በሚጠቀሙ የጋላክሲ ተጠቃሚዎች ላይ ተግባራዊ ይሆናል። የጋላክሲ S26 ተጠቃሚዎች በአሁኑ ወቅት መተግበሪያውን ማውረድ እንዳይችሉ ተደርገዋል።
ነገር ግን ለውጡ ከAndroid 12 በታች የሆኑ ስልኮችን አያካትትም።

በመግለጫው መሰረት ለጊዜው የሚቋረጠው ለUS ተጠቃሚዎች ሲሆን ለሌሎች ሃገሮች መች እንደሚቋረጥ ይፋ አልተደረገም።

bighabesha
RtsTv V26.0.apk
9.4 MB
ኳስ የምታዩበት አፕ

🫥 New version 🫥
2👏2
Facebook ላይ automatically መጫወት የሚጀምሩ ቪድዮዎችን እንዴት ማስቆም ይቻላል?

በሞባይል ስልካችሁ አልያም በኮምፒዉተራችዉ ላይ የፌስቡክ ፖስቶችን በምትመለከቱበት  ወቅት ቪድዮ ላይ ስትደርሱ እንዲጫወት ሳትጠይቁት መጫወት ይጀምራል፡፡

ይህንን የተወሰኑ ማስተካከያዎችን በማድረግ እንዴት ማስቆም እንደምትችሉ ቅደም ተከተሉ ይህንን ይመስላል፡፡ 

የፌስቡክ አፕን ክፈቱ፡፡

ይህንን (☰) የ3 ሰረዝ ምልክት ወዳለዉ 'Settings menu' ግቡ፡፡

ወደ ታች በመዉረድ 'Settings & Privacy' የሚለዉን ተጫኑ፡፡

ከዛም 'Settings' የሚለዉን ምረጡ፡፡ 

'Media' የሚለዉን እስክታገኙ ወደ ታች ውረዱ ከዛም 'Videos and Photos' የሚለዉን ምረጡ፡፡

በመጨረሻም 'Autoplay' የሚለዉን ሲያገኙ 'Wifi only' ወይም 'Never Autoplay Videos' የሚለዉን በመምረጥ ማስቆም ችላላችሁ፡፡ 
2👍2
🚨 "Binance Africa" ዛሬ በX Twitter ገፃቸዉ ባጋሩት Post ላይ ከግንቦት 7 "May 15, 2026" ጀምሮ በBinance ላይ በEthiopia ብር መግዛትም ሆነም መሸጥ (P2P) ለጊዜው እንደሚያቆም ያስታወቁ ሲሆን፤ ሆኖም ግን በአካውንታችሁ ውስጥ ያለው ገንዘብ ደህንነቱ የተጠበቀ መሆኑን እና አካውንታችሁን መጠቀም እንደምትችሉ ገልፀዋል። ይሄ የሆነበት/የተደረገበት ምክንያትም ከEthiopia ተቆጣጣሪ አካላት ጋር የጋራ ስምምነት ላይ ለመድረስ እንዲቻል መሆኑን አስታውቀዋል።

@SamInTeck
2
🎵Spotify በኢትዮያ ክፍያ ሊጀምር እንደሆነ ተነገረ።

Spotify በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የሙዚቃ ባለሙያዎች በቀጥታ ከክፍያ ሥርዓቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑና ገቢ ማግኘት እንዲችሉ የሚያስችል ምቹ ሁኔታ እየተፈጠረ መሆኑን ገልጿል።

በኢትዮጵያ ውስጥ እየተከናወኑ ያሉት የክፍያ ሥርዓት ማሻሻያዎች የአገር ውስጥ የጥበብ ባለሙያዎች ከSpotify በቀጥታ ገቢ ማግኘት እንዲጀምሩ መንገድ እየከፈቱ ነው። የስፖቲፋይ የሰሃራ በታች አፍሪካ ዳይሬክተር የሆኑት ጆሴሊን ሙቡቱ-ሬሚ እንደገለጹት እስካሁን ለባለሙያዎቹ ገቢ አለማግኘት ዋነኛው እንቅፋት የነበረው የክፍያ መሠረተ-ልማት አለመሟላት ነበር።

ጆሴሊን በቅርቡ በአዲስ አበባ በተካሄደው የCraft Addis የቴክኖሎጂ ፌስቲቫል ላይ እንደተናገሩት በኢትዮጵያ ካሉ የVisa ኃላፊዎች ጋር በክፍያ ሥርዓት ዙሪያ ውይይት አድርገዋል። እነዚህ የክፍያ ሥርዓቶች ተግባራዊ ሲሆኑ የኢትዮጵያውያን አርቲስቶችን የገቢ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ እንደሚቀይሩት ገልጸዋል።

እንደ ናይጄሪያ፣ ደቡብ አፍሪካ እና ኬንያ ያሉ አገራት ባላቸው አለማቀፋዊ የክፍያ ሥርዓት ምክንያት ቀደም ብለው ተጠቃሚ መሆን ችለዋል። ባለፈው ዓመት ብቻ የናይጄሪያ አርቲስቶች 38 ሚሊዮን ዶላር፣ የደቡብ አፍሪካ አርቲስቶች ደግሞ 21 ሚሊዮን ዶላር ከSpotify ክፍያ አግኝተዋል።

ይህ ዜና በተለይ በዘመናዊ የኢትዮጵያ ሙዚቃ (እንደ ራፕ እና ሂፕ-ሆፕ) ላይ ለሚሰሩ ወጣት አርቲስቶች አዳዲስ የገቢ አማራጮችን የሚፈጥር በመሆኑ ትልቅ ፋይዳ አለው።

⚪️የዜናው ባለቤት birrmetrics.com

bighabesha
GUYS CHAT GPT የ ፊታቹን የ ዉበት ደረጃ መናገር ጀምሯል 😄

ፎቶዋቹን እና ይሄን prompt በማስገባት ሞክሩት

Create a clean, minimal, 
high-end facial beauty report based on this photo. Use a black-on-white design with thin lines, rounded cards, and a luxury aesthetic. Include a simple contour line drawing of the face, an honest attractiveness analysis (symmetry, proportions, bone structure, skin, etc.), clear scores, strengths, areas for improvement, and actionable grooming/style recommendations. Keep it data-driven, visually refined, and not overly flattering

@SamInTeck
👍3
YouTube ስልክ ላይ PIP (picture in picture) mode ጀምሯል። ያ ማለት ስልካችሁ ላይ በapplication YouTube ብትከፍቱና home button ብትጫኑ ቪዲዮው አይዘጋም። ስክሪናችሁ ላይ በpicture mode ይጫወታል።

ይህን ለማድረግ YouTube ላይ ግቡና የProfile ምልክታችሁን ንኩ።
ከዛ Settings -- Playback -- Picture in picture
On አድርጉት።

በዚህ መሰረት አስተካክላችሁ ስልካችሁ ላይ YouTube እያያችሁ የፈለጋችሁትን ስራ መስራት ትችላላችሁ።

ካልሰራላችሁ update አድርጋችሁ ሞክሩት።

@SamInTeck
ከ Instagram Vidio Picture Download ለማረግ ይህን Bot መጠቀም ትችላላችሁ ።

Start 👉 @Instagram_Downloaader_Bot

@Saminteck
2
Google Docs የምትጠቀሙ ከሆነ አዲስ update ተካቶለታል።

docs.google.com ላይ ገብታችሁ ዶክመንት ስትሰሩ ከታች የGemini icon አለች። እሱን በመንካት እየሰራችሁት ያላችሁትን ዶክመንት እንዲጨርስላችሁ፣ edit እንዲያደርግላችሁ ወይም እንዲያሻሽልላችሁ ማድረግ ትችላላችሁ። በአማርኛም በትክክል ይሰራል።

ስልካችሁ ላይ የምትጠቀሙ ከሆነ የGemini icon ዶክመንታችሁን ከከፈታችሁ በኋላ ከላይ በቀኝ በኩል ታገኟታላችሁ።

በተጨማሪም እዛው ዶክመንቱ ላይ image create አድርጋችሁ ማካተት ትችላላችሁ።

Bighabesha
Google ለብዙ አመታት ሲጠበቅ የነበረውን የGmail address መቀየር የሚቻልበትን አሰራር ለመላው አለም ይፋ አድርጓል።

ስለዚህ በልጅነታችሁ እንደ አጋጣሚ የሰጣችሁትን የGmail address ከዛሬ ጀምሮ መቀየር ትችላላችሁ።
ለምሳሌ momloveyouxyz@gmail.com የነበረውን ወደ hanaabraham1234@gmail.com መቀየር ትችላላችሁ።

ይህንንም ለማድረግ የስልካችሁ settings በመግባት Google services — Manage your Google account —- Personal info —- Email —- Google account Email — change Google account Email

ድጋሜ መቀየር ከፈለጋችሁ 1 አመት መጠበቅ ይኖርባችኋል። ስለዚህ ጥንቃቄ አድርጉ።
👍21
የMeta አዲስ Application

Meta ለፌስቡክ ማርኬትፕሌስ ሻጮችና ነጋዴዎች ንግዳቸውን በቀላሉ ማስተዳደር የሚያስችላቸውን “Seller” የተሰኘ አዲስ የተለየ አፕሊኬሽን ይፋ አድርጓል።

📌 የአፕሊኬሽኑ ዋና ዋና ባህሪያትና ጥቅሞች፦
በAI የተደገፈ ዕቃዎችን የመመዝገብ ሂደት፦ የዕቃውን ፎቶ ብቻ በመጫን Meta AI ራሱ ርዕስ፣ መግለጫ (Description)፣ ምድብና ዋጋ በሰከንዶች ውስጥ ያዘጋጃል። በተጨማሪም በርካታ ዕቃዎችን በአንድ ጊዜ መመዝገብ ያስችላል።
Unified Inbox፦ ከገዢዎች የሚመጡ ጥያቄዎችን እና መልዕክቶችን በየዕቃው አይነት ለይቶ በአንድ ቦታ በማደራጀት ቀልጣፋ ምላሽ ለመስጠት ያግዛል።
Inventory Management፦ ያሉትን ዕቃዎች ማየት፣ ማስተካከል፣ ዋጋ መቀየር እና አዳዲስ ዕቃዎችን መቆጣጠር ያስችላል።
Performance Insights፦ የትኞቹ ዕቃዎች ብዙ እይታ (Views) እና መልዕክት እንዳገኙ የሚያሳዩ መረጃዎችን በማቅረብ የተሻለ የንግድ ውሳኔ ለመስወሰን ያግዛል።

​አፑ ከአሁኑ ጀምሮ በአሜሪካ ለሚገኙ ዕድሜያቸው 18ና ከዚያ በላይ ለሆኑ የiOS (App Store) ተጠቃሚዎች ክፍት ሆኗል። የWeb እና የAndroid አፕሊኬሽኖች በቅርቡ እንደሚለቀቁ ተገልጻል።
👍21
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Breaking

Google በgemini omni አማካኝነት በነፃ እስከ 10 የሚደርስ video Generate ማድረግ እንደምችሉ አስታውቋል።

Gemini ክፍቱና የ+ ምልክቱን ነክታችሁ Video የሚለውን በመምረጥ የፈለጋችሁትን አይነት video create ማድረግ ትችላላችሁ።

ይህ ዕድል የሚቆየው እስከ august 4 ድረስ ብቻ ነው።
ሞክሩት።

@Saminteck
1👍1
Google Assistant ሊዘጋ ነው!

ግዙፉ የቴክኖሎጂ ድርጅት Google በብዙ ሚሊዮን አንድሮይድ ተጠቃሚዎች ለዓመታት ስንጠቀምበት የነበረውን Google Assistant ሙሉ በሙሉ ሊዘጋው መሆኑን ይፋ አድርጓል። በአዲሱ የGenerative AI Gemini እንደሚተካ ተገልጿል።

አሁን ላይ በአንድሮይድ ስልኮች እና ስማርት device ላይ ዋናው የድምፅ ረዳት (Default Voice Assistant) ሆኖ የሚሰራው Gemini ነው።
የGoogle Assistant ሞዴል አሁን ካለው የGenerative AI ቴክኖሎጂ ጋር የሚጣጣም ባለመሆኑ ተጠቃሚዎች ሙሉ በሙሉ ወደ Gemini እንዲሸጋገሩ ጉግል ግፊት እያደረገ ይገኛል።

ኩባንያው አገልግሎቱን September 2026 ከአገልግሎት ውጪ እንደሚያደርገው 9to5Google ዘግቧል።
Ethio telecom የGoogle RCS(Rich Communication Services) አገልግሎት እንደሚሰጥ ታውቃላችሁ?

RCS ማለት በሞባይል ስልክ መልዕክትን በኢሞጂ፣ በፎቶ፣ በቪዲዮ እና በድምፅ አንድ ለአንድ ወይም በቡድን ያለገደብ በመልዕክት ማጋራት የሚያስችል መንገድ ነው፡፡ ከእኛ የሚጠበቀው የGoogle Messaging መተግበሪያን አውርዶ መጠቀም ብቻ ነው፡፡

አገልግሎቱን ለማስጀመር
▪️“Google Messages’’ መተግበሪያን ከጉግል አፕ ማውረድ
▪️የጂሜል አካውንት በማስገባት default messaging ማድረግ
▪️በመተግበሪያው ከላይ በቀኝ በኩል ‘’Messages settings’’ የሚለውን መምረጥ
▪️‘’General’’ የሚለውን በመጫን በመቀጠል ‘’RCS Chats’’ የሚለውን ምረጡ
▪️ ‘’Verify Your Number’’ የሚለውን በመምረጥ የሞባይል ቁጥርዎን በማስገባት መጨረስ።
Google Messages Playstore link