የሰሃቦች ታሪክ ሀያቱ ሰሃባ
6.06K subscribers
1.29K photos
395 videos
45 files
1.12K links
የሰሃቦች ታሪክ
Download Telegram
እስኪ አንድ መጽሐፍ ላስተዋውቃችሁ…
አሁን እያነበብኩት ያለሁት ይህን መጽሐፍ ነው። እውነት ለመናገር፣ መጽሐፉን እያነበብኩ ስሄድ የበለጠ ለማንበብ እንድጓጓ እያደረገኝ ነው።
ስለ ረሱል ﷺ የተጻፈ ብቻ አይደለም…
የረሱል ﷺ ስነ-ምግባርና ባህሪ

አስተምህሮታቸው

ስለእሳቸው የተነገሩ የተዛቡ አስተሳሰቦችና ምላሾቻቸው

ስለእሳቸው ﷺ የተነገሩ አስገራሚ ትንቢቶች

እና ከእኛ ዘመን ጋር የሚያገናኙ ጉዳዮችንም ይዳስሳል።
የሚገርመው ደግሞ አቀራረቡ ነው…

በጣም ሳቢ፣ ቀላል እና አንድ ገጽ ካነበብክ ቀጣዩን ገጽ ለማየት የሚያጓጓ አዘገጃጀት ነው።

እናንተም ስለ ረሱል ﷺ ማወቅ፣ መማር እና ማንበብ የምትወዱ ከሆነ፣ ይህን መጽሐፍ እንድታዩት እጋብዛችኋለሁ።
📌 መጽሐፉ፦ [ፍፁም ሰው ፍፁም ነብይ]

✍️ ደራሲ፦ [ኡስማን ሙስጠፋ]
📞0912027023/0921390122
Telegram @Usmanoman
Telegram channel👇 https://t.me/usmanic_psychology
👍5
ኒቃብ መልበስ እኮ ፊት መሸፈን ብቻ አይደለም ሙሉ አለባበስም የተስተካከለ መሆን አለበት የሚሰትር ልቅቅ ያለ ልብስ (ጅልባብ)መለበሰ አለበት አያዕ የሚባል ነገርም አለ ....!

@H20yatii
👍6🔥1
I will tell you again and again, ALLAH MOVES MOUNTAINS!!!!!

Just prayYYYYYYY and have Tawakkul❗️❗️❗️
👍4
ጌታችን አላህ ሆይ በአንተ እና በባሮችህ መሃል ፈራጅ ሆነን ጣልቃ የገባንበትን ሁሉ ማረን፣ሰው ላይ አይተን በጠላነውም አትፈትነን''🤲

@H20yatii
👍6
ኡኽቲ....አሁን የሚያስፈልግሽ አባትሽ ሳያዩሽ ላግኝሽ የሚለው ሳይሆን አባትሽን ጠይቄ ልውሰድሽ የሚለው ነው ....🩶አላህ ያግራው

@H20yatii
💯9
ቀስ እያለ ወጥመዱን እየዘረጋ ሳናስተውለው ከመንገድ የሚያስተንን ሸይጧን ረገምኩት። ሰዎችን ከመምከር አልፈን የፈረድንባቸው ነገር ላይ ቢዘገይም መውደቃችን ማይቀር መሆኑን ተሰማኝ።

አላህዪ መጨረሻዪን አሳምርልኝ ...🤲

@H20yatii
👍7🔥3
የአላህን ቃል የመሸምደድ ምኞትህን ፈጽሞ አትተው

የአላህን ቃል በውስጥህ የመቅረጽ (የማሐፈዝ) ምኞትህን ፈጽሞ አትተው ዕድሜህ የትኛውን ያህል ቢገፋም የሱ ሕዝብ የቁርአን ባለቤት ከመሆን ወደ ኃላ አትበል።

ይህንን ምኞት ሁልጊዜ ለውስጥህ አጫውተው፣ እቅድም አውጣለት።

ከዚህች ዓለም በምትለይበት ሰዓት ከሕይወትህ ታላላቅ ድሎች አንዱ እሱ እንደነበር በእርግጠኝነት ትገነዘባለህና......

ጥቂትም ቢሆን ከራስህ ጋር ታገል፤ ጉዞህ በቀላል፣ በተቀናጀ እና ባልተቋረጠ መልኩ እስካቀና ድረስ ወደ ግብህ መድረስህ አይቀርም.. 🌿

​በአላህ ታገዝ እና ጀምር 💪🏼🌸
http://t.me/ibrahim_furii
👍3💯1
አንዳንዴ ግን ምን አንዳንዴ ሁሌ  የምር ከስራዎቻቾን ጋር እንተሳሰብ፣ ንያችንንምም እንመርምር ደግሞም የሆነ የራስ ጊዜ ይኑረን እኛ ና ሀሳቦቻችን ምናወጋበት Socilaize  ማድረግ  ጥሩ ቢሆንም ራስን ሚያሳጣ በሰዎች መዋጥ እስኪያመጣብን አናብዛ!!



@Eslamicbooks1224
👍1
በራሴ ማንንም አርዓያ አላደርግም ከረሱል እና ከሰሀባዎች..ከሰሃባያት ውጪ....
ማንም ምንም ቢሰራ !!እኔንም አርዓያ እንዲያደርጉኝም አልፈልግም...የሆነ ሰዓት ከአቋሜ ዘንበል ብል ብዙ ነገሮች ይበላሻሉና ብቻ ግን አላህ ጠቃሚ ያድርገን!!

@H20yatii
👍5
አለባበስ ሀያዕን ነው ሚገልፀው የልብን ተቅዋ ግን አላህ ብቻ ነው የሚያውቀው ..!
@H20yatii
👍5👌1
አላህ ነው ምስክሬ ወላሂ እኔ በጣም ነው ሰው የማምነው በሰዎች ላይ ምንም መጥፎ ጥርጣሬ የለብኝም ሁሉም ለኔ መልካም እንደሆኑ ነው ሁሌም የማስበው አልሀምዱሊላህ እና ይሄን ሀሳቤን የሚያስቀይር ነገርም አይምጣብኝ ...አልሀምዱሊላህ ጌታዬ በባሪያዎችህ ስላልተፈተንኩ 🔐

@H20yatii
👍6🔥3
ለማን ብለን!!!?

ኢልምን እንፈልጋለን...ኒቃቡን እንለብሳለን....Business እንሞካክራለን...can i add something ...The real goal is jennnah🩶 አላህ ግርት ያድርግልን ወላሂ ..🤲

@H20yatii
🔥12👍4🏆4
በዚህ ቻነል ምን ይቅረብለችሁ?
Anonymous Poll
67%
የነቢያት ታሪክ
70%
የሶሀቦች ታሪክ
👌6
﴿إِنَّ ٱللَّهَ وَمَلَٰٓئِكَتَهُۥ يُصَلُّونَ عَلَى ٱلنَّبِىِّ ۚ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَءَامَنُواْ صَلُّواْ عَلَيْهِ وَسَلِّمُواْ تَسْلِيمًا ۝

ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ
👍5🔥2
Audio
ወደ አላህ መቃረብ
👍9
زاد القلوب ١٥
በኡስታዝ ተውፊቅ ራሕመቶ
🤍 زاد القلوب | የልቦች ስንቅ

🎧 የዛሬው ርዕስ፦ ነፍስን የማጥራት አሳሳቢነት

በሥራ ላይ ስትሆኚ፣ በመንገድ ስትጓዢ ወይም በእረፍት ጊዜሽ ይህን የልብ ስንቅ በማዳመጥ ተጠቀሚ። 🤍

ምናልባት ዛሬ የምታዳምጪው አንድ ሐሳብ በሕይወትሽ ላይ ትልቅ ለውጥ ያመጣ ይሆናል።


بَارَكَ اللهُ فِيكُنَّ وَنَفَعَ بِكُنَّ 🤍
↗️EMFSC
👍5
❒ አቡ ሁረይራ  ረድየሏሁ ዐንሁ❒
┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈

                ክፍል 1⃣
              ❒❒🌹❒❒

" አቡ ሁረይራ ለሙስሊሙ ህብረተሰብ (ኡምማ ከ 5374 በላይ ሐዲሶችን ጠብቆ አቆይቷል።" (የታሪክ ሊቃውንት)

ዐን አቢ ሁረይረተ ረድየሏሁ ዐንሁ ቃለ፣ ቃለ ረሱሉሏሂ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም...."

   በዚህ ሀረግ አማካኝነት ከኢስላም የመጀመርያ ታሪክ አንስቶ እስከ አሁን ድረስ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ሙስሊሞች አቡ ሁረይራ የሚለውን ስም ሊለምዱት ችለዋል። በንግግሮችና በትምህርቶች፤ በጁምአ ኹጥባወችና በአውደ ጥናቶች፤ በሐዲስ፤ በፊቂህና በታሪክ መጽሐፍት አቡ ሁረይራ የሚለው ስም በዚህ መልኩ ይጠቀሳል።

              •••✿❒🌹❒✿•••

  በእሳቸው አስደናቂ ጥረቶች አማካኝነት በሺወች የሚቆጠሩ ሐዲሶች (የረሱል ሰ.ዐ.ወ ንግግሮች) ለቀጣዩ ትውልድ ተላልፏል። በሐዲስ ዘጋቢወች መዝገብ ውስጥ የእሳቸው ስም ዝርዝር ግንባር ቀደም ነው። ከእሳቸው ቀጥሎ አብደላህ ኢብን ዑመር ረ.ዐ፣ አነስ ኢብን ማሊክ ረ.ዐ፤ ኡሙል ሙእሚን አዒሻ ረ.ዐ፣ ጃቢር ኢብን ዐብደላህና አቡ ሰኢድ አልኹድሪይ ረ.ዐንሁም ከአንድ ሺህ በላይ የሚሆኑ ሐዲሶችን እና ገቢር እንቅስቃሴዎች ለትውልድ አስተላልፈዋል።

  አቡ ሁረይራ እስልምናን የተቀበሉት እሳቸው የሚገኙበት ደውስ የተባለው ነገድ መሪ በሆነው ጡፈይል ኢብን ዐምር አማካኝነት ነው። የደውስ ጎሣ አባላት ይኖሩ የነበሩት በደቡብ ዐረቢያ የቀይ ባህር ዳርቻን ተከትሎ ባለው ክልል ውስጥ ነው። ጡፈይል ነብዩን ሰ.ዐ.ወ ከተገናኘና በእሳቸው ተልዕኮ የመጀመርያ አመታት ውስጥ ሙስሊም ከሆነ በኋላ ወደመኖሪያ ሰፈሩ በተመለሰ ጊዜ ጥሪውን ከተቀበሉት የመጀመሪያወቹ ሰወች አቡ ሁረይራ አንዱ ነበሩ። በድሮ እምነታቸው ላይ ለረጅም ጊዜ ችክ ብለው እንደቆዩት አብዛኞቹ የደውስ ተወላጆች አልነበሩም።

              •••✿❒🌹❒✿•••

    ጡፈይል በድጋሚ መካ በሄደ ጊዜ አቡ ሁረይራም ረ.ዐ ተከተሉ። እዚያም የተከበሩትን ነብይ ሰ.ዐ.ወ የማግኘት ክብርና ዕድልን ተጎናፀፉ። ረሱል ሰ.ዐ.ወ "ስምህ ማነው? ሲሉ ጠየቁት እሳቸውም "ዐብዲሸምስ-የፀሀይ ባርያ ብለው መለሱ። ረሱል ሰ.ዐ.ወ ከዚህ ይልቅ ዐብዱረህማን ብትባልስ አሉት።
"እሺ የአላህ መልእክተኛ ዐብዱረህማን ይሁንልኝ" በማለት መለሱ።

  ይሁንና አብዱረህማን ይበልጥ የሚታወቁት "አቡ ሁረይራ" በሚለው ቅፅል ስም ነው። የቃሉ ቀጥተኛ ትርጉም "የድመት አባት" ማለት ሲሆን ስያሜውን ያገኙት ድመቶችን ይወዱና ከልጅነታቸው ጀምሮ አጫዋች ድመት ያረቡ ስለነበር ነው።

              •••✿❒🌹❒✿•••

   አቡ ሁረይራ ለበርካታ ዓመታት የቆዩት በጢሀማህ ሲሆን ከሂጅራ በኋላ በሰባተኛው ዓመት መጀመሪያ ላይ ነበር ከሌሎች የጎሣቸው አባላት ጋር ሁነው መዲና የገቡት። በዚያ ጊዜ ነብዩ ሰ.ዐ.ወ ወደ ኸይበር ዘመቻ ሂደው ነበር። አቡ ሁረይራ ረ.ዐ ምግብና ሌሎች መሰረታዊ ቁሳቁሶች ስላልነበሯቸው ከ "አህለስ ሱፋህ" ሰወች ጋር ተቀላቀሉ ማረፊያቸውንም መስጊድ አደረጉ። ልጅም ሚስትም አልነበራቸውም።

   ይሁንና ከሙሽሪክነት (አጋሪነት) ያልተላቀቀችው እናታቸው አብራቸው ነበረች።

አቡ ሁረይራ ረ.ዐ ምግብና ሌሎች መሰረታዊ ቁሳቁሶች ስላልነበሯቸው ከ "አህለስ ሱፋህ" ሰወች ጋር ተቀላቀሉ ማረፊያቸውንም መስጊድ አደረጉ። ልጅም ሚስትም አልነበራቸውም።ይሁንና ከሙሽሪክነት (አጋሪነት) ያልተላቀቀችው እናታቸው አብራቸው ነበረች። እናታቸው ሙስሊም እንድትሆን በፅኑ ይመኙና ዱአ ያደርጉላት የነበረ ቢሆንም ማንገራገሯ አልቀረም።

   አንድ ቀን በአንድ አላህ ብቻ እንድታምንና የአላህንም ነብይ እንድትከተል ሲመክሯት ስለነብዩ አንዳንድ ቃላትን ተናገረች። አቡ ሁረይራ እጅግ አዘኑ። ዐይናቸው እንባ እንዳቀረረ ወደ ረሱል ሰ.ዐ.ወ ሄዱ። ረሱልም " አንተ አቡ ሁረይራ ለመሆኑ ምን ያስለቅሳል?" አሉዋቸው። እናቴ እናቴ ኢስላምን እንድትቀበል ከመገፋፋት ወደ ኋላ ብየ አላውቅም። እሷ ግን ሁልጊዜ በንቀት ትቃወመኛለች። ዛሬም እንደገና ብነግራት የማልወዳቸውን ቃላቶች ከእርሷ ሰማሁ። የአቡ ሁረይራ እናት ልብ ኢስላምን ለመቀበል እንዲገራ ሁሉን ማድረግ ለሚችለው አላህ ሱ.ወን ይለምኑልኝ ሲል አቡ ሁረይራ ረ.ዐ ረሱልን ሰ.ዐ.ወ ተማፀኑ

              •••✿❒🌹❒✿•••

ረሱል ሰ.ዐ.ወ የአቡ ሁረይራን ጥያቄ በመቀበል ዱአ አደረጉላት። ከዚያ በኋላ ስለሆነው አቡ ሁረይራ ረ.ዐ ሲናገሩ "ወደ ቤት ስሄድ በሩ ተዘግቶ አገኘሁት። የሚቀዳና የሚፈስ ውሀ ድምፅ ሰማሁ። ወደቤት ለመግባት ስሞክር እናቴ "አንተ አቡ ሁረይራ እዛው ቆይ" አለችኝ። ከዚያ ልብሷን ከለበሰች በኋላ ግባ አለችኝ ገባሁ "ከአላህ በስተቀር በሀቅ የሚገዙት ሌላ አምላክ እንደሌለ እመሰክራለሁ፤ ሙሀመድ የእሱ አገልጋይና መልእክተኛ መሆኑንም እመሰክራለሁ" በማለት ቃሏን ሰጠች።

   ቀደም ብየ በሀዘንና እያለቀስኩ እንደሄድኩት ሁሉ አሁን ደግሞ የደስታ እንባ እያፈሰስኩ ወደ ነብዩ ሙሀመድ ሰ.ዐ.ወ ተመልሸ ሄድኩና "የአላህ መልእክተኛ ሆይ፣ የምስራች ዜና አለኝ። አላህ ሱ.ወ የርሰወን ዱአ ተቀብሎ የአቡ ሁረይራን እናት ወደ ኢስላም መርቷታል አልኳቸው።

  አቡሁረይራ ረ.ዐ ነቢዩን ሰ.ዐ.ወ ሲበዛ ወደዷቸው። ውለታ ለመክፈልም ፈለጉ። የፀኃይን ጨረር ሁሉ የያዘ የሚመስላቸውን የነብዩን ሰ.ዐ.ወ ፊት ማየትና ንግግራቸውን ማዳመጥ በጭራሽ ሰልችቷቸው አያውቅም ነበር። ላገኙት መልካም ዕድል ዘወትር አላህን ያወድሱትና ለራሳቸው "አቡ ሁረይራን ወደ ኢስላም ለመራው አምላክ ምስጋና ይገባው። ለአቡ ሁረይራ የነብዩን ሰ.ዐ.ወ ጓደኝነት እንዲያገኝ ለረዳው አምላክ ምስጋና ይድረሰው" ይሉ ነበር።

              •••✿❒🌹❒✿•••

አቡ ሁረይራ ረ.ዐ መዲና ከደረሱበት ወቅት ጀምሮ እውቀት ለመሰብሰብ ልባቸውን ክፍት አድርገው ነበር። የረሱል ሰ.ዐ.ወ ታዋቂ ጓደኛ ዘይድ ኢብኑ ሳቢት ረ.ዐ የሚከተለውን ተናግረዋል፦ አቡ ሁረይራ እኔና ሌላ ጓደኛየ መስጊድ ውስጥ ዱአ እያደረግን ሳለን ረሱል ሰ.ዐ.ወ መጡ

              •••✿❒🌹❒✿•••
👍2🔥2👏2
የሰሃቦች ታሪክ ሀያቱ ሰሃባ pinned «❒ አቡ ሁረይራ  ረድየሏሁ ዐንሁ❒ ┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈                 ክፍል 1⃣               ❒❒🌹❒❒ " አቡ ሁረይራ ለሙስሊሙ ህብረተሰብ (ኡምማ ከ 5374 በላይ ሐዲሶችን ጠብቆ አቆይቷል።" (የታሪክ ሊቃውንት) ዐን አቢ ሁረይረተ ረድየሏሁ ዐንሁ ቃለ፣ ቃለ ረሱሉሏሂ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም...."    በዚህ ሀረግ አማካኝነት ከኢስላም የመጀመርያ ታሪክ አንስቶ እስከ አሁን…»