Sadat_Text_Posts
10K subscribers
291 photos
8 videos
12 files
378 links
Download Telegram
👆🏻ተውሂድን ለልጆች ማስተማር
ድል ለአላህ፣ ለመልክተኛውና ለአማኞች ነው፡፡
የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ለነዛ በሺርክ ጨለማ ውስጥ ተዘፍቀው ለነበሩ አጋሪያን ማህበረሰቦች ተላኩ፡፡ እሳቸውም ከጌታቸው የተላኩበትን የተውሒድ መልክት ይፋ አደረጉ፡፡ አለ የሚባል መከራ ሁሉ ደረሰባቸው፡፡ ስማቸውን ማጥፋት፣ እሳቸውንም ባልደረባዎቻቸውን ማሰቃየት፣ እሳቸውን ለመግደል መሞከር፣ ሲሰደዱ ጋር ሰውራ ድረስ ለመግደል ተከታተሏቸው፡፡ የሚወዷትን ውድ ከተማ መካ “ህዝቦችሽ ነው ያስወጡኝ እወድሻለሁ” እያሉ ዞር እያሉ እያዩት ጥለዋት ተሰደዱ፡፡
መዲና አላህ በሰላም አደረሳቸው፡፡ መካ በነበሩበት ጊዜ አማኞች ሲገደሉ፣ ሲደበቁ እንዳልነበር አላህ መዲና ላይ ባሉበት መልክተኛው (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ህልምን አዩ፡፡ አላህ ህልማቸውን አስመልክቶ እንዲህ ይለናል
لَّقَدْ صَدَقَ ٱللَّهُ رَسُولَهُ ٱلرُّءْيَا بِٱلْحَقِّ ۖ لَتَدْخُلُنَّ ٱلْمَسْجِدَ ٱلْحَرَامَ إِن شَآءَ ٱللَّهُ ءَامِنِينَ مُحَلِّقِينَ رُءُوسَكُمْ وَمُقَصِّرِينَ لَا تَخَافُونَ ۖ فَعَلِمَ مَا لَمْ تَعْلَمُوا۟ فَجَعَلَ مِن دُونِ ذَٰلِكَ فَتْحًا قَرِيبًا
አላህ ለመልክተኛው ሕልሙን እውነተኛ ሲኾን አላህ የሻ እንደ ኾነ ጸጥተኞች ኾናችሁ ራሶቻችሁን ላጭታችሁ፣ አሳጥራችሁም የማትፈሩ ስትኾኑ የተከበረውን መስጊድ በእርግጥ ትገባላችሁ፤ ያለውን በእርግጥ እውነት አደረገለት፡፡ (ከእርቁ) ያላወቃችሁትንም ነገር ዐወቀ፡፡ ከዚህም በፊት ቅርብን መክፈት አደረገ፡፡

ከዛም ያችን ውድ የከተሞች እናት መካ መልክተኛው (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ከአማኞች ጋር ሆነው ከፈቷት፡፡
وَقُلْ جَآءَ ٱلْحَقُّ وَزَهَقَ ٱلْبَٰطِلُ ۚ إِنَّ ٱلْبَٰطِلَ كَانَ زَهُوقًا
በልም «እውነት መጣ ውሸትም ተወገደ፤ እነሆ ውሸት ተወጋጅ ነውና፡፡»

መታገስ ነው እንጂ የአላህ ቃል ሁሌም እውነት ነው፡፡ ሁለት አገር ድል የፈለገ ነብያት ሁሉ የሄዱበትን ብቸኛ የሐቅ ጎዳና ይጓዝበት፡፡ ብቸኛዋን የሐቅ መንገድ ረዳቷ አላህ ነው፡፡ ከሐቅ፣ ከተውሒድ፣ ከሱና፣ ከመንሀጀ ሰለፍ ጎዳና ውጭ ያሉት ሁሉ የሚታገሉትም በሰይጣን መንገድ ላይ ነው፡፡ የሰይጣን መንገድ ደግሞ መቼም ቢሆን ድልን አይጎናፀፍም፡፡ ሁለት አገር ክስረት ነው፡፡ አማኞች እስከታገሱ በሐቅ ላይ እስከፀኑ ድረስ አላህ እንዳለው ሁለት አገር ድል ይቀምሳል፡፡
وَلِلَّهِ ٱلْعِزَّةُ وَلِرَسُولِهِۦ وَلِلْمُؤْمِنِينَ وَلَٰكِنَّ ٱلْمُنَٰفِقِينَ لَا يَعْلَمُونَ
«አሸናፊነትም ለአላህ፣ ለመልክተኛውና ለምእምናን ነው፡፡ ግን መናፍቃን አያውቁም፡፡
አልሐምዱሊላሂ ረቢል አለሚን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
3ቱ ታላላቅ አብዛኛው የካዳቸው እውነታዎች፡፡
በሐቅ ላይ መፅነት ነው፡፡
የአላህ ባሪያዎች ሆይ! ሐቅ በሰዎች አይለካም፡፡ ሰዎች በሐቅ ይላከሉ እንጂ፡፡አብዛኛው ሰው ብዙ ታላላቅ እውነታዎችን ይቃረናል፡፡ ይህ ማለት ግን ሐቅ ላይ ያሉ ሰዎች አብዛኛውን አይተው አቋማቸውን መቀየር አለባቸው ማለት አይደለም፡፡ አላህ መልክተኞቹን ሁሉ ከፀሐይ ብርሃን በላይ ፍንትው ያለውን የእሱን ብቸኛ ተመላኪነት እንዲያውጁና ከእርሱ ውጭ ከሚመለኩት እንዲያስጠነቅቁ ለየህዝቡ ልኳል፡፡ ግን ለመልክተኞቹ መልካምን መልስ የሰጠውና የተቀበላቸው በጣም ጥቂት ነው፡፡ መልክተኞቹ ግን ሰው ተቀበለም አልተቀበለም ከጌታቸው የተላኩበትን መልክት እስኪሞቱ ድረስ ይፋ አድርገዋል፡፡ መልክተኞቹን የተከተሉ በየዘመኑ ያሉ አማኞችም በቁጥር ጥቂት ቢሆኑም በሐቅ ላይ ፀንተዋል፡፡ እስቲ የሚከተሉትን ታላላቅ ሶስት እውነታዎች ልብ እንበል፡፡
1) አላህ እኛን የፈጠረን እሱን በብቸኝነት እንድናመልክ ነው፡፡ መፀሀፍትን ያወረደው፣ መልክተኞችን የላከው የሰው ልጆች የተውሒድን መልክት አውቀው፣ ጠንቅቀው ተረድተው፣ ተግብረው ወደ ጀነት እንዲገቡና ከእሳት እንዲጠበቁ ነው፡፡ እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ አብዛኛው ግን አልተቀበላቸውም፡፡ ካለመቀበልም አልፎ የሚከተሉትን አባባሎች እነዛ ሙሽሪኮች ተናገሩ
- قَالُوا۟ يَٰصَٰلِحُ قَدْ كُنتَ فِينَا مَرْجُوًّا قَبْلَ هَٰذَآ ۖ أَتَنْهَىٰنَآ أَن نَّعْبُدَ مَا يَعْبُدُ ءَابَآؤُنَا وَإِنَّنَا لَفِى شَكٍّ مِّمَّا تَدْعُونَآ إِلَيْهِ مُرِيبٍ
“ሷሊህ ሆይ! ከዚህ በፊት በእኛ ውስጥ (መሪ ልትሆን) በእርግጥ የምትከጅል ነበርክ፡፡ አባቶቻችን የሚገዙትን ከመገዛት ትከለክለናለህን? እኛም ወደርሱ ከምትጠራን ነገር በእርግጥ አወላዋይ በሆነ መጠራጠር ውስጥ ነን” አሉ፡፡
- وَعَجِبُوٓا۟ أَن جَآءَهُم مُّنذِرٌ مِّنْهُمْ ۖ وَقَالَ ٱلْكَٰفِرُونَ هَٰذَا سَٰحِرٌ كَذَّابٌ
ከእነርሱ የሆነ አስፈራሪም ስለ መጣላቸው ተደነቁ፡፡ ከሓዲዎቹም “ይህ ድግምተኛ (ጠንቋይ) ውሸታም ነው” አሉ፡፡
أَجَعَلَ ٱلْءَالِهَةَ إِلَٰهًا وَٰحِدًا ۖ إِنَّ هَٰذَا لَشَىْءٌ عُجَابٌ
“አማልክቶቹን አንድ አምላክ አደረጋቸውን? ይህ አስደናቂ ነገር ነው” (አሉ)፡፡
ነብዩ ሙሐመድ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) በአላህ ፍቃድ ከአሳማሚዉ የጀሀነም እሳት ለይተው ወደ ጀነት የሚገባበትን መንገድ ሲመክሯቸው የመካ አጋሪያን እሳቸውን እንዲህ ሲሉ ጠሯቸው
- “ቤተሰብን የሚበታትን፣ እብድ፣ ገጣሚ፣ ድግምተኛ……”
የተውሒድን እውነታ ማንም ቢቃወመው፣ አብዛኛው ባይከተለውም መልክተኞችና ተከታዬቻቸው ሁሌም ይለፉለታል፣ ይፀኑበታል፡፡ ነቃ እንበል የአላህ ባሪያዎች ሆይ! በሐቅ ላይ እንፅና፡፡
2) አላህ ነብዩን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) መታዘዝ አላህን እንደመታዘዝ ነው ብሎ ሲያበቃ፡፡ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የእኔን እና ቅኑን ፈለግ የተመሩ ምትኮቼን (አቡበክር፣ ኡመር፣ ኡስማን፣ አልይ) ሱና አደራ ተከተሉ፣ አዳዲስ በሃይማኖት ላይ ከተፈጠሩ መጤ ነገሮች ሁላ ራቁ ብለው ሲያበቁ፡፡ “ይህ የእኔ ኡመት 73 ቦታ ይከፋፈላል ሁሉም የእሳት ነው አንዷ ስትቀር” ብለው የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሲናገሩ ሰሃባዎች ጠየቁ “የቷ ናት ያቺ ብቸኛ ነጃ የምትወጣው መንገድ?” ተብለው ተጠየቁ፡፡ እሳቸውም “እኔና ሰሃባዎቼ ዛሬ ያለንባት መንገድ ናት” ሲሉ ተናገሩ፡፡ የሳቸው ሱና ብቸኛው የጀነት መንገድ እሱን የተቃረነ ሁሉ የእሳት መንገድ ሆኖ ሳለ፣ ዛሬ አብዛኛው አላህ ካዘነላቸው ጥቂቶች ውጭ ይህን እውነታ ተቃውመው የቢድኣና የጥመት ቡድኖችን አካሄድ ይሄዳሉ፡፡
ይህ ከመሆኑ ጋር ዛሬ ዛሬ የመልክተኛውን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሱና መከተል ብሎም መውሊድ የመሳሰሉትን ቢድኣዎች እንራቅ ማለት የሚከተሉትን ያስብላል
- ነብዩን የማይወዱ የነብዩ ጠላቶች፣
- ወሃቢዬች፣
- ቀብር ዚያራ ክልክል ነው የሚሉ ሰዎች መጥተዋል፣
- ዱኣ አይቻልም የሚሉ ሰዎች መጥተዋል፣
- ሰደቃ ክልክል ነው የሚሉ ሰዎች መጥተዋል፣
- ኋላ ቀሮች፣
- ደረቆች፣
- የሙስሊሙ ጉዳይ የማያሳስባቸው፣
- “መውሊድ አይለያየንም፣ መውሊድ ቅርንጫፍ ነው፣ መውሊድ አቂዳ አይደለም” ከዚህም አልፎ “መውሊድ” የሚል መፀሃፍ ፅፎ ቢድኣን ለማንገስ ሱናን ለማርከስ ብቅ ያለም አለ፡፡
- ጉዞ ወደ “አብሬት መውሊድ፣ ነጃሺ፣ ቃጥባሬ መውሊድ፣ አልከሶ መውሊድ፣ አሊ ጎንደር መውሊድ፣ ዳንግላ መውሊድ፣ ኑር ሁሴን…. ” አብዛኛዎቹ ቦታዎች በአላህ ላይ የሚጋራባቸው ናቸው፡፡
ምንም እንኳን አብዛኛው ሰው ይህን አስቀያሚ እርኩስ ቢድኣ ቢፈፅምም፣ ይህንን ተግባር አልፈፅምም የሚሉ ሰዎችን በመጥፎ ስም ቢጠራቸውም አማኞች በነብያችን ሱና ላይ ፀንተው ይሀው ቀጥ ብለዋል፡፡
3) አላህና መልክተኛው ለሙስሊም መሪ በመልካም እስካዘዝ ድረስ፣ ሰላትን እስከሰገዱ ድረስ ስሟቸው ታዘዟቸው ብለዋል፡፡ የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “መሪውን መምከር የፈለገ በድብቅ ይምከረው” ብለዋል፡፡ ደጋግ ቀደምቶቻች “አንድ ሰው ለሙስሊም መሪ ዱኣ ሲያደርግ ካየሀው እወቅ ይህ ሰው የሱና ሰው ነው፡፡ ሙስሊም መሪውን ሲራገም ካየሀው እወቅ ይህ ሰው የቢድኣ ሰው ነው፡፡” ብለዋል፡፡ የሙስሊም መሪን አለመታዘዝና እሱ ላይ አምፆ መውጣት ይሀው ተጨባጩ አረብ አገራት ላይ እንዳየነው አገርንና ክብርን ያጎድፋል፡፡ እውነታ ይህ ሆኖ ሳለ አብዛኛው ሙስሊም የተጠመደው መሪዎችን በመራገም፣ እነሱን በማዋረድ፡፡ ድንገት ይባል ይሆናል እነዚህ እውቀት ስለሌላቸው ነው፡፡ ነገር ግን አዋቂ የሚባሉት የመስጂድ ኢማሞች የኹጥባ ሚንበሮቻቸውን የሙስሊም መሪዎችን በመራገም ህዝብ እንዳይታዘዛቸው በማሳመፅ ላይ እና ፈተናን በመቀስቀስ ላይ ይገኛሉ፡፡ እውነተኛ የሱና ተከታዬች ግን አንድ የሙስሊም መሪ መጥፎ ሲሰራ ሲያዩ ይጠላሉ አይወዱትም፣ ካገኙት በድብቅ ይመክሩታል፣ አላህ እንዲያስተካክለው ዱኣ ያደርጉለታል፡፡ በነዚህ ሙስሊም መሪዎች ላይ ፋሲቅ ቢሆኑም አምፀውባቸው አይወጡም፡፡ ፈተናን ከማብረድ አኳያ ይታገሳሉ፡፡ የስሜት ተከታዬች እነዚህን ቁርኣንን፣ ሀዲስን የሰለፎችን አረዳድ አካሄዳቸው ያደረጉ ኡለማዎችንና አማኞችን በሚከተሉት አስፀያፊ ስሞች ይጠሯቸዋል፡፡
- “የቤተ መንግስት ፍርፋሪ ለቃቃሚዎች”፣
- “የዩሁዳ ቅጥረኞች”፣
- “መብታችንን እንዳይከበር የባለስልጣናትን እድሜ ለማራዘም የሚሰሩ”፣
- “ጃምያ፣ መድከሊያ” እና የመሳሰለውን

እውነታ ግን ከላይ ያሉትን ሶስታ ታላላቅ መርሆዎች (አላህን በብቸኝነት ማምለክ በእሱ ላይ ማንንም አለማጋራት፡፡ የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምን) ሱና መከተል ከቢድኣ ሁሉ መራቅ፡፡ ለሙስሊም ባለስልጣናት በመልካም እስካዘዙ ድረስ መስማትና መታዘዝ በእነሱም ላይ አምፆ አለመውጣት) አብዛኛው ሰው ቢቃረናቸውም ሐቅ የሚለካው በሰው አይደለምና በሐቅ ላይ መፅናት ግድ ይላል፡፡ ትእዛዙን ያዘዙት አላህና መልክተኛው ናቸውና፡፡

አላህ በሐቅ ላይ ከሚፀኑት ያድርገን፡፡ የአላህ ሰላትና ሰላም በመልክተኛው፣ በቤተሰቦቻቸው፣ በባልደረባዎቻቸውና ሃቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
በቁርኣን እንደማይጨፈረው፣ እንደማይጨበጨበው፣ እንደማይደነሰውና እንደማይፏጨው ሁሉ፣
በሰለዋትም አይጨፈርም፣ አይጨበጨብም፣ አይደነስም አይፏጭም፡፡
ሰለዋት ኢባዳ ነው፡፡ ኢባዳ ተውቂፍያ (አላህና መልክተኛው ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ባዘዙት መንገድ ብቻ የሚተገበር) ነው፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
የሳሎን ውስጥ ጭምብል ለባሽ ተቃውሞ ሰልፈኞች፡፡
حاكم غشوم خير من فتنة تدوم
وقال ابن مسعود رضي الله عنه
السعيد من وعظ بغيره
اللهم احفظ المملكة العربية السعودية وأهلها من مضلات الفتن
እንስቲ ተመልከቷቸው ወንድነት አጥተው በኢንተርኔት ላይ የተውሒድ አገር ሳውዲን ሊያምሱ የተዘጋጁ የቤት ውስጥ የሳሎን ውስጥ ኒቃብ ለባሽ ሰላማዊ ሰልፍ ወጪዎች፡፡ አላህ ከሸራቸው ይጠብቀን፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ሙስሊሞችን መሳሪያ ከያዙ መሪዎች ጋር እንዲጋፈጥ የሚቀሰቅሱት እንዲህ አይነት በቦታው ላይ የማይገኙ ፈሪዎች ወይንም ጭምብል ለባሾች ናቸው፡፡ መሪዎች እንዲስተካከሉ እኛ መጀመሪያ ስራችንን ከአላህም ከፍጡራን ጋር ያለንን ግንኙነት ማስተካከል ይጠበቅብናል፡፡ የጠላትን አላማ በማስፈፀም በኢስላም የሌለን የተቃውሞ ሰልፍ “መብትን ማስከበር” በሚል ሽፋን ቀረች የተባለችውን የሙስሊሞች ቂብላ የሚገኝባት አገር ሳውዲ ላይም ሰልፍ ካልተወጣ እያሉ የሚቀሰቅሱ አሉ፡፡ የኢስላም ጠላት የሆኑት የሁዳዎች እነዚህ ሙስሊም አገራት ላይ በመብት ስም ተቃውሞ ሰልፍ እንዲወጣና ብጥብጥ እንዲፈጠር ከዛም እነዚህ ሙስሊም አገራት ጉልበታቸው ሲደክም እነሱ የመስፋፋት አላማቸውን ያስፈፅማሉ፡፡
የዚህ ኡለማ ፈርጦች እንዲህ ሲሉ ይመክሩናል፡፡
ከሚቀጥል (ከማይቋረጥ) ፈተና በጣም በዳይ መሪ ይሻላል፡፡
አብደላህ ኢብን መስኡድ (ረድየላሁ አንሁ) “እድለኛ ማለት በሌሎች የተመከረ ነው፡፡” ይላሉ፡፡
አላህ ሆይ! መምለከተል አረቢያ ሰኡድያን መሪዎችን ህዝቿንም የአለም ሙስሊሞችንም ከአጥማሚ ከሆኑ ፈተናዎች ጠብቀን፡፡
አላህ ሆይ! አለም ላይ ያሉ ሙስሊም መሪዎችንና ህዝቦችን አስተካክለን፡፡ አንተ ለምትፈልገውም መልካም ነገር ምራን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
የሳውዲ መሪዎች አላህ ይጠብቃቸው፡፡
ሳውዲ ላይ ተቃውሞ ሰልፍ የሚሉ ሰዎች እውነት ለኢስላም አስበው ነው?
የሳውዲ መሪዎች አላህ ከውስጥም ከውጭም ጠላት ይጠብቃቸውና አላህ በሚከተለው አንቀፅ ያዘዘውን ትዕዛዝ ባለንበት ዘመን ይተገብራሉ
ٱلَّذِينَ إِن مَّكَّنَّٰهُمْ فِى ٱلْأَرْضِ أَقَامُوا۟ ٱلصَّلَوٰةَ وَءَاتَوُا۟ ٱلزَّكَوٰةَ وَأَمَرُوا۟ بِٱلْمَعْرُوفِ وَنَهَوْا۟ عَنِ ٱلْمُنكَرِ ۗ وَلِلَّهِ عَٰقِبَةُ ٱلْأُمُورِ
(እነርሱም) እነዚያ በምድር ላይ ብናስመቻቸው (ስልጣን ሲሰጣቸው) ሶላትን እንደሚገባ የሚያስተካክሉ (ሰላትን እራሳቸውም የሚሰግዱና እንዲሰገድ የሚያደርጉ)፣ ዘካንም የሚሰጡ፣ በደግ ነገርም የሚያዝዙ፣ ከመጥፎ ነገርም የሚከለክሉ ናቸው፡፡ የነገሮቹም ሁሉ መጨረሻ ወደ አላህ ነው፡፡

ቆይ ያልገባኝ እነዚህ የሳውዲ መሪዎች እራሳቸውም ይሰግዳሉ፣ ህዝባቸውንም የአላህን ትእዛዝ በመፈፀም በሰላት ሰኣት ንግድና ስራ ቆሞ እንዲሰግድ ያዛሉ፡፡ እንደነ ሰልማነል አውዳ ያሉ ኸዋሪጆች ምን ይሆን የሚመኙት? ሰልማነል አውዳና አምሳያዎቹ የዚህች አገር ሰላም መሆን እና በአንድ ሙስሊም መሪ ስር አንድ መሆናቸውን ለመበተን ቀን ከለሊት እየሰሩ ናቸው፡፡
አላህ ለግሶኝ ሐጅ በሄድኩበት የሳውዲ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የሚማሩበትን ካሪኩለም አይቼ በጣም ተገረምኩ፡፡ ተውሒድ፣ ሀዲስ፣ ፊቂህ እና የመሳሰለው እንደ ትምህርት ለተማሪዎች ከአመት እስከ አመት ይሰጣል፡፡
ውስጡ ያለውንም ስመለከት ወላሂ ይህችን አገር የጠበቃት የወታደሯ ብዛት ሳይሆን አዛኙ አላህ በእሱ መንገድ ላይ እየታገሉ ስለሆነ አግዟቸው መሆኑን ተረዳሁ፡፡
ሃጅና ኡምራ ላይ የሚያስተናግዱት ወታደሮችም “አላህ ይውደድህ”፣ “አላህ አፊያ ያድርግህ” እያሉ ሰዉን ያስተናግዳሉ፡፡
ሌላው አስገራሚ ነገር “የሳውዲ መንግስት ኡለማዎችን ያስራል” እየተባለ ይቀጠፍበታል፡፡
ኡለማ ማለት የሙስሊም አገርን ለማመስ አመፅን የሚቀሰቅስ ነውን? በፍፁም፡፡
ለምሳሌ ኻሊድ አል-ራሺድ የተባለው ግለሰብ የታሰረው “ሰዎችን ተቃውሞ ሰልፍ” ሲቀሰቅስ ነው፡፡ ተቃውሞ ሰልፍ የሙስሊሞች መንገድ አይደለም፡፡ ሙስሊሞች የሙስሊም መሪዎች ላይ ጉድለትና መጥፎ ነገር ቢያዩ ካገኟቸው በድብቅ ይመክሯቸዋል፡፡ ካላገኟቸው ዱኣ ያደርጉላቸዋል፡፡ ከዛ ውጭ ሰልማነል አውዳ፣ ኻሊድ ራሺድ፣ ሙሐመድ አሪፊና ሌሎችም የሳውዲን ወጣት በሙስሊም መሪው ላይ እንዲያምፅ ብሎም እነሱ ልጆቻቸውን በሰላም አቅፈው ተቀምጠው የሙስሊሙን ልጅ ሶሪያና ሌሎች ቦታዎች ላይ ቀስቅሰው ይልኩታል፡፡ ቢታሰሩም የሚታሰሩት በሚሰሩት መጥፎ በደል ነው፡፡
እነ አቡበክር አሕመድ የታሰሩት እራሱ የሰርግ ቤት አዳራሽ ያለ ፍቃድ ለሌላ ዝግጅት ስላዋሉት ነው፡፡ እውነት የሳውዲ መንግስት ሰዎች ዳእዋ በማድረጋቸው የሚያስር ቢሆን ኖሮ ብርቅየውን ኢትዬጵያዊ አሊም ሸይኽ ሙሐመድ አሊ አደም (ሀፊዘሁላህ) ባሰራቸው ነበር፡፡ ነገር ግን አደለም ሊያስራቸው መካ ሀረም ላይ ወንበር ሰጥቶ እንዲያስተምሩ አደረጋቸው፡፡
ስለዚህ እባካችሁ የውሸት ወሬን እየሰማችሁ የሙስሊም አገር የሆነችዋን ሳውዲ መሪዎች ለማጥላላት አንንደርደር፡፡ ወላሂ ሳውዲ የተውሒድ ባንዲራ ከፍ ብሎ የሚውለበለብባት አገር ናት፡፡ ይህ ሲባል ጉድለት የለባቸውም ማለት አይደለም፡፡ አላህ ይጠብቃት፡፡
አላህ ሁልን ሙስሊም ሀገራት መሪንም ተመሪንም ያስተካክልልን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
ትላንት ቀስቃሽ! ዛሬ አስለቃሽ! (ኢኽዋን- የዲን ነጋዴዎች!)
1. ኢኽዋኖች ዘንድ የአሜሪካ የጦር ካምፕ በሳዑዲ መኖሩ ኢጅቲሃድ የማያስተናግድ፣ በቀላል የማይታይ ከባድ ወንጀል ነው። ትልቅ የአሜሪካ የጦር ካምፕ በኳታር መኖሩ ግን ኢኸዋን ሰፈር ከነጭራሹም አይነሳም። አንተ ጭንቅላትህን ለኢኽዋን ያስረከብክ ተላላ ሆይ! እስኪ “ለምን?” በላቸውና ሲተጣጠፉ እያየህ ታዘባቸው።
2. አንድ የሳዑዲ ባለስልጣን ከእስራኤል ባለስልጣን ጋር መገናኘቱ በሙስሊሙ ኡማ ላይ ሸፍጥ መፈፀም ነው፣ የሙስሊሙን ጉዳይ አሳልፎ መሸጥ። ኳታርና ቱርክ ከእስራኤል ጋር ያላቸው ግልፅ የሆነ ግንኙነት ግን ህጋዊ ፖለቲካ እና የበሰለ አካሄድ ነው። ቱርክ ፍልስጤማውያንን ከሚያርደው የእስራኤል ጦር ጋር ይፋ የሆነ በተዋጊ ጄቶች ልምምድ ማድረጓ ብስለት ነው፣ ብቃት። ምክንያቱም እየተፈፀመ ያለው በቱርክ ነው፣ በኤርዶጋን። የሚፈፀመው በሳዑዲ ቢሆንስ? አይንህን ክፈት!! እስከመቼ በዲን ነጋዴዎች ትሸወዳለህ?
3. ግብፅና ዮርዳኖስ ከእስራኤል ጋር የንግግድ ልውውጥ ማድረጋቸው ክህደት ነው፣ ቅጥረኝነት። የንግድ ልውውጡ በቱርክና በእስራኤል መካከል ሲሆን ግን ይሄ ኖርማል ነገር ነው። “ነብዩስ ﷺ ከአይሁድ ጋር በገንዘብ ጉዳይ አልተዋዋሉምን?” ይባላል። በአንድ ጉዳይ የተለያየ ሚዛን፡፡
4. ሙስሊሞችን በመሪዎቻቸው ላይ ማነሳሳትና መቀስቀስ የንቃተ ህሊና ከፍታ ነው፣ ሙስሊሙን ከእንቅልፉ መቀስቀስ። ተቃውሞው በሙርሲና በኤርዶጋን ላይ ሲሆን ግን ሐራም ነው፣ ክህደት ነው፣ የምእራብ እጅ ያለበት ነው፣ የዐረብ መሪዎች እጅ ያለበት ነው። ከዚያም በመሪ ላይ ማመፅ እንደማይፈቀድ የሚጠቁሙ ሐዲሦችን ይዘረዝራሉ። ፊትና ሲያራግቡ ጊዜ ከአገልግሎት መስጫ ውጭ ያደረጓቸውን ሐዲሦች ከኢኽዋን ለመከላከል ሲሆን ግን ያለምንም ሃፍረት ያጣቅሷቸዋል።
5. የሳዑዲ መሪዎች አጅነቢ ሴት ሲጨብጡ አገር ያቃጥላሉ። ፎቶውን ያሰራጫሉ፡፡ እነ ቀርዷዊ፣ ሙርሲ፣ … አጀንቢ ሴት ሲጨብጡ፣ ከዚህም ያለፈ ሲፈፅሙ ግን ባላየ ያልፋሉ። እንዳየሩ ፀባይ የሚለዋወጡ ፖለቲከኞች!
6. ሙስሊም መሪዎችን “ሸሪዐን አልተገበሩም” እያሉ ያብጠለጥላሉ፣ በነሱም ላይ አመፅ ያነሳሳሉ፣ ያከፍራሉ። የኢኽዋን አውራዎች “ሃይማኖታዊ መንግስት አንመሰርትም” እያሉ ባደባባይ ሲናገሩ ግን ስለነሱ ትንፍሽ አይሉም። ከፊሉማ አይኑን ጨፍኖ ሊያስተባብልላቸው ይሞክራል፡፡
7. ሳዑዲ የኢራንን ሴራ ለመቀነስና ለመሰል አላማዎች ሙቅተዳ ሶደርን ስትጋብዝ በአህሉ ሱንና ላይ ማሴር፣ ለኢራን መንበርከክ ተብሎ ይራገባል። ልክ ኢኽዋን ሺዐን እንደሚጠላና ለሱንና እንደሚቆረቆር፡፡ ቱርክ ከኢራን ጋር ግንኙነቷን ማጠናከሯ፣ የዒራቅ ኢኽዋኖች ለጠርዘኛው ሺዐ ኑሪ አልማሊኪ በፓርላማ ድምፅ መስጠታቸው፣ የየመን ኢኽዋኖች በሑሢዮች ላይ ዝምታን መምረጣቸው፣ አርባ ሺህ ጦር አለኝ እያለ በከንቱ ሲኮፈስ የነበረው ዘንዳኒ ሑሢዮችን አለመጋፈጡ፣ የግብፁ ኢኽዋን መሪ ሳዑዲ ሑሢዮችን ከማጥቃት እንድትቆም መጠየቁ፣ በነቀርዷዊ “የዓለም ዑለማ ም/ቤት” ውስጥ ምክትሉ ሺዐ መሆኑ፣ ኢኽዋኖች ከዘመነ ሐሰን አልበንና ጀምሮ ከሺዐ ጋር የጋራ ቢሮ ከፍተው ለመቀራረብ መንቀሳቀሳቸው፣ ኳታር ከኢራን ጋር ግንኙነት መመስረቷ፣ ኳታር ለሺዐው ሒዝበላህ እና ለዒራቁ ሐሽደ አሽሸዕቢ የሺዐ ቡድኖች እርዳታ ማድረጓ፣ ሐማስ ከኢራን ጋር ጠንካራ ግንኙነት መመስረቱ፣ … ይሄ ሁሉ ኢኽዋኖች ሰፈር ሆደ ሰፊነት፣ የፖለቲካ ብስለት አለያም ደግሞ ሊነሳም የማይገባው ተራ ነገር ነው። ንቃ! የነዚህ ተለዋዋጭ ነጋዴዎች መጫወቻ አትሁን!!
8. ኢማራት ቤተ ክርስቲያን እንዲገነባ ስትፈቅድ ኢኽዋኖች ሰፈር በከባዱ ተራገበ፡፡ እስልምናቸውን ሳይቀር ጥያቄ ውስጥ ከተቱት። በባህረ ሰላጤው ክልል ትልቁ ቤተ ክርስቲያን ኳታር ደውሐ ውስጥ ሲገነባ ግን ኢኽዋኖች ሰፈር ኮሽታ አልተሰማም። ለምን?! ኢኽዋን! በአንድ እራስ ሺ ምላስ!
9. ንጉሳዊ ስርኣት ሳዑዲን ለማብጠልጠል ሲሆን በሰፊው ይኮነናል፡፡ የትላንት ኦቶማን ቱርኮችን፣ የዛሬ ኳታሮችን ንጉሳዊ ስርኣት ግን ጫፉንም አይነኩትም፡፡ ጥላቸው ከስርኣቱ እንዳይመስልህ! ሌላ ነው፡፡
10. ሳዑዲ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ የማያንማር ሙስሊሞች በሃገሯ የመኖሪያ ፈቃድ ስትሰጥ፣ በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር እርዳታ ስታደርግ፣ ሙሉ ወጪያቸውን ለመሸከም ከማንግላዴሽ ጋር ስትደራደር፣ ከ70 አመታት በላይ ጉዳያቸውን ጉዳዩዋ አድርጋ ከጎናቸው ስትቆም፣… ኢኽዋኖች ሰፈር ቁም ነገር ሆኖ ተወስቶ አያውቅም። ለኤርዶጋን ሲሆን ግን “ወደ በርማ ሰራዊት አስገባ” እያሉ በጠራራ ፀሐይ ይዋሻሉ። የሐሰት ምስል እያባዙ ያሰራጫሉ። ሁሉም ግን አይን ያወጣ ቅጥፈት ነው፡፡ በነዚህ በቀቀኖች የተሸወድክ ወንድሜ ሆይ! እስኪ ስለ በርማ ሙስሊሞች ካወቅክ ምን ያክል ጊዜ ሆኖሃል። አጭር ጊዜ ነው። ምክንያቱ ምን ይመስልሃል?! ለምንስ ከ70 አመታት በላይ ከጎናቸው የሆነችውን አገር ሚና እንድታውቅ አልተደረግክም?! አትጠራጠር! ከሙስሊሞች ጉዳይ በላይ የቡድናቸው ጉዳይ የሚያስጨንቃቸው ደጋሚዎች ፕሮፓጋንዳ ሰለባ ሆነሃል።
11. ሳዑዲ ሶሪያ ውስጥ በሻርን ከሚዋጉ ቡድኖች ለዘብተኛ የሆነውን መርዳቷ፣ በተደጋጋሚ ሪያድ ድረስ እየጠራች ልዩነታቸውን እንዲያስወግዱ መሞከሯ፣ የሶሪያ ስደተኞችን መቀበሏ፣ በዮርዳኖስ የሶሪያ ስደተኞችን ሰፋፊ ፕሮጀክት ዘርግታ ማስተናገዷ፣ በአለም አቀፍ መድረክ ብዙ ጥረቶችን ማድረጓ ኢኽዋኖች ሰፈር ቁም ነገር ሆኖ አይወሳም። እንዲያውም የሶሪያን ህዝብ እንደከዳች ተደርጎ በተደጋጋሚ ይራገባል። ወደ ቱርክና ኳታር ግን ተመሳሳይ ውንጀላ አይሰነዝሩም። ለምን?! ኢኽዋንኛ ቆሻሻ ስሌት!! ሐለብ ላይ ጭፍጨፋ ሲፈፀም በጥቂት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ጦር ያሰፈረው የቱርክ መንግስት እርምጃ ባለመውሰዱ ሳይወቅሱ ከሶሪያ ጋር የጋራ ድንበር የሌላትና ጎረቤት ያልሆነችው ሳዑዲን ግን ጣልቃ ባለመግባቷ ይወቅሳሉ። ከማገናዘብ የፀዳ ህብረት!!
12. ሳዑዲ ውስጥ አንድ ቆሻሻ አርቲስት ሲዘፍን በተለየ መልኩ ይራገባል። ቀርዷዊ ዘፈን ሲፈቅድ፣ 3ኛው የኢኽዋን ሙርሺድ ዑመር አትቲልሚሳኒ የፈረንጅ ዳንስ እየከፈለ መማሩ፣ ለሲኒማ ብሎ ጁሙዐ ሶላት ትቶ ከሲኒማ ቤቱ ጥግ ላይ ዙህርና ዐስርን አሳጥሮ ባንድ ላይ መስገዱ፣ በጋዜጣቸው ላይ ወደ “ኢስላማዊ” ሙዚቃ መጣራታቸው ይሄ ሁሉ ተራ ነገር ነው። ምናልባት የንቃተ ህሊና ከፍታ፣ የአስተሳሰብ አድማስ ስፋት ካልተደረገ። የአለም ዋንጫን ለማዘጋጀት የተመረጠችው ኳታርን በተመለከተስ ምን ሰማችሁ? በዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ ዝግጅት ውስጥ ብዙ የሙዚቃና ጭፈራ ድግስ የለምን? ከዚህም በላይ አስካሪ መጠጥ ለማስገባት ግልፅ ስምምነት የለምን? ግና ጉዳዩ የኳታር ነው። ኢኽዋንኛ መነፅር ደግሞ የቡድኑ ጥፋቶችን ተራራም ቢያካክሉ ከነጭራሹ አያሳይም።
13. ሳዑዲ በሃገሯ ውስጥ ፊትና የሚያራግቡ ተንኮለኞችን ስታስር “ዑለማዎች እስር ቤት ናቸው” ይባላል። ልክ እነ ፈውዛን፣ እነ ሉሐይዳን፣ እነ ኣሊ ሸይኽ የታሰሩ ይመስል። ቱርክ ከመፈንቅለ መንግስቱ ሙከራ በኋላ ከዐብደላህ ጎለን ጋር ንክኪ አላቸው በሚል 3 የዜና ወኪሎችን፣ 23 የሬዲዮ ጣቢያዎችን፣ 18 ቴሌቪዥን ጣቢያዎችን፣ 15 መፅሔቶችን፣ 45 ጋዜጦችን፣ 15 ዩኒቨርሲቲዎችን፣ 35 ሆስፒታሎችን፣ 104 የወቅፍ ተቋሞችን፣ 1000 መድረሳዎችን፣ 1225 የበጎ አድራጎት ተቋማትን፣ … ስትዘጋ፣ 32 ሺህ ህዝብ ስታስር፣ 40 ሺህ ህዝብ ላይ ምርመራ ስታደርግ፣ ከ100 በላይ ጋዜጠኞችና የማስታወቂያ ሰዎ
ችን ስታስር፣ 60 ሺህ ህዝብ ከመንግስት ስራዎች ብቻ ስታፈናቅል፣ ከ93 ሺህ በላይ ህዝብ አጠቃላይ ከስራ ሲፈናቀል ኢኽዋኖች ሰፈር በመጥፎ አልተራገበም። “ልክ አለፈም” አልተባለም። የሚደንቀው በመፈንቅለ መንግስቱ ሙከራ የተወነጀለው ዐብደላህ ጎለንም በነሰልማነል ዐውዳ የሚወደስ ሰው መሆኑ ነው። በብዙ ካርድ የሚቆምሩ ጉደኛ ፍጡሮች! በነገራችን ላይ እዚሁ ሃገራችን ውስጥ ጭምር የነጎለን ተቋም ተነጥቆ ለካፊር ተሰጥቷል፡፡
14. የሱንና ዑለማዎች ሺርክ ላይ ጠንካራ አቋም ሲይዙ ጠርዘኝነት፣ ተክፊር ተደርጎ ይራገባል። እነ ሰይድ ቁጥብ በጅምላ ሙስሊሙን ኡማ ሲያከፍሩ ግን በተጋነነ መልኩ እየተወደሱ ወጣቱን ለመበከል ስራዎቻቸው ይሰራጫሉ። ሰላማዊ ህዝብ መሀል የሚደርሱ ፍንዳታዎችን በደማቅ ብእር እየፃፉ ህዝብ ይበክላሉ፡፡ ተንኮላቸውን የሚያጋልጧቸው ዑለማዎችን በጠርዘኝነት ይፈርጃሉ፡፡ እንደ ሰይድ ቁጥብ፣ ኡሳማ ቢን ላደን፣ አይመን አዝዘዋሂሪ፣ አቡ ሙስዐብ አዝዘርቃዊ፣ ሱለይማን አልዒልዋን ያሉ ጠርዘኞችን ግን እያስተዋወቁ የጠርዘኝነት ተውሳክን ወደ ህዝብ ያሰራጫሉ፡፡
15. በሳዑዲ የሹራ ምክር ቤት ውስጥ ሒጃባቸውን የጠበቁ ሴቶች ቢገቡ ኢኽዋንና ሮቦቶቻቸው ዘንድ ሸሪዐን የማፍረስ ጥንስስ አካል ተብሎ ተራገበ። በቱኒዚያ ፀጉራቸው የተንጨባረሩ እርቃን ቀረሽ የኢኽዋን ሴት ተወካዮች ፓርላማ ውስጥ ሲገቡ፣ ከዚህም አልፎ “ሸሪዐ እንዳይተገበር እንሰጋለን” እያሉ በሚዲያ የኩፍር ቃል ሲናገሩ ኢኽዋን ሰፈር ኮሽታ ድምፅ አልተሰማም። ምክንያቱስ? ጥፋቱ የኢኽዋን ቡድን መሆኑ ብቻ ነው። አለቀ።
16. ሳዑዲ በአሜሪካ ጦር መታገዟ ዛሬም ድረስ ያልተረሳ ትልቅ ክህደት ነው። ኢኽዋኖች በሊቢያ፣ በሶሪያ፣ በግብፅ፣… በካፊር ለመታገዝ ሲወተውቱና ሲታገዙ ግን ማንም እንደጥፋት አይቆጥረውም። ምክንያቱም ጉዳዩ የኢኽዋኖች ነውና!!
17. የሱንና ዐሊሞች በመሪ ላይ ማመፅን ሲከለክሉ “ቅጥረኛ”፣ “የቤተ መንግስት ፍርፋሪ ለቃቃሚ” ይባላሉ። እነ ቀርዷዊ፣ እነ ዐሪፊ፣… ከነጋዳፊ ጋር፣ ከነ በሻረል አሰድ ጋር፣… ሲከንፉ ግን “ለሙስሊሙ ጥቅም እየተወያዩ ነው” ይባላል። ዑለማዎች በሳዑዲ የተቃውሞ ሰልፍ የሚጠሩ ጋጠ ወጦችን ሲቃወሙ በኢኽዋን ዋልጌዎች ይብጠለጠላሉ፡፡ ሰልፉን እነ ዐሪፊ፣ እነ ቀርኒ ሲቃወሙት ግን በንፍቅና በአሽከርነት አይወረፉም፡፡
18. የሳዑዲ መሪዎች እነ ሸይኽ ፈውዛንን፣ እነ ሸይኽ ረቢዕን ሲዘይሩ፣ ሲያሳክሙ “ዐሊሞቹ ወንበራቸውን ስለሚጠብቁላቸው ነው” ይባላል። ቀርኒ ፊሊፒን ላይ አደጋ ደርሶበት የሳዑዲ መንግስት ልዩ ሄሊኮፕተር አዞ አስመጥቶ ሲያሳክመው ግን የቀርኒን ታላቅነት፣ ወሳኝነት ነው የሚያሳየው። አጭበርባሪ ሰፋሪዎች!!
19. የሱንና ዑለማዎች ከዘመኑ ቆሻሻ ፖለቲካ ሲያስጠነቅቁ “ኋላ ቀርነት”፣ “የንቃተ ህሊና ማነስ” ነው። እነ ቀርኒ ይህንኑ ፖለቲካ በከባድ ቃላት ክፉኛ ሲኮንኑ ግን “ቅጥረኛ”፣ “ፊቅሁል ዋቂዕ ያልገባቸው” ተብለው አይኮነኑም። ምክንያቱም የኢኽዋን ማሕፀን ያገናኛቸዋልና።
20. ኢኽዋኖች አመፅ እየቀሰቀሱ የሙስሊም ሃገራትን አፈራረሱ፡፡ ጋዳፊን “ግደሉት! ደሙ በኔ ጫንቃ ላይ ነው” እያሉ እነ ቀርዷዊ ቀሰቀሱ፡፡ ዛሬ ግን ብዙ ኢኽዋኖች “ነጮች ጋዳፊን ጣሉት” እያሉ ይጮሃሉ፡፡ ትላንት ቀስቃሽ! ዛሬ አስለቃሽ!! ለምን እንደሆነ ታውቃለህ? የነሱን ፊክራ የሚያራምድ ሰው ካልነገሰ በምንም መልኩ አይረኩም፡፡ ሑስኒ ሙባረክን የተቃወሙት በሸሪዐ ስላላስተዳደረ እንዳይመስልህ፡፡ እነሱም መጥተው በሸሪዐ አላስተዳደሩም፡፡ ዛሬም በእጃቸው ባሉ ሃገራት የሸሪዐ ህግ የለም፡፡ እንዲያውም በሰው ሰራሽ ህግ እንጂ በሸሪዐ እንደማያስተዳድሩ ደጋግመው ተናግረዋል፡፡ የሚፈልጉት ስልጣን በነሱ እጅ እንዲሆን እንጂ የሸሪዐ ህግ እንዲዘረጋ አይደለም፡፡ ስልጣኑ በነሱ እጅ ከሆነ መሪያቸው ልክ እንደ አሕባሽ “አላህ የትም የለም” ቢልም፣ “የቀብር አምልኮ ውስጥ ቢዘፈቅም”፣ ሸሪዐን የሚነኩ ፀያፍ ውሳኔዎችን ቢያሳልፍም፣ … “የዘመኑ ኸሊፋ”፣ “ብቸኛው የሙስሊሞች መሪ”፣ “የዘመኑ ዑመር ኢብኑል ኸጣብ” እየተባለ ይሞካሻል፡፡ ጆሮ ከሰጧቸው የተራራቀ ወሬ ቢያወሩም አያሳፍራቸውም፡፡ እንዳሻቸው የሚቃረን ወሬ ቢያወሩም ሳያገናዝብ የሚውጥ ተከታይ እንዳፈሩ እርግጠኞች ናቸውና፡፡ እኔ እምልህ አንተ ከነዚህ ጭፍን ተከታዮቻቸው ውስጥ ከመሆን ተርፈሃልን?
21. ኡማውን የሚያከፍሩ፣ ሙዚቃን የሚፈቅዱ፣ ወደ ኩርና ሺርክ የሚጣሩ፣ ነብዩ ﷺ ስለደጃል መምጣት የተናገሩት ስህተት ነው የሚሉ፣ ሐዲሠ አዝዙባብን የሚያስተባብሉ፣ ወዘተ አውራዎቻቸው ጥመቶቻቸው ሲጋለጡ “ዑለማዎችን አትሙ”፣ “የህዝቡን ህብረት አትናዱ”፣ “ዓሊም አትሳደቡ” ይላሉ፡፡ እነሱ ግን ይህን በሚሉበት አንደበታቸው የሱንና ዑለማዎችን “የአንባገነን ቅጥረኞች”፣ “የቤተ መንግስት ፍርፋሪ ለቃቃሚዎች”፣ “የቱጃር አሽከሮች”፣… እያሉ ይወርፋሉ፡፡ “ጃሚያ” “መድኸሊያ” እያሉ የቡድን ታፔላ ይለጥፋሉ፡፡ ስለዑለማእ ክብር ሲጮሁ እውነታቸውን ከመሰለህ ወይ ተደግሞብሃል፡፡ ካልሆነ ቶሎ የማይሞቅህ እርጥብ ነገር ነህ ማለት ነው፡፡
22. ያለአንድ ተጨባጭ ማስረጃ የሳዑዲ መሪዎችን በሐሰት የስውሩ ማሱንያ (ፍሪ ማሰን) ማህበር አባላት እንደሆኑ ይወነጅላሉ፡፡ በራሳቸው መሪዎች ምስክርነት ከፊል የኢኽዋን አመራሮች የማሱኒያ አባል መሆናቸውን ግን ከነጭራሹ አይዘክሩትም፡፡ እንዲያውም ከፊሎቹ አይናቸውን በጨው አጥበው ይክዳሉ፡፡ ቀጥፎ አደር ፖለቲከኞች!!
23. ከሱንና ዑለማዎች ወይም ከሳዑዲ ፖለቲከኞች ወጣ ያለ የሚመስላቸው ንግግር ሲያገኙ ያለምንም ግንዛቤና መረጋጋት ያራግባሉ፡፡ ከኢኽዋኖች ወይም ከኢኽዋን ዘመም አካላት አስደንጋጭ ቃላት ሲወጡ ግን ዝምታን ይመርጣሉ፡፡ ለምሳሌ ያክል ቀርዷዊና ሙርሲ በኩፍር ላይ የሞቱ ጳጳሶችን አላህ እንዲምራቸው ዱዓ ማድረጋቸው፣ መውዱዲ ነብዩ ﷺ ስለደጃል የተናገሩት ስህተት ነው ማለቱ፣ ሙርሲ የእስራኤሉን ሰው በላ ኔታንያሁን “ታላቁ ወዳጃችን፡፡ እኛና አንተ በአንድ ጀልባ ላይ ነን” ማለቱ፣ ወዘተ ጥቂት ምሳሌዎች ናቸው፡፡
24. የሳዑዲ መሪዎች ለተውሒድ እና ለሱንና ድጋፍ ሲሰጡ “ስልጣናቸውን ለመጠበቅ ነው” ይላሉ፡፡ እነሱ ግን ተራራ የማይችላቸው ቅጥፈቶችን በዲን ስም እየፈፀሙ ሙስሊሙን ኡማ ወደ እሳት በመማገድ ለቡድናዊ አላማቸው ይሰራሉ፡፡ አንዱ በሶሪያ መላእክት ከታጋዮች ጋር ሆነው እንደሚዋጉ ይነዛል፡፡ “መላእክቱ” ግን እስካሁን ድረስ በሻርን አላሸነፉትም፡፡ አንዱ “በሙርሲ ወደ ስልጣን መመለስ ላይ መጠራጠር በአላህ መኖር ላይ እንደመጠራጠር ነው” ይላል፡፡ አንዱ አላህን ከኢኽዋኖች ሰልፍ ውስጥ አየሁት ይላል፡፡ አንዱ ቅልቅልና ዛዛታ ባለበት በራቢዐ አደባባይ በተካሄደው የኢኽዋኖች አድማ ላይ መገኘት በረመዳን የመጨረሻዎቹ አስር ቀናት ላይ ኢዕቲካፍ ከማድረግ የበለጠ ነው ይላል፡፡ አንዱ በራቢዐ አደባባይ ጂብሪል ወርዶ “ፅኑ” እያላቸው እንደሆነ ሲናገር ነበር፡፡ አንዱ በራቢዐ መድረክ ላይ ሆኖ ለሰልፈኞቹ “አላህ መላእክቱ ላይ ይኮራባችኋል” ሲል ነበር፡፡ አንዱ በሲትቲን አደባባይ አድማ ማድረግ ከሐጅና ከዑምራ፣ ዐረፋ ላይ ከመቆም ይበልጣል ሲል ነበር፡፡ አንዱ መሪያቸው የኤድስና የኮሮናን መድሃኒት አገኘሁ ብሎ በኛ ሃገር ሳይቀር ጋዜጣ ላይ አራግበውለት ነበር፡፡ ተከታታይ ምናብ! አንዱ በሻርን ድል አድርገን ቀጣዩን ጁሙዐ ደማስቆ እንሰግዳለን ብሎ ፎክሮ ነበር፡፡ ዛሬ ግን ዜግነቱን ተነጥቆ ከኩዌት ተባሮ ጁሙዐን በኳታር እየሰገደ ነው፡፡
25. ሳዑ
ዲን ዋሽተው ጭምር የሚያብጠለጥሉት ስሜታውያን የነብዩን ﷺ ኸሊፋዎችን፣ ሚስቶችንና ባጠቃላይ ሶሐቦችን እስከማክፈር በደረሰ መልኩ የሚያብጠለጥሉትን፣ የሐዲሥ ኪታቦችን የማይቀበሉትን፣ ሱንኒዎችን የሚጨፈጭፉትን፣ ለአይሁድ ቤተ አምልኮ እየፈቀዱ ለሱንኒዎች መስጂድ ከመስራት የሚከለክሉትን፣ ከኢስላም በብዙ ርቀት ላይ የሚገኙትን ኢራኖችን ግን ምንም ሲሏቸው አትሰማም፡፡ እንዲያውም ከነሱ ጋር ያለን ልዩነት ቀላል ነው ብለው ሲቀራረቡ ታያቸዋለህ፡፡ “ለምን?” በልማ ወንድሜ! ስሜታውያኑ በስሜት የተመላ መልስ ሲሰጡ ትመለከታለህ፡፡ ግን እስከጥግ ተከተላቸው፡፡ እስኪ ኢራን ውስጥ የሸሪዐ ህግ አለ? ሶሐቦችን ያከብራሉን፣ ሱንናን ያግዛሉን፣ ከሚሊዮን በላይ ሱንኒዮች ባሉባት የኢራን ዋና ከተማ ቴህራን ውስጥቡኻሪ ሙስሊም ከነሱ ዘንድ ዋጋ አላቸውን፣ የሙትዐህ (ሲርሪያ) ኒካሕ አየፈቅዱምን? ውሸት (ተቅያ) የዲናቸው አካል አይደለምን? በሃገሪቱ ውስጥ ለዑመር ገዳይ መታሰቢያ አልተሰራምን? ገና ከመግቢያው ቀደምት የኢስላም ኸሊፋዎችን የሚያወግዝ እርግማን አልፃፉበትምን? ይሄ ሁሉ ጉድ ያለባትን ሃገር አልፈው ከሳዑዲ ጋር መፋጠጣቸው ለምን ይመስልሃል? አስር ኢኽዋኖችን ለየብቻ ጠይቃቸው፡፡ አስራ አንድ አይነት መልስ ታገኛለህ፡፡ ጉዳቸው ተዘርዝሮ የማያልቅ አስገራሚ ፍጡሮች!!
(ኢብኑ ሙነወር፣ መስከረም 10/2010)
Forwarded from Sunnah Tube /ሱንና ቲዩብ (Seid Mohammed)
የዶላር ምንዛሬ መጨመርና ለኑሮ ውድነት?
ሰሞኑን ብዙ ቦታ ዶላር ዝርዝሩ ጨመረ፣ ኑሮ ተወደደ የሚባል ነገር ይወራል፡፡ እስቲ አዋቂዎች እንዲህ አይነት ሁኔታዎች ላይ ምን ብለው ነበር፡፡
بسم الله والحمد لله والصلاة والسلام على رسول الله ، وبعد
የሆኑ ሰዎች አቡ ሀዚም ዘንድ ለስሞታ መጡ እንዲህም አሉት “አቡ ሀዚም ሆይ! የእቃዎችን ውድነት (ሂሳብ መጨመር) አታይምን?”
እሱም እንዲህ ሲል መልስ ሰጣቸው “ይሄ ለምን ያሳስባችኋል? ነገሮች ውድ ከመሆናቸው በፊት ሲቀልበን የነበረው (አላህ) ነው ነገሮች ውድ ሲሆኑም የሚቀልበን” አል-ሂልያ (3/239)
ቢሽር ኢብን ሀሪስ እንዲህ አሉ “የነገሮች (የእቃዎች) መጨመር ካሳሰባችሁ (ካስጨነቃችሁ) ሞትን አስታውሱ፡፡ (ምክንያቱም ሞት) ከናንተ ላይ የሂሳብን መጨመር ያስረሳችኋልና” አል-ሂልያ (8/347)
የአላህ መልክተኛ صلى الله عليه وسلم እንዲህ አሉ “ጥፍጥና ቆራጭ የሆነውን በብዛት አውሱ” (ጥፍጥና ቆራጭ የተባለው ሞት ነው)
ሱነን አቲርሚዚ 2307፣ ሱነን ኢብን ማጃህ 4258፣ ሱነን አን-ነሳኢ 1824 ሸይኽ አልባኒ ሀሰን ሰሂህ ብለውታል (አላህ ሁሉንም ይዘንላቸውና)
የአላህ ባሪያዎች ሆይ! እኛ ከአላህ ጋር ያለን ግንኙነት ሲስተካከል ሁሉ ነገር ይስተካከላል፡፡ እኛ የአላህን እና የፍጡሮችን መብት ስናሟላ የእኛም መብት በፍጡራን ይሟላልናል፡፡መቼም ፈተና ሁለት አይነት ነው፡፡ አምኖ መፈተን እና ላጠፉት ጥፋት የእጃቸውን መቅመስ፡፡ እኛ ከጌታችንና ከፍጡራን መብት ያጓደልነው ብዙ አለ፡፡ እሱን እናስተካክል፡፡ ከሞት በኋላ ያለው ህይወታችን በጣም ባሳሰበን ጊዜ ይህቼ ጠፊ አለም ጠፊ መሆኗን መገንዘብ እንችላለን፡፡ ዛሬ ዱንያን ከዲን በላይ መውደድ ለዚህ ከባድ አደጋ አጋልጦናል፡፡
በዚሁ መጠቆም የምፈልገው ዋና መልክት ለጫት ቃሚዎች፣ ለመጠጥ ጠጪዎች፣ ለሲጋራ አጫሾች፣ ሺሻ ተጠቃሚዎች ህዝብ እንዲህ ተቸግሮ እናንተ ስትቅሙ፣ ስትጠጡ፣ ስታጨሱ፣ ሺሻ ስትነፉ ትንሽ አላህን አትፈሩትም ?አታፍሩትም?
አላህ ወደ ትክክለኛው ዲን ይመልሰን፣ ልቦናም ይስጠን፡፡
የአላህ ሰላትና ሰላም በመልክተኞች ሁሉ መደምደሚያ፣ በቤተሰቦቻቸው፣ በባልደረባዎቻቸውና ሐቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡ አሚን፡፡
ሌሎች ፅሁፎችን ለማግኘት የሚከተለውን የቴሌግራም ቻናል ጆይን ይበሉ
https://t.me/SadatTextPosts
ድጋሚ የተፖሰተ
October 19, 2015 · Addis Ababa ·
ህፃን ልጅ ለአባቱ ‹‹ለአላህ ነው የምነግርብህ›› አለው
ልጆችን አላህን እንዲያውቁ ከህፃንነታቸው መኮትኮት በጣም ተገቢ ነው፡፡
አንድ አባት ለህፃን ልጁ የሆነ ነገር ይለዋል፡፡ ልጅም ደስተኛ አልሆነም፡፡ ከዛም ህፃኑ ልጅ ለአባቱ ‹‹ለአላህ ነው የምነግርብህ›› አለው፡፡
ከዚህ የምንረዳው ይህ ህፃን የአላህን የበላይነት አውቆ አባቱን በአላህ ማስፈራራቱ ነው፡፡
የአላህ ባርያዎች ሆይ! ልጆቻችን አላህን፣ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)፣ ዲነል ኢስላምን እንዲያውቁ ትኩረት እንስጥ፡፡ ልጅ አእምሮው ላይ የያዘው በአላህ ፍቃድ አብሮት ይከርማል፡፡
አላህ ሆይ! እኛም ያንተን ትልቅነት ጠንቅቀን የምንረዳ፣ ልጆቻችንም እንዲሁ የሚረዱ እውነተኛ ያንተው ባርያዎች አድርገን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
መውሊድ
=====
ከአላህ እና ከመልክተኛው (ሰላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይሁን) ውጭ ሸሪዓን መደንገግ የሚችል አለን? አላሁ (ሱብሀነሁ ወተዓላ) ሃይማኖቱን ሞልቶታል፡፡ ይህ ታላቅ እውነታ ሊረሳ አይገባውም፡፡ በእስልምና ሀይማኖት የአላህ መልክተኛ በተግባር ሰርተው ያሳዩት እና ያዘዙበት ሁለቱን ኢዶች ብቻ ነው፡፡ የአላህ መልክተኛ ከመልክታቸው የደበቁት ነገር አለን? አላህን ከመልክተኛው ቀጥሎ አላህ ላይ ያመኑ፤ የወደዱት፤ ሀብት ንብረታቸውን ለአላህ ዲን የሰጡት ሰሃባዎች፤ ከማናችንም በላይ የአላህን መልክተኛ ይወዱ ነበር፡፡ የታዘዙትንም ይፈፅሙ ነበር፡፡ ይህንን የሚጠራጠር አለን?
አላህም ሙሃጂርና አንሳርን የተከተለን ሰው እንደሚወድ ተናግራል፡፡ የሚከተሉትን ጥያቄዎች እንመልስ
ነብያችን ሰርተውበታልን? እንዲሰራ አዘዋልን?
አቡበክር አሲዲቅ ሰርቶታልን? እንዲሰራ አዘዋልን?
ኡመር ሰርቶታልን? እንዲሰራ አዘዋልን?
ኡስማን ሰርቶታልን? እንዲሰራ አዘዋልን?
አልይ ሰርቶታልን? እንዲሰራ አዘዋልን?
ሙሃጂሮችና አንሳሮች ሰርተውታልን?
ታቢእዮች፤ አትባ ታቢኢን፤ አቡ ሀኒፋ፤ ኢማሙ ማሊክ፤ ኢማሙ ሻፊእ፤ ኢማሙ አህመድ፤፤፤፤፤ ሰርተውታልን?
መውሊድ ከዚህ ሁሉ አመታት በሃላ ዲን ላይ መጨመሩ ብቻ የጥፋት መንገድ ለመሆኑ በቂ ማስረጃ አይሆንምን?
አላህ መውሊድ በመስራቴ ይቀጣኛልን? ብሎ አንድ ሰው ቢጠይቅ፡፡ የሰይድ ሙሰየብ ንግግር መልስ ይሆናል፡፡ አንድ ሰው ከሱቢህ በሃላ ደጋግሞ ሰላት ሲሰግድ አዩት፤ ከዛም እሳቸው ተው ሲሉት እሱም እንዲህ አለ ‹‹አላህ ሰላት በመስገዴ ይቀጣኛልን?›› እሳቸውም እንዲህ ብለው መለሱለት ‹‹ሰላት በመስገድህ ሳይሆን መልክተኛውን በመቃረንህ ነው››
ይህ ከሆነ እውነታ፡፡ መውሊድን ለማክበር ችግር የለውም የሚሉ ሰዎች የአላህን ቅጣት አይፈሩምን?
የአላህ ባርያዎች ሆይ! መውሊድ እንደማይቻል መናገር አንዳንድ ሰዎች እንደሚሉት የሙስሊሙን አንድነት የሚበታትን አይደለም፤ እንዲያውም እውነተኛ ወንድማማችነትን፤ ታማኝ መካሪነትን የሚያሳይ ነው፡፡ በአላህ ስም ወንድምና እህቶቼን የምመክረው አላህና መላክተኛው ያዘዙንን በአቅማችን እንስራ፤ ከዛ በተረፈ ያልታዘዝነውን ከመስራት አላህን እንፍራ፡፡ አንድነት ይበታተናል እየተባለ ቢድዓ ዝም ማለት የአላህ ቅጣት ሲመጣ ሁላችንን ነው የሚነካን፡፡ አላህ የሃቅን መንገድ ሁላችንንም ይምራን፡፡ አሚን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
መውሊድ?
ማስረጃ የሚጠየቀው ማን ነው?
አንድ ግለሰብ ፌስቡክ ኮሜንት ላይ እንዲህ ሲል ጠየቀ/ች
“መውልድን አታክብሩ የሚል ደሊል ከቁርአንና ከሀድስ መልስ እፈልጋለሁ? ???????”
ትክክለኛው ጥያቄ
“መውሊድን አክብሩ የሚል ከቁርአን እና ከሀዲስ መልስ እፈልጋለሁ” ነበር፡፡
ምክንያቱም ማንኛውም አምልኮ በቁርአን እና ሀዲስ ካልታዘዝን እኛ በደመ ነፍስ ተነስተን ልንፈፅመው አንችልም፡፡
የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ይላሉ
“የእኛ ትእዛዝ የሌለበትን ስራ የሰራ ሰው ስራው ወደራሱ ተመላሽ ነው” ትክክለኛ ሀዲስ
በዚህ ሀዲስ መሰረት በቁርኣን እና ሀዲስ መውሊድ አውጡ የሚል ታዟልን?
በፍፁም፡፡ ስለዚህ ማስረጃ የሚጠየቀው በዲን ላይ የሌለን ነገር የሚሰራው እንጂ፣ በዲን ላይ የሌለን ነገር የሚቃወመው አይደለም፡፡
የአላህ መልክተኛ እንድንታገላቸው ካዘዙን ሰዎች ውስጥ “ያልታዘዙትን የሚሰሩ፣ የማይሰሩትን የሚናገሩ” ናቸው፡፡
የነብይም፣ የአገርም፣ የልጅም፣ የእናትም ብሎም የማንንም ልደት ባእል አመት ጠብቀን እንድናከብር ኢስላም አላዘዘንም፡፡ ስለዚህ እንርቀዋለን፡፡
ለምሳሌ ሁለቱ ኢዶች በሸሪአ ተደንግገዋል ስለዚህ የአላህ መልክተኛ፣ ሰሃባዎች፣ ፉቀሃዎች፣ ሙሀዲሶች እና የነሱን መንገድ የተከተሉ ሁሉ ይሀው እስከዛሬ ያከብሩታል፡፡ በተገላቢጦሹ መውሊድ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)፣ ሰሃባዎች፣ ፉቀሃዎች፣ ሙሀዲሶችና የነሱን መንገድ የተከተሉ ሁሉ አልሰሩትም፡፡
ታድያ ማን ነው ማስረጃ ከቁርኣን እና ሀዲስ ማቅረብ ያለበት?
አላህን እንፍራ ያልታዘዙትን መስራት ከአላህ ቢያርቅ እንጂ አያቃርብም፡፡ ሸይጧን ዘንድ ደግሞ ቢድኣ (በዲን ላይ የሚደረግ ጭማሪ) ከወንጀል በላይ ተወዳጅ ነው፡፡
አላህ ውብ የሆነውን የሱና ጎዳና ይምራን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
መውሊድና ቢዝነስ?
በነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ውዴታ ስም የንፁሀን ሙስሊሞችን ብር መበዝበዝ፡፡ ተመልከቱ አገራችን ላይ እነዚህ ሸህ ተብዬ እሾሆች መውሊድ እናክብር በሚል ስም ከሙስሊሙ ኪስ ላይ ገንዘብ በመሰብሰብ ለዋናዎቹ ሁለት ኢዶች የማያርዱትን ግመል ለዚህ አደገኛ ሺርክ የታጨቀበት ቢድኣ ያርዳሉ፡፡
አስገራሚው ለመውሊድ ተብሎ የሚወጣው ገንዘብ ከእነዚህ ሸህ ተብዬዎች ኪስ አይወጣme፡፡ ይልቁንስ ከምስኪኑ ህዝብ ነው፡፡ ሸህ ተብዬዎቹ ይበላሉ፣ ይጠጣሉ፣ ይቅማሉ፣ ይጨፍራሉ፣ ብሎም በዲን ስም የሰው ኪስ ያወልቃሉ፡፡ ይህን ተግባራቸውን “ጀባታ” ብለው ይጠሩታል፡፡ ከተራው ኪስ አውላቂ የባሱ ኪስ አውላቂዎች ናቸው፡፡
እነዛ አላህ የሚወዳቸው እነሱም የሚወዱት ሰሃባዎች አንድም ቀን መውሊድ አላከበሩም፡፡ እነዚህ ሸህ ተብዬዎች ከሰሃባዎች በላይ ነብዩን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ወደው ነውን? በፍፁም፡፡
የአላህ ባሪያዎች ሆይ! እራሳችንንም ቤተሰቦቻችንንም ከእንዲህ አይነት ኪስ አውላቂዎች፣ እምነት አበላሾች እንጠብቅ፡፡ ነብዩን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) መውደድ የሚገለፀው ሱናቸውን በመከተል ብቻና ብቻ ነው፡፡ መጨፈር፣ አደንዛዥ ቅጠል መብላት፣ ሴትና ወንድ ተቀላቅሎ መጨፈር በፍፁም ነብዩን የመውደድ መገለጫ አይሆንም፡፡ እንዲያውም እሳቸውን የማመፅ ተግባርና ክልከላቸውን መዳፈር ነው፡፡
አላህ በውቡ በነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሱና በሰሃባዎች አረዳድ (ሰለፉነ ሷሊሂን መንሃጅ) ላይ አኑሮ፣ በዛው መንገድ ላይ ይግደለን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
በእስልምና የሰው ስም አንስቶ መናገር ይቻላል ወይ?
========================
ኢማመ ነወዊ (አላህ ይዘንላቸውና) የሚከተሉትን ስድስት ነጥቦች ‹‹ሪያዱ ሷሊሂን››
የተባለው ኪታባቸው ላይ ከቁርዐንና ከሀዲስ ጨምቀው እንዲህ በማለት አስቀምጠዋል፡፡
እወቅ ሀሜት ትክክለኛ ለሆነ አላማ ይቻላል፡፡ ከዚህ መንገድ ውጭ (ስም አንስቶ መናገር)
ሌላ አማራጭ ከሌለ፤ እሱም በስድስት ምክንያት ነው፡፡
1. የተበደለ ሰው፡- የተበደለ ሰው ለሚመለከተው አካል፤ ለዳኛ ወይንም ለባለስልጣን፤
ለመሪ ሰውየው በሌለበት እገሌ በድሎኛል ቢል አይከለከልም፡፡
2. መጥፎን ነገር ለማስቆም (ለማገድ)፡- ለምሳሌ አከሌ መጥፎ ስራ እየወራ ነው፤
መጠጥ እየጠጣ ነው፤ እያጭበረበረ ነው ብለህ ለማስቆም ወይንም ለመምከር አቅም
ላለው ሰው መናገር፡፡ ይህን ሲያደርግ ሰውየውን ለመመለስ ብቻ መሆን አለበት፡፡
3. ፈትዋ ለመጠየቅ፡- ለምሳሌ ለዳኛ አባቴ፤ ወንድሜ፤ ሚስቴ ወይንም እገሌ በድሎኛል፡፡
ለዚህ አካል ይሄ ይገባዋልን? ይበቃለታል ወይ? የሚሻለው ግን አባቴ፤ ወንድሜ ሳይሉ
አንድ ሰው ነበር እንዲህ አደረገ ብሎ መጠየቅ ይሻላል፡፡
4. ሙስሊሞችን ከሸር ለማስጠንቀቅና ለመምከር፡- ለምሳሌ የሀዲስ ዘጋቢዎችና
መስካሪዎችን ችግር ካለባቸው ችግር አለባቸው ማለት (ለምሳሌ የሚረሱ ከሆነ ይረሳሉ
ብሎ መናገር)፤ እንዲያውም ይህ ዋጂብ ግዴታ ነው፡፡
ሌላ ምሳሌ፡- እገሌን ልጄን ልድረው ነበር፤ እገሌን ንግዴ ላይ ሸሪካ ላደርገው ነበር
ምንትላለህ ተብሎ ከተጠየቀ፤ የተጠየቀው ሰው ሀቁን መናገር አለበት፡፡
ሌላው፡- አንድን ጡላበል ኢልም (የዲን ትምህርት የሚቀስም) ሙብተዲዕ (ቢድዐ
የሚያራምድ ሰው) ጋር ወይንም ፋሲቅ ዘንድ ዲን ሊማር ሲመላለስ ካየሀው የሰውየውን
ማንነት መግለፅ ያስፈልጋል፡፡ መስፈርቱም ምክርን አስቦ መሆን አለበት፡፡ ምክንያቱም ይህ
ሰዎች የሚሳሳቱበት በመሆኑ ነው፤ ምክንያቱም ተናጋሪውን ምቀኝነት ሊያነሳሳው ይችላል፡፡
ሸይጧን ምክር ነው ብሎ ሊያመሳስልበት ይችላል፤ መጠንቀቅ ይገባል፡፡
ሌላው፡- ሰውየው ሀላፍትና ቦታ ይቀመጥና ሀላፍትናውን የማይወጣ ከሆነ ወይ ሀላፍትና
ላይ የተቀመጠው ሰው ለቦታው ብቁ ካልሆነ ወይንም ፋሲቅ ከሆነ ለሚመለከተው አካል፤
አከሌ ተነስቶ አከሌ ቢቀመጥ ብሎ መናገር ይቻላል፡፡
5. ሰውየው ወንጀሉንና ቢድዐውን ግልፅ የሚያደርግ ከሆነ፡- በግልፅ እየሰሩ ያሉትን
በግልፅ ለማህበረሰቡ ስም አንስቶ መጥቀስ
6. ለማስተዋወቅ፡- አንድ ሰው በሚታወቅበት ቅፅል ስም ማንሳት ለምሳሌ ሶስት
ሙሀመዶች ቢኖኑ አንዱን ሙሀመድ የሚያነክሰው ተብሎ ቢጠራ፡፡ ልብ ሊባል የሚገባው
ለመለየት ብቻ እንጂ ለማነወር ከሆነ አይቻልም፡፡ https://t.me/SadatTextPosts
ከኢማሙ ሻፊኢ (ረሂመሁላህ) እና ከድምፃችን ይሰማ ማንን ይቀበላሉ?
……………
እውነትን መናገር ሐቅን ለራስ አውቆ ለሰዎች ማብራራት ግድ ነው፡፡ ከላይ እንዳያችሁት ድምፃችን ይሰማ ብሎ እራሱን የሚጠራው አካል የጥመት ተከታዬች ስለሆኑት ሱፍዬች እያወደሰ የፃፋን ንግግር ከታላቁ የኢስላም ሊቃውንት ኢማሙ ሻፊኢ (ረሂመሁላህ) ስለ ሱፍያ የተናገሩትን እውነታ ለውድድርነት እናይበታለን፡፡
ያለ ማስረጃ ምንም አይነት ኮሜንት እንዳትሰጡ፣ ረጋ ብላችሁ ማስረጃውን እንድታነቡ፣ ከኡለማና ማንነቱ ከማይታወቅ አካል ማናቸው ለሐቅ የቀረቡ እንደሆኑ ረጋ ብላችሁ እንድታዩና ሐቁን እንድትቀበሉ፣ ባጢሉን እንድትርቁ በአላህ ስም ትጠየቃላችሁ፡፡
ሙስሊሞችን ወደ ጥመት ከሚመሩት ቡድኖች ውስጥ ሱፍዬች ይገኙበታል፡፡ ኢማሙ ሻፊዒ (ረሂመሁላህ) ሱፍዬችን አስመልክተው እንደሚከተለው ብለዋል
“አንደ ሰው ንጋት ላይ ሱፊይነት ከጀመረ ለዝሁር ተጃጅሎ እንጂ አይመጣም” ተልቢሱል ኢብሊስ 371
ድምፃችን ይሰማ የሚባለው ማንነቱ የማይታወቀው፣ ሙስሊሞችን የሚያስጨርሰው ደግሞ ሱፍዬችን አስመልክቶ ከአህባሽ ጋር ለማወዳደር ነው በሚል እንዲህ ሲል ያወድሳቸዋል
“ሱፊያዎች ጭንቀታቸው ሙስሊሙ እንዴት አንድ ሆኖ ንጹህ ቀልብ ይዞ አላህ ፊት ይቀርባል” ይህ የድምፃችን ይሰማ ፅሁፍ የቅጥፈቶች ሁሉ ቅጥፈት ነው፡፡
ድምፃችን ይሰማ ቢዋሽም ለሱፍዬች ሽንጡን ገትሮ ጥብቅና ቢቆምም የሱፍዬች እውነታ እንደሚከተለው ነው
- ሱፍዬች ማለት በአገራችን ላይ ኡማውን ወደ ቀብር አምልኮ የተጣሩ ናቸው፣
- ከአህባሽ ጋር ከ90 ፐርሰንት በላይ የሚያመሳስላቸው እምነት እና ተግባር አለባቸው፣
- ዛሬ አህባሾች እየተባሉ የሚጠሩት እንደነ ጠሀ ሀሩን (የአንዋሩ አሰጋጅ) ትላንት የድምፃችን ይሰማ ተከታዬች ሱፊ መሆናቸውን የሚያምኑላቸው አጥፊዎች ወደ ሺርክና ቢድኣ በግልፅ የሚጣሩ ሰዎች ያሉበት ነው፣
- በቢድዓ የተጨማለቁ፣ ሙስሊሙን ኡማ መውሊድ እያሉ ቀብር ለቀብር ሙታንን እንዲያመልክ አለ የሚሉትን ጥሪ ተጠቅመው ኡማውን ያበላሹ ናቸው፣
- ሙስሊሙን ኡማ የበታተኑ እና እራሳቸውም ጠሪቃ እያሉ የተበታተኑ (ለምሳሌ ሻዚሊ፣ ቃዲሪ፣ ቲጃኒ…..)፣ (የአብሬት ሙሪድ፣ የቃጥባሬ ሙሪድ… እያሉ የተበታተኑ) ናቸው፣
- የንፁሀን ሙስሊሞችን እምነት የበረዙ፣ ሀብትና ንብረት የዘረፉና የሚዘርፉ ናቸው፣
- ኡማውን ጫት ቃሚ እንዲሆን፣ ደካማ፣ ዝርክርክ እንዲሆን አድርገዋል፤
- ኡማው በተረተረት እንዲያምን እና ከትክክለኛው ሸሪኣዊ እውቀት እንዲርቅ አድርገውታል፣
እና ሌሎችም መጥፎ ተግባራትን የቃፉ ናቸው፡፡
እንግዲህ እነዚህን ሱፍዬች ነው ድምፃችን ይሰማ “ሱፊያዎች ጭንቀታቸው ሙስሊሙ እንዴት አንድ ሆኖ ንጹህ ቀልብ ይዞ አላህ ፊት ይቀርባል” እንዲህ ሲል ያወደሳቸው፡፡ የውሸት ምስክርነት ትርፉ ኪሳራ ነው፡፡ ሃይማኖታችን ኢስላም ለአንድ ሰው በውሸት መመስከርን እንኳን አይፈቅድም አይደለም ሙስሊሙን ኡማ ለሚያጠመው ሱፍያ ለተባለው የጥመት ቡድን ሊመሰከር ቀርቶ፡፡
ባጢል ላይ ያለ ስብስብ ሁሌም ለውርደት የቀረበ ነውና ለቀላቢው ያልታመነ ለፍጡራን አይታመንም፡፡ ድምፃችን ይሰማ ሙስሊሙን ካሰጨረሰው በላይ ሱፍያና አሻኢራ የተባሉትን የጥመት መንገድ ተከታዬች ለኡመተል ኢስላም እንደ ፃድቅ አድርጎ ማቅረቡ የባሰ በደል ነው፡፡
መቼም ጌታዬን እልፍ አእላፍ የደረሰ ምስጋና አቀርብለታለሁ፡፡ ምክንያቱም በነዚህ ሰዎች ሳንሸነገል፣ ከውሸት ፕሮፖጋንዳቸው ጠብቆን፣ በሐቅ ላይ እንድንፀና ላደረገን፡፡ አህባሽ ይዞ የመጣውን የሺርክና የቢድኣ አጀንዳ ነብያት ሁሉ ቅድሚያ ለተውሂድ እንደሰጡት በአላህ ፍቃድና እገዛ ቅድሚያ ለተውሒድ ሰጥተን ነብያት በሄዱበት መንገድ ሄደን ህዝቡን ከሺርክያት፣ ቢድኣ፣ ፖለቲካ፣ ነሺዳ፣ ድራማ፣ ፊልም፣ ኳስ አህባሽና ሌሎች የጥመት ቡድኖች ይዘውት ከመጡት ጥፋት አቅም በፈቀደ መልኩ ለመታደግ ተችሏል፡፡
ድምፃችን ይሰማን ሲከተሉ የነበሩት ደግሞ ለአቂዳ ሊሰጥ የሚገባውን ትኩረት ሳይሰጡ ወደ ተውሒድ የሚጣሩ ሰዎች ላይ የዋሸውን ቢቢኤን እያዳመጡ፣ ነሺዳቸውን እየዘፈኑ ልባቸውም የደረቀ አሉ፡፡
በሐቅ ላይ መሰባሰብ ስኬት ነው፡፡ በባጢል ላይ መሰባሰብ ውርደት ነው፡፡
አላህ ሆይ! ሐቅን በሀቅነቱ አሳየን የምንቀበለውም አድርገን፡፡ ባጢልን በባጢልነቱ አሳየን የምንርቀውም አድርገን፡፡ https://t.me/SadatTextPosts
እውነት የኢትዮጵያ ሙስሊም መውሊድ ማክበር ነበረበትን? በፍፁም።
ምክንያቱም ያኔ የረሱልን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ፊት ያዩት፣ መልክቱን ከምንጩ የጠጡት፣ የመጀመርያዎቹ ትውልዶች፣ ሙሀጂሮች ወደ ኢትዮጵያ ተሰደው ሲመጡ መውሊድን ይዘውት አልመጡም።
ታድያ አንዳንድ አላዋቂዎች "ሸህ አሊ ጎንደር፣ ሾንኪዎችና ሌሎች" ይፈቀዳል ብለዋል ቢሉ እውነት እንዳይመስልህ። እውነት ማለት የጥንት የጠዋቱ ሰሃባዎች ይዘውት የመጡት ነው።
የአባቶቻችን መንገድ ነው ቢሉህም እንዳትሰማቸው ምክንያቱም የጥንት የጠዋቱ አበዎቻችን ለስደት የመጡት ሰሃባዎች ያላሳዩን ተግባር ነውና እንረቀው። የሚገርመው ግን መውሊድን የሚያከብሩ የጥንት ተደርገውና፣ መውሊድን የሚከለክሉትና የሚያወግዙት እንደ መጤ መቆጠራቸው ነው። ከኀላ የመጣ አይን አወጣ እንደሚባለው ማለት ነው። አላሁል ሙስተአን።
ሰዎች በሀቅ ይለካሉ እንጂ ሀቅ በሰዎች አትለካም።
አገራችን ላይ የሚከበረው መውሊድ ታላቁ ሽርክ ሁሉ የተቀላቀለበት ነው።
ሽርክ ደግሞ ስራን ሁሉ ያበላሻል። አስደናቂው ይህን የታላላቅ ሽርኮች መናሀርያ "አይለያየንም" ብለው የሚሰብኩ ስሜታቸውን አምላኪዎች አሉ።
መውሊድን ሽሸው፣ ተጠንቀቅ አስጠንቅቅ።
https://t.me/SadatTextPosts