Sadat_Text_Posts
10K subscribers
291 photos
8 videos
12 files
378 links
Download Telegram
Forwarded from SadatKemal Abu Meryem
ስለ ሰሞኑን ከባድ ብርድ እስልምና ምን ይላል፡፡
የአላህ ባርያዎች ሆይ! አሁንም አረፈደም ንሰሃ እንግባ
ኢስላም የነብያት ሁሉ ሀይማኖት ነው፡፡ እንደሚታወቀው በሀይለኛ ሙቀት እና በሀይለኛ ብርድ ሰው ተቸግሯል፡፡ ይህም ከመሆኑ ጋር ለአላህ ካጠፋነው ጥፋቶች ንሰሀ ከመግባት ይልቅ በየዜና አውታሩ “የአለም በረዶ ስለቀለጠ ነው፣ ዛፎች በመቆረጣቸው ነው፣ ኦዞን በመሳሳቱ ነው…..” እና የመሳሰሉትን ምክንያቶች ናቸው እየተባለ ይለፈፋል፡፡
እስቲ የነብያት ሁሉ መደምደሚያ ነብዩ ሙሐመድ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ምን እንደሚሉ እንይ
አቡ ሁረይራ (ረድየላሁ አንሁ) ባስተላለፉት፣ ኡማሙ አል-ቡኻሪ በዘገቡት ትክክለኛ ሀዲስ ላይ የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ
“ጀሀነም (እሳት) ወደ ጌታዋ ስሞታ አቀረበች፡፡ ከፊሌ ከፊሌን በላው አለች፡፡ አላህ ሁለት ጊዜ እስትንፋስን ፈቀደላት፡፡ አንደኛው በቀዝቃዜ ወራት ሌላኛው ጊዜ በሙቀት ወራት፡፡ በሙቀት ጊዜ የምታገኙት ከባድ ሙቀት እና በቅዝቃዜ ጊዜ የምታገኙት ከባድ ውርጭ (ቅዝቃዜ፣ ቀቅ) (ናቸው)፡፡”
حَدَّثَنَا أَبُو الْيَمَانِ، أَخْبَرَنَا شُعَيْبٌ، عَنِ الزُّهْرِيِّ، قَالَ حَدَّثَنِي أَبُو سَلَمَةَ بْنُ عَبْدِ الرَّحْمَنِ، أَنَّهُ سَمِعَ أَبَا هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ يَقُولُ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ اشْتَكَتِ النَّارُ إِلَى رَبِّهَا، فَقَالَتْ رَبِّ أَكَلَ بَعْضِي بَعْضًا، فَأَذِنَ لَهَا بِنَفَسَيْنِ نَفَسٍ فِي الشِّتَاءِ وَنَفَسٍ فِي الصَّيْفِ، فَأَشَدُّ مَا تَجِدُونَ فِي الْحَرِّ، وَأَشَدُّ مَا تَجِدُونَ مِنَ الزَّمْهَرِيرِ ‏"‌‏.‏
ልብ እንበል ከባዱም ሙቀት እና ከባዱም ብርድ የአዋቂዎች ሁሉ አዋቂ፣ የአላህን ፈሪዎች ሁሉ ፈሪ፣ የነብያት ሁሉ መደምደሚያ እንደነገሩን የጀሃነም እሳት የምትተነፍሰው ሁለት ትንፋሽ ምክንያት ነው፡፡
ሌላው መገንዘብ ያለብን ነገር እስልምና ሙሉ መሆኑን ለማንኛውም አለም ላይ ላለ ክስተት በል እንዲያውም ለሚቀጥለው አለም ጉዳዩች፣ የሚቀጥለው አለም ላይ ምን እንደሚከሰት በዝርዝር እና በጥቅል የተናገር ዉድ፣ ልዩ፣ የማይበረዝ፣ የማይሰረዝ፣ የማይደለዝ፣ ዘመን የማያልፍበት ሀይማኖት ነውና አጥብቀን እንያዘው፡፡ ይሀው ተመልከቱ አከም “Econmic Crisese” ኢኮኖሚክ ክራይስስ ብለው ሲያወሩ አላህ ጥንትም የወለድ መጨረሻው ይህ መሆኑን ነግሮን ነበር፡፡
ትዳር እንዲመሰረት እና ከዝሙት እንድንታቀብ ከጥንትም የነብያት ሁሉ ሀይማኖት መክሮ ነበር፡፡ ግን ይህን አልሰማ ብለው አሁን አለም ላለችበት ከባባድ በሽታዎች ተዳርገዋል፡፡
በሁሉም የህይወት ዘርፍ ላይ የጥንት የጠዋቱ ኢስላም (ሰለፍያ) በሄደበት መንገድ መሄድ ብቻና ብቻ ነው ዋስትናው፡፡ ሁለት ሃቅ የለም፡፡ ሁሉም ሙስሊም ከጥመት ቡድኖች እርቆ ወደ ብቸኛዋ አማራጭ እና ሁለተኛ ወደሌላት ሃቅ ጎዳና፣ ሰለፉነ ሷሊሂን የተጓዙባት ጎዳና መመለስ ግድ ይለዋል፡፡ አለበለዚያ በሙስሊሙ አለም ላይ እንዳየነው አሁንም ከባድ ኪሳራ ይከሰታል፡፡
ታድያ ምን ይበጀን?
አማኞች ወደ ጌታቸው በንሰሃ ሊመለሱ፣ ያችን “ጭማሪ አለን?” ብላ የምትጠይቀውን ጀሀነም ከሷ ጌታችን እንዲጠብቀን እሱን ዘውትር መለመን ግድ ይለናል፡፡ የአላህ ባርያዎች ሆይ! አሁንም አረፈደም ንሰሃ እንግባ፡፡ አላህ እነዚህን ሁሉ ተዓምራት የሚያሳየን በሰጠን አእምሮ የሱን ጌትነት፣ በቸኛ ተመላኪነት አውቀን ወደሱ እንድንመለስ ነው፡፡
አላህ ሆይ! ሁሌ ወዳንተ በጸጸት ከሚመለሱት አድርገን፡፡
Forwarded from SadatKemal Abu Meryem
ትግሬ፣ አማራ፣ ኦሮሞ፣ ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀደሬ፣ ወለኔ፣ … አረብ፣ ነጭ፣ ጥቁር፣ እና የመሳሰለው ሁሉም
የዘር ሀረጋቸውን ወደላይ ሄዶ ሄዶ ከሰው ልጆች አባት ነብዩላህ አደም (አለይሂ ሰላም) ውጭ አይደለም፡፡ አደም ደግሞ የተፈጠረው ከአፈር ነው፡፡ ከአፈር የተፈጠረው የሰው ልጅ ደግሞ ሲሞት ወደ አፈር ይመለሳል፡፡
ታድያ ለምን ይሆን ዘሩን እንዲህ የሚመፃደቅበት እና አንዱ አንዱን የሚያንቋሽሽበት?
የፍጡራን ሁሉ ፈጣሪ፣ ብቸኛው አምላክ አላህ የሰው ልጆች የሚለያዩት ለእርሱ ባላቸው ፍራቻ ብቻና ብቻ እንደሆነ እንዲህ ሲል ይነግረናል፡፡
يَٰٓأَيُّهَا ٱلنَّاسُ إِنَّا خَلَقْنَٰكُم مِّن ذَكَرٍ وَأُنثَىٰ وَجَعَلْنَٰكُمْ شُعُوبًا وَقَبَآئِلَ لِتَعَارَفُوٓا۟ ۚ إِنَّ أَكْرَمَكُمْ عِندَ ٱللَّهِ أَتْقَىٰكُمْ ۚ إِنَّ ٱللَّهَ عَلِيمٌ خَبِيرٌ
እናንተ ሰዎች ሆይ! እኛ ከወንድና ከሴት ፈጠርናችሁ፡፡ እንድትተዋወቁም ጎሳዎችና ነገዶች አደረግናችሁ፡፡ አላህ ዘንድ በላጫችሁ በጣም አላህን ፈሪያችሁ ነው፡፡ አላህ ግልጽን ዐዋቂ ውስጥንም ዐዋቂ ነው፡፡
አንድ አምላክ ዘንድ የሰው ልጆች የሚበላለጡት እሱን በመፍራታቸው ብቻና ብቻ ነው፡፡
ለአእምሮ ባለቤቶች ይህ ትልቅ ትምህርት አለበትና ዘረኝነትን ሁላችንም እንራቀው፡፡
ጠለኣል በድሩ አለይና ትክክለኛ ሀዲስ አይደለም፡፡
ሃይማኖታችን በትክክለኛ ማስረጃ ላይ የተገነባ ነው፡፡
ሸይኽ ሷሊህ አል-ፈውዛን እንዲህ ሲባል ጥያቄ ቀረበላቸው፡፡
ጠያቂ፡- የተከበሩ ሸይኽ አላህ ትክክለኛውን ነገር ይግጠሞትና የመዲና ሰዎች መልክተኛውን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ጠለኣል በድሩ አለይና የሚለውን ነሺዳ እያሉ ተቀብለዋቸዋል የሚባለው እውነት ነውን?
(ይህንን ጥያቄ የጠየቅኩት) ይህንን ታሪክ (ቂሳ) ለነሺዳ ማስረጃ (መረጃ) የሚያደርጉ ሰዎች ስላሉ ነው፡፡

ሸይኽ ፈውዛን መልስ፡- ይህች ቂሳ (ታሪክ) ትክክለኛ ሆና አልተገኘችም (አልመጣችም)፡፡ በውስጧ ትክክለኛ አለመሆኗን የሚያመላክት ነገር አለ፡፡ ምክንያቱም (ስንኙ) “ጠለኣል በድሩ አለይና ሚን ሰንየቲል ወዳእ” ይላል፡፡ ሰንየተል ወዳእ (ከመዲና) በመካ አቅጣጫ አይደለም ያለው፡፡ ምክንያቱም መልክተኛው (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ወደ መዲና የመጡት በደቡብ አቅጣጫ ነው፡፡ መልክተኛው በሰሜን (አቅጣጫ) አልመጡም በሰንየተል ወዳእ ሊያልፉ ዘንድ፡፡ ሰንየተል ወዳእ ለመዲና በሰሜን አቅጣጫ ነው ያለው፡፡ ይሄ የማይገናኝ ነገር ነው፡፡

የሸይኽ ፈውዛን ንግግር እዚህ ላይ አበቃ፡፡
ሀይማኖታችን በማስረጃ ላይ የተገነባ ነው፡፡ በኢስላም ግጥም አለ፡፡ ግጥምን ለነሺዳ ማስረጃ አድርጎ ለማቅረብ መሞከር ወይ አላዋቂነት ወይ አውቆ አጥፊነት ነው፡፡ ኡመተል ኢስላም የተጠማው ኢስላማዊ ብለው የሚጠሩትን ዜማ፣ አዝማች፣ ሙዚቃ መሳሪያ ያለው፣ በኮምፒውተር የተቀናበረ ዘፈን ሳይሆን የጌታችንን ቃል ቁርኣን፣ የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሀዲስ፣ የሰሃባዎችና ፈለጋቸውን የተከተሉ አስተምህሮትን ነው፡፡
እባካችሁ ቻናል ከፍታችሁ ኡማውን በነሺዳ ቀልቡን የምታደርቁትና ከቁርኣን የምታዘናጉት ሰዎች አላህን ፍሩ፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
በቁድስ ስም መነገድ ይቁም፡፡
የአላህን ትእዛዛት ብትፈፅሙ አላህ ይረዳችኋል፡፡
አል አቅሷን ማስለቀቅ የሚቻለው በአላህ ዲን ላይ በመፅናት ብቻ ነው፡፡
ዛሬ ዛሬ ወደ ዲናችን እንመለስ የሚሉ ሰዎች የነ አል አቅሷና የሌሎች ሙስሊሞች ጉዳዬች የማያገቧቸው ተደርገው እንዲታዩ የጥፋት ተጣሪዎች ይፅፋሉ፡፡ ሺርክና ቢድኣ ከነባለቤቶቹ ማስጠንቀቂያ በተሰጠባቸው ቁጥር “የቁድስ፣ የቦርማ፣ የሶሪያ ጉዳይ አያሳስባችሁም ወይ?” እየተባለ በነቁድስ ስም ይነገዳል፡፡ እነ ቁድስን የጥፋታቸው አለመታረሚያ ሰበብ አድርገው ያቀርቧቿል፡፡ እውነታው ግን ወደ ትክክለኛው የአላህ ዲን ሳንመለስ አይደለም አላቅሷን ማስለቀቅ ይባስ መከራ ውስጥ ነው የምንገባው፡፡
ብዙ በአል አቅሷ ስም የሚነግዱ ግን አላህ ያዘዘውን ለመፈፀም ዝግጁ ያልሆኑ አሉ፡፡
አላህ እኮ የአላህን ህግጋት ብትከተሉ (ብትፈፅሙ) አላህ ይረዳችኋል ሲል ቃል ገብቶልናል፡፡ ከነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) አስተምህሮት እንደተነገረን ደጃል ሁሉን እያጠፋ መግደል የሚያቅተው የእምነት ባለቤት የሆነውን ግለሰብ ነው፡፡ ስለዚህ ደጃል ከባዱ ፈተና ሆኖ ሳ፣ የሁዳዎች ተከትለውት ሲያበቁ አብዛኛን ድል አድርጎ መጨረሻው ሲደርስ ያንን አንድ አማኛ ግለሰብ መግደል ያቅተዋል፡፡ ድል አላህና መልክተኛውን በመታዘዝ ነው፡፡ ውርደት አላህና መልክተኛውን በማመፅ ነው፡፡ ዛሬ አላህን በማመፅ፣ የመልክተኛውን ትእዛዝ በመራቅ ድል ይገኛል የተባለ ይመስል አላህን እያመፁ ኢስላማዊ ስም ይሰጡታል፡፡
አላህ ካዘነላቸው ጥቂቶች ውጭ
- ሙስሊም ነኝ እያሉ በታላላቅ ሺርክ ተጥለቅልቀዋል፣
- ቢድኣ ሙስሊም አገራት ላይ ሳይቀር ነግሶ፣
- የወላጅ ሀቅ እየተበደለና እየተጣሰ፣
- ሰሃባዎች እየተሰደቡና እየተተቹ፣ ብሎም ሰሃባ ተሰዳቢና ለሰሃባ ተሳዳቢ ጥብቅና የሚቆም እንደ አዋቂ እየተያ፣
- ዝሙት ተስፋፍቶ፣
- ወለድ እየተበላ፣
- ጀመኣ ሰላት በተለይ ፈጅር አንድ ሰፍ ሁለት ሰፍ እየተሰገደ (የሰላማዊ ሰልፍ ጊዜ አደባባይ ላይ ሚሊዬኖች ወጥተው)፣
- ሴቶች አላህ የረገመውን ቅንድብ መቀንደብ ማስቀንደብ፣ ዊግ መቀጠል ማስቀጠል፣ ንቅሳት መንቀስ ማስነቀስ እየፈፀሙ፣
- ከቀቁርኣን ተርቆ፣
- መጠጥ እየተጠጣ፣
- አደንዛዡን ጫት እየተቃመ፣
- ሲጋራ፣ ሺሻ እየተጨሰ፣
- ለኳስ ሲሉ ወንድ ልጆች ጀመኣ ሰላትን እየተዉ፣
- ሴቶች ሙሰልሰል እያሉ ፊልም እያዩ፣
- ከሀይማኖታዊ እውቀት ተርቆ እና ሌሎችም ………. መጥፎ ተግባራት እየተሰሩ ……
ቁድስ ልባችን ውስጥ ናት፣ ቦርማ፣ ዋ ሶሪያ እየተባለ በስማቸው ሶሺያል ሚድያ ላይ ይነገዳል፡፡
አል አቅሷን ትላንት ከየሁዳዎች እጅ አስለቅቋት የነበረው ኡመር ኢብኑ አል-ኸጣብ (ረድየላሁ አንሁ) ነው፡፡ ዛሬም ኡመርን የሚሳደቡ ራፊዳ ሺአዎች ወይንም ለነሱ ጥብቅና የሚቆሙት ኢኽዋኖች አያስለቅቋትም፡፡
እስቲ አላህን እንፍራና አላህ ግዴታ ያደረገብንን ሁላችንም በነፍስ ወከፍ እንፈፅም፡፡ ከከለከለን ሁሉ በቁርጥ እንራቅ፡፡ ሰላማዊ ሰልፍ ሲባል ከሚወጣው ሰው በላይ መስጂዳችንን ከፈጅር ሰላት ጀምሮ እናስውበው…….. እና ሌላም ትእዛዛትን መፈፀም ክልከላዎችን እንከልከል፡፡ ከዛም አላህ ይረዳናል፡፡
አላህን እንፍራ ኡመተል ኢስላም በጠቅላላ ወደ አላህ ስንመለስ ሁለት አገር ለስኬት እንበቃለን፡፡ በመጨረሻም ሙስሊሞች በነዚህ የሁዳዎች ላይ ድልን ይጎናፀፋሉ፡፡ አላህ እውነተኛ ሙስሊም ያድርገን፡፡ አል-ቁድስን፣ በርማን፣ ሶሪያም መላው አለም ላይ ያሉ ሙስሊሞችን መከራችንን ያንሳልን፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
አፍሪካ ቲቪ ላይ ማስታወቂያቸው ተለቀቀላቸው ስለተባሉት ሩቃ ቤቶች…..
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩሕሩሕ እጅግ በጣም አዛኝ፡፡
ይህች አጭር ፅሁፍ የምትሆነው ሰሞኑን ፌስቡክ ላይ በደንብ ስለ ተራገበው ቲቪ አፍሪካ ላይ ማስተወቂያቸው ስለ ተለቀቀላቸው ሩቃ ቤቶችና ስለሚሰሩት አፀያፊ ተግባር የሚጠቅስ ነው፡፡

ወንድም ኢድሪስ ኢብን ኢልያስ በፃፈው ፅሁፍ ላይ አፍሪካ ቲቪ ላይ ማስታወቂያ ከለቀቁት ሩቃ ቤቶች ውስጥ አብዛኛዎቹ እዚህ መጥፎ ተግባራት ላይ የተሰማሩ መሆናቸው ማስረጃ እንዳለ ጥናት እንዳለም ነግሮኛል፡፡

ይህ ከሆነ እውነታው አፍሪካ ቲቪ ማስታወቂያ ከለቀቁት አጥፊዎች ውስጥ በማስረጃ የተረጋጋጡትን እዛው ቻናል ላይ እነዚህ ሩቃ ቤቶች በዚህ በዚህ ማስረጃ ሙስሊሞችን የሚጎዳ ይህን ይህን ጥፋት ፈፅመዋል ብሎ በግልፅ ማጋለጥ አለበት፡፡
በዚሁ በሶሺያል ሚድያ ላይም እነዚህ መጥፎ ሩቃ ቤቶች ከትክክለኞቹ ይለዩ ዘንድ በስነስርኣት ሊጋለጡ እና ኡማው ሊጠነቀቃቸው ይገባል፡፡
አፍሪካ ቲቪ መጀመሪያ ላይ የነዚህን ሩቃ ቤቶች መጥፎ ስራ ሳይውቅ ቀርቶ ሊሆን ይችላል፡፡ አሁን ግን ጥናት የሰሩ ወንጀሎቹን የተከታተሉ ወንድሞች ስላሉ ያን ማስረጃ ይዞ ሙስሊሙን ማህበረሰብ ይቅርታ ሊጠይቅ፣ ለወደፊቱ እንዲህ አይነት ማስታወቂያዎችን ከመስራቱ በፊት ያ ማስታወቂያ እንዲለቀቅለት የሚፈልገውን ድርጅት አሰራር ከሸሪኣ አኳያ ማጥናት አለበት፡፡ እዚህ ጋር “እኛ ማስታወቂ እናግኝ እንጂ ስለሌላው ምን አገባን” የሚባል አባባል የለም፡፡ ምክንያቱም አፍሪካ ቲቪ እራሱን የሀይማኖት ተቋም አድርጎ ስለሚንቀሳቀስ፡፡

እነዚህ ሙስሊሙ ላይ በእምነቱ፣ በክብሩ፣ በገንዘቡ በተለይ ሴት እህቶቻችን ላይ የተጫወቱ ሩቃ ቤቶች አፍሪካ ቲቪን ተጠቅመው ማስታወቂያቸውን ረጭተው ህዝብ ዘንድ እንደደረሱ ሁሉ አፍሪካ ቲቪ አሁንም ስርጭቱን ተጠቅሞ፣ ለሙስሊሙ ማህበረሰብ ወግኖ፣ ጥቅም ሳያታለው፣ ሀፍረት ሳይዘው፣ እንዲህ አይነት አውሪዎችን ማስጠንቀቅም ከኢስላም ክፍሎች ስለሆነ ስማቸውን ጠቅሶ ተጠንቀቋቸው ማለት አለበት፡፡

በዚሁ ትክክለኛ የሩቃና የባህል ህክምና ቤቶች የምናውቅ ወንድም እና እህቶች ለሙስሊሙ ማህበረሰብ እነዚህ ትክክለኞቹ ጋር እንዲሄዱ መጠቆም አለብን፡፡

ሙስሊሞች ሆይ! እራሳችንን በቁርኣን፣ በሀዲስና ሸሪኣው ባስቀመጣቸው ማር ጥቁር አዝሙድ….. በመሳሰሉት ማከም እንችላለን፡፡
ኢንሻ አላህ በዚህ በኩል ተከታታይ ፅሁፎች መዘጋጀት ይኖርባቸዋለው፡፡
አላህ የታመሙ ሙስሊም ወንድም እና እህቶቻችንን ከበሽታቸው ይፈውሳቸው፡፡
ፍልስጤም መቼ ነው የምትመለስልን?
በሸይኽ ሙሐመድ ሰኢድ ረስላን (ሀፊዘሁላህ)
አለም ላይ ያለ ማንኛውም ሙስሊም “ፍልስጤም መቼ ነው የምትመለስልን?” ብሎ ከጠየቀ
መልሱም “ወደ አላህ (በትክክለኛው እምነት፣ መልካም ስራ፣ አላህና መልክተኛውን በመታዘዝ ክልከላቸውን በመራቅ) ስትመለስ ፍልስጤም ያኔ ትምለሳለች፡፡”
ይህ መልስ ከአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሀዲስ የተውጣጣ (የተጨመቀ) ነው፡፡ ኢማሙ አሕመድ እና አቡ ዳውድ ከሰውባን (ረድየላሁ አንሁ) ይዘው በዘገቡት ሀዲስ የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ
“ህዝቦች በናንተ ላይ ይጠራራሉ፡፡ ልክ ሰዎች እርስ በርስ ከቀስ (ሰፊ ትሪ ላይ የቀረበ ምግብ) ለመብላት እንሚጠራሩት፡፡”
እነሱም (ሰሃባዎች) ጠየቁ “የአላህ መልክተኛ ሆይ! ያን ቀን በቁጥር አንሰን ነውን?”
እሳቸውም (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ሲሉ መለሱ “በፍፁም፡፡ ያን ጊዜ በቁጥር በጣም ብዙ ናችሁ፡፡ ነገር ግን ልክ እንደ ጉሳእ (የባህር አረፋ) ናችሁ፡፡ አላህ ከጠላቶቻችሁ ልብ ውስጥ ለናንተ የነበራቸውን ፍራቻ ያነሳና እናንተ ልብ ውስጥ ዋህንን ያደርጋል፡፡”
እነሱም (ሰሃባዎች) አሉ “የአላህ መልክተኛ ሆይ! ዋህን ምንድን ነው?”
እሳቸውም አሉ “ዱንያን መውደድና ሞትን መጥላት”
ኢማሙ አሕመድ 21897 እና አቡ ዳውድ 4297. ኢማም አልባኒ አሰሂሃ ላይ ትክክለኛ ብለውታል 8183
ወደ አላህ (በትክክለኛው እምነት፣ በመልካም ስራ፣ ትእዛዝን በማክበር፣ ክልከላን በመራቅ፣ በተውበት) የተመለስን ጊዜ ከእኛ የተወሰደብንን ይመልስልናል፡፡ ከአላህ መራቁን (እምነታችንን ሳናስተካክል፣ ቢድኣን እያጨማለቅን፣ መልካም ስራን ሳንሰራ፣ ሳንታዘዝ፣ ክልከላን ሳንርቅ) ከቀጠልንበት በእጃችን ያለውንም እናጣዋለን፡፡
በእርግጥ አላሁ (ተባረከ ወተኣላ) ይህንን ፍርድ በተከበረው መፀሀፉ እንዲህ ሲል አስቀምጦታል
[Q 14:7] وَإِذْ تَأَذَّنَ رَبُّكُمْ لَئِن شَكَرْتُمْ لَأَزِيدَنَّكُمْ ۖ وَلَئِن كَفَرْتُمْ إِنَّ عَذَابِى لَشَدِيدٌ
ጌታችሁም «ብታመሰግኑ በእርግጥ እጨምርላችኋለሁ ብትክዱም (እቀጣችኋለሁ) ቅጣቴ በእርግጥ ብርቱ ነውና» በማለት ባስታወቀ ጊዜ (አስታውሱ)፡፡
እሱ (የላቀውና ከፍያለው) የተሰጠንን አለማመስገን ያንን ፀጋ እንደሚያጠፋው አብራርቶልናል፡፡ አዋቂዎቻችን እንዲህ ይላሉ “በረካ የሚታደን ነገር ነው፡፡ ለተሰጠን በረከት ማመስገን ደግሞ (በረከቱ) እንዲፀና እንዲቀጥል እንዳይጠፋ ያደርገዋል (መጠበቂያ ነው)፡፡”
[ምንጭ :መታ ተኡዱ ኢለይና ፍልስጢን፡ ገፅ 7-8]
የሸይኽ ሙሐመድ ሰኢድ ረስላን ንግግር እዚህ ጋር ተፈፀመ፡፡
በአላህ ፍቃድ እዚሁ ፊስ ቡክ ላይ፣ በየመንደሩ፣ በየትምህርት ቤት፣ በየመስጊዱና ሁሉ ቦታ ፍልስጤም መቼ ነው ወደኛ የምትመለሰው እያልን ለምናስብ ኢትዬጵያዊ ወንድም እና እህቶች ሁሉ የሚከተለውን ጥያቄዎች ከነፍሴ ጀምሮ እጠይቃለሁ
1) ምን ያህሉ ሰው የተፈጠረለትን አላማ ያውቃል?
2) አገራችን ኢትዬጵያ ላይ ነብያት ከምንም በፊት ያስቀደሙት የተውሒድ ጥሪ በገጠርም በከተማም የሚገባውን ያህል ተሰራጭቷል?
3) ምን ያህሉ ኡለማ፣ ዳኢ ነብያት ሁሉ የተላኩበትን ተውሒድ ለኡማው በየቋንቋው አድርሷል?
4) የኢትዬጵያ ሙስሊም ከ40 ሚሊዬን በላይ ነው ይባላል፡፡ ምን ያህሉ የላኢላሃ ኢለላህን መስፈርቶች፣ የላኢላሃ ኢለላህን ትርጉም፣ የላኢላሃ ኢለላህን መእዘናት፣ ላኢላሃ ኢለላህን የሚያፈርሷትን ማስረጃዎቿን ጠንቅቆ ያውቃል?
5) ምን ያህሉ አርካኑል ኢስላምና አርካኑል ኢማንን በዝርዝር ጠንቅቆ ያውቃል?
6) ምን ያህሉ ስለ ሺርክ አደገኝነት ያውቃል?
7) ምን ያህሉ በሺርክ ተዘፍቋል?
8) ምን ያህሉ ከአላህ አምልኮ ወጥቶ ለቀብር ይሰግዳል፣ ያርዳል፣ ይሳላል……? ኡለማዎችና ዱአቶች እውነት አደራቸውን ተወጥተዋልን?
9) የሩቅ እውቀት በጠቅላላ ለአላህ ብቻ ሆኖ ሳለ አገራችን ላይ የክህደት መፀሀፍ የሆነውን “የሸህ ሁሴን ትንቢት” ምን ያህል ሰው እውነት ነው ብሎ ይቀበለዋል?
10) ምን ያህሉ ጌታችን አላህ ከአርሽ በላይ ከፍጡራኑ ሁሉ በላይ መሆኑን ያምናል?
11) አላህ በሐቅ ላይ አንድ ሁኑ ብሎን ሲያበቃ አገራችን ላይ አንድ የሀቅ መንገድ ብቻ ነው ያለው ወይንስ አንዷን ብቸኛ የሐቅ መንገድ የሚቃረኑ ብዙ የጥመት መንገዶች? ለምሳሌ (አህባሽ፣ ሱፊ፣ አሽአሪ፣ ሺኣ፣ ተብሊግ፣ ኢኽዋን፣ ቲጃኒ፣ የቃጥባሪ ሙሪዶች፣ የአብሬት ሙሪዶች፣ የአልከሶ ሙሪዶች፣ የኑርሁሴን ሙሪዶች…………)
12) አገራችን ላይ አንድነት ሲባል በተግባር ያየነው በሐቅ ላይ መሰባሰብ ነው ወይንስ ሺርክና ቢድኣ የሚሰራውን ሁሉ ደባልቆ “አንድ ነን” ብሎ መዋሸት?
13) ምን ያህሉ ኡማ ሱናን እና የሚፃረራትን ቢድአ ለይቶ ያውቃል?
14) ምን ያህሉ ከቢድኣ ርቆ ጌታችንን አላህ በሱና ይገዛል?
15) ምን ያህል በኢስላም የሌለ መውሊድ ወይንም የልደት በአሎች አገራችን ላይ ይከበራሉ? ለምሳሌ “የአብሬት መውሊድ፣ የቃጥባሪ መውሊድ፣ የጀማ ንጉስ መውሊድ፣ የቦረናው መውሊድ፣ የዳንግላው መውሊድ፣ የአልከሶ መውሊድ፣ የአሊ ጎንደር መውሊድ…..”? ኡለማና ዳኢ የሚባሉ ይህንን ሱናን አፍራሽ ተግባር ላይ በመቃወም ሚናቸውና ትኩረታቸው ምን ያህል ነው?
16) አገራችን ላይ ትክክለኛው የአቂዳ ትምህርት አላህ ካዘነላቸው ጥቂቶች ውጭ በኡለማዎች፣ በዳኢዎች፣ በቻናሎች፣ በሪድዬ ጣቢያዎች ነብያት የሰጡትን ያህል ትኩረት ተሰጥቶታልን?
17) ምን ያህሉ ለዲን ቦታ ሰጥቶ ሸሪኣን ይማራል?
18) ምን ያህሉ ልጅ የቤተሰቡን ሃቅ ያሟላል?
19) ፔንጤ ሙስሊሙን እያከፈረ ነው ተብሎ በሰፊው ይነገራል፡፡ ፔንጤዎቹ ደግሞ ሙስሊሞቹን የሚያከፍሩት በዱንያ እንደሆነ በማስረጃ ሁሉ ይነገራል፡፡ ታድያ በዚህ ጊዜ አላህ መልካም የዋለለት በጣም ብዙ ሙስሊም ሀብታም አለ ምን ያህል እነዚህን በዱንያ ምክንያት ወደ ክህደት እየሄዱ ያሉ ግለሰቦችን ለመታደግ መፅውቷል? አገራችን ላይ በቀን ስንት ሚሊዬን ብር ሙስሊሞች ለጫት ያወጣሉ? እውነት በዱንያ ጉዳይ የሚከፍሩትን ሙስሊሞች ለመታደግ እነዚህ ጫት ቃሚዎች ለጫት የሚያወጡት ገንዘብ ፔንጤ ለሚያከፍራቸው ለምን አልተለገሰም?
20) አገራችን ላይ ባሉ ዳኢዎችና ኡለማዎች የጫትን አስከፊነት በተመለከተ ተገቢው ማስጠንቀቂያና ማንቂያ ደውል ለሙስሊሙ ኡማ ተደርጓልን?
21) ምን ያህሉ ባል የሚስቱን ሀቅ ይጠብቃል?
22) ምን ያህሉ ሚስት የባሉን ሃቅ ይጠብቃል?
23) ምን ያህሉ ሰው ሰላት ይሰግዳል?
24) ከሰጋጆች ውስጥ ለወንድ ልጅ ግዴታ የሆነውን ጀመኣ ሰላት ምን ያህሉ ይሰግዳል?
25) ምን ያህሉ ሴት አላህ የረገመውን ቅንድብ መቀንደብና ማስቀንደብ፣ ዊግ መስራትና ማሰራት፣ ንቅሳት መንቀስና ማስነቀስ ይሰራል?
26) ምን ያህሉ ወንድ ይህንን አደንዛዥ ቅጠል ጫት ይቅማል?
27) ምን ያህሉ ወንድ ሲጋራ ያጨሳል?
28) ምን ያህሉ ሰው ከዝሙት እራሱን ጠብቆ ወደ ትዳር በጊዜ ይገባል?
29) ምን ያህሉ ሙስሊም ወጣት መጠጥ ይጠጣል?
30) ምን ያህሉ ነጋዴ ከወለድ ፀድቷል?
31) ምን ያህሉ ከቁርኣን ከሱና ተዘናግቶ ወደ ፊልም ድራማ ሙዚቃ ተጎትቷል “ኢስላማዊ” የሚሉትን ጭምር?
32) እና የመሳሰሉትን በጣም ብዙ ጥያቄዎች ለነፍሳችን እንመልስ
ያኔ እውነት እኛ አሁን ያለንበት ሁኔታ ፍልስጤም እንድትመለስልን መስፈርቱን አሟልተናል ወይ? የሚለውን ቁልጭ ብሎ ይታየናል፡፡
እግር ኳስ አለ ሲባል ከለሊቱ 6 እና ሰባት ሰኣት ላይ አይኑ ዲሽ ቤት የሚፈጠው አብዛኛውን ወጣት ፈጅር ሰላት ላይ መስጂዶቻችንን ላይ መምጣት ማቃቱ ብቻ አእምሮ ላለው ትልቅ ጥቆማ ነው፡፡
እባካችሁ የፍልስጤምንም ይሁን አለም ላይ ሌሎች ሙስሊሞች ላይ የሚደርሰውን በደል እና ጭቆና ለአላህ ትክክለኛ ባሪያ ሳንሆን እዚሁ ሶሺያል ሚድያ ላይ አካኪ ዘራፍ “ዋ አቅሷ” ምናምን ብሎ መፎከሩ አያዋጣም፡፡ ይሄ በፍፁም ትክክለኛ መፍትሄ አይሆንም፡፡ ሰይጣንን እና ሰራዊቶቹን ማሸነፍ ማለት በአርሰናልና ማንቸስተር መሃል ያለ የእግር ኳስ ፍልሚያ እንዳይመስለን፡፡
አላህ እንዲህ ይላል
[Q 47:7] يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِن تَنصُرُوا۟ ٱللَّهَ يَنصُرْكُمْ وَيُثَبِّتْ أَقْدَامَكُمْ
እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን (ህግጋቱን ብትፈፅሙ) ብትረዱ፤ ይረዳችኋል፡፡ ጫማዎቻችሁንም ያደላድላል፡፡
መቼም ሰው ያልዘራውን አያጭድም፡፡ ሰሃባዎች በአላህ የሚገባውን ትክክለኛ እምነት አምነው ተገኙ፣ የመልክተኛውን ሱና አጥብቀው ያዙ ለሁለት አገር ድል በቁ፡፡
ስለዚህ የአላህ ባሪያዎች ሆይ! አላህ እንዲረዳን ከፈለግን በትክክለኛው እምነት፣ ብቸኛ አንዷ የሀቅ ጎዳና፣ የነብዩ ሱና፣ የሰሃባዎች አረዳድ፣ እውነተኛ አንድነት ላይ እንሰባሰብ፡፡ ከዛም ቃል ኪዳኑን በመሙላት የሚታወቀው አላህ ሁለት አገር ድል በድል ያደርገናል፡፡
የአላህ ሰላትና ሰላም በመልክተኛው፣ በቤተሰቦቻቸው፣ በባልደረባዎቻቸውና ሀቅን በተከተሉ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡ አሚን፡፡
ሌሎች ፅሁፎችን ለማንበብ የሚከተለውን የቴሌግራም ቻናል ይጫኑ
https://t.me/SadatTextPosts
“ሙስሊም አይዋሽም፡፡”፣ “ለቀልድ አንኳን ውሸት ሃራም ነው፡፡” ይላሉ ታማኙ የአላህ መልክተኛ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)
ከስሜት አምላኪዎችና የጥመት አራማጆች ውስጥ አንዱ እንዲህ ሲሉ ይዋሹብኛል
“ሰበር ዜና ሳዳት ከማል ለቢዝነስ ሲል የከፈተው ሩቃ ቤት ገቢያ እንዳያጣ አፍሪካ ቲቪን ማግባባት ጀመረ”
ማስረጃ አምጣ እውነተኛ ከሆንክ ቢሉት ማስረጃ የለውም፡፡ ውዱ ነብይ ለቀልድ እንኳን ውሸት ሀራም ነው ብለው ሲያበቁ፣ ስሜት ተከታዬች ከቻሉ ዲኑን ለሚፈልጉት አላማ ይጠመዝዙታል፣ ካልቻሉ ውሸት ይነዛሉ፡፡ አስገራሚው የአላህ መልክተኛ “ሙስሊም አይዋሽም” ሲሉ እነሱ ደግሞ እራሳቸውን የኢስላም ጠበቃ አድርገው ማቅረባቸውና በተከታዬቻቸው ዘንድ የሙስሊም ጠበቃ ተደርገው መወሰዳቸው ነው፡፡
በጣም የሚያሳዝነው እና እጅግ ገርሞ የሚገርመው ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “እውነተኞች ውሸታም፣ ውሸታሞች የሚታመኑበት ዘመን ይመጣል፡፡” ሲሉ ገልፀው ነበር፡፡ ዛሬ እንዲህ አይነት ውሸታሞች ለኡማው እራሳቸውን የሙስሊም ጠበቃ አድርገው መቅረባቸውና በምስኪኑ ዘንድ መታመናቸው ገርሞ የሚገርም ነው፡፡
ምስጋና ለአላህ ይገባው እኛ እነሱ የሚያጠፉትን ጥፋት ስናጋልጥ አንድም ቦታ ላይ አንዋሽባቸውም፡፡ በማስረጃ እውነቱን ብቻ እናስቀምጣለን፡፡ ዛሬ ሰው እየነቃ እና እየተለወጠ ከጥፋት ወጥቶ ወደ ሱና ሲመለስ ሲያዩት የመጨረሻ መሳሪያቸው የሆነውን ውሸት መርጨት ነው፡፡
ግን ውሸታም መጨረሻው ውርደት ነው፡፡ ልክ ሰውየው አሁንም እንደተዋረደው ሁሉ፡፡
አላህ እውነተኛ ባሪያዎቹ ያድርገን፡፡
ማንም ሰው ስሙን ቀይሮ፣ በስሙም፣ ወንዱ በሴት፣ ሴቷ በወንድ ስም ቢፅፉም አላህ በስማችን ነው የሚመዘግበው፡፡ አላህን እንፍራ፡፡
By Muhammedsirage MuhammedNur Gidey
بسم الله الرحمن الرحيم.
ነብዩ صلى الله عليه وسلم በህይወት ዘመናቸው በርካቶችን ለበርካታ ጉዳዮች ሾመዋል። ከነዚህ ተሿሚዎች ውስጥ ግን አንድም ሴት አይገኝበትም ። በግዜው አላህን የሚፈሩ በሸሪዓዊ እውቀታቸውም ከበርካታ ወንዶች ያላነሱ እነ ዐኢሻን የመሰሉ ጠንካራ ሴቶች የነበሩ ቢሆንም ታላቁ ነብይ ግን አንዳቸውንም ሙስሊሙን ይመሩት ዘንድ አልሾሙም ነበር ። ከነብዩም በሇላ በነብዩ አመላካችነት አቡበክር የሙስሊሞች መሪ ሆኖ የተሾመ ሲሆን በዚህ ወቅትም " ሴቶች ሆይ ኑና ምሩን " ያለ አንድም ሶሓባ አይታወቅም!!
ከአቡክር በሇላም ዑመር ፣ ዑስማን ፣ ዐልይ የአማኞች መሪ ሆነው ተመሪዎቻቸውን በፍትህ ያስተዳደሩ ሲሆን ላጠቃላይ መሪነትም ይሁን ላንዲት አነስተኛ አካባቢ መሪነት ወደ ሴቶች አሚርነት የጠቆመ የነብዩ ባልደረባ አልነበረም ። እነዛ ምርጥ ሴቶችም ስልጣን ይገባናል በማለት ዛሬ ዛሬ ወንድነታቸው የጠፋባቸው ወንዶች የሚጮሁትን "ሴቶች ይምሩ " ጩኸት አልጮሁም! !
ይህ ሁሉ የሚጠቁመው ሴት ልጅ በመሪነት ልትቀመጥ እንደማይገባት የሰለፎች የተግባር ስምምነት እንደነበረ ነው ። የሰለፎችን ስምምነቶች የሚነቅፉ ድርጊቶችና አቋሞች ደግሞ ጤና እንደሚጎላቸው አያጠራጥርም ። የሃሳቡ ወይም የአቋሙ ባለቤትም አቅሉና ዲኑ እንደሳሳ አያጠራጥርም!! ስልጣን ይገባናል የሚለው የሴቶች ጥያቄ የተነሳው ከምርጦቹ የሴት ምሳሌዎች ከነ ዐኢሻ፣ ሓፍሳ ፣ ዘይነብ ሳይሆን ከነ ሂላሪ ክሊንተንና መሰል ምናምንቴዎች ነውና ሴቶች ሆይ ምሳሌዎቻችሁን ልብ በሉ ።
ነብዩ صلى الله عليه وسلم እንከን በማይገኝለት ንግግራቸው ሴት ልጅን መሪ ያደረገ ህዝብ ድልን እንደማያገኝ ገልፀዋል ። እንዲህ ብለዋል ፣
لَنْ يُفْلِحَ قَوْمٌ وَلَّوْا أَمْرَهُمْ امْرَأَةً
* ቡኻሪ እና ሌሎችም ዘግበውታል።
ድል የሚገኘው የነብዩን ትእዛዝ በመከተል እንጂ የምእራቡን ከሃዲ ዱካ እየተከተሉ ሴቶችን ወደ ሹመት በመጣራት አይደለም ።
ሺአዎችን እንጠንቀቅ እናስጠንቅቅ፡፡
ጥያቄ፡- አያቶላህ ሁመይኒን አስመልኮ ኢስላማዊ ፍርዱ ምንድን ነው
መልስ፡- ኹመይኒ ኢማሞች ከነብያትና ከመልክተኞች (የአላህ ሰላትና ሰላም በነርሱ ላይ ይሁን) በላይ እንደሆኑ የፃፈበት ኪታብ አለው፡፡ በዚህ ንግግሩ መሰረት ሙስሊም አይደለም፡፡
ምንጭ አል-ሃዊ ሚን ፈትዋ አሽ-ሸይኽ አልባኒ ገፅ 349
ሺአዎች 12 ኢማሞች አሉ ብለው ያምናሉ፡፡ እነዚህ 12 ኢማሞች ምድርን ያስተናብራሉ ብለውም ይህን ኩፍር ያምናሉ፡፡ እነሱ ኢማም ብለው አምልኮን ቢፈፅሙላቸውም ግን ከነሱ ቅጥፈት የፀዱ ናቸው፡፡ ከነሱ ውስጥ የመልክተኛው የአጎት ልጅ የሆነውን አሊይ (ረድየላሁ አንሁ) ይገኝበታል፡፡ እውነታው ግን አሊይ ረድየላሁ አንሁ አይደለም ከነብያት ሊበልጥና ከ አቡበክር፣ ኡመርና ኡስማን እንኳን አይበልጥም፡፡ ይህን ስንል ደግሞ አሊይ እኛ ዘንድ የተወደደ ነው፡፡ ከደረጃው በላይ ከፍ ሊደረግ አይገባውም፣ ከደረጃውም ዝቅ ሊደረግ አይገባውም የሚለውን እያስረገጥን ነው፡፡ ሰሃባዎች ውስጥ አንድኛ አቡበክር፣ ሁለተኛ ኡመር፣ ሶስተኛ ኡስማን፣ አራተኛ አሊይ ናቸው፡፡ ሺአዎች በጣም መጥፎ ሰዎች ናቸው እንጠንቀቃቸው፡፡ የኢትዬጵያ ሙስሊሞች ሆይ! “ከሺአዎች ጋር ላኢላሃ ኢለላህ ሙሐመደ ረሱሉላህ አንድ ያደርገናል” የሚላችሁን አታላይ አትስሙት፡፡ የላኢላሃ ኢለላህ ሙሐመዱ ረሱሉላህን መልክት ከስር ከመሰረቱ የናዱ መጥፎ ፍጡሮች ናቸው፡፡
አላህ አገራችንን የመጀመሪያዎች ምርጥ ትውልዶች ወደ ሀገራችን ሁለት ጊዜ ተሰደውበት ወደ ነበረበት ጥርት ወዳለው ዲን ይመልስን፡፡ ከሁሉም የጥመት ቡድኖች ይጠብቅልን፡፡ የጥንት የጠዋቱን ብቸኛ የሐቅ መንገድ ለግሶን በሱ ላይ የምንሰባሰብ ያድርገን፡፡
አሚን፡፡ https://t.me/SadatTextPosts
Forwarded from Sunnah Tube /ሱንና ቲዩብ (Seid Mohammed)
በእስልምና ወሮች 12 ናቸው እነሱም
1) ሙሐረም፣
2) ሰፈር፣
3) ረቢእ አል-አወል፣
4) ረቢእ አስ-ሳኒ፣
5) ጀማዳ አል-አወል፣
6) ጀማዳ አስ-ሳኒ፣
7) ረጀብ፣
8) ሻእባን፣
9) ረመዳን፣
10) ሸዋል፣
11) ዙል ቃኢዳ፣
12) ዙል ሂጃህ ናቸው፡፡
https://t.me/SadatTextPosts
ተውሂድና ሱና አንድ ያደርጋሉ፣ የውሸተኛው አንድነት ፀር ናቸው፡፡
ሽርክና ቢድዐ ይበታትናሉ፣ የእውነተኛው አንድነት ፀር ናቸው፡፡
https://t.me/SadatTextPosts/58
አቂደቱል ዋሲጥያ በኡስታዝ ሙሐመድ ሲራጅ አቡ ኢምራን ከክፍል 1-25 የሚከተለውን የቴሌ ግራም ቻናል ጆይን በማለት ይጠቀሙ
https://t.me/Aqidetul_Wasiteya
ባሪከላሁ ፊኩም ሼር በማድረግ ለሌሎች ያዳርሱ
By Kal'amin Tsegaye
*መዲናሕ አረበኛ መፅሐፍ ሰዋሰዋዊ ማስታወሻ መፅሐፍ አንድ ሙሉእ*
በዚህ ሊንክ ተስፈንጥረው ዳውንሎድ ያድርጉ፡፡(http://bit.ly/2hBQsgF)
ሼር በማረግ እጅግ መሰረታዊ እውቀትን በነፃ ያሰራጩ!!
.
ማስታወሻ፡- ከዚህ በፊት የተለቀቀው ፒዲኤፍ የመፅሐፍ አንድን ቀዳማይ ክፍል ብቻ ያካተተ ሲሆን ይህ ግን ሌሎችም ርዕሶች ተካተውበት የመዲናህ መፅሐፍ ጥራዝ አንድ ሙሉውን ክፍል የዳሰሰ እጅግ ጠቃሚ ማስታወሻ ነው፡፡ የተዘለለ ክፍል አሊያ የትርጉም ስህተት ካስተዋሉ ይጠቁሙ!
-
በዚህ ክፍል ስር ከተቃኙ ርዕሶች ውስጥ
-
1. የንግግር ክፍሎች
2. አረበኛ ፊደሎች
3 .አናባቢ ቃላት
4. ማዕሪፋህ እና ነኪራህ
5. ይህ(هَذَا) vs. ያ (ذَلِكَ)
6. ፀሐያዊ እና ጨረቃዊ ቃላት
7. የስሞች መጨረሻ
8 .ስማዊ አረፍተነገር
9. هَمزَةُ الوَصَلِ وَهَمزَةُ القَطعِ
10. መስተዋድድ (حَرفُ جَرٍّ) & (مَجرُورٌ)
11. ገለልተኛ ተውላጠ ስም (ضَمِيرٌ مُنفَصِلٌ)
12. مُضَافٌ وَمُضَافٌ إِلَيهِ (ንብረትና ባለ ንብረት)
13. ፆታ
14. ምትክ (بَدَلٌ)
15. ተውሳከ ግስ (ظَرْفٌ)
16. ገላጭ (نَعتٌ)
17. አንፃራዊ ተውላጠ ስም (الاِسْمُ المَوْصُوْلُ)
18. አላፊ ግስ (الفِعْلُ المَاضِي)
19. ተቀጥያ ተውላጠ ስም (ضَمِيْرٌ مُتَّصِلٌ)
20 . خَبَرٌ مُقَدَّمٌ وَمُبتَدَأٌ مُؤَخَّرٌ (ቀዳማይ ዜና እና ዳህራይ ርዕስ )
21. ብዙ ቁጥር (جَمْعٌ)
22. ቁጥር (أَعدَادٌ)
23. ዲፕቶት (المَمنُوعُ مِنَ الصَّرفِ)
24. የኸበር አይነቶች (أَنوَاعُ الخَبرِ)

ዳውንሎድ ያድርጉ —- http://bit.ly/2hBQsgF