This program helps students build confidence and prepares them for future career opportunities in hospitality, catering services, and food industries. The class also promotes creativity, cooperation, and practical life skills that are valuable both at school and at home.
Forwarded from Edegilegn Kebedom
ለትምህርት ቤት ማህበረሰብ የቀረበ የክብር ጥሪ
የተከበራችሁ የትምህርት ቤት ርዕሰ መምህራን፣ መምህራን እና ውድ ተማሪዎች፤
በዛሬው እለት live የመከታተል ልዩ ጥሪ አቅርበንላችኋል
የቴሌግራም ቤተሰባችንን ይቀላቀሉ፦
ቴሌግራም ቻናል ሊንክ፦👉
https://t.me/Mekedonia7979
የመቄዶንያ ቀጥታ ስርጭት (Live)፦ ዛሬ 10፡00 ሰዓት ጀምሮ በቀጥታ ስርጭት እንድትከታተሉን በአክብሮት እንጋብዛችኋለን።
የዩቲዩብ ሊንክ፦👉 [ http://youtube.com/@mekedonia ]
"ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን በቂ ነው!"

Telegram
Mekedonia-መቄዶንያ
ይህ የቴሌግራም ግሩፕ ዓላማው ጎዳና ላይ ወድቀው የሚሰቃዩ አረጋውያኖችንና አዕምሮ ሕሙማንን በተለይም የአልጋ ቁራኛዎችን ለመርዳት ነው።
መቄዶንያ በአዲስ አበባ፣ ደሴ፣ ድሬዳዋ፣ ጋምቤላ፣ ጎሬ፣ አደዋ፣ ሐረር እና በአጠቃላይ 56 ቅርንጫፎችን በመክፈት ሰዎችን እየረዳ ነው።
ወደዚህ ቴሌግራም ግሩፕ ወዳጆቻችንን "Add" በማድረግ መልካም ነገር አብረን እንስራ!
www.youtube.com/@Mekedonia

Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
#BREAKING
የዒድ አልፈጥር በዓል አርብ (ጁምዓ) ይውላል።
ዛሬ የሸዋል ወር ጨረቃ ባለመታየቷ 1447ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል ከነገ ወዲያ አርብ (ጁምዓ) ተከብሮ ይውላል።
ዒድ ሙባረክ !
#Haramain
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መጋቢት 9 ቀን 2018
@tikvahethiopia

" ቀይ ስጋ እና ስብ የበዛበት ምግብ በተደጋጋሚ የሚበላ ሰው ለአንጀት ካንሰር ይዳርጋል፤ አመጋገብ ላይ ጥንቃቄ ይደረግ " - ፕሮፌሰር ብርሀኑ ቆጢሶ
በዓለም አቀፍ ደረጃ በየዓመቱ አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎች በአንጀት ካንሰር እንደሚጠቁ መረጃዎች ያሳያሉ።
በኢትዮጵያም በየዓመቱ ከሚመዘገቡ 80 ሺህ አዳዲስ የካንሰር ታማሚዎች መካከል ከ6 ሺህ በላይ የሚሆኑት በዚሁ በሽታ የሚጠቁ ወንዶች ናቸው። ሆኖም ትክክለኛው ቁጥር ከዚህም በላይ ሊሆን ይችላል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህን መረጃ ያገኘው የጤና ሚኒስቴር ከጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ጋር በመተባበር የመጋቢት ወር " የአንጀት ካንሰር ግንዛቤ ማስጨበጫ ወር " መሆኑን ምክንያት በማድረግ በሽታውን ለመከላከል ባዘጋጁት የንቅናቄ መድረክ ላይ ነው።
በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ትልቁ አንጀት ቀዶ ህክምና ሰብ ስፔሻሊቲ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ቆጢሶ ፤ " የአንጀት ካንሰር ከ50 ዓመት በላይ ባላቸው ሰዎች ላይ እየጨመረ ይሄዳል ቢባልም፣ በሀገራችን ግን ከ50 ዓመት በታች ያሉ #ወጣቶችም በዚህ በሽታ እየተጠቁ ነው " ብለዋል።
ፕሮፌሰር ብርሀኑ ቆጢሶ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በዝርዝር ምን አሉ ?
" የአንጀት ካንሰር እንደማንኛውም ካንሰር ድንገት የሚከሰት ነው። በሽታው የሚጀምረው የአንድ ሴል የእድገት ሁኔታ ሲለወጥ በሚፈጠር እብጠት ወይም ዕጢ ነው።
ይህ በሽታ በቁጥራዊ መረጃዎች ሲታይ ሲጋራ በሚያጨስ ሰው ላይ በዝቶ ይታያል። በጣም ጠጪ በሆነ ሰው ላይ መጠኑ የበለጠ ይታያል። ሲጋራ የማያጨስ ሰው የአንጀት ካንሰር ፈጽሞ አይዘውም ማለት ግን አይቻልም።
ቀይ ስጋ እና ስብ የበዛበት ምግብ በተደጋጋሚ የሚበላ ሰው ከሆነ ለአንጀት ካንሰር ይዳረጋል። በጥናትም የተረጋገጠ ነው። በተቻለ መጠን አመጋገብ ላይ ጥንቃቄ ማድረግ ተገቢ ነው።
ይህ በሽታ ከ50 አመት በላይ ባላቸው ሰዎች ላይ እየጨመረ እንደሚሔድ አለም አቀፍ መረጃዎች ይገልጻሉ። ጥናቶችም ያሳያሉ። እኛ ጋር ስንመጣ ከ50 አመት በታች ያሉ ወጣቶች በዚህ በሽታ እየተጠቁ ነው ያሉት። በሽታውም እየጨመረ ነው።
አሁን ባለን መረጃ መሰረት ኢትዮጵያ ውስጥ በወንዶች ላይ ካንሰሩ በብዛት እየታየ ነው። ስለዚህ በወንዶች ላይ የመጀመሪያው ካንሰር በሽታ ሆኖ እየተመዘገበም ነው። በዚህ በሽታ ሴቶች አይጠቁም ማለት አይቻልም። ሴቶች ላይ ግን ከጡት እና ከማህጸን በር ጫፍ ካንሰር በመቀጠል ሶስተኛ ደረጃ ላይ ያለ በሽታ ነው።
የበሽታው ምልክት የሚታየው በሽታው አድጎ ትልቅ ደረጃ ላይ ደርሷል በምንልበት ጊዜ ነው። በሽታው በውስጣችን ሆኖ ምንም የህመም ስሜት ላይሰማን ይችላል። ግን አልፎ አልፎ ፦
- የማስቀመጥ፣
- ደም የቀላቀለ እና ንፍጥ ነገር ያለበት ተቅማጥ መኖር ቀዳሚ ምልክቶቹ ናቸው። እንዲህ አይነት ምልክቶች ሲታዩ ወደ ጤና ተቋማት መሔድ አስፈላጊ ነው።
በአሁኑ ወቅት ህክምናው የሚሰጥባቸው ጥቁር አንበሳ፣ ቅዱስ ጳውሎስ፣ ዳግማዊ ምኒልክ፣ የካቲት 12 እና ጦር ሀይሎች ሆስፒታል ላይ ነው። የሰለጠነ ባለሙያ አስቀምጠናል በእነዚህ ቦታዎች ህክምናውን ማግኘት ይቻላል " ብለዋል።
በጤና ሚኒስቴር የበሽታ መከላከል እና መቆጣጠር መሪ ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ሕይወት ሰለሞን በበኩላቸው ፥ " ከ6,000 በላይ ሰዎች በአንጀት ካንሰር ይጠቃሉ ይባል እንጂ ይህ ቁጥር ትክክለኛ አይደለም፤ የበሽታውን መጠን የሚገልጽ አይደለም። ካልሆነ የበሽታውን ክብደት ማሳወቅ አንችልም፣ ከዚህ በኋላ የተቀናጀ ጥናት ማድረግ ይኖርብናል " ሲሉ አሳስበዋል።
አክለው " በሽታው ለታማሚው ራሱ በቀላሉ የሚታወቅ አይደለም። ስለዚህ እንደ ሀኪም ህብረተሰቡን የበሽታውን ምልክት ማሳየት፣ መግለፅ እና ለበሽታው አጋላጭ የሆኑትን ነገሮች ማሳወቅ ስራችን መሆን አለበት " ብለዋል።
" ብዙ ጊዜ በተቅማጥ የሚጠቁ ሰዎች አንድ እና ሁለት ጊዜ ከታዩ በኋላ ሁሌም የሆድ ጥገኛ ተህዋሲ ተብሎ ስለሚታሰብ በዚያው እየቆየ እንደሚሄድና በመጨረሻ ወደ ህክምና ሲመጡ በሽታውን ለማከም አዳጋች ነው " ሲሉ ገልጸዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA