Svenska Tech Group (STG)
18 subscribers
19 photos
5 files
34 links
Software Design Development and Implementation
Download Telegram
✴️ ሳምንታዊ ዜናዎች | ከቴክኖሎጂው አለም 📱

🔆 የSony Company አናውስ እንዳደረገው ከሆነ PlayStation 5 በወጣ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ በአለም ደረጃ ለ10 ሚሊዮን ሰወች እንደቸበቸቡ ተናግረዋል በPlaystion ሽያጭ ታሪክ ውስጥ በአጭር ግዜ በከፍተኛ ፍጥነት ከፍተኛ ሽያጭ ያስመዘገበ ነው ተብልዋል.

➲ Gamerሮች አረጋጉት

🔆 ''AbstractEmu'' የተባለ አደገኛ Malware በ Google Playstore ላይ መገኘቱ ተዘገበ Malwareሩ ከ7 በላይ በGoogle Playstoreላይ የተጫኑ አፕሊኬሽኖች አጥቅቷል Google በ Malwareሩ የተጠቁትን አፕሊኬሽኖች ወዲያው ያስወገደ ቢሆንም Remove ከመደረጉ በፊት በተጠቃሚዎች ዘንድ Download ተደርጓል
Malwareሩ አደገኛ ያደረገው አንዴ ስልካችን ላይ ከጫንን ቦሀሏ ራሱን ይደብቃል መረጃዎች ይሰርቃል Locationናችንን ይከታተላል.

🔆 በMalwareሩ የተጠቁት 7ቱ የአፕሊኬሽኖች ዝርዝሮች 👇
Anti-ads
BrowserData Saver
Life Launcher
My Phone
Night Light
All Passwords
Phone Plus

🔆 በMalware🐞 የተጠቁ መተግበሪያዎች በተደጋጋሚ Google Playstore ላይ መገኘታቸው የAndriod ተጠቃሚወችን ስጋት ውስጥ እየከተታቸው ነው😬

🔆 የGoogle Map አፕሊኬሽን በ 10Billion ስልኮች ላይ install እንደተደረገ Google ዘግቧል🔥

🔆 በአሜሪካ San Francisco የሚገኘው RiskIQ የተባለው የCyber Security Company ባደረገው ምርመራ Discord የተሰኘው የSocialmedia Platform ለተለያዩ ተንኮል አዘል አላማ ና ለMalicious Purposes ማለትም እንደ Hosting Malicious Botnet Malware Development ለመሳሰሉት ነገሮች ሃከሮች እየተጠቀሙ እንደሆነ RiskIQ ዘግቧል
😲

🔆 አንድ የCoinbase Crypto-currency ተጠቃሚ ከ አካውንቱ ውስጥ በ10 ደቂቃ ብቻ 11.6
ሚሊዮን $ መዘረፉ ተነገረ ባለቤቱ እንዳለው ማንነቱ ባልታወቀ ግለሰብ በተላከለት የScam Popup Notification እንደሆነ ና የCoinbase አካውንቱ እንደሚዘረጋ በማስጠንቀቅ በፍጥነት እንዲያመለከት በሚል Password እንደተሰረቀ ተናግሯል🤭😬

🔆 የተላከው Notification ከትክክለኛው የCoinbase Company እንዳልሆነ ተረጋግጧል


🔆 በHwang Dong-hyuk Directed ና Write የተደረገው በፈነጆቹ September 17 2021
የወጣው የSouth Koreaው Squid Game የተሰኘው Film በ Netflix ላይ ለእይታ በተለቀቀ በመጀመሪያ 4ሳምንት ውስጥ ብቻ ከ142 ሚሊዮን በላይ በአለምአቀፍ ደረጃ ተመልካቾቻችን ቀልብ ና ትኩረት የሳበ ሲሆን በNetflix በጣም ከፍተኛ Most Watched Series Movie ተብሏል
ፊልሙን ለተመልካች ለማድረስ 21.4 million የአሜሪካ Dollar አንጠፍጥፈዋል🤭

🔆 የSquid Game Directed ና Write የሆነው
Hwang Dong-hyuk እንደተናገረው
Squid Game Season 2 ለመመልከት ምናልባትም እስከ 2023 መጠበቅ እንዳለባቸው ለተመልካቹ አሳዉቋል.
ፊልሙን የጀመራችሁ እንግዲህ ተንቆራጠጡ 😆
©Tech በ አማርኛ

Svenska Tech Group(STG)
join & share
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/stggroup
Temperature.apk
2.1 MB
ሙቀታቹን በስልካችሁ የምትለኩበት አፕ

Svenska Tech Group(STG)
join & share
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/stggroup
#የሞባይል_ሚስጥራዊ_ኮዶች!

1ኛ. ሞባይሉ ዉስጥ ያለዉን ስልክ ቁጥር ለማግኘት፡-*111#ይደውሉ

2ኛ. የሞባይል ሚስጥረ ቁጥር/IMEI/ serial No፡-*#06#

3ኛ. ስልክዎ ሲደወልሎት ይህ ቁጥር አገልግሎት ላይ አልዋለም እንዲልላችሁ ከፈለጋቹ!
ወደ *21*900# ይደውሉ ወይም 1 ዲጂት በመቀነስ ወደ ራስዎ ስልክ ማድረግ!
ለምሳሌ ስልክ ቁጥርዎ 0910654321 ከሆነ ወደ *21*091065432# ይደውሉ
ለማጥፋት ሲፈልጉ #21# ብለው ይደውሉ! ከላይ የተገለጸው በ900 ቦታ የፈለጉት ሌላ ትክክለኛ የስልክ ቁጥር ያልሆነም ማድረግ ይችላሉ!

➜ሁሉም ጥሪዎችና መልእክቶች ወደ ሌላ ቁጥር ዳይቨርት ለማድረግ ሲልጉ
*21*0144123456# በ0144123456 ቦታ የፈለጉትን የሞባይል ወይም መደበኛ ስልክ ቁጥር ያስገቡ
ቀድሞ ወደ ነበረበት ለመመለስ ከፈለጉ #21# ብለው ይደውሉ ማለትም ስልክዎ ዳይቨርት ከተደረገ #21# ሲደውሉ ወደ ኖርማል ይመለሳል ዳይቨርቱ ይጠፋል
*#21# ከሆነ ስልኩ ዳይቨርት ተደርገዋል ወይስ አልተደረገም የሚል መረጃ ይሰጠናል

4ኛ. ስልክዎ ቢዚ ብቻ ሲሆን ዳይቨርት ለማድረግ *67*የፈለጉትቁጥር# ብለው ይደውሉ! ይህንን ዳይቨርት ለማጥፋት #67# ይደውሉ

5ኛ. ስልክዎ ካልተነሳ ብቻ ዳይቨርት ለማደረግ *61*የፈለጉትቁጥር# ይደውሉ!
ይህንን ዳይቨርት ለማጥፋት #61# ይደውሉ

6ኛ. ስልክዎ ከኔትዎርክ ዉጪ ብቻ ሲሆን ዳይቨርት ለማድረግ
*62*የፈለጉትቁጥር# ይደውሉ! ይህንን ለማጥፋት ሲፈልጉ #62# ብለው ይደውሉ!

7ኛ. ኮል ወይቲንግ አክቲቭ ለማደረግ ሲፈልጉ *43# ብለው ይደውሉ! ኮል ወይቲንግ ለማጥፋት ሲፈልጉ #43# ብለው ይደውሉ! ኮልወይቲንግ አክቲቬት መደረጉ ወይም አለመደረጉ ለማወቅ *#43# መደወል

Svenska Tech Group(STG)
join & share
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/stggroup
#ስለ_Google_አስር_የሚያስደንቁ_ነገሮች

ስለጉግል 10 ሊያስገርምዎ የሚችሉ መረጃዎች እነሆ ። 👇👇👇👇

ስያሜው
ግን ጉግል ምን ማለት ነው? ጉግል ስያሜውን ያገኘው በስህተት ነው።
በእንግሊዝኛው 'googol' ማለት በሂሳብ ቀመር 1 እና መቶ ዜሮዎች ማለት ነው።
እና ተሜው ተሳስቶ ስያሜውን ጉጎል ወደ ጉግል አመጣው፤ የጉግል ፈጣሪዎችም ይህንን ቃል ለመጠቀም መረጡ።

የጀርባ ማሻ
የጉግል ፈጣሪዎች ላሪ ፔጅ እና ሰርጌይ ብሪን ለጉግል የሰጡት የቀድሞ ስም በእንግሊዝኛው 'Backrub' ወይም የጀርባ ማሻ የሚል ትርጓሜ ሊሰጠው የሚችል ቃል ነበር።
ምክንያቱም ሰዎች ፈልገው የሚያገኙት መረጃ ጉግል ላይ ከሰፈሩ ሌሎች ድረ ገፆች ስለሆነ። ኋላ ላይ ስሙን ሊቀይሩት ተገደዱ እንጂ።

የተንጋደደ
ጉግል ንግድ እና ጠንከር ያሉ ጉዳዮች ብቻ ሳይሆኑ ጨዋታዎችም ይገኛሉ።
እንደማሳያ እስቲ ወደ ጉግል ይሂዱና ይህችን "askew" የእንግሊዝኛ ቃል መፈለጊያው ላይ ይፃፉት።

ፍየሎች
ጉግል አረጓንዴ ምድርን እደግፋለሁ ይላል፤ ለዚህም ነው የመሥሪያ ቤቱን ሳር ማጨጃ ማሽኖች በፍየሎች የተካው። አሜሪካ ካሊፎርኒያ ክፍለ ግዛት የሚገኘው የጉግል ዋና መሥሪያ ቤት ውስጥ 200 ያህል ፍየሎች ወዲያ ወዲህ ሲሉ ተመልክተው የየትኛው አርብቶ አደር ዘመናይ ግቢ ነው ብለው እንዳይደናገሩ። ፍየሎቹ የጉግል ናቸውና።

እየተመነደገ የሚገኝ 'ቢዝነስ'
ጂሜይል፣ ጉግል ማፕ፣ ጉግል ድራይቭ፣ ጉግል ክሮም ከተሰኙት በተጨማሪ ከፈረንጆቹ 2010 ጀምሮ ጉግል በየጊዜው የተለያዩ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎችን የግሉ ሲያደርግ ቆይቷል።
ሊያውቁትም ላያውቁትም ይችላሉ ግን እኛ እንንገርዎ፤ አንድሮይድ፣ ዩትዩብ፣ እንዲሁም አድሲን የተሰኙት ቴክኖሎጂዎች የጉግል ንበረቶች ናቸው።
ከሌሎች 70 ያክል ኩባንያዎች በተጨማሪ ማለት ነው።

ዱድል
ዱድል የተሰኘው የጉግል ውድድር መድረክ አሜሪካ የሚገኙ ተማሪዎች የድርጅቱን ምልክት ፈጠራቸውን ተጠቅመው እንደአዲስ እንዲቀርፁት የሚያበረታታ ነው።
ይህ ውድድር ከተጀመረ ወዲህ የጉግል አርማ በየቀኑ ሲቀያየር ይስተዋላል።
አንዳንዴም በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከበሩ ቀናት በማስመልከት የጉግል መለያ ይለዋወጣል።

ለሌሎች ያመለጠ ዕድል
በፈረንጆቹ 1999 ላሪ እና ሰርጌይ «ኧረ ጉግልን በአንድ ሚሊዮን ዶላር የሚገዛን» እያሉ ቢወትወቱ የሚሰሙ ጠፋ።
ዋጋው ላይ መደራደር ይቻላል ቢሉም ምንም ምላሽ አልተገኘም።
አሁን የጉግል ዋጋ ከ300 ቢሊዮን ዶላር በላይ ሆኗል፤ ሚሊዮን አላልንም፤ ልብ ያርጉ ቢሊዮን ነው።

መሪ ቃላት
'ከይሲ አይሁኑ' ከድርጅቱ ቀደምት መሪ ቃላት አንዱ ነበር።
'ምን አገባው' የሚሉ ብዙዎች ቢኖሩም ድርጅቱ ይህን መሪ ቃል አልተውም ብሎ ሙጥኝ ብሏል።

ምግብማ ግድ ነው
ከጉግል ባለቤቶች አንዱ የሆነው ሰርጌይ ብሪን ነው አሉ ማንኛውም የጉግል ቢሮ አካባቢ ምግብ የሚገኝበት አማራጭ መኖር አለበት ብሎ ያዘዘው፤ በቢዛ 60 ሜትር ርቀት ላይ።
የጉግል ኩባንያ ሠራተኞች ቢሯቸው እጅግ ያሸበረቀና ምግብ ባሰኛቸው ጊዜ ወጣ ብለው ሊመገቡበት የሚችሉበት እንደሆነም ይነገራል።

የጉግል ባልንጀራ
የጉግል ኩባንያ ሠራተኞች ውሾቻቸውን ወደ ሥራ ቦታቸው ይዘው መምጣት ይፈቅዳለቸዋል።
ውሾቹም ከቢሮው ነባራዊ ሁኔታ ጋር ራሳቸውን እንዲያመቻቹ ሥልጠና ይሰጣቸዋል።

ምንጭ፦BBC AMAHARIC

Svenska Tech Group(STG)
join & share
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/stggroup
የሳምንቱ Technology News

፩ YouTube የDislike Buttonኑን ከPublic እይታ ወደ Private ሊቀይር ነው ይሄም ማለት YouTube ላይ የሚለቀቁትን ማንኛውንም Video ተመልካቹ ወይም ግለሰብ Dislike ቢያደርግ ያን Dislike ሌሎች ሰወች ማየት አይችሉም ለChannleሉ ባለቤት ብቻ ይታያል ማለት ነው

YouTube ይሄንን ያደረገበት ምክንያት (Dislike Attackን) ለመከላከል ነው Dislike Attack ማለት አንዳንድ ሰወች በግልም በGroupፕም በመሆን ሆን ብለው አንዳንድ የYouTube Channelሎችን ኢላማ   በማድረግ እዛ Channle ላይ የሚለቀቁትን Video Dislike ያደርጋሉ ይሄ ደግሞ የChannel Creatorች ላይ ከፍተኛ ጮና እያሳደረ በመሆኑ ነው

፪ የGoogle ኩባንያ ምርት የሆኑት Pixel 6 ና 6 Pro ስልኮች ካሜራቸውን በመጠቀም የስልኩን ባለቤት የልብና የትንፋሽ መጠንን የሚለካ ና የሚከታተል Feature ይዞ መቷል

፫ Apple ና Microsoft ሁለቱም በአሁኑ ጊዜ ዋጋቸው 2.5 ትሪሊዮን💲አካባቢ ነው

፬ የYouTube የማስታወቂያ ገቢው በሦስተኛው ሩብ ዓመት 7.2 ቢሊዮን ዶላር አድርሷል

፭ Gmail በአንዳንድ ሀገራት የመቆራረጠ ችግር ገጥሞታል ብዙ ተጠቃሚወችም ችግሩን ለ Google Report እያደረጉ ነው በUS UK ና Europe ያሉ ሰወች የGmail አካውንታቸውን Login ለማድረግ እየተቸገሩ ነው

Google ችግሩን Fix ለማድረግ ተፍ ተፍ እያለ ይገኛል።

Svenska Tech Group(STG)
join & share
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/stggroup
#የፌስቡክ_ፕሮፋይላችንን_እንዴት_መቆለፍ_እንችላለን?

የፌስቡክ ፐሮፋይላችሁን እንድትቆልፉ እመክራለሁ፡፡

ፌስቡክ ላይ ፖስት የምታደርጉት ፎቶ፤ቪዲዮ፤ ወይም መልዕክት ከፌስቡክ ጋደኞቻችን ውጪ ሌላ ሰው እንዳያየው ለማድረግ ፐሮፋይላችንን መቆለፍ ይኖርብናል፡፡

እንዲሁም ፕሮፋይላችንንም ከጋደኞቻችን ውጪ ሌላ ሰው እንዳያይ ፕሮፋይላችንን መቆለፍ አለበት፡፡

ለአንድሮይድ ስልኮች ላይ ብቻ ነው ይሄ አገልግሎት ያለው፡፡iOS ስልኮች ላይ አይገኝም፡፡

እንዴት ነው የፌስቡክ ፕሮፋይላችንን ሎክ /መቆለፍ የምንችለው?

1ኛ፦ፌስቡክ አፕሊኬሽን እንከፍትና ወደ ፕሮፋይላችንን እንገባለን

2ኛ፦ በቀኝ በኩል በመደዳ የሚታዩትን ሶስት ነጥቦችን ክሊክ ማድረግ፤

3ኛ፦ “Lock Profile” የሚል አማራጭ ሲመጣ እሱን ክሊክ ማድረግ፤

4ኛ፦ ቀጥሎ “Lock Your Profile“ የሚል ምርጫ ከስር ይመጣል፡እሱን ክሊክ ማድረግ፤

5ኛ፦ በመጨረሻ‘You Locked Your Profile' የሚል ይመጣል፤እዛው ላይ OK ብለን እንጨርሳለን፡፡

አሁን ፌስቡክ ፕሮፋይላችን ተቆልፋል፡፡

ፕሮፋይላችንን ጨምሮ ፖስት የምናደርጋቸው ፎቶዎች፤ቪዲዮዎች እና መልዕክቶች ከፌስቡክ ጋደኞቻችን ውጪ ሌላ ማንም ሰው ማየት አይችልም፡፡

Svenska Tech Group(STG)
join & share
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/stggroup
✴️ቴሌግራም የክፍያ ማስታወቂያዎችን ለመጀመር በሙከራ ላይ ነኝ ብሏል።

📍የመልዕክት መለዋወጫ መተግበሪያ የሆነው ቴሌግራም የክፍያ ማስታወቂያ ሥርዓት ለመጀመር በሙከራ ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል። ይህ ሥርዓትም ቢያንስ ከ1000 በላይ ተከታይ ባላቸው ቻናሎች ላይ እንደሚጀመር ነው የገለጸው።

📍ከዚህ ቀደም የክፍያ ማስታወቂያ ሥርዓት የሌለው ቴሌግራም አሁን ላይ ተጠቃሚዎች ቻናላቸውንና ቦታቸውን በክፍያ እንዲያስተዋውቁ የሚያስችላቸውን አሰራር መዘርጋቱን ነው ይፋ ያደረገው።

📍የቴሌግራም መስራች እንዲሁም ዋና ስራ አስኪያጅ ፓቬል ዱሮቭ እንደጠቀሰው በሙከራ ላይ የሚገኘው የክፍያ ማስታወቂያ ሥርዓቱ የቴሌግራም ተጠቃሚዎችን የግል መረጃን አይጠቀምም ብሏል።

📍ከዚሁ ጋር ተያይዞ ማስታወቂያዎቹ በግል እና በቡድን መልዕክት መለዋወጫ ሰሌዳዎች ላይ የማይታዩ መሆናቸውንና በክፍያ የሚቀርቡት ማስታወቂያዎች በቻናሎች ላይ ብቻ እንደሚቀርቡ ገልጿል።

📍ማስታወቂያ ማስነገር የሚፈልጉ አስተዋዋቂዎች ቻናላቸውን ወይም ቡታቸውን ከ160 ባልበለጡ ፊደላት ገለጻ ማድረግ የሚችሉ ሲሆን በቋንቋ፣ በይዘት እንዲሁም በልዩነት ማስታወቂያው እንዲተላለፍላቸው የሚፈልጉትን ቻናል መርጠው ማስተዋወቅ ይችላሉ ተብሏል።

📍ቴሌግራም ከቻናል ባለቤቶች ጋር የትርፍ ክፍፍል የማድረግ እቅድ እንዳለውም ያስታወቀ ሲሆን ይህ የሚሆነው ግን መሰረታዊ ወጪዎቹን ከሸፈነ በኋላ እንደሆነ ገልጿል።

©Tikivah Magazine

Svenska Tech Group(STG)
join & share
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/stggroup
📮ሳፋሪ ኮም ኢትዮጵያ በእቅዱ መሠረት ሥራውን ለመጀመር ቅድመ-ዝግጅቶችን በማጠናቀቅ ላይ ነው ተባለ፡፡

መንግሥት የቴሌኮም ኢንዱስትሪውን ለግል ኢንቨስትመንት ክፍት ካደረገ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በውድድር አሸናፊ ሆኖ ወደ ሀገር ውስጥ በመግባት ሥራ ለመጀመር ዝግጅት በማድረግ ላይ የሚገኘው ‘ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ’ ቅድመ ዝግጅቶቹን በማጠናቀቅ ላይ ይገኛል ተብሏል፡፡

ፈቃድ ሰጪውና ተቆጣጣሪው ተቋም የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለሥልጣን፤ ከኩባንያው ጋር ባካሄደው ውይይት በቅርቡ የኩባንያው ሠራተኞች ከአገር እንደወጡ ተደርጎ በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን ስለተሰጠው መረጃ የባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ባልቻ ሬባ ማብራሪያ መጠየቃቸው ተሰምቷል፡፡

የኩባንያው ሥራ አስፈፃሚዎችም ለተፈጠረው ሁኔታ ይቅርታ ጠይቀው፣ ኩባንያው ላለፉት 5 ወራት አስፈላጊ በሆኑ የኔትዎርክ ዲዛይን፣ ቦታ የመምረጥ እንዲሁም ከውጪ የሚገቡ መሣሪያዎችን የማስገባትና የሰው ኃይል የማሟላት ሥራዎችን ሲያከናውን መቆየቱን ተናግረዋል፡፡

የቅድመ-ዝግጅት ሥራዎቹ እንደተጠናቀቁም ኩባንያው ወደ ስራ እንደሚገባና በፈቃድ ስምምነቱ መሠረት በወቅቱ አገልግሎት መስጠት ለመጀመር እንደሚንቀሳቀስ ተናግረዋል ተብሏል፡፡

በውይይቱ ላይ እስካሁን ድረስ በሥራው ላይ የተፈጠረ እንቅፋትም ሆነ የሚያዘገዩ ጉዳዮች እንዳላጋጠሙት የጠቀሰው ኩባንያው፣ በአዲስ አበባና በተለያዩ ክልሎች አብዛኞቹ ሥራዎች በታቀደላቸው ጊዜ እየተከናወኑ መሆናቸውን ተናግሯል።

ኩባንያው ከባለስልጣን መሥሪያ ቤቱ ጋር ተቀራርቦ እንደሚሰራና ዝግጅቱን አጠናቆም እ.ኤ.አ. በሚያዝያ 2022 አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር ተናግሯል ሲል ሸገር ኤፍ ኤም ዘግቧል።
©Tikvah Magazine

Svenska Tech Group(STG)
join & share
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/stggroup
✴️ ኢትዮጵያ ውድ የኢንተርኔት ክፍያ ከሚያስከፍሉ ሀገራት በቀዳሚነት ተቀመጠች

📍መቀመጫውን በዩናይትድ ኪንግደም ያደረገ 'ፕራይስ ኮምፓሪዝን' የተሰኘ የምርምር ተቋም አደረግኩት ባለው አዲስ ጥናት በዓለማችን ውድ የኢንተርኔት ክፍያ ከሚጠይቁ 10 ሀገራት መካከል ኢትዮጵያን በአንደኛ ደረጃ ላይ አስቀምጧታል።

📍ጥናቱ በኢትዮጵያ የብሮድባንድ ኢንተርኔት አገልግሎት በወር በ307.84 ዩሮ ገደማ እንደሆነ በመግለጽ ይህ ዋጋ ኢትዮጵያን በዓለም ላይ ከሚገኙት ሀገራት ከፍተኛ ዋጋ የሚጠየቅባት ሀገር ያደርጋታል ብሏል።

📍ይህም ለወርሃዊ ብሮድባንድ ኢንተርኔት አገልግሎት ሽያጭ በአማካኝ 30.99 ዩሮ ከምትጠይቀዉ ዩናይትድ ኪንግደም ጋር በንፅፅር ሲቀመጥ የኢትዮጵያ ዋጋ ወደ አስር እጥፍ እንደሚጠጋ ተጠቁሟል።

📍ውድ የኢንተርኔት አገልግሎት ክፍያ ታሪፍ ካለባቸዉ ሀገራት መካከል ለብሮድባንድ ኢንተርኔት አገልግሎት በወር 236.09 ዩሮ የምታስከፍለዉ የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ በሁለተኛ ደረጃ ተቀምጣለች።

📍በተቃራኒው በጥናቱ በአለም ላይ የብሮድባንድ ኢንተርኔት አገልግሎት በርካሽ ዋጋ ከሚገኝባቸው ሀገራት ተርታ መካከል ዩክሬን የአንደኝነት ደረጃን የያዘች ሲሆን ለአገልግሎቱ የሚከፈለዉ ወርሃዊ ክፍያ በአማካኝ 4.42 ፓውንድ ብቻ መሆኑ ተገልጿል።
©Tikvah Magazine

Svenska Tech Group(STG)
join & share
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/stggroup
Forwarded from ETHIO-MEREJA®
የአርቲስት ዳዊት ፅጌ ሀገራዊ ሙዚቃ ተለቀቀ!

ዳዊት ፅጌ - አንቺን ብዬ🎶
----------------------------
ከምድር ተመርጣ ለኔ የተሰጠች
ብዙ ሚስጥር ያላት አሀሀ፣ ሃገር አለች

ሁሉን ነገር ችዬ እንድኖር ያስቻለኝ
ፍቅርሽ ነው በምድር ሀገሬ እኔ ያለኝ
....... ይቀጥላል።👇
https://youtu.be/1LvtPJBVF7k

ሼር/share
T.me/ethio_mereja
✳️ጠቃሚ መረጃ የ H + ፣ H ፣ 3G ፣ E እና 4G በይነመረብ ግንኙነት ትርጉም
ከላይ የተጠቀሱት ምልክቶች ሁሉ እርስዎ የተገናኙበትን የመረጃ አይነት ያሳያሉ እና ይህ በእያንዳንዱ ISP ፍጥነት እና ምልክት ምልክቶች ይለያያል ፡፡
ከዚህ በታች የእያንዳንዱ ግንኙነት ማጠቃለያ እና የማውረድ ፍጥነት ነው፡፡
G = 14 KB
E = 48 KB
3G = 395 KB
H = 1.75 MB/s
H+ = 21MB
4G = 37Mb
5G = እስቲ ገምቱ??

Svenska Tech Group(STG)
join & share
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/stggroup
Telegram X v. 0.24.2.1473 arm64.apk
22.1 MB
ቴሌግራም በድሮ ቨርዥኖች መስራት ስላቆመ ሁላችሁም የምትጠቀሙበትን አፕ #Update አድርጉት 👆👆👆👆

Svenska Tech Group(STG)
join & share
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/stggroup
A.F-1.pdf
229.5 KB
#MiT

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የፈጠራ ሥራ ሃሳብ ውድድር ለማድረግ ተወዳዳሪዎች እየመዘገበ ነው።

የኅብረተሰብን ችግር ሊቀርፉ እና ህይወትን በማዘመን አስተዋጽዖ ሊያበረክቱ የሚችሉ የፈጠራ ሃሳብ ያላቸው መመዝገብ ይችላሉ ተብሏል።

ተማሪዎች፣ ግለሰቦች፣ ቡድኖች፣ ተመራማሪዎች እና ተቋማት በውድድሩ እንዲሳተፉ ሚኒስቴሩ ጥሪውን አቅርቧል፡፡

ለመመዝገብ ተከታዩን ሊንክ ይጫኑ፦

https://mint.gov.et/wp-content/uploads/2022/03/A.F-1.pdf
ቴሌግራምዎን hack እንዳይደረግብዎ ይፈልጋሉ?
መፍትሄውን እነሆ

❖ቴሌግራም ማለት እንደ ማንኛውም የ messaging application ነው ማለትም እንደ⇝whatsapp, viber, imo, tango.....etc
📌ቴሌግራም እንደ whatsapp, viber,imo...ሁሉ በቀላሉ በ "sms-based verification process" hack ሊደረግ ይችላል

ይህ ዘዴ ሌሎች hack ማድረጊያ hacking Tricks ሳያስፈልገን አፕሊኬሽኖች በመጠቀም
ማለትም የራሳችን ቴሌግራም አፕሊኬሽን ላይ ወይም pc ላይ ቴሌግራም install በማድረግ የምንፈልገውን ቁጥር በማስገባት ኮዱን ካስላክን ብኋላ ኮዱን የምናገኝበት አጋጣሚ ካለ....

በመጀመሪያም ይህ መሆኑን እና አለመሆኑን ለማረጋገጥ አሁን step by step ተከታተሉ
❶Telegram⇢seting⇢privecy and security⇢active session ላይ በመግባት በእናንተ አካውንት የገባ ሰው እንዳለና እንደሌለ ማወቅ ያስችላል።

■Note: እራስዎ በሌላ አፕ ከገቡም ያመጣልዎታል ስለዚህ በደንብ ይመልከቱ።

📌ከዛም Terminate all other sessions ክሊክ በሉት።
☛ ይህ ሚጠቅመው በሌላ ስልክ የእናንተን አካውንት የሚጠቀም ሰው ካለ remove ያደርገዋል።

⓶ Security ደግሞ ለማጠናከር
seting⇢privecy and security⇢two step verification⇢set aditional pasword ከዛ የፈለጉትን password ***..ግን የ gmail አካውንት ሊኖራቹ ይገባል።

❖ ይህ ጠንካራ የሚባለው #የቴሌግራም security ነው።

❖ የሚጠቅመው እንደፌስቡክ ሁላ በሌላ ስልክ ስንገባ password ይጠይቀናል (log in) እያልን ነው የምንገባው ማለት ነው።
====================
❖ ሌላ ሰው በsms የተላከውን ኮዳችሁን አግኝቶ እንኳ ቢከፍተው
ወደቴሌግራማችሁ በጭራሽ መግባት አይችልም።
====================
❖ ማንም ሰው ለመግባት በኢሜል የሰጣችሁት ኮድ ማወቅ ስለማይችል በጭራሽ መግባት አይችልም።

⚠️የፃፋችሁትን password እንዳትረሱት።

Svenska Tech Group(STG)
join & share
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/stggroup
*The most important words*
1.*PAN* - permanent account number.
2. *PDF* - portable document format.
3. *SIM* - Subscriber Identity Module.
4. *ATM* - Automated Teller machine.
5. *IFSC* - Indian Financial System Code.
6. *FSSAI(Fssai)* - Food Safety & Standards Authority of India.
7. *Wi-Fi* - Wireless fidelity.
8. *GOOGLE* - Global Organization Of Oriented Group Language Of Earth.
9. *YAHOO* - Yet Another Hierarchical Officious Oracle.
10. *WINDOW* - Wide Interactive Network
Development for Office work Solution.
11. *COMPUTER* - Common Oriented Machine. Particularly United and used under Technical and Educational Research.
12. *VIRUS* - Vital Information Resources Under Siege.
13. *UMTS* - Universal Mobile Telecommunications System.
14. *AMOLED* - Active-matrix organic light-emitting diode.
15. *OLED* - Organic light-emitting diode.
16. *IMEI* - International Mobile Equipment Identity.
17. *ESN* - Electronic Serial Number.
18. *UPS* - Uninterruptible power supply.
19. *HDMI* - High -Definition Multimedia
Interface.
20. *VPN* - Virtual private network.
21. *APN* - Access Point Name.
22. *LED* - Light emitting diode.
23. *DLNA* - Digital Living Network Alliance.
24. *RAM* - Random access memory.
25. *ROM* - Read only memory.
26. *VGA* - Video Graphics Array.
27. *QVGA* - Quarter Video Graphics Array.
28. *WVGA* - Wide video graphics array.
29. *WXGA* - Widescreen Extended Graphics Array.
30. *USB* - Universal serial Bus.

Svenska Tech Group(STG)
join & share
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/stggroup
❖አንዳንድ የኮምፒውተር #ክፍሎች ማብራሪያ

❶. #RAM (Random Access Memory)

ራም (RAM) ፕሮግራሞችን እና ዳታዎችን ይይዛል የሚኖረው መጠን ትልቅ በሆነ መጠን ውስብስብ የሆኑ ፕሮግራሞችን በቀላሉ ለመጠቀም እና ብዙ ዳታዎችን ለማገናዘብ ይችላል:: የራም ብቃት በሜጋ ባይት ይለካል::
(1 MG= 1 Million character) በአሁኑ ሰአት የምንጠቀምባቸው የግል ኮምፒዎተሮች (Personal computer) ከ512MB በላይ ራም ይኖራቸዋል::

❷. #ኤክስፓሽን_እስሎት (Expansion slot)

ማዘር ቦርድ የምንለው የኮምፒውተሩ አካል ላይ የሚገኝ ሶኬት ሲሆን Expansion card በቀላሉ በላዩ ላይ ለመሰካት ያገለግላል የምንጠቀምበት ኮምፒውተር ብዙ Expansion slot ባሉት ቁጥር ብዙ ተጨማሪ የኮምፒውተሩን አገልግሎት የሚጨምሩ ሁኔታዎችን ለመጠቀም ይረዳል:: Expansion slot ሌላው መጠሪያ Expansion bus እንለዋለን::

❸. #Heat_sinker

ሂት ሲንከር የምንለው ማዘርቦርድ ላየሚገኝ ሲሆን ስራውም
#Fan በተባለ Divice አማካኝነት ንፁ አየርን ተቀብሎ #CPU ስራውን በስርአቱ እንዲሰራ ያደርገዋል:: ይህ ማለት Cpu ብዙ ስራዎችን ሲሰራ ሙቀት ይፈጥራል Heat sinker ደግሞ ያቀዘቅዘዋል::

❹.#Fan

ፈን ብለን የምንጠራው ደግሞ ያው ከላይ እንዳየነው ንፁ አየር ወደ ኮምፒውተራችን ያደርጋል:: ይህ ማለት ቬንትሌተር እንደሚሰጠው ጥቅም ማለት ነው::

#CPU

#CPU ስለ ተባለው ዋነኛ እና ዋነኛ Divice እንመለከታለን::

#CPU (the brain of computer) ወይም የComputer አእምሮ እየተባለ የሚጠራው ይሄ Divice የኮምፒውተራችንን ሙሉ ስራ የሚሰራልን ነው::የትኛውንም አይነት ስራ ኮምፒውተር ላይ ከፍታቹ ስትሰሩ እና የምትፈልጉት ውጤት ወደናንተ የሚመጣው በተአምረኛው # CPU በተባለ Divice ነው::
ይህም የሚከናወነው በማይክሮ ሰከንድ ውስጥ ነው::

#CPU (Central procssing unit) ሶስት ዋና ክፍሎች አሉት እነሱም
:
▫️1. #Control_unit ይሄ የCpu ክፍል የሚሰራ ስራ ሁሉንም የኮምፒውተር ስራ መቆጣጠር ነው::ይሄ ማለት አንድ ሰው Computer ላይ ቁጭ ብሎ የሚፈልገውን ሙሉ ትእዛዝ የሚፈፀምለት በዚሁ control unit ውስጥ ነው::
:
▫️2. #Arthmatic and # logic_unit ሌላኛው ደግሞ arthmatic and logic unit በመባል የሚጠራው ሲሆን የተለያዩ ሂሳብ ነክ ነገሮችን ለመስራት ያገለግላል::
:
▫️3. #Regster
ይሄ ደግሞ # Cpu ላይ የሚገኝ ትንሽዬ ሚሞሪ ነው::
ይሂም #Cpu የሚሰራቸውን ስራዎች ይመዘግብልናል ማለት ነው::

#Port (ፓርት)
:
port ከኮምፒውተሩ ጀርባ የሚገኝ አገናኝ ሶኬት ነው:: በዚህም መሰረት ማንኛውም ውጫዊ የኮምፒውተር ክፍል የሚገናኙበት ቦታ ነው::

መመሪያዎችና መረጃዎች በዚሁ መስመር አማካኝነት ከኮምፒውተር አካላት መሀከል ኪቦርድ,ፕሪንተር,ማውስ, እና ሌሎችም ዩተለያዩ አካላት በየራሳቸው የማገናኛ ገመድና ሶኬት ከኮምፒውተር አካል ጋር በማገናኘት አስፈላጊውን ስራ ያከናውናሉ::

የኮምፒውተሩ ስርአቱ ያለ ችግር እንዲሰራ እነኝህ ክፍሎች በትክክል እርስ በራሳቸው ከተያያዙ በህዋላ ከሀይል ጋር መገናኘት አለበት:: ከሀይ ምንጭ ጋር ማገናኘት ስንፈልግ ሁል ግዜ #ኤሌክትሪክ #ጠፍቶ መሆን አለበት ይህም በተለያዩ ክፍሎች ላይ ብልሽትን ለመከላከል ነው::

#Power_Supply (የኤሌትሪክ ሀይል)

power supply በኮምፒውተሩ አካል የሀይል ሰጭ ክፍል ነው ይህም ክፍል የኤሌክትሪክ ሀይል ለኮምፒውተሩ አቅም በሚመጥን ለውጦ ለኮምፒውተሩ አገልግሎት ያቀርባል:: በሌላ አነጋገር Power supply convert Alternative current (AC) to Direct current (DC). Aalternative current ማለት የኤሌክትሪክ ሀይሉ ከሶኬቱ (ከማከፋፈያው) የሚመጣው ያልተመጠነ የኤሌክትሪክ ሀይል ሲሆን Direct current ደግሞ Power supply የሚቀበለው የተመጠነ የኤሌክትሪክ ሀይል ነው ማለት ነው::

የኤሌክትሪክ ሀይል መለክያ ዋት (Watt) ይባላል::ለአንድ ኮምፒውተር አገልግሎት 200 ወይም 230 ዋት በቂ ሀይል ነው::ይህንንም የኤሌክትሪክ ሀይል ለሴቶች የፀጉር ማድረቂያ ማሽን (ካስክ) ጋር ስናመዛዝነው ኮምፒውተሩ ከሚፈልገው የኤሌክትሪክ መጠን ሰባት እጥፍ ይፈልጋል::


#ሞደም (Modem):-

ይህ መሳርያ አገልግሎቱ ኮምፒዪተሩን ከስልክ መስመር ጋር በማያያዝ ለመረጃ ልውውጥ ያገለግላል::ሞደም በኤሌክትሪክ ለሚተላለፍ መልእክቶች (E-mail) በተለያዩ ቢሮ ውስጥ ኮምፒዩተሮች በማገናኘት መረጃን ለመለዋወጥ ያገለግላል::የተለያዩ የሞደም አይነቶች ሲኖሩ ፍጥነታቸውም እንዲሁ የተለየ ነው::
:

#ኪቦርድ Keybord:-

መረጃን ወደ ኮምፒዪተር ለማስገባት በፅሁፍ መሳርያነት የሚያገለግል መሳርያ ሲሆን ለዚህም አገልግሎት ይረዳ ዘንድ ፊደላት ቁጥሮች ምልክቶችና ሌሎች ቁልፎች በመጫን የተፃፈውን በምስል ማሳያው (Screen) ላይ እናያለን::
ውድ የቲታ(አደይ) ግሩፕ ፣ የቲታ(ኑኑ) ግሩፕ፣ ግጥምና ትረካ በቲታ(ኑኑ)፣ ግጥምና ትረካ በቲታ(ኑኑ) ሃሳብ መስጫ Svenska Tech Group(STG) ፣ EthiodDog Accessory፣ All In One online Shoping ፣ Abyssinia Online Store እናሽ Amandina's Home Made ICE Cream ቤተሰቦች የገናን በዓልን  ምክንያት በማድረግ  እረዳት ፣ ጧሪ ቀባሪና ደጋፊና አጉራሽ የሌላቸው  እና በተለያየ ምክንያት ኑሮዋቸውን በጎዳና ላይ ላደረጉ ወገኖቻችንን ምግብ የመመገብ፣ ልብስ የማልበስ እና በዓልን አብረውን እንዲያሳልፉ እንዲሁም እረዳት ጧሪ ቀባሪ እና ደጋፊና አጉራሽ የሌላቸውን ደግሞ ቤት ለቤት ለበዓል ዶሮ ፣ እንቁላል፣ ዘይት ፣ ፍርኖ ዱቄት እና ሽንኩርት ለማከፋፈል #የሐገር ፍቅር በጎ አድራጎት ድርጅት ማህበር የበኩሉን አስተዋፅኦ እያደረገ ይገኛል እነሆ እርሶም ወገኖቻችንን ለመርዳት በጉልበት ፣ በገንዘብ ፣ በአስቤዛ እና አልባሳትን በማሰባሰብ  ለበዓሉ በጎዳና ላይ ካሉ ወገኖቻችን ጋር ቤተሰባዊ ጊዜ ለማሳለፍ እና ለመመገብ  ለመርዳት በዓሉን አብረን ለማሳለፍ አስበናል። ውድ  ቤተሰቦቻችን በማንኛውም ሙያ ውስጥ ያላችሁ በአርቱ ሞያ ውስጥ ያላችሁ እና በሞዴሊንግ ሙያ ውስጥ ያላችሁ ውድ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ በበጎ ፈቃደኝነት ስራው ላይ ለመሳተፍ የመርዳት ፍላጎት ያላችሁ በሙሉ እድሉን ያላገኛችሁ #ከሀገር ፍቅር በጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በመሆን የበጎ ፍቃድ ስራዎችን በመስራት እድሉ እንድትጠቀሙ ተመቻችቶላችኋል ሁላችሁም ይህን በጎ አላማ በመሳተፍ ሁላችሁ የበኩላችሁን እንድትወጡ በልዑል እግዚአብሔር ስም ዝቅ ብዬ እጠይቃለሁ #የሀገር ፍቅር በጎ አድራጎት ድርጅት የክብር አማባሳደር አርቲስት ትዝታ አሸናፊ (ቲታ(ኑኑ) ነኝ ሁላችሁም እግዚአብሔር ያክብርልኝ! እነዚህን ወገኖቻችንን ለመርዳት በስልክ ቁጥር +251937678839 / 0901052854 ️ላይ በመደወል ወይም👉 ሀገር ፍቅር የበጎ አድራጎት ድርጅት የንግድ ባንክ አካውንት 1000347502557 👈 ላይ ገቢ በማድረግ እና ፈቃደኝነታችሁን በመግለፅ ቃል በመግባት መመዝገብ  ትችላላችሁ #ያለውን የሰጠ ንፉግ አይባልም! ስለምታደርጉልን ትብብር እጅግ በጣም እናመሰግናለን ክብረት ይስጥልን

#መልካምነት መልሶ ይከፍለናል!
ዋና ዋና የሳይበር ጥቃት አይነቶች

መረጃ ጠላፊዎች የግለሰቦችን ኮምፒውተር፣ የስልክ፣ የባንክ ካርድ እና ማንኛውንም በይነመረብ ላይ ያኖሩትን መረጃ በርብረው ሊመነትፉ ይችላሉ።

የሳይበር ጥቃት በግለሰብ ደረጃ ሲፈጸም ጉዳቱ እጅግ አስደንጋጭ ባይሆንም ችግሩ በአገር ደረጃ መዋቅራዊ ጉዳትን ያስከትላል ተብሏል።

የሳይበር ጥቃቶች በተለያዩ የማጥቂያ መንገዶች የሚፈጸሙ ሲሆን÷ በሳይበር ምህዳሩ በስፋት ከተለመዱ ከሳይበር ጥቃት አይነቶች ውስጥ የአገልግሎት መቋረጥ፣ የዲፌስምነት ጥቃት፣ የማልዌር ጥቃት፣ ስፓምናየፌሺንግ ጥቃቶች ናቸው፡፡

የአገልግሎት መቋረጥ ይህ የሳይበር ጥቃት አይነት የሲስተሞችን አቅም ባልተፈለገ ሁኔታ በማጨናነቅ ህጋዊ ተጠቃሚው አገልግሎት እንዳያገኝ ማድረግ ነው፡፡

የዲፌስምነት ጥቃት ( መልክን የመቀየር ጥቃት ) ሆን ተብሎ እና ሳይጠበቅ ጣልቃ በመግባት መደበኛ የኮምፒውተር ተግባርን የሚያውክ የጥቃት አይነት ነው።

የማልዌር ጥቃት የተጠቂውን ድረ- ገጽ በሀሰተኛ ሰነዶች በመቀየር የሚፈጸም የጥቃት አይነት ሲሆን÷ ስፓም (Spam): ደግሞ ብዛት ያለው እና የአጥፊነት ተልዕኮ ያላቸው ኢሜሎችን በመላክ የሚፈጸም የጥቃት አይነት ነው ተብሏል፡፡

የፊሺንግ ጥቃት የሚባለው የሳይበር ጥቃት የተለያዩ የማታለያ እና የማዘናጊያ ዘዴዎችን በመጠቀም አጭበርባሪዎች ከተጠቃሚዎች ሚስጥራዊ የሆኑ መረጃዎችን ለመመዝበር የሚደረግ የማህበራዊ ምህንድስና ጥቃት ነው።
✳️ የሞባይል ባንኪንግ ሲጠቀሙ ሊያደርጓቸው የሚገቡ ጥንቃቄዎች

🚩የሞባይል ባንኪንግ የባንክ አገልግሎቶችን ወደ ባንኮች ቅርንጫፍ መሄድ ሳያስፈልግ በተንቀሳቃሽ ስልኮች አማካኝነት ብቻ የባንክ አገልግሎቶችን ማለትም ገንዘብ መላክ እና መቀበል እንዲሁም የተለያዩ ክፍያዎችን ለመፈፀም የሚያስችል ቴክኖሎጂ ነው፡፡

🚩የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት የተጠቃሚዎችን ድካም ከመቀነስ ጋር በተያያዘ አገልግሎቱን ተመራጭና ቀላል ያደርገዋል፤ ታዲያ ይህ አገልግሎት የቴክኖሎጂ ውጤት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ተጓዳኝ የመረጃ መረብ ጥቃት ተጋላጭነት አያጣውም፡፡

🚩ተጠቃሚዎች አገልግሎቱን ሲጠቀሙ የሚከተሉትን ጉዳዮች ሊያውቋቸው እና ጥንቃቄ ሊያደርጉባቸው ይገባል ሲል የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር ይመክራል፡፡

➊. የተረጋገጡና ትክክለኛ የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያዎችን (application) ከተረጋገጡ ምንጮች አውርዶ መጠቀም፦ የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያዎች ትክክለኛ በባንኩ እውቅና ያላቸው መሆኑንና የሚገኙትም በትክክለኛው የመተግበሪያ ቋት ማለትም ለአንድሮይድ የመተግበሪያ ቋት ወይም ለአይ.ኦ.ኤስ ኦፕሬቲንግ ሲስተም በማውረድ መጠቀም ተገቢ ነዉ፡፡

➋. በስልኮች ላይ ያሉ ሌሎች መተግበሪያዎች ፍቃዶችን ማጥናት፡- በስልክዎ ላይ የሚገኙ ሌሎች መተግበሪያዎች የሚጠይቋቸውን ግንኙነቶች (አክሰስ) ልብ ይበሉ፡፡
መተግበሪያዎች ለአገልግሎቶቻቸው ከሚያስፈልጋቸው የሞባይል መረጃ ዉጪ ሌሎች መረጃዎች እንዲዳረሱ እንዳይፈቅዱ፡፡

➌. አፕሊኬሽኖችን /መተግበሪያዎችን ማዘመን፡- በስልኮች ላይ የሚገኙ የባንኪንግ መጠቀሚያ መተግበሪያዎችን ወቅቱን ጠብቀዉ ያዘምኑ፡፡
መተግበሪያዎች ላይ ለስርቆት የሚዳርጋቸው ክፍተቶች ሲገኙ በየወቅቱ ማዘመኛ ስለሚለቀቅላቸው የደህንነት ክፍተቶቹን ለመድፈንና የባንክ ሂሳብዎን ደህንነት ለማስጠበቅ በየጊዜው ያዘምኗቸው፡፡

➍. የሞባይል ስልክ ኦፕሬቲንግ ሲስተምን ማዘመን፡- የስልክዎን ደህንነት ክፍተት ለመሙላት በየጊዜው ክፍተት መሙያና ማሻሻያ እድሳቶች ስለሚለቀቁ በየወቅቱ እየተከታተሉ ያዘምኗቸው፡፡

➎. ከህዝብ መገልገያ ዋይፋይ ይልቅ የሞባይል ዳታ ይጠቀሙ፡- የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎቶችን በሞባይልዎ ለመጠቀም ለህዝብ መገልገያ የቀረቡ ነፃ ዋይፋዮችን ከመጠቀም ይልቅ የሞባይል ዳታዎችን ይጠቀሙ፡፡

➏. ዘርፈ-ብዙ የደህንነት ማስጠበቂያ የይለፍ-ቃሎችን ይጠቀሙ፦ ሞባይል ስልክዎን በአሻራ፣ ፊት ማንበብያ (ፌስ ሪኮግኒሽን)፣ ፓተርን፣ ፓስወርድ እና ፓስ ኮድ የመሳሰሉትን በመጠቀም ስልክዎን ይቆልፉ፡፡

➐. በማህበራዊ ሚዲያ የሚለቋቸውን ግላዊ መረጃዎች ይገድቡ፡- በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የሚለቀቁ መረጃዎች የተገደቡ ሊሆኑ ይገባል፡፡

➑. ፀረ-ቫይረስ (ማልዌር) ይጠቀሙ

➒. የሞባይል ስልክዎን አካላዊ ደህንነት ያስጠብቁ

➓. የባንክ ሂሳብዎን ዘወትር ይከታተሉ፡- በተጨማሪ ተገቢውን ሁሉ ጥናቃቄ ካደረጉ በኋላም ስለ ባንክ አካውንትዎ የሚደርሱ ማንቂያዎችን (notifications) በአግባቡ መከታተል እንዲሁም በየጊዜው ስለ አካውንትዎ ሁናቴ (ስታተስ) መከታተል እና የማያውቁት የሂሳብ ለውጥ ካለ በአፋጣኝ ለባንክዎ ያሳውቁ፡፡