SOCIAL SCIENCE(S.S)
264 subscribers
567 photos
12 videos
757 files
74 links
👉 MID,FINAL,MODEL,MATRIC🇪🇹
💪(G9-12) Social science subject
😊 Question🙋 and Learning outcome🏆

📯 share 🏆
Download Telegram
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
ትምህርት ሚኒስቴር፣ የተቋምና የትምህርት መስክ ምርጫ ጊዜ መራዘሙን አሳውቋል።

በ2018 ዓ.ም. የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ሰርተፊኬት ፈተና ወስደው በመደበኛው የትምህርት መርሃ ግብር የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋምና የትምህርት መስክ ምርጫ ማጠናቀቂያ ቀን እስከ መስከረም 5 ቀን 2019 ዓ/ም መራዘሙን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

በመሆኑም በተለያዩ ምክንያቶች ምርጫቸውን እስካሁን ያላስገቡ ተማሪዎች የተቋምና የትምህርት መስክ ምርጫቸውን እስከ መስከረም 5 ቀን ማጠናቀቅ ይችላሉ ተብሏል።

ተማሪዎች ምርጫቸውን ለማስገባት student.ethernet.edu.et የተሰኘውን ድረ-ገጽ በመጠቀም የራሳቸውን ፋይዳ (የመለያ ቁጥር) በማስገባት ሂደቱን እንዲያጠናቅቁ መልዕክት ተላልፏል።

#MoE

@tikvahethiopia
❤2
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
የሪሚዲያል መርሃ ግብር የዩኒቨርሲቲ ቅበላ መቁረጫ ነጥብ ይፋ ሆነ።

ለ2019 ዓ/ም የሪሚዲያል መርሃ ግብር ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት የሚያስችላቸው የመቁረጫ ነጥብ በተማሪዎች ውጤት፣ በዩኒቨርሲቲዎች የቅበላ አቅም፣ እና በሀገራዊ የትምህርት ፍትሃዊነት መርህ ላይ ተመስርቶ መወሰኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

በዚህም መሰረት ከታችን የተገለጸውን ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ለሪሚዲያል መርሃ ግብር የዩኒቨርሲቲ ቅበላ ብቁ መሆናቸውን ሚኒስቴሩ አሳውቋል።

1. የተፈጥሮ እና የማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 👉 ከ600 ውስጥ 240 እና ከዚያ በላይ (40%)

2. የተፈጥሮ እና የማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች 👉 ከ600 ውስጥ 228 እና ከዚያ በላይ (38%)

በልዩ ድጋፍ የሚታይ የተማሪ ምድብ

1. ከአፋር፣ ሶማሌ፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ እና ጋምቤላ ክልሎች የተፈጥሮ ወይም ማህበራዊ ሳይንስ ለተፈተኑ ወንድና ሴት ተማሪዎች 👉 ከ600 ውስጥ 222 እና ከዚያ በላይ (37%)

2. ከአርብቶ አደርና ከፊል አርብቶ አደር አካባቢዎች የተፈጥሮ ወይም ማህበራዊ ሳይንስ ለተፈተኑ ተማሪዎች 👉 ከ600 ውስጥ 222 እና ከዚያ በላይ (37%)

3. በማህበራዊ ሳይንስ የተፈተኑ ዓይነ ስውር ወንድና ሴት ተማሪዎች 👉 ከ500 ውስጥ 185 እና ከዚያ በላይ (37%)

4. በተፈጥሮ ወይም በማህበራዊ ሳይንስ የተፈተኑ መስማት የተሳናቸው ወንድና ሴት ተማሪዎች 👉 ከ600 ውስጥ 222 እና ከዚያ በላይ (37%)

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 4 ቀን 2019 ዓ/ም

@tikvahethiopia
Forwarded from Remedial HUB
🧑‍🎓 በ2018 የትምህርት ዘመን ሪሚዲያል (Remedial) ተማሪዎችን የተቀበሉ ዩኒቨርሲቲዎች ዝርዝር፦

🔻ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ
🔺ጎንደር ዩኒቨርሲቲ
🔹ወሎ ዩኒቨርሲቲ
🔻ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ
🔺ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ
🔹ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ
🔻መቀሌ ዩኒቨርሲቲ
🔺ወለጋ ዩኒቨርሲቲ
🔹ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ
🔻አምቦ ዩኒቨርሲቲ
🔺መቱ ዩኒቨርሲቲ
🔹ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ
🔻ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ
🔺ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ
🔹አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
🔻ዲላ ዩኒቨርሲቲ
🔺ወቸሞ ዩኒቨርሲቲ
🔹ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ
🔻ጂንካ ዩኒቨርሲቲ
🔺ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ
🔹ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ
🔻ወራቤ ዩኒቨርሲቲ
🔺ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ
🔹ሰመራ ዩኒቨርሲቲ
🔻አሶሳ ዩኒቨርሲቲ

@Remedial_Hub ✔️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤2
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
#ምደባ

የትምህርት ሚኒስቴር የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን የዩኒቨርሲቲ ምደባ ማጠናቀቁን አስታወቀ።

ምደባው የተማሪዎችን ውጤትና ምርጫ፣ የዩኒቨርሲቲዎችን የቅበላ አቅም፣ የክልል፣ የወረዳ፣ የዞን እና የትምህርት ቤት ስርጭት እንዲሁም የፆታ ሚዛን ታሳቢ በማድረግ መከናወኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

በተጨማሪም ከ600 ነጥብ 500 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ ተማሪዎች በመጀመሪያ ምርጫቸው መመደባቸውን አስታውቋል።

ተማሪዎች የምደባ ውጤታቸውን በተዘጋጀው የኦንላይን ሥርዓት https://student.ethernet.edu.et/view-placement ማየት ይችላሉ ብሏል።

ቅሬታ ያላቸው ምደባው ይፋ ከሆነበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ በኦንላይን  ፦ https://student.ethernet.edu.et/complaints ብቻ ቅሬታ ማቅረብ እንደሚችሉ ተገልጿል።

መስከረም 6 ቀን 2019 ዓ/ም

@tikvahethiopia
❤2
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
70 በመቶ ተማሪዎች ከተማሩበት ክልል ወይም ዞን ውጭ እንዲመደቡ ተደረገ።

የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ የተደረገ ሲሆን አንዱ ታሳቢ የተደረገው የተማሪዎች የክልል፣ የዞን፣ የወረዳና የትምህርት ቤት ስርጭት መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

በዚህም 70 በመቶ የሚሆኑ ተማሪዎች ከተማሩበት ክልል ወይም ዞን ውጭ ወደሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች፣ 30 በመቶዎቹ ደግሞ በተማሩበት ክልል ወይም ዞን ውስጥ ወደሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲመደቡ መደረጉን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

በተጨማሪ የዞን፣ የወረዳ እና የትምህርት ቤት ስርጭት በምደባው ሂደት ታሳቢ ተደርጎ መመደቡንም ገልጿል።

ምደባ ለማየት ፦ https://student.ethernet.edu.et/view-placement

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 6 ቀን 2019 ዓ/ም

@tikvahethiopia
❤1
Forwarded from Tikvah-University
#MoE
 
የሪሚዲያል ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምርጫ አድርጉ ተብሏል፡፡
 
በ2018 ዓ.ም የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ የሪሚዲያል ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምደባ ምርጫችሁን ከመስከረም 7-11/2019 ዓ.ም ድረስ እንድታደርጉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡
 
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለመምረጥ 👇
https://student.ethernet.edu.et/preferences
 
@tikvahuniversity
❤1
Forwarded from ስኬት Freshman 2019
ለከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች በሙሉ የተሰጠ ጠቃሚ ማሳሰቢያ!

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ላይ "ዩኒቨርሲቲ/ካምፓስ ልዋወጥ" (Campus Exchange / Student Swap) የሚሉ ጥሪዎች እና ማስታወቂያዎች ፍጹም ሐሰተኛ እና ሕገ-ወጥ መሆናቸውን እንገልጻለን።

ሊታወቁ የሚገባቸው ዋና ዋና ነጥቦች፦

የተማሪዎች ለውጥ (Swap) የለም፦ በሁለት ተማሪዎች መካከል በስምምነት የሚደረግ የካምፓስ ወይም የትምህርት ክፍል ዝውውር በትምህርት ሚኒስቴር አሰራር ውስጥ የለም።

ዝውውር የሚካሄደው በሕጋዊ መንገድ ብቻ ነው፦ የዩኒቨርሲቲ ዝውውር የሚከናወነው በትምህርት ሚኒስቴር እና በዩኒቨርሲቲዎቹ የተማሪዎች አገልግሎት (Student Affairs) በኩል፣ በተወሰነ ጊዜ በሚከፈት ሕጋዊ ፖርታል ብቻ ነው።

ለማጭበርበር አትጋለጡ፦ "ካምፓስ አስቀይራለሁ" ወይም "እንለዋወጥ" በሚሉ የማህበራዊ ሚዲያ ልጥፎች በመታለል ገንዘባችሁን፣ ጊዜያችሁን እና ግልጽ መረጃችሁን አሳልፋችሁ እንዳትሰጡ።

መረጃውን ለሌሎች ጓደኞቻችሁ ሼር (Share) በማድረግ ከማጭበርበር ይታደጓቸው!

📥Join Our Channel👉
@Siket_Freshman_2019
Forwarded from SOCIAL SCIENCE GROUP (:)
ከቤተሰብ ባትርቁ እና ቅርብ የሆነ university ብትሞሉ እመክራለሁ!
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
ምደባ ይፋ ሆነ።
 
በ2018 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና ወስደው በሪሚዲያል (Remedial) መርሃ ግብር የመግቢያ ውጤት ላስመዘገቡ እና በ2019 ዓ.ም በትግራይ ክልል በሚገኙ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ለተመደቡ ተማሪዎች ምደባ ይፋ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋቃ።
 
በሪሚዲያል (Remedial) መርሃ ግብር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተመደቡበትን ዩኒቨርሲቲ በሚከተለው ማስፈንጠሪያ (Link) በመግባት መመልከት ይችላሉ።
👉 https://student.ethernet.edu.et/view-placement

ቅሬታ ለማቅረብ፡ https://student.ethernet.edu.et/complaints ተጠቀሙ ተብሏል።
 
በሌላ በኩል፤ በዝውውር በጊዜያዊነት ከትግራይ ክልል ውጪ ወደሚገኙ ሌሎች የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የተመደቡ አዲስ ገቢ ተማሪዎች የተመደቡበትን ዩኒቨርሲቲ በሚከተለው ማስፈንጠሪያ (Link) በመግባት መመልከት እንደሚችሉ ተገልጿል።
 
👉 https://student.ethernet.edu.et/view-placement  

እንዲሁም በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ሲማሩ የነበሩ ነባር ተማሪዎች በጊዜያዊነት የተመደቡበትን ዩኒቨርሲቲ በ https://student.ethernet.edu.et/university-transfer/ ማስፈንጠሪያ በመግባት የራሳችሀውን ፋይዳ (የመለያ ቁጥር) በመጠቀም መመልከት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

#MoE
መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ/ም

@tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ክፍያ ከ750 ወደ 2,000 ብር ከፍ አለ።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ለሚሰጣቸው ልዩ ልዩ አገልግሎቶች የሚከፈል ክፍያን የሚያሻሽል አዲስ ደንብ ወጥቷል።

በዚህም ቀደም ሲል 750 ብር የነበረው የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና (Exit Exam) ክፍያ ወደ 2,000 ብር ከፍ ብሏል። ከዚህ ውስጥ 500 ብር የምዝገባ፣ 1,500 ብር ደግሞ የፈተና ክፍያ ሲሆን፣ ለውጭ ዜጎች 100 ዶላር ተወስኗል።

በተጨማሪም፦

👉 የድህረ-ምረቃ መግቢያ ፈተና (NGAT) ፦ ለኢትዮጵያውያን 3,500 ብር፤ 500 ብር የምዝገባና 3,000 ብር የፈተና ክፍያ። ለውጭ ዜጎች 100 ዶላር።

👉 የ12ኛ ክፍል ፈተና ምዝገባ ፦ ለኢትዮጵያውያን 950 ብር፤ ለውጭ ዜጎች 100 ዶላር።

👉 የሙያ ፈቃድና ብቃት ምዘና ፦ ለኢትዮጵያውያን 3,500 ብር፤ 1,000 ብር የምዝገባና 2,500 ብር የፈተና ክፍያ። ለውጭ ዜጎች 150 ዶላር።

👉 የትምህርት ማስረጃ ምትክ ሰርተፊኬት ፦ ለኢትዮጵያውያን 600 ብር ፤ ለውጭ ዜጎች 115 ዶላር።

👉 ምትክ ሰርተፊኬትና ማረጋገጫ ፦ ለኢትዮጵያውያን 900 ብር ፤ ለውጭ ዜጎች 170 ዶላር።

👉 የትምህርት ማስረጃ ማረጋገጥ/ማጣራት ፦ ለኢትዮጵያውያን 400 ብር፤ ለውጭ ዜጎች 75 ዶላር።

👉 በስም ላይ የፊደል ግድፈት ለማስተካከል ፦ ለኢትዮጵያውያን 700 ብር፤ ለውጭ ዜጎች 130 ዶላር።

👉
ኦፊሴላዊ ትራንስክሪፕት መላክ ፦ ለኢትዮጵያውያን 750 ብር፤ ለውጭ ዜጎች 50 ዶላር።

የፈተና ውጤት መረጃን ለምርምር ለሚጠይቁ ተቋማት በአንድ ጥናት 10,000 ብር፣ ለውጭ ተቋማት 1,875 ዶላር ክፍያ ተወስኗል። ለግለሰቦች ደግሞ ለኢትዮጵያውያን 1,000 ብር፣ ለውጭ ዜጎች 190 ዶላር እንደሚከፈል ተገልጿል።

በተጨማሪም ያገለገሉ የምዘና መሳሪያዎችን ለመጠቀም ከጠቅላላ ወጪው 5 በመቶ፣ አዲስ የምዘና መሳሪያ ለማዘጋጀት ደግሞ 10 በመቶ ክፍያ እንደሚፈጸም ደንቡ ያስቀምጣል።

ደንቡ ለሌሎች የምዘናና የማረጋገጫ አገልግሎቶችም አዳዲስ የክፍያ ተመኖችን አካቷል።

የተሻሻለው ደንብ ቁጥር 593/2018 ሙሉ ይዘት ከላይ በተያያዘው ምስል ላይ ይገኛል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 17 ቀን 2019 ዓ/ም

@tikvahethiopia