SOA COMMUNITY POLICE 2 CAMPUS
606 subscribers
784 photos
39 videos
81 files
34 links
ይህ ድህረ ገፅ የተለያዩ የትምህርት አይነቶች አጠቃሎ የያዘ ሲሆን የሚለቀቁት ጥያቄዎችም ሆኑ ማስታወሻዎች በቀላሉ ታገኛላችሁ። በ👉👉👉SOAPO2
Download Telegram
የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ት/ፅ/ቤት የ2015 ዓ.ም የትምህርት አፈፃፀም እና ግምገማ በቀን 17/12/2015 ዓ.ም አከናውኗል።
በዚህም ለግልና ለመንግስት ት/ቤቶች በ6ኛ እና 8ኛ ክፍል የሚኒስትሪ ውጤት ከፍተኛ ነጥብ ያስመዘገቡ ተማሪዎች እና ት/ቤቶች የእውቅና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። በመሆኑም ከ6ኛ ክፍል ተማሪ ፀደንያ ስለሺ ከክፍለ ከተማ ከፍተኛ ነጥብ በማምጣት ሰርተፍኬት እና የ2000 ብር ተሸላሚ ሆናለች። በተመሳሳይ ት/ቤታችን በ6ኛ እና 8ኛ ክፍል የሚኒስትሪ ውጤት እጅግ ከፍተኛ ነጥብ በማስመዝገብ የዋንጫ እና ሰርተፍኬት ሽልማት ማግኘት ችሏል። ለዚህ ውጤት መሳካት ከፍተኛ ሚና የተጫወታችሁ መምህራን የአስተዳደር ሰራተኞች የተማሪ ወላጆች እና ሌሎችንም ጭምር ከልብ እናመሰግናለን።

🙏🙏SOA የስኬት ት/ቤት
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በቀን 18 እና 19/12/2015 ዓ.ም 30ኛው የትምህርት ጉባኤ አሰመልክቶ ውይይት አከናውኗል።
በዚህም የ6ኛ ክፍል የሚኒስትሪ ውጤት ከፍተኛ ነጥብ ያስመዘገበችው ተማሪ
👉 ፀደኒያ ስለሺ
ከአዲስ አበባ የግልና የመንግስት ት/ቤት ከሚማሩ ተማሪዎች ጋር በመፎካከር ከፍተኛ ነጥብ ካስመዘገቡ ተማሪዎች መካከል አንዷ በመሆኗ የታብሌት እና ሰርተፍኬት ተሸላሚ ሆናለች። በተመሳሳይ ት/ቤታችንም በከተማ ደረጃ እውቅና ማግኘት ችሏል።
የምስራች👏👏
በቀን 11/01/2016 ዓ.ም በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 09 ት/ፅ/ቤት አማካኝነት የ2015 ዓ.ም መማር ማስተማር ሂደት በክፍል እና በሚኒስትሪ ውጤት ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። በተመሳሳይ ት/ቤታችንም የእውቅና ሽልማት ማግኘት ችሏል።