SDA የትንቢት ጹሑፎች
2.09K subscribers
203 photos
18 videos
160 files
183 links
“ዘመኑ ቀርቦአል፤ እንግዲህ ይህን የትንቢት ቃል የሚያነብ ብፁዕ ነው፤ የሚሰሙትና የተጻፈውንም የሚጠብቁ ብፁዓን ናቸው።”
— ራእይ 1፥3 (አዲሱ መ.ት)
Download Telegram
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የትኛውም መጽሐፍ ከሐይማኖት መጽሐፍ ልቆ አናገኝም የሰው ልጅ የሰው ልጅን ሀሳብ ተረድቶ ዓለምን መቀየር ከቻለ የፈጣሪን ሀሳብ ቢረዳ ደግሞ ምን ልፈጥር እንደሚችል መገመት ይቻላል!
የመጨረሻው ዘመን ክስተቶች

                     ምዕራፍ 2

➡️ የክርስቶስ በቶሎ የመመለስ ምልክቶች

                        (ክፍል አንድ)

             ➡️ የጌታችን ታላቁ ትንቢት

ስለ ኢየሩሳሌም ጥፋትና የሰው ልጅ ከመምጣቱ በፊት ስለሚከሰቱ ምልክቶች ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱን አስጠንቅቆ ነበር። የማቴዎስ ወንጌል 24ኛው ምዕራፍ በሙሉ ከዚህ ክስተት በፊት የሚፈጸሙ ትንቢቶችን የሚመለከት ሲሆን የኢየሩሳሌም ጥፋት ደግሞ በመጨረሻ ዓለም በሞላ በታላቅ እሳት እንደሚጠፋ በምሳሌነት የሚያሳይ ነው።— Manuscript 77, 1899.

ክርስቶስ በደብረ ዘይት ከተማ ከእርሱ ዳግም ምጽዓት በፊት የሚከሰቱ አስፈሪ ፍርዶችን አንድ በአንድ ዘረዘረ። “ጦርንም የጦርንም ወሬ ትሰሙ ዘንድ አላችሁ።…ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣልና ራብም ቸነፈርም የምድርም መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራ ይሆናል፤ እነዚህም ሁሉ የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸው" (ማቴዎስ 24:6-8)። እነዚህ ትንቢቶች በኢየሩሳሌም ጥፋት ከፊል ፍጻሜ ቢያገኙም ቀጥተኛ ተፈጻሚነት የሚያገኙት በመጨረሻዎቹ ቀናት ነው።—Testimonies for the Church 5:753 (1899).

          ➡️ ምልክቶች በሰማያት

ታላቁ ጳጳሳዊው ስደት ሲጠናቀቅ ፀሐይ እንደሚጨልምና ጨረቃ ብርሃኗን እንደማትሰጥ ክርስቶስ ተናግሮ ነበር። ቀጥሎም ከዋክብት ከሰማይ ወደ ምድር ይወድቃሉ። ኢየሱስ እንዲህ ብሏል፡- "ምሳሌውን ከበለስ ተማሩ፤ ጫፍዋ ሲለሰልስ ቅጠልዋም ሲያቆጠቁጥ፣ ያን ጊዜ በጋ እንደቀረበ ታውቃላችሁ። እንዲሁ እናንተ ደግሞ ይህን ሁሉ ስታዩ በደጅ እንደቀረበ እወቁ።” (ማቴዎስ 24:32፣ 33)።

ክርስቶስ የመምጫውን ምልክቶች ሰጥቷል። የእርሱ መምጫ ሲቀርብና በደጅ ሲሆን እንደምናውቅ ተናግሮአል። “ይህ ሁሉ እስኪሆን ድረስ ይህ ትውልድ አያልፍም:: እነዚህ ምልክቶች ሆነው አልፈዋል።. [ታላቁ ተጋድሎ የሚለውን መጽሐፍ ገጽ 306-308፣ 333፣ 334ን ይመልከቱ።] አሁን የጌታ መምጣት ቅርብ መሆኑን በእርግጠኝነት እናውቃለን ።-The Desire of Ages, 632 (1898).

           ➡️ ምልክቶች በምድር ላይ

ኢየሱስ እንዲህ ብሏል፡- “በፀሐይና በጨረቃም በከዋክብትም ምልክት ይሆናል፤ በምድር ላይም አህዛብ ከባህሩና ከሞገዱ ድምጽ የተነሣ እያመነቱ ይጨነቃሉ” (ሉቃስ 21:25፤ ማቴዎስ 24:29፤ ማርቆስ 13:24-26፤ ራዕይ 6:12-17)። የመምጫው አመላካች የሆኑ እነዚህን ነገሮች የሚመለከቱ ሰዎች “በቅርብ፣ እንዲያውም በደጅ መሆኑን ያውቃሉ" (ማቴዎስ 24:33). -The Great Controversy, 37, 38 (1911).

ሕዝቦች በአመጽ ውስጥ ናቸው። ግራ የሚያጋቡ ጊዜያት በላያችን ናቸው፡፡ በምድር ላይ እየመጡ ካሉ ነገሮች የተነሣ የሰዎች ልብ እየደከመ ነው፡፡ ነገር ግን በእግዚአብሔር የሚያምኑ ሰዎች በወጀቡ መካከል “እኔ ነኝ፤ አትፍሩ" የሚለውን የእግዚአብሔርን ድምጽ ይሰማሉ።:-The Signs of the Times, October 9, 1901.

በሰማይ መጻሕፍት ውስጥ እንግዳና አስደናቂ ታሪክ እየተጻፈ ነው– ከታላቁ የእግዚአብሔር ቀን ትንሽ ቀድመው እንደሚከሰቱ የተነገሩ ክስተቶች። በዓለም ላይ ያለው ነገር በሙሉ ባልተረጋጋ ሁኔታ ውስጥ ይገኛል።—-Manuscript Releases 3:313 (1908).

ይቀጥላል ...
👍6
የመጨረሻው ዘመን ክስተቶች

ምዕራፍ 2

➡️ የክርስቶስ በቶሎ የመመለስ ምልክቶች

(ክፍል ሁለት)

➡️ ሀሰተኛ ነቢያት

ኢየሱስ የኢየሩሳሌም ጥፋት ምልክቶች ከሆኑት ነገሮች አንዱን እንዲህ በማለት ገልጾ ነበር፡-“ብዙ ሀሰተኛ ነቢያቶች ይነሣሉ፣ ብዙዎችንም ያስታሉ" (ማቴ. 24:11)። ሀሰተኛ ነቢያት ሰዎችን እያሳቱና ብዙዎችን ወደ ምድረ በዳ እየመሩ ተነስተዋል፡፡ አስማተኞችና መተተኞች ተዓምራዊ ኃይል እንዳለቸው በመናገር ሕዝቡን ወደ ተራራማ ብቸኛ ስፍራዎች እንዲከተሉአቸው ስበዋል። ነገር ግን ይህ ትንቢት የተነገረው ስለ መጨረሻዎቹ ቀናትም ጭምር ነው። ይህ ምልክት የተሰጠው እንደ ዳግም ምጽዓት ምልክት ነው። The Desire of Ages, 631 (1898).

በሀሰት «ነን›› የሚሉ ንግግሮች ያጋጥሙናል፣ ሀሰተኛ ነቢያቶች ይነሳሉ፣ ሀሰተኛ ህልሞችና ራዕዮች ይኖራሉ፣ ነገር ግን ቃሉን ስበኩ፤ በቃሉ ውስጥ ካለው ከእግዚአብሔር ድምፅ ወደ ሌላ አትውሰዱ ። --Selected Messages 2:49 (1894).

በተለየ ሁኔታ ከእግዚአብሔር እንደተማሩ የሚናገሩና ሌሎችን ለመምራት የሚሞከሩ ሰዎችን እንዳይ ተደርጌያለሁ። እነዚህ ሰዎች ስለ ሥራ ካሉአቸው የተሳሳቱ ሀሳቦች የተነሣ እግዚአብሔር በፍጹም ያልሰጣቸውን ሥራ ይሰራሉ። የዚህ ውጤቱ ውዝግብ ነው፡፡ እያንዳንዱ ግለሰብ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለመረዳት እግዚአብሔርን ከእውነተኛ ልቡ ተግቶ ይፈልግ። -- Selected Messages 2:72 (1893).

➡️ ከሀሰተኛ ነቢይ ጋር የነበረ ልምምድ

ባለፈው ምሽት ለሁላችንም እንግዳ የሆነ ወጣት ከቪክቶሪያ [አውስትራሊያ) የመጣ ወንድም እንደሆነ ከነገረን በኋላ እህት ኋይትን ላገኛት እፈልጋለሁ ብሎ ጠየቀን። ምሽት ስለነበር ላገኘው አልፈለግኩም፡፡ ነገር ግን ሌሊቱን ከእኛ ጋር እንዲሆንና ጧት ቁርስ እንዲበላ ጋበዝነው። ከተለመደው የጧት አምልኮአችን በኋላ ወደ ተለያዩ ተግባሮቻችን ለመሄድ እየተዘጋጀን ሳለን ይህ ወጣት ተነስቶ የማስገደድ ትዕዛዝ በሚመስል መልኩ እንድንቀመጥ ጠየቀን። "የውዳሴ መዝሙር መጻሕፍት አሉአችሁን? አንድ መዝሙር ከዘመርን በኋላ የማቀርብላችሁ መልእክት አለኝ" አለን። ከዚያ በኋላ እርሱ ራሱ የፃፈውን የሆነ ነገር ማንበብ ጀመረ። ጽሁፉ ከሌሎች ነገሮች በተጨማሪ አሁን የሕያዋን ፍርድ ተጀምሯል ይላል።...

ንግግሩን እየቀጠለ ሳለ ሰማሁትና በመጨረሻ እንዲህ አልኩት፡- “ወንድሜ ሆይ፣ አእምሮህ ትክክል አይደለም፡፡ መልእክትህ እንዴት እንደሚመለከተን በግለጽ ንገረን። አሁኑኑ እንወቀው። አእምሮህ ከመጠን በላይ ተጨንቋል፣ ስለ ሥራህ ያለህ መረዳት የተሳሳተ ነው። ያልከው አብዛኛው ነገር ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር የሚስማማ ስለሆነ ከቃሉ ጋር የሚስማማውን እያንዳንዱን ቃል እናምናለን። ነገር ግን በውስጥህ ያለው ግለት ከልክ ያለፈ ነው። ለእኛ ያለህን ነገር ተናገር።"

አሁኑኑ ያለንን ነገር ሰብስበን ወደ ባትል ክሪክ መንቀሳቀስ እንዳለብን ነገረን። ለዚህ ምክንያቱ ምን እንደሆነ ስጠይቀው “የሕያዋን ፍርድ መጀመሩን የሚገልጸውን ይህንን መልእክት ለማስተላለፍ ነው" ብሎ መለሰልኝ። እኔም እንዲህ ብዬ መለስኩለት፡- “ጌታ እንድንሰራ የሰጣን ሥራ ገና አላለቀም። እዚህ ያለው ሥራችን ሲያልቅ አንተ ሥራችንን ከምታስተምረን ይልቅ ወደ ባትል ክሪክ ለመሄድ ጊዜው መሆኑን ጌታችን እንደሚያሳውቀን እርግጠኛ ነን።..” እኔ የጽሁፍ ሥራዬን እየጀመርኩ ሳለሁ ተጨማሪ ውይይት እንዲያደርጉ ከወንድም እስታር ጋር ተውኩት።

እህት ኋይት በትህትናና በሥልጣን ስትናገረው መሳሳቱን ማየት መጀመሩን እና እጅግ በኃይል ያንቀሳቀሱት ተጽእኖዎች እርስ በርሳቸው የማይስማሙና ምክንያታዊ ያልሆኑ እንደሆኑ ለወንድም እስታርስ ነገረው። ምንም እንኳን ቤተሰባችን ሶስት እንግዶችን ሳይጨምር አስር አባላት ያሉበት ትልቅ ቤተሰብ ቢሆንም ይህ ወጣት ለተወሰነ ጊዜ ከእኛ ጋር እንዲቆይ ወሰንን፡፡ በጭካኔ ከሚናገሩትና ከሚኮንኑት ሰዎች ጋር እንዲሄድ ልንተወው አልደፈርንም፣ “መገለጦቹን" እንዲደግማቸውም አልፈለግንም። አብረነው ልንሆንና ከተቻለም ከአደጋ ነጻ በሆነና እርግጠኛ በሆነ መንገድ ላይ መምራት እንድንችል ለጥቂት ጊዜ ከእኛ ጋር እንዲቆይ ፈለግን።—Letter 66, 1894.

@MesayD

Facebook:- https://www.facebook.com/share/1CYVnKE4SW/

ይቀጥላል ...
4👏1
የመጨረሻው ዘመን ክስተቶች

ምዕራፍ 2

➡️ የክርስቶስ በቶሎ የመመለስ ምልክቶች

(ክፍል ሦስት)

➡️ ሆዳምነትና መሻትን አለመግዛት

ሆዳምነት (ከልክ በላይ መብላት) እና መሻትን አለመግዛት በዓለማችን ላይ ላለው ታላቅ ሕገወጥነት (ምግባረ ብልሹነት) መሰረት ነው፡፡ ሰይጣን ይህን ስለሚያውቅ ወንዶችና ሴቶች ጤናቸውን፣ እንዲያውም ሕይወታቸውን ጭምር መስዋዕት በማድረግ የምግብ ፍላጎትን እንዲያረኩ ያለማቋረጥ ይፈትናቸዋል፡፡ በዓለም ዘንድ መብላት፣ መጠጣትና መልበስ የሕይወት ዓላማ ሆነዋል። ይህንን የሚመስሉ ነገሮች ከውኃ ጥፋት በፊት ነበሩ። ይህ ማባከን የምድር ታሪክ በቶሎ እንደሚዘጋ ከሚያመለክቱ ግልጽ ምልክቶች አንዱ ነው። Letter 34, 1875.

የትንቢት መንፈስ ከውኃ ጥፋት በፊት ለነበረው ዓለም የሰጠው ስዕል የዘመኑ ማህበረሰብ በፍጥነት እየተጣደፈ በመሄድ ያለበትን ሁኔታ በትክክል ይወከላል።— Patriarchs and Prophets, 102 (1890).

ጌታ በቅርብ እንደሚመጣ እናውቃለን፡፡ ዓለም በፍጥነት በኖህ ዘመን እንደነበረው ዓለም እየሆነ ነው፡፡ የራስን ፍላጎት ለማሟላት አልፎ ተሰጥቷል። ከልክ በላይ መብላትና መጠጣት የተለመደ ነገር ሆኗል፡፡ ሰዎች የሚያሳብዳቸውን መርዘኛ የሆነ አስካሪ መጠጥ እየጠጡ ነው ። Letter 308, 1907.

➡️ የሁከት ተግባራት

በኖህ ዘመን አብዛኛው ሕዝብ እውነትን የሚቃወም ስለነበር በውሸት ልምድ የተሞላ ነበር። ምድሪቱ በሁከት ተሞልታ ነበር። ጦርነት፣ ወንጀልና ግድያ በዚያን ዘመን የተለመደ ዕለታዊ ተግባር ነበር። ከክርስቶስ ዳግም ምጽዓት በፊትም እንዲሁ ይሆናል።—The S.D.A. Bible Commentary 1:1090 (1891).

የሰራተኛ ማህበራት ፍላጎቶቻቸው ካልተፈጸሙላቸው በፍጥነት ለሁከት ይነሳሳሉ። የምድር ኗሪዎች ከእግዚአብሔር ጋር ተስማምተው እየሄዱ አለመሆናቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ ግልጽ እየሆነ ነው። በሰይጣን የጦር መሪነት ሥር ተሰልፈው ያሉትን የክፋት ሰራተኞች ቀጣይነት ያለው ሰልፍ ምንም ዓይነት ሳይንሳዊ ንድፈ ሀሳብ ማብራራት አይችልም። በእያንዳንዱ ለአመጽ በተነሳሳ ቡድን ውስጥ ሰዎች የሁከት ተግባራትን እንዲፈጽሙ ለማነሳሳት ክፉ መላእክት ሥራ ላይ ናቸው።…

የሰዎች የተዛባ አመለካከትና ጭካኔ እግዚአብሔር ራሱን በግርማ እስከሚገልጥበት ከፍታ ይደርሳል። በቅርቡ የዓለም ክፋት በኖህ ዘመን እንደነበረው ከገደቡ ይደርስና እግዚአብሔር ፍርዶቹን ያፈሳል። - The Upward Look, 334 (1903).

ስለ ግድያና ዝርፊያ የምንሰማቸው አሰቃቂ ዘገባዎች፣ የባቡር መንገድ አደጋዎችና የሁከት ተግባራት፣ የሁሉም ነገር መጨረሻ ቅርብ የመሆኑን ታሪክ ይናገራሉ። አሁኑኑ ለጌታ ዳግም ምጽዓት መዘጋጀት አለብን።—Letter 308, 1907.

➡️ ጦርነቶችና መቅሰፍቶች

አውሎ ንፋሱ እየመጣ ስለሆነ ለእግዚአብሔር በመናዘዝና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ለቁጣው መዘጋጀት አለብን፡፡ እግዚአብሔር ምድርን በአሰቃቂ ሁኔታ ሊያናውጥ ይነሳል። በሁሉም አቅጣጫዎች ችግሮችን እናያለን። በሺሆች የሚቆጠሩ መርከቦች ወደ ባህር ጥልቅ ይወረወራሉ። የባህር ኃይሎች ይሰምጡና በሺሆች የሚቆጠሩ ሰብአዊ ሕይወቶች ይሰዋሉ። የሰደድ እሳቶች በድንገት ይነሱና ማንኛውም ሰብአዊ ኃይል ሊያጠፋቸው አይችልም፡፡ የምድር ቤተ መንግሥቶች በእሳት ነበልባል ይወድማሉ፡፡ የባቡር አደጋዎች ተደጋግመው ይደርሳሉ፡፡ ግራ መጋባት፣ ግጭትና ለአፍታ እንኳን ማስጠንቀቂያ ሳይሰጥ የሚከሰት ሞት በትላልቅ የጉዞ መስመሮች ላይ ይከሰታሉ። ፍጻሜው ቅርብ ነው፣ የምህረት በር እየተዘጋ ነው። እግዚአብሔርን በሚገኝበት ጊዜ ፈልጉት፣ ቀርቦ ሳለም ጥሩት! - Messages to Young People, 89, 90 (1890).

በእነዚህ የመጨረሻዎቹ የምድር ታሪክ ትዕይንቶች ወቅት ጦርነት ከቁጥጥር ውጭ ይሆናል። ቸነፈር፣ መቅሰፍትና ረሃብ ይሆናል። ጥልቅ የውኃ አካላት ወሰናቸውን አልፈው ያጥለቀልቃሉ። በእሳትና በጎርፍ ንብረትና ሕይወት ይጠፋል። ክርስቶስ እርሱን ለሚወዱት ሊያዘጋጅላቸው ለሄደው መኖሪያዎች መዘጋጀት አለብን።—Maranatha, 174 (1897).

@MesayD

Facebook: https://www.facebook.com/share/1CYVnKE4SW/

ይቀጥላል ....
6
የመጨረሻው ዘመን ክስተቶች

ምዕራፍ 2

➡️ የክርስቶስ በቶሎ የመመለስ ምልክቶች

(ክፍል አራት)

➡️ ታላላቅ የእሳት ኳሶች

ባለፈው አርብ ጧት፣ ከእንቅልፍ ከመንቃቴ በፊት፣ እጅግ ሳቢ የሆነ ትዕይንት በፊቴ አልፎ ነበር። ከእንቅልፍ የነቀሁ መስሎኝ ነበር፣ ነገር ግን በቤቴ ውስጥ አልነበርኩም። በመስኮት እጅግ አሰቃቂ የሆነ ቃጠሎ እመለከት ነበር። በቤቶች ላይ ታላላቅ የእሳት ኳሶች እየወደቁ ነበር፣ ከእነዚህ ኳሶች የእሳት ቀስቶች በየአቅጣጫው ይወረወሩ ነበር። እነዚያን ይነዱ የነበሩ እሳቶችን መቆጣጠር የማይቻል ከመሆኑ የተነሣ ብዙ ቦታዎች እየወደሙ ነበር። የሰዎች ጭንቀት (ሽብር) ሊገለጽ የማይቻል ነበር። ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ስነቃ ራሴን በቤት ውስጥ አገኘሁት።- Evangelism, 29 (1906).

በአንዳንድ ውብ በሆኑ መኖሪያዎች መካከል ትልቅ የእሳት ኳስ ሲወድቅና በቅጽበት ሲያወድማቸው ተመለከትሁ፡፡ የሆነ ሰው እንዲህ ሲል ሰማሁ፡- “የእግዚአብሔር ፍርዶች በምድር ላይ እንደሚመጡ እናውቅ ነበር፣ ነገር ግን በዚህ ፍጥነት ይመጣሉ ብለን አልጠበቅንም ነበር።" ሌሎች በጭንቀት (በመቃተት) ድምጽ እንዲህ አሉ፡- “ታውቁ ነበር! ታዲያ ለምን አልነገራችሁንም? እኛ አላወቅንም ነበር።" Testimonies for the Church 9:28 (1909).

➡️ የመሬት መናወጥና የውኃ ጥፋት

ጠላት ሥራውን ሰርቷል፣ አሁንም እየሰራ ነው። በታላቅ ኃይል ከሰማይ ወርዷል፣ የእግዚአብሔር መንፈስም ምድርን እየለቀቀ ነው (ከምድር እየተወሰደ ነው)። እግዚአብሔር እጁን ከምድር ላይ አንስቷል። ለዚህም ጆንስ ታወንን [ፔንስልቫንያ] ብቻ መመልከት አለብን። ያችን ከተማ ሰይጣን ሙሉ በሙሉ እንዳትኖር እንዳያደርጋት (እንዳያጠፋት) አልከለከለም። [በጎርጎሮሳውያን አቆጣጠር መጋቢት 31/ 1889 ዓ.ም ለብዙ ቀናት ከዘነበው ዝናብ የተነሳ በጆንስ ታወን በተከሰተው ጎርፍ በግምት 2200 የሚደርሱ ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል፡፡] የዚህች ምድር ታሪክ እስኪዘጋ ድረስ እነዚህ ነገሮች እየጨመሩ ይሄዳሉ። - Sermons and Talks 1:109 (1889).

በመሬት ሆድ ውስጥ ተደብቀው ያሉ ነገሮች በመፈንዳታቸው ምክንያት የመሬት ውጭኛው ክፍል ይቀደዳል። እነዚህ ጥንተ ነገሮች አንዴ ከተለቀቁ ተቀጣሪዎቻቸው እየተራቡ ሊከፍሉአቸው ከሚገባው ዋጋ በማስቀረት በማግበስበስ ባካበቱት ትልቅ ሀብት ላይ ለአመታት ይጨሯቸው የነበሩትን መዝገቦች (ሀብቶች) ይጠራርጉአቸዋል። የሁሉም ነገር መጨረሻው ቅርብ ስለሆነ ኃይማኖታዊው ዓለምም በአሰቃቂ ሁኔታ ይነቃነቃል። -Manuscript Releases 3:208 (1891).

በአንድ ቅጽበት ጠጣር መሬት ላይ ቆመን በሌላኛው ቅጽበት ምድር ከእግራችን ሥር የሚናወጥበት ጊዜ አሁን መጥቷል። ባልተጠበቁ ጊዜያቶች የመሬት መናወጦች ይከሰታሉ።-Testimonies to Ministers and Gospel Workers, 421 (1896).

በሰደድ እሳቶች፣ በውኃ ጥፋቶች (ጎርፎች)፣ በመሬት መናወጦች፣ በታላቁ ጥልቅ ቁጣዎች፣ በባህርና በምድር በሚከሰቱ መቅሰፍቶች የእግዚአብሔር መንፈስ ሁልጊዜ ከሰዎች ጋር እንደማይኖር ማስጠንቀቂያ እየተሰጠ ነው።—Manuscript Releases 3:315 (1897).

የሰው ልጅ በሰማይ ደመና ከመገለጡ በፊት በተፈጥሮ ውስጥ ያለው እያንዳንዱ ነገር ይናወጣል። ከሰማይ የሚወርደው መብረቅ ከምድር ከሚነሳው እሳት ጋር አንድ በመሆን ተራራዎች እንደ እቶን እሳት እንዲነዱና የቀለጡ ዓለቶቻቸውን ጎርፍ በመንደሮችና በከተሞች ላይ እንዲያፈሱ ያደርጋል። በምድር ውስጥ የተደበቁ ነገሮች ከመናወጣቸው የተነሣ ወደ ውኃ የሚወረወሩ የአለት ቅላጮች ውኃው እንዲፈላና አለቶችን ወደ ምድር እንዲሰድ ያደርጋሉ። ኃይለኛ የሆኑ የመሬት ነውጦች ስለሚከሰቱ ታላቅ የሰብአዊ ሕይወት ጥፋት ይከሰታል። The S.D.A. Bible Commentary 7:946 (1907).

@MesayD

ይቀጥላል ...
9
የመጨረሻው ዘመን ክስተቶች

ምዕራፍ 2 :- የክርስቶስ በቶሎ የመመለስ ምልክቶች

(ክፍል አምስት)

➡️ ወንጀል፣ ረሃብና ቸነፈር

ሰይጣን በከባቢ አየር ውስጥ እየሰራ ነው፤ ከባቢ አየሩን እየበከለው ስለሆነ ለአሁኑም ሆነ ለዘላለማዊው ሕይወታችን የምንደገፈው በእግዚአብሔር ላይ ነው። አሁን ባለንበት ቦታ ሆነን እጅግ መንቃት፣ ሙሉ በሙሉ መሰጠት፣ ሙሉ በሙሉ መለወጥና ለእግዚአብሔር መቀደስ አለብን። ነገር ግን ሽባ ሆነን የተቀመጥን እንመስላለን። የሰማይ አምላክ ሆይ እባክህን አንቃን! - Selected Messages 2:52 (1890).

የጨለማው ኃይላት የሕይወትና የአልሚ ምግም ምንጮች ከሆኑት አንዱ የሆነውን አየር ሞት አስከታይ በሆነ ቀፋፊ የአየር ፀባይ (ዝገት) የማበላሸት (የመበከል) አስከፊ ሥራቸውን እንዳይፈጽሙ እግዚአብሔር አልገደባቸውም። ጉዳት የደረሰበት የአትክልት ሕይወት ብቻ ሳይሆን ሰውም በቸነፈር እየተሰቃየ ነው።…እነዚህ ነገሮች የእግዚአብሔር ቁጣ ጥና ጠብታዎች ውጤት ናቸው [እግዚአብሔር ለሚፈቅዳቸው ወይም ለማይከለክላቸው ነገሮች ሀላፊነቱን ይወስዳል። ዘጸአት 7:3፤ 8:32፤ 1ኛ ዜና 10:4፣ 13፣ 14ን ይመልከቱ።] እነዚህ ነገሮች በምድር ላይ መረጨታቸው በቅርቡ ምን ሊሆን እንደሚችል ደብዘዝ ባለ ሁኔታ ያሳዩናል።—Selected Messages 3:391 (1891).

ረሃብ እየጨመረ ይሄዳል። ቸነፈሮች በሺሆች የሚቆጠሩ ሰዎችን ጠራርገው ያጠፋሉ። ከውጭ ከሆኑ ኃይሎችና በውስጥ ሆኖ ከሚሰራቸው ሰይጣናዊ አሰራሮች የተነሣ አደጋዎች በዙሪያዎቻችን ሁሉ ናቸው፡፡ ነገር ግን የእግዚአብሔር የመግታት ኃይል አሁን እየተተገበረ ይገኛል። - Manuscript Releases 19:382 (1897).

የእግዚአብሔር መንፈስ ከምድር ላይ እየተወሰደ እንደሆነ የእግዚአብሔር መንፈስ አሳይቶኛል። የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት አልቀበል በማለት ከሚቀጥሉት ሁሉ ላይ የእርሱ የጥበቃ ኃይል በቅርቡ ይነሳል። የማጭበርበር ንግዶች፣ ግድያዎችና የተለያዩ ዓይነት ወንጀሎች በየቀኑ ወደ እኛ እየመጡ ናቸው፡፡ ኃጢአት እጅግ የተለመደ እየሆነ ከመምጣቱ የተነሣ ከዚህ በፊት እንደነበረው የሰዎችን ስሜት አይረብሽም።—Letter 258, 1907.

➡️ በመቅሰፍቶቹ ውስጥ የእግዚአብሔር ዓላማ

በባህር የሚከሰቱ መቅሰፍቶች ማለት ምን ማለት ነው?—ለአፍታ እንኳን ማስጠንቀቂያ ሳይሰጥ መርከቦች ወደ ዘላለም ጥፋት መወርወር ማለት ምን ማለት ነው? አደጋዎች በምድር ማለት ምን ማለት ነው?—ሰዎች ድሆችን በመጨቆን ያከማቹአቸውን ሀብቶች እሳት ይበለዋል ማለት ምን ማለት ነው? ሕጉን የሚተላለፉና ትዕዛዛቱን በመጣስ በእርሱ ፈንታ የውሸት የእረፍት ቀንን የሚቀበሉ ሰዎችን ንብረት ከጥፋት ለመጠበቅ እግዚአብሔር ጣልቃ አይገባም፡፡

የእግዚአብሔር መቅሰፍቶች በምድር ላይ በመውረድ ላይ ናቸው። እነዚህ መቅሰፍቶች፣ ከሰማይ በሆነ የእሳት እስትንፋስ እንደሚሆን፣ እጅግ ውድ የሆኑግንባታዎችን በመጠራረግ ላይ ናቸው። እነዚህ ፍርዶች ክርስቲያን ነን ባዮችን ወደ ህሊናቸው አያመጡአቸውምን? እነዚህ መቅሰፍቶች እንዲመጡ እግዚአብሔር የሚፈቅድበት ምክንያት ዓለም እንዲሰማ፣ ኃጢአተኞች እንዲፈሩና በፊቱ እንዲንቀጠቀጡ ነው።— Manuscript Releases 3:311 (1902).

እግዚአብሔር እነዚህ መቅሰፍቶች እንዲከሰቱ ሲፈቅድ ዓላማ አለው፡፡ ወንዶችንና ሴቶችን ወደ ህሊናቸው ለመጥራት ከሚጠቀምባቸው መንገዶች አንዱ ነው፡፡ እግዚአብሔር በተፈጥሮ በሚፈጸሙ ያልተለመዱ አሰራሮች አማካይነት ተጠራጣሪ ለሆኑ ሰብአዊ ወኪሎች በቃሉ ውስጥ በግልጽ የተቀመጠውን ነገር ይገልጻል።—Manuscript Releases 19:279 (1902).

ስለ መሬት መንቀጥቀጥና አውሎ ነፋሶች፣ በእሳትና በጎርፍ ስለሚከሰቱ ጥፋቶችና እነዚህ ጥፋቶች ስለሚያስከትሉአቸው ታላላቅ የሕይወትና የንብረት ውድመቶች የምንሰማው ምን ያህል ጊዜ ነው! እነዚህ መቅሰፍቶች ያልተቀናጁና ቁጥጥር የማይደረግባቸው ከሰው ቁጥጥር ውጭ የሆኑ፣ ነገር ግን በእነርሱ ውስጥ የእግዚአብሔር ዓላማ የሚነበብባቸው ቶሎ ቶሎ የሚከሰቱ የተፈጥሮ ኃይሎች መነሣት ናቸው፡፡ እነዚህ መቅሰፍቶች ወንዶችንና ሴቶችን ተደቅኖባቸው ስላለው አደጋ ወደ ህሊናቸው እንዲመለሱ ለመቀስቀስ እርሱ ከሚጠቀምባቸው ወኪሎች መካከል ናቸው::— Prophets and Kings, 277 (c. 1914).

@MesayD

ይቀጥላል ...
3
የመጨረሻው ዘመን ክስተቶች

ምዕራፍ 2 :- የክርስቶስ በቶሎ የመመለስ ምልክቶች

(የመጨረሻ ክፍል)

➡️ መጪዎቹ ክስተቶች በጌታ እጆች ናቸው

ዓለም ያለ ገዥ አይደለችም፡፡ እየመጡ ያሉ ክስተቶች ፕሮግራም በእግዚአብሔር እጆች ውስጥ ነው። የሰማይ ንጉሥ የሕዝቦች መዳረሻ ያለው ሲሆን የቤተ ክርስቲያኑን ጉዳይ ኃላፊነት የሚወስደውም እርሱ ራሱ ነው::—Testimonies for the Church 5:753 (1889).

እነዚህ የምልክት ውከልናዎች [በምድረ በዳ የነበሩ የእሳት እባቦች] ለሁለት ዓላማዎች ያገለግላሉ። በፈጣሪ ቁጥጥር ሥር ያሉት በምድር ላይ ያሉ አካላዊ ኃይላት ብቻ ሳይሆኑ የሕዝቦች መንፈሳዊ እንቅስቃሴዎችም በእርሱ ቁጥጥር ሥር መሆናቸውን የእግዚአብሔር ሕዝብ ከእነርሱ ይማራሉ። ይህ በተለየ ሁኔታ የእሁድ ጥበቃ አስገዳጅ መሆንን በተመለከተም እውነት ነው። —Manuscript Releases 19:281 (1902).

በታላቁ የመዝጊያ ሥራ ምን ማድረግ እንዳለብን የማናውቃቸው ግራ መጋባቶች ይገጥሙናል፣ ነገር ግን ሶስት ታላላቅ ሰማያዊ ኃይላት እየሰሩ መሆናቸውን፣ መለኮታዊው እጅ በመንኮራኩሩ ላይ እንደሆነ እና እግዚአብሔር ዓለማውን እንደሚፈጽም አንርሳ።— Evangelism, 65 (1902).

መንኮራኩር የመሰሉ ውስብስብ ነገሮች በኪሩቤሉ ክንፎች ሥር ባለው እጅ ምሪት ሥር እንደሆኑ ሁሉ በሰዎች መካከል የሚፈጸሙ ክስተቶች ውስብስብ ትወናም በመለኮት ቁጥጥር ሥር ነው። በሕዝቦች መካከል እየተከናወነ ባለው ጠብና ህውከት ውስጥ ከኪሩቤሎች በላይ የሚቀመጠው የምድርን ጉዳዮች ይመራል። [ ሕዝቅኤል 1:4፣ 26፤10:8፤ ዳንኤል 4:17፣ 25:32ን ይመልከቱ :: - Education, 178 (1903).

በሰው ዘር የታሪክ መዛግብት ውስጥ የሕዝቦች እድገት፣ የመንግሥታት መነሳትና መውደቅ በሰው ፈቃድና ብቃት የሚደገፍ ይመስላል። የክስተቶች በከፍተኛ ደረጃ ቅርጽ መያዝ በእርሱ ኃይል፣ ፍላጎት ወይም ድንገተኛ ድርጊት የሚወሰን ይመስላል። ነገር ግን በእግዚአብሔር ቃል መጋረጃው ተገልጦአል። ከዚህ የተነሣ ከላይ፣ ከኋላ እና በሰብአዊ ፍላጎትና ኃይል ተውኔት እና ተቃራኒ ተውኔት ሁሉ ውስጥ መሃሪ የሆነው አምላክ ወኪሎች የእርሱን ፈቃድ ምክሮች በጸጥታና በትዕግሥት እየሰሩ (እየፈጸሙ) ናቸው::—Prophets and Kings, 499, 500 (c. 1914).

➡️ ሰማይ ለምድራዊ ጉዳዮች ያለው ትኩረት

እግዚአብሔር የመጀመሪያውን ነፍሰ ገዳይ ሕይወት በማዳን በመላው ዩኒቨርስ ፊት በታላቁ ተጋድሎ ላይ ተጽእኖ የሚፈጥረውን ትምህርት አቅርቧል።...የእርሱ ዓላማ አመጽን ማቆም ብቻ ሳይሆን ለመላው ዩኒቨርስ የአመጽን ባህርይ ማሳየትም ነበር።.. በሌሎች ዓለማት ያሉ ቅዱሳን ኗሪዎች በምድር ላይ እየሆኑ ያሉ ከስተቶችን እጅግ ጥልቅ በሆነ ፍላጎት እየተመለከቱ ናቸው።...

የእርሱ ታላቅ ዕቅድ ደረጃ በደረጃ ወደ ሙሉ ተፈጻሚነት እየገሰገሰ ሳለ እግዚአብሔር የመላውን ዩኒቨርስ ርኅራኄና ማረጋገጫ ይይዛል።—Patriarchs and Prophets, 78, 79 (1890).

ለሰው ድነት የክርስቶስ መሞት ሰማይን ለሰዎች ተደራሽ ማድረግ ብቻ ሳይሆን በመላው ዩኒቨርስ ፊት እግዚአብሔርና ልጁ በሰይጣን አመጽ ላይ የወሰዱት እርምጃ ትክክል መሆኑን ያረጋግጣል።- Patriarchs and Prophets, 68, 69 (1890).

መላው ዓለም በመልካምና በክፉ መካከል የሚካሄዱ የታላቁ ተጋድሎ የመዝጊያ ትዕይንቶችን ሊገለጽ በማይቻል ፍላጎት እየተመለከተ ነው::— Prophets and Kings, 148 (c. 1914).

ትንሽዋ ዓለማችን የዩኒቨርስ መማሪያ መጽሐፍ ነች።—The Desire [31] of Ages, 19 (1898). [ያልወደቁ ዓለማትና ሰማያዊ መላእክት ክርስቶስ በጌተሰማኔ ሲታገል “በጥልቅ ፍላጎት” መመልከታቸውን ኤለን ኋይት ትናገራለች።" (The Desire of Ages, 693). ክርስቶስ ከሰይጣን ጋር ለ4000 ዓመታት ያደረገውን ጦርነትና በመጨረሻም በመስቀል ላይ ስላገኘው ድል ስትናገር “ሰማያዊው ዩኒቨርስ ተመለከተ፣” “ሰማይ በሞላ እና ያልወደቁ ዓለማት ምስክሮች ነበሩ፣” “እነርሱ ሰሙ፣” “ተመለከቱ፣” “ሰማይ ተመለከተ፣” “ለሰማያዊው ዩኒቨርስ ምንኛ አስገራሚ እይታ ነው!" የሚሉ ሀረጎችን ትጠቀማለች። [ የዘመናት ምኞት ከሚለው መጽሐፍ ገጽ 693፣ 759፣ 760ን ይመልከቱ።]

@MesayD

My Facebook https://www.facebook.com/share/1CYVnKE4SW/

ምዕራፍ 3 ይቀጥላል ...
4👏1
የመጨረሻው ዘመን ክስተቶች.pdf
94.1 KB
የመጨረሻው ዘመን ክስተቶች ምዕራፍ 1.pdf
2
የመጨረሻው ዘመን ክስተቶች

ምዕራፍ 3 :- “ እነዚህ ነገሮች የሚሆኑት መቼ ነው ?”

(ክፍል አንድ)

➡️ ደቀ መዛሙርቱ ክርስቶስን ስለ መምጫው ጠየቁት

"ቃላቱ [ማቴዎስ 24:2] የተነገሩት ብዙ ሰዎች እየሰሙ ነበር፣ ነገር ግን እርሱ ብቻውን እያለ ጴጥሮስ፣ ዮሐንስ፣ ያዕቆብና እንድሪያስ በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ተቀምጦ ሳለ ወደ እርሱ መጡ። “ንገረን፣ እነዚህ ነገሮች የሚሆኑት መቼ ነው? የመምጣትህና የዓለም ፍጻሜ ምልክቶችስ ምንድር ናቸው?” ብለው ጠየቁት።

"ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ የኢየሩሳሌምን ጥፋትና ታላቁን የእርሱ መምጫ ቀን ነጣጥሎ አልነገራቸውም፡፡ የእነዚህን ሁለት ክስተቶች መግለጫ ቀላቅሎ ነገራቸው፡፡ ሊመጡ ያሉ ክስተቶችን እርሱ በሚያያቸው ሁኔታ ለደቀ መዛሙርቱ ገልጦላቸው ቢሆን ኖሮ ያዩትን ነገር መቋቋም አይችሉም ነበር። ለእነርሱ ካለው ምህረት የተነሣ ትርጉሙን ለራሳቸው _ እንዲያጠኑት በመተው የሁለቱን ታላላቅ ጥፋቶች መግለጫ ቀላቅሎ ነገራቸው።"-The Desire of Ages, 628 (1898).

➡️ ክርስቶስ የሚመለስበት ጊዜ አይታወቅም

"ራሳቸውን አድቬንቲስቶች ነን ብለው የሚጠሩ ብዙዎች ጊዜን ወስነው የሚያስቀምጡ ናቸው። ብዙ ጊዜ ስለ ክርስቶስ መምጣት ጊዜ ተወስኖ ነበር፣ ነገር ግን ውጤቱ ተደጋጋሚ ውድቀት ነበር። የጌታችን መምጫ ሰዓት ሟች ከሆኑ ሰዎች እውቀት ባሻገር መሆኑ ተነግሯል። የድነት ወራሾች ለሆኑት የሚያገለግሉ መላእክት እንኳን ቀኑንና ሰዓቱን አያውቁም። “ስለዚያች ቀንና ሰዓት ከአባቴ በቀር ማንም ሰው፣ የሰማይ መላእክት እንኳ ቢሆኑ አያውቁም።" —Testimonies for the Church 4:307 (1879).

"ስለ መንፈስ ቅዱስ መውረድም ሆነ ስለ ክርስቶስ ምጽዓት የተወሰነውን ጊዜ ማወቅ አያስፈልገንም፡፡…እግዚአብሔር ይህን እውቀት ያልሰጠን ለምንድር ነው? ገልጾልን ቢሆን ኖሮ በትክክል ስለማንጠቀምበት ነው። ይህ እውቀት ሊመጣ ባለው ቀን ሰዎች እንዲቆሙ ለማዘጋጀት የሚደረገውን ሥራ በሕዝባችን መካከል በከፍተኛ ደረጃ እንዲያዘግም የሚያደርግ ሁኔታን ይፈጥራል፡፡ ስለ ጊዜው ለማወቅ በመፈለግ መነሳሳት ውስጥ መኖር የለብንም።....

"እርሱ በአንድ፣ በሁለት ወይም በአምስት ዓመት ውስጥ ይመጣል ማለት አትችሉም፤ መምጫውን እስከ አሥር ወይም ሃያ ዓመታት ሊቆይ ይችላል ብላችሁ ማራዘምም አትችሉም።" -The Review and Herald, March 22, 1892.

"ወደ ታላቁ የእግዚአብሔር ቀን እየተቃረብን ነን። ምልክቶቹ እየተፈጸሙ ናቸው። ሆኖም ክርስቶስ የሚመለስበትን ጊዜና ሰዓት የሚነግር መልእክት የለንም። በሰማይ ደመና የሚመለሰውን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን ሁልጊዜ እየጠበቅን ዝግጁ እንድንሆን እግዚአብሔር በጥበቡ ደብቆታል።" Letter 28, 1897.

"የሰው ልጅ ዳግም ምጽዓት ትክክለኛው ጊዜ የእግዚአብሔር ምስጢር ነው፡፡"—The Desire of Ages, 633 (1898).

➡️ የእኛ መልእክት ጊዜን የሚወስን መልእክት አይደለም

"ኢየሱስ በኃይልና በታላቅ ክብር ከመምጣቱ በፊት የሚሆነውን ትክክለኛውን ጊዜ ወስነው ከሚናገሩት ሰዎች ቡድን አይደለንም፡፡ አንዳንዶች ጊዜን ወስነው ያስቀመጡ ሲሆን ያ ጊዜ ሲያልፍ በራስ የሚተማመን (ትዕቢተኛ) መንፈሳቸው ተግሳጽን ካለመቀበሉ የተነሣ ደጋግመው ሌላ ጊዜ ወስነው አስቀምጠዋል። ነገር ግን እነዚህ ወስነው ያስቀመጡአቸው ጊዜያት ለበርካታ ተከታታይ ጊዜያት አለመፈጸማቸው ሀሰተኛ ነቢያት መሆናቸውን አረጋገጡ። "-Fundamentals of Christian Education, 335 (1895).

"የዚህች ምድር ታሪክ ከመዘጋቱ በፊት አምስት ወይም አስር ወይም ሃያ አመታት ይኖራሉ የሚልን መልእክት እግዚአብሔር ለማንም አይሰጥም፡፡ ለመገለጡ መደረግ ያለበትን ዝግጅት ለሚያዘገይ ለማንኛውም ሕያው ፍጡር ይቅርታ አይሰጥም፡፡ ለዚያ ለታላቁ ቀን እንድንዘጋጅ የተሰጡንን መልካም አጋጣሚዎችንና ዕድሎችን ባልተገባ ሁኔታ ችላ ወደማለት ስለሚመራን፣ ማንም ሰው ታማኝ ያልነበረው ባሪያ “ጌታዬ ይዘገያል” እንዳለው ማለት የለበትም።" -The Review and Herald, November 27, 1900.

@MesayD

ይቀጥላል ....
5👍1
የመጨረሻው ዘመን ክስተቶች

ምዕራፍ 3:- እነዚህ ነገሮች የሚሆኑት መቼ ነው ?

(ክፍል ሁለት)

➡️ ጊዜን መወሰን ወደ አለማመን ይመራል

"ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ የተወሰኑ ጊዜያቶች ሳይፈጻሙ ከማለፋቸው የተነሳ በቅርቡ ሊሆን ስላለው የክርስቶስ ዳግም ምጽዓት ዓለም ከበፊቱ ይልቅ አሁን ባለማመን ጸንቷል። ጊዜን ወስነው ያልተሳካላቸውን ሰዎች በንቀት ይመለከቱአቸዋል፤ ሰዎች ከመታለላቸው የተነሳ የሁሉም ነገር መጨረሻው በደጅ ስለመሆኑ የእግዚአብሔር ቃል ድጋፍ ካለው እውነት ይርቃሉ።" - Testimonies for the Church 4:307 (1879).

"ወንድም [ኢ.. ፒ.] ዳንኤልስ ከዚህ በፊት እንዳደረገው ሁሉ ጌታ በአምስት አመት ጊዜ ውስጥ ይመጣል ብሎ ጊዜ እንደወሰነ እረዳለሁ። አሁን እኛ ጊዜን የምንወስን ሰዎች እንደሆንን የሚያመለክት ነገር ወደ ሌላ አገር እንደማይደርስ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ የዚህ ዓይነት አስተያየቶች አይምጡ፡፡ አይጠቅሙም። ይህን በመሰሉ ጉዳዮች ላይ ተሃድሶን ለማግኘት አትፈልጉ፣ ነገር ግን ጥራዝ ነጠቆች ሽብር ለመፍጠር ማግኘት የሚችሉትን ማንኛውም ነገር እንዳይጠቀሙና የእግዚአብሔርን መንፈስ እንዳያሳዝኑ በእያንዳንዱ ከአፍ በሚወጣ ቃል ላይ ጥንቃቄ ይደረግ።

"ስሜቶችን ለመቀስቀስና መርሆዎች የማይቆጣጠሩትን መነሳሳትን ለመፍጠር ስንል የሰዎችን ኃይለኛ ስሜቶች መቀስቀስ አያስፈልግም። ሰይጣን ጉዳት ለማድረስ ኃይል የሚሆኑትን የማታለል ስልቶቹንና መሳሪያዎቹን ሥራ ላይ ለማዋል ማድረግ የሚችለውን ሁሉ ለማድረግ ሥራ ላይ ስለሆነ በሁሉም አቅጠጫ መጠበቅ እንዳለብን ይሰማኛል። ማንኛውም የሚያውክና በተሳሳተ ነገር ላይ የተመሰረተ ሽብር የሚፈጥር ነገር በእርግጠኝነት የአጸፋ መልስ ስለሚኖረው መፈራት አለበት።"— Letter 34, 1887.

"በእግዚአብሔር ተመርተናል በሚሉ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ባሉ ሰዎች አማካይነት ሁልጊዜ የውሸትና ጥራዝ ነጠቅ እንቅስቃሴዎች ይደረጋሉ። እነዚህ ሰዎች ከመላካቸው በፊት የሚሮጡና ላልተፈጸመው ትንቢት ቀንና ዓመተ ምህረት ወስነው የሚሰጡ ናቸው። እነዚህ ሰዎች የወሰኑአቸው ቀናትና ዓመታት አለመፈጸምና ወደ ውሸት መንገዶች መምራት ግራ መጋባትንና አለማመንን ስለሚፈጥር በድርጊታቸው ጠላት ይደሰታል።"-Selected Messages 2:84 (1897).

➡️ 1844 ባሻገር ሌላ የጊዜ ትንቢት የለም

"በጃክሰን በነበረው የካምፕ ስብሰባ ላይ እነዚህ ጥራዝ ነጠቅ ሰዎች የነፍሳት ጠላትን ሥራ እየሰሩ እንደሆነ በግልጽ ተናግሬያለሁ፡፡ በጨለማ ውስጥ ነበሩ። የምህረት በር በጥቅምት 1884 ዓ.ም እንደሚዘጋ የሚገልጽ ትልቅ ብርሃን እንዳላቸው ተናገሩ። በዚያ ቦታ በሕዝብ ፊት ከ1844 ወዲህ በተሰጡ መልእክቶች ውስጥ የተወሰነ ጊዜ እንደማይኖር እግዚአብሔር ለእኔ በማሳየቱ ደስተኛ መሆኑን ነግሬያቸው ነበር።" Selected Messages 2:73 (1885).

"አቋማችን በ1844 በተፈጸሙ ትንቢታዊ ጊዜያቶችና በጌታ መገለጥ ጊዜ መካከል ምንም ዓይነት የጊዜ እወጃን ጣልቃ ሳናስገባ ነቅቶ መጠበቅ ነው::"—Manuscript Releases 10:270 (1888).

"የተወሰነ ጊዜን በተመለከተ ሕዝቡ ሌላ መልእክት አይሰጠውም። ከዚህ ጊዜን ከሚመለከት ወቅት በኋላ (ራዕይ 10:4-6)፣ ከ1842 እስከ 1844፣ የተወሰነ ትንቢታዊ ጊዜን የሚጠቅስ ሌላ ወቅት ሊኖር አይችልም። ረዥሙ የጊዜ ስሌት እስከ 1844 የመከር ወቅት ይደርሳል።" -The S.D.A. Bible Commentary 7:971 (1900).

@MesayD

ይቀጥላል ....
👍3
የመጨረሻው ዘመን ክስተቶች

ምዕራፍ 3:- እነዚህ ነገሮች የሚሆኑት መቼ ነው ?

(ክፍል ሦስት)

➡️ ኤሌን ኋይት በእርሷ ዘመን ክርስቶስ ይመለሳል ብላ ጠብቃ ነበር

በኮንፍራንሱ የነበረውን ቡድን እንዳይ ተደርጌ ነበር። መልአኩ እንዲህ አለ፡ - አንዳንዶች የትላትል ምግብ፣ ሌሎች የመጨረሻዎቹ ሰባት መቅሰፍቶች ሰለባ ሲሆኑ አንዳንዶች ደግሞ በክርስቶስ መገለጥ ወደ ሰማይ ለመነጠቅ በምድር ላይ በሕይወት ይኖራሉ።"-Testimonies For The Church 1:131, 132 (1856).

"ጊዜው አጭር ስለሆነ በትጋትና በዕጥፍ ጉልበት መስራት አለብን፡፡ ልጆቻችን በፍጹም ወደ ኮሌጅ ላይገቡ ይችላሉ።"—Testimonies for the Church 3:159 (1872).

"አሁን ልጆችን መውለድ በእርግጠኝነት የሚመከር አይደለም። ጊዜው አጭርነው፣ የመጨረሻዎቹ ቀን አደጋዎች በላያችን ናቸው፣ ከዚህ በፊት ትናንሽ ልጆች በአብዛኛው ይሞታሉ”——Letter 48, 1876.

"የምድር ታሪክ ትዕይንቶች በቶሎ ሊዘጉ ባሉበት እና ከዚህ በፊት በፍጹም ሆኖ ወደማያውቅ የመከራ ጊዜ ልንገባ ባለንበት በዚህ ዘመን የሚፈጸሙ ጋብቻዎች ጥቂት ቢሆኑ ለወንዶችም ለሴቶችም የተሻለ ነው::"-Testimonies for the Church 5:366 (1885).

"ሰዓቱ ይመጣል፤ ሩቅ አይደለም፣ አሁን አምነው ካሉት ሰዎች መካከል አንዳንዶቻችን በምድር ላይ በሕይወት በመኖር ትንቢቱ ተፈጻሚ ሲሆን እንመለከታለን፣ የመላእክት አለቃ ድምጽና የእግዚአብሔር መለከት ድምጽ ከተራራ፣ ከሜዳና ከባህር ወደ ምድር ጫፎች ሲያስተጋባ እንሰማለን።" - The Review and Herald, July 31, 1888.

"የሶስተኛው መልአክ ታላቅ ጩኸት ኃጢአትን ይቅር ባይ በሆነው አዳኝ በክርስቶስ ጽድቅ መገለጥ ስለተጀመረ የፈተናው ጊዜ በላያችን ነው። "-Selected Messages 1:363 (1892).

➡️ መዘግየቱ ተብራራ

"የሙሽራው ረዥም ሌሊት ፈታኝ ነው፣ ነገር ግን ጌታ ቢመጣ ኖሮ እጅግ ብዙ ሰዎች ሳይዘጋጁ ስለሚገኙ ንጋቱ ወደ ፊት የገፋው በምህረት ነው::"—Testimonies for the Church 2:194 (1868).

"አድቬንቲስቶች በ1844 ዓ.ም ከገጠማቸው ታላቅ ተስፋ መቁረጥ በኋላ እምነታቸውን አጥብቀው ቢይዙና የሶስተኛውን መልአክ መልእክት በመቀበል በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ለዓለም በማወጅ እግዚአብሔር የከፈተላቸውን መሰናዶ አንድ ሆነው ተከትለው ቢሆን ኖሮ የእግዚአብሔርን ማዳን ባዩ፤ በጥረቶቻቸው እግዚአብሔር በኃይል በሰራና ክርስቶስ ሕዝቡን ሽልማታቸውን እንዲቀበሉ ለመውሰድ በመጣ ነበር።-የክርስቶስ መምጣት እንዲህ መዘግየት የእግዚአብሔር ፈቃድ አልነበረም። …አለማመን፣ ማጉረምረምና አመጽ የጥንቶቹን እሥራኤላውያን ወደ ከነዓን ምድር እንዳይገቡ ለ40 ዓመታት ዘጋባቸው። የዘመኑ እሥራኤልም ወደ ሰማያዊው ከነዓን እንዳይገባ ተመሳሳይ ኃጢአት አዘግይቶታል። በሁለቱም ሁኔታ የእግዚአብሔር ተስፋ ስህተት የለውም፡፡ በዚህ የኃጢአትና የሀዘን ዓለም ውስጥ ለብዙ ዓመታት እንድንቆይ ያደረገን የእግዚአብሔር ሕዝብ ነን በሚሉ ሰዎች መካከል ያለው አለማመን፣ ዓለማዊነት፣ አለመቀደስና ጠብ ናቸው ።"-Evangelism, 695, 696 (1883).

"የከርስቶስ ቤተ ክርስቲያን እግዚአብሔር እንደሾማት የተሰጣትን ሥራ ሰርታ ቢሆን ኖሮ መላው ዓለም ከዚህ በፊት ማስጠንቀቂያ በተሰጠውና ጌታ ኢየሱስ በኃይልና በታላቅ ክብር ወደ ምድራችን በመጣ ነበር። -The Desire of Ages, 633, 634 (1898).

@Mesay Desalegn

ይቀጥላል ...
5
የመጨረሻው ዘመን ክስተቶች

ምዕራፍ 3:- እነዚህ ነገሮች የሚሆኑት መቼ ነው ?

(ክፍል አራት)

➡️ የእግዚአብሔር ተስፋዎች በሁኔታዎች የሚደገፉ ናቸው

"የእግዚአብሔር መላእክት ለሰዎች ባቀረቡአቸው መልእክቶች ጊዜው እጅግ አጭር መሆኑን አመልክተዋል (ሮሜ 13፡11፣ 12፤ 1ኛ ቆሮ. 7፡29፤ 1ኛ ተሰ. 4፡15፣ 17፤ ዕብ. 10፡25፤ ያዕ. 5፡8፣ 9፤ 1ኛ ጴጥ. 4፡7 እና ራዕይ 22፡ 6፣ 7ን ይመልከቱ)። በዚህ መልክ ሁልጊዜ በፊቴ ቀርቦልኝ ነበር። በዚህ መልእክት ጅምር ላይ ከጠበቅነው ይልቅ ጊዜው እየረዘመ መምጣቱ እውነት ነው፡፡ አዳኛችን ይመጣል ባልነው ፍጥነት አልመጣም። ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል ሳይፈጸም ቀርቷልን (ዋሽቷልን)? በፍጹም! የእግዚአብሔር ተስፋዎችም ሆኑ ማስጠንቀቂያዎች በሁኔታዎች የሚደገፉ መሆናቸውን ማስታወስ አስፈላጊ ነው። (ኤር. 18፡ 7-10፤ ዮናስ 3፡ 4-10ን ይመልከቱ)።...

"ለእግዚአብሔር ባለመገዛታችን እንደ እሥራኤል ልጆች በዚህ ዓለም ለብዙ ዓመታት ልንቆይ እንችላለን፣ ነገር ግን የእግዚአብሔር ሕዝብ በእነርሱ የተሳሳተ መንገድ ለመጣው ነገር እግዚአብሔርን ተጠያቂ በማድረግ በኃጢአት ላይ ኃጢአትን እንዳይጨምሩ በክርስቶስ ስም እጠይቃቸዋለሁ፡:" Evangelism, 695, 696 (1901).

➡️ ክርስቶስ እየጠበቀ ያለው ነገር

"ክርስቶስ ራሱን በቤተ ክርስቲያኑ ለመግለጥ በታላቅ ናፍቆት እየጠበቀ ነው። የከርስቶስ ባህሪ በሕዝቡ ውስጥ በሙላት ሲባዛ የራሱ የሆኑትን ሊወስድ ይመጣል።

"የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን መምጣት መፈለግ ብቻ ሳይሆን ማፋጠንም የእያንዳንዱ ክርስቲያን መልካም ዕድል ነው፡፡ ስሙን የሚጠሩ ሁሉ ለእርሱ ክብር የሚሆን ፍሬ ቢያፈሩ ኖሮ የወንጌል ዘር እንዴት ባለ ፍጥነት በመላው ዓለም በተዘራ ነበር። የመጨረሻው ታላቅ መከር በፍጥነት ይበስልና ከቡር ዘሮችን ለመሰብሰብ ክርስቶስ ይመጣል።"—Christ's Object Lessons, 69 (1900).

"ወንጌልን ለዓለም በመስጠት የጌታን መመለስ ማፋጠን በእኛ አቅም ሥር ያለ ነገር ነው። የጌታን ቀን መጠበቅ ብቻ ሳይሆን ማስቸኮልም አለብን፡፡ (2ኛ ጴጥ 3:12 መጨረሻ )" -The Desire of Ages, 633 (1898). "

"ከእርሱ ጋር በመተባበር ይህንን የችግር ትዕይንት ወደ መጨረሻው ማምጣትን በእኛ አቅም ሥር አድርጎታል።" - Education, 264 (1903).

➡️ የእግዚአብሔር ትዕግሥት ገደብ

"ኃይሉ ወሰን የሌለው አምላክ የሕዝቦችን ሁሉ መዝገብ በማይሳሳት ትክክለኛነት ይጠብቃል። ምህረቱ ለንስሃ ከሚቀርቡ ጥሪዎች ጋር የተዋሃደ ሆኖ ሳለ ይህ መዝገብ ክፍት ሆኖ ይቆያል፣ ነገር ግን ቁጥሮቹ እግዚአብሔር ከወሰነው መጠን ላይ ሲደርሱ የቁጣ አገልግሎቱ ይጀመራል።" - Testimonies for the Church 5:208 (1882).

"እግዚአብሔር የሕዝቦችን ጉዳይ መዝግቦ ይይዛል። በሰማይ መጻሕፍት ውስጥ በእነርሱ ላይ የተጻፉ ነገሮች ቁጥር እየጨመረ ስለሆነ የሳምንቱን የመጀመሪያ ቀን ሕግ መተላለፍ ቅጣት ሲያስከትል ጽዋቸው ይሞላል።"—The S.D.A. Bible Commentary 7:910 (1886).

"እግዚአብሔር ሕዝቦችን ይቆጣጠራል።…ኃጢአት ወደተገለጸው የእግዚአብሔር ምህረት ገደብ የሚደርስበት ጊዜ ሲመጣ ትዕግሥቱ ያበቃል። በሰማይ የኃጢአት መመዝገቢያ መጻሕፍት ውስጥ የተመዘገቡ የተጠራቀሙ ነገሮች ቁጥር የመተላለፍ ድምርን ሲሞላ ቁጣ ይመጣል።" -Testimonies for the Church 5:524 (1889).

"የእግዚአብሔር ምህረት ሕግ ተላላፊውን ለረዥም ጊዜ ቢታገሰውም ሰዎች በኃጢአት መቀጠል የማይችሉበት ገደብ አለ። ያ ገደብ ሲደርስ የምህረት ስጦታዎች ይወገዱና የፍርድ አገልግሎት ይጀምራል።"—Patriarchs and Prophets, 162, 165 (1890).

"ሰዎች በማጭበርበርና በብልግና ተግባራቸው ቀጥለውበት እንዲያልፉ እግዚአብሔር የማይፈቅድበት ነጥብ ላይ የሚደርሱበት ጊዜ እየመጣ ነው፤ ያኔ የያህዌ ትዕግሥት ገደብ እንዳለው ያውቃሉ።" -Testimonies for the Church 9:13 (1909).

የያህዌ ፍርድ ከዚያ ባሻገር መዘግየት የማይችልበት ገደብ አለው።—Prophets and Kings, 417 (c. 1914).

@MesayD

ይቀጥላል ...
👍2
የመጨረሻው ዘመን ክስተቶች

ምዕራፍ 3:- እነዚህ ነገሮች የሚሆኑት መቼ ነው ?

(የመጨረሻ ክፍል)

➡️ መተላለፍ ከገደቡ ደርሷል

"የምድር ኗሪዎች የበደለኝነት ጽዋቸውን እስኪሞሉ ድረስ ለጥቂት ጊዜ መዘግየት የሚኖር ሲሆን ከዚያ በኋላ ለረዥም ጊዜ በእንቅልፍ ላይ የነበረው የእግዚአብሔር ቁጣ ይቀሰቀስና ይህ የብርሃን አገር የእርሱን ያልተቀላቀለ ቁጣ ወይን ጠጅ ይጠጣል።"— Testimonies For The Church 1:363 (1863).

"የበደለኝነት ጽዋ ለመሙላት የቀረበ ሲሆን የእግዚአብሔር የበቀል ፍርድ በበደለኞች ላይ ሊወርድ ነው ።" -Testimonies for the Church 4:489 (1880).

"የዓለም ኗሪዎች ክፋት የኃጢአታቸውን ስፍር ሞልቷል። ይህቺ ምድር አጥፊው የእርሱን ፈቃድ እንዲፈጽም እግዚአብሔር ወደሚፈቅድበት ደረጃ ደርሳለች።” Testimonies for the Church 7:141 (1902).

"መተላለፍ ከገደቡ ላይ ደርሷል። ዓለም በውዝግብ ስለተሞላ በሰብአዊ ፍጡራን ላይ በቅርቡ ታላቅ ሽብር ሊመጣ ነው፡፡ መጨረሻው እጅግ ቅርብ ነው። እኛ እውነቱን የምናውቅ ሰዎች በዓለም ላይ ከአቅም በላይ የሆነ አድናቆትን በሚጭር መልኩ ሊከሰት ስላለው ነገር መዘጋጀት አለብን።"— Testimonies for the Church 8:28 (1904).

➡️ የእግዚአብሔርን ታላቅ ቀን በአእምሮአችን ጠብቀን ማቆየት አለብን

"ከፊታችን _ ስላሉት ታላላቅ የፍርድ ትዕይንቶች ለማሰብና በሕይወታችን ለመተግበር ራሳችንን ማስተማር አለብን። ከዚያም ሁሉም ነገር የሚገለጥበትን የእግዚአብሔርን ታላቅ ቀን ትዕይንቶች በፊታችን ስንይዝ በባሕርያችን ላይ ተጽእኖ ይኖረዋል። አንድ ወንድም “እህት ኋይት፣ ጌታ በአስር አመት ጊዜ ውስጥ ይመጣል ብለሽ ታስቢያለሽ?” ብሎ ጠየቀኝ። እኔም “በሁለት፣ በአራት ወይም በአሥር ዓመት የሚመጣ ቢሆን ምን ልዩነት ያመጣል?" አልኩት። እርሱም “ጌታ በአሥር ዓመት ውስጥ የሚመጣ መሆኑን ባውቅ ኖሮ አንዳንድ ነገሮችን በተለየ ሁኔታ አደርጋለሁ ብዬ አስባለሁ” አለ። እኔም “ምን ታደርጋለህ?" አልኩት፡፡ እርሱም “ንብረቴን ሽጬ የእግዚአብሔርን ቃል መመርመር እጀምርና ሕዝቡ ለመምጫው እንዲዘጋጅ ለማስጠንቀቅ እሞክራለሁ፤ እኔም ለመምጫው ዝግጁ መሆን እንድችል ወደ እግዚአብሔር እማጸናለሁ" አለ፡፡

ከዚያም “ጌታ እስከ ሃያ ዓመት ድረስ እንደማይመጣ ብታውቅ ኖሮ ከአሁን በተለየ ሁኔታ ትኖር ነበር?” ብዬ ጠየቅኩት። እርሱም “እንደዚያ አደርጋለሁ ብዬ አስባለሁ" አለ።.

"ኢየሱስ በአስር አመት ውስጥ እንደሚመጣ ቢያውቅ ኖሮ የተለየ ሕይወት እንደሚኖር የሚገልጸው መግለጫ እንዴት ያለ ራስ ወዳድነት ነው! ሔኖክ ለምን ለ300 ዓመታት አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር አደረገ? በየቀኑ ከእግዚአብሔር ጋር እየተራመድንና ነቅተን እየጠበቅን ካልሆነ ከአደጋ ነጻ እንዳልሆንን ይህ ለእኛ ትምህርት ነው ። "-Manuscript 10, 1886.

➡️ የጊዜው ማጠር

"ለእግዚአብሔር ሥራ ግድየለሽና ሰነፍ ለሆኑት ቀንም ሆነ ማታ እግዚአብሔር እረፍት አይስጣቸው፡፡ መጨረሻው ቅርብ ነው፡፡ የጊዜው አጭር የመሆን ጉዳይ ኢየሱስ ሁልጊዜ በፊታችን እንድናደርገው የሚፈልገው ነገር ነው::"—Letter 97, 1886.

"ከፊታችን ሊለካ የማይችል ዘላለም ተዘርግቶ በእጃችን የወርቅ በገናዎችንና የክብር ዘውዶችን ይዘን ከዳኑት ጋር በብርጭቆ ባህር ላይ ስንቆም ያሳለፍነው የመጠበቂያ ጊዜ ምን ያህል አጭር እንደነበር ያኔ እንመለከታለን።”—Manuscript Releases 10:266 (1886).

@MesayD

ምዕራፍ 4 ይቀጥላል ...
የመጨረሻው ዘመን ክስተቶች

ምዕራፍ 4:- የእግዚአብሔር የመጨረሻው ዘመን ቤተ ክርስቲያን

(ክፍል አንድ)

➡️ የእግዚአብሔር ሕዝብ ትዕዛዛቱን ይጠብቃሉ

"እግዚአብሔር በምድር ላይ የተረገጠውን ሕጉን ከፍ ከፍ የምታደርግና የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግደውን የእግዚአብሔርን በግ ለዓለም የምታቀርብ ቤተ ከርስቲያን አለችው፡፡..

"እግዚአብሔር አሁን በፈረሰው አጥር አጠገብ ያለችና አጥሩን መልሳ የምትገነባና ያረጀውንም ቦታ የምትጠግን አንዲት ቤተ ክርስቲያን በዓለም ውስጥ አለችው፡፡…

"ስለ ቅሬታዋ የተሰጠውን መግለጫ በምታሟላው ማለትም የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት በምትጠብቀውና የኢየሱስ ኃይማኖት ባላት ብቸኛ ቅሬታ ቤተ ክርስቲያን ላይ ተቃውሞን ከማንሳት ሁሉም ይጠንቀቁ።...

"እግዚአብሔር የተለየ ሕዝብ፣ ማንም የማይቀድማት ነገር ግን እውነትን ለማስተማርና የእግዚአብሔርን ሕግ ለመግለጽ ብቃት ያላት ከሁሉም በላይ የሆነች ቤተ ክርስቲያን በምድር ላይ አለችው፡፡.. ወንድሜ ሆይ፣ ሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተ ክርስቲያን ባቢሎን ነች ብለህ እያስተማርክ ከሆነ ተሳስተሃል።"—Testimonies to Ministers and Gospel Workers, 50, 58, 59 (1893) [የራዕይ መጽሐፍ በሁለት ቡድን የእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ ትኩረት ያደርጋል፡- የሚታዩ ቅሬታዎች (ራዕይ 12፡ 17) እና በባቢሎን ውስጥ ያሉ “ሕዝቤ” (ራዕይ 18፡4) የተባሉት ናቸው፡፡ ይህ ምዕራፍ የሚዳስሰው የመጀመሪያውን ቡድን እና ራዕይ ምዕራፍ 14ን ሲሆን “ታላቁ ጩኸት” የሚዳስሰው የኋለኛውን ቡድን ነው።]

➡️ የኢየሱስ ምስክር አላቸው

"መጨረሻው እየቀረበና ለዓለም የመጨረሻውን ማስጠንቀቂያ የመስጠት ሥራ እየቀጠለ ሲሄድ ከመነሻው ጀምሮ እግዚአብሔር በራሱ ፈቃድ ከሶስተኛው መልአክ መልእክት ጋር ያገናኘውን የወቅቱን እውነት የሚቀበሉ ሁሉ ስለ ምስከሮች ባህሪይና ተጽእኖ የጠራ መረዳት ማግኘት ሊኖራቸው ይገባል።"—Testimonies for the Church 5:654 (1889).

"ሰዎች የተለያዩ እቅዶችን ነድፈው ሊነሱ ይችላሉ። ጠላትም የእነርሱን ዕቅዶች በመጠቀም ነፍሳትን ከእውነት ሊያስታቸው ይሻል፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ለእህት ኤለን ጂ ኋይት መልእክት እንደሰጣትና በእርሷ አማካይነት እንደተናገረ የሚያምኑ ሁሉ በዚህ የመጨረሻ ዘመን ከሚመጡ ብዙ ማታለያዎች ይድናሉ።"—Selected Messages 3:83 84 (1906).

"ራዕይ እንደተሰጣቸው የሚናገሩ ብዙዎች ይኖራሉ። ራዕዩ ከእርሱ ስለመሆኑ እግዚአብሔር ግልጽ የሆነ ማረጋገጫ ሲሰጥህ መቀበል ትችላለህ። ነገር ግን በውጭ አገሮችና በአሜሪካ ብዙ ሰዎች ከእውነት እየራቁ (እየሳቱ) ሊሄዱ ስለሆነ በማንኛውም ሌላ ማረጋገጫ መቀበል የለብህም።" -Selected Messages 2:72 (1905).

➡️ድንበር አመልካች ምልክቶቻቸው'' መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተምህሮዎች ናቸው

"እ.አ.አ የ1844 ዓ.ም ማለፍ በመደነቅ በተሞሉ ዓይኖቻችን ፊት በምድር ላይካለው የእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር ወሳኝ ግንኙነት ያለውን የሰማያዊውን ቤተ መቅደስ መንጻት የገለጸበት ወቅት እንደመሆኑ የታላላቅ ክስተቶች ወቅት ነበር። እንዲሁም “የእግዚአብሔር ትዕዛዛትና የኢየሱስ እምነት' የሚል የእግዚአብሔር አርማ የተጻፈባቸው የመጀመሪያውና የሁለተኛ መላእክት መልእክቶች እና የሶስተኛው መልአክ መልእክት የተገለጠበት ወቅት ስለነበር የታላላቅ ክስተቶች ወቅት ነበር። በዚህ መልእክት ሥር ከነበሩ ምልክቶች መካከል አንዱ እውነትን ወዳድ በሆነ ሕዝቡ በሰማይ የታየው የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስና የእግዚአብሔርን ሕግ የያዘው ታቦት ነበር። የአራተኛው ትዕዛዝ የሰንበት ብርሃን የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት በሚተላለፉ ሰዎች ፊት ኃይለኛ የብርሃን ጮራዎችን አንጸባረቀ። ኃጢአተኞች ሟች መሆናቸው ጥንታዊ የእውነት ምልክት ነው። በጥንት ምልክቶች ሥር በሚመጣ እውነት ላይ ምንም ነገር መጨመር አልችልም።"—Counsels to Writers and Editors, 30, 31 (1889).

@MesayD

ይቀጥላል ...
👍42👏1🙏1
የመጨረሻው ዘመን ክስተቶች

ምዕራፍ 4:- የእግዚአብሔር የመጨረሻው ዘመን ቤተ ክርስቲያን

(ክፍል ሁለት)

➡️ የሰባተኛ ቀን አድቬንቲስቶች ልዩ ተልዕኮ

"እግዚአብሔር የሕጉ ተሸካሚዎች (ጠባቂዎች) አድርጎናል። ለሌሎች በታመኑ ማስጠንቀቂያዎች፣ ተግሳፆችና ማበረታቻዎች ሊሰጥ የሚገባውን ቅዱስና ዘላለማዊ እውነት ሰጥቶናል። "-Testimonies for the Church 5:381 (1885).

"የሰባተኛ ቀን አድቬንቲስቶች ከዓለም የተለዩ ሕዝብ ሆነው በእግዚአብሔር ተመርጠዋል። በታላቅ የእውነት መቁረጫ ከዓለም ዓለት ቆርጦ ከራሱ ጋር አገናኝቷቸዋል። በመጨረሻው የድነት ሥራ ውስጥ የራሱ ተወካዮች አድርጎ አምባሳደሮቹ እንዲሆኑ ጠርቷቸዋል። ለሟች ሰው ተሰጥተው ከሚያውቁ ታላላቅ የእውነት ሀብቶች ሁሉ በላይና ከእግዚአብሔር ለሰው ተልከው ከሚያውቁ በጣም ግልጽና አስፈሪ ማስጠንቀቂያዎች ሁሉ በላይ የሆነ ማስጠንቀቂያ ለዓለም እንዲያስተላልፉ ተሰጥቷቸዋል።" Testimonies for the Church 7:138 (1902).

"የሰባተኛ ቀን አድቬንቲስቶች በዓለም ውስጥ በተለየ ሁኔታ እንደ ጠባቂዎችና ብርሐን ተሸካሚዎች ሆነው ተቀምጠዋል። ለጠፊው ዓለም የመጨረሻውን ማስጠንቀቂያ የመስጠት ሀላፊነት ተሰጥቷቸዋል። በእነርሱ ላይ ከእግዚአብሔር ቃል የሚወጣ አስደናቂ ብርሐን እየበራ ነው። በጣም ታላቅ ጠቀሜታ ያለውን የመጀመሪያውን፣ የሁለተኛውንና የሶስተኛውን መላእክት መልእክት የማስተላለፍ ሥራ ተሰጥቷቸዋል። የዚህን ያህል ታላቅ ጠቀሜታ ያለው ሌላ ሥራ የለም። ምንም ሌላ ነገር ትኩረታቸውን እንዲስብ መፍቀድ የለባቸውም። "-Testimonies for the Church 9:19 (1909).

➡️ የ7ኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተ ክርስቲያን የተቋቋመችበት ምክንያቶች

"ቁጥራችን እየጨመረ ሲመጣ የቤተ ክርስቲያን ድርጅታዊ መዋቅር ከሌለ በስተቀር ታላቅ ግራ መጋባት ከመከሰቱም በላይ ሥራው በተሳካ ሁኔታ ወደ ፊት መቀጠል አለመቻሉ እሙን ነው፡፡ ለአገልግሎቱ ድጋፍ ለመስጠት፣ ሥራውን ወደ አዳዲስ መስኮች ለማድረስ፣ ቤተ ክርስቲያኗንና መልእክቷን ከማይረቡ አባላት ለመጠበቅ፣ የቤተ ክርስቲያንን ንብረት ለመያዝ፣ እውነትን በማተሚያ ቤቶች ለማተምና ለሌሎች ብዙ ዓላማዎች የቤተ ክርስቲያን ድርጅት አስፈላጊ ነው፡፡...

"በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ቅንጅትና ሥርዓት መኖር እንዳለበትና የቤተ ክርስቲያን ድርጅት አስፈላጊ ስለመሆኑ በመንፈሱ ብርሐን ተሰጥቶኛል። ሥርዓትና ቅንጅት በዓለማት ባሉ የእግዚአብሔር ሥራዎች በሙሉ ይታያሉ። ሥርዓት የሰማይ ሕግ እንደሆነ ሁሉ በምድር ላይ ያለው የእግዚአብሔር ሕዝብም ሕግ መሆን አለበት።"—Testimonies to Ministers and Gospel Workers, 26 (1902).

➡️ ድርጅት ሁልጊዜም አስፈላጊ ነው

"ቤተ ክርስቲያናት ሥርዓትን ማክበርና ማስከበር እንዲችሉ ካልተደራጁ በቀር ለወደፊት ተስፋ የሚያደርጉት ምንም ነገር ሊኖር አይችልም።"— Testimonies For The Church 1:270 (1862).

"ቅንነት የጎደላቸውን ተቃውሞዎች ለመከላከልና የእግዚአብሔር ቃል እውቅና የማይሰጣቸውን ሀሳቦች ስህተትነታቸውን ለማጋለጥ ፍጹም የቤተ ክርስቲያን ድርጅት በሚያስፈልግበትና ታላቅ ኃይል በሚሆንበት ወቅት ሰይጣን በእግዚአብሔር ሕዝቦች መካከል በመግባት ውዝግብ መፍጠር ሲችልና ሲሳካለት እጅግ ይደሰታል። ጥበብና ጥንቃቄ በተሞላበት ጥረት (ልፋት) የተገነባው የቤተ ክርስቲያን ድርጅት ሥርዓትና ቅንጅት እንዳይፈርስ መስመሮቹን በትክክል መያዝ እንፈልጋለን። በዚህ ወቅት ሥራውን ለመቆጣጠር ፍላጎት ላላቸው ሥርዓት አልበኞች ፈቃድ ሊሰጣቸው አይገባም።

"ወደ ዘመን መጨረሻ እየተቃረብን በሄድን ቁጥር እያንዳንዱ የእግዚአብሔር ልጅ ከማንኛውም የኃይማኖት ድርጅት ነጻ ሆኖ ለብቻው ይቆማል የሚል ሀሳብ ያላቸው አንዳንድ ሰዎች አሉ። ነገር ግን በዚህ ሥራ ላይ እያንዳንዱ ሰው ለብቻው ይቆማል የሚባል ነገር እንደሌላ ጌታ አስተምሮኛል።" [From manuscript read before the delegates at the General Conference Session, Washington, D.C., May 30, 1909. Testimonies for the Church 9:257, 258 (1909).

"ወደ መጨረሻው አስጨናቂ ጊዜ ስንቃረብ የተግባር ቅንጅትና መጣጣም ብዙም አያስፈልግም ብሎ ከማሰብ ይልቅ ከበፊቱ የበለጠ ሥርዓትን ተከትለን የምንሰራ መሆን አለብን።" -Selected Messages 3:26 (1892).

➡️ የእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን ልዩ ሥልጣን

እግዚአብሔር ማንም ባይቀበል ወይም ቢንቅ ከበደል ነጻ መሆን የማይችል ኃይልና ሥልጣን ለቤተ ክርስቲያን ሰጥቷል። የቤተ ክርስቲያንን ሥልጣን የሚንቅና የማይቀበል የእግዚአብሔርን ድምፅ ንቋል።-Testimonies for the Church 3:417 (1875).

እግዚአብሔር ከሰማይ በታች ታላቁን ኃይል የሰጠው ለቤተ ክርስቲያን ነው፡፡ መከበር ያለበት በተባበረችው ቤተ ክርስቲያን ችሎታ ውስጥ ያለው የእግዚአብሔር ድምጽ ነው ።-Testimonies for the Church 3:451 (1875).

@MesayD

ይቀጥላል ...
3
የመጨረሻው ዘመን ክስተቶች

ምዕራፍ 4:- የእግዚአብሔር የመጨረሻው ዘመን ቤተ ክርስቲያን

(ክፍል ሦስት)

➡️ መንፈሳዊ ድካምና እውርነት የታየበት ጊዜ

በሚኒያፖሊስ በተናገርኳቸው ነገሮች ሁሉ በቤተ ክርስቲያን ተሃድሶ መካሄድ እንዳለበት ማረጋገጫ ተሰጥቶኛል። በታላቅ ብርሃን እና በከበሩ ዕድሎችና አጋጣሚዎች በተባረከ ሕዝብ ላይ ስለሚታየው መንፈሳዊ ድካምና እውርነት ተሃድሶ መካሄድ አለበት፡፡ እነዚህ ሰዎች እንደ ተሃድሶ አራማጆች የእምነት ተቋም ካላቸው ቤተ ክርስቲያናት የወጡ ሲሆን አሁን እየፈጸሙ ያሉት ትተዋቸው የወጡባቸው ቤተ ክርስቲያናት ያደርጉ የነበረውን ሥራ ነው። ሌላ መውጣት አያስፈልግም ብለን ተስፋ አድርገን ነበር። [ኤለን ጂ ኋይት ከጻፈቻቸው ጽሁፎች ውስጥ በሰባተኛው ቀን አድቬንቲስት ቤተ ክርስቲያን ድርጅት ላይ እምነት ማጣትዋን የሚገልጽ አረፍተ ነገር ይህ ብቻ ነው። የዚህ ዓይነቱ ጥርጣሬ ቀጥለው በነበሩ የሕይወት ዘመኖቿ 26 ዓመታት ውስጥ አልተደገሙም።] በሰላም ማሰሪያ “የመንፈስ አንድነትን ለመጠበቅ” ጥረት እያደረግን ሳለ ግትርነትን በብዕር ወይም በድምጽ መቃወማችንን አናቆምም።- The Ellen G. White 1888 Materials, 356, 357 (1889).

በተሰጣቸው ብርሃን ለሚኩራሩና ለማይመላለሱበት ክርስቶስ እንዲህ ይላል፡-“ነገር ግን እላችኋለሁ፡- በፍርድ ቀን ከእናንተ ይልቅ ለጢሮስና ለሲዶና ይቀልላቸዋል። አንቺ ቅፍርናሆም (ታላቅ ብርሃን የተሰጣችሁ የሰባተኛ ቀን አድቬንቲስቶች) ሆይ! ራስሽን ወደ ላይ ከፍ ከፍ ያደረግሽ (ከተሰጡሽ ዕድሎች አንጻር)፣ ወደ ሲዖል ትወርጂያለሽ። በአንቺ የተደረጉ ታላላቅ ሥራዎች በሶዶም ተደርገው ቢሆን ኖሮ ሶዶም እስከ ዛሬ በኖረች ነበር።"—The Review and Herald, August 1, 1893. [በቅንፍ ውስጥ ያሉ አስተያየቶች በኤለን ኋይት የተሰጡ ናቸው።]

ቤተ ክርስቲያን በላውዶቂያነት ሁኔታ ውስጥ ነች። እግዚአብሔር በመካከልዋ አይደለም።- Notebook Leaflets 1:99 (1898).

➡️ በቤተ ክርስቲያን ዋና ቢሮዎች ሥልጣንን ያለ አግባብ መጠቀም

ጄኔራል ኮንፍራንስ እራሱ በስህተት አመለካከቶችና መርሆዎች እየረከሰ ነው።_

ሰዎች በሥልጣናቸው ሥር መሆን እንዳለባቸው ከሚገምቱአቸው አግባብነት የሌለው ጥቅም እያገኙ ነው፡፡ ግለሰቦቹን በእነርሱ ሀሳብ እንዲስማሙ ለማድረግ ወስነዋል፡፡ ይገዙአቸዋል ወይም ያጠፉአቸዋል።….

ሥልጣን ሰውን አማልክት ያደርግ ይመስል የተፈጠረው የበላይነትን የሚሰጥ ሥልጣን ያስፈራኛል፣ ማስፈራትም አለበት። ሥልጣን በማንም፣ የትም ቦታ ቢሆን በዚህ ሁኔታ ጥቅም ላይ ከዋለ እርግማን ነው። Testimonies to Ministers and Gospel Workers, 359-361 (1895).

ከአቅም በላይ የሆኑ እጅግ ከባድ ኃላፊነቶች በጥቂት ሰዎች ላይ ተጭነዋል፤ ከእነዚህ መካከል አንዳንዶቹ እግዚአብሔርን አማካሪያቸው የማያደርጉ ናቸው። እነዚህ ሰዎች በውጭ አገሮች ስላለው ሥራ ስለሚያስፈልጉ ነገሮች ምን ያውቃሉ? መረጃን ለማግኘት ወደ እነርሱ በሚቀርቡ ጥያቄዎች ላይ እንዴት መወሰን እንዳለባቸው እንዴት ማወቅ ይችላሉ? በውጭ አገር ያሉ ሰዎች ለጥያቄዎቻቸው መልስ ለማግኘት በመጻፍ ላይ መዘግየት ካልተፈጠረ ሶስት ወር ይጠይቃል።—Testimonies to Ministers and Gospel Workers, 321 (1896).

በሩቅ አገሮች የሚኖሩ ሰዎች ከባትል ክሪክ ፈቃድ ለማግኘት አስቀድመው ካልላኩ በቀር አእምሮአቸው ትክክል እንደሆነ የሚነግራቸውን ነገር አይፈጽሙም። አንድን ነገር ከማድረጋቸው በፊት (አንድ እርምጃ ከመሄዳቸው በፊት) የይሁንታን መልስ ከዚያ ይጠብቃሉ።-Special Testimonies, Series A 9:32 (1896).

በጄነራል ኮንፍራንስ አንድ ሰው ብቻ ፕሬዝደንት አድርጎ መምረጥ አይመከርም። የጄኔራል ኮንፍራንስ ሥራ ከመስፋፋቱ የተነሳ አንዳንድ ነገሮች አላስፈላጊ በሆነ ሁኔታ ተወሳስበዋል፡፡ የማስተዋል ጉድለቶች ታይተዋል፡፡ አሁን ያለውን ሁኔታ ለመለወጥ የፊልድ ክፍፍል ወይም ሌላ እቅድ መቀየስ አለበት፡፡ Testimonies to Ministers and Gospel Workers,342 (1896).

[የሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተ ክርስቲያን የተመሰረተችው እ.አ.አ 1863 ዓ.ም ሲሆን 3500 አባላት፣ 6 ኮንፍራንሶች፣ 30 የሚሆኑ የወንጌል አገልጋዮችና ሶስት አባላት የነበሩት የጄኔራል ኮንፍራንስ ኮሚቴ ነበራት። ለዚህ ትንሽ ድርጅት የጄኔራል ኮንፍራንሱ ፕሬዝደንት አመራርና ምክር መስጠት ይችል ነበር። እያንዳንዱን አስፈላጊ ስብሰባ በአካል ተገኝቶ ለመካፈልና ለሕትመት ሥራ የሚወጣውን ወጪ መቆጣጠር ይችል ነበር። ነገር ግን እ.አ.አ 1896 ዓ.ም አካባቢ ሥራው በአሜሪካ፣ በአውሮፓ፣ በአውስትራሊያና በአፍሪካ በጣም ተስፋፍቶ ነበር። ስለዚህ ለአንድ ሰው በቂ ክትትልና መመሪያ ለመስጠት አዳጋች ነበር። በዓለም ዙሪያ ያሉ የቤተ ክርስቲያን አባሎቻችን ከአንድ ሰው ብቻ ምክር መጠበቅ ስለሌለባቸው የፊልድ ክፍፍል እንዲኖር ኤለን ጂ ኋይት ገፋፍታለች፡፡ ይህም የዩኒየን ኮንፍራንሶችንና የዓለም ዲቪዥኖችን በመፍጠር ተፈጻሚ ሆኗል።

@MesayD

ይቀጥላል ...
🔥52
የመጨረሻው ዘመን ክስተቶች

ምዕራፍ 4:- የእግዚአብሔር የመጨረሻው ዘመን ቤተ ክርስቲያን

(ክፍል አራት)

➡️ ጥበብ የሌላቸው (ሞኝ) መሪዎች ለእግዚአብሔር አይናገሩም

ሥራው እንዴት መሰራት እንዳለበት በመምከር ረገድ ሥልጣን እንዳለው ይታይ የነበረው ከባትል ክሪክ ይወጣ የነበረው ድምጽ የእግዚአብሔር ድምጽ መሆኑ ቀርቷል። Manuscript Releases 17:185 (1896).

የጄኔራል ኮንፍራንስን ድምጽ እንደ እግዚአብሔር ድምጽ አድርጌ እወስድ የነበረው ከተወሰኑ ዓመታት በፊት ነበር።- Manuscript Releases 17:216 (1898).

በአንድ ወቅት ጄኔራል ኮንፍራንስ የእግዚአብሔር ድምጽ እንደሆነ እናምን እንደነበረው እነዚህም ሰዎች ለሕዝቡ እንደ እግዚአብሔር ድምጽ ለመሆን በተቀደሰ ቦታ የመቆማቸው ጉዳይ ጊዜ አልፎበታል። The General Conference Bulletin, April 3, 1901, p.25.

➡️ አዲስ የኃይማኖት ድርጅት አያስፈልግም

ከምስክሮች ውስጥ ስለ ምህረት በር መዘጋትና በእግዚአብሔር ሕዝቦች መካከል ስለሚኖረው ብጠራ የሚናገሩ አንዳንድ ጽሁፎችን በመውሰድ ከዚህ ሕዝብ መካከል ንጹህና ቅዱስ ሕዝብ እንደሚነሳ ትናገራለህ። አሁን ይህ ሁሉ ጠላትን ያስደስተዋል። አንተ ያለህን አመለካከት ብዙዎች ተቀብለው ቢናገሩና ቢፈጽሙ ኖሮ በሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ ታላቅ ጥራዝ ነጠቅ መነቃቃት ይፈጠር ነበር። ሰይጣን የሚሻው ይህን ነው::—Selected Messages 1:179 (1890).

እግዚአብሔር የሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተ ክርስቲያንን ባቢሎን እንድትልና ከእርሷ እንዲወጡ ሰዎችን እንድትጠራ መልእክት አልሰጠህም። የዚህን ዓይነት መልእክት የሚቃወም ጽኑ ብርሃን እግዚአብሔር ስለሰጠኝ የምታቀርባቸው ምክንያቶች በሙሉ በእኔ ዘንድ ቦታ የላቸውም።....

እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያኑን እንደሚወድ አውቃለሁ፡፡ ቤተ ክርስቲያን እንድትዝረከረክና ወደ ጥቃቅን አቶሞች እንድትከፋፈል አያስፈልግም፡፡ በዚህ ነጥብ ላይ ትንሽ ስምምነት እንኳን የለም። የዚህ ዓይነት ነገር እንደሚሆን የሚደግፍ ትንሽ ማስረጃ እንኳን የለም። -Selected Messages 2:63, 68, 69 (1893).

ወንድሞቼ ሆይ፣ እግዚአብሔር ሥራውን የሚሰራበት የተደራጀ አካል እንዳለው እነግራችኋለሁ። ማንም ቢሆን ከዚህ ከተደራጀ የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት ከሚጠብቅ ሕዝብ ሲለይ እና ቤተ ክርስቲያንን በራሱ ሰብአዊ ሚዛን መመዘንና በእነርሱ ላይ መፍረድ ሲጀምር፣ ያኔ እግዚአብሔር እየመራው አለመሆኑን መረዳት ትችላላችሁ፡፡ ይህ ግለሰብ ያለው በተሳሳተ መንገድ ላይ ነው። - Selected Messages 3:17, 18 (1893).

➡️ እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር በሥርዓት ያስቀምጠዋል

ሥራው እንደማይሳካ አድርጎ መፍራትና መጠራጠር አያስፈልግም፡፡ ሥራውን የሚመራው እግዚአብሔር ስለሆነ ሁሉንም ነገር በሥርዓት ያስኬደዋል። እግዚአብሔር ሥራውን እየመራ ሳለ መስተካከል ያለባቸው ነገሮች ካሉ እነዚያን ነገሮች እርሱ ይከታተላቸውና መጥፎውን ሁሉ ወደ መልካም ይለውጣል፡፡ እግዚአብሔር ሕዝቡን የተሸከመውን አስደናቂ መርከብ በሰለም ወደ ወደቡ እንደሚያደርስ እምነት ይኑረን።— Selected Messages 2:390 (1892).

እግዚአብሔር ሕያው ቤተ ክርስቲያን የለውምን? ቤተ ክርስቲያን አለችው፣ ነገር ግን ድል የነሳች ቤተ ክርስቲያን ሳትሆን በጦርነት ላይ ያለች ቤተ ክርስቲያን ነች። ጉድለት ያለባቸው አባላት በመኖራቸውና በስንዴው መካከል እንክርዳድ በመኖሩ እናዝናለን።…. ምንም እንኳን በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ክፋት (እርኩሰት) ቢኖርም፣ እስከ ዓለም መጨረሻ ድረስም የሚኖር ቢሆንም፣ በዚህ በመጨረሻው ዘመን የምትኖር ቤተ ክርስቲያን በኃጢአት ለረከሰውና ለወደቀው ዓለም ብርሃን መሆን አለባት። ቤተ ክርስቲያን ደካማና ጉድለት ያለባት፣ ማስጠንቀቂያ፣ ምክርና ተግሳጽ የሚያስፈልጋት ብትሆንም፣ በምድር ላይ ክርስቶስ ከሁሉም በላይ ትኩረት የሚያደርግባት ብቸኛ አካል ነች።— Testimonies to Ministers and Gospel Workers, 45, 49 (1893).

የሰይጣን መከላከያዎች በፍጹም ድል አይነሱም፡፡ ድል የሶስተኛውን መልአክ መልእክት ይከተላል። የእግዚአብሔር ሰራዊት መሪ የኢያሪኮን ግንብ እንዳፈረሰው ሁሉ የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት የሚጠብቁ ሕዝቦችም እንዲሁ ድልን ይቀዳጃሉ። ተቃዋሚ ኃይላት በሙሉ ይሸነፋሉ።- Testimonies to Ministers and Gospel Workers, 410 (1898).

@MesayD

ይቀጥላል ....
5👏3
የመጨረሻው ዘመን ክስተቶች

ምዕራፍ 4:- የእግዚአብሔር የመጨረሻው ዘመን ቤተ ክርስቲያን

(ክፍል አምስት)

➡️ ሀላፊነትን ለማጋራት የቀረበ አስቸኳይ ጥሪ

አሁን የምንፈልገው እንደገና መደራጀት ነው። ከመሰረቱ ጀምረን ልዩ በሆነ መርህ ላይ መገንባት እንፈልጋለን፡፡….

በተለያዩ አገሮች ባሉን ልዩ ልዩ ድርጅቶች፣ የትምህርት ተቋማት እና በተለያዩ ቦታዎችና ግዛቶች ባሉ ኮንፍራንሶች የሥራ መሪ የሆኑ ሰዎች አሉን፡፡ እነዚህ ሁሉ መፈጸም ያለባቸውን እቅዶች በመቅረጽና በማስተካከል ድምጽ እንዲኖራቸው እንደ ተወካዮች ሆነው መቆም አለባቸው፡፡ ጠቅላላውን ሰፊ የሥራ መስክ ለመከታተል ከአንድ ወይም ከሁለት ወይም ከሶስት ሰዎች በላይ መሆን አለባቸው። ሥራው ትልቅ ስለሆነ መሰራት ላለበት ሥራ ሁሉ ማቀድ የሚችል አንድ ሰብአዊ አእምሮ የለም።....

ይህንንም ሆነ ያንን የሥራ ዘርፍ ለመቆጣጠር የሚያስችል ንጉሣዊ ሥልጣን እግዚአብሔር እንዳልሰጠን መግለጽ እፈልጋለሁ። በየአቅጣጫው ሥራውን ለመቆጣጠር በሚደረግ ጥረት ምክንያት ሥራው በጣም ከፍተኛ በሆነ ሁኔታ ተገትቷል። ተሃድሶና እንደገና መደራጀት ያስፈልጋል፡፡ ኃይልና ብርታት አስፈላጊ ለሆኑ ኮሚቴዎች መሰጠት አለበት።" [From Ellen White's opening address on April 2, 1901, to the General Conference Session in Battle Creek.] The General Conference Bulletin, April 3, 1901, pp. 25, 26.

አዳዲስ ኮንፍራንሶች መመስረት አለባቸው። በአውስትራሊያ የተቋቋማው ኮንፍራንስ የተመሰረተው በእግዚአብሔር ትዕዛዝ ነው። ምክርን ለመጠየቅ ብዙ ሺህ ማይሎችን አቋርጦ ወደ ባትል ክሪክ መላክና ለመልስ ሳምንታትን መጠበቅ አስፈላጊ አይደለም፡፡ ምን መደረግ እንዳለበት በቦታው ያሉ ትክክለኛ አቋም ያላቸው ሰዎች መወሰን አለባቸው።- The General Conference Bulletin, April 5, 1901, pp. 69, 70.

➡️ እ.አ.አ. የ1909 ዓ.ም የጄኔራል ኮንፍራንስ ስብሰባ ምላሽ ሰጠ

ይህ ኮንፍራስ ከተጀመረ ወዲህ በመካከላችን ያለው ማን ነው ብላችሁ ትገምታላችሁ? በዚህ ዓይነቱ ስብሰባ ላይ የሚያስጠሉ ሁኔታዎችን የተቆጣጠረው ማን ነው? በዚህ ምኩራብ/አዳራሽ መካከል ወደ ላይና ወደ ታች የተመላለሰው ማን ነው? የሰማይ አምላክና መላእክቱ ናቸው፡፡ ወደዚህ የመጡት ሊበታትኑአችሁ ሳይሆን ትክክለኛና ሰላም የተሞላ አእምሮ ሊሰጡአችሁ ነው። በመካከላችን የነበሩት እግዚአብሔር ያቀደው ሥራ እንዲሰራና እንዳይገታ የእግዚአብሔርን ሥራ ለመስራትና የጨለማ ኃይሎችን ወደ ኋላ ለመመለስ ነው። የእግዚአብሔር መላእክት በመካከላችን ሲሰሩ ነበር።….

በዚህ ስብሳባ ላይ ነገሮች የተከናወኑበትን መንገድ ተመልከቼ የተደነቅኩትን ያህል በሕይወቴ ያስደነቀኝ ምንም ነገር የለም። ይህ የእኛ ሥራ አይደለም፡፡ ያደረገው እግዚአብሔር ነው። ይህን በተመለከተ መመሪያ ተሰጥቶኝ ነበር፣ ነገር ግን በዚህ ስብሰባ ላይ ውጤቱ እስኪሰራ ድረስ ይህንን መመሪያ መገንዘብ አልቻልኩም ነበር። በዚህ ጉባኤ ውስጥ የእግዚአብሔር መላእክት ወደ ላይና ወደ ታች ሲመላለሱ ነበር። ይህን ነገር እያንዳንዳችሁ እንድታስታውሱት የምፈልግ ሲሆን እግዚአብሔር የሕዝቡን ቁስሎች እፈውሳለሁ ማለቱንም እንድታስታውሱ እፈልጋለሁ።—The General Conference Bulletin, April 25, 1901, pp. 463, 464.

በጄኔራል ኮንፍራስ ስብሰባ ጊዜ እግዚአብሔር ለሕዝቡ በኃይል ሰርቷል። ስለዚያ ስብሰባ በማስታውስበት ጊዜ ሁሉ ጣፋጭ የሆነ የአክብሮት ስሜት ወደ አእምሮዬ በመምጣት ለነፍሴ የአመስጋኝነትን ግለት ይልካል። አዳኛችን የሆነውን የጌታን አስደናቂ እርምጃዎች ተመልክተናል። ሕዝቡን ነጻ ስላወጣ ቅዱስ ስሙን እናወድሳለን። The Review and Herald, November 26, 1901.

ጄኔራል ኮንፍራንስ ተለያይተው ባሉ ኮንፍራንሶች ሁሉ ላይ አምባገነንነትን እንዳያሳይ የዩኒየን ኮንፍራንሶችን ማደራጀት አስፈላጊ ነበር። ለኮንፍራንስ የተሰጠው ሥልጣን አንድ ወይም ሁለት ወይም ስድስት ሰዎችን ማዕከል ያደረገ መሆን የለበትም፡፡ በተለያዩ ዲቪዥኖች ላይ የሰዎች መማክርት ጉባኤ መኖር አለበት። Manuscript 26, 1903 (April 3). [በ1901 ዓ.ም በተካሄደው የጄኔራል ኮንፍራንስ ስብሰባ ላይ ስለተደረጉ የአደረጃጀት ለውጦች ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ የሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት እንሳይክሎፒዲያን ይመልከቱ (Vol. 10 of the Commentary Reference Series), Revised Edition, pp. 1050-1053.]

@MesayD

ይቀጥላል ...
3
የመጨረሻው ዘመን ክስተቶች

ምዕራፍ 4:- የእግዚአብሔር የመጨረሻው ዘመን ቤተ ክርስቲያን

(ክፍል ስድስት)

➡️ በሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ድርጅት መተማመን እንደገና ተረጋገጠ

አሁን እግዚአብሔር የመሰረተውን መሰረት ትተን መውጣት አንችልም። ወደ አዲስ ድርጅት መግባት ማለት እውነትን መካድ ስለሆነ አሁን ወደ ማንኛውም አዲስ ድርጅቱ መግባት አንችልም።- Selected Messages 2:390 (1905).

በዓለም ላይ ላሉ አድቬንቲስቶች ይህንን እንድል ታዝዣለሁ፣ እግዚአብሔር እንደ ሕዝብ የተለየ ከቡር ሕዝብ እንድንሆን ጠርቶናል። በምድር ላይ ያለችው ቤተ ክርስቲያን እስከ ዘመን መጨረሻ ድረስ በመንፈስና በሰራዊት ጌታ ምክር ፍጹም የተባበረች እንድትሆን አስቀምጦአታል።- Selected Messages 2:397 (1908).

አንዳንድ ጊዜ የሥራው አጠቃላይ ሀላፊነት የተሰጣቸው ጥቂት ቡድኖች በጄኔራል ኮንፍራንስ ስም የእግዚአብሔርን ሥራ የሚገድቡ ጥበብ የጎደላቸውን ዕቅዶች ለመተግበር ሲሹ በእነዚህ ጥቂት ሰዎች የተወከለውን የጄኔራል ኮንፍራንስ ድምጽ እንደ እግዚአብሔር ድምጽ እንደማልቆጥር ተናግሬያለሁ። ይህ ማለት ግን ከሁሉም የሥራ መስኮች ተውጣጥተው በአግባቡ የተሾሙ የጄኔራል ኮንፍራንስ ተወካዮች ውሳኔዎች መከበር የለባቸውም ማለት አይደለም።

ከሁሉም የምድር ክፍሎች የተውጣጡ የቤተ ክርስቲያን ተወካዮች በጄኔራል ኮንፍራንስ ላይ ሲሰበሰቡ ሥልጣን እንዲኖራቸው እግዚአብሔር ቀብቷቸዋል። አንዳንዶች ሊፈጽሙ የሚችሉት ስህተት አደጋ ያለው ሊሆን የሚችለው እግዚአብሔር ለሥራው ስኬትና ወደ ፊት መሄድ በፍርድ ለቤተ ክርስቲያንና ለተሰበሰበው የጄኔራል ኮንፍራንስ ድምጽ የሰጠውን ሥልጣንና ተጽእኖ ሙሉ በሙሉ ለአንድ ሰው ወይም ለጥቂት የሰዎች ቡድን አእምሮና ውሳኔ አሳልፎ በመስጠት ነው። Testimonies for the Church 9:260, 261 (1909).

እግዚአብሔር ማንም ባይቀበል ወይም ቢንቅ ከበደል ነጻ መሆን የማይችልበትን ኃይልና ሥልጣን ለቤተ ክርስቲያኑ ሰጥቷል፤ የቤተ ክርስቲያንን ሥልጣን የሚንቅና የማይቀበል የእግዚአብሔርን ሥልጣን እየናቀ ነው።- The Acts of the Apostles, 164 (1911).

የእሥራኤል አምላክ እስካሁን ሕዝቡን እየመራ በመሆኑና ወደፊትም እስከ መጨረሻው ድረስ ከእነርሱ ጋር እንደሚሆን በመገንዘቤ ተደፋፍሬያለሁ ተባርኬያለሁም።—Selected Messages 2:406 (1913). [በጄኔራል ኮንፍራንስ ስብሰባ ጊዜ ለሰባተኛ ቀን አድቬንቲስት ቤተ ክርስቲያን ኤለን ኋይት ከሰጠችው የመጨረሻ መልእክት የተወሰደ ነው። እነዚህ እርግጠኛ እንዲሆኑ የተሰጡ ቃላት በጄኔራል ኮንፍራንስ ስብሰባ ላይ የጄኔራል ኮንፍራንስ ፕሬዝደንት በሆኑት በኤ ጂ ዳንኤልስ እ.አ.አ ግንቦት 27፣ 1913 ዓ.ም. ተነበው ነበር።]

➡️ በደብሊዩ ሲ የተነገረ ዓረፍተ ነገር

እናቴ የቅሬታዋን ቤተ ክርስቲያን ልምምድና ሌላ ቤተ ክርስቲያን እስኪወጣ ድረስ ሙሉ ክህደት እንዲከሰት እግዚአብሔር እንደማይፈቅድ ያስተማረችውን አዎንታዊ ትምህርቷን እንዴት ትመለከት እንደነበር ነገርኳት [ለሚስስ ሊዳ እስኮት)።—W..C. White to E. E. Andross, May 23, 1915, White Estate Correspondence File.

@MesayD

ይቀጥላል ...
4