እግዚአብሔር ይመስገን የመጀመሪያ አካዳሚያዊ አርቲክሌ ለህትመት በቅቷል። download እያደረጋችሁ አንብቧት። ነገርየው book review ነው። ያው ብዙ ሰው ባነበበ ቁጥር ብዙ ለመጻፍ ያበረታታልና አንብባችሁ ሃሳብ አስታያየታችሁን አጋሩኝ። ጆርናሉ ላይ ሌሎች ቆንጆ ቆንጆ articles አሉ በነጻ እያወረዳችሁ ማንበብ ትችላላችሁ። መልካም ንባብ!
https://ethiopiantheologicaljournal.com/index.php/ethiopiantheologicaljournal/article/view/11
https://ethiopiantheologicaljournal.com/index.php/ethiopiantheologicaljournal/article/view/11
❤21😱3
Natty's Perspectives pinned «እግዚአብሔር ይመስገን የመጀመሪያ አካዳሚያዊ አርቲክሌ ለህትመት በቅቷል። download እያደረጋችሁ አንብቧት። ነገርየው book review ነው። ያው ብዙ ሰው ባነበበ ቁጥር ብዙ ለመጻፍ ያበረታታልና አንብባችሁ ሃሳብ አስታያየታችሁን አጋሩኝ። ጆርናሉ ላይ ሌሎች ቆንጆ ቆንጆ articles አሉ በነጻ እያወረዳችሁ ማንበብ ትችላላችሁ። መልካም ንባብ! https://ethiopiantheologicaljourna…»
Natty's Perspectives
አስደሳች ዜና! የፊታችን ሰኞ ሕትመት ቤት ልትገባ ነው! የኑ! እናስብ ቅጽ አንድ መጽሐፍ በገበያ ላይ ሊውል ጥቂት ቀናት ቀሩት፤ ለዚያ እንዲያግዝ በቅድመ ሽያጭ መጽሐፉን ለማሳተም ክፍያና ምዝገባ ተጀምሯል። የአከፋፈል ሂደቱ ይህን ይመስላል፦ 1) 600 ብር ለአገር ውስጥ ወይም $20 ለውጪ ነዋሪ በመክፈል ደረሰኙን ከታች በተቀመጠው የቴሌግራም ዩዘርኔም መላክ፣ 2) በዚህ @homme45 (ወይም…
ወዳጆች፣
የየሹ መጽሐፍ ለህትመት የአማዞን partner በሆነው በኩሉ ላይ ተለቋል። ከሃገር ውጭ ያላችሁ እየገዛችሁ ብታነቡ እነሰደምትጠቀሙ አምናለሁ። የሹዬ በርታልኝ። እግዚአብሔር በልፋትህ ይክበር።
https://kulu1.com/product/%e1%8a%91-%e1%8a%a5%e1%8a%93%e1%88%b5%e1%89%a5/
የየሹ መጽሐፍ ለህትመት የአማዞን partner በሆነው በኩሉ ላይ ተለቋል። ከሃገር ውጭ ያላችሁ እየገዛችሁ ብታነቡ እነሰደምትጠቀሙ አምናለሁ። የሹዬ በርታልኝ። እግዚአብሔር በልፋትህ ይክበር።
https://kulu1.com/product/%e1%8a%91-%e1%8a%a5%e1%8a%93%e1%88%b5%e1%89%a5/
KULU1 – KULU1.COM
ኑ! እናስብ – KULU1
...ሰዎች ለምን በውሳኔዎቻቸው ይሳሳታሉ? ለምን ይሆን በአስተሳሰባቸው የማያስፈልግ ነገር የሚታየው? ለምንስ ነው ተፋልሶ የሚፈጽሙት? እነዚህንና የመሳሰሉትን ጥያቄዎች እንድንጠይቅ የሚያደርገን የሰዎች አስተሳሰብ መጥራት በሚገባው ልክ አለመጥራቱ ነው። ስለ ተፋልሶና በአጠቃላይ ስለ አመክንዮ (ምክንያታዊነት) በማንበብና ጽሑፍ በማዘጋጀት ላይ እያለሁ በአንዳንድ ጽሑፎች የተፋልሶ ወይም በዐረፍተ ነገራዊ ብይን…
❤10
መልካም የእናቶች ቀን ወዳጆች፣
ዛሬ ቤተክርስቲያናችን የተካፈልነው፣ እንዲሁም እኔም ከሰሞኑ ሳስብ የነበረው 1 ሳሙኤል 1 ነበር።
ሐናን ልብ ብለን ካየናት በመከራ ውስጥ በእግዚአብሔር ላይ ያላትን እምነትና በጸሎት መጽናት እንመለከታለን። እንዲሁም ከባሏ ጋር ያላትን መልካም ህብረትና ለጌታ ያላትን መሰጠት እናያለን።
በተጨማሪም፣ ልጁ ጡት እስኪጥል ድረስ በቤቷ ሆና ልጇን ለማሳደግ ያላትን ቆራጥነት ስንመለከት፣ ለእናትነት ያላትን ትልቅ ቦታ እንረዳለን። ሳሙኤልን ለእግዚአብሔር አሳልፋ ስትሰጥ ደግሞ፣ የእናትነት ዓላማዋ ለእግዚአብሔር የሚሆን ትውልድ መቅረጽ እንደሆነ እናያለን።
ብቻ ምናለፋችሁ፣ ሐና ብርቱ፣ ጠንካራ፣ ለቤቷ ቅድሚያ የምትሰጥና ልጇቿን ለጌታ ብላ የምታሳድግ ብርቱ እናት ናት። ፍሬዋም ሃያል ነው። በመሳፍንት ዘመን፣ የእግዚአብሔር ድምጽ ከሕዝቡ በራቀበት፣ የእግዚአብሔርን ድምጽ የሚያሰማ ነብይ ለትውልዱ አበርክታለች። የካህናት ልጆች በምንዝርና በተሞሉበት እሷ ግን እግዚአብሔርን የሚፈራ ድምጹ ከጫፍ እስከጫፍ የሚሰማ ሃያል እንዲነሳ ምክንያት ሆናለች።
እግዚአብሔር እንዲህ ያሉ ጀግና እናቶቸን ያስነሳልን! ደግሞም እንዲህ ያሉ ጀግና እናቶችን በያሉበት በበረከቱ ያግኛቸው።
@Romans148

❤24
እግሮችም ፡ የሉኝም ፡ ፊትህ ፡ የምቆምበት
ዓይኖችም ፡ የሉኝም ፡ አንተን ፡ የማይበት
የጠራኸኝ ፡ አምላክ ፡ ውርደቴን ፡ ተመልከት
ከገባሁበት ፡ ማጥ ፡ አውጣኝ ፡ በአንተ ፡ ምህረት
አዝ፦ ስብራቴ ፡ የማይፈወስ ፡ ይመስላል
መደኃኒቴ ፡ አንተ ፡ ግን ፡ ምን ፡ ይሳንሃል
ምህረትህ ፡ ካለ ፡ ማጉረምረም ፡ ምን ፡ ይጠቅመኛል
በእጅህ ፡ ውስጥ ፡ መውደቅ ፡ ኦ ፡ እጅግ ፡ ይሻለኛል
ከአንተ ፡ የተሰወረ ፡ ምን ፡ አለ ፡ ጌታ ፡ ሆይ
ፍፁም ፡ ሳይገለጽ ፡ ተደብቆ ፡ የሚቆይ
የልቤ ፡ መርማሪ ፡ የእኔ ፡ ውስጥ ፡ አዋቂ
ጉድለቴን ፡ ይቅር ፡ በል ፡ የነፍሴ ፡ ጠባቂ
አዝ፦ ስብራቴ ፡ የማይፈወስ ፡ ይመስላል
መደኃኒቴ ፡ አንተ ፡ ግን ፡ ምን ፡ ይሳንሃል
ምህረትህ ፡ ካለ ፡ ማጉረምረም ፡ ምን ፡ ይጠቅመኛል
በእጅህ ፡ ውስጥ ፡ መውደቅ ፡ ኦ ፡ እጅግ ፡ ይሻለኛል
ምንም ፡ ቸር ፡ ብትሆን ፡ በአንተ ፡ አይዘበትም
ጉዴን ፡ ለመሸፈን ፡ ምክንያት ፡ አላቀርብም
ያው ፡ ከነበደሌ ፡ ራሴን ፡ ሰጥቻለሁ
ምረህ ፡ ተቀበለኝ ፡ ቃልህን ፡ ጥሻለሁ
አዝ፦ ስብራቴ ፡ የማይፈወስ ፡ ይመስላል
መደኃኒቴ ፡ አንተ ፡ ግን ፡ ምን ፡ ይሳንሃል
ምህረትህ ፡ ካለ ፡ ማጉረምረም ፡ ምን ፡ ይጠቅመኛል
በእጅህ ፡ ውስጥ ፡ መውደቅ ፡ ኦ ፡ እጅግ ፡ ይሻለኛል
ምንም ፡ እንኳን ፡ ዛሬ ፡ ሃፍረት ፡ ቢሸፍነኝ
ፊትህን ፡ ለማየት ፡ ከቶ ፡ ቢያዳግተኝ
በተስፋ ፡ ዝም ፡ ብዬ ፡ ቀኔን፡ ጠብቃለሁ
በድል ፡ ልታድሰኝ ፡ እንደምትችል ፡ አምናለሁ
አዝ፦ ስብራቴ ፡ የማይፈወስ ፡ ይመስላል
መደኃኒቴ ፡ አንተ ፡ ግን ፡ ምን ፡ ይሳንሃል
ምህረትህ ፡ ካለ ፡ ማጉረምረም ፡ ምን ፡ ይጠቅመኛል
በእጅህ ፡ ውስጥ ፡ መውደቅ ፡ ኦ ፡ እጅግ ፡ ይሻለኛል
https://youtu.be/7oXQGbIQI20?si=UIwYN4kztyZ-bNBQ

YouTube
ዘማሪ ፓስተር ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ ስብራቴ የማይፈወስ ይመስላል / pastor tesfaye gabiso seberate yemayefewese yemeselal
ዘማሪ ፓስተር ተስፋዬ ፡ ጋቢሶ ስብራቴ የማይፈወስ ይመስላል / pastor tesfaye gabiso seberate yemayefewese yemeselal
እግሮችም ፡ የሉኝም ፡ ፊትህ ፡ የምቆምበት
ዓይኖችም ፡ የሉኝም ፡ አንተን ፡ የማይበት
የጠራኸኝ ፡ አምላክ ፡ ውርደቴን ፡ ተመልከት
ከገባሁበት ፡ ማጥ ፡ አውጣኝ ፡ በአንተ ፡ ምህረት
አዝ፦ ስብራቴ ፡ የማይፈወስ ፡ ይመስላል
መደኃኒቴ ፡ አንተ ፡…
እግሮችም ፡ የሉኝም ፡ ፊትህ ፡ የምቆምበት
ዓይኖችም ፡ የሉኝም ፡ አንተን ፡ የማይበት
የጠራኸኝ ፡ አምላክ ፡ ውርደቴን ፡ ተመልከት
ከገባሁበት ፡ ማጥ ፡ አውጣኝ ፡ በአንተ ፡ ምህረት
አዝ፦ ስብራቴ ፡ የማይፈወስ ፡ ይመስላል
መደኃኒቴ ፡ አንተ ፡…
❤19😭3
እንደ ሐዋርያቱ መረቤንና የኔ የምለውን ነገር ሁሉ በሚያስጥል ብርቱ ድምጽህ ስለጠራኸኝ፣ እንደነ ማሪያም ካሰረኝ ጭለማ ስለፈታኸኝ፣ በምትሄድበት ሁሉ እከተልሃለሁ፣ እንደምትሻውም ሆኜ በሁለንተናዬ አገለግልሀለሁ።
@Romans148
@Romans148
❤28👍1
Natty's Perspectives
የመጨረሻው ክፍል፣ የዘሪቱ ዝማሬ አስተንትኖት ክፍል 3፤ ክርስቶስ ብቻ "ጸጋው" በተሰኘው መዝሙር ውስጥ በቀደሙት ሁለት ክፍሎች ውስጥ ጸጋው በተሰኘው የዘሪቱ ዝማሬ ውስጥ ኃጢአትና የእግዚአብሔር ጸጋ እንዴት እንደተንጸባረቁ ለመተንተን ሞክሬያለሁ። ኃጢአት አቅመቢስነት፣ በእግዚአብሔር ፊት አለመብቃት፣ የሰውን ዘር ሁሉ ያጥለቀለቀ ጥልቅ ሁለንተናዊ ብልሽት፣ ወዘተ መሆኑን ተመልክተናል። እንዲሁም፣ እንዲህ…
የዓለም ኃጢአተኞች እንኳን ደስ አላችሁ
ኢየሱስ ክርስቶስ መጥቷል ሊያድናችሁ
የዓለም ኃጢአተኞች እንደኔ ያላችሁ
ኢየሱስ ያድናል በእርሱ ተስፋ አላችሁ
ኢየሱስ ሰርቶታል በእርሱ ተስፋ አላችሁ
ኢየሱስ ሆኖታል በእርሱ ተስፋ አላችሁ
~ዘሪቱ ከበደ~
በዚህ "ጸጋው" የተሰኘ ዝማሬዋ ላይ የጻፍኩትን የሶስት ክፍል ነገረ መለኮታዊ አስተንትኖት ያላነበባችሁ እነኚህን መስፈንጠሪያዎች ተጭናችሁ ማንበብ ትችላላችሁ፤
ክፍል 1፦ https://t.me/Romans148/262
ክፍል 2፦ https://t.me/Romans148/269
ክፍል 3፦ https://t.me/Romans148/296

❤15👍5🥰1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የተሐድሶ ጸሎት ("እጅህ ይዳሰን")
በምዕራቧ ቤተክርስቲያን የዘመን አቆጣጠር መሠረት የትላንቱ እሁድ በዓለ ጰራቅሊጦስ (Pentecost Sunday) ነው። በዚህ ቀን ከጌታችን እርገት በኋላ መንፈስ ቅዱስ በሐዋርያት ሥራ 2 ላይ መውረዱና የቤተክርስቲያን መወለድ ይታሰባል።
በእኛ ቤተክርስቲያንም ይህን ቀን በማሰብ፤ ነገር ግን እንዳለፈ ታሪክ ብቻ ሳይሆን እግዚአብሔር በመንፈሱ ዛሬም ለቃሉና ለጸሎት እንዲያበረታን፣ ከሱ ጋር ያለንን ህብረት እንዲያድስና ለወንጌል እንዲያጀግነን በመጸለይና ቃሉን በመማር አሳልፈናል። በዚህ ፕሮግራም ላይ ስጸልይ በተቀረጸው፣ በዚህ ቪዴኦ አብራችሁኝ እንድተጸልዩ እጋብዛችኋለሁ።
ይህን ቀን ስናስብ መንፈስ ቅዱስ ከለብታ ሕይወት (lukewarmness) አላቆ በክርስቶስ ፍቅር ይሙላን፣እንደገና ያድሰን ያበርታንም።
የቤተክርስቲያናችንን live ፕሮግራሞች ለመከታተል የFacebook ገጻችንን Christ Memorial Mekane Yesus Church መጎብኘት ትችላላችሁ።

❤19😭4🙏2👎1
አንድን ፡ ነገር ፡ ሽቼ ፡ ደጅ ፡ ጠናለሁኝ
ፈቃድህ ፡ ከሆነ ፡ በዓይንህ ፡ ተመልከተኝ
ያቺን ፡ ብሩክ ፡ እጅህን ፡ ዘርጋብኝ
አዝ፦ እንባዬን ፡ አይተህ ፡ ጌታ
ለቅሶዬን ፡ ሰምተህ ፡ ጌታ
መሻቴን ፡ ስጠኝና ፡ ኢየሱስ ፡ ላመስግንህ (፪x)
አንተን ፡ ተስፋ ፡ አድርጌ ፡ በቃልህ ፡ ፀንቼ
መልሴን ፡ አጠብቃለሁ ፡ በተመስጦ ፡ ሆኜ
ታማኝነትህን ፡ ተማምኜ
አዝ፦ እንባዬን ፡ አይተህ ፡ ጌታ
ለቅሶዬን ፡ ሰምተህ ፡ ጌታ
መሻቴን ፡ ስጠኝና ፡ ኢየሱስ ፡ ላመስግንህ (፪x)
በጐ ፡ ስጦታና ፡ ፍፁም ፡ በረከት ፡ ሁሉ
ከብርሃናት ፡ አባት ፡ ከላይ ፡ ይወርዳሉ
ከዙፋንህ ፡ ይንቆረቆራሉ
አዝ፦ እንባዬን ፡ አይተህ ፡ ጌታ
ለቅሶዬን ፡ ሰምተህ ፡ ጌታ
መሻቴን ፡ ስጠኝና ፡ ኢየሱስ ፡ ላመስግንህ (፪x)
መራራነቴ ፡ ያብቃ ፡ እሾህነቴም ፡ ያብቃ
መፈራረሴም ፡ ያብቃ ፡ በአንተ ፡ ፀጋ ፡ ልገንባ
ጐስቋላነቴን ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ እንካ
አዝ፦ እንባዬን ፡ አይተህ ፡ ጌታ
ለቅሶዬን ፡ ሰምተህ ፡ ጌታ
መሻቴን ፡ ስጠኝና ፡ ኢየሱስ ፡ ላመስግንህ (፪x)
ተስፋዬ ጋቢሶ
https://youtu.be/YuC7KMJwmnQ?si=GydBt721tnV8GOUM

እንባዬን ፡ አይተህ ፡ ጌታ በፓስተር ተስፋዬ ጋቢሶ Enbayen Ayteh Geta by Pastor Tesfaye Gabbiso Vol 1 Track 4
አንድን ፡ ነገር ፡ ሽቼ ፡ ደጅ ፡ ጠናለሁኝ
ፈቃድህ ፡ ከሆነ ፡ በዓይንህ ፡ ተመልከተኝ
ያቺን ፡ ብሩክ ፡ እጅህን ፡ ዘርጋብኝ
እንባዬን ፡ አይተህ ፡ ጌታ
ለቅሶዬን ፡ ሰምተህ ፡ ጌታ
መሻቴን ፡ ስጠኝና ፡ ኢየሱስ ፡ ላመስግንህ (፪x)
አንተን ፡ ተስፋ ፡ አድርጌ ፡ በቃልህ ፡ ፀንቼ
መልሴን ፡ አጠብቃለሁ ፡ በተመስጦ ፡ ሆኜ
ታማኝነትህን ፡ ተማምኜ
እንባዬን ፡ አይተህ ፡ ጌታ
ለቅሶዬን ፡ ሰምተህ…
ፈቃድህ ፡ ከሆነ ፡ በዓይንህ ፡ ተመልከተኝ
ያቺን ፡ ብሩክ ፡ እጅህን ፡ ዘርጋብኝ
እንባዬን ፡ አይተህ ፡ ጌታ
ለቅሶዬን ፡ ሰምተህ ፡ ጌታ
መሻቴን ፡ ስጠኝና ፡ ኢየሱስ ፡ ላመስግንህ (፪x)
አንተን ፡ ተስፋ ፡ አድርጌ ፡ በቃልህ ፡ ፀንቼ
መልሴን ፡ አጠብቃለሁ ፡ በተመስጦ ፡ ሆኜ
ታማኝነትህን ፡ ተማምኜ
እንባዬን ፡ አይተህ ፡ ጌታ
ለቅሶዬን ፡ ሰምተህ…
❤13
በዚች ፡ ምድር ፡ ላይ ፡ ብርቱ ፡ ሰልፍ ፡ አለብኝ
አኔ ፡ ዝም ፡ አላለሁ ፡ አንተ ፡ ተዋጋልኝ
አንተን ፡ ያሰለፉ ፡ ስልፉ ፡ ሰምሮላቸው
አይቼ ፡ ተምሬያለሁ ፡ ከድል ፡ ዝማሬያቸው
አዝ፦ ዝም ፡ ብዬ ፡ አቆማለሁ
ሰልፉን ፡ ለአንተ ፡ ለቃለሁ
በእምነት ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ አያለሁ ፡ ጌታ ፡ ሆይ
ድልህን ፡ አጠብቃለሁ (፪x)
ሰልፉ ፡ የእኔ ፡ መስሎኝ ፡ አረታለሁ ፡ ብዬ
በሥጋዬ ፡ ስታገል ፡ ተዝለፍልፌ ፡ ዝዬ
መረታቴ ፡ ነው ፡ እኮ ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታዬ
ኧረ ፡ ቶሎ ፡ ናልኝ ፡ አይብዛ ፡ መከራዬ
አዝ፦ ዝም ፡ ብዬ ፡ አቆማለሁ
ሰልፉን ፡ ለአንተ ፡ ለቃለሁ
በእምነት ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ አያለሁ ፡ ጌታ ፡ ሆይ
ድልህን ፡ አጠብቃለሁ (፪x)
የእሳት ፡ ሰረገላው ፡ መለኮታዊው ፡ ጦር
የድምፅህ ፡ ነጐድጓድ ፡ ጠላት ፡ የሚያሸብር
ይምጣ ፡ ይዋጋልኝ ፡ እኔ ፡ ኃይል ፡ የለኝም
አሁን ፡ አውቄያለሁ ፡ ሰልፉ ፡ የእኔ ፡ አይደለም
አዝ፦ ዝም ፡ ብዬ ፡ አቆማለሁ
ሰልፉን ፡ ለአንተ ፡ ለቃለሁ
በእምነት ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ አያለሁ ፡ ጌታ ፡ ሆይ
ድልህን ፡ አጠብቃለሁ (፪x)
ተስፋዬ ጋቢሶ
https://youtu.be/TRMAcznCzqE?si=Lp_DCgaiArHvygAh

ዝም ፡ ብዬ በመጋቢ ተስፋዬ ጋቢሶ Zim Beye by Pastor Tesfaye Gabiso Album 1 Vol 9
በዚች ፡ ምድር ፡ ላይ ፡ ብርቱ ፡ ሰልፍ ፡ አለብኝ
እኔ ፡ ዝም ፡ አላለሁ ፡ አንተ ፡ ተዋጋልኝ
አንተን ፡ ያሰለፉ ፡ ሰልፉ ፡ ሰምሮላቸው
አይቼ ፡ ተምሬያለሁ ፡ ከድል ፡ ዝማሬያቸው
ዝም ፡ ብዬ ፡ አቆማለሁ
ሰልፉን ፡ ለአንተ ፡ እለቃለሁ
በእምነት ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ አያለሁ ፡ ጌታ ፡ ሆይ
ድልህን ፡ እጠብቃለሁ (፪x)
ሰልፉ ፡ የእኔ ፡ መስሎኝ ፡ እረታለሁ ፡ ብዬ…
እኔ ፡ ዝም ፡ አላለሁ ፡ አንተ ፡ ተዋጋልኝ
አንተን ፡ ያሰለፉ ፡ ሰልፉ ፡ ሰምሮላቸው
አይቼ ፡ ተምሬያለሁ ፡ ከድል ፡ ዝማሬያቸው
ዝም ፡ ብዬ ፡ አቆማለሁ
ሰልፉን ፡ ለአንተ ፡ እለቃለሁ
በእምነት ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ አያለሁ ፡ ጌታ ፡ ሆይ
ድልህን ፡ እጠብቃለሁ (፪x)
ሰልፉ ፡ የእኔ ፡ መስሎኝ ፡ እረታለሁ ፡ ብዬ…
❤9
Ἔστιν δὲ πίστις ἐλπιζομένων ὑπόστασις, πραγμάτων ἔλεγχος οὐ βλεπομένων."
~Heb 11:1~
የኔ ትርጉም፦
ነገር ግን እምነት ተስፋ ስለሚደረጉት ነገሮች አካል/እውነታ/ሕላዌ፣ ስለማይታዩት ነገሮች ማረጋገጫ ነው።
" አካል/እውነታ/ሕላዌ" ብዬ በአማራጭ ያስቀመጥኳቸው ቃላት በሙሉ የግሪኩን ὑπόστασις/ሂፖስታሲስ/ የሚለውን ቃል ለመተርጐም ነው። ቃሉ በዕብ 11፥3 "ባህርይ" የብሎ ተተርጉሟል። ምንም እንኳን ውዝግብ ለማጥራትና ከ4ኛው ክፍለ ዘመን በኋላ ከስላሴ አስተምህሮ ጋር በተያያዘ "አካል/person/" ተብሎ በዋናነት ቢተረጎምም፤ በመጽሐፍ ቅዱሳችን "ባህርይን"(essence) ለማመልከት አገልግሎት ላይ ውሏል በዕብ 11፥3 እንደምናየው።
በስብከቱ ላይ Piper ለማብራራት እንደሞከረው፣ የቃሉን ትርጓሜ በዚህ መንገድ መረዳት ለእምነት በምንሰጠው ትርጓሜና ጥቅሱን የምንተረጎምበትን መንገድ ይወስናል።
በተለይ በምዕራፍ 1፥3 ዓይን ቃሉን ከተረዳነው፣ በዚህ ክፍል የዕብራውያን ጸሐፊ እምነትን ሊመጣ ያለ ተስፋ አሁን ላይ በተወሰነ መልኩ እውነታ ሲሆንና አሁን ማየትና መረዳት እንደሆነ ነው እየነገረን ያለው። እምነት እንዲሁ ጌታ ሞቶ በመነሳቱ ላይ ያለንን መስማማት መግለጽ አይደለም፣ እሱን reality መጨበጥ ነው። ጌታ በሰራው ስራ ምክንያት የተሰጠንን የዘላለም ተስፋ አሁን በተወሰነ መልክ እውነታ ሆኖልን መያዝና ማየት ማለት ነው።
እንዲህ ባለ እምነት ነው ሙሴ በኃጢአት የሚገኘውኝ ደስታ የናቀው። ምክንያቱም መሲሁን ትኩር ብሎ አይቶታል፣ ያን ተስፋ ጨብጦታል።
ጳውሎስ እንዲህ ያለውን እምነት ሲገልጥ "ክርስቶስም በእምነት በልባችሁ እንዲኖር" ይላል። ይህ ዓይነት እምነት ምኞት/wish አይደለም። የነገው ተስፋ reality በሆነ form አሁን ላይ present ሲሆንልን ማለት ነው። በዕብ 12፥1-4 ላይ ጌታችን ደግሞ ይህን እምነት በደስታ መልክ ነው experience ያደረገው።
ይህን ስብከት ስሰማ እየጸለይኩ የነበረው ለናንተም ጸሎቴ ነው። በክርስቶስ የተደረገልን እውነትና ልናገኘው ያለነው ተስፋ እንዲሁ መረጃ ብቻ ሳይሆን፣ እውነታ እንዲሆንልን፣ እንድንጨብጠው እና ልባችን ፈጽሞ እርግጠኛ እንዲሆንበት እግዚአብሔር በመንፈሱ ይርዳን።
@Romans148
https://www.desiringgod.org/messages/true-faith-tastes-future-joy#full-audio

Desiring God
True Faith Tastes Future Joy
Jesus endured for the joy set before him. Moses obeyed, expecting the Messiah. The early church suffered for a better reward. This is faith.
❤10🔥1👏1
Check this out if you are interested: phd in Theological Education.
https://seteca.edu/welcome-to-seteca/phd-in-global-theological-education/
https://seteca.edu/welcome-to-seteca/phd-in-global-theological-education/
SETECA
PhD in Global Theological Education
SETECA offers over a dozen programs on different levels and in different formats. All the courses are taught in Spanish.
❤3
የገደለን እጅ ሕያዋን ያደርገናል
የምወደው መምህሬ Professor Robert Kolb ብዙ ጊዜ "እግዚአብሔር በጥምቀት ይገለናል እንዲሁም ህያው ያደርገናል። ይኸውም የየዕለት የክርስትና የሕይወት ዘይቤ ነው እንጂ አንድ ጊዜ ተጸፍሞ የሚያልቅ አይደለም።" ብሎ ይናገራል።
እግዚአብሔር እየገደለ ሕያዋን ያደርገናል ሲል፣ የአሮጌውን ሰው ሞትና የአዲሱን ሕያው መሆን ለማመልከት ነው።
ቅድና ማለት ይህ ነው፣ ዕለት ዕለት እየሞቱ መነሳት ነው። ቅዱስ ጳውሎስ ይህን ሲገልጥ እንዲህ ይላል፣ "ፊተኛ ኑሮአችሁን እያሰባችሁ እንደሚያታልል ምኞት የሚጠፋውን አሮጌውን ሰው አስወግዱ፥በአእምሮአችሁም መንፈስ ታደሱ፥ለእውነትም በሚሆኑ ጽድቅና ቅድስና እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠረውን አዲሱን ሰው ልበሱ።" (ኤፌ 4፥22-24)
ምንም እንኳን አርጌውን አስወግደን አዲሱን መልበስ የእኛ ድርሻ አድርጎ ጳውሎስ በዚህ ክፍል ቢያዘንም፣ ነገር ግን ይህን የምናደርገው በመንፈስ ቅዱስ ኃይል እንደሆነ በሮሜ 8፥13 ላይ ይነግረናል፣ "እንደ ሥጋ ፈቃድ ብትኖሩ ትሞቱ ዘንድ አላችሁና፤ በመንፈስ ግን የሰውነትን ሥራ ብትገድሉ በሕይወት ትኖራላችሁ።"
ታዲያ ከሁለቱ ክፍል እንደምንገነዘበው አሮጌውን የማስወገድ ሥራ አንድም የመንፈስ ቅዱስ ሁለትም የእኛነው። ይህ ማለት መንፈስ ቅዱስ እኛ አሮጌውን ሰው ሳንገነዘብ በምስጢር የማስወገድ ሥራ አይሰራም ማለት ነው። ይልቅ ያን የከረፋ ማንነት በእግዚአብሔር ቃል አማካኝነት ያሳየናል፣ መወገድ እንዳለበት ያሳምነናል፣ ከዛም ለማስወደገድ አቅም ይሆነናል።
አሮጌውን ማንነታችንን ሲያሳየንና ምን ያህል በእግዚአብሔር ላይ እንዳመጽን ሲያስገነዝበን በጣም painful ነው። ምን ያህል የከረፋን እንደሆንን ስናይ በኃጢአታችን ክብደት ልባችን ይሰበራል። መዝሙረኛው ይህንን ህመም ሲገልጥ፣ "ኃጢአቴ በራሴ ላይ ከፍ ከፍ ብሎአልና፥ እንደ ከባድ ሸክምም በላዬ ከብዶአልና" ይላል (መዝ 38፥4)።
ይህን የእግዚአብሔር ሥራ በነገረ መለኮት ቋንቋ alien work of God (የእግዚአብሔር ባዕድ አሰራር) ብለን እንጠራዋለን። በዚህ አሰራሩ፣ ጌታ በመፈሱና በቃሉ አማካኝነት ስብርብራችንን ያወጣል፣ ያደቀናል፣ ይገለናልም።
ነገር ግን ይህ alien work ወደ proper work of God (እኔ ይህን የእግዚአብሔር ዋና ሥራ/አሠራር ብዬ ልተርጉመው) ሊመራን፤ ይኸውም ወደ ጸጋ ዙፋኑ ሊያስጠጋንና ሕያዋን እንዲያደርገን እንጂ ለኩነኔ አይደለም። መሰበራችንን ያየን እኛ፣ አቅመ ቢስነታችንን የተገነዘብን እኛ፣ አዳኛችንን ፍለጋ ዘወር እንድንል በመንፈሱ በውስጣችን ይሰራል። የገደለን እሱ መልሶ ሕያዋን ያደርገናል፣ በጸጋውም ኃይል ያቆመናል። ያለቀስን እኛን ደግሞ በምህረቱ ያስቀናል። ስንኩልነታችን እርምጃችንን የገታብንን እኛን ደግሞ በመንፈሱ ኃይል ያስኬደናል።
ስለዚህ ደክማችሁ፣ ኃጢአታችሁ በፊታችሁ ተደቅኖ፣ የጎበጣችሁ ወዳጆቼ፣ አይዟችሁ። የሰበራችሁ፣ እሱ ይጠግናችኋል። ስለናንተ በመስቀል ላይ ወደ ዋለውና ኃጢአታችሁን ወደ ተሸከመው ኢየሱስ ተመልከቱ። በእርሱ ውስጥ ተደብቃችሁ የእግዚአብሔር ቁጣ አልፏችኋል። እሱጋ ተስፋ አለ፣ እሱጋ ይቅርታ አለ፣ እሱጋ መቆም አለ።
"እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።" (የማቴዎስ ወንጌል 11:28)
በርቱልኝ!

❤14🥰1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
This song made my morning.
Let our eyes be fixed on You, Jesus.
Let our feet learn to follow Your steps, Jesus.
Let our hearts be set on You, Jesus.
Let our ears learn to listen to Your word, Jesus.
Let our numbered days be spent for You, Jesus.
Let our whole being be devoted to You, Jesus.
Let us die so that You may live in us, Jesus.

ቤተክርስቲያን ሂዱ የእግዚአብሔርንም በረከት ተካፈሉ
ዛሬ ማር 11:15 - 19 ነበር ሳሰላስልና ስጸልይ የነበረው። ክፍሉ የሚተርክልን ጌታችን በቤተ-መቅደስ የሚደረገውን ግብይት የሚያጸዳበትን ኩነት ነው።
ጌታችን ለምን ማጽዳት እንዳስፈለገው ሲያስተምራቸው እንዲህ በማለት ነው፣ "ቤቴ ለአሕዛብ ሁሉ የጸሎት ቤት ትባላለች ተብሎ የተጻፈ አይደለምን?" (15፥17)
ከዚህ የምንረዳው፤
1. የእግዚአብሔር ቤት የጸሎት ቤት ነው ማለትም ቤቱ በዋናነት እግዚአብሔር የሕዝቡን ጸሎት የሚሰማበትና ጸሎታቸውን በመመለስ ሕዝቡን የሚባርክበት ቦታ ነው።
2. የእግዚአብሔር ቤት የሕዝብ ሁሉ ነው። እግዚአብሔር ቤት ውስጥ ሊገኝ የማይገባ ሰው የለም።
የእግዚአብሔር ቤት የቅዱሳን ሕብረት ነው፣ በአዲስ ኪዳን። ስለዚህ በእግዚአብሔር ቤት ስትገኙ፣ አንድም፣ በክርስቶስ በተሰራላችሁ ስራ የመግባት መብት ሙሉ በሙሉ እንዳላችሁ በማመን ይሁን።
ሁለትም፣ የመገኘታችሁ ዋነኛ ምክንያት ለእርሱ አምልኮ ለማቅረብ ብቻ እንደሆነ አታስቡ። ይልቅ እግዚአብሔር የሚሰበስባችሁ በቃሉና በቅዱስ ምስጢራቱ በረከቱን ለእናንተ ለማደልና እምነታችሁን ለማበርታት እንደሆነ እወቁ። የእናንተ አምልኮ ከሱ ለሚፈሰው ታላቅ በረከት ምላሽ ነው።
ወደ ጌታ ቤት ሂዱ፣ በረከቱንም ተካፈሉ፤ ለባረካችሁ ለሱ ደግሞ የምስጋና እና የአምልኮን ምላሽ ስጡ።
መልካም የጌታ ቀን!

❤16
ቀናችሁን በዚህ መዝሙር ተባርካችሁ ጀምሩ።
መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ፍቅር በልባችሁ ውስ እያፈሰሰ የምትውሉበት ቀን ያርግላችሁ።
'በተሰጠንም በመንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን ስለ ፈሰሰ ተስፋ አያሳፍርም። '
ወደ ሮም ሰዎች 5:5
መልካም ቀን!
https://www.youtube.com/watch?v=mers6q5LlU4
መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ፍቅር በልባችሁ ውስ እያፈሰሰ የምትውሉበት ቀን ያርግላችሁ።
'በተሰጠንም በመንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን ስለ ፈሰሰ ተስፋ አያሳፍርም። '
ወደ ሮም ሰዎች 5:5
መልካም ቀን!
https://www.youtube.com/watch?v=mers6q5LlU4
YouTube
Daniel Amdemikael "ክብርህን ላውራው" lyrics video
Enjoy the videos and music you love, upload original content, and share it all with friends, family, and the world on YouTube.
❤4
ስንት ጊዜ ራሴን ከራሴ አዳንከኝ?! እንኳንም አጥብቀህ ያዝከኝ፣ ለፈቃዴ እንዳልኖር። እንዲያ ባይሆንማ ኖሮ፣ ሕይወቴን ባጠፋሁት፣ ወድቄም በተገኘሁ ነበር።
ምስጋና ንግባው የያዘኝ ታማኝ እጅህ።
[28] እኔም የዘላለም ሕይወትን እሰጣቸዋለሁ፥ ለዘላለምም አይጠፉም፥ ከእጄም ማንም አይነጥቃቸውም። [29] የሰጠኝ አባቴ ከሁሉ ይበልጣል፥ ከአባቴም እጅ ሊነጥቃቸው ማንም አይችልም። [30] እኔና አብ አንድ ነን።”
- የዮሐንስ ወንጌል 10:28-30

"(አቤቱ)፣ ለራስህ ፈጥረኸናልና በአንተ አስኪያርፍ ድረስ ልባችን እረፍተ-ቢስ ነው።"
~ አውግስጢኖስ
በእግዚአብሔር ያልረካች ነፍስ፣ በገንዘብ፣ በዝና፣ በፍቅር ግንኙነት፣ በክብርና በየትኛውም በዓለም በሚገኝ ነገር ልትረካ አትችልም። እግዚአብሔር ለራሱ መኖሪያ ያበጀውን የነፍስ ቀዳዳ ምንም ነገር ገብቶ ሊሞላው አይችልም። እነዚህ ነገሮች የእግዚአብሔርን ቦታ ሊሞሉ ሲሞክሩ "ጣዖታት" ይሆናሉ። ነገር ግን ቅዱስ ጳውሎስ እንደሚነግረን "ጣዖት ሁሉ በዓለም ከንቱ እንደ ሆነ ከአንዱም በቀር ማንም አምላክ እንደሌለ እናውቃለን።" (1 ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 8:4 )
ስለዚህ ወደ እውነተኛው የነፍሳችሁ እረኛ ተመለሱ (1 ጴጥ 2፥25)። እርሱን የበላ ለዘለዓለም አይራብም (ዮሐ 6፥35)፣ እርሱን የጠጣ ለዘለዓለም አይጠማም ይልቅ የሕይወት ውሃ ወንዝ ከሆዱ ይፈልቃል እንጂ (ዮሐ 4፥14)።
"... ኢየሱስ ቆሞ፦ 'ማንም የተጠማ ቢኖር ወደ እኔ ይመጣና ይጠጣ። በእኔ የሚያምን መጽሐፍ እንዳለ፥ የሕይወት ውኃ ወንዝ ከሆዱ ይፈልቃል' ብሎ ጮኸ።"
~የዮሐንስ ወንጌል 7:37ለ-38

❤15🔥1🥰1🙏1
Bekagn Yemalilew
Aster Abebe
ጥቂት ፡ አንተን ፡ ቀምሶ ፡ እንደ ፡ ጠገበ ፡ ሰው
መሆን ፡ የጤና ፡ አይደለም ፡ ረሃቤን ፡ ፈውሰው
ዕለት ፡ ዕለት ፡ ባዶ ፡ ትሁንና ፡ ነፍሴ
በመገኘትህ ፡ ውስጥ ፡ ይረስርስ ፡ መንፈሴ...
ናና ፡ እስኪ ፡ አጠጣኝ
ናና ፡ እስኪ ፡ አጉርሰኝ
የእጅህን ፡ ሳይሆን ፡ ክብር ፡ መልክህን
የምድሩን ፡ ሳይሆን ፡ ሕልውናህን
ሌላውን ፡ ሳይሆን ፡ አንተው ፡ እራስህን
@Romans148
መሆን ፡ የጤና ፡ አይደለም ፡ ረሃቤን ፡ ፈውሰው
ዕለት ፡ ዕለት ፡ ባዶ ፡ ትሁንና ፡ ነፍሴ
በመገኘትህ ፡ ውስጥ ፡ ይረስርስ ፡ መንፈሴ...
ናና ፡ እስኪ ፡ አጠጣኝ
ናና ፡ እስኪ ፡ አጉርሰኝ
የእጅህን ፡ ሳይሆን ፡ ክብር ፡ መልክህን
የምድሩን ፡ ሳይሆን ፡ ሕልውናህን
ሌላውን ፡ ሳይሆን ፡ አንተው ፡ እራስህን
@Romans148
❤15🤔1