"እግዚአብሔር ያደረገውን አየ፥እነሆም እጅግ መልካም ነበር።ማታም ሆነ ጧትም ሆነ ስድስተኛ ቀን"(ዘ.ፍ 1፥31)
✍🏽.ከንቱ ውዳሴ አይሁንብኝና አለማወቃቸውን የማያውቁ ሙህር ነኝ ባዮች የሥነ-ፈለክ ዕውቀት ምንጭ አንድና አንድ ነጮች መስለዋቸው ይሄን ዕውቀት ለማግኘት በተለያዩ ማህበራዊ ድህረ ገፆች መንከራተታቸው አይቀሬ ነው።መጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ እና ዶክተር ጌትነት ፈለቀ ደግሞ ቅዱሳት መጽሓፍትን እና የብራና መጽሓፍትን መርምረው ተዝቆ የማያልቀውን የኢትዮጵያውን ዕውቀት ለማቋደስ ሀ ብለው ከተነሱ ሰነባብተዋል በዚህም ዙሪያ ከፃፏቸው መጽሓፍት አንድሮ ሜዳ 1 እና 2 ተጠቃሽ ናቸው።ዛሬ ደግሞ የክርስቶስ መልካም ፈቃድ ሆኖ አንብበው ተብዬ ከተሰጠውት መጽሓፍ አንዱ የሆነውን በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ የተፃፈውን ማዛሮትን ሳነብ የተሰማኝን ነገር ለማጋራት ወሰንኹ።
✍🏽.ልቤ የስነ-ፈለክ ጥማቱን ለማርካት እንዲሁም የምድራዊያኑን እና የሰማይ አካላትን ምስጢር የስነ-ፈለክ ርሀቡን ለማስታገስ ጉዞውን ጀመረ።የመጽሓፉን ሽፋን ገልጬ ስመለከት የሆነ ንጉሥ በእስ ትርሳብ(የሰማይ መመልከቻ) የሰማይ አካላት እየተመለከቱ የሚያሳይ በብራና የተከተበ ስእል አየኹ ልቤም የአባቶቼን ዕውቀት እያደነቀ ወደ ዋናው የጥበብ ማዕድ ሊቋደስ ገባ።ንባቤንም ስጀምር በመጀሪያው ምዕራፍ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ምሣሌ የሆነችውን ፀሐይን አገኘኹ በዚህም የፀሐይን ትልቀት፣ብርሃን፣ግርዶሽ እና ምሣሌ ከመጽሐፍ ቅዱስ እና ከሳይንስ አንፃር ዳሰስኹ በመቀጠልም የጥበብ ውቅያኖስን እየቀዘፍኹ ወደ ቀጣዩ ምዕራፍ ወደ ከዋክብት አመራኹ የከዋክብትንም ድንቅ አፈጣጠርና ባህሪይ አየኹ በዚህም የክርስቶስን ጥበብና ስራ ምን ያህል ረቂቅ እንደሆነ ከተመለከትኹ በኋላ እንደ ጅራታማ ኮከብ(ዘቦ ዘነብ) ተምዘግዝጌ ጨረቃ ላይ ደረስኹ በዚህ ምዕራፍም የጨረቃን ምሣሌ፣ብርሃንና ሌሎች ነገሮችን ዳሰስኹ ።ፀሐይን በክርስቶስ ጨረቃን በፍጥረት መሰልኹ ፀሐይ ለጨረቃ ብርሃን እንደምትሰጥ ክርስቶስም ለፍጡሩ ብርሃን ይሰጣል ብዬ ጉዞዬን ቀጠልኹ።ፀሐይ፣ከዋክብት ፣ጨረቃን ከዳሰስኹ በኋላ አየራትን፣ነፋሳትንና ደመናትን በጥልቀት ዳሰስኹ በጥበብ ባሕር ዋኘው ሰማዬ ሰማያትን ፈለከ ፈለካትን በምናቤ ቃኘኹ በሰማዩ አካላት ላይ ያለው የእግዚአብሔር ጥበብ አላልቅ ቢለኝ በዓይነ ሕሊና ተዋነይን እያሰብኹ በደመና ተጭኜ ወደ ምድራዊው ፍጥረት መጣኹ በዚህም የዕፅዋትን፣የአዝዕርትንና የእንስሳትን ምስጢር ቃኘው። ለካስመዝሙረኛው ዳዊትም ወዶም አየል "ሰማያት ይነግራ ስብሐተ እግዚአብሔ"(መዝ 31፥1) ያለው።
✝.ክርስቶስ ላያስፈፅም አያስጀምርምና እኔም በዚህ ድንቅ መጽሐፍ የነበረኝን ጉዞ በዚህ ገታኹ ነገር ግን በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ እና በሌሎች ሰዎች መጽሐፍ ጉዞዬን መቀጠሌ አይቀሬ ነው።
✍🏽.አደራ ይሄን መጽሐፍ ገዝታችኹ አንብቡት ዋጋ 200 ነው።
✍🏽.ተፃፈ በዮሐንስ ኃ/ማርያም 18/07/2014 ዓ.ም
✝ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን።✝

"መጽሐፈ ሰዓታት፥ ንባቡና ትርጓሜው"
~•••★•••~~
ይኽ መጽሐፍ በውስጡ 19 ምዕራፎች 478 ገጾች ያሉት ሲኾን በእያንዳንዱ ምዕራፍ ደግሞ፦
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ
- ይትባረክ እግዚአብሔር
- ግነዩ ለእግዚአብሔር
- እዌድሰኪ ኦ ድንግል
-ዘይክል ኩሎ
-ንዒ ኀቤየ ኦ ድንግል
-ንሴብሖ ለእግዚአብሔር
- ገነይነ ለኪ
- የምንባብ ክፍል ከነመርገፉ
- ኩሎሙ ዘዘወትር
- ኩሎሙ ዘእግዝእትነ ማርያም
- ኩሎሙ ዘኪዳነ ምሕረት ወዘፍልሰታ
- ኩሎሙ ዘቁስቋም
- ኩሎሙ ዘመላእክት
- ዘቅድስት ሥላሴ
- ኩሎሙ ዘበዓለ እግዚአብሔር
- ሞገስነ ወክብርነ
- ሚካኤል ሊቀ መላእክት
- ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ
- ሰአሊ ለነ ማርያም
- ይዌድስዋ መላእክት
- እሴብሕ ጸጋኪ ዘዘወትር
- እሴብሕ ጸጋኪ ዘቁስቋም
- እሴብሕ ጸጋኪ ዘሐዋርያት ወሰማዕታት ወጻድቃን
- ዘደብረ ዘይት ወዘጷጉሜን
- እሴብሕ ጸጋኪ ዘዘመነ ጽጌ
- እሴብሕ ጸጋከ ዘመስቀል ወዘመድኀኔ ዓለም፤ ናቸው፡፡
👉 ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ የደረሱትን የነዚኽን ኹሉ ምስጢር በሕይወተ ሥጋ ሳሉ አለማወቅ ስንፍና ነው።
👉 መጽሐፉ በሁሉም የመጻሕፍት መሸጫ ይገኛል። ወይም +251913422447 ደውለው ያገኙታል።
(መጋቤ ሐዲስ ዶ/ር ሮዳስ ታደሰ) 2014 ዓ/ም፡፡
★★★

Watch "ዘይት የምታፈሰው የእመቤታችን ሥዕል በእንጦጦ ኪዳነ ምሕረት" on YouTube
https://youtu.be/fCWoFdw9qWI
https://youtu.be/fCWoFdw9qWI
YouTube
ዘይት የምታፈሰው የእመቤታችን ሥዕል በእንጦጦ ኪዳነ ምሕረት
መጋቢት 24 እንጦጦ ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት
መዝሙረ፡ዳዊት ( PDFDrive ).pdf
22.4 MB
Emailing መዝሙረ፡ዳዊት ( PDFDrive ).pdf
👉 የእመቤታችን የሥዕሏ ክብርና ተአምር ቅዳሜ መጋቢት 24 በሠርክ ከ11 ሰዓት ጀምሮ በእንጦጦ ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት ገዳም በታላቅ ጉባኤ ይታሰባል።
👉 በዕለቱ በፓወር ፓይንት ስለ ቅዱሳት ሥዕላት ክብር መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርት ይሰጣል። በበራሪ ጽሑፍም ትምህርቱ በነጻ ለሁሉ ይሰጣል።
👉 በእመቤታችን ሥዕል ተማፅነው ዐይናቸው የበራላቸውና ተአምር የተደረገላቸው ምስክርነት ይሰጣሉ።
👉 በግብጽ ፓርት ሳይድ ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ከምትገኘው ከእመቤታችን ሥዕል ላይ ያለማቋረጥ የሚፈሰው ሕሙማንን የሚፈውሰው የተቀደሰ ዘይት (ቅብዕ ቅዱስ) በዕለቱ በጉባኤው ለመጡ በገዳሙ ይሰጣል።
👉 የእመቤታችን በረከት የሚገኝበት ታላቅ ጉባኤ በመኾኑ በዕለቱ ኹላችንም ተገኝተን የዚህ ሰማያዊ በረከት ተሳታፊ እንድንኾን ገዳሙ መልእክቱን ያስተላልፋል።
"ሰላም ለሥዕልኪ እንተ ሠዓላ በእዱ
ሉቃስ ጠቢብ እምወንጌላውያን አሐዱ
አመ ተቀብዑ ማርያም እምሐፈ ሥዕልኪ ቅብዐ ናርዱ
በሕማም እኩይ እለ ደወዩ ወውኅዱ
ጽዑራነ ዓለም ጥዕዩ ወጥቀ ፈድፈዱ"
( ከወንጌላውያን አንዱ ጠቢብ ሉቃስ በእጁ ለሣላት ሥዕልሽ ሰላምታ ይገባል። ማርያም ሆይ የናርዶስ ቅብዐት ከኾነው ከሥዕልሽ ወዝ በተቀቡ ጊዜ በክፉ ሕመም የታመሙና የተባበሩ በዓለም የሚጨነቁ ዳኑ፤ በእጅጉ በዙ) (መልክአ ሥዕል)

Watch "ገብር ሔር የዐቢይ ጾም ስድስተኛ ሳምንት በሊቀ ሊቃውንት አባ ታፈሰ ደሳለኝ" on YouTube
https://youtu.be/aDNysL08Sa4
https://youtu.be/aDNysL08Sa4
YouTube
ገብር ሔር የዐቢይ ጾም ስድስተኛ ሳምንት በሊቀ ሊቃውንት አባ ታፈሰ ደሳለኝ
ማቴዎስ 25
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁴ ወደ ሌላ አገር የሚሄድ ሰው ባሮቹን ጠርቶ ያለውን ገንዘብ እንደ ሰጣቸው እንዲሁ ይሆናልና፤
¹⁵ ለእያንዳንዱ እንደ ዓቅሙ፥ ለአንዱ አምስት መክሊት ለአንዱ ሁለት ለአንዱም አንድ ሰጠና ወደ ሌላ አገር ወዲያው ሄደ።

Watch "የተቀደሰ ዘይትን የሚያፈሱ ቅዱሳት ሥዕላት" on YouTube
https://youtu.be/LMT8zTDSYyg
https://youtu.be/LMT8zTDSYyg
YouTube
የተቀደሰ ዘይትን የሚያፈሱ ቅዱሳት ሥዕላት
Watch ""በእግዚአብሔር ቤት በአደባባዩ እንገናኝ" በሊቀ ማእምራን ዐባይ አጥሌ" on YouTube
https://youtu.be/gcap39KIfD8
https://youtu.be/gcap39KIfD8
YouTube
"በእግዚአብሔር ቤት በአደባባዩ እንገናኝ" በሊቀ ማእምራን ዐባይ አጥሌ
ድንቅ ስብከት
[የመጋቢት 24 የእንጦጦ ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት አስደናቂ ጉባኤና የቀጣይ መርሐ ግብር ማስተካካያ]
✍️ ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
💥 መጋቢት 24 በእንጦጦ ሐመረ ኖህ ኪዳነ ምሕረት ገዳም የነበረው ጉባኤ በእጅጉ የሚያስደንቅ የእመቤታችንን በረከት በስፋት ያገኘንበት ነበር፡፡ አስቀድመን ስለጉባኤው ከመጋቤ ሃይማኖት ብርሃኑ ጋር በፌስ ቡክ በጣም ዐጭር ማብራሪያ ነበር የሠጠነው ነገር ግን የእመቤታችን ፍቅር በኤልሳቤጥ ማሕፀን ያለውን ፅንሱን በደስታ እንደቀሰቀሰውና በደስታ እንደዘለለ ክርስቶስ አምላካቸው፣ ቅድስት ድንግል ማርያም እናታቸው፣ መንግሥተ ሰማያት ርስታቸው የሆኑ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ምእመናን ከክፍለ ሀገራት ጭምር ነበር በወላዲተ አምላክ ፍቅሯ ተቀሰቅሰው የተገኙት፡፡
💥 የእንጦጦ ሐመረ ኖኅ ገዳም ግቢውም ከውስጥ እስከ ውጪ ነጫጭ በለበሱ በብዙ ሺሕ በሚቆጠሩ ምእመናን ተመልቶ ሲታይ ዮሐንስ በራእዩ “አንድ እንኳ ሊቆጥራቸው የማይችል ከሕዝብና ከነገድ ከወገንም ከቋንቋም ሁሉ እጅግ ብዙ ሰዎች ነበሩ፤ ነጭ ልብስም ለብሰው የዘንባባንም ዝንጣፊዎች በእጆቻቸው ይዘው በዙፋኑና በበጉ ፊት ቆሙ” (ራእይ 7፥9) በማለት የተናገረላቸው ክቡራን ምእመናንን ያሳስባል፡፡
💥 በዕለቱም የበረከት አባት፣ የጸሎት ገበሬ፣ የወንጌል መምህር፣ ሀብተ ፈውስ የተሰጣቸው የታዕካ ነገሥት በአታ ለማርያም ገዳምና የመንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን የበላይ ጠባቂ ብዑዕ አቡነ ሰላማ በዚኽ ታላቅ ጉባኤ መገኘታቸው ታላቅ በረከት ነበር፡፡ በተለይ በእጅጉ የተወደዱት ብጹዕ አቡነ ሰላማ በእንጦጦ ኪዳነ ምሕረት ኪዳነ ምሕረት በነሐሴ 7 በእመቤታችን የጽንሰቷ በዓል ላይ የእመቤታችን ሥዕለ ማርያም የገዳሙን ስጦታ አስቀድመው የሰጡኝ በእጅጉ ከማከብራቸው ሊቃነ ጳጳሳት አንዱ ናቸው፡፡
💥 በመቀጠል በገዳሙ አባቶች የሠርክ ምሕላ፣ ጸሎተ ወንጌል፣ የሠርክ የኪዳን ጸሎት ተደረገ፡፡ ከጸሎቱ ፍጻሜ በኋላ ስለ ቅዱሳት ሥዕላት መጽሐፍ ቅዱሳዊና የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ የጻፍኩት በራሪ ጽሑፍ ለምእመናን ሁሉ ተዳረሰ፡፡
💥 ከዚያም መጋቤ ሃይማኖት ብርሃኑ መርሐ ግብሩን መርቶት የዝማሬ መርሐ ግብር በዘማርያን፣ የመልክአ ሥዕል ዜማ፣ የቅኔ መርሐ ግብር በገዳሙ አበው ሊቃውንት ተደረገ፡፡ በመቀጠል “ዐቃቢተ ኆኅት” ተብላ በምትጠራው በእመቤታችን ሥዕል ዐይናቸው የበራላቸው በዚያ ታላቅ የእግዚአብሔር ጉባኤ ወ/ሮ አልማዝ ለገሰ ምስክርነታቸውን ሰጡ፡፡ እኔም በዐይኔ አይቼ እንደምመሰክረው ይህቺ ሥዕል ወዝን የምታወጣ ሲሆን ይህንንም ከዚህ በፊት በቪዲዮ አቅርቤዋለሁ፡፡
https://youtube.com/shorts/is2CjDMa3TU?feature=share
💥 በመቀጠል ስለ ቅዱሳት ሥዕላት መጽሐፍ ቅዱሳዊ አስተምህሮና የቤተ ክርስቲያን ትውፊት በእመቤታችን ዕድሜ ልክ 64 ስላይድ የያዘ በፓወር ፓይንት የተደገፈ ትምህርትን ሰጠሁ፡፡ ከዚያም ከላያቸው የተቀደሰ ቅብዕ የሚፈሳቸውን በመላው ዓለም ስላሉ ቅዱሳት ሥዕላት አስደናቂ የኾኑ የ10 ደቂቃ ቪዲዮ ለምእመናን አሳየሁ፡፡ https://youtu.be/LMT8zTDSYyg
💥 ከዚያም በፓርት ሳይድ የእመቤታችንና የአባ ብሾይ ቤተ ክርስቲያን ካለችው የተቀደሰ ቅብዕን ከምታፈሰው ሕሙማንን የምትፈውሰውን መዐዛዋ እጅግ የተለየ የሆነውን፤ ሊቁ በመልክአ ሥዕል ላይ፡-
“ሰላም ለሥዕልኪ ሐፈ ማሕየዌ
በጼዴንያ ወግብጽ ዘአውሐዘት በኢሕሳዌ”
(ያለማበል በእውነት በጼዴንያና በግብጽ የሚያድን ወዝን የአፈሰሰች ለሆነች ሥዕልሽ ሰላምታ ይገባል) ብሎ ካወደሳት ከእመቤታችን ሥዕል የተገኘውን ከግብጽ የተላከልኝን 5 ቅብዕ ቅዱስ ለገዳሙ አስረከብኩኝ፡፡
💥 የገዳሙ አበምኔት ጸባቴ አባ ወልደ ማርያም በዚህ ዓመት ከአንጾኪያ ከሥዕለ ማርያም ከሚፈሰው በወዛ የረሰረሰው ጥጥ ይዘው ሥዕሏንም ይዘው መጥተው ነበርና ይህም ልዩ ያደርገዋል፡፡ ከዚያም ብፁዕ አቡነ ሰላማ ቡራኬ ሰጡ፡፡ ከዚያም ከእመቤታችን ሥዕለ ማርያም የፈሰሰውን የተቀደሰውን ቅብዕ በተዘጋጀው ውሃ ውስጥ ባርከው ጨመሩት፡፡ ወዲያው እጅግ ዕጹብ ድንቅ በሆነ መዐዛ አካባቢው ተሞላ፡፡
💥 በእመቤታችን ተአምር ላይ እንደተጻፈው ቅድስት ድንግል ማርያም በደብረ ምጥማቅ ጉልላት ላይ በተገለጸች ጊዜ በኋላም በመጋቢት 24/ 1960 ዓ.ም. በዘይቱን ማርያም ጉልላት ላይ በተገለጸች ጊዜ እንደነበረው ግፊያ ከእመቤታችን ከሥዕሏ ከሚፈሰው ቅብዕ ቅዱስ ለማግኘት፣ ከእመቤታችን በረከት ለመሳተፍ ከፍተኛ ግፊያ ቢኖርም ግን በተቻለ አቅም ለማዳረስ አስተናባሪዎች ሞክረዋል፡፡
💥 በእጅጉ የሚደንቀው በ1960 ዓ.ም. መጋቢት 24 ቀን በዘይቱን ማርያም ቤተ ክክርስቲያን ከ250,000 ሕዝብ በላይ ተጨናንቆ በጉልላቱ ላይ በአስደናቂ ብርሃን ተከባ እመቤታችን ስትገለጽ ያይ እንደነበር ከ54 ዓመት በኋላ በሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት ገዳም የእመቤታችንን በረከት ለማግኘት የጸጋ ልጆቿ ምእመናን ሲጋፉ ሳይ በኅሊናዬ ወደ ደብረ ምጥማቅ፣ ወደ ዘይቱን ማርያም በመኼድ በዐይነ ኅሊናዬ እየተመለከትኩ አምላኬን ካመሰገንኩ በኋላ በርስት ሀገሯ በኢትዮጵያ የምትገልጠው ታላቅ ክብርና ድንቅ እናታዊ ተአምር ሩቅ እንዳልሆነ በመረዳት ደጋግሜ ፈጣሪዬ ክርስቶስን አመሰገንኊ፡፡
https://youtu.be/tVU8bhbQInw
💥 ይህ ታላቅ ጉባኤ በምሥራቀ ፀሐይ ቀበና መድኀኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን በድጋሚ በመጋቢት 27 ለማድረግ የታሰበ ቢሆንም በእንጦጦ ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት ገዳም የተገኘው እጅግ ከፍተኛ ሕዝብ ስለኾነ ከፍተኛ ዝግጅት ተደርጎ ጉባኤው ቢደረግ የበለጠ መልካም ስለሚሆን ላልተወሰነ ጊዜ ጉባኤውን ያራዘምነው ሲሆን ይህንንም ወደ ፊት እንገልጣለን፡፡
“በኢትዮጵያ ወግብጽ ወሶርያ በአንጾኪያ ወሮም
ለሥዕላትኪ ዘሀለዋ ማርያም ሰላም”
(በኢትዮጵያና በግብጽ በሶርያ፣ በአንጾኪያና በሮም ያሉ ለኾኑ ለሥዕላቶችሽ ሰላምታ ይገባል) (መልክአ ሥዕል)
መጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
በእጅጉ የምንወዳት የእመቤታችን በረከቷ ይደርብን።

የመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ "ማዛሮት" 24ኛ መጽሐፍ ምረቃ በጸደይ ሙሉ ጨረቃ ቀን ቅዳሜ በ8ኛ ወራችን በሚያዝያ 8 ከቀኑ በ8 ሰዓት በዲ ሊኦፓል ሆቴል በደመቀ መልኩ ይመረቃል።
በዕለቱ፦
👉 የማዛሮት መጽሐፍ ዳሰሳ - በዶ/ር ጌትነት ፈለቀና በመምህር ማዕበል ፈጠነ ይቀርባል።
👉 በዕውቅ ገጣምያን ግጥም ይገጥማል።
👉 በቅኔ ሊቃውንት ቅኔ ይዘረፋል።
👉 ተመራማሪ የአንድሮሜዳ ሕፃናትና ታዳጊዎች የምርምር ሥራቸውን ያቀርባሉ።
👉 በዕለቱ ዶ/ር አብርሃም አምኃና ሌሎች ተመራማሪዎች፣ ታዋቂ ሰዎች ይገኛሉ።
👉 በዕለቱ የመጀመሪያዋ የጸደይ ሙሉ ጨረቃ ምትታይበት ነውና ምስጢሯ ይገለጻል። የሥነ ፈለክ ምልከታ ይኖራል።
👉 ኮክቴልና ውሃ ለታዳሚዎች ይቀርባል።
የመግቢያ ዋጋ፦ 100 ብር (መግቢያው በዕለቱ ያገኙታል)
አድራሻ፦ ካሳንችንስ ዑራኤል፤ ከባንቢስ አጠገብ በቂ የመኪና ማቆሚያ በሆቴሉ አለ።
👉 በዚህ ታላቅ መርሐ ግብር ላይ አብሮ ለመሥራት ለሚፈልጉ ድርጅቶች በዚህ ስልክ ይደውሉ +251965248300

💥የፀሐይ አክሊል በመላ ኢትዮጵያ በመታየቱ ዙሪያ የተሰጠ ማብራሪያ💥
✍️ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
💥 ይህ ድንቅ ክስተት ዛሬ በሰአሊተ ምሕረት ግቢ ኾኜ ሳለሁ በተመለከትኩ ጊዜ በእጅጉ ደስ ብሎኝ ፎቶ አንሥቼ ከለቀኩ በኋላ ብዙዎች ክስተቱን አስመልክቼ እንድጽፍ ስለጠየቁኝ ጊዜዬን በማጣበብም ቢኾን የተወሰነ ጽፌያለሁ።
💥 እንደ እውነቱ ይህ አስደሳች ቅርጽ በሳይንስ፣ በባሕል፣ በሃማኖት በስፋት ይተነተናል፡፡ በዚህ አክሊል መታየት ዙሪያ የተለያየ እይታ እንደየባሕሉ እንደየሃይማኖቱ እንደየምልከታው ይነገራል፡፡ ሁሉንም በዚህ ላይ ለመተንተን ጊዜ ስለሌለ የተወሰነውን በዐጭሩ ስናይ በሳይንስ ይህ ክስተት አክሊለ ፀሐይ ወይም የ22 ዲግሪ አክሊል በመባል ይታወቃል፡፡
💥የሚከሰተውም ስድስት ማእዘን የሆኑ በከባቢ አየር ላይ ተንሳፈው የሚገኙ በሚሊየን የሚቆጠሩ የበረዶ ክሪስታሎች ላይ የፀሐይ ብርሃን ሲያልፍ ቀስተ ደመና መስሎ የሚታይ በአማካይ 22 ዲግሪ ራዲየስ ላይ ሠርቶ የሚታይ ቀለበት ነው፡፡
💥 ክብ አክሊል የሚፈጠረው ከእኛ በላይ20 ሺ ጫማ (6 km) በሚርቀው ስስ ሽፋን ባለው ሲሩስ በተባለው ደመና ነው ይላል የዘመናችን ሳይንስ፡፡ ይኸውም በብርሃን መጉበጥና መከፈል ወይም ከበረዶው ክሪስታል ብርቅርቅታ የተነሣ ነው፡፡ እያንዳንዱ የሚታየው እንደየቆመበት ቦታ ሲወሰን ቢሆንም ትኩር ብሎ መመልከት በአልትራ ባዮሌት ጨረር ምክንያት ዐይንን ሊጎዳ ይችላል ይላል ሳይንስ፡፡
💥 የጥንት የሥነ አየር ተመራማሪዎች በጨረቃ ዙሪያ የሚፈጠር አክሊል ካለ ከፍተኛ ዝናብ ይዘንባል ይላሉ፡፡ ምክንያቱም የሲሩስ ደመና ከወጀብ በፊት የሚመጣ ስለኾነ የሚል ምልከታ ነበራቸው፡፡
💥 ወደ ሃይማኖት ሊቃውንት ምልከታ ስንሄድ ደግሞ "ቀስተ ደመናዊ የፀሐይ ቀለበት" ይሉታል፡፡ እነዚህ ጥቃቅን የበረዶ ክሪስታል መስታወት መሰል ቅንጣቶች “በዙፋኑም ፊት ብርሌ የሚመስል የብርጭቆ ባሕር ነበረ” በመባል በራእ 4፡6 ላይ የተጠቀሰውት ነው ይላሉ፡፡ ስሙንም "ባሕረ ማሕው" በማለት ይጠቅሱታል፡፡
💥 አንዳንድ የሃይማኖት መምህራን ደግሞ “በፀሐይና በጨረቃም በከዋክብትም ምልክት ይሆናል” (ሉቃ 21፡25) የሚለውን በመያዝ ምልክት በፀሐይ፣ በጨረቃ፣ በከዋክብት መታየታቸው የክፉ ቀን መቃረብ መልእክት ከእግዚአብሔር ሲገለጽ ነው ይላሉ፡፡ ቢሆንም ግን የክፉ ቀን መምጫ መቃረብ የተጠቀሰው አብዛኛውን ከመጨለም ጋር ተያይዞ ያለው ነው እንጂ የፀሐይ አክሊል አይደለም ይላሉ አንዳንድ ምሁራን፡፡ በዚህ ዙሪያ ማዛሮት መጽሐፌን አንብቡ፡፡
💥 እኩሌቶቹ ደግሞ “ሌላም ብርቱ መልአክ ደመና ተጐናጽፎ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፤ በራሱም ላይ ቀስተ ደመና ነበረ፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ እግሮቹም እንደ እሳት ዓምዶች ነበሩ” (ራእ 10፡1) የሚለውን በመያዝ የመገለጥ ትርጕምን ይሰጡታል፡፡
💥 አንዳንዶች ደግሞ በሕልምም በውንም የምናየው የአክሊሉን ቀለም የሚከበንን መንፈሳዊ ኀይልን ጠቋሚ የሚያደርጉ አሉ፡፡ ይኸውም በጣም ሰፊ ሲሆን በዐጭሩ ለመግለጽ ብሩህ አክሊል በፀሐይ ዙሪያ ከኾነ ንጽሕናንና ከአምላክ ጋር መገናኘትን ይገልጻል ይላሉ፡፡ ሰማያዊ አክሊል ፍቅርን መጠበቅን ወካይ ሲሆን በመላእክት መከበብን ያሳያል ይላሉ፡፡ ቀይ አክሊልን ከቁጣ ጋር፤ ጨለማዊ አክሊልን ከባዶነት ከመንፈሳዊነት መራቆት ጋር ጋር የሚያይዙ አሉ፡፡
💥 በዚህ ዙሪያ ከግሪክ እነ አሪስቶትል (Meteorology III.2, 372a14) በሚል ሥራው።
👉 ከሮማ ፈላስፎች በ2ኛው ክፍለ ዘመን አፑሊዩስ Apologia XV ሥራው።
👉 ሉይስ ሴኔካ Naturales Quaestiones. መጽሐፉ፤ 👉 ጸሐፊው ካህኑ ፑሊቸር በ12ኛው ክፍለ ዘመን ላይ Historia Hierosolymitana (1127) መጽሐፉ።
👉 የዮርኩ ኮማንደር ኤድዋርድ ከጦርነት ታሪክና ድል ጋር አያይዞ።
👉 በሮም በ1629 ድጋሚ በ1630 ላይ በታየው የፀሐይ አክሊል ዙሪያ ክሪቶፍ ሼነር Parhelia በሚል መጽሐፉ ብዙ አስገራሚ ነገራትን ጽፈዋል፡፡
👉 በ1661 ላይ ጆርጅ ፌላው “7 ክፍል ያለው የፀሐይ ተአምር” በሚለው በበራሪ ጽሑፉ ላይ ዘርዝሮ የጊዜውን የፀሐይ አክሊል ክስተት ሲጽፍ በቀጣዩ ዓመት ላይ ዮሀኔስ ሄቬሉስ Mercurius in Sole visus Gedani በሚል መጽሐፉ ላይ አስፍሮታል፡፡
👉 በ1790 በተከሰተው በሴንት ፕተርስበርግ ሩሲያ በተከሰተው ጆሀን ቶቢያስ ጽፏል፡፡
👉 በ1843 በኒው ፋውንድ ላንድ በተከሰተው፤ በ1876-77 በነበረው ጦርነት ጊዜ በተከሰተው የፀሐይ አክሊል፤
👉በ2020 ፌቡሯሪ 14 በኢነር ሞንጎሊያ ቻይና በተከሰተው ብዙ ተጽፈዋል፡፡
💥 ሁሉንም ለመጻፍ ጊዜ ስለሌለ ነባር የአሜሪካ ሕዝቦችና ሕንዳውያን የሚሉትን ብቻ ላስቀምጥ፡፡ እነዚህ ጥንታውያን ሕዝቦች ይህንን “የለውጥ ምልክት” “ጥምዝ ቀስተ ደመና” ይሉታል፡፡ ይህንን አክሊል ቅርጽ አስመልክቶ የጥንት አሜሪካና ሕንዳውያን ትንቢት ነበራቸው ይህም "Ancient American Indian Prophecy" በመባል ሲታወቅ ታላቅ ለውጥ በምድር ላይ ለመምጣቱ ምልክት ይላሉ፤ በጥቂቱ ስናየው “ኹሉም ነገዶች፣ ሕዝቦች ያላቸውን ልዪነት በመተው ምድርንና ነዋሪዎቿን ለመፈወስ በሕብረት ለአንድነት የሚቆሙበት ጊዜ ይመጣል፡፡ ሰላምን ለማምጣት እንደ ክብ ቀስተ ደመና በምድር ሁሉ ይመላለሳሉ፡፡ ሁሉም እኩል የሚሆኑበት፣ ሕፃናት የሚጠበቁበት፣ አረጋውያን የሚከበሩበት፣ ጦርነት በሽታ የሚያበቃትን የምድር መፈወሻ ጊዜ የጥበብ ጊዜ መቃረብን ያመለክታል፡፡” ይላሉ፡፡ በቡዲዝም እይታ አክሊል የመልካም ዕድል ምልክት ይሉታል፡፡
💥 በመሆኑም ክቡራን ተመልካቾቻችን ይህን ያህል በዐጭሩ ከሳይንሱም፣ ከባህልም ይህን ያህል ካሰፈርኩ በዝርዝር ስለ ሥነ ፈለክ ለማወቅ አንድሮሜዳና ማዛሮት መጽሐፍን ያንብቡ፡፡
💥 በሙሉ የጸደይ ጨረቃ በ8ኛ ወር ሚያዝያ በ8ኛው ቀን 8 ሰዓት ስለ ሰማይ ምስጢር የሚተነትነው ማዛሮት መጽሐፌን ለመመረቅ በዕለቱ ተገኝተው ብዙ ያልተሰሙ ምስጢራትን ይስሙ።

Watch "(የምሥራች) የተቀደሰ ዘይት የምታፈሰው ሥዕለ ማርያምን ሄዳችሁ ለማየት ለምትፈልጉ" on YouTube
https://youtu.be/iJAeidCazgw
https://youtu.be/iJAeidCazgw
YouTube
(የምሥራች) የተቀደሰ ዘይት የምታፈሰው ሥዕለ ማርያምን ሄዳችሁ ለማየት ለምትፈልጉ
ቀርሜሎስ አስጎብኚ ድርጅት ኢየሩሳሌምንና ግብጽን 0947212121/ 0947272727
Watch "የኒቆዲሞስ የዐቢይ ጾም ትምህርት፣ መዝሙር በሊቀ ሊቃውንት አባ ታፈሰ ደሳለኝ" on YouTube
https://youtu.be/IeMjDhp5prU
https://youtu.be/IeMjDhp5prU
YouTube
የኒቆዲሞስ የዐቢይ ጾም ትምህርት፣ መዝሙር በሊቀ ሊቃውንት አባ ታፈሰ ደሳለኝ
መደመጥ የሚገባው ድንቅ ትምህርት
Watch "ምርጥ የኢትዮጵያ ሕፃናት በቤቴ መጡ ድንቅ ምሽት" on YouTube
https://youtu.be/o2GuJy7rTkY
https://youtu.be/o2GuJy7rTkY
YouTube
ምርጥ የኢትዮጵያ ሕፃናት በቤቴ መጡ ድንቅ ምሽት
Watch "ዕውቀት ከሕፃናት አንደበት ሲቀዳ መጪውን ያሳያል" on YouTube
https://youtu.be/q6kDBHTwwpw
https://youtu.be/q6kDBHTwwpw
YouTube
ዕውቀት ከሕፃናት አንደበት ሲቀዳ መጪውን ያሳያል
💥3 ቀናት ቀሩት💥
የመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ "ማዛሮት" 24ኛ መጽሐፍ ምረቃ በጸደይ ሙሉ ጨረቃ ቀን ቅዳሜ በ8ኛ ወር በሚያዝያ 8 በ8 ሰዓት በዲ ሊኦፓል ሆቴል በደመቀ መልኩ ይመረቃል።
በዕለቱ፦
👉 የማዛሮት መጽሐፍ ዳሰሳ - በዶ/ር ጌትነት ፈለቀና በመምህር ማዕበል ፈጠነ ይቀርባል።
👉 በዕውቅ ገጣምያን ግጥም ይገጥማል።
👉 በቅኔ ሊቃውንት ቅኔ ይዘረፋል።
👉 ተመራማሪ የአንድሮሜዳ ሕፃናትና ታዳጊዎች የምርምር ሥራቸውን ያቀርባሉ።
👉 በዕለቱ ዶ/ር አብርሃም አምኃና ሌሎች ተመራማሪዎች፣ ታዋቂ ሰዎች ይገኛሉ።
👉 በዕለቱ የመጀመሪያዋ የጸደይ ሙሉ ጨረቃ ምትታይበት ነውና ምስጢሯ ይገለጻል። የሥነ ፈለክ ምልከታ ይኖራል።
👉 የከበሩ ማዕድናት መጥተው ለሕዝቡ ይታያሉ።
👉 ኮክቴልና ውሃ ለታዳሚዎች ይቀርባል።
የመግቢያ ዋጋ፦ 100 ብር (መግቢያው በዕለቱ ያገኙታል)
አድራሻ፦ ካሳንችንስ ዑራኤል፤ ከባንቢስ አጠገብ በቂ የመኪና ማቆሚያ በሆቴሉ አለ።
👉 በዚህ ታላቅ መርሐ ግብር ላይ አብሮ ለመሥራት ለሚፈልጉ ድርጅቶች በዚህ ስልክ ይደውሉ +251965248300
💥የአንድሮሜዳ ቤተሰቦች በ8 ወር/8 ቀን/ 8 ሰዓት አይቀርም።💥