መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (ዶክተር) Dr Rodas Tadese
39.7K subscribers
564 photos
42 videos
5 files
1K links
ትክክለኛው ቻናሌ ይሄ ብቻ ነው። በዚ ብቻ ትምህርተ ሃይማኖትንና የኢትዮጵያ ምስጢራትን ሳይንሳዊ ጉዳዮችን በጥልቀት እንዳስሳለን። ሌሎቹ ቻናሎች የእኔ አይደሉም
Download Telegram
📖 እልፋ እግዚአብሔር ይመስገን!
🎉📚 100 ጥንታውያት ሥዕላትን ያካተተው
"መልክአ ሥዕል ንባቡና ትርጓሜው"
📖 30ኛው መጽሐፌ

👥 እጅግ ብዙ የመጻሕፍት ወዳጆች በተገኙበት
🏨 በዮድ አቢሲኒያ
🎊 በደመቀ መልኩ ተመረቀ።

📜 ሙሉ የቀለም ሕትመት የኾነው መጽሐፉ የሚያካትተው፦

ቅዱሳት ሥዕላት
📖 ከብሉይ ኪዳን እስከ ሐዲስ ኪዳን

🏛️ ከጥንት ክርስቲያኖች የካታኮምብ ቅዱሳት ሥዕላት
🌸 እስከ 245 የቅድስት ደንግል ማርያም ሥዕላት

ከሥዕለ ጸባኦት
✝️ እስከ ሥዕለ ቬሮኒካና ሌሎች ምስጢራት

📚 ያካተተው ጥናታዊ መጽሐፍ

📍🇪🇹 በኢትዮጵያ የሚገኝበት፦
🏢 4 ኪሎ ሥላሴ ሕንጻ
📖 ብርሃኑ መጻሕፍት መደብር
📞 0902327081

🌍📦 በውጪ ሀገር ላሉ፦
🛒 በአማዞን
👉 https://www.amazon.com/dp/B0GXQV2QC7
በማዘዝ ማግኘት ትችያለሽ።

🙏 ክብር ኹሉ ለእግዚአብሔር ይኹን!
100👏16🔥3🥰3😁1
📖 "ትእምርተ ድንግል" (የድንግል ምልክት)
📚 ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ (ሚያዝያ 21)
📖 (መልክአ ሥዕል ንባቡና ትርጓሜው ገጽ 208)

🕊️ ከ240 ዓይነቶች የእመቤታችን ሥዕላት መካከል ይኽቺ “ትእምርተ ድንግል” (Παναγία Ορωμένη) ተብላ የምትጠራው ሥዕለ ማርያም እጆቿን ወደ ላይ አንሥታ መዳፏ ወደ ላይ ዞረው ጣቶቿ የተዘረጉ ኾነው የተሣለች ናት፡፡

🙌🌌 ወደ ሰማይ የተዘረጋ እጇ ጸሎትን ምልጃን፣ ጸሎትን ወደ ሰማይ መላኳን ያመለክታል፡፡

👁️ ፊቷ ፊት ለፊት ተመልካቾችን በቀጥታ የሚያይ ሲኾን ክበብ በኾዷ ዙሪያ ሲኖር በክበብ ውስጥ ብላቴናው ኢየሱስ ተሥሏል፡፡

📖 “ትእምርተ ድንግል” (የድንግል ምልክት፣ የእመቤታችን ምልክት / Our Lady of the Sign) ተብሎ መሰየሙ በኢሳ ፯፥፲፬ ላይ፦

✍️ “ስለዚኽ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም ዐማኑኤል ብላ ትጠራዋለች”
የሚለውን የሚገልጽ ስለኾነ ነው፡፡

🌸🕊️ ዳግመኛም እመቤታችን፦

✍️ “እንደ ቃልኽ ይደረግልኝ”
📖 (ሉቃስ ፩፥፴፰)
ባለችበት ቅጽበት ሥግው ቃል ክርስቶስ በድንግል ማርያም ማሕፀን ውስጥ መፀነሱን ያመለክታል፡፡

👶👑 በሥዕሉ ላይ ጌታ እንደ ፅንስ ሳይኾን ሰማያዊ ልብሶችን ለብሶ እና ጥቅል ይዞ መምህርነቱን የሚያሳይ ኾኖ ይታያል።

👁️🕊️ ፊቱም ሕፃን ኾኖ ሳለ በዐዋቂ አምሳል ይመስላል፡፡

ይኽም ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ እንደኾነ ለመግለጽ ነው፡፡

ክቡ ቅርጽ የሚያመለክተው
🌟 ዘላለማዊነት
👑 መለኮታዊ ክብር
💡 አማናዊ ብርሃንን ነው፡፡

🏛️📜 ይኽ የቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕል በጣም ጥንታዊ ሲኾን በ፫፻፬ (304) ዓ.ም. ሰማዕትነትን በተቀበለችው በሮም በሚገኘው የቅድስት አግነስ መካነ መቃብር ውስጥ እጆቿን ወደ ላይ አንሥታ እና ሕፃኑን ኢየሱስን በጉልበቷ ላይ ተቀምጦ የሚያሳይ ሥዕላዊ መግለጫ በአራተኛው ክፍለ ዘመን ነበር።

🙏 የአምላክ እናት ሆይ እንወድሻለን።

📍🇪🇹 መጽሐፉ በኢትዮጵያ የሚገኝበት፦
🏢 4 ኪሎ ሥላሴ ሕንጻ
📖 ብርሃኑ መጻሕፍት መደብር
📞 0902327081

🌍📦 በውጪ ሀገር ላሉ፦
🛒 በአማዞን https://www.amazon.com/dp/B0GXQV2QC7
በማዘዝ ማግኘት ትችላላችኹ።
99👏6
በኢትዮጵያ ስዓት 9:33 ላይ ይጀምራል
71👍14👏7
🙏 በማሕፀን ጠብቀኸኝ
🌍 ይኽችን ድንቅ ምድር
📅 ሚያዝያ 22 እንድቀላቀል
የፈቀድኽ አልፋ እግዚአብሔር ሆይ
አመሰግንሃለኹ።

🎂 ይኽ ልደቴ ለእኔ ልዩ ነው፤
📖 30ኛ መጽሐፌን ሚያዝያ 18 በተመረቀ
🌸 በ4ኛው ቀን ሚያዝያ 22
👨‍👩‍👧‍👦 ከቤተሰቦቼና ከጓደኞቼ ጋር
🎉 አክብሬያለኹ።

🇪🇹 ቀጣይ ዘመኔን
ለምወዳት ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን፤
ለምወዳት ኢትዮጵያ
🌍 ለሰው ዘር በመላ የሚጠቅም ሥራ ብቻ
እንዳስብ፣ እንድናገር፣ እንድሠራ
እንደምታደርገኝ ስለማምን
🙏 አመሰግንሃለኹ።
159👍22👏6🔥5👎1
የቅዱስ ጊዮርጊስ ሥዕል ኃይልና ምሳሌ
📖 በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ (መልክአ ሥዕል ንባቡና ትርጓሜው መጽሐፍ ገጽ 40)

🛡️ ቅዱስ ጊዮርጊስን ጨምሮ በዘመነ ሰማዕታት ዘመን የነበሩ ክርስቲያን ወታደሮች “ጣዖት አናመልክም ክርስቶስን አንክድም” በማለት ታማኝነታቸውን ከምድራዊ ንጉሥ፤ ወደ ሰማያዊ ንጉሥ ወደ ክርስቶስ በማድረጋቸው የሰማዕትነትን አክሊል ተቀዳጅተዋል፡፡

🎖️ በዚኽ ምክንያት ከ10ኛው ክፍለ ዘመን አስቀድመው በተሣሉ የቅዱስ ጊዮርጊስ ሥዕላትና የሌሎች ሰማዕታት ሥዕል በቆመ ወታደር አምሳል ይሣሉ ነበረ፡፡

👤 የቅዱስ ጊዮርጊስም ሥዕል ወጣት፣ ጢም የሌለው፣ ዐጭር ጠጒር ያለው እና የሮማን ከፍተኛ መኮንን ልብስ ለብሶ ይሣል ነበር።

✝️ በተጨማሪም የሰማዕትነቱ ምልክት መስቀል ወይም የጦር ሥዕል ዐብሮ ተሥሎ ነበረ እንጂ የደራጎን ሥዕል እምብዛም ተሥሎ አይታይም ነበር፡፡

🌍 እንደዚኽ ዓይነት ሥዕላት በሶርያ፣ ሊባኖስ፣ ቀጰዶቅያ፣ ቁስጥንጥንያ ይገኛሉ፡፡

🐉 ከዚያ በኋላ ቅዱስ ጊዮርጊስን ጨምሮ አስቀድመው ወታደር የነበሩ ሌሎች ቅዱሳን ሰማዕታት ሥዕላት ላይ ደራጎንን በመጨመር በብዛት ተሥለዋል፡፡

🔥 ደራጎን የሚወክለው ሰይጣንን፣ አረማዊነትን፣ አምባገነንነትን፣ ክፋትን ሲኾን ሰማዕታቱ እነዚኽን ድል መንሣታቸውን ያመለክታል፡፡

🏜️ በሲና በረሓ በሚገኘው በቅድስት ካትሪና ገዳም በሚገኘው የዘጠነኛው ክፍለ ዘመን ሥዕል ቅዱስ ጊዮርጊስ በነጭ ፈረስ ተቀምጦ ከቅዱስ ቴዎዶር ጋር ዐብሮ ተሥሏል፡፡

🐎 ይኸውም በዮሐንስ ራእይ ላይ ክርስቶስ በነጭ ፈረስ ላይ ኾኖ እንደተገለጠ፤ ቅዱስ ጊዮርጊስም የንጹሐ ባሕርይ የክርስቶስ አገልጋይ መኾኑን፤ ዳግመኛም ጽድቅ ከጨለማው ሰራዊት ጋር የሚያደርገው የውጊያ ምልክትና ድልን ይወክላል፡፡

🇪🇹 በኢትዮጵያ በሚገኙ ሥዕላቱ ላይ በነጭ ፈረስ ተቀምጦ የሚሣል ሲኾን ቅድስት ድንግል ማርያም በደብረ ምጥማቅ ስትገለጽ፤ ቅዱስ ጊዮርጊስም በነጭ ፈረስ ላይ ተቀምጦ ይገለጥ እንደነበር ተአምሯ ያስረዳል፡፡

📜 በስብሐተ ፍቁር ዘቅዱስ ጊዮርጊስ ላይም ደራሲው፡-
“ነዓ ጊዮርጊስ እንዘ ትጼዓን በፈረስ ወነዓ ፍቁርየ ዘልዳ ንጉሥ”
(ጊዮርጊስ ሆይ በፈረስ ተቀምጠኽ ና፤ የልዳ ንጉሥ ወዳጄ ጊዮርጊስ ሆይ ና) ይላል፡፡

⚔️ በወታደራዊ ትጥቅ፣ ዘንዶውን የሚወጋበትን ጦር ይዞ ሲታይ ጦሩ ብዙውን ጊዜ ጫፉ ላይ ትንሽ መስቀል አለው፤ ይኸውም ክፉውን በእምነት እንጂ በጉልበት አለመግደሉን ያመለክታል፡፡

🏰 ልዕልቷ (ቤሩታዊት) ወይም ከተማ ከበስተጀርባው ኾነው ተሥለዋል እነዚኽ ሥዕላቱ በጣም የሚታወቁት ናቸው፡፡

👑 በ፲፩ኛው – ፲፪ኛው ክፍለ ዘመን በመስቀል ጦርነት ወቅት ቅዱስ ጊዮርጊስ የወታደሮች ጠባቂ ነው ተብሎ ይታመን ነበርና ቅዱስ ጊዮርጊስ በወጣት አምሳል ይሣላል፣ ይኽም ንጽሕናን፣ ጥንካሬን፣ መንፈሳዊ ድፍረትን ይወክላል፡፡

🔴 ደሙን በክርስቶስ ስም ማፍሰሱን ለማመልከት የሰማዕትነት ምሳሌ የኾነ ደማቅ ቀይ ቆብ አድርጎ አክሊለ ብርሃን ከበላዩ ይታያል፤ ይኽም ቅድስናውን ያገኘውን ድል ይገልጻል፡፡

🌍 እንደዚኽ ዓይነት ሥዕላቱ ቁስጥንጥንያ፣ ቆጵሮስ፣ አንጾኪያ፣ ጆርጂያ፣ ቡልጋሪያ፣ ሰርቢያ ውስጥ ይገኛሉ፡፡

🙏 የቅዱስ ጊዮርጊስ በረከት አይለየን።
120👍4👏4🔥3🥰2
በልደቴ ማግስት የሚያዝያ ወር ሙሉ ጨረቃ ሚያዝያ 23 የእናንተን ፎቶ አጋሩኝ በዚ ሊንክ

https://t.me/+xN518gdGKvswNzE0
31👍28