መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (ዶክተር) Dr Rodas Tadese
39.4K subscribers
527 photos
36 videos
5 files
897 links
ትክክለኛው ቻናሌ ይሄ ብቻ ነው። በዚ ብቻ ትምህርተ ሃይማኖትንና የኢትዮጵያ ምስጢራትን ሳይንሳዊ ጉዳዮችን በጥልቀት እንዳስሳለን። ሌሎቹ ቻናሎች የእኔ አይደሉም
Download Telegram
ቅዳሜ ማታ 2:07 ላይ "የኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔርነት በሐዲስ ኪዳን" በሚል ርዕስ ካለፈው የቀጠለውን የክፍል 2 መርሐ ግብር በዚህ YouTube Channel ይዤላችሁ እቀርባለሁ። ይህንን ጥልቅ ትምህርት በመከታተል በዚህ የፈተና ዘመን እራሶትን በሃይማኖት ያጽኑ። ለሌላውም ይመስክሩ።
ሰማዩን በቀመረ አቡሻኽር እኔና የኔታ ማዕበል የዳሰስንበት ምሽት
ማዛሮት!

ንጋትን አብሥራ፣ ሙሉ ቀኑን ብርሃንን ከሙቀቷ ጋር እየመገበች፣ ከድሮ እስካሁን የሰው ልጅ ቀና ብሎ ሲያያት ግርምትን ከምትቸረው፣ ጥያቄን ከምታጭረው ፀሐይ ጀምሮ፣ ምሽት ላይ ሰማዩን ተቆጣጥረዉ ስለሚያስውቡት፣ ጌታችን፣ መድኀኒታችን፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ከእመቤታችን ድንግል ማርያም ሰው ሆኖ ዓለምን በደሙ ሊያነፃ፣ በሞቱ ሕይወትን ሊሰጥ መምጣቱን ለማብሠር፣ ሰብአ ሰገልን እየመሩ ወደ ቤተልሔም አድርሰው የዓለምን መድኀኒት እውንም ሰው መሆን ያበሠሩት፣ ግብፃውያንንም የዐባይን ውሀ መሙላት መጉደል የሚያበሥሩት፣ የሚያራቅቁትና እና የሚያመራምሩትን ከዋክብት ሳይተው፣ በከዋክብት ታጅባ የምትወጣዋ፣ ስትታይ መንፈስን የምታድሰዋን፣ ነፍስን በሐሴት የምትሞላዋ የጨለማዋ ድምቀት፣ስለ ውቢቷ ጨረቃ ሰፊ ትንታኔን እና ማብራሪያን ሰጥቶ፣በመጨረሻም ሥነ አየርን እና ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ያላቸውን ቁርኝት እያዝናና የሚያስተምር፣ እያዋዛ እውቀትን ከጭንቅላት እንዳይጠፋ አትሞ የሚያኖር፣ ከውጭ ሀገር ግኝቶች ጀምሮ ጥንታዊ የብራና እውቀቶች እንዲሁም ሃይማኖታዊ ትንታኔዎች ጋር እያቆራኘ፣ ሳያምታታ ለዘመናት የሚዘልቅ ትምህርትን የሚመግብ የዘመናችን ምርጡ መጽሐፍ ነውና፣ በኔ አስተያየት ከሊቅ እስከ ደቂቅ ቢያነበው እድሜ ዘመኑን የሚዘልቅ እውቀትን ያስጨብጣልና ቢነበብ ብዬ የምመክረው ትልቅ የእውቀት ሙዳይ ነው።

#ማዛሮት #ዶክተር_ሮዳስ_ታደሰ
ከቤተልሔም
💥 ለመጻሕፍት ወዳጆች እንኳን ደስ አላችሁ። አልቆ የነበረው ሰማያዊ ምስጢራትን የያዘው "ማዛሮት" የተባለው ብዙዎች ሲጠባበቁት የነበረው 24ኛ መጽሐፌ በ376 ገጾች ተዘጋጅቶ ፈልገው ላላገኙት አንባብያን ሲባል በጥቂት ኮፒዎች በድጋሚ ታተመ።

💥 ይህ መጽሐፍ በ 4 ታላላቅ ምዕራፎች የተከፈለና 170 ርዕሶችን የያዘ ሲሆን፦ ከእነዚህ ውስጥ ጥቂቶቹ፦
✍️ ፀሐይ የያዘችውን 35 መንፈሳዊ ምስጢራትን በዝርዝር ይዟል።
✍️ የዮሐንስ ራእይን 7ቱን ማሕተም ለሚያጠኑ ሊቃውንት እስከ 2100 ዓ.ም. ድረስ የሚከሰቱ የ100 ዓመታት የደም ጨረቃ ግርዶሽ (Super Blood Moon) መቼ እንደሚከሰቱ
✍️ 46 ቱ ሕብራተ ከዋክብት የያዙት ረቂቅ ሙሉ መንፈሳዊ ሰማያዊ ምስጢር
✍️ ፀሐይ የምትዞራቸው የ12ቱ የዞዲያክ መገብተ አውራኅ ከዋክብት ምስጢርና ምሳሌ
✍️ ፕላኔቶች የያዙት ረቂቅ ምስጢርና ምሳሌ
✍️ የኢትዮጵያ ፊደላት ከፕላኔት ጋር ያላቸው ድንቅ ትስስር
✍️ ሰብአ ሰገልን ስለመራው የቤተልሔም ኮከብ ምስጢር
✍️ የጨረቃ መንፈሳዊ ምሳሌ
✍️ በመሉ ጨረቃ ጊዜ በሰዎች፣ በአራዊት የሚከሰተው የጠባይ መለዋወጥ መነሾው
✍️ ጨረቃ በምታስነሣው ማዕበል ስለሚከሰተው ቀጣይ ጎርፍ
✍️ የሴቶች የወር አበባ ዑደትና የጨረቃ ዑደት ያለው ትስስር
✍️ 12ቱ ነፋሳት፣ ደመናት፣ መባርቅት፣ ነጎድጓድ፣ ዝናብ፣ በረዶ የያዙት ምሳሌዎች
✍️ የኢትዮጵያ ሊቃውንት ያመሰጠሩት በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተጠቀሱት ሰማያት አካላት በሙሉ ትርጓሜ ተካቶበታል።

✍️ ያለንበት ዘመን የዕውቀት፣ የጥበብ፣ የማስተዋል ጊዜ ነውና ይህን መጽሐፍ አንብበው ከፍተኛ ሥጋዊና መንፈሳዊ ዕውቀትን ይሸምቱ። የዐቢይ ጾም ስጦታ አድርገው ለሚወዱት ሁሉ ይስጡ።
✍️ መጽሐፉን በሁሉም የመጻሕፍት መደብርና በሚያዞሩት በ200 ብር ያገኙታል። ወይም በከተማም በክፍለ ሀገርም ላሉ ብርሃን መጻሕፍት አከፋፋይ 0913422447 ደውለው ያገኙታል።
✍️ በውጭ ሀገራት ለምትፈልጉ በአማዞን https://www.amazon.com/dp/0578260875/ref=cm_sw_r_apan_glt_i_ZP0XDRH8DPNN29PB1R7X
ይገኛል።

✍️ በሰላም አስጀምረህ ያስፈጸምከኝ ልቡናን የምትመረምር ጥበብን፣ ማስተዋልን የምትሰጥ ብርሃኔ እግዚአብሔር ሆይ አመሰግንሃለሁ። ዘወትር በአንተ ብርሃንነት ብቻ አኑረኝ።
ኀሙስ ከምሽቱ 2:30 ላይ "የስዋስቲካ መስቀል ኮድ በ49 ቀመር ሲከፈት" በሚል ርዕስ ምርጥ መርሐ ግብር በዚህ YouTube Channel ላይ ይዤላችሁ እቀርባለሁ።
"አለማወቅ ድቅድቅ ጨለማ ሲኾን፤ ዕውቀትና ጥበብ ፍጹም ብርሃን ነው"
መጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
ክቡራን የዚህ YouTube Channel ተከታታዮች በሕይወተ ሥጋ የሌሊቱ የመጻሕፍተ ሊቃውንትና የአቡሻህር መምህሬ ሊቀ ሊቃውንት አባ ታፈሰ ደሳለኝ ተቀድተውት የነበረው የዓመቱ (የ52 ቱ ሰንበታት ስብከታቸው ዘወትር ዐርብ ከምሽቱ 2:15 የምለቅላችሁ ይኾናል። የሰንበቱ መዝሙር፣ ምስባክ፣ ወንጌሉ ከትርጓሜው ጋር ይለቀቃል።
የኔታ በረከቶ ይደርብን።
መጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
ሰብስክራይብ አድርገው ይከታተሉ።
በጉጉት የምትጠብቁት የኔታ ማዕበል ፈጠነን የክፍል 2 ቃለ መጠይቅ ቅዳሜ ማታ በባላገሩ ቴሌቭዥን በአንድሮሜዳ ላይ ከምሽቱ 3 ሰዓት ይጠብቁ። አስገራሚ ድንቅ ነገርን ይሰሙበታል። በቴሌቭዥን ለማይከታተሉ በባላገሩ YouTube ቀጥታ ይከታተሉ።