መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (ዶክተር) Dr Rodas Tadese
39.8K subscribers
572 photos
42 videos
5 files
1.05K links
ትክክለኛው ቻናሌ ይሄ ብቻ ነው። በዚ ብቻ ትምህርተ ሃይማኖትንና የኢትዮጵያ ምስጢራትን ሳይንሳዊ ጉዳዮችን በጥልቀት እንዳስሳለን። ሌሎቹ ቻናሎች የእኔ አይደሉም
Download Telegram
💍🕊️ ከቃል በላይ የሆነ ምስጋና

ቀኑ ዐለፈ… ግን አላበቃም!
የዕለቱ ድምቀት ወደ ትዝታ ተለወጠ፤ ነገር ግን አንድ ነገር ከእኛ ጋር ቀርቷል የእናንተ ፍቅር! ❤️

🤍 መስከረም 10 ቀን 2019 ዓ.ም.

እኛ ቀለበት ተለዋወጥን፤ እናንተ ፍቅር ሰጣችሁን።
እኛ አክሊል ተቀዳጀን፤ እናንተ በጸሎታችሁ ባረካችሁን።
እኛ ዐዲስ ሕይወት ጀመርን፤ እናንተ ጅማሬያችንን በፍቅር አጀባችሁት።

🙏 በዚህ የሕይወታችን ታላቅ ምዕራፍ ውስጥ በጸሎት፣ በበረከት፣ በፍቅርና በአገልግሎት ዐብራችሁን የቆማችሁትን ሁሉ በስም ባንጠራችሁም በልባችን እያንዳንዳችሁን እናስባለን።

⛪ በቅድሚያ ሥርዓተ ተክሊላችንን በጸሎትና በበረከት የፈጸሙልንን ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ እንጦንስና ብፁዕ አቡነ ማርቆስ በክቡር እጆቻችሁ ተባርከን፣ በአባታዊ ጸሎታችሁ ታጅበን የተክሊልን ምሥጢር እንድንፈጽም ስላደረጋችሁን ከልብ እናመሰግናለን።

🕊️ የቶታል ደብረ ገነት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ማኅበረ ካህናት በሙሉ ሥርዓተ ተክሊሉ በክብር፣ በሥርዓትና በመንፈሳዊ ድምቀት እንዲፈጸም ላደረጋችሁልን አገልግሎትና ድካም ልዩ ምስጋናችን ይድረሳችሁ።

🙏 በሥርዓተ ተክሊሉ የተገኛችሁ ሊቃውንት አበው በሙሉ በመገኘታችሁ፣ በጸሎታችሁና በአባታዊ በረከታችሁ ያከበራችሁን፣ ክብራችሁ በልባችን የማይረሳ ትዝታ ሆኖ ይኖራል።

🌹 በጸሎተ ማርያም ያሰባችሁን አበው በእመቤታችን ፊት ስማችንን በጸሎት ያነሣችሁ፣ አዲሱን ቤታችንን በምልጃዋ እንዲጸና የተመኛችሁልን፣ ጸሎታችሁ ለቤታችን የማይጠፋ መብራት ይሁንልን።

✈️ ከውጭ ሀገራት ለዚህ ጋብቻ ብላችሁ ረጅም መንገድ አቋርጣችሁ የመጣችሁ ውድ ወዳጆቻችን ርቀትን አቅርባችሁ፣ ጊዜያችሁንና ጉልበታችሁን ሰጥታችሁ ደስታችንን ለመካፈል ስለመጣችሁ፣ የእያንዳንዳችሁ ጉዞ ለእኛ የፍቅር ትልቅ ማስረጃ ነው። ❤️

📱 በማኅበራዊ ሚዲያዎች ሁሉ ፍቅራችሁን፣ መልካም ምኞታችሁንና ጸሎታችሁን የሰጣችሁን በሙሉ በአካል ባትገኙም በቃላችሁና በፍቅራችሁ ርቀቱን አጥፍታችሁ ከጎናችን ነበራችሁ።

💬 እንዲሁም «ይህ ቢስተካከል የተሻለ ይሆናል» ብላችሁ በፍቅርና በቅንነት ገንቢ አስተያየት የሰጣችሁን ሁሉ ከልብ እናከብራለን። ፍቅር ማለት ማድነቅ ብቻ ሳይሆን፣ የተሻለ እንድንሆን በቅንነት መናገርም ነው። የፍቅር ምክራችሁን በክብር ተቀብለነዋል።

🤍 ከሌሊት ጀምራችሁ እስከ አሁን ድረስ ያልተለያችሁን ሁላችሁ ድካምን ሳትቆጥሩ፣ ሰዓትን ሳትለኩ፣ በየቦታው ከጎናችን ሆናችሁ የእኛን ደስታ እንደራሳችሁ ደስታ የተሸከማችሁ የልባችን ሰዎች ናችሁ።

👏 ሠርጉ ውብ፣ የተደራጀና የማይረሳ እንዲሆን ቀንና ሌሊት የደከማችሁ የሠርጋችን ኮሚቴዎች ከመጋረጃው ጀርባ ያፈሰሳችሁትን ላብ፣ የሰጣችሁትን ጊዜ፣ የተሸከማችሁትን ኃላፊነትና ያሳያችሁን ፍቅር በቃል ብቻ ልንከፍለው አንችልም።

❤️ እያንዳንዳችሁ የሠርጋችን ተመልካች አልነበራችሁም፤ የደስታችን አካል፣ የበረከታችን ተካፋይ፣ የሕይወታችንም ውብ ታሪክ ናችሁ።

🙏 ስለዚህ ምስጋናችን በቃል ብቻ አያበቃም ወደ ጸሎት እንለውጠዋለን።

እግዚአብሔር የደከማችሁትን ድካም በበረከት፣ የሰጣችሁትን ፍቅር በፍቅር፣ ያፈሰሳችሁትን ደስታ በእጥፍ ደስታ ይመልስላችሁ።

በደስታችን የተደሰታችሁትን በደስታችሁ እንድንደሰት፣
በበዓላችን የቆማችሁትን በበዓላችሁ ከጎናችሁ እንድንቆም፣
ለቤታችን የጸለያችሁትን ቤታችሁ በሰላምና በበረከት ሲሞላ እንድናይ፣
እግዚአብሔር ያብቃን። 🕊️

ቤታችሁ የሰላም ማደሪያ፣
ልባችሁ የፍቅር መኖሪያ፣
ማዕዳችሁ የበረከት ማዕድ፣
ዘመናችሁም የጸጋና የደስታ ዘመን ይሁንላችሁ። 🙏🤍

ቀኑ አልፏል፤ ያደረጋችሁልን ግን አላለፈም።
ድግሱ ተጠናቋል፤ ፍቅራችሁ ግን በልባችን ይቀጥላል።
ሠርጉ ትዝታ ሆኗል፤ እናንተ ግን የትዝታው ውበት ሆናችሁ ቀርታችኋል። ❤️💍🕊️

በፍቅር፣ በጸሎትና በማይረሳ ምስጋና፣
መጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ 💍 ወ/ት ሣምራዊት መልአኩ
❤389🥰42👍20👏17🔥10
📖👑 በቅርቡ ይጠብቁ! በቅርቡ ለንባብ ይበቃል!

🌹💎 «አክሊለ ድንግል» በቅዱስ ደቅስዮስ

📚 የመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ 31ኛ መጽሐፍ፤ ለመጀመሪያ ጊዜ ለንባብ ሊበቃ ነው!

📘 28 ምዕራፎች!
📄 250 ገጾች!
🖋️ 370 የግርጌ ማስታወሻዎች (Footnotes)!
👑 24 የምስጋና ምሥጢራት!

✨ ቅዱስ ደቅስዮስ ለድንግል ማርያም የምስጋና አክሊል ጎነጎነላት፤ እመቤታችንም በሰማያዊ ልብስ አስከበረችው!

ቅዱስ ደቅስዮስ ማን ነው? የምስጋናው አክሊልስ ምን ምሥጢራትን ይዟል?

💎 12 የከበሩ ድንጋዮች!
🌟 6 የሰማይ አካላት!
🌹 6 ውብ አበቦች!

👑 24 የፍጥረት ምሳሌዎች፤ 24 መንፈሳዊ ምሥጢራት፤ አንድ የምስጋና አክሊል!

💎 መረግድ፣ ሰንፔርና ቶጳዝዮን ስለ ድንግል ማርያም ምን ይመሰክራሉ?

🌌 ፀሐይ፣ ጨረቃ፣ ኦሪዮንና አርክቱረስ በእመቤታችን ምስጋና ውስጥ ምን ያመለክታሉ?

🌹 ጽጌረዳ፣ የሱፍ አበባና የበረሓ አበባ የእመቤታችንን ንጽሕና፣ ትሕትናና ቅድስና እንዴት ይገልጻሉ?

📖 እነዚህን ሁሉ ምሥጢራት የሚያብራራው «አክሊለ ድንግል» በቅርቡ ለአንባብያን ይቀርባል!

🌟 የአበቦችን ውበት፣ የዕንቁዎችን ድምቀትና የከዋክብትን ብርሃን ከነገረ ማርያም ረቂቅ ምሥጢራት ጋር የሚያስተሳስር ልዩ መጽሐፍ!

📣 ውድ አንባብያን!

የ24ቱን የምስጋና አክሊሎች ምሥጢር ለማወቅ ከወዲሁ ተዘጋጁ!

📚 እመቤታችን ይህንን መጽሐፍ ደቅስዮስ ሲጽፍላት በታላቅ ክብር እንደባረከችው በተአምሯ ላይም ተጽፏል። ታዲያ ይኽ መጽሐፉ ሲወጣ ከመጀመሪያዎቹ አንባብያን መካከል ለመሆን ይዘጋጁ፤ ለቤተሰብዎና ለወዳጆችዎም የንባብ ግብዣውን ከወዲሁ ያስተላልፉ!

👑🌹 «አክሊለ ድንግል» — የምድር ዕንቁዎች፣ የሰማይ ከዋክብትና የአበቦች ውበት በአንድ የምስጋና አክሊል የሚገናኙበት ድንቅ መጽሐፍ!

⏳📖 በቅርቡ ይጠብቁ!

💎 24 ምሥጢራት፤ 28 ምዕራፎች፤ 250 ገጾች፤ አንድ አስደናቂ የንባብ ጉዞ!

📣 የመጽሐፉን መውጣት ለሚጠባበቁ ወዳጆችዎ ይህን መልእክት ያጋሩ!
❤76🔥8👏7👍5
📖👑 በዚኽ ሳምንት ለአንባብያን ከሚቀርበው ከአክሊለ ድንግል የቅዱስ ደቅስዮስ መጽሐፍ የወሰደ ገጽ 222 የተወሰደ:

🌹💐 በዕንባና በትካዜ ውስጥ ኾነው ለሚጮኹት ሐዘንተኞች ኹሉ ፍጹም መጽናኛቸው ነሽ፥ እናትነትሽ እያንዳንዱን በጭንቀት የሚፈሰውን የልመና ዋይታ በደግነት ይስማው፡፡

🌸🕊️ እናትነትሽ ፍጹም ጣፋጭ በኾኑ ሰማያዊ መዐዛዎች (ሽቱዎች) የተሞላ ነው፥ እነዚያም (መዐዛዎች) በጥልቅ ለሚናፍቁትና ለሚሹት የስሜት ሕዋሳት ኹሉ ታላቅ ዕረፍትን የሚሰጡ ናቸው፤

💎✨ እንደዚያ ሰማያዊ ሰንፔር ዕንቊ ፍጹም ብሩህና የደመቅሽ ነሽ፥ ይልቁንም ደግሞ እንደ አልማዝ ይበልጥ ንጹሕና ግልጽ የኾነ የብርሃን ጮራ ነሽ፡፡

💚👑 እንደ መረግድ ዕንቁ ያ የሚያምረውና የሚያበራው ለምለም ውበትሽ (ግርማሽ)፥ በእሳት እንደተፈተነና እድፍ እንደሌለበት ፍጹም ንጹሕና እውነተኛ ወርቅ ነው፤ ከምንም ጋር ወደር የማይገኝልሽ፥ ብርቅዬና እጅግ የከበርሽ ነሽ፥ ፍጹም ውብና የዋሂት የኾንሽ ድንግል ሆይ! እናትነትሽ በትክክል እንዲኽ ናት!
❤36👏8
📖👑 "አክሊል ድንግል በቅዱስ ደቅስዮስ"
✍️ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ የተዘጋጀ ገጽ 166
🌹 አንቺ በእምነትና በትዕግሥት ከአባቶች ይልቅ የከበርሽ ነሽ፤ በዕውቀትና በማስተዋል (በትንቢት እይታ) ከነቢያት ይልቅ የላቅሽ ነሽ፤ በቅድስና ፍጹምነትም ከሐዋርያት ኹሉ በላይ ከፍ ከፍ ያልሽ ነሽ።

🕊️ ስለ ክርስቶስ መከራን በመቀበልና በመታገስ ከሰማዕታት ኹሉ በላይ የላቅሽ ነሽ፤ በበጎ ምግባርም ሥራ ቅዱሳንን ኹሉ ቀድመሻል።

🌸 በንጽሕናሽ ከደናግል ኹሉ በላይ ነሽ፤ በጸጋሽም መብዛት (ሙላት) መላእክትንና ሊቃነ መላእክትን ኹሉ ትበልጫለሽ።

✨ በጥበብሽ ግርማ ከኪሩቤል ይልቅ እጅግ የምታበሪ ነሽ፤ በፍቅርሽም ኃይልና ሙቀት (ትኩሳት) ከሱራፌል ይልቅ እጅግ የገዘፍሽ (የበራሽ) ነሽ!

👑 በእውነት አንቺ በጥበብ፥ በቅድስናና በጸጋ ከተፈጠሩት ፍጥረታት ኹሉ በላይ እጅግ የላቅሽ ነሽ፤ በአጽናፈ ዓለምም የሚወዳደርሽ (የሚስተካከልሽ) ማንም የለም።

💎 ስለዚኽም ለአንቺ የሚገባሽን ክብርና ምስጋና ለማቅረብ የምናፍቅ ምስኪን ኃጢአተኛ የኾንኊ እኔ በዚያ በከበረው አክሊልሽ በዐሥራ አንደኛው ስፍራ ላይ የከበረውን የኢያሰጲድ ዕንቁ አኖራለኊ።

💠 ኢያሰጲድ በሚያስደንቅ የሕብረ ቀለማት ውበት የተሞላና ድብቅ (ረቂቅ) የፈውስ በረከቶች ያሉት ድንቅ ዕንቁ ነው። እርሱ ከቁስል የሚፈሰውን ደም የመግታትና የማቆም ተፈጥሯዊ የፈውስ ኃይል አለው።

🌹 እመቤቴ ሆይ! ይኽ ዕንቁ ለተቀደሰው አክሊልሽ ፍጹም የሚስማማ ጌጥ ነው፤ ምክንያቱም አንቺ በተለያዩ የበጎ ምግባራት ውበቶች የተሸለምሽ፥ የድንግልናና የቅድስናም ጥምር ኃይላት የተዋሐዱብሽ ነሽና።

📚 የቅዱስ ደቅስዮስ መጽሐፉን ሰርድዮን መጻሕፍት መደብር ያገኙታል 0910934578 ይገኛል
❤24👏2