መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (ዶክተር) Dr Rodas Tadese
40.1K subscribers
569 photos
42 videos
5 files
1.05K links
ትክክለኛው ቻናሌ ይሄ ብቻ ነው። በዚ ብቻ ትምህርተ ሃይማኖትንና የኢትዮጵያ ምስጢራትን ሳይንሳዊ ጉዳዮችን በጥልቀት እንዳስሳለን። ሌሎቹ ቻናሎች የእኔ አይደሉም
Download Telegram
34. 🇪🇨 የቅዱስ ሩፋኤል ፓሪሽ (San Rafael Parish) — ኢኳዶር፤ ይፋዊ የአካባቢው መረጃ ስሙ በሊቀ መልአኩ ክብር መሰጠቱን በቀጥታ ያረጋግጣል።

35. 🇬🇹 የቅዱስ ሩፋኤል ፔትሳል ማዘጋጃ ቤት (San Rafael Pétzal) — ጓቲማላ፤ አጠቃላይ የማዘጋጃ ቤቱ ስም የሊቀ መልአኩን ስም ይይዛል።

36. 🇳🇮 የቅዱስ ሩፋኤል ዴል ኖርቴ ማዘጋጃ ቤት (San Rafael del Norte) — ኒካራጓ፤ ቅዱስ ሩፋኤል በይፋ የከተማዋ ጠባቂ ነው።

37. 🇳🇮 የቅዱስ ሩፋኤል ዴል ሱር ማዘጋጃ ቤት (San Rafael del Sur) — ኒካራጓ፤ ቅዱስ ሩፋኤል ዋና የአካባቢው ጠባቂ መሆኑ በመንግሥታዊ የባህል ምንጭ ተመዝግቧል።

✨ ከጥናቱ የሚታየው

❤ የቅዱስ ሩፋኤል ስም ከከተማ አልፎ ለማዘጋጃ ቤት፣ ዲስትሪክት፣ ወንዝ፣ ተራራ፣ በረሃ፣ የድንጋይ ሰንሰለት፣ ደሴት፣ የጂኦሎጂ ንብርብር እና የከተማ አርማ ድረስ ደርሷል።

በተለይ በሰሜን አሜሪካ USA 🇺🇸 ዩታ ውስጥ የቅዱስ ሩፋኤል ወንዝ (San Rafael River)
→ የቅዱስ ሩፋኤል ስዌል (San Rafael Swell)
→ የቅዱስ ሩፋኤል ሪፍ (San Rafael Reef)
→ የቅዱስ ሩፋኤል በረሃ (San Rafael Desert) → የቅዱስ ሩፋኤል ግሩፕ (San Rafael Group) ተብሎ አንድ ስም በጂኦግራፊና በጂኦሎጂ ውስጥ መስፋፋቱ ልዩ ነው።

ከሁሉ አስገራሚው ግን 🇫🇷 ቅዱስ ሩፋኤል (Saint-Raphaël) በፈረንሳይ ያለው ክብሩ ነው፤ ስሙ ብቻ ሳይሆን በከተማዋ አርማ ላይ ሩፋኤል ሊቀ መልአክ ከጦቢያ ጋር ጦቢያ ዓሣ ይዞ በይፋ ተሥሏል።

❤ በሀገራችን በኢትዮጵያ በስሙ የተሰየሙ በጣም ጥቂት አብያተ ክርስቲያናት እንጂ በስሙ የተጠሩ ተራራዎች፣ ወንዞች፣ ሀገሮች እስካኹን በግሌ አልሰማኹም። ወደፊት ግን እንደሚኾን አምናለኹ። እመኛለኹም።
👉 በአስተያየት መስጫው ላይ ቅዱስ ሩፋኤልን በፍቅር አወድሱት
https://t.me/+xN518gdGKvswNzE0
✍️ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ (ጳጉሜን 2 ሌሊት ተጻፈ)
❤161👏14🥰10👍9
🌼☀️ እንኳን ለዘመነ ሉቃስ በሰላም አደረሳችኹ🌙🌼
«ዐዲስ ዓመት የተዘጋን በር ትተን ወደ ዐዲስ ተስፋ የምንገባበት፣ የትናንትን ትምህርት ይዘን የነገን ታሪክ መጻፍ የምንዠምርበት ዐዲስ ምዕራፍ ነው።»
💥 በአልፋ እግዚአብሔር ቸርነት
🌼 እንደ ዐደይ አበባ ከክረምት በኋላ ውበታችን ይገለጥ፤
☀️ እንደ ፀሐይ ተስፋችን በየቀኑ ይብራ፤
🌙 እንደ ጨረቃ በጨለማ ውስጥ ብርሃን እንኹን፤
🌱 የደረቀው ይለምልምልን፣ የጠፋው ተስፋችን ይመለስ፣ የጀመርነው በበረከት ይፈጸም።

2019 ዓ.ም. በፀሐይ ☀️
2080 ዓ.ም. በጨረቃ 🌙

ዓመቱ ቁጥሩ ብቻ ዐዲስ የሚኾንበት ሳይኾን፣ ልባችን፣ ሐሳባችን፣ ሥራችንና ሕይወታችን የሚታደስበት ዓመት ይኹን!

🙏 እግዚአብሔር 2019 ዓ.ም.ን የሰላም፣ የፍቅር፣ የይቅርታ፣ የጤና፣ የስኬትና የበረከት ዓመት ያድርግልን!

🌼 እንኳን ከዘመን ማርቆስ ወደ ዘመን ሉቃስ በሰላም አሸጋገራችኹ! 🌼

💥 በምሥራቀ ፀሐይ ቀበና መድኃኔ ዓለም መስከረም 1 ታቦተ ዮሐንስ መጥምቅ ወጥቶ በባሕረ ሐሳብ አወጣጥ በዓሉ ስለሚከበር የምትችሉ መጥታችኹ ዐዱሱን ዓመት በበረከት ጀምሩት።
❤273👏19👍14🔥8🥰7
📖 30 መጻሕፍትን ጻፍኩ፤ አሁን ግን ከሁሉም የሚለየውን መጽሐፍ ልጀምር ነው፤ ብዕሩ ፍቅር፣ ቀለሙ ቃል ኪዳን፣ ርዕሱም “ትዳር” ነው! 💍❤️

30ኛ መጽሐፌን አጠናቅቄ አስመርቄ፤ አሁን ደግሞ የሕይወቴን ዐዲስና ውብ ምዕራፍ ከወት ሣምራዊት ጋር ልከፍት ነው። 📚➡️💍

አንድ ሰው መጽሐፍን ብቻውን ሊጽፍ ይችላል፤ የትዳርን ታሪክ ግን ኹለት ልቦች በአንድ ቃል ኪዳን ይጽፉታል። ❤️

🌸 እሑድ መስከረም 10 ቀን 2019 ዓ.ም.
🌺 በተቀጸል ጽጌ፣
🕊️ በበዓለ ጼዴንያ፣
✝️ በበዓለ መስቀል ዕለት፣

በቶታል ሰፈረ ገነት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል፣ ከወይዘሪት ሣምራዊት መልአኩ ጋር ጋብቻችንን በቅዱስ ሥርዓተ ተክሊል እንፈጽማለን። 👑💍🕊️

ውድ ወዳጆቼ፣ ዘመዶቼ፣ በሕይወት ጉዞዬ አብራችሁኝ የቆያችሁ ኹላችሁ፤ በዕለቱ በሌሊትም ይኹን በጠዋቱ የዐውደ ምሕረት መርሐ ግብር ላይ ወደ ቤተ ክርስቲያን መጥታችሁ የጸሎታችን፣ የበረከታችንና የደስታችን ተካፋይ እንድትኾኑ በታላቅ ፍቅር እጋብዛችኋለሁ። 🙏❤️

📍 የቤተ ክርስቲያኑ አድራሻ፦
ከጦር ኃይሎች ወደ ቶታል በሚወስደው መንገድ፣ ከዱባይ (United Arab Emirates Embassy) አጠገብ፣ ቶታል ሰፈረ ገነት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል።

📚 30ኛው መጽሐፌ ተጠናቀቀ፤
💍 የሕይወቴ ዐዲስ ምዕራፍ ይከፈታል፤
✝️ በክርስቶስ በመስቀሉ ጥላ ሥር ሁለት ሕይወት በአንድ ቃል ኪዳን ይተሳሰራል።

እስከዛሬ 30 መጻሕፍትን ጽፌ ለአንባቢዎቼ አቀረብኩ፤
ከዚህ በኋላ ግን እግዚአብሔር የሚመራውን የሕይወት ታሪክ ሁለት ሆነን እንጽፋለን። 💍📖❤️

ኑ፤ የዚህ ዐዲስ ምዕራፍ የመጀመሪያ ገጽ ሲጻፍ ከእኛ ጋር ኹኑ! 🙏🌹

መጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
💍
ወ/ት ሣምራዊት መልአኩ

https://t.me/+xN518gdGKvswNzE0
❤465👏50👍28🥰20🔥11
💍🕊️ ከቃል በላይ የሆነ ምስጋና

ቀኑ ዐለፈ… ግን አላበቃም!
የዕለቱ ድምቀት ወደ ትዝታ ተለወጠ፤ ነገር ግን አንድ ነገር ከእኛ ጋር ቀርቷል የእናንተ ፍቅር! ❤️

🤍 መስከረም 10 ቀን 2019 ዓ.ም.

እኛ ቀለበት ተለዋወጥን፤ እናንተ ፍቅር ሰጣችሁን።
እኛ አክሊል ተቀዳጀን፤ እናንተ በጸሎታችሁ ባረካችሁን።
እኛ ዐዲስ ሕይወት ጀመርን፤ እናንተ ጅማሬያችንን በፍቅር አጀባችሁት።

🙏 በዚህ የሕይወታችን ታላቅ ምዕራፍ ውስጥ በጸሎት፣ በበረከት፣ በፍቅርና በአገልግሎት ዐብራችሁን የቆማችሁትን ሁሉ በስም ባንጠራችሁም በልባችን እያንዳንዳችሁን እናስባለን።

⛪ በቅድሚያ ሥርዓተ ተክሊላችንን በጸሎትና በበረከት የፈጸሙልንን ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ እንጦንስና ብፁዕ አቡነ ማርቆስ በክቡር እጆቻችሁ ተባርከን፣ በአባታዊ ጸሎታችሁ ታጅበን የተክሊልን ምሥጢር እንድንፈጽም ስላደረጋችሁን ከልብ እናመሰግናለን።

🕊️ የቶታል ደብረ ገነት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ማኅበረ ካህናት በሙሉ ሥርዓተ ተክሊሉ በክብር፣ በሥርዓትና በመንፈሳዊ ድምቀት እንዲፈጸም ላደረጋችሁልን አገልግሎትና ድካም ልዩ ምስጋናችን ይድረሳችሁ።

🙏 በሥርዓተ ተክሊሉ የተገኛችሁ ሊቃውንት አበው በሙሉ በመገኘታችሁ፣ በጸሎታችሁና በአባታዊ በረከታችሁ ያከበራችሁን፣ ክብራችሁ በልባችን የማይረሳ ትዝታ ሆኖ ይኖራል።

🌹 በጸሎተ ማርያም ያሰባችሁን አበው በእመቤታችን ፊት ስማችንን በጸሎት ያነሣችሁ፣ አዲሱን ቤታችንን በምልጃዋ እንዲጸና የተመኛችሁልን፣ ጸሎታችሁ ለቤታችን የማይጠፋ መብራት ይሁንልን።

✈️ ከውጭ ሀገራት ለዚህ ጋብቻ ብላችሁ ረጅም መንገድ አቋርጣችሁ የመጣችሁ ውድ ወዳጆቻችን ርቀትን አቅርባችሁ፣ ጊዜያችሁንና ጉልበታችሁን ሰጥታችሁ ደስታችንን ለመካፈል ስለመጣችሁ፣ የእያንዳንዳችሁ ጉዞ ለእኛ የፍቅር ትልቅ ማስረጃ ነው። ❤️

📱 በማኅበራዊ ሚዲያዎች ሁሉ ፍቅራችሁን፣ መልካም ምኞታችሁንና ጸሎታችሁን የሰጣችሁን በሙሉ በአካል ባትገኙም በቃላችሁና በፍቅራችሁ ርቀቱን አጥፍታችሁ ከጎናችን ነበራችሁ።

💬 እንዲሁም «ይህ ቢስተካከል የተሻለ ይሆናል» ብላችሁ በፍቅርና በቅንነት ገንቢ አስተያየት የሰጣችሁን ሁሉ ከልብ እናከብራለን። ፍቅር ማለት ማድነቅ ብቻ ሳይሆን፣ የተሻለ እንድንሆን በቅንነት መናገርም ነው። የፍቅር ምክራችሁን በክብር ተቀብለነዋል።

🤍 ከሌሊት ጀምራችሁ እስከ አሁን ድረስ ያልተለያችሁን ሁላችሁ ድካምን ሳትቆጥሩ፣ ሰዓትን ሳትለኩ፣ በየቦታው ከጎናችን ሆናችሁ የእኛን ደስታ እንደራሳችሁ ደስታ የተሸከማችሁ የልባችን ሰዎች ናችሁ።

👏 ሠርጉ ውብ፣ የተደራጀና የማይረሳ እንዲሆን ቀንና ሌሊት የደከማችሁ የሠርጋችን ኮሚቴዎች ከመጋረጃው ጀርባ ያፈሰሳችሁትን ላብ፣ የሰጣችሁትን ጊዜ፣ የተሸከማችሁትን ኃላፊነትና ያሳያችሁን ፍቅር በቃል ብቻ ልንከፍለው አንችልም።

❤️ እያንዳንዳችሁ የሠርጋችን ተመልካች አልነበራችሁም፤ የደስታችን አካል፣ የበረከታችን ተካፋይ፣ የሕይወታችንም ውብ ታሪክ ናችሁ።

🙏 ስለዚህ ምስጋናችን በቃል ብቻ አያበቃም ወደ ጸሎት እንለውጠዋለን።

እግዚአብሔር የደከማችሁትን ድካም በበረከት፣ የሰጣችሁትን ፍቅር በፍቅር፣ ያፈሰሳችሁትን ደስታ በእጥፍ ደስታ ይመልስላችሁ።

በደስታችን የተደሰታችሁትን በደስታችሁ እንድንደሰት፣
በበዓላችን የቆማችሁትን በበዓላችሁ ከጎናችሁ እንድንቆም፣
ለቤታችን የጸለያችሁትን ቤታችሁ በሰላምና በበረከት ሲሞላ እንድናይ፣
እግዚአብሔር ያብቃን። 🕊️

ቤታችሁ የሰላም ማደሪያ፣
ልባችሁ የፍቅር መኖሪያ፣
ማዕዳችሁ የበረከት ማዕድ፣
ዘመናችሁም የጸጋና የደስታ ዘመን ይሁንላችሁ። 🙏🤍

ቀኑ አልፏል፤ ያደረጋችሁልን ግን አላለፈም።
ድግሱ ተጠናቋል፤ ፍቅራችሁ ግን በልባችን ይቀጥላል።
ሠርጉ ትዝታ ሆኗል፤ እናንተ ግን የትዝታው ውበት ሆናችሁ ቀርታችኋል። ❤️💍🕊️

በፍቅር፣ በጸሎትና በማይረሳ ምስጋና፣
መጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ 💍 ወ/ት ሣምራዊት መልአኩ
❤371🥰40👍17👏16🔥10